ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
333 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“አቤቱ፥ ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትቅረብ፤ እንደ ቃልህም አስተዋይ አድርገኝ።”
              መዝሙር 119፥169




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት


ሮሜ 9፥6-13

ጳውሎስ ከሚያስደስተው ከምዕራፍ 8 ኀዘን ወደ ተሞላው ወደ ምዕራፍ 9 መራመዱ ግልጽ ነው፡፡ ክርስቶስን ሲያይ ተደሰተ፤ የጠፉትን እስራኤላውያንን ሲያይ ደግሞ አለቀሰ፡፡ እንደ ሙሴ (ዘጸ. 32:30-35) ስለ እስራኤል መዳን ራሱ የተረገመ ይሆን ዘንድ ፈቃደኛ ነበር:: ይሄ ጳውሎስ ምን ዓይነት ሰው ነው? ስላልዳኑት ከመንግሥተ ሰማይ መጉደልን እንኳ መረጠ (9፡3)፤ ስለጠፉትም ሲል ሲዖል መውረድን ፈቀደ፡፡

ጭብጡ እግዚአብሔር እስራኤልን የመምረጡ ጉዳይ ሲሆን፣ በመጀመሪያ የዳሰሰው የመመረጣቸውን በረከት ነው (ቁ. 4-5)። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ልጆቹ አድርጎ መርጦአቸዋል (ዘጸ. 4:22-23)። በመገናኛ ድንኳንና በቤተ መቅደስ ክብሩን አሳይቶአቸዋል (ዘጸ. 40:34-38፣ 1ኛ ነገ. 8:10-11):: ሙሴ በሲና ተራራ ላይ ያየው ክብር በእስራኤል መካከል ኖረ (ዘጸ. 24:16-17):: እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ለእስራኤል ሰጠ፣ በመጀመሪያ ለአብርሃም፣ ከዚያም ተጨማሪ ቃል ኪዳኖችን ለሙሴና ለዳዊት ሰጠ፡፡ ፖለቲካዊ፤ ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ሕይወት የሚያስተዳድር ሕግ የሰጣቸው ሲሆን፣ በታዘዙት መሠረት እንደሚባርካቸው ዋስትና ነበራቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳንና በቤተ መቅደስ እንዲያገለግሉት «የእግዚአብሔርን አገልግሎት» ሰጣቸው፡፡ የተስፋ ቃልንና አባቶችን ሰጣቸው፡፡ የዚህ ሁሉ በረከት ዓላማ ኢየሱስ ክርስቶስ በእነርሱ በኩል ወደ ዓለም እንዲመጣ ነው:: (ቁ. 5 ኢየሱስ አምላክ መሆኑን እንደሚያስረግጥ አስታውሉ፡፡) እነዚህ ሁሉ በረከቶች ለእስራኤል በነፃ የተሰጡ ሲሆን፣ ለሌሎች አሕዛብ ግን አልተሰጡም ነበር፡፡

እነዚህ ሁሉ በረከቶች ቢኖሩም እስራኤል ግን አልተሳካላትም፡፡ መሢሑ በመጣ ጊዜ እስራኤላውያን ገፉት፣ ሰቀሉትም፡፡ ጳውሎስ ራሱ አሳዳጅ ስለነበረ፣ ይህን ከእርሱ በተሻለ መልኩ የሚያውቅ አይኖርም፡፡ የእስራኤል መውደቅ የእግዚአብሔርን ቃል ይሽራልን? መልሱ «በፍጹም! የሚል ነው:: ሰዎች በቃሉ ላይ የፈለጋቸውን ቢያደርጉም፣ እግዚአብሔር ግን ታማኝ ነው»፡፡ በዚህ ስፍራ ጳውሎስ የእስራኤልን የመመረጥ ምክንያት ያብራራል፡፡

ሀ) በሥጋ የዘር ሐረግ አልነበረም (9:6-10)

