#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል
ሐዋርያት 20 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ እኛ ግን ጳውሎስን ለመቀበል ቀድመን ወደ መርከቡ ሄድን፤ ከዚያም በመርከብ ወደ አሶን ተጓዝን፤ ይህን ያደረግነውም ጳውሎስ በየብስ በእግሩ ሊሄድ ስላሰበ ነበር።
¹⁴ በአሶን ከተገናኘንም በኋላ፣ ተቀብለነው አብረን በመርከብ ወደ ሚጢሊኒ ሄድን።
¹⁵ በማግስቱም በመርከብ ተጒዘን ከኪዩ ደሴት ትይዩ ደረስን። በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞን ተሻገርን፤ በማግስቱም ሚሊጢን ደረስን።
¹⁶ ጳውሎስም በእስያ አውራጃ ብዙ መቈየት ስላልፈለገ፣ ወደ ኤፌሶን ሳይ ገባ ዐልፎ ለመሄድ ወሰነ፤ ቢቻል በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ለመዋል ቸኵሎ ነበርና።
¹⁷ ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ሰው ልኮ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሽማግሌዎች አስጠራ፤
¹⁸ በመጡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ወደ እስያ አውራጃ ከገባሁባት ከመጀመሪያዋ ዕለት አንሥቶ ዘወትር ከእናንተ ጋር እንዴት እንደኖርሁ ታውቃላችሁ።
¹⁹ ምንም እንኳ ከአይሁድ ሤራ የተነሣ መከራ ቢያደርሱብኝም፣ ጌታን በታላቅ ትሕትናና በእንባ ከማገልገል አልተቈጠብሁም፤
²⁰ በአደባባይም ሆነ ከቤት ቤት በመዘዋወር፣ እናንተን ከማስተማርና ይጠቅማችኋል ብዬ ያሰብሁትን ከመስበክ ወደ ኋላ አላልሁም።
²¹ በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ፣ ለአይሁድም ለግሪክ ሰዎችም አጥብቄ መስክሬላቸዋለሁ።
²² “አሁንም እዚያ ስደርስ የሚደርስብኝን ባላውቅም፣ መንፈስ ቅዱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው።
²³ ነገር ግን በምሄድባቸው ከተሞች ሁሉ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀኝ መንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል።
²⁴ ይሁን እንጂ ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን ሩጫዬንና የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎቴን ብፈጽም፣ ለእኔ ሕይወቴ ከምንም እንደማይቈጠር እንደ ከንቱ ነገር ናት።
²⁵ “አሁንም ቢሆን፣ በመካከላችሁ ተዘዋውሬ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሰበክሁላችሁ፣ እናንተ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲያ ፊቴን እንደማታዩ ዐውቃለሁ።
²⁶ ስለዚህ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ መሆኔን በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ፤
²⁷ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽ የተቈጠብሁበት ጊዜ የለምና።
²⁸ ለራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ኤጲስቆጶሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።
²⁹ እኔ ከሄድሁ በኋላ፣ ነጣቂ ተኵላዎች መጥተው በመካከላችሁ ሰርገው እንደሚገቡና ለመንጋውም እንደማይራሩ ዐውቃለሁ።
³⁰ ከእናንተው መካከል እንኳ የራሳቸውን ደቀ መዛሙርት ለማፍራት እውነትን የሚያጣምሙ ይነሣሉ።
³¹ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ሦስት ዓመት ሙሉ ሌሊትና ቀን ምንም ያህል ሳላቋርጥ በእንባ እያንዳንዳችሁን እንደ መከርኋችሁ አስታውሱ።
³² “አሁንም ለእግዚአብሔር፣ እንዲሁም ሊያንጻችሁና በቅዱሳኑ ሁሉ መካከል ርስት ሊያወርሳችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል ዐደራ እሰጣችኋለሁ።
³³ የማንንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤
³⁴ እነዚህ እጆቼ ለእኔና ከኔ ጋር ላሉት በሚያስፈልገን ነገር እንዳገለገሉን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
³⁵ በጒልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብን ባደረግሁት ሁሉ አሳይቻችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለውን የጌታ የኢየሱስን ቃል እናስታውስ።”
³⁶ ይህን ካለ በኋላ፣ ተንበርክኮ ከሁሉም ጋር ጸለየ።
³⁷ ሁሉም እጅግ አለቀሱ፤ ጳውሎስንም አንገቱን ዐቅፈው ሳሙት፤
³⁸ ከሁሉም በላይ ልባቸውን የነካው፣ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቱን እንደማያዩ የተናገራቸው ቃል ነበር። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት።
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

