ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
1ኛ ሳሙኤል 3


ይህ ምዕራፍ እንደሚከተለው ይጀምራል፦

“ብላቴናውም ሳሙኤል በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይገለጥም ነበር።” (ቁ. 1)

ሲደመድም፦

“እግዚአብሔርም ደግሞ በሴሎ ተገለጠ፤ እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ቃል ለሳሙኤል በሴሎ ይገለጥ ነበር። የሳሙኤልም ቃል ለእስራኤል ሁሉ ደረሰ።” (ቁ. 21)

ለመሆኑ በእነዚህ ቁጥሮች መካከል ምን ለውጥ እንመለከታለን?

1. የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ(ቁ.1) እና ለሳሙኤል የእግዚአብሔር ቃል ይገለጥ ነበር (ቁ. 21)

2. ራእይም አይገለጥም ነበር (ቁ. 1) እና እግዚአብሔር ደግሞ በሴሎ ተገለጠ (ቁ. 21)

ታዲያ ይህ ለውጥ እንዴት ተከሰተ? ከሳሙኤል ሕይወት ምን እንማራለን?

1. ምንም የሚታይ ነገር በሌለበት እግዚአብሔርን በታማኝነት ያገለግል ነበር። (ቁ.1)

2. ሳሙኤል እግዚአብሔር ባለበት ይገኛል(ቁ. 3)

3. ቅን ነበር። ኤሊ ምንም ያህል ለእግዚአብሔር ቤት የሚቀና ባይሆንም ይታዘዘው፣ ይሰማው እና እግዚአብሔር ላስቀመጠው ታላቅን የማክበር ትእዛዝ ተገዢ ነበር። (ቁ. 5-9)

4. የኤሊ ልጆች በክፋት የተሞሉ ቢሆኑም ሳሙኤል እራሱን በቅድስና የጠበቀ ሰው ነው። (ቁ. 13)

5. የእግዚአብሔርን እውነት ያለፍርሃት የሚናገር ሰው ነው። (ቁ. 18)


ውጤቱስ

1. እግዚአብሔር እና ቃሉ ተገለጠ። (ቁ. 21)

2. የሳሙኤል ቃል በምድር ላይ አይወድቅም ነበር (ቁ. 19)

3. ሕዝቡ ከእስራኤል ጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ ለእግዚአብሔር ነቢይ ለመሆን የታመነ እንደሆነ አወቀ (ቁ. 20)

ነቢይ እንደሆነ እያወጀ አልሄደም። ነገር ግን ሕዝቡ ነቢይ ለመሆን የታመነ እንደሆነ መሰከሩለት።

በዘመናችን እግዚአብሔር እንዲገለጥ እንፈልጋለን? ከፈለግን በግል ሕይወታችን ይህን የሳሙኤልን ፈለግ እንከተል!




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍154
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እኔ ለእግዚአብሔር ሕያው ሆኜ እኖር ዘንድ በሕግ በኩል ለሕግ ሞቼ ነበርና።”
             ገላትያ 2፥19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
bereket-1.pdf
1.9 MB
👉ርዕስ፦ በረከት ወይስ መርገም አንዱን ምረጥ!
✍️ደራሲ፦ ዴሬክ ፕሪንስ
📑የገጽ ብዛት፦ 200
bereket-2.pdf
2.1 MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፥ በማያውቋትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፥ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውምም።”
                ኢሳይያስ 42፥16



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት ያስተዳድሩ የነበሩ ሄሮድሶች የምን ወገን ነበሩ?
Anonymous Quiz
38%
ሀ. ይሁዳ
5%
ለ. ኤሳው
3%
ሐ. ኤፍሬም
11%
መ. ኤዶም
13%
ሠ. ለ እና መ
12%
ረ. ሀ እና መ
18%
ሰ. መልስ የለም
👍4
ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በየትኛው አውራጃ ተወልዶ በየትኛው አውራጃ አደገ?
Anonymous Quiz
59%
ሀ. ቤተልሔም እና ናዝሬት
7%
ለ. ይሁዳ እና ናዝሬት
8%
ሐ. ይሁዳ እና ገሊላ
27%
መ. ቤተልሔም እና ገሊላ
👍5
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እርሱንና ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን ሁሉ አላጠርህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱም በምድር ላይ በዝቶአል።”
               ኢዮብ 1፥10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት



ሮሜ 9፥6-13

6. እንግዲህ እስራኤል በመጀመሪያ ይህን ያህል የተባረከ ሕዝብ ከነበረ፥ በኋላ ምን ነካው? አይሁዳውያን ለምን ደኅንነትን ሳያገኙ ቀሩ? የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ተሻረባቸው ወይስ ተሰበረ? ይህ ሁሉ በጭራሽ አልሆነባቸውም! እግዚአብሔር ለእስራኤል የሰጠውን ተስፋ አላጠፈውም። ነገር ግን እነዚያ ሁሉ ተስፋዎች፥ ማለትም አዳኝ የመላክ ተስፋ፥ የደኅንነት ተስፋ፥ ለእውነተኞች አይሁዳውያን ተሰጥተዋል። ጳውሎስ ራሳቸውን አይሁዳውያን ብለው የሚጠሩ ሁሉ እውነተኞች አይሁዳውያን አይደሉም ብሎአል (ሮሜ 2፥28-29 ይመለከቷል)። የእስራኤል ዝርያዎች ሁሉ በትውልድ አይሁዳዊ የሆኑት) እስራኤላዊ (እውነተኞች አይሁዳውያን) አይደሉም።

ስለዚህ እግዚኣብሔር ለአይሁዳውያን የሰጠው ተስፋ አልተሻረም። ምክንያቱም ከአይሁዳውያን ብዙዎቹ «እውነተኞች አይሁዳውያን» አልነበሩም። እውነተኞች አይሁዳውያን በኢየሱስ የሚያምኑ አይሁዳውያን ብቻ ናቸው። በቁ. 8 ላይ ጳውሎስ በተፈጥሮ አይሁዳውያንና (በትውልድ የአብርሃም ዘር የሆኑ) የተስፋው ልጆች በሆኑ አይሁዳውያን (በተስፋው ማለት በኢየሱስ ያመኑ አይሁዳውያን) መካከል ያለውን ልዩነት ይናገራል። «የተስፋው ልጆች» የሆኑት ማለትም በክርስቶስስ ኢየሱስ ያመኑ እውነተኛ አይሁዳውያን፥ የእግዚአብሔር ተስፋ የተፈጸመላቸው ለእነርሱ ብቻ ነው (ሮሜ 4፥11-17)፡፡

«የተስፋው ልጆች» በእምነት ጻድቃን ለመሆን የሚፈልጉ ናቸው። «በሥጋ የተወለዱት» ደግሞ በራሳቸው ጥረትና በመልካም ሥራ ጻድቃን ለመሆን የሚፈልጉት ናቸው (ሮሜ 9፥32፤ ገላ. 3፥6-9)፡፡

7-9. በሥጋ የተወለዱ ልጆች (በመወለድ ዝርያዎች) የሆኑ ሁሉ የውርስ ተስፋ መቀበል እንደሌለባቸው ለማሳየት ጳውሎስ የአብርሃምን ምሳሌነት ይጠቅሳል። አብርሃም ሁለት «ከእርሱ የተወለዱ ልጆች» ነበሩት። እነርሱም ይስሐቅና እስማኤል ናቸው። ነገር ግን ከሁለቱ አንዱ ማለትም ይስሐቅ ብቻ ነው የአብርሃም እውነተኛ ልጅ፤ ውርስ ያገኘውም ይስሐቅ ብቻ ነበር። አብርሃም በመጀመሪያ ከሚስቱ ገረድ የወለደው እስማኤልን ቢሆንም (ዘፍ. 16፥1-4፥ 15-16) የእስማኤል ዝርያዎች ግን አይሁዳውያን አልነበሩም። አይሁዳውያን የመጡት አብርሃም ከሚስቱ ከሳራ ካገኘው ከሁለተኛ ልጁ ክይስሐቅ ነው። ይህ ልጅ እግዚአብሔር ለአብርሃም እስጥሃለሁ ብሎ ተስፋ የገባለት ነበር (ዘፍ. 18:14 ፤ 2፥1-13፤ ገላ. 4፥22-23)። እግዚአብሔር እውነተኛ ዝርያዎችን በመወለድ ብቻ አይቆጥርም። በእግዚአብሔር ፊት እውነተኛ ዝርያዎች በእግዚአብሔር ተስፋ መሠረት የሚመጡት ናቸው። ይህም በእምነት በኩል የሚመጡት ማለት ነው። አብርሃም በእግዚአብሔር ተስፋ በማመኑ ምክንያት ነበር እግዚአብሔር አብርሃምንና ሳራን በልጅ የባረካቸው።

