' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በሄድህበትም ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁ፤ በምድርም ላይ እንዳሉ እንደ ታላላቆቹ ስም ታላቅ ስም አደርግልሃለሁ።”
2ኛ ሳሙኤል 7፥9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤3👍2
ከእስራኤል ወይም ከይሁዳ መሪዎች መካከል በሕይወት እያለ ልጁን አንግሶ የሞተ ንጉሥ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
12%
ሀ. ኢዮሣፍጥ
5%
ለ. ሕዝቅያስ
64%
ሐ. ዳዊት
11%
መ. ሰሎሞን
7%
ሠ. ሁሉም
👍5
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለስልጣን ሲል ሰባ ወንድሞቹን ያሳረደው ሰው የማን ልጅ ነው?
Anonymous Quiz
3%
ሀ. ሰሎሞን
9%
ለ. ዳዊት
11%
ሐ. ጌዴዎን
53%
መ. ይሩበኣል
10%
ሠ. ሐ እና መ
13%
ረ. መልስ የለም
👍8
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“አምላካችን እግዚአብሔር በኮሬብ እንዲህ ብሎ ተናገረን። በዚህ ተራራ የተቀመጣችሁት በቃ”
ዘዳግም 1፥6
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“አምላካችን እግዚአብሔር በኮሬብ እንዲህ ብሎ ተናገረን። በዚህ ተራራ የተቀመጣችሁት በቃ”
ዘዳግም 1፥6
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤8🥰1
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#ሲካር፤ ከሴኬም በስተደቡብ አንድ ኪኪሎሜትር ርቆ የሚገኝ ቦታ። በሲካር ያዕቆብ መሠዊያ ሠራ፤ የውሃ ጕድጓድም ቈፈረ። ኢየሱስም በዚህ የውሃ ጕድጓድ አጠገብ አንዲት የሰማርያን ሴት አነጋገረ፤ ዘፍ. 33፥18-20፤ ዮሐ. 4፥5-7። ዛሬ የውሃው ጕድጓድ በአንዲት ቤተክርስቲያን ውስጥ ይታያል። የጕድጓዱ መግቢያ ከዛሬው የመሬት አቀማመጥ ልክ ስድስት ሜትር ዝቅ ያለ ነው፤ የጕድጓዱ ጥልቀት 32 ሜትር ነው።
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 78

👍8❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ።”
ዕብራውያን 11፥8

❤5👍1
#እራሳችንን_እንመርምር
መቼስ በእውነት እግዚአብሔርን የሚፈልግ እና የሚወድ በዘመኑም እግዚአብሔር ፈቃዱን እንዲፈጽም የሚሻ ሰው መሆንን እንፈልጋለን። እግዚአብሔር በታላቅ እጁ በዘመናችን ሁሉ ከእኛ ጋር እንዲሆንስ? ተገኝቶ ነው? የሚያስብል ነው። ታዲያ ይህ እንዲሆን ምን እናድርግ? ምንስ ከሕይወታችን ይወገድ?
“እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ።”
ሐዋርያት 13፥2
“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።”
ኤርምያስ 15፥19
“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ።”
ዘካርያስ 3፥7
“እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ከጠቀስኋቸው ነገሮች ቢያነጻ ለክቡር አገልግሎት የሚውል፣ የተቀደሰ፣ ለጌታው የሚጠቅም፣ ለመልካም ሥራም ሁሉ የተሰናዳ ዕቃ ይሆናል።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥21 (አዲሱ መ.ት)

❤6👍6
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አያይም።”
ዮሐንስ 8፥51

❤8👍3
የመጽሐፉ የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ሲሆን መግቢያው እንደሚከተለው ይላል፦
የገላትያ መልእክት መግቢያ አደገኛ መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ በዘመናችን ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ እውነተኛውን መንፈሳዊ ሕይወት በመተካት ላይ የሚገኘውን የሕግ አክራሪነት ዝንባሌ የሚያጋልጥ ነው። «በሐሰተኛ ትምህርቶች መካከል ያለ» ከማለት ይልቅ «በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ» ውስጥ ያልኩበት ዋናው ምክንያት በዚህ ዘመን ሕግ አክራሪነት የበለጠ የሰፈነው በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሆነ ነው።
በሚሊየን የሚቆጠሩ አማኞች አንዳንድ ድርጊቶችን ከመፈጸም በመቆጠባቸው ወይም አንድ የሃይማኖት መሪ በመከተላቸው ወይም የአንድ ቡድን አባል በመሆናቸው ብቻ «መንፈሳዊ» እንደሆኑ ያስባሉ። ዳሩ ግን ይህ ስሕተት መሆኑንና ወደ ትክክለኛው ሕይወት መምጣት የምንችለው ራሳችንን መንፈስ ቅዱስ እንዲቆጣጠረን በፈቀድንለት መጠን መሆኑን ጌታ በገላትያ መልእክት ውስጥ በግልፅ አሳይቶናል።