👍6❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ብርሃን ወደ ሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ።”
ሰቆ. 3፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ብርሃን ወደ ሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ።”
ሰቆ. 3፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤3👍3
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ኃይላቸውም እንደ ደከመ፥ የተዘጋ የተለቀቀም እንደሌለ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፥ ስለ ባሪያዎቹም ያዝናል።”
ዘዳግም 32፥36

❤5👍2
የዋናተኛው ታሪክ
እግዚአብሔር ክቡር ነው፡፡ እግዚአብሔርን ማወቅ ርካሽ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን በየመንገዱ አንረዳውም፡፡ እግዚአብሔርን ማወቅ የሚጠይቃቸው ነገሮች አሉ፡፡
እግዚአብሔር ርካሽ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ቀን ራሱን አያፈስልንም፡፡ እግዚአብሔር አንድ ነገር ያሳየንና ምላሻችንን ይጠብቃል፡፡ እግዚአብሔር ራሳችንን በሰጠነው መጠን ብቻ ነው ራሱን የሚሰጠን፡፡
"የእግዚአብሔር ክብር ነገርን መሰወር ነው፤ የነገሥታት ክብር ግን ነገርን መመርመር ነው።" ምሳሌ 25፡2
እግዚአብሔር በድንገት አይታወቅም፡፡ ሰው ካላረፈ እግዚአብሔርን አያውቀውም፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ውሳኔ ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ትጋት ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ አንድ ሃሳብነት ይጠይቃል፡፡
"እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።" ኤርምያስ 29፡13
እግዚአብሔር ሁልጊዜ በህይወታችን መስራት ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን የሚሰራው እኛ ስናርፍ ነው፡፡ እኛ ከተቅበዘበዝንና ካላረፍን እርሱ መስራት አይፈልግም፡፡ እኛ እየተቅበዘበዝንና እየተወራጨን ቢሰራም እግዚአብሔር የሰራ አይመስለንም፡፡ እኛ እየተቅበዘበዝንና እየተወራጨን ቢሰራ ክብሩን እኛ እንጂ እርሱ አይወስድም፡፡
"ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።" መዝሙር 46፡10
ለዚህ ነው እግዚአብሔር የስጋ ሃይላችንን አስክንጨርስ የሚጠብቀን፡፡ ለዚህ ነው ከስጋ ሃይላችን ጋር ሃይሉን ማቀላቀል የማይፈልገው፡፡ ለዚህ ነው እርሱን እንድንለይውና እንድንቀድሰው ከምንም ነገር ጋር እንዳናቀላቅለው የሚፈልገው፡፡
"ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት።በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።" 1ኛ ጴጥሮስ 3፡15
ታዋቂው የመፅሃፍ ቅዱስ አስተማሪው ዎች ማን ኒ ክርስትና እንዲህ ነው ተብሎ ወደ አማርኛ በተተረጎመው "The Normal Christian Life" በሚለው መፅሃፋቸው ላይ በመንፈስ ቅዱስ ላይ እንዴት መደገፍ እንዳለብን ሲፅፉ አንድን ታሪክ ይናገራሉ፡፡
በድሮ ጊዜ ሰውነታችንን የምንታጠበው ወንዝ ወርደን ነበር፡፡ አንድ ጊዜ አንዱ ዋና የማይችል ጓደኛችን ውሃ ውስጥ ይወድቃል፡፡ አንድ ሌላ ጓደኛችን ዋና ይችል ስለነበር አውጣው ብለን ጮኽን፡፡ እሱ ግን ፈጥኖ አላወጣውም ነበር፡፡ ቶሎ አውጣው ብለን በጣም ብንጮኽም ረጋ ይል ነበር፡፡ ከዚያም በኋላ ግን ውሃ ውስጥ ገብቶ አወጣው፡፡ በኋላ በጣም ተገርመን ምን ሆነህ ነበር ወዲያው ያላወጣኸው? ብለን ጠየቅነው፡፡ እርሱ ሲመልስ እኔ ውሃ ውስጥ የወደቀ ጊዜ ወዲያው ላወጣው ውሃ ውስጥ ብገባ እስከ ሙሉ ጉልበቱ ስለነበር እኔም ላይ ይጠመጠምና እንዳልዋኝ እንቅ አድርጎ ይዞኝ እኔም እርሱም ልንሞት እንችል ነበር፡፡ ቆየት ካለ በኋላ በራሱ ሞክሮ ከደከመ በኋላ ግን በቀላሉ አወጣሁት በማለት አስረዳቸው፡፡
እኛም ካላረፍን በራሳችን ጉልበት እንደምናደርገው ካሰብን እግዚአብሔር አይገባበትም፡፡ ለእግዚአብሔር ስፍራ ልንሰጠው ይገባል፡፡ እግዚአብሔር እንዲሰራ እኛ ልናርፍ ይገባል፡፡
"ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።" ሮሜ 12፡19
እኛ ስንጨርስና ስናርፍ እርሱ ይጀምራል፡፡ እኛ ስናርፍ እርሱ ይሰራል፡፡
"የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤" ኢሳያስ 30፡15
ምንጭ:-አብይ ዋቁማ

