ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
333 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ቅዱሳት መጻሕፍት
https://www.youtube.com/watch?v=KW3rUHsm5Q8 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📹አጭር እና ግልጽ የሆነ የትንቢተ ኤርምያስ ዳሰሳ።
የቪድዮ ርዝመት፦ 8:49


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።”
               ዮሐንስ 4፥10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


መዝሙር 29
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የአምላክ ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥ ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ።
² የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
³ የእግዚአብሔር ድምፅ በውኆች ላይ፥ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥ እግዚአብሔር በብዙ ውኆች ላይ።
⁴ የእግዚአብሔር ድምፅ በኃይል ነው፤ የእግዚአብሔር ድምፅ በታላቅ ክብር ነው።
⁵ የእግዚአብር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።
⁶ እንደ ጥጃ ሊባኖስን፥ አንድ ቀን እንዳለው አውሬ ልጅ ስርዮንን ያዘልላቸዋል።
⁷ የእግዚአብሔር ድምፅ የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
⁸ የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፥ እግዚአብሔር የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
⁹ የእግዚአብሔር ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል፥ ጫካዎቹንም ይገልጣል ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
¹⁰ እግዚአብሔር የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።
¹¹ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍3
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤”
         2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥12




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መክፈቻ.pdf
1.7 MB
✍️ ርዕስ፦ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መክፈቻ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?”
          ኢሳይያስ 40፥27




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍52😁1
የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው



ክፍል - ፩



፩. ሮቤል

ዘፍ. 49፥3-4፤ ዘዳ. 33፥6

ሮቤል የያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ነው፡፡ ሮቤል የተወለደው ከልያ ሲሆን እግዚእብሔር መከራዋን እንዳየላትና ከዚህም በኋላ ያዕቆብ ይወደኛል ስትል ስሙን ሮቤል ብላ ጠራችው (ዘፍ. 29፥31-32)። ያዕቆብ ድብቅ ያልሆነ በገሃድ የመውደድ ፍቅሩን የገለጸው ለራሔል ስለ ነበር ልያ አስቀድማ ልጅ በመውለዷ የያዕቆብን የፍቅር ልብ እንደምታገኝ በመገመቷ የማህጸኗን መክፈቻና የመጀመሪያዋን ወንድ ልጅ ስም ከዚህ የተነሳ ሰየመችው፡፡ የስሙም ትርጓሜ እነሆ ወንድ ልጅ ማለት ነው፡፡ ወንድ ልጅ ሰጥቼሃለሁ፣ አንተም የፍቅር ልብህን አትንፈገኝ በማለት ልያ ለያዕቆብ ፍቅር መለመኛ እንዲሆናት ሮቤል መጠሪያውን አገኘ፡፡

ሮቤል ዮሴፍን ወንድሞቹ ሊያጠፉት በተነሱ ጊዜ ደም እንዳያፈሱ ነገር ግን በጉድጓድ እንዲጥሉት አደረገ (ዘፍ. 37፥22 )። በኋላም ወንድሞቹ ከጉድጓድ አውጥተው ሲሸጡት በአጠገባቸው እንዳልነበረና ከወንድሞቹም ተለይቶ ብቻውን ወደ ጉድጓዱ በተመለሰ ጊዜ ዮሴፍን እንዳጣው የእግዚአብሔር ቃል ይመስክራል (ዘፍ. 37፥29 ) ፡፡ ሮቤል በልቡ ያለውን ሰውሮ ሌሎቹ ከሚያደርጉት ጋር ይሄድ ስለ ነበር በኋላ በእንባ ቢጮህም ዮሴፍን ማዳን አልቻለም፡፡ እውነት ሊያስከፍል የሚችለውን ዋጋ ፊት ለፊት ከመክፈል ተሰውሮ በድብቅ በልቡ ያሰበውን መፈጸምን መረጠ፡፡ ብቻውንም በስውር ዮሴፍን አድናለሁ ብሎ ላሰበው ድርጊቱ ግን ሰዓት ስላለፈበት ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ እንደሚሉት እንደ አገራችን ተረት ሆነበት፡፡ የወንድሞቹንም ክፋት ልክ ባለ ማወቁ ሊያደርግ ባስበው የልቡ ውሳኔ ላይ ፀሐይ ጠለቀችበት፡፡ ጊዜም አመለጠው፡፡

