ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
333 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#እራሳችንን_እንመርምር

የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ለመሆን ከብዶን እና አቅም አጥተን ይሆን? ይህ ለምን ተከሰተ? መፍትሄውስ ምን ይሆን?


“ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።”
ሐዋርያት 1፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍4
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፤ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጥተዋል፤ ንጉሣቸውም በፊታቸው አልፎአል፥ እግዚአብሔርም በራሳቸው ላይ ነው።”
             ሚክያስ 2፥13




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት


ሮሜ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለብኝ ስል በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል።
³ በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምሁ እንድሆን እጸልይ ነበርና።
⁴ እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፤
⁵ አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።


ሮሜ 9 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በክርስቶስ ሆኜ እውነት እናገራለሁ፤ አልዋሽም፤ ኅሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል።
² ታላቅ ሐዘንና የማያቋርጥ ጭንቀት በልቤ አለ።
³ ለወገኖቼ ስል ስለ ወንድሞቼ እኔ ራሴ የተረገምሁና ከክርስቶስም ተለይቼ የተጣልሁ እንድሆን እንኳ እወድ ነበር፤
⁴ እነርሱም የእስራኤል ሕዝብ ናቸው፤ ልጅ መሆን፣ መለኮታዊ ክብር፣ ኪዳን፣ ሕግን መቀበል፣ የቤተ መቅደስ ሥርዐትና ተስፋ የእነርሱ ናቸውና።
⁵ አባቶችም የእነርሱ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የትውልድ ሐረጉ የሚቈጠረው ከእነርሱ ነው፤ እርሱም፣ ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ ነው፤ አሜን።


ሮሜ 9 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በክርስቶስ ውስጥ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ። እንደማልዋሽም መንፈስ ቅዱስ ለሕሊናዬ ያረጋግጥልኛል። የሥጋ ዘመዶቼ ስለሆኑት ስለወንድሞቼ ስለእሥራኤላውያን ሳስብ
²¯³ ልቦናዬ ከባድ ኀዘን ሳይሰማው ፥ መንፈሴም ክፉኛ ሳይጨነቅ ውሎ ያደረበት ቀን የለም። እነርሱ ይዳኑልኝ እንጂ ከክርስቶስ ተለይቼ ኵነኔ እንኳ ቢደርስብኝ ቅር አይለኝም።
⁴ እነርሱ እግዚአብሔር ከዓለም ሕዝብ ለይቶ የመረጣቸው ፥ ልጆቹ ያደረጋቸው፥ ክብሩን የገለጠላቸው፥ ቃል ኪዳን የገባላቸው፥ ሕጉን የሰጣቸው፥ የአምልኮን ሥርዓት ያስተማራቸው የተስፋውንም ቃል የሰጣቸውና
⁵ የአሥራ ሁለቱ ነገደ እሥራኤል አባቶች ዝርያ ናቸው። ከሁሉ በላይ የሆነውና ለዘላለም የተባረከው አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ የተወለደው ከእነርሱው ወገን ነው። እርሱም ለዘላለም የተመሰገነ ነው፤ አሜን!



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ለዳንኤል ነገር ተገለጠለት፤ ነገሩም እውነት ነበረ፥ እርሱም ታላቅ ጦርነት ነው፤ ነገሩንም አስተዋለ፥ በራእዩም ውስጥ ማስተዋል ተሰጠው።”
                 ዳንኤል 10፥1




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#ቆጵሮስ

በሜዲቴራኒያን በስተምሥራቅ የሚገኝ ደሴት። ብዙ አይሁድ ይኖሩበት ነበር። በርናባስ ቆጵሮሳዊ ነበር፤ ሐ.ሥ. 4፥36። የቆጵሮስ ሰዎች ወደ አንጾኪያ ሲሄዱ ወንጌልን ለግሪክ ሰዎች ሰበኩ፤ ሐ.ሥ. 11፥19:20። ጳውሎስ፥ በርናባስና ማርቆስ ደሴቱን ጐብኝተው ወንጌል ሰበኩ፤ ሐ.ሥ. 13፥4-13። በኋላም በርናባስና ማርቆስ እንደገና ወደ ቆጵሮስ ሄዱ፤ ሐ.ሥ. 15፥39።



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 101




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
ቅዱሳት መጻሕፍት
https://www.youtube.com/watch?v=KW3rUHsm5Q8 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📹አጭር እና ግልጽ የሆነ የትንቢተ ኤርምያስ ዳሰሳ።
የቪድዮ ርዝመት፦ 8:49


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።”
               ዮሐንስ 4፥10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


