ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
333 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው



                   ክፍል - ፫


ለ. ወደ አባትህ መኝታ ወጥተሃልና አረከስኸው፤ ወደ አልጋዬም ወጣ

ሮቤል ከልቡ መዋዕል ጋር በአባቱ በያዕቆብ እየተወቀሰ እንዲኖርና ብኩርናውንም እንዲያጣ ያደረገው ከአባቱ ቁባትና ለወንድሞቹም እናት ከምትሆን ከራሔል አገልጋይ ከባላ ጋር መተኛቱ ነው (ዘፍ. 35፥22)፡፡ ያልተገባውን፥ የእርሱም ካልሆነችው፥ ያውም ደግሞ ከወንድሞቹ እናትና ከአባቱም ቁባት ጋር በመተኛቱ አባቱን በድርጊቱ አሳዘነ፡፡ የአባቱንም አልጋ በክፉ ተግባሩ አረከሰ፡፡ ባልተገባው ቦታ ተገኘ፡፡ የአባቱን ክብር አቃለለ፡፡ ያልተገባውን ስለነካ፥ የአባቱንም መኝታ ስላረከሰ የክብር አለቅነትና የኃይልም አለቅነት ክእርሱ እንዲወሰድ ተጨማሪ ምክንያት ሆነ።

ሰው ያልተገባውን ሲያደርግና ስፍራውንም ለቆ ያለቦታው ያልታዘዘውን ሲፈጽም እግዚኣብሔርን ያሳዝናል:: በድርጊቱም በዙሪያው ያሉትን ሁሉ ይጎዳል፡፡ ከዚህም የተነሳ ያልጠበቀውን፥ ያሳሰበውንና ያልገመተውን ዋጋ እንዲከፍል ይሆናል፡፡ የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ የሆነው ሳኦል ያልታዘዘውንና ያልተገባውን ድርጊቶች ደጋግሞ አደረገ፡፡ በነዚህም ድርጊቶቹ ምክንያት የእስራኤል ነገሥታት በኩር ሆኖ የነበረው ሳኦል መንግሥቱ ከእርሱ ተወስዳ ለእሴይ ልጅ ለዳዊት ተሳለፈች (1ኛ ሳሙ. 13፥8-14፤ 1ኛ ሳሙ. 15፥ 24-29)::

የባቢሎኑ ንጉሥ ናቡከደነጹር በኃይልና በዝናው እጅግ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ የማይገባውን ክብርና ሞገስ አብዝቶ ፈለገ፡፡ የሚሆነውን ነገር ሁሉ እርሱ ብቻውን ባለው ጉልበቱና ኃይሉ እንደሚያደርገው እንጂ ከእርሱ በላይ ሌላ እንዳለ ረሳ፡፡ ለእግዚእብሔር ብቻ የሆነውን የአምላክነትና የክብር ስፍራ ሊወስድ ወደደ፡፡ በዚህም ምክንያት እግዚእብሔር ከነበረው ክብርና አለቅነት አውርዶ እንደ እንስሳ ሳር እንዲበላና በዱርም ለዓመታት እንዲቀመጥ አደረገው (ዳን. 4፥28- 33)::

ያልተገባንን ማድረግ በምንጀምርበት ጊዜ እግዚአብሔር ከሚፈልገን ስፍራ ሳይሆን ለእኛ የሚመቸንንና የሚስማማንን ነገር ለማድረግ እየጣርን እንደ ሆነ ግልጽ ነው:: ይህንንም እያበዛን ከእግዚአብሔር አሳብ በምንርቅ ጊዜ በልጅነት መብታችን የተገባንን በረከት ለማጣት መንገድን ማዘጋጀት እንጀምራለን፡፡ ሮቤል በአባቱ መኝታ ላይ በመገኘቱና የእርሱም ባልሆነ አልጋ ላይ የእርሱ ካልሆነች ሴት ጋር በመተኛቱ ታላቅ በረከት ከእርሱና ከትውልዱ ተወሰደበት፡፡ ዛሬም የእነርሱ ባልሆነ አልጋ ላይ የእነርሱ ካልሆኑ ጋር የተገኙ ጸጸታቸው ከማያድናቸው ሀዘን ውስጥ የወደቁ አጅግ ብዙ ናቸው፡፡ የእድሜያቸው ገመድ በድርጊታቸው እየተያዘ ሕይወታቸው የተቀጠፈ አያሌ ናቸው፡፡