👍5❤1🥰1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።”
2ኛ ቆሮ 2፥11
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።”
2ኛ ቆሮ 2፥11
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤2
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... #የሮሜ_መልእክት_ጥናት ከአሸናፊዎች እንበልጣለን (8:31-39) ቁ. 31 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፥ ማን ሊቃወመን ይችላል? ሰይጣን ይቃወመናል፤ በመጨረሻ ግን እውነተኛን አማኝ ተቃውሞ ሊያሸንፈው አይችልም። ቁ. 32 እግዚአብሔር ብዙ አስደናቂ ስጦታዎችን ሰጥቶናል። ጸጋ፥ ፍቅር፥ ደስታ፥ ይቅርታ፥ ደኅንነት፥ በሰማይ ያለን ውርስ፥ ከስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ስጦታ የሆነው ግን…
የቀጠለ...
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ከአሸናፊዎች እንበልጣለን (8:31-39)
ቁ 36. እዚህ ላይ ጳውሎስ ከመዝ. 44፥22 ይጠቅሳል። ልክ ክርስቶስ ለእኛ ብሎ እንደሞተ እኛም ለእርሱ ስንል ቀኑን ሙሉ ሞትን ለመገናኘት መዘጋጀት አለብን (1ቆሮ. 15፥31፤ 2ቆሮ. 4፥8-12፤ 16-17)። ሞት እንኳ ቢሆን ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም። ክርስቶስ ልክ እንደሚታረድ በግ ሥጋውን አሳልፎ ለእኛ እንደሰጠ፣ እኛም ሥጋችንን ሕያው መሥዋዕት በማድረግ ለእግዚአብሔር ማቅረብ ይኖርብናል (ሮሜ 12፥1)። ብንኖርም ሆነ ብንሞት በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ እንቀራለን።
ቁ. 37 ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን አሸነፈ (ዮሐ. 16፥33)። ጥላቻን፣ ስደትን፣ ሞትንም ጭምር አሸነፈ (2ጢሞ. 1፥10)። እኛም ብንሆን በእነዚህ ሁሉ. . . ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ይህም በራሳችን ብርታት ሳይሆን ነገር ግን በእርሱ በወደደን በክርስቶስ ነው። (1ቆሮ. 15:57)
ቁ. 38-39 ከጳውሎስ ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ እነዚህ ጥቅሶች ለብዙ ክርስቲያኖች ታላቅ መጽናናት፥ ማበረታቻና ተስፋ ሰጥተዋል። እነዚህ ጥቅሶች የያዙት አሳብ በፍጹም እውነት ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ ካለን ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን የሚችል ከፍጥረት ሁሉ አንዳች ነገር የለም። ይሁን እንጂ፥ ክርስቲያኖች ይህን አስደናቂ ጥቅስ በመደጋገም ሲጠቅሱት እግዚአብሔር ያልፈጠረው አንድ ነገር መኖሩን ይረሳሉ፤ ያም ነገር በእርግጥ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለያቸው ይችላል፤ እርሱም ኃጢአት ነው።
