ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
333 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ።”
            ይሁዳ 1፥2




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
paullife-1-cr.pdf
1.7 MB
📚ርዕስ፦ የጳውሎስ ህይወቱና ትምህርቱ
👤ጸሐፊ፦ ሎውስ ብክስቢ
የገጽ ብዛት፦ 114



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍3
paullife-2-cr.pdf
2.1 MB
📚ርዕስ፦ የጳውሎስ ህይወቱና ትምህርቱ
👤ጸሐፊ፦ ሎውስ ብክስቢ
የገጽ ብዛት፦ 114




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በእኔ ደስ ተሰኝተህ ከሆነ፣ አንተን ዐውቅህና ያለ ማቋረጥ በፊትህ ሞገስ አገኝ ዘንድ መንገድህን አስተምረኝ፤ ይህ ሕዝብ የአንተ ሕዝብ መሆኑን አስታውስ።”
             ዘጸአት 33፥13 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
🌟የገና በዓል ታሪካዊ  አመጣጥ


                  ክፍል-፩


                     በጳውሎስ ካሱ

የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በየዓመቱ በደማቅ (በተለየ የአሜሪካና አውሮፓ) ሁኔታ ከሚያከብሯቸው በዓላት አንዱ ገና ነው፡፡የገና በዓል አከባበር በየአገሩ መጠነኛ  ልዩነት ቢኖረውም በየዓመቱ አዳዲስ  መሻሻሎች እየተደረገበት ደማቅነቱ እንደቀጠለ መጥቷል፡፡ 

ይህንኑ ተከትሎም የበዓሉን አጀማመርና ታሪክ ለማግኘት ብዙ ጥናቶች ተደርገዋል:: የጥናቶቹ ግኝትም ብዙዎቹን እርግጥ ይህ በዓል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን? ብለው እንዲጠይቁ ሲያደርግ ብዙዎቹን ግን በዓሉን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማድረግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በመጥቀስ ትክክለኛነቱን ለማሳየት ይሞክራሉ፡፡የተቀሩት ደግሞ  ትኩረታቸውን ከበዓሉ በሚገኘው ደስታ ላይ ብቻ በማድረግ የአያገባኝም አቋም ወስደዋል፡፡ እርግጥ የገና በዓል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው? መልሱ በሚከተሉት የጥናት ግኝቶች ውስጥ ይገኛል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው በእርግጥ በፈረንጆቹ ዲሴምበር 25 ወይም በኢትዮጵያዊያን ታኅሣሥ 29 ነውን? አዲስ ኪዳን ኢየሱሰ ክርስቶስ የተወለደበትን ቀን በትክክል አይናገርም::

ከወንጌላቱ ሁሉ መጀመርያ እንደተጻፈ የሚታመነው የማርቆስ ወንጌል ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ65 ዓ.ም. የተጻፈ ሲሆን፣ ታሪኩን የሚጀምረው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ነው። ይህም የሚጠቁመው የመጀመርያዎቹ ክርስቲያኖች የክርስቶስን የልደት ቀን እንደማያውቁ ለማወቅም ፍላጎት እንዳልነበራቸው ነው፡፡ ይህም አንድ ጥያቄ ማስነሳቱ አልቀረም፤ ክርስቶስ በዲሴምበር 25 ወይም ታኅሣሥ 29 ተወለደ ብሎ የጻፈው ማነው? እንዴትስ አወቀ? ታሪክ እንደሚናገረው ጌታ ተወለደ ተብሎ የሚታመንበትን ዓመት የወሰነው ዲዮኒሲየስ ኤግዚገስ (Dionysisus Exiguus) የተባለ የካቶሊክ መነኩሴ ነው፡፡

ክርስቶስ የተወለደበትን ዓመት ለመወሰን የተጠቀመው ቀመርም የሚከተለውን ይመስላል፡- 

በቅድመ ክርስትና ሮም ዓመታት የሚቆጠሩት "ከአበ አርበ ኮንዲታ" (ab Urbe Condita) ማለትም ሮም ከተመሠረተችበት ቀን ጀምሮ ነው፤ ይህም AUC ይባላል እንደኛ ዓ.ም. ማለት ነው፡፡ ስለዚህ 1 AUC ሮም የተመሠረተችበትን ቀን ይወክላል፡፡ 5 AUC የሮምን ግዛት አምስተኛ ዓመት ይወክላል ወዘተ.