ሙሴም ሰለ ሮቤል ምርቃት ሲናገር የብኩርናውን ነገር በፍጹም አላነሳም፡፡ ብኩርናው ከእርሱ ስለ ተወሰደበት የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሙሴ በሁለት ነገሮች ብቻ መረቀው (ዘዳ. 33፥6)፡፡ የሙሴም በረከቶች ለሮቤል እንደሚከተሉት ነበሩ፦

1ኛ. በሕይወት ይኑር፤ አይሙት

2ኛ. ሰዎቹም በቁጥር ብዙ ይሁኑ


ምንም እንኳ ሮቤል በተግባሩ ሞት ተገብቶት ቢሆንም ምሕረት ለእርሱ ይሁን፥ ዘሩም ብዙ ይሁን፤ በቁጥርም ይብዛ ብሎ ሙሴ መረቀው፡፡ ብዙ የሆነው የእግዚአብሔርን ምሕረት ሙሴ በሮቤልና በልጆቹ ላይ አወጀ፡፡ የእግዚአብሔርም ምሕረት ሮቤልንና ቤቱን ጎበኘ፡፡ በብኩርናው የተገባውን ቢነጠቅም ከአግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት የተነሳ በሕይወት እንዲኖርና ዘሩም እንዲበዛ ሆነ፡፡ ሮቤል ምንም እንኳ በሰው ቁጥር እንዲበዛ ቢባልለትም በሰው ቁጥር መብዛት ኃይል ሆኖ ሳለ ለእርሱ ግን ኃይል እንዳይሆንለት ስለ ተወሰደበት አለቅነትና ኃይል ለይሁዳ፤ ብኩርናውም ለዮሴፍ ልጆች ተላለፈ፡፡

በሁለት ልብ የሚያነክሰና ልቡም እንደ ውኃ የሚዋልል ከእግዚአብሔር የሚቀበለው ብዙ የለም፡፡ ሳይሞት በሕይወት ይኖር ይሆናል፡፡ ኃይልና ጉልበት ግን ከእርሱ ይርቃል፡፡ የእግዚአብሔርም ቃል ሲመሰክር “ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው” (ያዕ. 1፥7 ) በማለት ይናገራል፡፡


ይቀጥላል...


ምንጭ፦ አበራ ጌታሁን (ዶ/ር)፤ የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው፤ ገጽ 9-11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፤ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።”
                 መሳፍንት 7፥2




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍53
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?



2ኛ ቆሮ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ስለዚህ ምክንያት ምሕረት እንደ ተሰጠን መጠን ይህ አገልግሎት ስላለን አንታክትም።
² ነገር ግን የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናልና በተንኮል አንመላለስም የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናመሰግናለን።
³ ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው።
⁴ ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።
⁵ ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።
⁶ በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና።
⁷ ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤
⁸ በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፤ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤
⁹ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤
¹⁰ የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን።
¹¹ የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና።
¹² ስለዚህ ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል።
¹³ ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤
¹⁴ ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛን ደግሞ ከኢየሱስ ጋር እንዲያስነሣን ከእናንተም ጋር እንዲያቀርበን እናውቃለንና።
¹⁵ በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን ያበዛ ዘንድ፥ ሁሉ ስለ እናንተ ነውና።
¹⁶ ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።
¹⁷-¹⁸ የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በሄድህበትም ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁ፤ በምድርም ላይ እንዳሉ እንደ ታላላቆቹ ስም ታላቅ ስም አደርግልሃለሁ።”
          2ኛ ሳሙኤል 7፥9