እያወቅን አንድ ኃጢአት መሥራታችንን ብንቀጥል በእርሱም ንስሐ መግባት እምቢ ብንል፥ ያ ኃጢአት በእርግጥ ከእግዚአብሔር ፍቅር ይለየናል። በጣም አሠቃቂ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቁጣና ፍርድ በላያችን ያመጣል። ክርስቲያን ከመሆናችን በፊት በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ተለይተን ነበር፣ የእግዚአብሔር ጠላቶችም ነበርን (ሮሜ 5:10)። በኃጢአታችን ንስሓ ከገባንና በክርስቶስ ካመንን በኋላ ግን ክእግዚአብሔር ጋር ታረቅን። ነገር ግን ዳግመኛ ወደ ኃጢአት የምንመለስ ከሆነ፥ ደግሞም እያወቅን ንስሓ ሳንገባ በኃጢአታችን የምንቀጥል ከሆነ፥ እንደገና ከእግዚአብሔር እንዳንለይ ያስፈራል (ዕብ. 10፥26-27)፡፡ በፍርድ ቀን ያ መለየት ለዘላለም ይጸናብናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተሰጡን የተስፋ ቃላት ሁሉ በዚህ በቁ. 38-39 ውስጥ የተሰጠን የተስፋ ቃል ከሁሉም የሚበልጥ ነው። የተስፋ ቃሉን ስናስብ የተስፋ ቃሉ የሚፀናበትንም ሁኔታ አንዘንጋ። የመጽሐፍ ቅዱስን ተስፋ ቃሎች ማስታወስ መልካም ነው፣ ነገር ግን ተስፋውን ለመቀበል አስፈላጊ የሆኑ ግዴታዎችና ማስጠንቀቂያዎች መርሳት የለብንም!
ይህን ሮሜ ምዕ. 8 መለስ ብለን ስንመለከተው (አንዳንዶች ከመላው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ታላቅ ምዕራፍ ነው ብለው ያስባሉ)፥ ሙሉና ክብር ያለው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በፊታችን ሰፍሮ እናገኘዋለን። በፊት የተፈረደብን አሁን ጸድቀን እናያለን፤ በፊት እስረኞች እንደ ነበርን አሁን ግን ነፃ እንደወጣን፤ በፊት ሞተን እንደ ነበር አሁን ግን ሕያው እንደ ሆንን እናያለን። እነሆ አሁን አዲስና ድል አድራጊ ሕይወት ተሰጥቶናል፤ በውስጣችን በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ሁሉ ነገር ተችሎናል። በዚህ መንፈስ የምንመራ ከሆንን በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ተቀባይነት ይኖረናል። የእግዚአብሔር ልጆችም ተብለን ወራሾች እንሆናለን። በመጨረሻም ዘላለማዊ ኑሮአችን መልካም ሆኖ እናገኘዋለን። ምክንያቱም ዓለም ከመፈጠሩ በፊት በእግዚአብሔር የታቀደ በመሆኑ ነው። የወደፊት ኑሮአችን ሁኔታም በቁ. 29 ላይ ጠቅለል ተደርጎ ቀርቧል፤ የወደፊት ኑሮአችን የልጁን የኢየሱስ ክርስቶስን መልክ በመምሰል ለዘላለም ተጠቃሏል።
ወዳጆቼ ሆይ! ይህ በሕይወታችን የሚቃጠል ታላቅ ፍላጎታችን መሆን ይገባዋል። ኢየሱስ ክርስቶስን ለመምሰል መትጋት! ከዚህ የበለጠ ጥሪ የለንም፤ ከዚህም የበለጠ ክብር የለም።
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ ፤ ገጽ 370-371