ብዙ ጊዜ ስናመነታ፤ ቀን ስላለ በሌላ ጊዜ እደርሳለሁ እያልን በምናስተላልፋቸው ብዙ ነገሮቻችን ላይ ሳናስብና ሳናውቅ ጊዜ አምልጦን ሁኔታዎችም ተለውጠው ራሳችንን እናገኛለን፡፡ በዚያን ሰዓት የጸጸት እንባ፣ የምሬት ጩኸት፣ የፀጉር መንጨት፤ የደረት መድቃት ባዶ እሪታ ብቻ ይሆናል፡፡ ቀን ሳለ ወይም ጊዜ ሳለ ማድረግ የሚገባንን ለማድረግ የታጠቅንና የቆረጥን ልንሆን ያስፈልጋል (ዮሐ.9፥4)::

ያዕቆብ ስለ ሮቤል ሲናገር እንዲህ አለ (ዘፍ. 49፥4)፦

1ኛ. ሮቤል አንተ የበኩር ልጄና ኃይሌ፥ የጉብዝናዬም መጀመሪያ ነህ

እግዚእብሔር ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና በኋላም ለያዕቆብ በሰጠው የኪዳን ሐረግ የተስፋውን ቃል ለመሙላት ከያዕቆብ ልጆች ሮቤል በኩር ሆኖ ተወለደ፡፡ የነገድ መጀመሪያ፤ የበረከት መጀመሪያ፤ የአባቱ መተኪያና የአባቱ መጠሪያ እንዲሆን እነሆ ወንድ ልጅ ተወለደ፡፡ የበኩር ልጅ የአባትንና የእናትን ፍቅር ያለምንም ተሻሚ የሚጠግብ ልጅ ነው:: ከዚህም የተነሳ ያዕቆብ እነዚያን ቀናቶች እያስታወሰ ወንድ ልጅ ተወለደልህ የተባለለትን ቀን እያሰበ ኃይሌና የጉብዝናዬ መጀመሪያ ነህ እያለ የትዝታውን ማህደር ይፈትሻል፡፡ ከሮቤል መወለድ ጋር የያዕቆብ ትዝታ እርሱን ተክቶ በአብርሃም የተጀመረውን አዲስ ወገን የሚቀጥል ተኪ ሰው መገኘቱን አይቶ ልቡ በደስታ ይፍለቀለቅ እንደ ነበር መገመት አያስቸግርም፡፡ ትውልድን መተካት እንኳን በሰው ዘር በእንስሳትም ያለ ትልቅ የተፈጥሮ ግፈት ስለሆነ የመጀመሪያ የበኩር ልጁን ማግኘቱ የትውልድ ሐረጉ የመቀጠል ምልክቱ ስለሆነ ለደስታው መጠን አልነበረውም ነበር፡፡

2ኛ. የክብር አለቃና የኃይል አለቃ

የበኩር ልጅ በአባቱ እግር ተተክቶ አባቱ በነበረው ክብርና ኃይል የሚንቀሳቀስ፤ የሚገባና የሚወጣም ነው:: መጀመሪያ መወለድ በሚስጠው እድል ተጠቃሚ ስለሆነ የበኩር ልጅ የቤተስብ ድርሻው ሁልጊዜ ትልቅ ነው፡፡ በተለይ አባቱ በውርስ ሊያስተላልፍ የሚችለው የክብርና የኃይል ስፍራ ካለ በዚያ ስፍራ የመጀመሪያው ተተኪ ሆኖ የሚቀርበው የበኩር ልጅ ነው፡፡ በቀድሞው ዘመንና አሁንም በምድር ላይ የቀሩት ጥቂት ነገሥታት የመግዛት ዘመናቸው ሲያበቃ የግዛት በትራቸውንና ዙፋናቸውን የሚያስረክቡት ለመጀመሪያ ልጃቸው ነው::

ይህ ታላቅ መታደል ግን ለሁሉም የበኩር ልጅ በታሪክ ውስጥ ተከናውኗል ባይባልም የመጀመሪያ ልጆች ለዚህ መታደም አስቀድመው መታስባቸው የማይቀር የብኩርና ክብራቸው ነው::



ይቀጥላል...


