ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ጴጥሮስም መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ አለው።”
          ማቴዎስ 14፥28




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍5
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል


የተለየ ትኩረት ሳይሰጥ የሚያነብ አንባቢ እንኳን መጽሐፍ ቅዱስን በሚያነብበት ጊዜ መጽሐፉ ፍጹም ልዩ መሆኑን ይገነዘባል። መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ልጅ የብዙ ሺህ ዓመታት ታሪክ የሚያጠቃልል ሲሆን ፥ ከአርባ በሚበልጡ በተለያዩ ዘመናትና፥ የኑሮ ሁኔታዎች ውስጥ ባለፉ ጸሐፊዎች የተጻፈ ነው። ይሁን እንጂ የማይገናኙ ልዩ ልዩ ጽሑፎች ስብስብ ሳይሆን፥ አስደናቂ ተከታታይነትና ወጥነት ያለው፥ መጽሐፍ ነው። በአማርኛችን መጽሐፍ ቅዱስ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ድንቅ መጽሐፍ፥ በግሪክኛ “#ቢብሉስ” በሚል ስያሜ ይታወቃል። እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች “ዘ ባይብል” የሚል ስያሜ የሰጡትም ከዚህ ቃል የተነሣ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች የተጻፈ ቢሆንም በእርግጥ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ይህ ነው ልዩ ባሕርዩ።

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን የሚደግፉ ሁለት ማረጋገጫዎች አሉ።

1. አንዱ ውስጣዊው ማረጋገጫው ነው።

ይኸውም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተመለከቱት እውነታዎች እና መጽሐፉ ራሱ ስለመለኮታዊነቱ የሚገልጠው ሲሆን፤

2. ውጫዊው ማረጋገጫ ደግሞ፥ ልዕለ-ተፈጥሮ የሆነ ባሕርይውን የሚደግፉትና ውስጡ የተጠቀሱት እውነቶች ናቸው።

ሀ. ውስጣዊ ማረጋገጫ

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በመቶ በሚቆጠሩ የንባብ ክፍሎቹ ራሱ ገልጧል (ዘዳ. 6፡6-9፥ 17-18፤ ኢያሱ 1፡8፤ 8፡32-35፤ 2ኛ ሳሙ. 22፡31፤ መዝ. 1፡2፤ 12፡6፤ 19፡7-11፤ 93፤5፤ 119፡9፥ 11፥ 18፥ 89-93፥ 97-100፥ 104-105፥ 130፤ ምሳሌ 30፡5-6፤ ኢሳ. 55፡10-11፤ ኤር. 15፡ 16፤ 23፡29፤ ዳን. 10፡21፤ ማቴ. 5፡17-19፤ 22፡29፤ ማር. 13፡31፤ ሉቃስ 16፡17፤ ዮሐ. 2፡22፤ 5፡24፤ 10፡35፤ ሐዋ. 17፡ 11፤ ሮሜ 10፡17፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡13፤ ቆላ. 3፡ 16፤ 1ኛ ተሰ. 2፡13፤ 2ኛ ጢሞ. 2፡15፤ 3፡15-17፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡23-25፤ 2ኛ ጴጥ. 3፡15-16፤ ራእይ 1፡2፤ 22፡18)። ለማንም ግልጥ በሚሆን ሁኔታና በብዙ መንገዶች፥ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ገልጠዋል። የብሉይ ኪዳንና የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ክርስቶስም ጭምር፥ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ገላጭነት የተጻፈ ቃል ነው ይላሉ። ለምሳሌ መዝሙር 19፡7-11 ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑ ተገልጦ፥ ፍጹምነትንና በአንጻሩ በቃሉ አማካይነት የተለወጡ ስድስት ሰብአዊ ባሕርዮች ተመልክተዋል። ኢየሱስ ክርስቶስም ሕግ መፈጸም እንደነበረበት ገልጧል (ማቴ. 5፡17-18)። ዕብራውያን 1፡ 1-2 ውስጥም እግዚኣብሔር በብሉይ ኪዳን ለነቢያቱ፥ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ለልጁ የተናገረ መሆኑ ተረጋግጧል። ሰው የመጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃልነት የማይቀበል የሚሆነው፥ መጽሐፉ የእግዚአብሔር ቃል ስለመሆኑ ራሱ የሚሰጠውን የተደጋገሙ መረጃዎች የማይቀበል ሲሆን ብቻ ነው።

ይቀጥላል. . .


ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2😁1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።”
             ሉቃስ 21፥15




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍3
#እራሳችንን_እንመርምር

በሥራ ወይም በትምህርት ቦታችን አልያም በማንኛውም የሌተቀን እንቅስቃሴያችን በምን አይነት ውሎ ነው የምንውለው? በጥንቃቄ እና በማስተዋል ተቃኝተን ወይስ በግድ የለሽነት?