መዝሙር 29
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የአምላክ ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥ ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ።
² የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
³ የእግዚአብሔር ድምፅ በውኆች ላይ፥ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥ እግዚአብሔር በብዙ ውኆች ላይ።
⁴ የእግዚአብሔር ድምፅ በኃይል ነው፤ የእግዚአብሔር ድምፅ በታላቅ ክብር ነው።
⁵ የእግዚአብር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።
⁶ እንደ ጥጃ ሊባኖስን፥ አንድ ቀን እንዳለው አውሬ ልጅ ስርዮንን ያዘልላቸዋል።
⁷ የእግዚአብሔር ድምፅ የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
⁸ የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፥ እግዚአብሔር የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
⁹ የእግዚአብሔር ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል፥ ጫካዎቹንም ይገልጣል ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
¹⁰ እግዚአብሔር የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።
¹¹ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍3
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤”
         2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥12




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መክፈቻ.pdf
1.7 MB
✍️ ርዕስ፦ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መክፈቻ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?”
          ኢሳይያስ 40፥27




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍52😁1
የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው



ክፍል - ፩



፩. ሮቤል

ዘፍ. 49፥3-4፤ ዘዳ. 33፥6

ሮቤል የያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ነው፡፡ ሮቤል የተወለደው ከልያ ሲሆን እግዚእብሔር መከራዋን እንዳየላትና ከዚህም በኋላ ያዕቆብ ይወደኛል ስትል ስሙን ሮቤል ብላ ጠራችው (ዘፍ. 29፥31-32)። ያዕቆብ ድብቅ ያልሆነ በገሃድ የመውደድ ፍቅሩን የገለጸው ለራሔል ስለ ነበር ልያ አስቀድማ ልጅ በመውለዷ የያዕቆብን የፍቅር ልብ እንደምታገኝ በመገመቷ የማህጸኗን መክፈቻና የመጀመሪያዋን ወንድ ልጅ ስም ከዚህ የተነሳ ሰየመችው፡፡ የስሙም ትርጓሜ እነሆ ወንድ ልጅ ማለት ነው፡፡ ወንድ ልጅ ሰጥቼሃለሁ፣ አንተም የፍቅር ልብህን አትንፈገኝ በማለት ልያ ለያዕቆብ ፍቅር መለመኛ እንዲሆናት ሮቤል መጠሪያውን አገኘ፡፡

ሮቤል ዮሴፍን ወንድሞቹ ሊያጠፉት በተነሱ ጊዜ ደም እንዳያፈሱ ነገር ግን በጉድጓድ እንዲጥሉት አደረገ (ዘፍ. 37፥22 )። በኋላም ወንድሞቹ ከጉድጓድ አውጥተው ሲሸጡት በአጠገባቸው እንዳልነበረና ከወንድሞቹም ተለይቶ ብቻውን ወደ ጉድጓዱ በተመለሰ ጊዜ ዮሴፍን እንዳጣው የእግዚአብሔር ቃል ይመስክራል (ዘፍ. 37፥29 ) ፡፡ ሮቤል በልቡ ያለውን ሰውሮ ሌሎቹ ከሚያደርጉት ጋር ይሄድ ስለ ነበር በኋላ በእንባ ቢጮህም ዮሴፍን ማዳን አልቻለም፡፡ እውነት ሊያስከፍል የሚችለውን ዋጋ ፊት ለፊት ከመክፈል ተሰውሮ በድብቅ በልቡ ያሰበውን መፈጸምን መረጠ፡፡ ብቻውንም በስውር ዮሴፍን አድናለሁ ብሎ ላሰበው ድርጊቱ ግን ሰዓት ስላለፈበት ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ እንደሚሉት እንደ አገራችን ተረት ሆነበት፡፡ የወንድሞቹንም ክፋት ልክ ባለ ማወቁ ሊያደርግ ባስበው የልቡ ውሳኔ ላይ ፀሐይ ጠለቀችበት፡፡ ጊዜም አመለጠው፡፡

ብዙ ጊዜ ስናመነታ፤ ቀን ስላለ በሌላ ጊዜ እደርሳለሁ እያልን በምናስተላልፋቸው ብዙ ነገሮቻችን ላይ ሳናስብና ሳናውቅ ጊዜ አምልጦን ሁኔታዎችም ተለውጠው ራሳችንን እናገኛለን፡፡ በዚያን ሰዓት የጸጸት እንባ፣ የምሬት ጩኸት፣ የፀጉር መንጨት፤ የደረት መድቃት ባዶ እሪታ ብቻ ይሆናል፡፡ ቀን ሳለ ወይም ጊዜ ሳለ ማድረግ የሚገባንን ለማድረግ የታጠቅንና የቆረጥን ልንሆን ያስፈልጋል (ዮሐ.9፥4)::

