ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፥ እጁንም ጭኖበት፦ ወንድሜ ሳውል ሆይ፥ ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፥ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ አለ።”
             ሐዋርያት 9፥17




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት


ሮሜ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ እንግዲህ ምን እንላለን? በእግዚአብሔር ዘንድ ዓመፃ አለ ወይ? አይደለም።
¹⁵ ለሙሴ፦ የምምረውን ሁሉ እምረዋለሁ ለምራራለትም ሁሉ እራራለታለሁ ይላልና።
¹⁶ እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ።
¹⁷ መጽሐፍ ፈርዖንን፦ ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ ይላልና።
¹⁸ እንግዲህ የሚወደውን ይምረዋል፥ የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል።


ሮሜ 9 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር አድልዎ ያደርጋልን? በፍጹም አያደርግም!
¹⁵ ለሙሴ፣ “የምምረውን እምረዋለሁ፤ ለምራራለትም እራራለታለሁ” ይላልና።
¹⁶ እንግዲህ ይህ ከሰው ፍላጎት ወይም ጥረት ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው።
¹⁷ መጽሐፍ ፈርዖንን፣ “ኀይሌ በአንተ እንዲታይ፣ ስሜም በምድር ሁሉ እንዲነገር ለዚህ አስነሣሁህ” ይላልና።
¹⁸ ስለዚህ እግዚአብሔር ሊምረው ለሚወደው ምሕረት ያደርግለታል፤ ልቡ እንዲደነድን የፈለገውንም ያደነ ድነዋል።


