ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
plumbbob-2.pdf
2.8 MB
👉ርዕስ፦ የተራራው ትምህርት
ለላቀ የሕይወት ሥርዓት ከጌታ ዘንድ የተለቀቀ ቱንቢ
✍️ጸሐፊ፦ መርዓዊሥላሴ ንጉሤ (መጋቢ)
📑 የገጽ ብዛት፦ 291

💡መጽሐፉ የተራራው ስብከት የሚባለውን ማቴዎስ ምዕራፍ 5-7 ድረስ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረውን መሠረት በማድረግ የሚያብራራ እና የሚተነትን መጽሐፍ ነው።


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እያለቀሱ ይመጣሉ፤ እያጽናናሁ አመጣቸዋለሁ፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፣ ኤፍሬም በኵር ልጄ ነውና፣ በውሃ ምንጭ ዳር፣ በማይሰናከሉበት ቀና መንገድ እመራቸዋለሁ።”
        ኤርምያስ 31፥9 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት

#መጊዶ፤ የጦር ሠራዊት ሰፈር ማለት ነው። በቀርሜሎስ ተራራዎች ከሰሜን ወደ ደቡብ ጋዛንና ደማስቆን የሚያገናኘውን መንገድ ለመጠበቅ የተመሸገ ከተማ ነበር። እስራኤል እስከ ሰሎሞን ድረስ በከተማው አልተቀመጡም። በሰሎሞን ጊዜ ምሽጉ 200 በ300 ሜትር ገደማ ነበር፤ 1ነገ. 9፥15። በመጊዶ ብዙ ጦርነት ተደርጓል። በመጊዶ አጠገብ ዲቦራ ሲሣራን ድል አደረገች (መሳ. 5፥19)፤ ፈርዖን ኒካዑም ኢዮስያስን ገደለ፤ 2ነገ. 23፥29:30። ታላቁ የዓለም መጨረሻ ጦርነት በአርማጌዶን ይደረጋል፤ አርማጌዶን ማለት የመጊዶ አምባ ማለት ነው፤ ራእ. 16፥16።



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 45




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ንቂ፥ ንቂ፥ ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፥ ንቂ፥ ቅኔውን ተቀኚ፤ ባርቅ ሆይ፥ ተነሣ፤ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፥ ምርኮህን ማርክ።”
           መሳፍንት 5፥12




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
#እራሳችንን_እንመርምር

እግዚአብሔር የሰጠንን፣ በእጃችን የያዝነውን ይዘን፣ እርሱን ከማመስገን ይልቅ እዚህ ግባ ለማይባል ነገር ሁሉ ነገር እንደሌለን ሆነን በእግዚአብሔር ፊት በምሬት የምናለቅሰው ለምንድነው? ኧረ እግዚአብሔር ይፈውሰን!

“አሁን ግን ሰውነታችን ደረቀች፤ ዓይናችንም ከዚህ መና በቀር ምንም አታይም አሉ።”
ዘኍልቁ 11፥6


“ሙሴም ሕዝቡ በወገኖቻቸው፥ ሰው ሁሉ በድንኳኑ ደጃፍ፥ ሲያለቅሱ ሰማ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ እጅግ ነደደ፤ ሙሴም ተቈጣ።”
ዘኍልቁ 11፥10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።”
                ሐዋርያት 7፥35




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ሙሴም ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ለማገናኘት ከሰፈር አወጣቸው፤ ከተራራውም እግርጌ ቆሙ።”
              ዘጸአት 19፥17




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
mason-4-cr.pdf
2.3 MB
👉ርዕስ፦ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ማውቅና በአግባቡ መጠቀም
✍️ጸሐፊ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ
📑የገጽ ብዛት፦ 384
🖨 የታተመበት ዓመት፦1993 ዓመት/ 2000 እ. ኤ.አ

💡መጽሐፉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱትን የጸጋ ስጦታዎችን ከሞላ ጎደል አንድ በአንድ በዝርዝር ለመዳሰስ የሚሞክር ነው።


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍2🔥2
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እንግዲያስ ሰላም የሚቆምበትን እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን እንከተል።”
                ሮሜ 14፥19




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
ቅዱሳት መጻሕፍት
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል የተለየ ትኩረት ሳይሰጥ የሚያነብ አንባቢ እንኳን መጽሐፍ ቅዱስን በሚያነብበት ጊዜ መጽሐፉ ፍጹም ልዩ መሆኑን ይገነዘባል። መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ልጅ የብዙ ሺህ ዓመታት ታሪክ የሚያጠቃልል ሲሆን ፥ ከአርባ በሚበልጡ በተለያዩ ዘመናትና፥ የኑሮ ሁኔታዎች ውስጥ ባለፉ ጸሐፊዎች የተጻፈ ነው። ይሁን እንጂ የማይገናኙ ልዩ ልዩ ጽሑፎች ስብስብ ሳይሆን፥ አስደናቂ ተከታታይነትና…
የቀጠለ...


መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል


ለ. ውጫዊ ማረጋገጫ

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በራሱ የሚያስረግጥ ብቻ ሳይሆን፥ ተጠራጣሪዎችን እንኳን ለማሳመን በሚችሉ ብዙ መረጃዎች የተሞላ ነው።

1. የመጽሐፍ ቅዱስ ተከታታይነት ወይም ወጥነት።

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ከተገለጡት እጅግ አስገራሚ እውነቶች አንዱ፥ ወደ 1600 ዓመታት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ በኖሩና ከአርባ በላይ በሚሆኑ የተለያዩ ሰዎች የተጻፈ መሆኑ ነው። ይሁን እንጂ መጽሐፉ የስድሳ ስድስት መጻሕፍት ስብስብ ሳይሆን፥ አንድና ወጥ ነው። ጸሐፊዎቹ ከተለያየ ማኅበራዊ መሠረት የመጡ ናቸው፤ ነገሥታት፥ ጭሰኞች፥ ፈላስፋዎች፥ ዓሣ አጥማጆች፥ ሐኪሞች፥ የመንግሥት ባለሥልጣናት፥ ምሁራን፥ ባለቅኔዎች እና ገበሬዎች ነበሩ። እነዚህ ሰዎች በተለያዩ ባህሎችና ልምዶች መኖር ብቻ ሳይሆን፥ የተለያዩ ባህርያትም ነበሯቸው። ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ በግልጥ የሚታይ ተከታታይነትና ወጥነት አለው።

የመጽሐፉ ተከታታይነት ከአሁኑ ዓለም አፈጣጠር እስከ አዲሱ ሰማይና ምድር መፈጠር ድረስ ባለው ታሪካዊ ቅደም ተከተል ሥርዓት ሊታይ ይችላል። ብሉይ ኪዳን ስለ እግዚኣብሔር ባህርይ ፥ ስለ ኃጢአት፥ ስለ ድነት፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ስለ መላው ዓለም፥ ስለ እስራኤልና ስለ ቤተ ክርስቲያን ያለውን ዓላማና ዕቅድ ይገልጣል። መለኮታዊ ትምህርት ከዝቅተኛው፥ ማለት ቀለል ካለ መግቢያ ተነሥቶ እስከተወሳሰበ ትምህርትነት ደረጃ በደረጃ ይቀርባል። መጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌያዊ አገላለጦችን በቀጥተኛ ትርጉማቸው፥ ትንቢቶችን ደግሞ በተወሰነ ጊዜ ክንውናቸው ያሳያል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ዐበይት ጉዳዮች አንዱ፥ በሰማይና በምድር እጅግ ስለከበረውና ፍጹም ስለሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በቅድሚያ መተንበይ፥ የትንቢቱን እውንነት ማመልከትና ኢየሱስን ከፍ ማድረግ ነው። ይህ አስደናቂ መጽሐፍ በሰዎች ተጻፈ ብሉ ከማመን ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ገላጭነት ተጻፈ የሚለውን መቀበሉ ይቀልላል። ስለሆነም፥ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑ ሁሉ፥ የተለያዩት የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክቶች በተለያዩ ሰዎች የተጻፉ መሆናቸውን በመቀበል፥ የመልእክቶቹን አንድ ወጥነት በመንፈስ ቅዱስ ምሪትና አነሳሽነት ይረዳሉ።

