ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
333 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።”
            1ኛ ቆሮንቶስ 9፥25



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
#እራሳችንን_እንመርምር

በዘመናችን ምን ማድረግ እንዳለብን እናውቃለን ወይስ በደመነፍስ ነው የምንኖረው? እሺ በዘመናችን ምን ማድረግ እንዳለብን ካወቅንስ፣ ላወቅነው ነገር እየታዘዝን ነው?


“እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር።”
1 ዜና 12፥32


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ንጋትም በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዓምድ ሆኖ የግብፃውያንን ሠራዊት ተመለከተ፥ የግብፃውያንንም ሠራዊት አወከ።”
             ዘጸአት 14፥24



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ አዳናችሁ።”
          ዘዳግም 7፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


2ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²-³ የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
⁴ ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።
⁵ ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥
⁶ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥
⁷ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።
⁸ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤
⁹ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል።
¹⁰ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።
¹¹ እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍72
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ወድጃቸዋለሁና የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ አደላድላቸዋለሁም፤ እመልሳቸዋለሁ፤ እኔም አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁና እንዳልጣልኋቸው ይሆናሉ።”
              ዘካርያስ 10፥6




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51👏1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት


ሮሜ 9፥1-5


1-3. ስለምን ጳውሎስ ይህን የሚያህል ታላቅ ሐዘንና የማያቋርጥ ጭንቀት ሊኖረው ቻለ? ምክንያቱም የራሱ ዘር ከሆኑት ከአይሁዳውያን ብዙዎቹ ገና በኢየሱስ ክርስቶስ አላመኑም ነበር። ምንም እንኳ፥ አይሁዳውያን ልዩና የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ ቢሆኑም፤ ባለማመናቸው ምክንያት የደኅንነትን ምቹ ጊዜ አጥተዋል። ክርስቶስ የመጣው በመጀመሪያ ለአይሁዳውያን አዳኝ በመሆን ነበር (ማቴ. 15፥24፤ ሮሜ 1፥16)፤ ነገር ግን ብዙዎቹ አልተቀበሉትም፤ ስለሆነም ወንጌል ለአረማውያን ተሰበከ። ጳውሎስ ራሱ ለአረማውያን ሐዋርያ እንዲሆን እግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ መረጠው (የሐዋ. 9፥15፤ ገላ. 2፥8)። በዚህ ሁኔታ አረማውያን በክርስቶስ ማመን ጀመሩ፤ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ከአይሁዳውያን ክርስቲያኖች ይልቅ በጣም ብዙ አረማውያን ክርስቲያኖች ነበሩ።

ጳውሎስ የተረገመ እስከሚሆን በመመኘት በጣም ታላቅ ሐዘን በልቡ ነበር። ይህም አይሁዳውያን ወንድሞቹ የሚድኑ ቢሆን፥ በአንፃሩ ማለት እርሱ የተረገመ መሆንን ይመርጥ ነበር። ጳውሎስ ለሌሎች ሰዎች የነበረው ፍቅርና የሃላፊነት ስሜት በጣም ታላቅ ከመሆኑ የተነሣ ለእነርሱ ሲል የዘላለም ደኅንነትን ቢያጣ ይወድ ነበር። በብሉይ ኪዳን ታላቁ የአይሁድ መሪ ሙሴ ተመሳሳይ ነገር ለማድረግ ራሱን አሳልፎ ሰጥቷል፤ ይኸውም የአይሁድን ሕዝብ ከእግዚአብሔር ቁጣ ለማዳን ሲል ራሱ ቢጠፋ ፈልጎ ነበር (ዘጸ. 32፥30-32)።

4. ጳውሎስ እዚህ ላይ አይሁዳውያንን የእስራኤል ሕዝብ ይላቸዋል። እስራኤል የአይሁድ ሕዝብ የመጀመሪያ ስም ነው፤ አይሁዳውያንም እስራኤላውያን ይባሉ ነበር (ሮሜ 10፥1)። እግዚአብሔር የራሱ ልዩ ሕዝብ እንዲሆኑ እስራኤልን መረጠ፤ እንደ ልጅ አድርጎም ተቀበላቸው፤ መብትም ሰጣቸው። መለኮታዊ ክብር፥ የልጅነትን ማለትም የእግዚአብሔር መገኘት ከእነርሱ ጋር ነበር። እግዚአብሔር የራሱን ቃል ኪዳን ለአይሁዳውያን ሰጥቷቸዋል። በተለይም ከመጀመሪያው አይሁዳዊ ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን ገብቶ ነበር (ዘፍ. 17፥3-8)። እግዚአብሔር የራሱንም ሕግ ለአይሁዳውያን ሰጥቷቸዋል በዚህም ሕግ የራሱን ፈቃድ ገልጦላቸው ነበር። ክርስቶስ የሚባል አዳኝ እንደሚልክላቸው የሚያስረዱ ተስፋዎችንም ሰጥቶአቸው ነበር። ልክ አብርሃም በእምነቱ ምክንያት ጻድቅ ተብሎ እንደተጠራ ሁሉ (ዘፍ. 15፥6) አይሁዳውያንም እምነታቸውን በክርስቶስ ላይ ቢያደርጉ ጻድቃን ተብለው ይጠራሉ፤ ደኅንነትንም ይቀበላሉ።
5. ክርስቶስ ራሱ ከአይሁድ አባቶች ማለትም ከአብርሃም፥ ከይስሐቅ፥ ከያዕቆብና ከይሁዳ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ አይሁዳዊ ነበር (ማቴ. 1፥1-2)። በእርግጥ እስራኤል በእግዚአብሔር የተባረከ ነገድ ነው።

እዚህ ላይ ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ አንድ ቃል መጨመር ተገድዶአል፤ ይኸውም ክርስቶስ በሁሉም ላይ አምላክ እንደሆነ ነው። ክርስቶስ አንድ ታላቅ ሰው ብቻ እንዳልሆነ ሁልጊዜ ማስታወስ ይገባናል፤ ነገር ግን ታላቅ መሪ፥ ነቢይና አስተማሪም ነበር። እንዲውም ራሱ አምላክ ነው፤ በሁሉም ላይ አምላክ ነው።



ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ ፤ ገጽ 371




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ሕዝቡም ወጥቶ የሶርያውያንን ሰፈር በዘበዘ፤ እንደ እግዚአብሔርም ቃል አንድ መስፈሪያ መልካም ዱቄት በአንድ ሰቅል፥ ሁለትም መስፈሪያ ገብስ በአንድ ሰቅል ተሸመተ።”
             2ኛ ነገሥት 7፥16



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
የመፅሐፍ_ቅዱስ_ማጥኛ_እቅድ_bible_reading.pdf
182.9 KB
መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ ዓመት ውስጥ አጥንቶ ለመጨረስ የሚረዳ የጥናት እቅድ

👉 እያንዳንዱ ወር 25 የማጥኛ ቀናቶች አሉት:: ቀሪዎቹ 5 ቀናት ምናልባትም
የተዘለለ ቀን ካለ ወይም ለክለሳ የሚሆን ነው::

👉 እያንዳንዱ ቀን ከ ብሉይ ኪዳን እና ከ አዲስ ኪዳን ሁለቱንም ያጠቃለለ ሲሆን
የመፅሐፍ ቅዱስ ውህደቱንም በሚገባ እንድንረዳ ይረዳናል::

👉ይሄ pdf የተዘጋጀው ከ JUNE - M A Y /ሰኔ-ግንቦት) ግን ከማንኛውም ወር መጀመር ይቻላል::
   