👍5
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እነሆ፥ ተራሮችን የሠራ፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ የልቡንም አሳብ ለሰው የሚነግር፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።”
አሞጽ 4፥13

❤4👍3
#እራሳችንን_እንመርምር
የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ለመሆን ከብዶን እና አቅም አጥተን ይሆን? ይህ ለምን ተከሰተ? መፍትሄውስ ምን ይሆን?
“ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።”
ሐዋርያት 1፥8

❤4👍4
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፤ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጥተዋል፤ ንጉሣቸውም በፊታቸው አልፎአል፥ እግዚአብሔርም በራሳቸው ላይ ነው።”
ሚክያስ 2፥13

❤1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ሮሜ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለብኝ ስል በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል።
³ በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምሁ እንድሆን እጸልይ ነበርና።
⁴ እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፤
⁵ አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።
ሮሜ 9 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በክርስቶስ ሆኜ እውነት እናገራለሁ፤ አልዋሽም፤ ኅሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል።
² ታላቅ ሐዘንና የማያቋርጥ ጭንቀት በልቤ አለ።
³ ለወገኖቼ ስል ስለ ወንድሞቼ እኔ ራሴ የተረገምሁና ከክርስቶስም ተለይቼ የተጣልሁ እንድሆን እንኳ እወድ ነበር፤
⁴ እነርሱም የእስራኤል ሕዝብ ናቸው፤ ልጅ መሆን፣ መለኮታዊ ክብር፣ ኪዳን፣ ሕግን መቀበል፣ የቤተ መቅደስ ሥርዐትና ተስፋ የእነርሱ ናቸውና።
⁵ አባቶችም የእነርሱ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የትውልድ ሐረጉ የሚቈጠረው ከእነርሱ ነው፤ እርሱም፣ ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ ነው፤ አሜን።
ሮሜ 9 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በክርስቶስ ውስጥ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ። እንደማልዋሽም መንፈስ ቅዱስ ለሕሊናዬ ያረጋግጥልኛል። የሥጋ ዘመዶቼ ስለሆኑት ስለወንድሞቼ ስለእሥራኤላውያን ሳስብ
²¯³ ልቦናዬ ከባድ ኀዘን ሳይሰማው ፥ መንፈሴም ክፉኛ ሳይጨነቅ ውሎ ያደረበት ቀን የለም። እነርሱ ይዳኑልኝ እንጂ ከክርስቶስ ተለይቼ ኵነኔ እንኳ ቢደርስብኝ ቅር አይለኝም።
⁴ እነርሱ እግዚአብሔር ከዓለም ሕዝብ ለይቶ የመረጣቸው ፥ ልጆቹ ያደረጋቸው፥ ክብሩን የገለጠላቸው፥ ቃል ኪዳን የገባላቸው፥ ሕጉን የሰጣቸው፥ የአምልኮን ሥርዓት ያስተማራቸው የተስፋውንም ቃል የሰጣቸውና
⁵ የአሥራ ሁለቱ ነገደ እሥራኤል አባቶች ዝርያ ናቸው። ከሁሉ በላይ የሆነውና ለዘላለም የተባረከው አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ የተወለደው ከእነርሱው ወገን ነው። እርሱም ለዘላለም የተመሰገነ ነው፤ አሜን!

“በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ለዳንኤል ነገር ተገለጠለት፤ ነገሩም እውነት ነበረ፥ እርሱም ታላቅ ጦርነት ነው፤ ነገሩንም አስተዋለ፥ በራእዩም ውስጥ ማስተዋል ተሰጠው።”
ዳንኤል 10፥1

❤2👍2
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#ቆጵሮስ፤
በሜዲቴራኒያን በስተምሥራቅ የሚገኝ ደሴት። ብዙ አይሁድ ይኖሩበት ነበር። በርናባስ ቆጵሮሳዊ ነበር፤ ሐ.ሥ. 4፥36። የቆጵሮስ ሰዎች ወደ አንጾኪያ ሲሄዱ ወንጌልን ለግሪክ ሰዎች ሰበኩ፤ ሐ.ሥ. 11፥19:20። ጳውሎስ፥ በርናባስና ማርቆስ ደሴቱን ጐብኝተው ወንጌል ሰበኩ፤ ሐ.ሥ. 13፥4-13። በኋላም በርናባስና ማርቆስ እንደገና ወደ ቆጵሮስ ሄዱ፤ ሐ.ሥ. 15፥39።
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 101