2. የመጽሐፍ ቅዱሳዊ መገለጥ ጥልቅነት።

እውነትን በመግለጥ ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ ተመርምሮ አያልቅም። ቴሌስኮፕ የሰማይን ከፍታ እንደሚያሳይ፥ መጽሐፍ ቅዱስም የእግዚአብሔርን የእጅ ሥራዎች ከመነሻ እስከ ፍጻሜ፥ ከሰማያት ከፍታ፥ እስከ ሲኦል ጥልቀት ያመለክታል። ማይክሮስኮፕ ረቂቅ ነገሮችን እንደሚያሳይ ሁሉ፥ ረቂቁ የእግዚአብሔር ሥራ፥ ዕቅድና ዓላማው እንዲሁም የፍጥረቱ ፍጹምነት በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጧል። ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱት ብዙ መጻሕፍት የተጻፉት፥ ጸሐፊዎቹ ስለዘመናዊው ግኝት ግምት ባልነበራቸው ጊዜና በጥንታዊው የሰው ልጅ እውቀት ደረጃ ቢሆንም፥ በቅርቡ የተገኙት የሥነ-ምድር ምርምር ጥናቶች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን እውነቶች ከመቃረን ይልቅ ይደግፋሉ። ጥንታዊዎቹ ቅዱሳት መጻሕፍት በሚያስደንቅ አኳኋን ከዘመናዊው የሥነ-ምድር ምርምር ግኝቶች ጋር ይስማማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ዘላለማዊነት ያላቸውንና በእግዚአብሔር ብቻ የሚታወቁትን እውነቶች ስለሚገልጥ፥ ከሰው ምርምርና ግኝት በላይ የሆኑ እውነቶችን ይዟል። መጽሐፍ ቅዱስ እውነትን በሙላትና በረቂቅነት የሚያሳየንን ያህል የሚያሳይ ሌላ መጽሐፍ በዓለም የለም።

3. የመጽሐፍ ቅዱስ የመለወጥ ኃይልና ኅትመቱ።

በዓለማችን የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ለተለያዩ ሕዝቦችና ባህሎች በተለያዩ አያሌ ቋንቋዎች የታተመ ሌላ መጽሐፍ የለም። የማተሚያ መኪና እንደተፈለሰፈም ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በዓለም ታላላቅ ቋንቋዎች ሁሉ በብዙ ሚሊዮን ቅጂዎች ታትሟል። ጽሑፍ ያለው እያንዳንዱ ቋንቋ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቢያንስ ጥቂት ክፍሎች የታተመ ነገር አለው። ምንም እንኳን እንደ ፈረንሳዊው ቮልቴር ያሉ ሃይማኖት የለሾች መጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ ትውልድ ዕድሜ በኋላ ከአገልግሎት ውጪ ይሆናል ቢሉም፥ የሀያኛው ክፍለ-ዘመን ደራሲያንም መጽሐፉ ይረሳል ወይም ፈላጊ አይኖረውም ቢሉም፥ ካለፈው ይበልጥ በብዙ ቋንቋዎች በመታተም ላይ ነው። በተከታዮች ብዛት ከክርስትና የሚበልጡ ሌሎች ሃይማኖቶች፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሊወዳደር የሚችልና መገለጥ ያለው ጽሑፍ ሊያቀርቡ አልቻሉም። የመጽሐፍ ቅዱስ ሕይወትን የመለወጥ ኃይል በዘመናችንም ቀጥሏል። ላልዳነ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ “የመንፈስ ሰይፍ” ነው (ኤፌ. 6፡17)፤ ለዳነው የሚያነጻ፥ የቅድስናና ድል አድራጊነት ኃይል ነው (ዮሐ. 17፡17፤ 2ኛ ቆሮ. 3፡ 17፥ 18፤ ኤፌ. 5፡25-26)። መጽሐፍ ቅዱስ የሕግና የሥነ-ምግባር ብቸኛው መለኮታዊ መሠረት እንደሆነ ይኖራል።


ይቀጥላል. . .



ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ምሕረትህን በሚያውቁህ ላይ፥ ጽድቅህንም ልባቸው በቀና ላይ ዘርጋ።”
                መዝሙር 36፥10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት



የእግዚአብሔር ጽድቅ (9:14-18)


እግዚአብሔር አንዱን መርጦ ሌላውን መተዉ ዐመፀኛ መሆኑን የሚያመለክት ይመስላል፡፡ «በእግዚአብሔር ዘንድ ዐመፃ አለ ወይ?» ብሎ ጳውሎስ ጠይቋል:: ራሱ «አይደለም» ብሎ መልስ ይሰጣል፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ዐመፅ ያደርጋል ማለት የማይታሰብ ነገር ነው:: ምርጫ የጸጋ ጉዳይ ነው፡፡ እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ እንደ ጽድቃችን ቢሰጠን ኖሮ፣ ማንም አይድንም ነበር፡፡ ጳውሎስ ዘጸአት 33:19 ጠቅሶ የእግዚአብሔር ምሕረትና ርኅራኄ የሚቀጥሉት እንደ ሰው ፈቃድ ሳይሆን፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን አሳይቷል:: ሁላችንም ምሕረት ሳይሆን፣ ፍርድ የተገባን ነበርን፡፡ ዘጸአት 33 የሚናገረው ሙሴ በተራራው ላይ ሕግጋተ እግዚአብሔርን ሲቀበል እስራኤላውያን ስለማመንዘራቸው ነው፡፡ ሕዝብ ሁሉ መሞት ሲገባቸው፣ እግዚአብሔር የቀሰፈው ግን 3,000 ሰዎችን ብቻ ነው:: ያልሞቱት ቅዱሳን ስለሆኑ ወይም የሞቱት ከእነርሱ የባሱ ክፉና ርኩሳን ስለሆኑ ሳይሆን፣ በምሕረቱና በጸጋው ነው::