በአክሊሉ ተፈራ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ኢዮአታምም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ።”
               2 ዜና 27፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
የስሙ ትርጉም "እግዚአብሔር አምላኬ ነው" የሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
33%
ሀ. ኤልያስ
11%
ለ. ኤርምያስ
15%
ሐ. ኢሳይያስ
23%
መ. ዳንኤል
18%
ሠ. ሕዝቅኤል
3👍2😁1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“አብርሃምም በግምባሩ ወደቀ፥ ሳቀም፥ በልቡም አለ፦ የመቶ ዓመት ሰው በውኑ ልጅ ይወልዳልን? ዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለችን?”
              ዘፍጥረት 17፥17



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው



                   ክፍል - ፪


3ኛ. እንደ ውኃ የምትዋልል ነህ፤ አለቅነት ለአንተ አይሁን፤ ወደ አባትህ መኝታ ወጥተሃልና አረከሰኸው፣ ወደ አልጋዬም ወጣ

በበኩርነት መብቱ ተገብቶት የነበረውን የክብርና የኃይል አለቅነት፤ በኃይልና በብርታት በአባቱ እግር ተተክቶ ወገኑን የመምራት ሥልጣኑን ሮቤል እዚህ ስፍራ ይነጠቃል፡፡ የበኩርነቱን ስፍራ የማጣቱን ምክንያት ያዕቆብ በሁለት ነገሮች ይጠቀልለዋል፡፡ እነዚህም ሁለት ነገሮች አንዱ ባህሪውን ሌላው ደግሞ ድርጊቱን የሚያካትቱ ናቸው::

ሀ. እንደ ውኃ የምትዋልል ነህ

ውኃ ፈሳሽ ስለሆነ ቁልቁለት ወዳለበትና ወደ ተመቸው ይፈሳል፡፡ የነፋስም ጉልበት ያንቀሳቅሰዋል፡፡ ወዲያና ወዲህም ያፈሰዋል፡፡ ውኃ በፈሳሽነት ባህሪው ምክንያት የራሱ የሆነ ቅርጽ የለውም፡፡ ውኃ ሊኖረው የሚችለው ቅርጽ ውኃው የተቀመጠበት ዕቃ ቅርጽ ነው፡፡ በብርጭቆ ውስጥ ያለ ውኃ የብርጭቆውን ቅርጽ ይይዛል፡፡ በኮካ ኮላና በአንቦ ውኃ ጠርሙሶች ውስጥ የተቀመጡ ፈሳሾች የጠርሙሱን ቅርጽ ይዘው ይቀመጣሉ፡፡ ከየጠርሙሶቻቸው ውስጥ ግን ሊወጡ የመሬትን ስበት እየተከተሉ ቁልቁል ወዳለበት ለመፍስስ ይፈጥናሉ፡፡ ስለዚህ ውኃ የርሱ የሆነና የኔ ነው የሚለው፤ የሚታወቅበትና የሚጠራበትም ቅርጽ የሌለው ፈሳች ስለሆነ በቅርጽ ባህሪ ስለሚገለጥ መልክ ስለ ውኃ መናገር አይቻልም፡፡