ሮሜ 9 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ እንግዲህ ይህ ምንን ያመለክታል? እግዚአብሔር ያዳላል ማለት ነው? ይህን ማለት አንችልም።
¹⁵ ምክንያቱም እግዚአ ብሔር ለሙሴ ፥ «ልምረው የምፈልገውን እምረዋለሁ፤ ልራራለት ለምፈልገውም እራራለታለሁ» ብሎታል።
¹⁶ ስለዚህ የእግዚአብሔርን በረከት ማግኘት የሚቻለው በሰው ፈቃድ ወይም ጥረት ሳይሆን በእግዚአብሔር ምሕረትና ቸርነት ብቻ ነው።
¹⁷ በቅዱሳት መጻሕፍት፥ “ፈርዖን ሆይ፥ ኃይሌን ለማሳየትና ስሜንም በሰዎች ሁሉ ዘንድ ለማሳወቅ አነሣሣሁህ» ተብሎ የተነገረውን እዚህ ላይ ልንጠቅሰው እንችላለን።
¹⁸ ስለዚህ እግዚአብሔር ሊምረው የፈለገውን ሲምረው ሌላውን ደግሞ እልኸኛ ያደርገዋል።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2🔥1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“አንተ ግን፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የምነግርህን ስማ፤ እንደዚያ እንደ ዓመፀኛው ቤት ዓመፀኛ አትሁን፤ አፍህን ክፈት የምሰጥህንም ብላ።”
          ሕዝቅኤል 2፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ሚልክያስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አሁንም እናንተ ካህናት ሆይ፥ ይህ ትእዛዝ ለእናንተ ነው።
² ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ ባትሰሙ፥ በልባችሁም ባታደርጉት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እርግማን እሰድድባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማታለሁ፤ አሁንም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና እኔ ረግሜአታለሁ።
³ እነሆ፥ ክንዳችሁን እገሥጻለሁ፥ የመሥዋዕታችሁንም ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፤ ከእርሱም ጋር በአንድነት ትወሰዳላችሁ።
⁴ ቃል ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ይሆን ዘንድ ይህን ትእዛዝ እንደ ሰደድሁላችሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
⁵ ቃል ኪዳኔ ከእርሱ ጋር የሕይወትና የሰላም ቃል ኪዳን ነበረ፤ ይፈራ ዘንድም እነርሱን ሰጠሁት፤ እርሱም ፈራኝ፥ ከስሜም የተነሣ ደነገጠ።
⁶ የእውነት ሕግ በአፉ ውስጥ ነበረች፥ በከንፈሩም ውስጥ በደል አልተገኘበትም፤ ከእኔም ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፥ ብዙ ሰዎችንም ከኃጢአት መለሰ።
⁷ ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።
⁸ እናንተ ግን ከመንገዱ ፈቀቅ ብላችኋል፤ በሕግም ብዙ ሰዎችን አሰናክላችኋል፤ የሌዊንም ቃል ኪዳን አስነውራችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
⁹ ስለዚህ መንገዴን እንዳልጠበቃችሁ፥ በሕግም ለሰው ፊት እንዳዳላችሁ መጠን፥ እኔ ደግሞ በሕዝብ ሁሉ ፊት የተናቃችሁና የተዋረዳችሁ አድርጌአችኋለሁ።
¹⁰ ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳንዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን?
¹¹ እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።
¹² ይህን ከሚያደርግ ሰው፥ እግዚአብሔር የሚጠራውንና የሚመልሰውን ለሠራዊትም ጌታ ለእግዚአብሔር ቍርባን የሚያቀርበውን ከያዕቆብ ድንኳን ያጠፋል።
¹³ ይህንም ደግሞ አድርጋችኋል እግዚአብሔር ቍርባኑን ዳግመኛ እንዳይመለከት፥ ከእጃችሁም በደስታ እንዳይቀበለው መሠዊያውን በእንባና በልቅሶ በኀዘንም ትከድናላችሁ።
¹⁴ እናንተም፦ ስለ ምንድር ነው? ብላችኋል። ሚስትህ ባልንጀራህና የቃል ኪዳንህ ሚስት ሆና ሳለች እርስዋን አታልለሃታልና እግዚአብሔር በአንተና በልጅነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለ ሆነ ነው።
¹⁵ እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድር ነው? ዘር አይደለምን? ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።
¹⁶ መፋታትን እጠላለሁ፥ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ልብሱንም በግፍ ሥራ የሚከድነውን ሰው እጠላለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ እንዳታታልሉ መንፈሳችሁን ጠብቁ።
¹⁷ እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችኋል። እናንተም፦ ያታከትነው በምንድር ነው? ብላችኋል። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል፤ ወይስ፦ የፍርድ አምላክ ወዴት አለ? በማለታችሁ ነው።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔርን ለመቋቋም የሚያስችል፣ አንዳችም ጥበብ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።”
           ምሳሌ 21፥30 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍72
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
HARM_Intro.pdf
322.1 KB
👉ርዕስ፦ የወንጌላት ስምምነትና ንጽጽር
✍️ጸሐፊ፦ ሮበርት ኤል ቶማስ እና ስታንሊ ኤን ጉንድሪ
🖨አሳታሚ፦ ላፕስሊ/ ብሩክስ ፋውንዴሽን


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍4
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ኃጢአትን የሚሠሩ ይሰወሩበት ዘንድ ጨለማ ወይም የሞት ጥላ የለም።”
             ኢዮብ 34፥22




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍41
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ጴጥሮስም መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ አለው።”
          ማቴዎስ 14፥28




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍5
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል


የተለየ ትኩረት ሳይሰጥ የሚያነብ አንባቢ እንኳን መጽሐፍ ቅዱስን በሚያነብበት ጊዜ መጽሐፉ ፍጹም ልዩ መሆኑን ይገነዘባል። መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ልጅ የብዙ ሺህ ዓመታት ታሪክ የሚያጠቃልል ሲሆን ፥ ከአርባ በሚበልጡ በተለያዩ ዘመናትና፥ የኑሮ ሁኔታዎች ውስጥ ባለፉ ጸሐፊዎች የተጻፈ ነው። ይሁን እንጂ የማይገናኙ ልዩ ልዩ ጽሑፎች ስብስብ ሳይሆን፥ አስደናቂ ተከታታይነትና ወጥነት ያለው፥ መጽሐፍ ነው። በአማርኛችን መጽሐፍ ቅዱስ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ድንቅ መጽሐፍ፥ በግሪክኛ “#ቢብሉስ” በሚል ስያሜ ይታወቃል። እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች “ዘ ባይብል” የሚል ስያሜ የሰጡትም ከዚህ ቃል የተነሣ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች የተጻፈ ቢሆንም በእርግጥ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ይህ ነው ልዩ ባሕርዩ።