ያዕቆብ ስለ ሮቤል ሲናገር እንዲህ አለ (ዘፍ. 49፥4)፦

1ኛ. ሮቤል አንተ የበኩር ልጄና ኃይሌ፥ የጉብዝናዬም መጀመሪያ ነህ

እግዚእብሔር ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና በኋላም ለያዕቆብ በሰጠው የኪዳን ሐረግ የተስፋውን ቃል ለመሙላት ከያዕቆብ ልጆች ሮቤል በኩር ሆኖ ተወለደ፡፡ የነገድ መጀመሪያ፤ የበረከት መጀመሪያ፤ የአባቱ መተኪያና የአባቱ መጠሪያ እንዲሆን እነሆ ወንድ ልጅ ተወለደ፡፡ የበኩር ልጅ የአባትንና የእናትን ፍቅር ያለምንም ተሻሚ የሚጠግብ ልጅ ነው:: ከዚህም የተነሳ ያዕቆብ እነዚያን ቀናቶች እያስታወሰ ወንድ ልጅ ተወለደልህ የተባለለትን ቀን እያሰበ ኃይሌና የጉብዝናዬ መጀመሪያ ነህ እያለ የትዝታውን ማህደር ይፈትሻል፡፡ ከሮቤል መወለድ ጋር የያዕቆብ ትዝታ እርሱን ተክቶ በአብርሃም የተጀመረውን አዲስ ወገን የሚቀጥል ተኪ ሰው መገኘቱን አይቶ ልቡ በደስታ ይፍለቀለቅ እንደ ነበር መገመት አያስቸግርም፡፡ ትውልድን መተካት እንኳን በሰው ዘር በእንስሳትም ያለ ትልቅ የተፈጥሮ ግፈት ስለሆነ የመጀመሪያ የበኩር ልጁን ማግኘቱ የትውልድ ሐረጉ የመቀጠል ምልክቱ ስለሆነ ለደስታው መጠን አልነበረውም ነበር፡፡

2ኛ. የክብር አለቃና የኃይል አለቃ

የበኩር ልጅ በአባቱ እግር ተተክቶ አባቱ በነበረው ክብርና ኃይል የሚንቀሳቀስ፤ የሚገባና የሚወጣም ነው:: መጀመሪያ መወለድ በሚስጠው እድል ተጠቃሚ ስለሆነ የበኩር ልጅ የቤተስብ ድርሻው ሁልጊዜ ትልቅ ነው፡፡ በተለይ አባቱ በውርስ ሊያስተላልፍ የሚችለው የክብርና የኃይል ስፍራ ካለ በዚያ ስፍራ የመጀመሪያው ተተኪ ሆኖ የሚቀርበው የበኩር ልጅ ነው፡፡ በቀድሞው ዘመንና አሁንም በምድር ላይ የቀሩት ጥቂት ነገሥታት የመግዛት ዘመናቸው ሲያበቃ የግዛት በትራቸውንና ዙፋናቸውን የሚያስረክቡት ለመጀመሪያ ልጃቸው ነው::

ይህ ታላቅ መታደል ግን ለሁሉም የበኩር ልጅ በታሪክ ውስጥ ተከናውኗል ባይባልም የመጀመሪያ ልጆች ለዚህ መታደም አስቀድመው መታስባቸው የማይቀር የብኩርና ክብራቸው ነው::



ይቀጥላል...


ምንጭ፦ አበራ ጌታሁን (ዶ/ር)፤ የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው፤ ገጽ 4-6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍43
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፥ ከጨካኞችም ጡጫ እቤዥሃለሁ።”
             ኤርምያስ 15፥21




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍5
ሙሴ የሰራውን የናስ እባብ የሰባበረው ማን ነው?
Anonymous Quiz
63%
ሀ. አሮን
4%
ለ. ዳዊት
4%
ሐ. ሰሎሞን
29%
መ. ሕዝቅያስ
8👍3👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።”
            1ኛ ቆሮንቶስ 9፥25



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
#እራሳችንን_እንመርምር

በዘመናችን ምን ማድረግ እንዳለብን እናውቃለን ወይስ በደመነፍስ ነው የምንኖረው? እሺ በዘመናችን ምን ማድረግ እንዳለብን ካወቅንስ፣ ላወቅነው ነገር እየታዘዝን ነው?


“እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር።”
1 ዜና 12፥32


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ንጋትም በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዓምድ ሆኖ የግብፃውያንን ሠራዊት ተመለከተ፥ የግብፃውያንንም ሠራዊት አወከ።”
             ዘጸአት 14፥24



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ አዳናችሁ።”
          ዘዳግም 7፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


2ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²-³ የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
⁴ ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።
⁵ ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥
⁶ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥
⁷ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።
⁸ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤
⁹ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል።
¹⁰ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።
¹¹ እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍72
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ወድጃቸዋለሁና የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ አደላድላቸዋለሁም፤ እመልሳቸዋለሁ፤ እኔም አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁና እንዳልጣልኋቸው ይሆናሉ።”
              ዘካርያስ 10፥6




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51👏1