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
ከእስራኤል ወይም ከይሁዳ መሪዎች መካከል በሕይወት እያለ ልጁን አንግሶ የሞተ ንጉሥ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
12%
ሀ. ኢዮሣፍጥ
5%
ለ. ሕዝቅያስ
64%
ሐ. ዳዊት
11%
መ. ሰሎሞን
7%
ሠ. ሁሉም
👍5
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለስልጣን ሲል ሰባ ወንድሞቹን ያሳረደው ሰው የማን ልጅ ነው?
Anonymous Quiz
3%
ሀ. ሰሎሞን
9%
ለ. ዳዊት
11%
ሐ. ጌዴዎን
53%
መ. ይሩበኣል
10%
ሠ. ሐ እና መ
13%
ረ. መልስ የለም
👍8
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“አምላካችን እግዚአብሔር በኮሬብ እንዲህ ብሎ ተናገረን። በዚህ ተራራ የተቀመጣችሁት በቃ”
              ዘዳግም 1፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8🥰1
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት



#ሲካር፤ ከሴኬም በስተደቡብ አንድ ኪኪሎሜትር ርቆ የሚገኝ ቦታ። በሲካር ያዕቆብ መሠዊያ ሠራ፤ የውሃ ጕድጓድም ቈፈረ። ኢየሱስም በዚህ የውሃ ጕድጓድ አጠገብ አንዲት የሰማርያን ሴት አነጋገረ፤ ዘፍ. 33፥18-20፤ ዮሐ. 4፥5-7። ዛሬ የውሃው ጕድጓድ በአንዲት ቤተክርስቲያን ውስጥ ይታያል። የጕድጓዱ መግቢያ ከዛሬው የመሬት አቀማመጥ ልክ ስድስት ሜትር ዝቅ ያለ ነው፤ የጕድጓዱ ጥልቀት 32 ሜትር ነው።



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 78




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍82
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ።”
              ዕብራውያን 11፥8




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1
#እራሳችንን_እንመርምር

መቼስ በእውነት እግዚአብሔርን የሚፈልግ እና የሚወድ በዘመኑም እግዚአብሔር ፈቃዱን እንዲፈጽም የሚሻ ሰው መሆንን እንፈልጋለን። እግዚአብሔር በታላቅ እጁ በዘመናችን ሁሉ ከእኛ ጋር እንዲሆንስ? ተገኝቶ ነው? የሚያስብል ነው። ታዲያ ይህ እንዲሆን ምን እናድርግ? ምንስ ከሕይወታችን ይወገድ?

“እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ።”
ሐዋርያት 13፥2

“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።”
ኤርምያስ 15፥19


“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ።”
ዘካርያስ 3፥7


“እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ከጠቀስኋቸው ነገሮች ቢያነጻ ለክቡር አገልግሎት የሚውል፣ የተቀደሰ፣ ለጌታው የሚጠቅም፣ ለመልካም ሥራም ሁሉ የተሰናዳ ዕቃ ይሆናል።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥21 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍6
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አያይም።”
                ዮሐንስ 8፥51




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👍3
የመጽሐፉ የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ሲሆን መግቢያው እንደሚከተለው ይላል፦

የገላትያ መልእክት መግቢያ አደገኛ መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ በዘመናችን ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ እውነተኛውን መንፈሳዊ ሕይወት በመተካት ላይ የሚገኘውን የሕግ አክራሪነት ዝንባሌ የሚያጋልጥ ነው። «በሐሰተኛ ትምህርቶች መካከል ያለ» ከማለት ይልቅ «በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ» ውስጥ ያልኩበት ዋናው ምክንያት በዚህ ዘመን ሕግ አክራሪነት የበለጠ የሰፈነው በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሆነ ነው።

በሚሊየን የሚቆጠሩ አማኞች አንዳንድ ድርጊቶችን ከመፈጸም በመቆጠባቸው ወይም አንድ የሃይማኖት መሪ በመከተላቸው ወይም የአንድ ቡድን አባል በመሆናቸው ብቻ «መንፈሳዊ» እንደሆኑ ያስባሉ። ዳሩ ግን ይህ ስሕተት መሆኑንና ወደ ትክክለኛው ሕይወት መምጣት የምንችለው ራሳችንን መንፈስ ቅዱስ እንዲቆጣጠረን በፈቀድንለት መጠን መሆኑን ጌታ በገላትያ መልእክት ውስጥ በግልፅ አሳይቶናል።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
arnet-1-cr.pdf
1.8 MB
የገላትያ መልእክት

