ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
333 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው አሙት፦ እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድን ያሰናዳ ዘንድ ይችላልን?”
             መዝሙር 78፥19




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
የእውነተኛ ደቀ መዝሙር ባህርያት



በአለማችን ላይ እውነተኛ ደቀመዛሙርቶች አሉ፡፡ የስም ብቻ ደቀመዛሙርቶች ደግሞ አሉ፡፡ እውነተኛ ደቀመዝሙር የሚያደርገን ምን እንደሆነ ማወቅ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡ የእውነተኛ ደቀመዝሙርነት መንገድ ላይ መሆናችንን ማወቅ ህይወታችንን በከንቱ እንዳናባክነው ያደርገናል፡፡ እውነተኛ ደቀመዝሙርነታችን እውነተኛ ነፃነት ውስጥ ያስገባናል፡፡

"ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፦ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።" ዮሐንስ 8፡31-32

የእውነተኛ ደቀመዝሙርነት መለያ መፅሃፍ ቅዱሳዊ መስፈርቶች

👉ጌታ ኢየሱስን ከሁሉም ነገር በላይ መውደድ


ኢየሱስን ከአባቱና ከእናቱን ከሚስቱም ከልጆቹም በላይ መውደድ አለበት፡፡ ከኢየሱስ በላይ የምንወደው ምንንም ነገር ካለ እውነተኛ ደቀመዛሙርት አልሆንም ማለት ነው፡፡

"ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።" ሉቃስ 14፡26

👉ራስን መካድ – ቃሉን ማስቀደም ትህትናና በእግዚአብሄር ፊት መዋረድ

እውነተኛ ደቀመዝሙርነት የሚለየው ራስን በመካድ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ከነፍሳችን ፍላጎትና ጥቅም በላይ ማስቀደም ራስን መካድ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ለመጠበቅ ብለን ጥቅማችንን የምንተው ከሆነ ራሳችንን ክደናል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለመታዘዝ ነፍሳችንን የምንክድ ከሆንን እውነተኛ የኢየሱስ ተከታዮች ነን፡፡

"ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።" ሉቃስ 9፡23
 
👉ፍቅር – ከራስ ወዳድነት የፀዳ ህይወት

ደቀመዝሙር እግዚአብሄር የሚወደውን ሁሉ ይወዳል፡፡ እግዚአብሄር ሰዎችን ሁሉ እንደሚወድ ሁሉ የኢየሱስ ደቀመዝሙር ሰዎችን ሁሉ ይወዳል፡፡ የሚጠላው ሰው ያለው ሰው እውነተኛ የኢየሱስ ደቀመዝሙር አይደለም፡፡

"እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።" ዮሐንስ 13፡35

👉በእግዚአብሄር መደገፍና መታመን

እውነተኛ ደቀመዝሙር ስለሁሉም ነገር በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ አለበት፡፡ ባለው በምንም ነገር ላይ የሚደገፍ ሰው የኢየሱስ ደቀመዝሙር ሊሆን አይችልም፡፡ ደቀመዝሙር ስለሁሉም ነገሩ በእግዚአብሄር ላይ በመታመን እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡

"እንግዲህ እንደዚሁ ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።" ሉቃስ 14፡33

👉በእግዚአብሄር ድምፅ እለት እለት መመራት

እውነተኛ ደቀመዝሙር የራሱን ነገር አድርጎ አንዳንዴ እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሳይሆን ለህይወቱ እለት እለት የእግዚአብሄርን ምሪት የሚፈልግ ነው፡፡ ደቀመዝሙር ከእግዚአብሄር ጋር የአባትና የልጅ ግንኙነት ያለውና እግዚአብሄርን ለማስደሰት ራሱ የሰጠ ነው፡፡

"በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤" ዮሃንስ 10፡27

👉ከኑሮ ፍርሃት እስራት መውጣት

በኑሮ ፍርሃት የሚወጣና የሚገባ ሰው እውነተኛ የኢየሱስ ደቀመዝሙር አይደለም፡፡ እውነተኛ የኢየሱስ ደቀመዝሙር የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስት ይፈልጋል፡፡ ሌላውን ሁሉ እንደሚጨመርለት ያውቃል፡፡ ሰው ለጌታም ለገንዘብም መገዛት ስለማይችል ገንዘብ የሚገዛው ሰው እውነተኛ የኢየሱስ ደቀመዝሙትር ሊሆ አይችልም፡፡

"የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል።" ማርቆስ 4፡19

👉ብዙ ፍሬን ማፍራት

እውነተኛ ደቀመዝሙር የሆነ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል በመኖር ለእግዚአብሄር ቤተክርስትያን በሁሉ ጠቃሚ ሲሆን ይታያል፡፡ ደቀመዝሙር ከክርስትያን እህቶችና ወንድሞች ጋር በፍቅር ይኖራል፡፡

"ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።" ዮሐንስ 15፡8
 
👉ክርስቶስን ይመስላል

እውነተኛ ደቀመዝሙር ትህትናው ፣ ትግስቱ ፣ የዋህነቱ ባህሪው ሁሉ ስለ እርሱ ይመሰክራል፡፡ 

"የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።" ገላትያ 5፡22

👉ደቀመዝሙር ያፈራል

እውነተኛ ደቀመዝሙር በንፁህ የህይወት ምስክርነቱና የወንጌል ስብከት አገልግሎቱ ሌሎችን ደቀመዛሙርት ያፈራል፡፡

"እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።" ማቴዎስ 28፡19-20



ምንጭ:- አብይ ዋቁማ ዲንሳ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍92
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“አሁንም፣ ተነሣና በእግርህ ቁም፤ ስለ እኔ ስላየኸውና ወደ ፊትም ስለማሳይህ ነገር አገልጋይና ምስክር እንድትሆን ልሾምህ ተገልጬልሃለሁ።”
        ሐዋርያት 26፥16 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
#እራሳችንን_እንመርምር

እግዚአብሔርን መጠበቅ ላይ እንዴት ነን? መጠበቅስ ምን ማለት ነው? ምን እያደረግን እግዚአብሔርን እንጠብቅ? እግዚአብሔርን መጠበቅ ምን ያመጣልናል? ከመጠበቅ ይልቅ መወራጨቱስ ትርፍ ይኖረው ይሆን?


“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
ኢሳይያስ 40፥31



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ፤”
                ቆላስይስ 2፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
የኢየሱስ ምሣሌያዊ አስተምህሮዎች.pdf
3.7 MB
ርዕስ፦የኢየሱስ ምሳሌያዊ አስተምህሮዎች፣ የመንግሥተ ሰማይ ምስጢራት መፍቻ
👤ጸሐፊ፦ጄ. ድዋይት(ዶ/ር)
🗣ተርጓሚ፦ አብይ ደምሴ
📑የገጽ ብዛት፦ 180
💾 መጠን፦ 3.7 MB


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“መንፈስን አታጥፉ፤”
        1ኛ ተሰሎንቄ 5፥19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1
የቀጠለ...


#የሮሜ_መልእክት_ጥናት




ከአሸናፊዎች እንበልጣለን (8:31-39)


ቁ. 31 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፥ ማን ሊቃወመን ይችላል? ሰይጣን ይቃወመናል፤ በመጨረሻ ግን እውነተኛን አማኝ ተቃውሞ ሊያሸንፈው አይችልም።

ቁ. 32 እግዚአብሔር ብዙ አስደናቂ ስጦታዎችን ሰጥቶናል። ጸጋ፥ ፍቅር፥ ደስታ፥ ይቅርታ፥ ደኅንነት፥ በሰማይ ያለን ውርስ፥ ከስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ስጦታ የሆነው ግን ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ገና የእግዚአብሔር ጠላቶች በነበርንበት ጊዜ ተወዳጅ ልጁን የሰጠን ከሆነ፥ አሁን ልጆቹ ከሆንን በኋላ እነዚህን ታናናሽ ስጦታዎችንስ ጨምሮ አይሰጠንምን?