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን የሚደግፉ ሁለት ማረጋገጫዎች አሉ።

1. አንዱ ውስጣዊው ማረጋገጫው ነው።

ይኸውም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተመለከቱት እውነታዎች እና መጽሐፉ ራሱ ስለመለኮታዊነቱ የሚገልጠው ሲሆን፤

2. ውጫዊው ማረጋገጫ ደግሞ፥ ልዕለ-ተፈጥሮ የሆነ ባሕርይውን የሚደግፉትና ውስጡ የተጠቀሱት እውነቶች ናቸው።

ሀ. ውስጣዊ ማረጋገጫ

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በመቶ በሚቆጠሩ የንባብ ክፍሎቹ ራሱ ገልጧል (ዘዳ. 6፡6-9፥ 17-18፤ ኢያሱ 1፡8፤ 8፡32-35፤ 2ኛ ሳሙ. 22፡31፤ መዝ. 1፡2፤ 12፡6፤ 19፡7-11፤ 93፤5፤ 119፡9፥ 11፥ 18፥ 89-93፥ 97-100፥ 104-105፥ 130፤ ምሳሌ 30፡5-6፤ ኢሳ. 55፡10-11፤ ኤር. 15፡ 16፤ 23፡29፤ ዳን. 10፡21፤ ማቴ. 5፡17-19፤ 22፡29፤ ማር. 13፡31፤ ሉቃስ 16፡17፤ ዮሐ. 2፡22፤ 5፡24፤ 10፡35፤ ሐዋ. 17፡ 11፤ ሮሜ 10፡17፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡13፤ ቆላ. 3፡ 16፤ 1ኛ ተሰ. 2፡13፤ 2ኛ ጢሞ. 2፡15፤ 3፡15-17፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡23-25፤ 2ኛ ጴጥ. 3፡15-16፤ ራእይ 1፡2፤ 22፡18)። ለማንም ግልጥ በሚሆን ሁኔታና በብዙ መንገዶች፥ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ገልጠዋል። የብሉይ ኪዳንና የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ክርስቶስም ጭምር፥ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ገላጭነት የተጻፈ ቃል ነው ይላሉ። ለምሳሌ መዝሙር 19፡7-11 ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑ ተገልጦ፥ ፍጹምነትንና በአንጻሩ በቃሉ አማካይነት የተለወጡ ስድስት ሰብአዊ ባሕርዮች ተመልክተዋል። ኢየሱስ ክርስቶስም ሕግ መፈጸም እንደነበረበት ገልጧል (ማቴ. 5፡17-18)። ዕብራውያን 1፡ 1-2 ውስጥም እግዚኣብሔር በብሉይ ኪዳን ለነቢያቱ፥ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ለልጁ የተናገረ መሆኑ ተረጋግጧል። ሰው የመጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃልነት የማይቀበል የሚሆነው፥ መጽሐፉ የእግዚአብሔር ቃል ስለመሆኑ ራሱ የሚሰጠውን የተደጋገሙ መረጃዎች የማይቀበል ሲሆን ብቻ ነው።

ይቀጥላል. . .


ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2😁1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።”
             ሉቃስ 21፥15




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍3
#እራሳችንን_እንመርምር

በሥራ ወይም በትምህርት ቦታችን አልያም በማንኛውም የሌተቀን እንቅስቃሴያችን በምን አይነት ውሎ ነው የምንውለው? በጥንቃቄ እና በማስተዋል ተቃኝተን ወይስ በግድ የለሽነት?

“የዚያን ጊዜም አለቆችና መሳፍንቱ ስለ መንግሥቱ በዳንኤል ላይ ሰበብ ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን የታመነ ነበረና፥ ስሕተትና በደልም አልተገኘበትምና በእርሱ ላይ ሰበብና በደል ያገኙበት ዘንድ አልቻሉም።”
ዳንኤል 6፥4




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures