' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።”
ዮሐንስ 3፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤2
በመጽሐፍ ቅዱስ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስጦታ ይዘው የመጡት ሰብአ ሰገል ቁጥራቸው ስንት ነው
Anonymous Quiz
51%
ሀ. 3
11%
ለ. 7
1%
ሐ. 10
5%
መ. 12
32%
ሠ. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቁጥራቸው አልተጠቀሰም
👍9
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤”
ገላትያ 4፥4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤”
ገላትያ 4፥4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ምድርም ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች። የምድርን ጥልቅ ስፍራ ሁሉ ጨለማ ውጦት ነበር። የእግዚአብሔርም (ኤሎሂም) መንፈስ በውሆች ላይ ይረብብ ነበር።”
ዘፍጥረት 1፥2 (አዲሱ መ.ት)

👍2❤1
የገና በዓል ታሪካዊ አመጣጥ
ክፍል-፪
በጳውሎስ ካሱ
🎄የገና በዓል አመጣጥ🎄
ድሮ ሰዎች ፀሐይ አምላክ ናት ብለው ያምኑና ያመልኳት ነበር፡፡ ክረምት የሚመጣውም ፀሐይ ስትታመም ወይም ስትደክም ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ በምድራችን በሰሜን ንፍቀ ክበብ አካባቢ አጭር የሚባለው ቀን የሚውለው እ.ኤ.አ. በዲሴምበር (ታኅሣሥ) 21 ወይም 22 ነው፡፡ ይህንንም ጊዜ የክረምት ሶልስቲስ ይሉታል (ፀሐይ የድካሟ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የምትደርስበት ማለት ነው)፡፡ ፀሐይ ከመጨረሻ ድካሟ በኋላ ወደ ቀድሞ ጥንካሬዋ ስለምትመለስ ይህ ወቅት በልዩ ሁኔታ ይከበር ነበር፡፡ ይህ በዓል በተለያዩ አገሮች በተለያየ ሁኔታ ይከበር ነበር፡፡ ለምሳሌ ግብፃውያን ራ ብለው የሚጠሩት ፀሐይን እንደ ኮፍያ ያጠለቀ አምላካቸውን የሚያስቡበትና የሚያከብሩበት በዓል ሲሆን፣ የጥንት ሮማውያን ደግሞ ሳተርን የሚሉትን የእርሻ አምላክ ለማክበር በዓሉን ሳቱርናሊያ (Saturnalia) ብለው ያከብሩ ነበር፡፡ ቀጥሎ የሚመጣውን አረንጓዴነት በማሰብም ቤተ መቅደሳቸውንና ቤታቸውን በአረንጓዴ ዕፀዋት ያስጌጡ ነበር፡፡
ለዛሬው ገና ዋና መሠረቱ የሮማ አረማውያን ሳቱርናልያ የሚባለውና ከዲሴምበር (ታኅሣሥ)17 እስከ 25 የሚቆይው የአንድ ሳምንት ሕግ አልባ ክብረ በዓል ነው። በዚህ ሳምንት የሮማ ፍርድ ቤቶች በሙሉ ይዘጉ ነበር፡፡ የሮማ ሕግም በዚህ ሳምንት ውስጥ ንብረት ያጠፋም ሆነ ሰው ያቆሰለ እንደማይቀጣ ይደነግጋል፡፡ ሳምንት የሚቆየው በዓል የሚጀምረው የሮማ ባለሥልጣኖች የሮማውያን ጠላት ብለው የሚሰይሙትና የመጥፎ መንግሥት ጌታን የሚወክለውን ሰው/ሰዎች ከመረጡ በኋላ ነው፡፡ እነዚህ የሚመረጡት ሰዎች ምንም ጥፋት ያላጠፉ ንፁኃን ሰዎች ነበሩ። እያንዳንዱ የሮማ ማኅበረሰብ የየራሱን የሮማውያን ጠላት ይመርጥና ሳምንቱን ሙሉ እነዚህን ንፁኃን ሰዎች ከመጠን በላይ እንዲበሉ፣ እንዲጠጡና እንዲዳሩ ያስገድዷቸዋል፡፡ ሮማውያኑም በዓሉን የሚያከብሩት ከመጠን በላይ በመብላት፣በመጠጣት፣በመዳራትና በመዋጋት ነበር። በበዓሉ የመጨረሻ ቀንም ማለትም ዛሬ የክርስቶስ የልደት ቀን ነው ተብሎ በሚታመንበት ዲሴምበር 25 እነዚህን ሳምንቱን ሙሉ የተሰቃዩ ንፁኃን ወንዶችና ሴቶች በመግደል ሮማውያን ጠላቶቻቸውን እንዳጠፉ በመቁጠር ይኩራሩ ነበር፡፡