እዚህ ላይ የጳውሎስ ዋና ነጥብ በመወለድ የአብርሃም የሥጋ ልጆች በመሆናቸው ብቻ አይሁዳውያን የእግዚአብሔር ልጆች ነን ሊሉ አለመቻላቸውን ነው። የእግዚአብሔር እውነተኛ ልጆች የተስፋው ልጆች ብቻ ናቸው። የአብርሃም ዝርያዎች ተብለው የሚታወቁት ወይም በሌላ መንገድ ለማየት፥ እውነተኛ አይሁዳውያን የሚባሉት የእምነት ልጆች እንጂ የሥጋ ልጆች አይደሉም። ስለሆነም እውነተኞቹ የአብርሃም ዝርያዎች በክርስቶስ ያመኑት ብቻ ናቸው። አይሁዳውያን (በትውልድ) ክርስቶስን አንቀበለውም ባሉት ጊዜ፥ ራሳቸውን ናቁ፥ ውርሳቸውንም አጠፉ፥ በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ የነበራቸውንም ክቡር ቦታ አጡ።

10-12. በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እግዚአብሔር በሥጋ ትውልድ ብቻ እውነተኛ ወራሾቹን እንደማይመርጥ፥ ጳውሎስ ሁለተኛ ምሳሌውን ይሰጣል። የይስሐቅ ሚስት ርብቃ መንትያ ልጆችን ወለደች። በአይሁድ ባሕል መሠረት ከመንትዮቹ በመጀመሪያ የተወለደው ኤሳው የቤተሰቡን ውርስ የመቀበል መብት ነበረው። እግዚአብሔር ግን በራሱ ፈቃድ ውርሱ ከመንትያዎቹ ሁለተኛ ሆኖ ለተወለደው ለያዕቆብ እንዲሆን አደረገ(ዘፍ. 25፥20-26፤ 27፥1-35)።

እዚህ ላይ እግዚአብሔር ውርስን ከልደት የተነሣ እንደማይሰጥ እናያለን። ነገር ግን የሚሰጠው በራሱ ፈቃድ ነው። ይህም በመምረጥ ያለው ዓላማ ጸንቶ እንዲቆምለት ነው (ቁ. 11)። ገና ከመወለዱ በፊት እንኳ እግዚአብሔር ያዕቆብን መረጠው፤ ወይም የውርሱ ወራሽ እንዲሆን ሾመው። ያዕቆብ ለዚህ የተገባ ሆኖ እንዲገኝ መልካም ሥራን ለመሥራት ምንም ዓይነት አጋጣሚ አልነበረውም፤ ጨርሶም ገና አልተወለደም ነበር። የእግዚአብሔር ምርጫ በሥራ ላይ የተመሠረተ አይደለም፤ ነገር ግን በራሱ በእግዚአብሔር የበላይነት ፈቃዱ ላይ ብቻ የተመሠረተ ነው። እግዚአብሔር የተገባን ስለሆንን አይመርጠንም፤ እርሱ የሚመርጠን ከጸጋው የተነሣ ብቻ ነው።

13. በዚህ መንገድ እግዚአብሔር ያዕቆብንና ዝርያዎቹን ወደደ (መረጠ)። ኤሳውንና ዝርያዎቹንም ጠላ (ናቀ) (ሚል. 1፥2-3)። ያዕቆብና ኤሳው ሁለቱም የይስሐቅ ልጆች ነበሩ፤ ነገር ግን ያዕቆብ ብቻ ውርስ ተቀበለ። እውነተኞቹ አይሁዳውያን ወይም እውነተኞቹ እስራኤላውያን የሚፈልቁት ከያዕቆብ ብቻ ሆነ።