በሮሜ 2፡25-29 እንዳየነው፣ በሥጋ የአብርሃም ዘር በሆኑና በመንፈስ የአብርሃም ልጆች በሆኑት መካከል ልዩነት እንዳለ አይተናል፡፡ አብርሃም ሁለት ልጆች ነበሩት፣ እስማኤልና (ከአጋር) ይስሐቅ (ከሣራ)፡፡ እስማኤል የበኩር ልጅ ስለሆነ፣ መመረጥ ነበረበት፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የመረጠው ይስሐቅን ነበረ፡፡ ይስሐቅና ርብቃ ዔሣውና ያዕቆብ የተባሉ ሁለት መንትያ ልጆች ነበሯት፡፡ የመጀመሪያ ልጅ በመሆኑ ዔሣው መመረጥ ሲገባው ፣ እግዚአብሔር የመረጠው ግን ያዕቆብን ነበረ፡፡ በተለይ ዔሣውና ያዕቆብ እንደ ይስሐቅና እስማኤል የተወለዱት ከሁለት እናቶች ሳይሆን፣ የአንድ እናት የአንድ አባት ልጆች ነበሩ፡፡ የእግዚአብሔር ምርጫ በሚታይ ነገር ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ ስለዚህ የአብርሃም የሥጋ ዘር የሆኑት እስራኤላውያን የእግዚአብሐርን ቃል ቢገፉ፣ የእግዚአብሔርን ምርጫ ከንቱ አያደርገውም፡፡

ለ) በሰው ጥረት አይደለም (9:11-13)

ሕፃናቱ ከመወለዳቸው አስቀድሞ እግዚአብሔር ያዕቆብን መረጠ፡፡ ልጆቹ በጎ ወይም ክፉ አላደረጉም፣ የእግዚአብሔር ምርጫ በባሕርያቸው ወይም በፀባያቸው ላይ የተመረኮዘ አልነበረም:: ቁጥር 13 ከሚልክያስ 1:2-3 የተወሰደ ሲሆን፣ የሚያወሳውም ስለ እስራኤልና ስለ ኤዶም ነው እንጂ ስለ ኃጢአተኛ ግለሰቦች አይደለም:: ዮሐ. 3:16 እንደሚያመለክተው እርሱ ኃጢአተኞችን ይወዳል፡፡ ምንባቡ የሚናገረው ስለ አንድ አገር መመረጥ እንጂ ስለ ግለሰቦች አይደለም፡፡ እግዚአብሔር እስራኤልን የመረጠው በሰው ጥረት ላይ ተመሥርቶ ስላልነበረ፣ አለመታዘዛቸው የእግዚአብሔርን የምርጫ ዓላማ ከንቱ አያደርገውም፡፡ ሕዝቡ ታማኞች ባይሆኑም እንኳ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፡፡


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ተስማማ፤ ገጽ 94-96




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና፥ ለራሱም የሚሞት የለም፤”
                  ሮሜ 14፥7



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#ተሰሎንቄ፤ ሐዋርያው ጳውሎስ በ2ኛ የስብከት ጕዞው ከሲላስና ከጢሞቴዎስ ጋር ወደ ተሰሎንቄ ሄደ። ከተማይቱ በግሪክ አገር የመቄዶንያ አውራጃ ዋና ከተማና ታላቅ ወደብ ስትሆን፥ ወደ ምሥራቅ በሚወስደው በታላቁ የሮም መንገድ ላይ ትገኝ ነበር። ጳውሎስ በፊልጵስዩስ ከተማ ስደት ከደረሰበት በኋላ ወደ ተሰሎንቄ ደረሰ፤ እዚያም 3 ሳምንት ያህል አስተማረ፤ ሐ.ሥ. 17፥1-10፤ 1ተሰ. 2፥2።


ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 121




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስንት ጊዜ ሐዋርያዊ ጉዞ አደረገ ተብሎ ይታመናል!
Anonymous Quiz
8%
ሀ. ሁለት
26%
ለ. አራት
18%
ሐ. ሰባት
37%
መ. ሶስት
9%
ሠ. አምስት
2%
ረ. አንድ
👍8
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እኔም፦ ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ አልሁ።”
                  ዮናስ 2፥5