ሉሲያን (Lucian) የተባለ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊና ባለቅኔ በጊዜው የሳቱርናልያ በዓል በግሪክ እንዴት ይከበር እንደነበር ሲጽፍ እንደ ሮማውያኑ ሰዎችን ከመሰዋት በተጨማሪ ከቅጥ ያለፈ መጠጥ ወይም ስካር፣ እርቃን ሆኖ ከቤት ቤት እየሄዱ መዝፈን (እንደ ኢትዮጵያውያን እንቁጣጣሽና ሆያ ሆዬ)፣ ሴቶችን መድፈርና ሌሎች የልቅ ወሲብ ድርጊቶችና በሰው ቅርፅ የተሠሩ ብስኩቶችን መብላት (እነዚህ ብስኩቶች አሁንም በገና ወቅት በእንግሊዝና በጀርመን ይዘጋጃሉ) የበዓሉ ዋና ገጽታዎች እንደነበሩ ገልጿል፡፡
በአራተኛው ክፍለ ዘመን የቤተክርስቲያን መሪዎች እነዚህን አረማውያን አባል ለማድረግ በማሰብ ክርስትናን ከተቀበሉ በኋላም ሳቱርናልያን ማክበር መቀጠል እንደሚችሉ በማሳመን የክርስትናን እምነት እንዲቀበሉና ሳቱርናልያና ወደ ቤተክርስቲያን ይዘው እንዲገቡ ፈቀዱላቸው፡፡ ሆኖም ሳቱርናልያንና ክርስትናን የሚያገናኛቸው አንድም ነገር አልነበረም፡፡ ይህን ችግር ለመፍታትና ሳቱርናልያን ክርስቲያናዊ ለማስመሰል የወቅቱ የቤተክርስቲያን መሪዎች የሳቱርናልያን የመዝጊያ ቀን (ዲሴምበር 25) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን ብለው በመሰየም በዓሉ እንዲቀጥል አደረጉ። ሳቱርናልያም ክሪስማስ (ገና) ተባለ፡፡የሚያሳዝነው እነዚህ የስመ ክርስቲያን መሪዎች በበዓሉ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ለውጥ ለማድረግ አለመቻላቸው ነው፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት ይህ ‹‹የክርስቶስ ልደት ቀን›› የሚከበረው ልክ እንደ ሳቱርናልያ በመጠጣት፣ በመዳራትና፣ በራቁት የጎዳና ላይ ዳንስ (የክሪስማሰ ካሮል መሠረቱ ይኼ ነው) ነበር፡፡
ኢንከሪዝ ማዘር የተባሉ አሜሪካዊ በ1687 ዓ.ም. ባሳተሙት ጽሑፍቸው ላይ ‹‹ዲሴምበር 25ን የክርስቶስ የልደት ቀን ነው ብለው ማክበር የጀመሩት ክርስቲያኖች ቀኑን የሚያከብሩት ክርስቶስ በዚህ ቀን ተወልዷል በሚል እምነት ላይ ተመሥርተው አልነበረም፡፡ የአረማውያኑ ሳቱርናልያ የሚከበረው በተመሳሳይ ወቅት ስለነበረ በዓሉ ወደ ቤተ ክርስቲያን አንዲገባ ፍቃደኛ ስለሆኑ ብቻ ነበር፤›› በማለት አብራርተዋል፡፡ በዚሁ ግልጽ የሆነ አረማዊ መሠረቱ ምክንያት ቀደም ባሉት ጊዜያት በአንዳንድ አክራሪዎች ዘንድ የገናን በዓል ማክበር በሕግ የተከለከለ ነበር፡፡
አንዳንድ አፀያፊ የሳቱርናልያ አከባበር ገጽታዎች በጥንቷ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አማካይነት በ1466 ዓ.ም. አንደ አዲስ አንዲከበሩና ዕውቅና እንዲያገኙ እንደተሞከረ አንዳንድ የታሪክ ምንጮች ይጠቅሳሉ፡፡ ለምሳሌ በ1466 ዓ.ም. የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ሁለተኛው ጳውሎስ የሮማን ዜጎች ለማስደሰት ሲል አይሁዶች እርቃናቸውን በጎዳና እንዲሮጡ ማድረግ እንደጀመረ የታሪክ ማስረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሩጫውን ከባድ ለማድረግና ሕዝብን የበለጠ ለማሳቅ ሲባልም ሯጮቹ ከመጠን በላይ እንዲመገቡ ይደረግ እንደነበር እነዚሁ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ ጳጳሱም ከሕዝቡ ጋር ተቀምጦ በሩጫው ይስቅ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ ዛሬ ‹‹የክርስቶስ ልደት›› እየተባለ የሚከበረው በዓል መሠረቱ ይኼ ነው፡፡
የገና ዛፍ፣ የገና ስጦታዎች አመጣጥና የገና አባት...
ይቀጥላል...
ምንጭ:- ethiopianreporter.com

👍7❤1🔥1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ጌታም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ቢሰጥህም አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፤ ዓይኖችህ ግን አስተማሪህን ያያሉ፥”
ኢሳይያስ 30፥20

❤3
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ምሳሌ 27
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ቀን የሚያመጣውን ምን እንደ ሆነ አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ።
² ሌላ ያመስግንህ እንጂ አፍህ አይደለም፤ ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይደለም።
³ ድንጋይ ከባድ ነው አሸዋም ሸክሙ ጽኑ ነው፤ ከሁለቱ ግን የሰነፍ ቍጣ ይከብዳል።
⁴ ቍጣ ምሕረት የሌለው ነው፥ መዓትም እንደ ጎርፍ ነው፤ በቅንዓት ፊት ግን ማን ይቆማል?
⁵ የተገለጠ ዘለፋ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።
⁶ የወዳጅ ማቍሰል የታመነ ነው፤ የጠላት መሳም ግን የበዛ ነው።
⁷ የጠገበች ነፍስ የማር ወላላ ትረግጣለች፤ ለተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር ሁሉ ይጣፍጣታል።
⁸ ስፍራውን የሚተው ሰው ቤቱን ትቶ እንደሚበርር ወፍ ነው።
⁹ ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤ እንዲሁ ነፍስ በወዳጁ ምክር ደስ ይላታል።
¹⁰ ወዳጅህንና የአባትህን ወዳጅ አትተው፤ በመከራህም ቀን ወደ ወንድምህ ቤት አትግባ፤ የቀረበ ወዳጅ ከራቀ ወንድም ይሻላል።
¹¹ ልጄ ሆይ፥ ጠቢብ ሁን፥ ልቤንም ደስ አሰኘው፥ ለሚሰድበኝ መልስ መስጠት ይቻለኝ ዘንድ።
¹² ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፤ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይጐዳሉ።
¹³ ለማያውቀው ከተዋሰ ሰው ልብሱን ውሰድ፥ ለእንግዳ የተዋሰውንም እርሱን አግተው።
¹⁴ ባልንጀራውን በታላቅ ቃል ማለዳ የሚባርክ ሰው እንደሚራገም ያህል ነው።
¹⁵ በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው፤
¹⁶ እርስዋንም መከልከል ነፍስን መከልከልና ዘይትን በቀኝ እጅ መጨበጥ ነው።
¹⁷ ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን ይስላል።
¹⁸ በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።
¹⁹ ፊት በውኃ ላይ ለፊት እንደሚታይ፥ እንዲሁ የሰው ልብ ለሰው ይታያል።
²⁰ ሲኦልና ጥፋት እንዳይጠግቡ፥ እንዲሁ የሰው ዓይን አይጠግብም።
²¹ ብር በከውር ወርቅም በማቅለጫ ይፈተናል፤ ሰውም በሚያመሰገኑት ሰዎች አፍ ይፈተናል።
²² ሰነፍን በሙቀጫ ውስጥ ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠው፥ ስንፍናው ከእርሱ አይርቅም።
²³ የበጎችህን መልክ አስተውለህ እወቅ፥ በከብቶችህም ላይ ልብህን አኑር፤
²⁴ ባለጠግነት ለዘላለም አይኖርምና፥ ዘውድም ለትውልድ ሁሉ አይጸናምና።
²⁵ ደረቅ ሣር በታጨደ ጊዜ፥ አዲስ ለምለም በታየ ጊዜ፥ ከተራራውም ቡቃያ በተሰበሰበ ጊዜ፥
²⁶ በጎች ለልብስህ ፍየሎችም የእርሻ ዋጋ ይሆናሉ።
²⁷ ለሲሳይህ ለቤተ ሰቦችህም ሲሳይ ለገረዶችህም ምግብ የፍየል ወተት ይበቃል።