እነዚህ ሌሎች ስጦታዎች ሁሉ በክርስቶስ የተሰጡን ናቸው። መንፈሳዊ በረከት ሁሉ የሚገኘው በክርስቶስ ነው (ኤፌ. 1፥3)። ከእነዚህ መንፈሳዊ ስጦታዎች ለአንዱ እንኳ ዋጋ መክፈል ይኖርብናልን? በጭራሽ አንከፍልም፤ በክርስቶስ ላመኑ ሁሉ እነዚህ ሁሉ በረከቶች በነፃ የሚሰጡ ናቸው።

ጳውሎስ እንደሚለው እግዚአብሔር ለሚወዱና እንደፈቃዱ ለተጠሩ ሁሉ፤ ክርስቶስን ለእኛ አሳልፎ ሰጠው (ቁ 28)።

እግዚአብሔር ለራሱ ልጅ አልራራም እግዚአብሔር ከእኛ ሰውሮ ሊያስቀር የፈለገው ነገር አልነበረምና ክቡር ስጦታውን ልጁን ሰጥቶናል። ከስጦታዎቹም ጋር ብዙ መንፈሳዊ በረከቶችንም ሰጥቶናል። እግዚአብሔር ከእኛ የሰወረው ምንም ነገር ስለሌለው እኛም ከእርሱ ሰውረን የምናስቀረው ምንም ነገር እንዳይኖር ይጠበቅብናል። ክርስቶስን ለእኛ አሳልፎ እንደሰጠው፥ እኛም ራሳችንንና ያለንን ነገር ሁሉ ለእርሱ አሳልፈን ልንሰጥ ይገባናል።

ይህ ታላቅ እውነት በብሉይ ኪዳን ከተገለጡት በጣም ጠቃሚ ድርጊቶች በአንዱ ምሳሌነት ይቀርባል። ይህም ድርጊት አብርሃም ልጁን ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረቡ ነው (ዘፍ. 22፥1-14)። አብርሃም ልጅ ለማግኘት ብዙ ዓመት ጠበቀ፤ በመጨረሻ ልጁ ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ የመቶ ዓመት ሰው ነበር። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ልጅህን ይስሐቅን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ ብሎ አዘዘው። እስከ ዛሬ ሲጠብቀው የነበረውን ልጁን እንዲገድል ተናገረው ማለት ነው። ይሁን እንጂ፥ አብርሃም እግዚአብሔርን ታዘዘ፣ ይስሐቅንም ለመሠዋት ተዘጋጀ። አብርሃም ልክ ልጁን ሊገድል ሲል እግዚአብሔር አቆመው፤ በይስሐቅም ምትክ አንድ የበግ ሙክት አዘጋጀ። እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "አንተ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሰው መሆንህን አውቄአለሁ፤ አንዱን የገዛ ልጅህን ከእኔ ሰውረህ ለማስቀረት አላሰብክም» (ዘፍ. 22፥12)። እግዚአብሔር ልጁን እንዲሠዋለት አብርሃምን የጠየቀው የአብርሃምን እምነትና ታዛዥነት ለመፈተን ነበር። ጥቂት ቆይቶም እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው:- ". አንተ ይህን ስላደረግህና ልጅህንም መሥዋዕት ከማድረግ ስላልተቆጠብህ በእርግጥ እኔ እባርክሃለሁ» (ዘፍ. 22፥15-18)።

እስቲ ራሳችንን እንፈትን፤ እስከ ዛሬ ከእግዚአብሔር የሰወርነው ነገር አለን? ለእግዚአብሔር አንሰጥም ብለን የያዝነው በጣም የምንወደውና እጅግ የከበረ ነገር ይኖራልን? ከእግዚአብሔር ይበልጥ እወደዋለሁ የምንለውስ ነገር ይኖረን ይሆን? ለምሳሌ እንደ ሀብት፥ እንደ ቤተሰብ፥ እንደ ዝና የመሰለ ነገር ይኖር ይሆን? እግዚአብሔር በስተጀርባው ያስቀረብን ነገር ምንም የለውም፤ እኛም የአብርሃምን ምሳሌ በመከተል ከእግዚአብሔር ምንም የምንሰውረው ነገር አይኑር (ዕብ. 11፥17-19)፡፡

በጣም የምንወደውን ነገር ለእግዚአብሔር በምናቀርብበት ጊዜ ምን ይሆናል? ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር መልሶ ይሰጠናል። እኛ አሳልፈን መስጠታችንን ካየ በኋላ ልክ አብርሃም ይስሐቅን ይዞት እንደቀረ ሁሉ እኛንም ይዘናቸው እንድንቀር ያደርገናል።