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
ይህ የመዝሙር 23 ክፍል ምን ማለት እንደሆነ ሁልጊዜ አስብ ነበር። "ራሴን በዘይት ይቀባል" እግዚአብሔር የመዝሙረኛውን ጤና ይጠብቅለት ዘንድ ምሳሌያዊ አነጋገር መስሎኝ ነበር። ይህን ንጽጽር አላውቅም ነበር።

በጎች ጭንቅላታቸውን ተጠቅተው ሊሞቱ ይችላሉ። በአፍንጫቸው እንቁላሎች በመጣል በጎችን ማሰቃየት የሚወዱ አስፈሪ ትናንሽ ዝንቦች ወደ ትል ተለውጠው በጎቹን ጭንቅላታቸውን በመምታት አንዳንዴም ለሞት ይዳርጋሉ። ጆሮዎቻቸው እና ዓይኖቻቸውም በነፍሳትን ለመጠቃት የተጋለጡ ናቸው። ስለዚህ እረኛው ራሳቸውን በሙሉ በዘይት ይቀባሉ፤ ከዚያም ሰላም አለ። ያ ዘይት በጎቹን ሊያጠፋ ከሚሞክር ክፉ ነገር ይከላከላል።

በአእምሮ የምትሰቃይበት ጊዜ አለህ? አስጨናቂ ሀሳቦች ወደ አእምሮዎ ደጋግመው ይወርራሉ? ራስህን በዘይት እንዲቀባ እግዚአብሔርን ጠይቀህ ታውቃለህ? እሱ ማለቂያ የሌለው አቅርቦት አለው! የእሱ ዘይት፣ ዛሬ እና ሁል ጊዜ ልብህን፣ አእምሮህን እና አይንህን በእሱ ላይ እንድታስተካክል እና እንዲረዳህ ያደርጋል። በሸለቆው ውስጥ ሰላም አለ! ጽዋህ በበረከት ይፍሰስ ዘንድ ቸሩ አባታችን ዛሬ ራስህን በዘይት ይቀባል! እግዚአብሔር መልካም ነው ታማኝም ነው!!" አሜን ኢየሱስ ይወድሃል እኔም እወድሃለሁ በርታ!



ምንጭ፦ ከፌስቡክ መንደር (Watchman Nee)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
14👍2
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።”
             1ኛ ጴጥሮስ 5፥7



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍3
#እራሳችንን_እንመርምር



ምን እና ስለማን እያሰብን ነው? አሳባችንስ ምን እያመጣልን ነው? ደስታ ወይስ ሐዘን? ጽናት ወይስ ነውጥን?


“ባሪያዎቹ የእስራኤል ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱንም የአፉንም ፍርድ።”
1 ዜና 16፥12-13


“ስለ መንገዶችህ አሰብሁ፥ እግሬንም ወደ ምስክሮችህ መለስሁ።”
መዝሙር 119፥59

“በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤”
         ፊልጵስዩስ 4፥8

“በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም።”
ቆላስይስ 3፥2

“ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ፥ ይህንም አዘውትር።”
1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥15

“በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥8




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍74
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“የሚሰማኝ ሰው ምስጉን ነው ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ።”
               ምሳሌ 8፥34




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍53
👍91
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ከባሪያዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹሙ ወይስ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ዕውር የሆነ ማን ነው?”
            ኢሳይያስ 42፥19




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
pent-1-cr.pdf
1.8 MB
👉ርዕስ፦ ፔንታቱክ
✍️አዘጋጅ፦ መምህር ጉስታቭ ካይዘር

የመጽሐፉ ዝግጅት በጥያቄና መልስ መልኩ ነው። ፔንታቱክ አምስቱ የሙሴ መጻሕፍት ወይም ሕገ ኦሪትን የሚዳስስ መጻሕፍ ነው።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
pent-2-cr.pdf
2.3 MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1
pent-3-cr.pdf
1.4 MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
pent-4-cr.pdf
2.6 MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ።”
            ሐዋርያት 4፥31