👍5❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል።”
ምሳሌ 14፥15
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል።”
ምሳሌ 14፥15
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤4👍1
የገና በዓል ታሪካዊ አመጣጥ
ክፍል-፫
በጳውሎስ ካሱ
🎄የገና ዛፍ፣ 🎁የገና ስጦታዎች አመጣጥና
🎅የገና አባት
ልክ እንደ በዓሉ ሁሉ የገና ዛፍ፣ ስጦታና የገና አባት መሠረታቸው አረማውያን ናቸው፡፡
🎄የገና ዛፍ
ከሳቱርናልያ ተከታዮች ጋር በገፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን ከገቡትና ልማዳቸው ክርስቲያናዊ ከተደረገ አረማውያን መካከል የአሸይራ (Asheira) አምላኪዎች ይገኙበታል፡፡ የዛፎች አምልኮ የቆየ ነው፡፡ በቅድመ ክርስቶስ ዘመን አህዛብ በተለይ ትላልቅና ዓመቱን ሙሉ አረንጓዴ እንደሆኑ ለሚቆዩ ዕፀዋት ልዩ ትርጉም ይሰጧቸውና ያመልኳቸው ነበር፡፡ እርኩሳት መናፍስትን፣ አስማተኞችን፣ በሽታን የመሳሰሉትን ይከላከሉ ብለው ስለሚያምኑ ቅርንጫፎቻቸውን እየቆረጡ በበራቸው ላይ ወይም በቤታቸው ውስጥ ይሰቅሉ ነበር፡፡ አይሸራውያን እንደ ብዙ አረማውያን በደን ውስጥ ያሉ ትላልቅ ዛፎችን ያመልኩ የነበረ ሲሆን ምሳሌዎቻቸውን (ቅርንጫፎቻቸውን) ወደ ቤታቸው በማምጣት ያስጌጧቸው እንደነበረና እነዚህም ቅርጫፎች እርኩሳት መናፍስትን ይከላከላሉ የሚል እምነት እንደነበራቸው ታሪክ ይጠቁማል፡፡ ልክ እንደ ሳቱርናልያ ልማዶች ይህም ልማድ የክርስትና ስም ተሰጥቶት ቤተ ክርስቲያን ገባ፡፡
🎁የገና ስጦታዎች አመጣጥ
በቅድመ ክርስትና ሮም ቄሳሮች በሳቱርናልያ በዓል ወቅት የተናቁ ተገዥዎቻቸው መስዋትና ስጦታ እንዲያመጡላቸው ያስገድዱ ነበር፡፡ በኋላ ላይም ይህ ግዴታ በሕዝቡ መካከል ተሠራጭቶ እንደ መልካም ልማድ ተቀባይነት ስላገኘ በሳቱርናልያ በዓል ወቅት ሕዝቡ ስጦታ መለዋወጥ ጀመረ። የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ልማድ ቅዱስ ኒኮላስ ይሰጥ ነበር ከሚባለው አፈ ታሪካዊ ስጦታ ጋር በማያያዝ ክርስቲያናዊ አደረጋቸው፡፡
🎅የገና አባት
በ19ኛ ክፍለ ዘመን በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ‹‹ቅዱስ›› የሚል ማዕረግ የተሰጠው በ270 ዓ.ም. በቱርክ እንደተወለደ በቱርክ ሊቀጳጳስ እንደነበረና ታኅሣሥ 6፣345 ዓ.ም. እንደ ሞተ የሚነገርለት ኒኮላስ የተባለ ሰው አለ፡፡ ኒኮላስ በ325 ዓ.ም. በተደረገው የኒቅያ ጉባዔ ላይ ከተገኙ ሊቀጳጳሶች አንዱ እንደ ነበር የታሪክ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ በ1087 ዓ.ም. ለኒኮላስ ከፍተኛ አክብሮት የነበራቸው መርከበኞች አጽሙን ከቱርክ ወደ ጣሊያን ወስደው ቤሪ በተባለች ስፍራ በሚገኝ መቅደስ ውስጥ አስቀመጡት፡፡ ቀደም ብላ በዚህ መቅደስ ውስጥ የነበረችው ለሕፃናት ስጦታ ትሰጣለች የሚል ታሪክ ያላት ኢፊፋበያ የተባለችው የአረማውያን አማልክትም ከመቅደሱ ተወግዳ በኒኮላስ ተተካች፡፡ ኒኮላስም መቅደሷንም ታሪኳንም ወረሰ፤ ቦታውም የኒኮላስ አምላኪዎች መሀከል ሆነ፡፡ የኒኮላስ ተከታዮች በየዓመቱ ታኅሣሥ 6ን ሲያከብሩ ስጦታ ይለዋጡ ነበር፡፡ የኒኮላስ አምልኮ በሰሜን እየተስፋፋ በጀርመን አረማውያን ተቀባይነት አገኘ፡፡ እነዚህ የጀርመን አረማውያን ዋደን የተባለ ነጭ ፂም ያለውና በዓመት አንድ ጊዜ በሰማይ ውስጥ በፈረስ እንደሚጋልብ የሚነገርለት አምላክ ያመልኩ ነበር፡፡ ለዚህ አምላክ የተፈጠረው ታሪክ ሁሉ ለኒኮላስ ተሰጠ፡፡ ቀደም ብላ እንዳደረገችው አረማውያኑን ለመሳብ ብላ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የኒኮላስን አምላኪዎች ተቀብላ ታሪኩንም እውነት ነው ብላ በማስተማር ስጦታ ከታኅሣሥ 6 ይልቅ በታኅሣሥ 25 እንዲሆን ማስተማር ጀመረች፡፡ የስፓኝ ስሙ ሳንታ ክላውስ (Santa Claus) የበለጠ ዕውቀና እያገኘ መጣ፡፡ አዳዲስ የፈጠራ ታሪኮች ተጨመሩለት፡፡ በ1931 ዓ.