👍7
arnet-1-cr.pdf
1.8 MB
የገላትያ መልእክት
📔ርዕስ፦ አርነት መውጣት
👤ጸሐፊ፦ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ተርጓሚ፦ጌቱ ግዛው
📑የገጽ ብዛት፦140
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📔ርዕስ፦ አርነት መውጣት
👤ጸሐፊ፦ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ተርጓሚ፦ጌቱ ግዛው
📑የገጽ ብዛት፦140
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።”
ማቴዎስ 4፥22
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።”
ማቴዎስ 4፥22
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤3👍1👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ወዳጅ ሆይ፥ በጎ የሆነውን እንጂ ክፉን አትምሰል። በጎ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው፤ ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።”
3ኛ ዮሐንስ 1፥11

❤3👍3
1ኛ ሳሙኤል 3
ይህ ምዕራፍ እንደሚከተለው ይጀምራል፦
“ብላቴናውም ሳሙኤል በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይገለጥም ነበር።” (ቁ. 1)
ሲደመድም፦
“እግዚአብሔርም ደግሞ በሴሎ ተገለጠ፤ እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ቃል ለሳሙኤል በሴሎ ይገለጥ ነበር። የሳሙኤልም ቃል ለእስራኤል ሁሉ ደረሰ።” (ቁ. 21)
ለመሆኑ በእነዚህ ቁጥሮች መካከል ምን ለውጥ እንመለከታለን?
1. የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ(ቁ.1) እና ለሳሙኤል የእግዚአብሔር ቃል ይገለጥ ነበር (ቁ. 21)
2. ራእይም አይገለጥም ነበር (ቁ. 1) እና እግዚአብሔር ደግሞ በሴሎ ተገለጠ (ቁ. 21)
ታዲያ ይህ ለውጥ እንዴት ተከሰተ? ከሳሙኤል ሕይወት ምን እንማራለን?
1. ምንም የሚታይ ነገር በሌለበት እግዚአብሔርን በታማኝነት ያገለግል ነበር። (ቁ.1)
2. ሳሙኤል እግዚአብሔር ባለበት ይገኛል(ቁ. 3)
3. ቅን ነበር። ኤሊ ምንም ያህል ለእግዚአብሔር ቤት የሚቀና ባይሆንም ይታዘዘው፣ ይሰማው እና እግዚአብሔር ላስቀመጠው ታላቅን የማክበር ትእዛዝ ተገዢ ነበር። (ቁ. 5-9)
4. የኤሊ ልጆች በክፋት የተሞሉ ቢሆኑም ሳሙኤል እራሱን በቅድስና የጠበቀ ሰው ነው። (ቁ. 13)
5. የእግዚአብሔርን እውነት ያለፍርሃት የሚናገር ሰው ነው። (ቁ. 18)
ውጤቱስ
1. እግዚአብሔር እና ቃሉ ተገለጠ። (ቁ. 21)
2. የሳሙኤል ቃል በምድር ላይ አይወድቅም ነበር (ቁ. 19)
3. ሕዝቡ ከእስራኤል ጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ ለእግዚአብሔር ነቢይ ለመሆን የታመነ እንደሆነ አወቀ (ቁ. 20)
ነቢይ እንደሆነ እያወጀ አልሄደም። ነገር ግን ሕዝቡ ነቢይ ለመሆን የታመነ እንደሆነ መሰከሩለት።
✍በዘመናችን እግዚአብሔር እንዲገለጥ እንፈልጋለን? ከፈለግን በግል ሕይወታችን ይህን የሳሙኤልን ፈለግ እንከተል!

👍15❤4
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እኔ ለእግዚአብሔር ሕያው ሆኜ እኖር ዘንድ በሕግ በኩል ለሕግ ሞቼ ነበርና።”
ገላትያ 2፥19

❤6
bereket-1.pdf
1.9 MB
👉ርዕስ፦ በረከት ወይስ መርገም አንዱን ምረጥ!
✍️ደራሲ፦ ዴሬክ ፕሪንስ
📑የገጽ ብዛት፦ 200
✍️ደራሲ፦ ዴሬክ ፕሪንስ
📑የገጽ ብዛት፦ 200
bereket-2.pdf
2.1 MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፥ በማያውቋትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፥ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውምም።”
ኢሳይያስ 42፥16

ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት ያስተዳድሩ የነበሩ ሄሮድሶች የምን ወገን ነበሩ?
Anonymous Quiz
38%
ሀ. ይሁዳ
5%
ለ. ኤሳው
3%
ሐ. ኤፍሬም
11%
መ. ኤዶም
13%
ሠ. ለ እና መ
12%
ረ. ሀ እና መ
18%
ሰ. መልስ የለም
👍4