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው



                   ክፍል - ፫


ለ. ወደ አባትህ መኝታ ወጥተሃልና አረከስኸው፤ ወደ አልጋዬም ወጣ

ሮቤል ከልቡ መዋዕል ጋር በአባቱ በያዕቆብ እየተወቀሰ እንዲኖርና ብኩርናውንም እንዲያጣ ያደረገው ከአባቱ ቁባትና ለወንድሞቹም እናት ከምትሆን ከራሔል አገልጋይ ከባላ ጋር መተኛቱ ነው (ዘፍ. 35፥22)፡፡ ያልተገባውን፥ የእርሱም ካልሆነችው፥ ያውም ደግሞ ከወንድሞቹ እናትና ከአባቱም ቁባት ጋር በመተኛቱ አባቱን በድርጊቱ አሳዘነ፡፡ የአባቱንም አልጋ በክፉ ተግባሩ አረከሰ፡፡ ባልተገባው ቦታ ተገኘ፡፡ የአባቱን ክብር አቃለለ፡፡ ያልተገባውን ስለነካ፥ የአባቱንም መኝታ ስላረከሰ የክብር አለቅነትና የኃይልም አለቅነት ክእርሱ እንዲወሰድ ተጨማሪ ምክንያት ሆነ።

ሰው ያልተገባውን ሲያደርግና ስፍራውንም ለቆ ያለቦታው ያልታዘዘውን ሲፈጽም እግዚኣብሔርን ያሳዝናል:: በድርጊቱም በዙሪያው ያሉትን ሁሉ ይጎዳል፡፡ ከዚህም የተነሳ ያልጠበቀውን፥ ያሳሰበውንና ያልገመተውን ዋጋ እንዲከፍል ይሆናል፡፡ የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ የሆነው ሳኦል ያልታዘዘውንና ያልተገባውን ድርጊቶች ደጋግሞ አደረገ፡፡ በነዚህም ድርጊቶቹ ምክንያት የእስራኤል ነገሥታት በኩር ሆኖ የነበረው ሳኦል መንግሥቱ ከእርሱ ተወስዳ ለእሴይ ልጅ ለዳዊት ተሳለፈች (1ኛ ሳሙ. 13፥8-14፤ 1ኛ ሳሙ. 15፥ 24-29)::

የባቢሎኑ ንጉሥ ናቡከደነጹር በኃይልና በዝናው እጅግ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ የማይገባውን ክብርና ሞገስ አብዝቶ ፈለገ፡፡ የሚሆነውን ነገር ሁሉ እርሱ ብቻውን ባለው ጉልበቱና ኃይሉ እንደሚያደርገው እንጂ ከእርሱ በላይ ሌላ እንዳለ ረሳ፡፡ ለእግዚእብሔር ብቻ የሆነውን የአምላክነትና የክብር ስፍራ ሊወስድ ወደደ፡፡ በዚህም ምክንያት እግዚእብሔር ከነበረው ክብርና አለቅነት አውርዶ እንደ እንስሳ ሳር እንዲበላና በዱርም ለዓመታት እንዲቀመጥ አደረገው (ዳን. 4፥28- 33)::

ያልተገባንን ማድረግ በምንጀምርበት ጊዜ እግዚአብሔር ከሚፈልገን ስፍራ ሳይሆን ለእኛ የሚመቸንንና የሚስማማንን ነገር ለማድረግ እየጣርን እንደ ሆነ ግልጽ ነው:: ይህንንም እያበዛን ከእግዚአብሔር አሳብ በምንርቅ ጊዜ በልጅነት መብታችን የተገባንን በረከት ለማጣት መንገድን ማዘጋጀት እንጀምራለን፡፡ ሮቤል በአባቱ መኝታ ላይ በመገኘቱና የእርሱም ባልሆነ አልጋ ላይ የእርሱ ካልሆነች ሴት ጋር በመተኛቱ ታላቅ በረከት ከእርሱና ከትውልዱ ተወሰደበት፡፡ ዛሬም የእነርሱ ባልሆነ አልጋ ላይ የእነርሱ ካልሆኑ ጋር የተገኙ ጸጸታቸው ከማያድናቸው ሀዘን ውስጥ የወደቁ አጅግ ብዙ ናቸው፡፡ የእድሜያቸው ገመድ በድርጊታቸው እየተያዘ ሕይወታቸው የተቀጠፈ አያሌ ናቸው፡፡