ም. የኮካ ኮላ ኩባንያ በሠራው ማስታወቂያ ላይም ሳንታ ቀይ ፀጉራም ልብስ የለበሰ ነጭ ፂም ያለው ወፍራም ሰውዬ ሆኖ ቀረበ፡፡ ይህ ሳንታም ሊቀ ጳጳስ፣ የአረማውያን አምላክና የንግድ ማስታወቂያ ሆኖ እስከ ዛሬ ቀጥሏል፡፡
የገና በዓል ብዙ ደጋፊዎች ያሉት በዓል ነው፡፡ ደጋፊዎች በሦስት ይከፈላሉ፡፡ የመጀመርያዎቹ በዓሉ መጸሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው በዓል ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው (ከልባቸውም ይሁን ከአፋቸው)፡፡ ሁለተኛዎቹ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ባይኖረውም የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ እውነት እስከሆነ ድረስ ልደቱን ማክበሩ ክፋት የለውም ብለው የሚያምኑ ናቸው፡፡ ሦስተኛው አካል የሚከራከረው በዓሉ ለንግድና ቤተሰቦችን/ሰዎችን በማቀራረብ ካለው ጠቀሜታ አኳያ ነው፡፡
ተፈፀመ

👍3
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው አሙት፦ እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድን ያሰናዳ ዘንድ ይችላልን?”
መዝሙር 78፥19

👍3❤1
የእውነተኛ ደቀ መዝሙር ባህርያት
በአለማችን ላይ እውነተኛ ደቀመዛሙርቶች አሉ፡፡ የስም ብቻ ደቀመዛሙርቶች ደግሞ አሉ፡፡ እውነተኛ ደቀመዝሙር የሚያደርገን ምን እንደሆነ ማወቅ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡ የእውነተኛ ደቀመዝሙርነት መንገድ ላይ መሆናችንን ማወቅ ህይወታችንን በከንቱ እንዳናባክነው ያደርገናል፡፡ እውነተኛ ደቀመዝሙርነታችን እውነተኛ ነፃነት ውስጥ ያስገባናል፡፡
"ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፦ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።" ዮሐንስ 8፡31-32
የእውነተኛ ደቀመዝሙርነት መለያ መፅሃፍ ቅዱሳዊ መስፈርቶች
👉ጌታ ኢየሱስን ከሁሉም ነገር በላይ መውደድ
ኢየሱስን ከአባቱና ከእናቱን ከሚስቱም ከልጆቹም በላይ መውደድ አለበት፡፡ ከኢየሱስ በላይ የምንወደው ምንንም ነገር ካለ እውነተኛ ደቀመዛሙርት አልሆንም ማለት ነው፡፡
"ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።" ሉቃስ 14፡26
👉ራስን መካድ – ቃሉን ማስቀደም ትህትናና በእግዚአብሄር ፊት መዋረድ
እውነተኛ ደቀመዝሙርነት የሚለየው ራስን በመካድ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ከነፍሳችን ፍላጎትና ጥቅም በላይ ማስቀደም ራስን መካድ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ለመጠበቅ ብለን ጥቅማችንን የምንተው ከሆነ ራሳችንን ክደናል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለመታዘዝ ነፍሳችንን የምንክድ ከሆንን እውነተኛ የኢየሱስ ተከታዮች ነን፡፡
"ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።" ሉቃስ 9፡23