ስለዚህ በዚህ ክፍል የጳውሎስ ዋና ትምህርት ይህ ነው፥ በልደት ብቻ አይሁዳውያን የሆኑትን ወይም በመልካም ሥራቸው ጻድቃን ለመሆን የሚፈልጉትን እግዚአብሔር አልመርጣቸውም፥ ልጆቹም አላደርጋቸውም። ይልቁንም እርሱ የመረጣቸው ጥሪውን ሰምተው እምነታቸውን በልጁ በኢየሱስ ላይ ያደረጉትን ብቻ ነው።



ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 371-372




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍41
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፦ ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብፅም እንዳይመለስ ብሎአልና።”
                ዘጸአት 13፥17




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
#እራሳችንን_እንመርምር

ዘመናችን ምን ያህል እየሄደ ነው? ምን ያክል ዘመናችንን ቀድመን ወይም ዘግይተን እንዳለን እናውቃለን ወይ? ከዘመን መቅደም ወይም ከዘመን መዘግየት ምን ማለት ነው?


“አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ።”
መዝሙር 39፥4

“እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣ የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤ አላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ።”
መዝሙር 39፥4 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።”
           1ኛ ተሰሎንቄ 5፥17-18



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍52
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#ቀርሜሎስ፤ ፍሬያማ ቦታ ማለት ነው። ከገሊላ ባሕር በስተምዕራብ 20 ኪ.ሜ. ርቆ የሚገኝ ተራራማ አገር። ወሰኑ እስከ ታላቁ ባሕር ይደርሳል። ኤልያስ እሳት ከሰማይ ወርዶ መሥዋዕቱን እንዲበላ፥ ዝናብም እንዲዘንብ በቀርሜሎስ ተራራ ጸለየ፤ 1ነገ. 18፥17-46። ኤልሳዕም በዚህ ቦታ ይኖር ነበር፤ 2ነገ. 4፥25።



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 89




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፥ እጁንም ጭኖበት፦ ወንድሜ ሳውል ሆይ፥ ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፥ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ አለ።”
             ሐዋርያት 9፥17




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት


ሮሜ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ እንግዲህ ምን እንላለን? በእግዚአብሔር ዘንድ ዓመፃ አለ ወይ? አይደለም።
¹⁵ ለሙሴ፦ የምምረውን ሁሉ እምረዋለሁ ለምራራለትም ሁሉ እራራለታለሁ ይላልና።
¹⁶ እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ።
¹⁷ መጽሐፍ ፈርዖንን፦ ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ ይላልና።
¹⁸ እንግዲህ የሚወደውን ይምረዋል፥ የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል።


ሮሜ 9 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር አድልዎ ያደርጋልን? በፍጹም አያደርግም!
¹⁵ ለሙሴ፣ “የምምረውን እምረዋለሁ፤ ለምራራለትም እራራለታለሁ” ይላልና።
¹⁶ እንግዲህ ይህ ከሰው ፍላጎት ወይም ጥረት ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው።
¹⁷ መጽሐፍ ፈርዖንን፣ “ኀይሌ በአንተ እንዲታይ፣ ስሜም በምድር ሁሉ እንዲነገር ለዚህ አስነሣሁህ” ይላልና።
¹⁸ ስለዚህ እግዚአብሔር ሊምረው ለሚወደው ምሕረት ያደርግለታል፤ ልቡ እንዲደነድን የፈለገውንም ያደነ ድነዋል።