ሙሴም ሰለ ሮቤል ምርቃት ሲናገር የብኩርናውን ነገር በፍጹም አላነሳም፡፡ ብኩርናው ከእርሱ ስለ ተወሰደበት የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሙሴ በሁለት ነገሮች ብቻ መረቀው (ዘዳ. 33፥6)፡፡ የሙሴም በረከቶች ለሮቤል እንደሚከተሉት ነበሩ፦

1ኛ. በሕይወት ይኑር፤ አይሙት

2ኛ. ሰዎቹም በቁጥር ብዙ ይሁኑ


ምንም እንኳ ሮቤል በተግባሩ ሞት ተገብቶት ቢሆንም ምሕረት ለእርሱ ይሁን፥ ዘሩም ብዙ ይሁን፤ በቁጥርም ይብዛ ብሎ ሙሴ መረቀው፡፡ ብዙ የሆነው የእግዚአብሔርን ምሕረት ሙሴ በሮቤልና በልጆቹ ላይ አወጀ፡፡ የእግዚአብሔርም ምሕረት ሮቤልንና ቤቱን ጎበኘ፡፡ በብኩርናው የተገባውን ቢነጠቅም ከአግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት የተነሳ በሕይወት እንዲኖርና ዘሩም እንዲበዛ ሆነ፡፡ ሮቤል ምንም እንኳ በሰው ቁጥር እንዲበዛ ቢባልለትም በሰው ቁጥር መብዛት ኃይል ሆኖ ሳለ ለእርሱ ግን ኃይል እንዳይሆንለት ስለ ተወሰደበት አለቅነትና ኃይል ለይሁዳ፤ ብኩርናውም ለዮሴፍ ልጆች ተላለፈ፡፡

በሁለት ልብ የሚያነክሰና ልቡም እንደ ውኃ የሚዋልል ከእግዚአብሔር የሚቀበለው ብዙ የለም፡፡ ሳይሞት በሕይወት ይኖር ይሆናል፡፡ ኃይልና ጉልበት ግን ከእርሱ ይርቃል፡፡ የእግዚአብሔርም ቃል ሲመሰክር “ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው” (ያዕ. 1፥7 ) በማለት ይናገራል፡፡


ይቀጥላል...


ምንጭ፦ አበራ ጌታሁን (ዶ/ር)፤ የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው፤ ገጽ 9-11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፤ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።”
                 መሳፍንት 7፥2




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍53
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?



2ኛ ቆሮ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ስለዚህ ምክንያት ምሕረት እንደ ተሰጠን መጠን ይህ አገልግሎት ስላለን አንታክትም።
² ነገር ግን የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናልና በተንኮል አንመላለስም የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናመሰግናለን።
³ ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው።
⁴ ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።
⁵ ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።
⁶ በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና።
⁷ ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤
⁸ በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፤ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤
⁹ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤
¹⁰ የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን።
¹¹ የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና።
¹² ስለዚህ ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል።
¹³ ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤
¹⁴ ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛን ደግሞ ከኢየሱስ ጋር እንዲያስነሣን ከእናንተም ጋር እንዲያቀርበን እናውቃለንና።
¹⁵ በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን ያበዛ ዘንድ፥ ሁሉ ስለ እናንተ ነውና።
¹⁶ ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።
¹⁷-¹⁸ የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32👏1