👉ፍቅር – ከራስ ወዳድነት የፀዳ ህይወት
ደቀመዝሙር እግዚአብሄር የሚወደውን ሁሉ ይወዳል፡፡ እግዚአብሄር ሰዎችን ሁሉ እንደሚወድ ሁሉ የኢየሱስ ደቀመዝሙር ሰዎችን ሁሉ ይወዳል፡፡ የሚጠላው ሰው ያለው ሰው እውነተኛ የኢየሱስ ደቀመዝሙር አይደለም፡፡
"እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።" ዮሐንስ 13፡35
👉በእግዚአብሄር መደገፍና መታመን
እውነተኛ ደቀመዝሙር ስለሁሉም ነገር በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ አለበት፡፡ ባለው በምንም ነገር ላይ የሚደገፍ ሰው የኢየሱስ ደቀመዝሙር ሊሆን አይችልም፡፡ ደቀመዝሙር ስለሁሉም ነገሩ በእግዚአብሄር ላይ በመታመን እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡
"እንግዲህ እንደዚሁ ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።" ሉቃስ 14፡33
👉በእግዚአብሄር ድምፅ እለት እለት መመራት
እውነተኛ ደቀመዝሙር የራሱን ነገር አድርጎ አንዳንዴ እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሳይሆን ለህይወቱ እለት እለት የእግዚአብሄርን ምሪት የሚፈልግ ነው፡፡ ደቀመዝሙር ከእግዚአብሄር ጋር የአባትና የልጅ ግንኙነት ያለውና እግዚአብሄርን ለማስደሰት ራሱ የሰጠ ነው፡፡
"በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤" ዮሃንስ 10፡27
👉ከኑሮ ፍርሃት እስራት መውጣት
በኑሮ ፍርሃት የሚወጣና የሚገባ ሰው እውነተኛ የኢየሱስ ደቀመዝሙር አይደለም፡፡ እውነተኛ የኢየሱስ ደቀመዝሙር የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስት ይፈልጋል፡፡ ሌላውን ሁሉ እንደሚጨመርለት ያውቃል፡፡ ሰው ለጌታም ለገንዘብም መገዛት ስለማይችል ገንዘብ የሚገዛው ሰው እውነተኛ የኢየሱስ ደቀመዝሙትር ሊሆ አይችልም፡፡
"የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል።" ማርቆስ 4፡19
👉ብዙ ፍሬን ማፍራት
እውነተኛ ደቀመዝሙር የሆነ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል በመኖር ለእግዚአብሄር ቤተክርስትያን በሁሉ ጠቃሚ ሲሆን ይታያል፡፡ ደቀመዝሙር ከክርስትያን እህቶችና ወንድሞች ጋር በፍቅር ይኖራል፡፡
"ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።" ዮሐንስ 15፡8
👉ክርስቶስን ይመስላል
እውነተኛ ደቀመዝሙር ትህትናው ፣ ትግስቱ ፣ የዋህነቱ ባህሪው ሁሉ ስለ እርሱ ይመሰክራል፡፡
"የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።" ገላትያ 5፡22
👉ደቀመዝሙር ያፈራል
እውነተኛ ደቀመዝሙር በንፁህ የህይወት ምስክርነቱና የወንጌል ስብከት አገልግሎቱ ሌሎችን ደቀመዛሙርት ያፈራል፡፡
"እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።" ማቴዎስ 28፡19-20
ምንጭ:- አብይ ዋቁማ ዲንሳ

👍9❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“አሁንም፣ ተነሣና በእግርህ ቁም፤ ስለ እኔ ስላየኸውና ወደ ፊትም ስለማሳይህ ነገር አገልጋይና ምስክር እንድትሆን ልሾምህ ተገልጬልሃለሁ።”
ሐዋርያት 26፥16 (አዲሱ መ.ት)

#እራሳችንን_እንመርምር
እግዚአብሔርን መጠበቅ ላይ እንዴት ነን? መጠበቅስ ምን ማለት ነው? ምን እያደረግን እግዚአብሔርን እንጠብቅ? እግዚአብሔርን መጠበቅ ምን ያመጣልናል? ከመጠበቅ ይልቅ መወራጨቱስ ትርፍ ይኖረው ይሆን?