ቁ. 33 ሰይጣን በእኛ ላይ የፈለገውን ክስ ማቅረብ ይችላል፤ ይሁን እንጂ ሊፈርድብን አይችልም። ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት ያላቸው አሁን ኩነኔ (ፍርድ) የለባቸውም (ቁ. 1)። እውነት ነው፥ በዚህ ዓለም ሰዎች ሊፈርዱብን ይችላሉ፤ ነገር ግን በክርስቶስ ላሉት ሁሉ በሰማይ ያ ፍርድ ይሰረዛል። ጳውሎስ ፍርድ የለባቸውም ሲል እርሱ የሚናገረው ስለሰማይ ነው እንጂ ስለ ምድር አይደለም።

ቁ. 34 የሚፈርድስ ማን ነው? በመጨረሻ ማንም አይደለም። ምክንያቱም ሰይጣን በእኛ ላይ የሚያቀርበውን ክስ እግዚአብሔር አይሰማውም። እግዚአብሔር የሚሰማው ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ሲሆን፤ እርሱ በእግዚአብሔር ቀኝ ሆኖ ለእኛ የሚማልድልንና ጠበቃችን ነው (ኤፌ. 1፥20-23)።

ቁ. 35 ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ማን ነው? ማንም የለም! ከኃጢአት በቀር (ቁ. 38-39)። በዚህ ሕይወታችን ከሚያጋጥመን ነገር ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለነውን ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም የለም። በዚህ ጥቅስ ላይ ጳውሎስ ችግርና ስደት ጨርሰው አይደርሱብንም አይደለም የሚለው። የእርሱ አባባል እነዚህ ሁሉ ነገሮች ክእግዚአብሔር ፍቅር ሊለዩን አይችሉም ነው።



ይቀጥላል...



ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ ፤ ገጽ 370




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍81
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።”
           ዕንባቆም 3፥19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት 1.pdf
1.5 MB
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ያመለጠው የይሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰድዳል፥ ወደ ላይም ያፈራል።”
             2ኛ ነገሥት 19፥30




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
ከሐሰተኛ ነቢያት፣ ሐዋርያት. . . አስተማሪዎች ለመጠበቅ ምን እናድርግ? (ከይሁዳ መልእክት)



👉የእግዚአብሔርን ቃል ማሰብ፣ ማስታወስ

"እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤" (ቁ. 17)


👉በሃይማኖት ለማደግ፣ ለመጠንከር፣ ለመጎልበት፣ ለመታነጽ መትጋት

"እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ" (ቁ. 20)


👉 በመንፈስ ቅዱስ የሚመራን ጸሎት መጸለይ

"በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ" (ቁ. 20)


👉 በእግዚአብሔር ምሕረት እየተደገፍን የዘላለምን ሕይወት ለመውረስ መጠባበቅ

"ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ" (ቁ. 21)

👉 በእግዚአብሔር ፍቅር ራስን መጠበቅ

"በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ" (ቁ. 21)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን የሙሴን ሕግ አስቡ።”
           ሚልክያስ 4፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን ባስጨነቋቸው መጠን የእስራኤላውያን ቍጥር በዛ፤ በምድሪቱም እየተስፋፉ ሄዱ፤ ከዚህም የተነሣ ግብፃውያኑ እስራኤላውያንን እጅግ ፈሯቸው፤”
               ዘጸአት 1፥12 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
የዘንባባ ባህርያት


“ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።”
መዝሙር 92፥12

👉 በአውሎንፋስ አይሰበርም። ንፋስን ዝቅ ብሎ ያሳልፋል

👉 ስሩን ወደታች በጥልቀት ይሰዳል

👉 ቀጥ ብሎ ነው የሚያድገው

👉 በድርቅ አይጠቃም

👉 ቅጠሉ ዓመቱን በሙሉ አረንጓዴ ነው

👉 ከሌሎች ዘንባባዎች ጋር መዳቀል አይችልም

👉 የማያቋርጥ እድገት አለው

👉 ፍሬው አይበላሽም



ምንጭ፦ https://www.faithwriters.com/article-details.php?id=120686

https://www.tblfaithnews.com/faith-religion/palm-trees-do-you-have-the-character-that-they-do



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5🔥2
የጥምቀት በዓልን ለምታከብሩ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3