📔ርዕስ፦ አርነት መውጣት
👤ጸሐፊ፦ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ተርጓሚ፦ጌቱ ግዛው
📑የገጽ ብዛት፦140



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
arnet-2-cr.pdf
1.7 MB
📔ርዕስ፦ አርነት መውጣት
👤ጸሐፊ፦ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ተርጓሚ፦ጌቱ ግዛው
📑የገጽ ብዛት፦140



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
arnet-3-cr.pdf
1.7 MB
📔ርዕስ፦ አርነት መውጣት
👤ጸሐፊ፦ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ተርጓሚ፦ጌቱ ግዛው
📑የገጽ ብዛት፦140



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።”
            ማቴዎስ 4፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ወዳጅ ሆይ፥ በጎ የሆነውን እንጂ ክፉን አትምሰል። በጎ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው፤ ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።”
          3ኛ ዮሐንስ 1፥11




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3
1ኛ ሳሙኤል 3


ይህ ምዕራፍ እንደሚከተለው ይጀምራል፦

“ብላቴናውም ሳሙኤል በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይገለጥም ነበር።” (ቁ. 1)

ሲደመድም፦

“እግዚአብሔርም ደግሞ በሴሎ ተገለጠ፤ እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ቃል ለሳሙኤል በሴሎ ይገለጥ ነበር። የሳሙኤልም ቃል ለእስራኤል ሁሉ ደረሰ።” (ቁ. 21)

ለመሆኑ በእነዚህ ቁጥሮች መካከል ምን ለውጥ እንመለከታለን?

1. የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ(ቁ.1) እና ለሳሙኤል የእግዚአብሔር ቃል ይገለጥ ነበር (ቁ. 21)

2. ራእይም አይገለጥም ነበር (ቁ. 1) እና እግዚአብሔር ደግሞ በሴሎ ተገለጠ (ቁ. 21)

ታዲያ ይህ ለውጥ እንዴት ተከሰተ? ከሳሙኤል ሕይወት ምን እንማራለን?

1. ምንም የሚታይ ነገር በሌለበት እግዚአብሔርን በታማኝነት ያገለግል ነበር። (ቁ.1)

2. ሳሙኤል እግዚአብሔር ባለበት ይገኛል(ቁ. 3)

3. ቅን ነበር። ኤሊ ምንም ያህል ለእግዚአብሔር ቤት የሚቀና ባይሆንም ይታዘዘው፣ ይሰማው እና እግዚአብሔር ላስቀመጠው ታላቅን የማክበር ትእዛዝ ተገዢ ነበር። (ቁ. 5-9)

4. የኤሊ ልጆች በክፋት የተሞሉ ቢሆኑም ሳሙኤል እራሱን በቅድስና የጠበቀ ሰው ነው። (ቁ. 13)

5. የእግዚአብሔርን እውነት ያለፍርሃት የሚናገር ሰው ነው። (ቁ. 18)


ውጤቱስ

1. እግዚአብሔር እና ቃሉ ተገለጠ። (ቁ. 21)

2. የሳሙኤል ቃል በምድር ላይ አይወድቅም ነበር (ቁ. 19)

3. ሕዝቡ ከእስራኤል ጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ ለእግዚአብሔር ነቢይ ለመሆን የታመነ እንደሆነ አወቀ (ቁ. 20)

ነቢይ እንደሆነ እያወጀ አልሄደም። ነገር ግን ሕዝቡ ነቢይ ለመሆን የታመነ እንደሆነ መሰከሩለት።

በዘመናችን እግዚአብሔር እንዲገለጥ እንፈልጋለን? ከፈለግን በግል ሕይወታችን ይህን የሳሙኤልን ፈለግ እንከተል!




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍154
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እኔ ለእግዚአብሔር ሕያው ሆኜ እኖር ዘንድ በሕግ በኩል ለሕግ ሞቼ ነበርና።”
             ገላትያ 2፥19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
bereket-1.pdf
1.9 MB
👉ርዕስ፦ በረከት ወይስ መርገም አንዱን ምረጥ!
✍️ደራሲ፦ ዴሬክ ፕሪንስ
📑የገጽ ብዛት፦ 200
bereket-2.pdf
2.1 MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1