እንደ ውኃ የሚዋልል ልብ ያለው፥ በልቡም ባለ አሳብ መቆምና መቁረጥ የማይችል ሰው ብርቱ መሪና አለቃ ሆኖ መገኘት ያስቸግረዋል፡፡ ዮሴፍን እንኳ ከጨከኑበት ወንድሞቹ እጅ ለማዳን ሮቤል የልቡን አሳብ ደብቆ በሽፋን ቋንቋ ወንድሞቹን ሲናገር ተመልክተናል (ዘፍ.37፥22-29)፡፡ እንደ ውኃ የሚዋልል ልብ ያለውን መደገፍና ማመን አይቻልም፡፡ ደግፎ የመሸከም ጉልበቱ ቶሎ ስለሚከዳው የተደገፈበትን ሁሉ ይጎዳል፡፡ የራሳቸው አሳብ የሌላቸው፤ የሚሠሩትንና የሚያደርጉትን ሁሉ ሌሎች የሚያቀርቡላቸው፤ እንደ ነገሩአቸው ብቻ እንጂ ተጨማሪን ነገር የማያሰቡ፥ የመምራት አቅም ስለማይኖራቸው የመሪነት ቦታ ላይ እንኳ ቢቀመጡ ጊዜያቸው አጭር ይሆናል፡፡ ሮብዓም የሚባል የእስራኤል ንጉሥ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ከሕዝቡ ለገጠመው ጥያቄ ምክርን ከሁለት ወገን ጠየቀ፡፡ ሁለቱም ወገኖች የሰጡት ምክር አንዱ ከሌላው አጅግ የተለያየ ሆነ፡፡ በእንዲህ ያለ ጊዜ ጥሩ መሪና የራሱም አሳብ ያለው አሰተዳዳሪ ከሁለቱም ወገኖች የተሰጡትን ምክሮች መርምሮ፤ ለምንም እንዲህ ሊለያዩ እንደቻሉ አጢኖ ዳኝነት መሰጠት ሲገባው ያልሆነውን ምክር በመሰማቱ የሕዝቡን ልብ አሳዘነ፡፡ በኋላም ከዚህ ክፉ ምክር የተነሳ የመንግሥቱ ግዛትና የእሰራኤልም ሕዝብ በእጠቃላይ ለሁለት እንዲከፈል ምክንያት ሆነ (1ኛ ነገ. 12፥1 - 15 )።

እንዲህም ባለ የልብ መዋለል ባህሪው ምክንያት የክብርና የኃይል አለቅነት የተገባው ሮቤል ብኩርናው ተወሰደበት፡፡ ብኩርናውም ለዮሴፍ ልጆመች እንደተሰጠ የእግዚአብሔር ቃል ይመሰከራል (1ኛ ዜና. 5፥1፡ ዘፍ. 48፥5)፡፡ የበኩር ልጅን በረከት ማጣት ምንነት ለሮቤል አዲስ ነገር አይመስለኝም፡፡ ወይም ደግሞ የሩቅ ዘመን ጨዋታና ትውስታ ብቻ አይደለም፡፡ አጎቱ የሆነው የአባቱ ታላቅ ወንድም እንዴት አድርጎ ብኩርናውን በትንሽ ነገርና ጥቂት ቢታገሰ ሊያልፍ በሚችል ነገር አንደ ለወጠው ለእርሱ ድብቅ ምሥጢር አይደለም (ዘፍ. 25፥27-34)፡፡ ነገር ካለፈና የሆዱ ረሃብም ከታገሰለት በኋሳ ዔሳው ብኩርናውን በብዙ እንባም ቢፈልገው መልሶ ሊያገኘው አልቻለም (ዕብ. 12፥16-17)፡፡ ሊመለስ በማይችል ነገር ላይ እንባና ጩኸት ትርፉ ጉዳት ብቻ በመሆኑ የዔሳውም ጸጸት ዘመኑን ሁሉ ሊከተለው ኖረ።

ዲቦራና ባርቅ በዝማሬ ቅኔያቸው ስለ እስራኤል ነገዶች በተቀኙ ጊዜ ስለ ሮቤል ልብ መዋለልና እንደ ውኃ መፍሰስ እንዲህ በማለት ገለጹ፦ “በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ብዙ የልብ ማመንታት ነበረ...በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ” (መሳ. 5፥15-16)::


ይቀጥላል...


ምንጭ፦ አበራ ጌታሁን (ዶ/ር)፤ የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው፤ ገጽ 6-8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👎1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ስምዖንም መልሶ፦ አቤቱ፥ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ አለው።”
               ሉቃስ 5፥5




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3
#እራሳችንን_እንመርምር


የነገሮች ቅለት እና ክብደት የሚወሰነው እግዚአብሔር ፈቅዷል ወይስ አልፈቀደም? ወይም ወዷል ወይስ አልወደደም በሚለው እንደሆነ በሚገባ የተረዳን ይመስላችኋል? ስንት ጊዜ በነገሮች ፊት ቆመን የእግዚአብሔርን ፈቃድ አጣርጠን በዚያ ከመንቀሳቀስ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር ላይ በማመጽ ተንቀሳቀስን? ብቻ እግዚአብሔር ይውደደን!