“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
ኢሳይያስ 40፥31

❤3👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ፤”
ቆላስይስ 2፥6

👍6❤1
የኢየሱስ ምሣሌያዊ አስተምህሮዎች.pdf
3.7 MB
✍ርዕስ፦የኢየሱስ ምሳሌያዊ አስተምህሮዎች፣ የመንግሥተ ሰማይ ምስጢራት መፍቻ
👤ጸሐፊ፦ጄ. ድዋይት(ዶ/ር)
🗣ተርጓሚ፦ አብይ ደምሴ
📑የገጽ ብዛት፦ 180
💾 መጠን፦ 3.7 MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👤ጸሐፊ፦ጄ. ድዋይት(ዶ/ር)
🗣ተርጓሚ፦ አብይ ደምሴ
📑የገጽ ብዛት፦ 180
💾 መጠን፦ 3.7 MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤4👍1
የቀጠለ...
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ከአሸናፊዎች እንበልጣለን (8:31-39)
ቁ. 31 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፥ ማን ሊቃወመን ይችላል? ሰይጣን ይቃወመናል፤ በመጨረሻ ግን እውነተኛን አማኝ ተቃውሞ ሊያሸንፈው አይችልም።
ቁ. 32 እግዚአብሔር ብዙ አስደናቂ ስጦታዎችን ሰጥቶናል። ጸጋ፥ ፍቅር፥ ደስታ፥ ይቅርታ፥ ደኅንነት፥ በሰማይ ያለን ውርስ፥ ከስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ስጦታ የሆነው ግን ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ገና የእግዚአብሔር ጠላቶች በነበርንበት ጊዜ ተወዳጅ ልጁን የሰጠን ከሆነ፥ አሁን ልጆቹ ከሆንን በኋላ እነዚህን ታናናሽ ስጦታዎችንስ ጨምሮ አይሰጠንምን?
እነዚህ ሌሎች ስጦታዎች ሁሉ በክርስቶስ የተሰጡን ናቸው። መንፈሳዊ በረከት ሁሉ የሚገኘው በክርስቶስ ነው (ኤፌ. 1፥3)። ከእነዚህ መንፈሳዊ ስጦታዎች ለአንዱ እንኳ ዋጋ መክፈል ይኖርብናልን? በጭራሽ አንከፍልም፤ በክርስቶስ ላመኑ ሁሉ እነዚህ ሁሉ በረከቶች በነፃ የሚሰጡ ናቸው።
ጳውሎስ እንደሚለው እግዚአብሔር ለሚወዱና እንደፈቃዱ ለተጠሩ ሁሉ፤ ክርስቶስን ለእኛ አሳልፎ ሰጠው (ቁ 28)።
እግዚአብሔር ለራሱ ልጅ አልራራም እግዚአብሔር ከእኛ ሰውሮ ሊያስቀር የፈለገው ነገር አልነበረምና ክቡር ስጦታውን ልጁን ሰጥቶናል። ከስጦታዎቹም ጋር ብዙ መንፈሳዊ በረከቶችንም ሰጥቶናል። እግዚአብሔር ከእኛ የሰወረው ምንም ነገር ስለሌለው እኛም ከእርሱ ሰውረን የምናስቀረው ምንም ነገር እንዳይኖር ይጠበቅብናል። ክርስቶስን ለእኛ አሳልፎ እንደሰጠው፥ እኛም ራሳችንንና ያለንን ነገር ሁሉ ለእርሱ አሳልፈን ልንሰጥ ይገባናል።
ይህ ታላቅ እውነት በብሉይ ኪዳን ከተገለጡት በጣም ጠቃሚ ድርጊቶች በአንዱ ምሳሌነት ይቀርባል። ይህም ድርጊት አብርሃም ልጁን ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረቡ ነው (ዘፍ. 22፥1-14)። አብርሃም ልጅ ለማግኘት ብዙ ዓመት ጠበቀ፤ በመጨረሻ ልጁ ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ የመቶ ዓመት ሰው ነበር። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ልጅህን ይስሐቅን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ ብሎ አዘዘው። እስከ ዛሬ ሲጠብቀው የነበረውን ልጁን እንዲገድል ተናገረው ማለት ነው። ይሁን እንጂ፥ አብርሃም እግዚአብሔርን ታዘዘ፣ ይስሐቅንም ለመሠዋት ተዘጋጀ። አብርሃም ልክ ልጁን ሊገድል ሲል እግዚአብሔር አቆመው፤ በይስሐቅም ምትክ አንድ የበግ ሙክት አዘጋጀ። እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "አንተ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሰው መሆንህን አውቄአለሁ፤ አንዱን የገዛ ልጅህን ከእኔ ሰውረህ ለማስቀረት አላሰብክም» (ዘፍ. 22፥12)። እግዚአብሔር ልጁን እንዲሠዋለት አብርሃምን የጠየቀው የአብርሃምን እምነትና ታዛዥነት ለመፈተን ነበር። ጥቂት ቆይቶም እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው:- ". አንተ ይህን ስላደረግህና ልጅህንም መሥዋዕት ከማድረግ ስላልተቆጠብህ በእርግጥ እኔ እባርክሃለሁ» (ዘፍ. 22፥15-18)።
እስቲ ራሳችንን እንፈትን፤ እስከ ዛሬ ከእግዚአብሔር የሰወርነው ነገር አለን? ለእግዚአብሔር አንሰጥም ብለን የያዝነው በጣም የምንወደውና እጅግ የከበረ ነገር ይኖራልን? ከእግዚአብሔር ይበልጥ እወደዋለሁ የምንለውስ ነገር ይኖረን ይሆን? ለምሳሌ እንደ ሀብት፥ እንደ ቤተሰብ፥ እንደ ዝና የመሰለ ነገር ይኖር ይሆን? እግዚአብሔር በስተጀርባው ያስቀረብን ነገር ምንም የለውም፤ እኛም የአብርሃምን ምሳሌ በመከተል ከእግዚአብሔር ምንም የምንሰውረው ነገር አይኑር (ዕብ. 11፥17-19)፡፡
በጣም የምንወደውን ነገር ለእግዚአብሔር በምናቀርብበት ጊዜ ምን ይሆናል? ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር መልሶ ይሰጠናል። እኛ አሳልፈን መስጠታችንን ካየ በኋላ ልክ አብርሃም ይስሐቅን ይዞት እንደቀረ ሁሉ እኛንም ይዘናቸው እንድንቀር ያደርገናል።
ቁ. 33 ሰይጣን በእኛ ላይ የፈለገውን ክስ ማቅረብ ይችላል፤ ይሁን እንጂ ሊፈርድብን አይችልም። ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት ያላቸው አሁን ኩነኔ (ፍርድ) የለባቸውም (ቁ. 1)። እውነት ነው፥ በዚህ ዓለም ሰዎች ሊፈርዱብን ይችላሉ፤ ነገር ግን በክርስቶስ ላሉት ሁሉ በሰማይ ያ ፍርድ ይሰረዛል። ጳውሎስ ፍርድ የለባቸውም ሲል እርሱ የሚናገረው ስለሰማይ ነው እንጂ ስለ ምድር አይደለም።
ቁ. 34 የሚፈርድስ ማን ነው? በመጨረሻ ማንም አይደለም። ምክንያቱም ሰይጣን በእኛ ላይ የሚያቀርበውን ክስ እግዚአብሔር አይሰማውም። እግዚአብሔር የሚሰማው ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ሲሆን፤ እርሱ በእግዚአብሔር ቀኝ ሆኖ ለእኛ የሚማልድልንና ጠበቃችን ነው (ኤፌ. 1፥20-23)።
ቁ. 35 ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ማን ነው? ማንም የለም! ከኃጢአት በቀር (ቁ. 38-39)። በዚህ ሕይወታችን ከሚያጋጥመን ነገር ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለነውን ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም የለም። በዚህ ጥቅስ ላይ ጳውሎስ ችግርና ስደት ጨርሰው አይደርሱብንም አይደለም የሚለው። የእርሱ አባባል እነዚህ ሁሉ ነገሮች ክእግዚአብሔር ፍቅር ሊለዩን አይችሉም ነው።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ ፤ ገጽ 370

👍8❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።”
ዕንባቆም 3፥19