“የዚያን ጊዜም አለቆችና መሳፍንቱ ስለ መንግሥቱ በዳንኤል ላይ ሰበብ ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን የታመነ ነበረና፥ ስሕተትና በደልም አልተገኘበትምና በእርሱ ላይ ሰበብና በደል ያገኙበት ዘንድ አልቻሉም።”
ዳንኤል 6፥4




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።”
                ሐዋርያት 24፥16




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና፥ በእርሱም ታምነዋልና ተለመናቸው፤ በላያቸውም ረዳት ሆናቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተሰጡ።”
               1 ዜና 5፥20




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
ቅዱሳት መጻሕፍት
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል የተለየ ትኩረት ሳይሰጥ የሚያነብ አንባቢ እንኳን መጽሐፍ ቅዱስን በሚያነብበት ጊዜ መጽሐፉ ፍጹም ልዩ መሆኑን ይገነዘባል። መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ልጅ የብዙ ሺህ ዓመታት ታሪክ የሚያጠቃልል ሲሆን ፥ ከአርባ በሚበልጡ በተለያዩ ዘመናትና፥ የኑሮ ሁኔታዎች ውስጥ ባለፉ ጸሐፊዎች የተጻፈ ነው። ይሁን እንጂ የማይገናኙ ልዩ ልዩ ጽሑፎች ስብስብ ሳይሆን፥ አስደናቂ ተከታታይነትና…
የቀጠለ...


መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል


ለ. ውጫዊ ማረጋገጫ

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በራሱ የሚያስረግጥ ብቻ ሳይሆን፥ ተጠራጣሪዎችን እንኳን ለማሳመን በሚችሉ ብዙ መረጃዎች የተሞላ ነው።

1. የመጽሐፍ ቅዱስ ተከታታይነት ወይም ወጥነት።

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ከተገለጡት እጅግ አስገራሚ እውነቶች አንዱ፥ ወደ 1600 ዓመታት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ በኖሩና ከአርባ በላይ በሚሆኑ የተለያዩ ሰዎች የተጻፈ መሆኑ ነው። ይሁን እንጂ መጽሐፉ የስድሳ ስድስት መጻሕፍት ስብስብ ሳይሆን፥ አንድና ወጥ ነው። ጸሐፊዎቹ ከተለያየ ማኅበራዊ መሠረት የመጡ ናቸው፤ ነገሥታት፥ ጭሰኞች፥ ፈላስፋዎች፥ ዓሣ አጥማጆች፥ ሐኪሞች፥ የመንግሥት ባለሥልጣናት፥ ምሁራን፥ ባለቅኔዎች እና ገበሬዎች ነበሩ። እነዚህ ሰዎች በተለያዩ ባሕሎችና ልምዶች መኖር ብቻ ሳይሆን፥ የተለያዩ ባሕርያትም ነበሯቸው። ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ በግልጥ የሚታይ ተከታታይነትና ወጥነት አለው።

የመጽሐፉ ተከታታይነት ከአሁኑ ዓለም አፈጣጠር እስከ አዲሱ ሰማይና ምድር መፈጠር ድረስ ባለው ታሪካዊ ቅደም ተከተል ሥርዓት ሊታይ ይችላል። ብሉይ ኪዳን ስለ እግዚኣብሔር ባሕርይ፥ ስለ ኃጢአት፥ ስለ ድነት፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ስለ መላው ዓላም፥ ስለ እስራኤልና ስለ ቤተ ክርስቲያን ያለውን ዓላማና ዕቅድ ይገልጣል። መለኮታዊ ትምህርት ከዝቅተኛው፥ ማለት ቀለል ካለ መግቢያ ተነሥቶ እስከተወሳሰበ ትምህርትነት ደረጃ በደረጃ ይቀርባል። መጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌያዊ አገላለጦችን በቀጥተኛ ትርጉማቸው፥ ትንቢቶችን ደግሞ በተወሰነ ጊዜ ክንውናቸው ያሳያል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ዐበይት ጉዳዮች አንዱ፥ በሰማይና በምድር እጅግ ስለከበረውና ፍጹም ስለሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በቅድሚያ መተንበይ፥ የትንቢቱን እውንነት ማመልከትና ኢየሱስን ከፍ ማድረግ ነው። ይህ አስደናቂ መጽሐፍ በሰዎች ተጻፈ ብሉ ከማመን ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ገላጭነት ተጻፈ የሚለውን መቀበሉ ይቀልላል። ስለሆነም፥ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑ ሁሉ፥ የተለያዩት የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክቶች በተለያዩ ሰዎች የተጻፉ መሆናቸውን በመቀበል፥ የመልእክቶቹን አንድ ወጥነት በመንፈስ ቅዱስ ምሪትና አነሳሽነት ይረዳሉ።