"እግዚአብሔርስ ከወደደን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው።"
ዘኍልቁ 14፥8-9



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔርም ለሙሴ እንደ ነገረው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደ ክፍላቸውና እንደ ነገዳቸው ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከሰልፍ ዐረፈች።”
            ኢያሱ 11፥23




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍4
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት



ሮሜ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም። እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና፤ የአብርሃምም ዘር ስለሆኑ ሁላቸው ልጆች አይደሉም፥
⁷ ነገር ግን፦ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል ተባለ።
⁸ ይህም፥ የተስፋ ቃል ልጆች ዘር ሆነው ይቆጠራሉ እንጂ እነዚህ የሥጋ ልጆች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም ማለት ነው።
⁹ ይህ፦ በዚህ ጊዜ እመጣለሁ ለሳራም ልጅ ይሆንላታል የሚል የተስፋ ቃል ነውና።
¹⁰ ይህ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ርብቃ ደግሞ ከአንዱ ከአባታችን ከይስሐቅ በፀነሰች ጊዜ፥
¹¹ ልጆቹ ገና ሳይወለዱ፥ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ፥ ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ፥
¹² ለእርስዋ፦ ታላቁ ለታናሹ ይገዛል ተባለላት።
¹³ ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን ጠላሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።


ሮሜ 9 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ተሽሮአል ማለት አይደለም፤ ከእስራኤል የተወለደ ሁሉ እስራኤላዊ አይደለምና።
⁷ ከአብርሃም ዘርም ስለሆኑ፣ ሁሉም ልጆቹ አይደሉም፤ ይልቁንስ፣ “ትውልድህ በይሥሐቅ በኩል ይጠራልሃል” እንደ ተባለው ነው።
⁸ ይህም ማለት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት የሥጋ ልጆች አይደሉም፤ ነገር ግን የአብርሃም ልጆች የተባሉት የተስፋው ልጆች ናቸው።
⁹ “ጊዜው ሲደርስ እመለሳለሁ፤ ሳራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች” ተብሎ ተስፋው ተሰጥቶአልና።
¹⁰ ይህም ብቻ ሳይሆን፣ የርብቃ ልጆች አንድ አባት አላቸው፤ እርሱም አባታችን ይሥሐቅ ነው።
¹¹ መንትዮቹ ገና ሳይወለዱ፣ ወይም በጎም ሆነ ክፉ ሳያደርጉ፣ የእግዚአብሔር ሐሳብ በምርጫ ይጸና ዘንድ፣
¹² በሥራ ሳይሆን ከጠሪው በመሆኑ፣ “ታላቁ ታናሹን ያገለግላል” ተብሎ ተነገራት።
¹³ ይህም፣ “ያዕቆብን ወደድሁ፤ ዔሳውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።