ጳውሎስ ዘጸአት 9:16 በመጥቀስ ፈርዖንን እንደ ምሳሌ አቅርቧል:: ሙሴ አይሁድ ነበር፣ ፈርዖን ደግሞ አረማዊ፣ ነገር ግን ሁለቱም ኃጢአተኞች ነበሩ፡፡ ሁለቱም ነፍሰ ገዳዮች ነበሩ፡፡ ሁለቱም የእግዚአብሔርን ተአምራት አይተዋል፡፡ ሙሴ ሲድን፣ ፈርዖን ግን ጠፋ፡፡ እግዚአብሔር ፈርዖንን ያስነሣው ክብሩንና ኃይሉን ሊገልጥ ነው:: ሙሴን ደግሞ የማረው ሕዝቡን እስራኤልን ነፃ እንዲያወጣ ነው፡፡ ፈርዖን ገዥ ነው፣ ሙሴ ደግሞ ባሪያ ነበር፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ምሕረትና ርኅራኄ የተለማመደው ሙሴ ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ እንዲሆን ፈቀደ፡፡ እግዚአብሔር ሉዓላዊ ስለሆነ በሥራውና በአደራረጉ እንደ ፈቀዱና እንደ ዓላማው ያደርጋል፡፡ ነገሩ የጽድቅ ጉዳይ ሳይሆን፣ ልዑል የሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ጉዳይ ነው፡፡

እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና ኃጢአትን ሊቀጣ ይገባዋል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር አፍቃሪና ኃጢአተኞችን ለማዳን መሻት ያለው አምላክ ነው:: ሰው ሁሉ ቢድን፣ ቅድስናውን መካዱ ነው፤ ሰው ሁሉ ቢጠፋ ደግሞ፣ ፍቅሩን ሊክድ ነው፡፡ መፍትሔው የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምርጫ ነው፡፡

እግዚአብሔር እስራኤልን መርጦ ግብፅን ኮነነ፣ ሉዓላዊ፣ ዓላማው ይህ ነበርና፡፡ እግዚአብሔር ጻድቅ ስለሆነ፣ ምሕረቱን በምን መንገድ እንደሚሰጥ ማንም ሊጠይቅ አይችልም፡፡

ይህን ክፍል ስንጨርስ ስለ ፈርዖን ልብ «መደንደን» እንነጋገራለን (ቁ. 18)። «የልብ መደንደን» ሂደት ከዘጸአት 7-14 ድረስ 15 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፈርዖን ልቡን እንዳደነደነ ተነግሮናል (ዘጸ. 8:15፣19፣32)፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ እንዳደነደነ ተጽፎአል (ዘጸ. 9:12፤10:1፣20፣27)፡፡ ቃሉን በማወጅና ኃይሉን በመግለጥ ፈርዖን ንስሐ እንዲገባ ዕድል ቢሰጠውም፣ እርሱ ግን እግዚአብሔርን በመቋቋም ልቡን አደነደነ:: ችግሩ ያለው በእግዚአብሔር ዘንድ ሳይሆን፣ በፈርዖን ላይ ነው:: በረዶን የሚያቀልጥ የፀሐይ ብርሃን ሽክላን ያደርቃል፡፡ እግዚአብሔር ፈርዖንን በንስሐ ገብቶ እንዲያምን ዕድል ስለሰጠው፣ እግዚአብሔር ዐመፀኛ አልነበረም፡፡

ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ተስማማ፤ ገጽ 96-98




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም በሞገስ ጠግቦአል፥ የእግዚአብሔርንም በረከት ተሞልቶአል፤ ባሕሩንና ደቡቡን ይወርሳል።”
              ዘዳግም 33፥23



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6🔥1
👍6🔥2
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“የዔሊም ልጆች ምናምንቴዎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርንም አያውቁም ነበር።”
         1ኛ ሳሙኤል 2፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32