2. የመጽሐፍ ቅዱሳዊ መገለጥ ጥልቅነት።

እውነትን በመግለጥ ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ ተመርምሮ አያልቅም። ቴሌስኮፕ የሰማይን ከፍታ እንደሚያሳይ፥ መጽሐፍ ቅዱስም የእግዚአብሔርን የእጅ ሥራዎች ከመነሻ እስከ ፍጻሜ፥ ከሰማያት ከፍታ፥ እስከ ሲኦል ጥልቀት ያመለክታል። ማይክሮስኮፕ ረቂቅ ነገሮችን እንደሚያሳይ ሁሉ፥ ረቂቁ የእግዚአብሔር ሥራ፥ ዕቅድና ዓላማው እንዲሁም የፍጥረቱ ፍጹምነት በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጧል። ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱት ብዙ መጻሕፍት የተጻፉት፥ ጸሐፊዎቹ ስለዘመናዊው ግኝት ግምት ባልነበራቸው ጊዜና በጥንታዊው የሰው ልጅ እውቀት ደረጃ ቢሆንም፥ በቅርቡ የተገኙት የሥነ-ምድር ምርምር ጥናቶች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን እውነቶች ከመቃረን ይልቅ ይደግፋሉ። ጥንታዊዎቹ ቅዱሳት መጻሕፍት በሚያስደንቅ አኳኋን ከዘመናዊው የሥነ-ምድር ምርምር ግኝቶች ጋር ይስማማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ዘላለማዊነት ያላቸውንና በእግዚአብሔር ብቻ የሚታወቁትን እውነቶች ስለሚገልጥ፥ ከሰው ምርምርና ግኝት በላይ የሆኑ እውነቶችን ይዟል። መጽሐፍ ቅዱስ እውነትን በሙላትና በረቂቅነት የሚያሳየንን ያህል የሚያሳይ ሌላ መጽሐፍ በዓለም የለም።

3. የመጽሐፍ ቅዱስ የመለወጥ ኃይልና ኅትመቱ።

በዓለማችን የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ለተለያዩ ሕዝቦችና ባሕሎች በተለያዩ አያሌ ቋንቋዎች የታተመ ሌላ መጽሐፍ የለም። የማተሚያ መኪና እንደተፈለሰፈም ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በዓለም ታላላቅ ቋንቋዎች ሁሉ በብዙ ሚሊዮን ቅጂዎች ታትሟል። ጽሑፍ ያለው እያንዳንዱ ቋንቋ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቢያንስ ጥቂት ክፍሎች የታተመ ነገር አለው። ምንም እንኳን እንደ ፈረንሳዊው ቮልቴር ያሉ ሃይማኖት የለሾች መጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ ትውልድ ዕድሜ በኋላ ከአገልግሎት ውጪ ይሆናል ቢሉም፥ የሀያኛው ክፍለ-ዘመን ደራሲያንም መጽሐፉ ይረሳል ወይም ፈላጊ አይኖረውም ቢሉም፥ ካለፈው ይበልጥ በብዙ ቋንቋዎች በመታተም ላይ ነው። በተከታዮች ብዛት ከክርስትና የሚበልጡ ሌሎች ሃይማኖቶች፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሊወዳደር የሚችልና መገለጥ ያለው ጽሑፍ ሊያቀርቡ አልቻሉም። የመጽሐፍ ቅዱስ ሕይወትን የመለወጥ ኃይል በዘመናችንም ቀጥሏል። ላልዳነ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ “የመንፈስ ሰይፍ” ነው (ኤፌ. 6፡17)፤ ለዳነው የሚያነጻ፥ የቅድስናና ድል አድራጊነት ኃይል ነው (ዮሐ. 17፡17፤ 2ኛ ቆሮ. 3፡ 17፥ 18፤ ኤፌ. 5፡25-26)። መጽሐፍ ቅዱስ የሕግና የሥነ-ምግባር ብቸኛው መለኮታዊ መሠረት እንደሆነ ይኖራል።


ይቀጥላል. . .


ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በፍጹም ልባቸው የሚታመኑበትን ለማበርታት የእግዚአብሔር ዐይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይመለከታሉና። የሞኝነት ሥራ ስለ ሠራህ ከእንግዲህ ወዲያ ጦርነት አይለይህም።”
          2 ዜና 16፥9 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


