ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
333 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
የጥምቀት በዓልን ለምታከብሩ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተውኝ።”
                መዝሙር 27፥9



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
#እራሳችንን_እንመርምር

በእግዚአብሔር ፊት በጸሎት ቀርበን እየለመንን እና እየጸለይን ነው ወይስ እኛ በጉልበታችን ምኞቶቻችንን ለማሳካት እየተጋደልን? እግዚአብሔር ጸሎትን ስለማይሰማ ነው ወይስ ፈቃዳችን ከእርሱ ፈቃድ በልጦብን ይሆን መጸለይ ያቆምነው?

"አንድ ነገር ለማግኘት ትጓጓላችሁ። ያንን የጓጓችሁለትን ነገር ለማግኘት ነፍስ እስከ ማጥፋት ትደርሳላችሁ። የእናንተ ያልሆነውን ትመኛላችሁ። የተመኛችሁትን ለማግኘት ጠብ ትፈጥራላችሁ ፤ ትጋደላላችሁ። ይህን ሁሉ አድርጋችሁም የምትመኙትን አታገኙም። የምትፈልጉትን ነገር የማታገኙትም እግዚአብሔርን በጸሎት ስላልጠየቃችሁት ነው።"
ያዕቆብ 4፥2 (ሕያው ቃል)


“በስውር ወይም በጨለማ ምድር ስፍራ አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን እናገራለሁ ቅንንም አወራለሁ።”
ኢሳይያስ 45፥19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍63
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔርም በሌሒ ያለውን አዘቅት ሰነጠቀ፥ ከእርሱም ውኃ ወጣ፤ እርሱም ጠጣ፥ ነፍሱም ተመለሰች፥ ተጠናከረም። ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ዓይንሀቆሬ ብሎ ጠራው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በሌሒ አለ።”
            መሳፍንት 15፥19




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
4-utmost-1-cr.pdf
2.2 MB
📔ርዕስ፦ ሁለንተናዬ ለእርሱ ክብር
👤ጸሐፊ፦ ኦዝዋልድ ቻንበርስ
🗣ተርጓሚ፦ ተስፋዬ መስፍን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
4-utmost-2-cr.pdf
2.1 MB
📔ርዕስ፦ ሁለንተናዬ ለእርሱ ክብር
👤ጸሐፊ፦ ኦዝዋልድ ቻንበርስ
🗣ተርጓሚ፦ ተስፋዬ መስፍን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
4-utmost-3-cr.pdf
2 MB
📔ርዕስ፦ ሁለንተናዬ ለእርሱ ክብር
👤ጸሐፊ፦ ኦዝዋልድ ቻንበርስ
🗣ተርጓሚ፦ ተስፋዬ መስፍን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
4-utmost-4-cr.pdf
2.1 MB
📔ርዕስ፦ ሁለንተናዬ ለእርሱ ክብር
👤ጸሐፊ፦ ኦዝዋልድ ቻንበርስ
🗣ተርጓሚ፦ ተስፋዬ መስፍን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
4-utmost-5-cr.pdf
2.3 MB
📔ርዕስ፦ ሁለንተናዬ ለእርሱ ክብር
👤ጸሐፊ፦ ኦዝዋልድ ቻንበርስ
🗣ተርጓሚ፦ ተስፋዬ መስፍን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
4-utmost-6-cr.pdf
2.5 MB
📔ርዕስ፦ ሁለንተናዬ ለእርሱ ክብር
👤ጸሐፊ፦ ኦዝዋልድ ቻንበርስ
🗣ተርጓሚ፦ ተስፋዬ መስፍን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
እግዚአብሔር በየቀኑ በሕይወታቸው ውስጥ የሚያደርገውን በጎነት የማናስተውል ብዙ ነን። ከእንቅልፋችን በሰላምና ጤና ነቅተን የማለዳዋን ፀሓይ ለማየት ስለመታደላችን ምስጋና ስናቀርብ አንታይም። በመሰለን መንገድ ያልተከናወነ ነገር ብንቀበልም፥ መብታችን እንጂ ቸርነት አይመስለንም። በሕይወት መኖር እንደ ቀልድ ይታለፋል። ስፍር ቍጥር የሌላቸው ቅጽበታዊ ዕለታዊና የዘመናችን ሙሉ የበጎነት ስጦታዎቹ በቸልታ ተወርውረው ይኖራሉ። እኛ ሰዎች እንገርማለን እኮ። እናሳዝንማለን።

የገዛ ምራቁ ትን ብሎት ሕይወቱን በሰከንዶች ውስጥ ሊያጣ የሚችል ሰው በሕይወት መቈየት የቻለው በእግዚአብሔር ምሕረት መኾኑን ይዘነጋል። ፍጥረት ሕግና ሥርዐት ጠብቆ የሚኖረው በጌታ ነው። ምድር በአምላካዊ ቸርነት ተጠብቃ ሕይወት ያብብባታል። ሥጋት በወጠረው ዓለም ውስጥ በሰላም ወጥተን መግባት መቻላችን ትርጕሙ የሚገባን አገር ምድሩ ሲታመስ መኾን የለበትም።

ከስንት አስፈሪ ነገሮች ተረፍን? ስንቱን የሞት ሸለቆዎች በምሕረቱ ተሻገርን? ስንት ጊዜ ወድቀን ስንት ጊዜ በቸርነቱ ተደግፈን ተነሣን? ዛሬስ ቢኾን ከእጆቹ ምን ተቀብለናል? ወዳጃችን፥ "ነፍሴ ሆይ፥ ውለታውን አትርሺ" ማለቱ ቁምነገረኝነት ያለው ሰው በመኾኑ ነው። ጌታችን ማዳኑ ዛሬም አዲስ ነው።


መጋቢ ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ፣ ለአይሁድም ለግሪክ ሰዎችም አጥብቄ መስክሬላቸዋለሁ።”
         ሐዋርያት 20፥21 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
ቅዱሳት መጻሕፍት
#መጻሕፍትን_እንመርምር የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በሙሉ ስለጌታችን እና ስለመድኃኒታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚናገር የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ይናገራሉ። ስለሆነም በብሉይ ኪዳን ያለውን በዝርዝር ከመመልከታችን በፊት እስቲ አንዳንድ ስለኢየሱስ የተነገሩትን ትንቢቶች እንመልከት። 1. መሲሕ የሚወለደው ከሴት ነው። (ዘፍጥረት 3:15፤ ማቴዎስ 1:20፤ ገላትያ 4-4) 2. መሲሕ የሚወለደው በቤተልሔም…
#መጻሕፍትን_እንመርምር



8. መሲሕ የንጉስ ዳዊትን ዙፋን ይወርሳል 

2 ሳሙኤል 7፥ 12-13፤ ኢሳይያስ 9፥ 7፤ ሉቃስ 1 32-33፤ ሮሜ 1፥ 3

9. የመሲሁ ዙፋን የተቀባና ዘላለማዊ ይሆናል

መዝሙር 45፥ 6-7፤ ዳንኤል 2፥44፤ ሉቃስ 1፥33፤
ዕብራውያን 1፥ 8-12

10. መሲሑ አማኑኤል ይባላል 

ኢሳይያስ 7፥14፤ ማቴዎስ 1፥23

11. መሲሕ አንድ ጊዜ በግብፅ ያሳልፋል

ሆሴዕ 11፥1፤ ማቴዎስ 2፥ 14-15

12. በመሲሑ የትውልድ ቦታ ላይ ሕፃናት ጭፍጨፋ ይደርስባቸዋል

ኤርምያስ 31፥15፤ ማቴዎስ 2፥ 16-18

13. አንድ መልእክተኛ ለመሲሁ መንገድ ያዘጋጃል

ኢሳይያስ 40፥ 3-5፤ ሉቃስ 3፥ 3-6

14. መሲሑ በገዛ ወገኖቹ ይገለላል

መዝሙር 69፥ 8፤ ኢሳይያስ 53፥ 3፤ ዮሐንስ 1፥11፤ ዮሐንስ 7፥ 5

15. መሲሕ ነቢይ ይሆናል

ዘዳ 18፥15፤ የሐዋርያት ሥራ 3፥ 20-22

16. መሲሑ ቀደም ሲል ከኤልያስ አስቀድሞ ተተካ

ሚልክያስ 4፥ 5-6፤ ማቴዎስ 11፥ 13-14

17. መሲሕ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል 

መዝሙር 2፥7፤ ማቴዎስ 3፥16-17

18. መሲሑ ናዝራዊ ይባላል

ኢሳይያስ 11፥1፤ ማቴዎስ 2፥23

19. መሲሑ ወደ ገሊላ ብርሃን ያመጣል

ኢሳ. 9፥1-2፤ ማቴዎስ 4፥ 13-16

20. መሲህ በምሳሌዎች ይናገር ነበር

መዝሙር 78፥2-4፤ ኢሳይያስ 6፥9-10፤ ማቴዎስ 13፥10-15፣ 34-35



ይቀጥላል...



ምንጭ፦ https://am.eferrit.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍43
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበር የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለት ነበር።”
       1ኛ ሳሙኤል 18፥14 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል


ሐዋርያት 20 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ እኛ ግን ጳውሎስን ለመቀበል ቀድመን ወደ መርከቡ ሄድን፤ ከዚያም በመርከብ ወደ አሶን ተጓዝን፤ ይህን ያደረግነውም ጳውሎስ በየብስ በእግሩ ሊሄድ ስላሰበ ነበር።
¹⁴ በአሶን ከተገናኘንም በኋላ፣ ተቀብለነው አብረን በመርከብ ወደ ሚጢሊኒ ሄድን።
¹⁵ በማግስቱም በመርከብ ተጒዘን ከኪዩ ደሴት ትይዩ ደረስን። በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞን ተሻገርን፤ በማግስቱም ሚሊጢን ደረስን።
¹⁶ ጳውሎስም በእስያ አውራጃ ብዙ መቈየት ስላልፈለገ፣ ወደ ኤፌሶን ሳይ ገባ ዐልፎ ለመሄድ ወሰነ፤ ቢቻል በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ለመዋል ቸኵሎ ነበርና።
¹⁷ ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ሰው ልኮ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሽማግሌዎች አስጠራ፤
¹⁸ በመጡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ወደ እስያ አውራጃ ከገባሁባት ከመጀመሪያዋ ዕለት አንሥቶ ዘወትር ከእናንተ ጋር እንዴት እንደኖርሁ ታውቃላችሁ።
¹⁹ ምንም እንኳ ከአይሁድ ሤራ የተነሣ መከራ ቢያደርሱብኝም፣ ጌታን በታላቅ ትሕትናና በእንባ ከማገልገል አልተቈጠብሁም፤
²⁰ በአደባባይም ሆነ ከቤት ቤት በመዘዋወር፣ እናንተን ከማስተማርና ይጠቅማችኋል ብዬ ያሰብሁትን ከመስበክ ወደ ኋላ አላልሁም።
²¹ በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ፣ ለአይሁድም ለግሪክ ሰዎችም አጥብቄ መስክሬላቸዋለሁ።
²² “አሁንም እዚያ ስደርስ የሚደርስብኝን ባላውቅም፣ መንፈስ ቅዱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው።
²³ ነገር ግን በምሄድባቸው ከተሞች ሁሉ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀኝ መንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል።
²⁴ ይሁን እንጂ ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን ሩጫዬንና የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎቴን ብፈጽም፣ ለእኔ ሕይወቴ ከምንም እንደማይቈጠር እንደ ከንቱ ነገር ናት።
²⁵ “አሁንም ቢሆን፣ በመካከላችሁ ተዘዋውሬ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሰበክሁላችሁ፣ እናንተ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲያ ፊቴን እንደማታዩ ዐውቃለሁ።
²⁶ ስለዚህ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ መሆኔን በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ፤
²⁷ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽ የተቈጠብሁበት ጊዜ የለምና።
²⁸ ለራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ኤጲስቆጶሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።
²⁹ እኔ ከሄድሁ በኋላ፣ ነጣቂ ተኵላዎች መጥተው በመካከላችሁ ሰርገው እንደሚገቡና ለመንጋውም እንደማይራሩ ዐውቃለሁ።
³⁰ ከእናንተው መካከል እንኳ የራሳቸውን ደቀ መዛሙርት ለማፍራት እውነትን የሚያጣምሙ ይነሣሉ።
³¹ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ሦስት ዓመት ሙሉ ሌሊትና ቀን ምንም ያህል ሳላቋርጥ በእንባ እያንዳንዳችሁን እንደ መከርኋችሁ አስታውሱ።
³² “አሁንም ለእግዚአብሔር፣ እንዲሁም ሊያንጻችሁና በቅዱሳኑ ሁሉ መካከል ርስት ሊያወርሳችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል ዐደራ እሰጣችኋለሁ።
³³ የማንንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤
³⁴ እነዚህ እጆቼ ለእኔና ከኔ ጋር ላሉት በሚያስፈልገን ነገር እንዳገለገሉን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
³⁵ በጒልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብን ባደረግሁት ሁሉ አሳይቻችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለውን የጌታ የኢየሱስን ቃል እናስታውስ።”
³⁶ ይህን ካለ በኋላ፣ ተንበርክኮ ከሁሉም ጋር ጸለየ።
³⁷ ሁሉም እጅግ አለቀሱ፤ ጳውሎስንም አንገቱን ዐቅፈው ሳሙት፤
³⁸ ከሁሉም በላይ ልባቸውን የነካው፣ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቱን እንደማያዩ የተናገራቸው ቃል ነበር። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ብርሃን ወደ ሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ።”
            ሰቆ. 3፥2



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3
እግዚአብሔርን መምሰል.pdf
3.2 MB
📚ርዕስ፦ እግዚአብሔርን መምሰል
👤ጸሐፊ፦ ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ኃይላቸውም እንደ ደከመ፥ የተዘጋ የተለቀቀም እንደሌለ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፥ ስለ ባሪያዎቹም ያዝናል።”
            ዘዳግም 32፥36



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2
የዋናተኛው ታሪክ



እግዚአብሔር ክቡር ነው፡፡ እግዚአብሔርን ማወቅ ርካሽ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን በየመንገዱ አንረዳውም፡፡ እግዚአብሔርን ማወቅ የሚጠይቃቸው ነገሮች አሉ፡፡

እግዚአብሔር ርካሽ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ቀን ራሱን አያፈስልንም፡፡ እግዚአብሔር አንድ ነገር ያሳየንና ምላሻችንን ይጠብቃል፡፡ እግዚአብሔር ራሳችንን በሰጠነው መጠን ብቻ ነው ራሱን የሚሰጠን፡፡

"የእግዚአብሔር ክብር ነገርን መሰወር ነው፤ የነገሥታት ክብር ግን ነገርን መመርመር ነው።" ምሳሌ 25፡2

እግዚአብሔር በድንገት አይታወቅም፡፡ ሰው ካላረፈ እግዚአብሔርን አያውቀውም፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ውሳኔ ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ትጋት ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ አንድ ሃሳብነት ይጠይቃል፡፡

"እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።"  ኤርምያስ 29፡13

እግዚአብሔር ሁልጊዜ በህይወታችን መስራት ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን የሚሰራው እኛ ስናርፍ ነው፡፡ እኛ ከተቅበዘበዝንና ካላረፍን እርሱ መስራት አይፈልግም፡፡ እኛ እየተቅበዘበዝንና እየተወራጨን ቢሰራም እግዚአብሔር የሰራ አይመስለንም፡፡ እኛ እየተቅበዘበዝንና እየተወራጨን ቢሰራ ክብሩን እኛ እንጂ እርሱ አይወስድም፡፡

"ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።" መዝሙር 46፡10

ለዚህ ነው እግዚአብሔር የስጋ ሃይላችንን አስክንጨርስ የሚጠብቀን፡፡ ለዚህ ነው ከስጋ ሃይላችን ጋር ሃይሉን ማቀላቀል የማይፈልገው፡፡ ለዚህ ነው እርሱን እንድንለይውና እንድንቀድሰው ከምንም ነገር ጋር እንዳናቀላቅለው የሚፈልገው፡፡

"ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት።በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።" 1ኛ ጴጥሮስ 3፡15

ታዋቂው የመፅሃፍ ቅዱስ አስተማሪው ዎች ማን ኒ ክርስትና እንዲህ ነው ተብሎ ወደ አማርኛ በተተረጎመው "The Normal Christian Life" በሚለው መፅሃፋቸው ላይ በመንፈስ ቅዱስ ላይ እንዴት መደገፍ እንዳለብን ሲፅፉ አንድን ታሪክ ይናገራሉ፡፡ 

በድሮ ጊዜ ሰውነታችንን የምንታጠበው ወንዝ ወርደን ነበር፡፡ አንድ ጊዜ አንዱ ዋና የማይችል ጓደኛችን ውሃ ውስጥ ይወድቃል፡፡ አንድ ሌላ ጓደኛችን ዋና ይችል ስለነበር አውጣው ብለን ጮኽን፡፡ እሱ ግን ፈጥኖ አላወጣውም ነበር፡፡ ቶሎ አውጣው ብለን በጣም ብንጮኽም ረጋ ይል ነበር፡፡ ከዚያም በኋላ ግን ውሃ ውስጥ ገብቶ አወጣው፡፡ በኋላ በጣም ተገርመን ምን ሆነህ ነበር ወዲያው ያላወጣኸው? ብለን ጠየቅነው፡፡ እርሱ ሲመልስ እኔ ውሃ ውስጥ የወደቀ ጊዜ ወዲያው ላወጣው ውሃ ውስጥ ብገባ እስከ ሙሉ ጉልበቱ ስለነበር እኔም ላይ ይጠመጠምና እንዳልዋኝ እንቅ አድርጎ ይዞኝ እኔም እርሱም ልንሞት እንችል ነበር፡፡ ቆየት ካለ በኋላ በራሱ ሞክሮ ከደከመ በኋላ ግን በቀላሉ አወጣሁት በማለት አስረዳቸው፡፡

እኛም ካላረፍን በራሳችን ጉልበት እንደምናደርገው ካሰብን እግዚአብሔር አይገባበትም፡፡ ለእግዚአብሔር ስፍራ ልንሰጠው ይገባል፡፡ እግዚአብሔር እንዲሰራ እኛ ልናርፍ ይገባል፡፡

"ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።" ሮሜ 12፡19

እኛ ስንጨርስና ስናርፍ እርሱ ይጀምራል፡፡ እኛ ስናርፍ እርሱ ይሰራል፡፡

"የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤" ኢሳያስ 30፡15



ምንጭ:-አብይ ዋቁማ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51🥰1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።”
         2ኛ ቆሮ 2፥11




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2