❤4
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።”
ዮሐንስ 4፥10

#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
መዝሙር 29
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የአምላክ ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥ ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ።
² የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
³ የእግዚአብሔር ድምፅ በውኆች ላይ፥ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥ እግዚአብሔር በብዙ ውኆች ላይ።
⁴ የእግዚአብሔር ድምፅ በኃይል ነው፤ የእግዚአብሔር ድምፅ በታላቅ ክብር ነው።
⁵ የእግዚአብር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።
⁶ እንደ ጥጃ ሊባኖስን፥ አንድ ቀን እንዳለው አውሬ ልጅ ስርዮንን ያዘልላቸዋል።
⁷ የእግዚአብሔር ድምፅ የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
⁸ የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፥ እግዚአብሔር የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
⁹ የእግዚአብሔር ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል፥ ጫካዎቹንም ይገልጣል ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
¹⁰ እግዚአብሔር የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።
¹¹ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።

“ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥12

“ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?”
ኢሳይያስ 40፥27

👍5❤2😁1
የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው
ክፍል - ፩
፩. ሮቤል
ዘፍ. 49፥3-4፤ ዘዳ. 33፥6
ሮቤል የያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ነው፡፡ ሮቤል የተወለደው ከልያ ሲሆን እግዚእብሔር መከራዋን እንዳየላትና ከዚህም በኋላ ያዕቆብ ይወደኛል ስትል ስሙን ሮቤል ብላ ጠራችው (ዘፍ. 29፥31-32)። ያዕቆብ ድብቅ ያልሆነ በገሃድ የመውደድ ፍቅሩን የገለጸው ለራሔል ስለ ነበር ልያ አስቀድማ ልጅ በመውለዷ የያዕቆብን የፍቅር ልብ እንደምታገኝ በመገመቷ የማህጸኗን መክፈቻና የመጀመሪያዋን ወንድ ልጅ ስም ከዚህ የተነሳ ሰየመችው፡፡ የስሙም ትርጓሜ እነሆ ወንድ ልጅ ማለት ነው፡፡ ወንድ ልጅ ሰጥቼሃለሁ፣ አንተም የፍቅር ልብህን አትንፈገኝ በማለት ልያ ለያዕቆብ ፍቅር መለመኛ እንዲሆናት ሮቤል መጠሪያውን አገኘ፡፡