ሮሜ 9 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ይህ ከሆነ፥ ታዲያ እግዚአብሔር ለአይሁድ ሕዝብ የሰጠውን ተስፋ ሽሮታል ማለት ነው? ይህን ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ከእሥራኤል ዘር የተወለዱ ሁሉ እሥራኤላውያን ናቸው ማለት አይደለም።
⁷ በልደተ ሥጋ ከአብርሃም ዘር ስለተገኙ ብቻ የአብርሃም ልጆች ናቸው ማለት አይቻልም። አብርሃም ሌሎች ልጆች እንዳሉት ቢታወቅም፥ ተስፋ የተነገረለት ለልጁ ለይስሐቅና ከእርሱም ለሚገኘው ልጅ ለያዕቆብ ዘር መሆኑ በቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፏል።
⁸ ይህም ማለት በሥጋ ከአብርሃም ተወለዱና ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው የሚቆጠሩት፥ እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባለት የተስፋ ቃል መሠረት የተወለዱለት ብቻ ናቸው።
⁹ እግዚአብሔር ፥ «የዛሬ ዓመት መጥቼ እጐበኛችኋለሁ። ሚስትህ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች» የሚል የተስፋ ቃል ለአብርሃም ሰጥቶት ነበር።
¹⁰ ይህም ብቻ አይደለም። ርብቃ ከአባታችን ከይስሐቅ መንታ ልጆች በፀነሰች ጊዜ፥
¹¹ ልጆቹ ተወልደው አድገው ክፉ ወይም ደግ ከመሥራ ታቸው በፊት ገና በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ እግዚአብሔር ለርብቃ፥
¹² «ታላቁ ለታናሹ ይገዛል» ብሏታል። ይህም
¹³ «ያዕቆብን ወደድኩ፤ ዔሳውን ግን ጠላሁ» ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈው ቃል እግዚአብሔር የሰውን ድርጊት ተከትሎ ሳይሆን፥ ማንኛውንም ነገር በራሱ የምርጫ እቅድ የሚሠራ መሆኑን ያስገነዝበናል።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
ከሚከተሉት መካከል የአብርሃም ልጅ የሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
39%
ሀ. ይስሐቅ
0%
ለ. ምድያም
1%
ሐ. እስማኤል
15%
መ. ሀ እና ለ
44%
ሠ. ሁሉም
2
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።”
                  ዮሐንስ 7፥37




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍4
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?



ሐዋርያት 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በዚያም ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን ጫነባቸው።
² የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።
³ አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ ጴጥሮስን ደግሞ ያዘው። የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ።
⁴ በያዘውም ጊዜ ወደ ወኅኒ አገባው ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ያወጣው ዘንድ አስቦ እያንዳንዱ አራት ወታደሮች ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍራ ክፍል አሳልፎ ሰጠው።
⁵ ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቆ ይደረግ ነበር።
⁶ ሄሮድስም ሊያወጣው ባሰበ ጊዜ፥ በዚያች ሌሊት ጴጥሮስ በሁለት ሰንሰለት ታስሮ ከሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባቂዎችም በደጁ ፊት ሆነው ወኅኒውን ይጠብቁ ነበር።
⁷ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና፦ ፈጥነህ ተነሣ አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ።
⁸ መልአኩም፦ ታጠቅና ጫማህን አግባ አለው፥ እንዲሁም አደረገ።
⁹ ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም።
¹⁰ የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው፤ ወጥተውም አንዲት ስላች አለፉ ወዲያውም መልአኩ ከእርሱ ተለየ።
¹¹ ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ፦ ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ አለ።
¹² ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ።
¹³ ጴጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሉአት አንዲት ገረድ ትሰማ ዘንድ ቀረበች፤
¹⁴ የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ ደጁን አልከፈተችም፥ ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ጴጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች።
¹⁵ እነርሱም፦ አብደሻል አሉአት። እርስዋ ግን እንዲሁ እንደ ሆነ ታስረግጥ ነበር። እነርሱም፦ መልአኩ ነው አሉ።
¹⁶ ጴጥሮስ ግን ማንኳኳቱን አዘወተረ፤ ከፍተውም አዩትና ተገረሙ።
¹⁷ ግን ዝም እንዲሉ በእጁ ጠቅሶ ጌታ ከወኅኒ እንዴት እንዳወጣው ተረከላቸውና፦ ይህን ለያዕቆብና ለወንድሞች ንገሩ አላቸው። ወጥቶም ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ናቡከደነፆርም መልሶ፦ መልአኩን የላከ፥ ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ።”
              ዳንኤል 3፥28




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1