ሮሜ 9 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ እንግዲህ ይህ ምንን ያመለክታል? እግዚአብሔር ያዳላል ማለት ነው? ይህን ማለት አንችልም።
¹⁵ ምክንያቱም እግዚአ ብሔር ለሙሴ ፥ «ልምረው የምፈልገውን እምረዋለሁ፤ ልራራለት ለምፈልገውም እራራለታለሁ» ብሎታል።
¹⁶ ስለዚህ የእግዚአብሔርን በረከት ማግኘት የሚቻለው በሰው ፈቃድ ወይም ጥረት ሳይሆን በእግዚአብሔር ምሕረትና ቸርነት ብቻ ነው።
¹⁷ በቅዱሳት መጻሕፍት፥ “ፈርዖን ሆይ፥ ኃይሌን ለማሳየትና ስሜንም በሰዎች ሁሉ ዘንድ ለማሳወቅ አነሣሣሁህ» ተብሎ የተነገረውን እዚህ ላይ ልንጠቅሰው እንችላለን።
¹⁸ ስለዚህ እግዚአብሔር ሊምረው የፈለገውን ሲምረው ሌላውን ደግሞ እልኸኛ ያደርገዋል።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2🔥1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“አንተ ግን፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የምነግርህን ስማ፤ እንደዚያ እንደ ዓመፀኛው ቤት ዓመፀኛ አትሁን፤ አፍህን ክፈት የምሰጥህንም ብላ።”
          ሕዝቅኤል 2፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ሚልክያስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አሁንም እናንተ ካህናት ሆይ፥ ይህ ትእዛዝ ለእናንተ ነው።
² ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ ባትሰሙ፥ በልባችሁም ባታደርጉት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እርግማን እሰድድባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማታለሁ፤ አሁንም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና እኔ ረግሜአታለሁ።
³ እነሆ፥ ክንዳችሁን እገሥጻለሁ፥ የመሥዋዕታችሁንም ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፤ ከእርሱም ጋር በአንድነት ትወሰዳላችሁ።
⁴ ቃል ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ይሆን ዘንድ ይህን ትእዛዝ እንደ ሰደድሁላችሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
⁵ ቃል ኪዳኔ ከእርሱ ጋር የሕይወትና የሰላም ቃል ኪዳን ነበረ፤ ይፈራ ዘንድም እነርሱን ሰጠሁት፤ እርሱም ፈራኝ፥ ከስሜም የተነሣ ደነገጠ።
⁶ የእውነት ሕግ በአፉ ውስጥ ነበረች፥ በከንፈሩም ውስጥ በደል አልተገኘበትም፤ ከእኔም ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፥ ብዙ ሰዎችንም ከኃጢአት መለሰ።
⁷ ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።
⁸ እናንተ ግን ከመንገዱ ፈቀቅ ብላችኋል፤ በሕግም ብዙ ሰዎችን አሰናክላችኋል፤ የሌዊንም ቃል ኪዳን አስነውራችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
⁹ ስለዚህ መንገዴን እንዳልጠበቃችሁ፥ በሕግም ለሰው ፊት እንዳዳላችሁ መጠን፥ እኔ ደግሞ በሕዝብ ሁሉ ፊት የተናቃችሁና የተዋረዳችሁ አድርጌአችኋለሁ።
¹⁰ ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳንዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን?
¹¹ እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።
¹² ይህን ከሚያደርግ ሰው፥ እግዚአብሔር የሚጠራውንና የሚመልሰውን ለሠራዊትም ጌታ ለእግዚአብሔር ቍርባን የሚያቀርበውን ከያዕቆብ ድንኳን ያጠፋል።
¹³ ይህንም ደግሞ አድርጋችኋል እግዚአብሔር ቍርባኑን ዳግመኛ እንዳይመለከት፥ ከእጃችሁም በደስታ እንዳይቀበለው መሠዊያውን በእንባና በልቅሶ በኀዘንም ትከድናላችሁ።
¹⁴ እናንተም፦ ስለ ምንድር ነው? ብላችኋል። ሚስትህ ባልንጀራህና የቃል ኪዳንህ ሚስት ሆና ሳለች እርስዋን አታልለሃታልና እግዚአብሔር በአንተና በልጅነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለ ሆነ ነው።
¹⁵ እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድር ነው? ዘር አይደለምን? ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።
¹⁶ መፋታትን እጠላለሁ፥ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ልብሱንም በግፍ ሥራ የሚከድነውን ሰው እጠላለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ እንዳታታልሉ መንፈሳችሁን ጠብቁ።
¹⁷ እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችኋል። እናንተም፦ ያታከትነው በምንድር ነው? ብላችኋል። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል፤ ወይስ፦ የፍርድ አምላክ ወዴት አለ? በማለታችሁ ነው።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔርን ለመቋቋም የሚያስችል፣ አንዳችም ጥበብ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።”
           ምሳሌ 21፥30 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍72
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1