ምንጭ፦ አበራ ጌታሁን (ዶ/ር)፤ የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው፤ ገጽ 4-6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍43
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፥ ከጨካኞችም ጡጫ እቤዥሃለሁ።”
             ኤርምያስ 15፥21




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍5
ሙሴ የሰራውን የናስ እባብ የሰባበረው ማን ነው?
Anonymous Quiz
63%
ሀ. አሮን
4%
ለ. ዳዊት
4%
ሐ. ሰሎሞን
29%
መ. ሕዝቅያስ
8👍3👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።”
            1ኛ ቆሮንቶስ 9፥25



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
#እራሳችንን_እንመርምር

በዘመናችን ምን ማድረግ እንዳለብን እናውቃለን ወይስ በደመነፍስ ነው የምንኖረው? እሺ በዘመናችን ምን ማድረግ እንዳለብን ካወቅንስ፣ ላወቅነው ነገር እየታዘዝን ነው?


“እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር።”
1 ዜና 12፥32


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ንጋትም በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዓምድ ሆኖ የግብፃውያንን ሠራዊት ተመለከተ፥ የግብፃውያንንም ሠራዊት አወከ።”
             ዘጸአት 14፥24



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ አዳናችሁ።”
          ዘዳግም 7፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


2ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²-³ የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
⁴ ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።
⁵ ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥
⁶ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥
⁷ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።
⁸ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤
⁹ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል።
¹⁰ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።
¹¹ እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍72
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ወድጃቸዋለሁና የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ አደላድላቸዋለሁም፤ እመልሳቸዋለሁ፤ እኔም አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁና እንዳልጣልኋቸው ይሆናሉ።”
              ዘካርያስ 10፥6




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51👏1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት


ሮሜ 9፥1-5


1-3. ስለምን ጳውሎስ ይህን የሚያህል ታላቅ ሐዘንና የማያቋርጥ ጭንቀት ሊኖረው ቻለ? ምክንያቱም የራሱ ዘር ከሆኑት ከአይሁዳውያን ብዙዎቹ ገና በኢየሱስ ክርስቶስ አላመኑም ነበር። ምንም እንኳ፥ አይሁዳውያን ልዩና የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ ቢሆኑም፤ ባለማመናቸው ምክንያት የደኅንነትን ምቹ ጊዜ አጥተዋል። ክርስቶስ የመጣው በመጀመሪያ ለአይሁዳውያን አዳኝ በመሆን ነበር (ማቴ. 15፥24፤ ሮሜ 1፥16)፤ ነገር ግን ብዙዎቹ አልተቀበሉትም፤ ስለሆነም ወንጌል ለአረማውያን ተሰበከ። ጳውሎስ ራሱ ለአረማውያን ሐዋርያ እንዲሆን እግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ መረጠው (የሐዋ. 9፥15፤ ገላ. 2፥8)። በዚህ ሁኔታ አረማውያን በክርስቶስ ማመን ጀመሩ፤ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ከአይሁዳውያን ክርስቲያኖች ይልቅ በጣም ብዙ አረማውያን ክርስቲያኖች ነበሩ።

ጳውሎስ የተረገመ እስከሚሆን በመመኘት በጣም ታላቅ ሐዘን በልቡ ነበር። ይህም አይሁዳውያን ወንድሞቹ የሚድኑ ቢሆን፥ በአንፃሩ ማለት እርሱ የተረገመ መሆንን ይመርጥ ነበር። ጳውሎስ ለሌሎች ሰዎች የነበረው ፍቅርና የሃላፊነት ስሜት በጣም ታላቅ ከመሆኑ የተነሣ ለእነርሱ ሲል የዘላለም ደኅንነትን ቢያጣ ይወድ ነበር። በብሉይ ኪዳን ታላቁ የአይሁድ መሪ ሙሴ ተመሳሳይ ነገር ለማድረግ ራሱን አሳልፎ ሰጥቷል፤ ይኸውም የአይሁድን ሕዝብ ከእግዚአብሔር ቁጣ ለማዳን ሲል ራሱ ቢጠፋ ፈልጎ ነበር (ዘጸ. 32፥30-32)።