መዝሙር 118
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ናትና።
² ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘላለም እንደ ሆነች የእስራኤል ቤት አሁን ይንገሩ።
³ ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘላለም እንደ ሆነች የአሮን ቤት አሁን ይንገሩ።
⁴ ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘላለም እንደ ሆነች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ አሁን ይንገሩ።
⁵ በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ሰማኝ አሰፋልኝም።
⁶ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?
⁷ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ እኔም በጠላቶቼ ላይ አያለሁ።
⁸ በሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።
⁹ በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ ይሻላል።
¹⁰ አሕዛብ ሁሉ ከበቡኝ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤
¹¹ መክበቡንስ ከበቡኝ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤
¹² ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፥ እሳትም በእሾህ ውስጥ እንዲነድድ ነደዱ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው።
¹³ ገፋኸኝ፥ ለመውደቅም ተንገዳገድሁ፤ እግዚአብሔር ግን አገዘኝ።
¹⁴ ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም መድኃኒት ሆነልኝ።
¹⁵ የእልልታና የመድኃኒት ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው፤ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች።
¹⁶ የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ፤ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች።
¹⁷ አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ።
¹⁸ መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ፤ ለሞት ግን አልሰጠኝም።
¹⁹ የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤ ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
²⁰ ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት፤ ወደ እርስዋ ጻድቃን ይገባሉ።
²¹ ሰምተኸኛልና፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
²² ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤
²³ ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆነች፥ ለዓይናችንም ድንቅ ናት።
²⁴ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።
²⁵ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፤ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና።
²⁶ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤ ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ።
²⁷ እግዚአብሔር አምላክ ነው፥ ለእኛም በራልን፤ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ የበዓሉን መሥዋዕት በገመድ እሰሩት።
²⁸ አንተ አምላኬ ነህ አመሰግንህማለሁ። አንተ አምላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ሰምተኸኛልና፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
²⁹ እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ናትና።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍4
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።”
            1ኛ ጴጥሮስ 4፥11




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
plumbbob-2.pdf
2.8 MB
👉ርዕስ፦ የተራራው ትምህርት
ለላቀ የሕይወት ሥርዓት ከጌታ ዘንድ የተለቀቀ ቱንቢ
✍️ጸሐፊ፦ መርዓዊሥላሴ ንጉሤ (መጋቢ)
📑 የገጽ ብዛት፦ 291

💡መጽሐፉ የተራራው ስብከት የሚባለውን ማቴዎስ ምዕራፍ 5-7 ድረስ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረውን መሠረት በማድረግ የሚያብራራ እና የሚተነትን መጽሐፍ ነው።


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እያለቀሱ ይመጣሉ፤ እያጽናናሁ አመጣቸዋለሁ፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፣ ኤፍሬም በኵር ልጄ ነውና፣ በውሃ ምንጭ ዳር፣ በማይሰናከሉበት ቀና መንገድ እመራቸዋለሁ።”
        ኤርምያስ 31፥9 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት

#መጊዶ፤ የጦር ሠራዊት ሰፈር ማለት ነው። በቀርሜሎስ ተራራዎች ከሰሜን ወደ ደቡብ ጋዛንና ደማስቆን የሚያገናኘውን መንገድ ለመጠበቅ የተመሸገ ከተማ ነበር። እስራኤል እስከ ሰሎሞን ድረስ በከተማው አልተቀመጡም። በሰሎሞን ጊዜ ምሽጉ 200 በ300 ሜትር ገደማ ነበር፤ 1ነገ. 9፥15። በመጊዶ ብዙ ጦርነት ተደርጓል። በመጊዶ አጠገብ ዲቦራ ሲሣራን ድል አደረገች (መሳ. 5፥19)፤ ፈርዖን ኒካዑም ኢዮስያስን ገደለ፤ 2ነገ. 23፥29:30። ታላቁ የዓለም መጨረሻ ጦርነት በአርማጌዶን ይደረጋል፤ አርማጌዶን ማለት የመጊዶ አምባ ማለት ነው፤ ራእ. 16፥16።



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 45




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ንቂ፥ ንቂ፥ ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፥ ንቂ፥ ቅኔውን ተቀኚ፤ ባርቅ ሆይ፥ ተነሣ፤ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፥ ምርኮህን ማርክ።”
           መሳፍንት 5፥12




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
#እራሳችንን_እንመርምር

እግዚአብሔር የሰጠንን፣ በእጃችን የያዝነውን ይዘን፣ እርሱን ከማመስገን ይልቅ እዚህ ግባ ለማይባል ነገር ሁሉ ነገር እንደሌለን ሆነን በእግዚአብሔር ፊት በምሬት የምናለቅሰው ለምንድነው? ኧረ እግዚአብሔር ይፈውሰን!

“አሁን ግን ሰውነታችን ደረቀች፤ ዓይናችንም ከዚህ መና በቀር ምንም አታይም አሉ።”
ዘኍልቁ 11፥6


“ሙሴም ሕዝቡ በወገኖቻቸው፥ ሰው ሁሉ በድንኳኑ ደጃፍ፥ ሲያለቅሱ ሰማ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ እጅግ ነደደ፤ ሙሴም ተቈጣ።”
ዘኍልቁ 11፥10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7