ሮቤል ዮሴፍን ወንድሞቹ ሊያጠፉት በተነሱ ጊዜ ደም እንዳያፈሱ ነገር ግን በጉድጓድ እንዲጥሉት አደረገ (ዘፍ. 37፥22 )። በኋላም ወንድሞቹ ከጉድጓድ አውጥተው ሲሸጡት በአጠገባቸው እንዳልነበረና ከወንድሞቹም ተለይቶ ብቻውን ወደ ጉድጓዱ በተመለሰ ጊዜ ዮሴፍን እንዳጣው የእግዚአብሔር ቃል ይመስክራል (ዘፍ. 37፥29 ) ፡፡ ሮቤል በልቡ ያለውን ሰውሮ ሌሎቹ ከሚያደርጉት ጋር ይሄድ ስለ ነበር በኋላ በእንባ ቢጮህም ዮሴፍን ማዳን አልቻለም፡፡ እውነት ሊያስከፍል የሚችለውን ዋጋ ፊት ለፊት ከመክፈል ተሰውሮ በድብቅ በልቡ ያሰበውን መፈጸምን መረጠ፡፡ ብቻውንም በስውር ዮሴፍን አድናለሁ ብሎ ላሰበው ድርጊቱ ግን ሰዓት ስላለፈበት ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ እንደሚሉት እንደ አገራችን ተረት ሆነበት፡፡ የወንድሞቹንም ክፋት ልክ ባለ ማወቁ ሊያደርግ ባስበው የልቡ ውሳኔ ላይ ፀሐይ ጠለቀችበት፡፡ ጊዜም አመለጠው፡፡
ብዙ ጊዜ ስናመነታ፤ ቀን ስላለ በሌላ ጊዜ እደርሳለሁ እያልን በምናስተላልፋቸው ብዙ ነገሮቻችን ላይ ሳናስብና ሳናውቅ ጊዜ አምልጦን ሁኔታዎችም ተለውጠው ራሳችንን እናገኛለን፡፡ በዚያን ሰዓት የጸጸት እንባ፣ የምሬት ጩኸት፣ የፀጉር መንጨት፤ የደረት መድቃት ባዶ እሪታ ብቻ ይሆናል፡፡ ቀን ሳለ ወይም ጊዜ ሳለ ማድረግ የሚገባንን ለማድረግ የታጠቅንና የቆረጥን ልንሆን ያስፈልጋል (ዮሐ.9፥4)::
ያዕቆብ ስለ ሮቤል ሲናገር እንዲህ አለ (ዘፍ. 49፥4)፦
1ኛ. ሮቤል አንተ የበኩር ልጄና ኃይሌ፥ የጉብዝናዬም መጀመሪያ ነህ
እግዚእብሔር ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና በኋላም ለያዕቆብ በሰጠው የኪዳን ሐረግ የተስፋውን ቃል ለመሙላት ከያዕቆብ ልጆች ሮቤል በኩር ሆኖ ተወለደ፡፡ የነገድ መጀመሪያ፤ የበረከት መጀመሪያ፤ የአባቱ መተኪያና የአባቱ መጠሪያ እንዲሆን እነሆ ወንድ ልጅ ተወለደ፡፡ የበኩር ልጅ የአባትንና የእናትን ፍቅር ያለምንም ተሻሚ የሚጠግብ ልጅ ነው:: ከዚህም የተነሳ ያዕቆብ እነዚያን ቀናቶች እያስታወሰ ወንድ ልጅ ተወለደልህ የተባለለትን ቀን እያሰበ ኃይሌና የጉብዝናዬ መጀመሪያ ነህ እያለ የትዝታውን ማህደር ይፈትሻል፡፡ ከሮቤል መወለድ ጋር የያዕቆብ ትዝታ እርሱን ተክቶ በአብርሃም የተጀመረውን አዲስ ወገን የሚቀጥል ተኪ ሰው መገኘቱን አይቶ ልቡ በደስታ ይፍለቀለቅ እንደ ነበር መገመት አያስቸግርም፡፡ ትውልድን መተካት እንኳን በሰው ዘር በእንስሳትም ያለ ትልቅ የተፈጥሮ ግፈት ስለሆነ የመጀመሪያ የበኩር ልጁን ማግኘቱ የትውልድ ሐረጉ የመቀጠል ምልክቱ ስለሆነ ለደስታው መጠን አልነበረውም ነበር፡፡
2ኛ. የክብር አለቃና የኃይል አለቃ
የበኩር ልጅ በአባቱ እግር ተተክቶ አባቱ በነበረው ክብርና ኃይል የሚንቀሳቀስ፤ የሚገባና የሚወጣም ነው:: መጀመሪያ መወለድ በሚስጠው እድል ተጠቃሚ ስለሆነ የበኩር ልጅ የቤተስብ ድርሻው ሁልጊዜ ትልቅ ነው፡፡ በተለይ አባቱ በውርስ ሊያስተላልፍ የሚችለው የክብርና የኃይል ስፍራ ካለ በዚያ ስፍራ የመጀመሪያው ተተኪ ሆኖ የሚቀርበው የበኩር ልጅ ነው፡፡ በቀድሞው ዘመንና አሁንም በምድር ላይ የቀሩት ጥቂት ነገሥታት የመግዛት ዘመናቸው ሲያበቃ የግዛት በትራቸውንና ዙፋናቸውን የሚያስረክቡት ለመጀመሪያ ልጃቸው ነው::
ይህ ታላቅ መታደል ግን ለሁሉም የበኩር ልጅ በታሪክ ውስጥ ተከናውኗል ባይባልም የመጀመሪያ ልጆች ለዚህ መታደም አስቀድመው መታስባቸው የማይቀር የብኩርና ክብራቸው ነው::
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ አበራ ጌታሁን (ዶ/ር)፤ የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው፤ ገጽ 4-6

👍4❤3