4. ጳውሎስ እዚህ ላይ አይሁዳውያንን የእስራኤል ሕዝብ ይላቸዋል። እስራኤል የአይሁድ ሕዝብ የመጀመሪያ ስም ነው፤ አይሁዳውያንም እስራኤላውያን ይባሉ ነበር (ሮሜ 10፥1)። እግዚአብሔር የራሱ ልዩ ሕዝብ እንዲሆኑ እስራኤልን መረጠ፤ እንደ ልጅ አድርጎም ተቀበላቸው፤ መብትም ሰጣቸው። መለኮታዊ ክብር፥ የልጅነትን ማለትም የእግዚአብሔር መገኘት ከእነርሱ ጋር ነበር። እግዚአብሔር የራሱን ቃል ኪዳን ለአይሁዳውያን ሰጥቷቸዋል። በተለይም ከመጀመሪያው አይሁዳዊ ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን ገብቶ ነበር (ዘፍ. 17፥3-8)። እግዚአብሔር የራሱንም ሕግ ለአይሁዳውያን ሰጥቷቸዋል በዚህም ሕግ የራሱን ፈቃድ ገልጦላቸው ነበር። ክርስቶስ የሚባል አዳኝ እንደሚልክላቸው የሚያስረዱ ተስፋዎችንም ሰጥቶአቸው ነበር። ልክ አብርሃም በእምነቱ ምክንያት ጻድቅ ተብሎ እንደተጠራ ሁሉ (ዘፍ. 15፥6) አይሁዳውያንም እምነታቸውን በክርስቶስ ላይ ቢያደርጉ ጻድቃን ተብለው ይጠራሉ፤ ደኅንነትንም ይቀበላሉ።
5. ክርስቶስ ራሱ ከአይሁድ አባቶች ማለትም ከአብርሃም፥ ከይስሐቅ፥ ከያዕቆብና ከይሁዳ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ አይሁዳዊ ነበር (ማቴ. 1፥1-2)። በእርግጥ እስራኤል በእግዚአብሔር የተባረከ ነገድ ነው።

እዚህ ላይ ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ አንድ ቃል መጨመር ተገድዶአል፤ ይኸውም ክርስቶስ በሁሉም ላይ አምላክ እንደሆነ ነው። ክርስቶስ አንድ ታላቅ ሰው ብቻ እንዳልሆነ ሁልጊዜ ማስታወስ ይገባናል፤ ነገር ግን ታላቅ መሪ፥ ነቢይና አስተማሪም ነበር። እንዲውም ራሱ አምላክ ነው፤ በሁሉም ላይ አምላክ ነው።



ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ ፤ ገጽ 371




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ሕዝቡም ወጥቶ የሶርያውያንን ሰፈር በዘበዘ፤ እንደ እግዚአብሔርም ቃል አንድ መስፈሪያ መልካም ዱቄት በአንድ ሰቅል፥ ሁለትም መስፈሪያ ገብስ በአንድ ሰቅል ተሸመተ።”
             2ኛ ነገሥት 7፥16



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
የመፅሐፍ_ቅዱስ_ማጥኛ_እቅድ_bible_reading.pdf
182.9 KB
መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ ዓመት ውስጥ አጥንቶ ለመጨረስ የሚረዳ የጥናት እቅድ

👉 እያንዳንዱ ወር 25 የማጥኛ ቀናቶች አሉት:: ቀሪዎቹ 5 ቀናት ምናልባትም
የተዘለለ ቀን ካለ ወይም ለክለሳ የሚሆን ነው::

👉 እያንዳንዱ ቀን ከ ብሉይ ኪዳን እና ከ አዲስ ኪዳን ሁለቱንም ያጠቃለለ ሲሆን
የመፅሐፍ ቅዱስ ውህደቱንም በሚገባ እንድንረዳ ይረዳናል::

👉ይሄ pdf የተዘጋጀው ከ JUNE - M A Y /ሰኔ-ግንቦት) ግን ከማንኛውም ወር መጀመር ይቻላል::
   

በአክሊሉ ተፈራ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ኢዮአታምም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ።”
               2 ዜና 27፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
የስሙ ትርጉም "እግዚአብሔር አምላኬ ነው" የሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
33%
ሀ. ኤልያስ
11%
ለ. ኤርምያስ
15%
ሐ. ኢሳይያስ
23%
መ. ዳንኤል
18%
ሠ. ሕዝቅኤል
3👍2😁1