ዲዮኒሲየስ የሮማው ቄሳር አውግስጦስ ለ43 ዓመታት ከገዛ በኋላ በቄሳር ጢባርዩስ ተተካ የሚለውን ታሪክ አምኖ በመቀበል ቀመሩን በዚህ ላይ መሥርቷል፡፡

በሉቃስ ውንጌል ምዕራፍ 3 ቁጥር 1 እና 2 ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ 30 ዓመት ሲሞላው የጢባርዩስ 15ኛ የንግሥ ዓመት እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ በጢባርዮስ ዘመነ መንግሥት 30 ዓመቱ ከሆነ በቄሳር አውግስጦስ አገዛዝ ሥር 15 ዓመት ኖሯል ማለት ነው (ይህም የኢየሱስን ልደት በአውግስጦስ 28ኛ የሥልጣን ዓመት ላይ ያደረገዋል)፡፡

አውግስጦስ የነገሠው በ727 AUC ነው::እዚህ ላይ ተመሥርቶ ዲዮኒሲየስ የክርስቶስ ልደት በ754 AUC ነው ብሎ ደመደመ፡፡ 

መጽሐፍ ቅዱስ በሉቃስ 1፥5 ላይ ክርስቶስ የተወለደው በሄሮድስ ዘመነ መንግሥት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ታሪክ እንደሚናገረው ደግሞ ሄርድስ የሞተው በ750 AUC ነው፡፡ ይህም ዲዮኒሲየስ ክርስቶስ ተወለደ ካለበት አራት ዓመታት ቀደም ብሎ ማለት ነው፡፡ ዮሴፍ ፊትዝመየር የተባሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮፌሰር ይህ የዲዮኒሲየስ ቀመር የተሳሳተ እንደሆነና በዚሁ ቀመር ላይ የተመሠረተው ክርስቶስ የተወለደው በ1 ዓ.ም. (የክርስቲያኖች ዓመት መጀመርያ ተብሎ ከሚታመንበት ዓመት) ነው የሚለው እምነትም የተሳሳተ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ እንደ ፕሮፌሰሩ ጥናት ክርስቶስ የተወለደው ሰፕቴምበር(መስከረም) 11 ክርስቶስ ተወለደ ተብሎ ከሚታመንበት ዓመት 3 ዓመት ቀደም ብሎ ነው፡፡ በማን እንደተጻፈ የማይታወቀውና Depaschg Computus  በመባል የሚታወቅና ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ243 ዓ.ም. በሰሜን አፍሪካ እንደተጻፈ የሚታመን ጽሑፍ ክርስቶስ በፈረንጆቹ ማርች 28 እንደ ተወለደ ይናገራል፡፡ 

ከሊመንት የተባለ የአሌክሳንደሪያ ሊቀ ጳጳስ ደግሞ በ215 ዓ.ም. በጻፈው ጽሑፍ ውስጥ ክርስቶስ ኖቨምበር(ኅዳር) 18 አንደተወለደ እንደሚያምን ገልጿል፡፡
ከተደረጉ ጥናቶች አንዱም እንኳን ክርስቶስ ዲሴምበር 25 ወይም ታኅሣሥ 29 ተወለደ የሚል የለም፡፡ ይህም እነዚህ ቀናት የክርስቶስ ልደት ነው የሚለው እምነት ከየት መጣ የሚለውን ጥያቄ ያስነሳሉ፡፡ የገና በዓል፣ የገና ዛፍና የገና አባት ወዘተ. አንድ ላይ የነበሩና በአንድ ጊዜ የመጡ ጉዳዮች ሳይሆኑ በየዘመናቱ የተጨመሩ ነገሮች ናቸው፡፡


ይቀጥላል...



ምንጭ:- ethiopianreporter.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛን ደግሞ ከኢየሱስ ጋር እንዲያስነሣን ከእናንተም ጋር እንዲያቀርበን እናውቃለንና።”
               2ኛ ቆሮ 4፥14




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
ለምን ተወለደ?



                 በሳምሶን ጥላሁን

‘ለምን ተወለደ?’ የሚለው ጥያቄ የሕይወት ጥያቄ ነው። ሆኖም ግን በአዲስ ኪዳን “ተወለደ” የሚለው ቃል፣ ወልድ ፍጹም ሰው ስለ መሆኑ (ስለ ነገረ ትሥጉት/incarnation) ከሚነግሩን ገለጻዎች አንዱና ዋነኛው ይሁን እንጂ፣ “ብቸኛው” ግን አይደለም። በአዲስ ኪዳን የትሥጉት ነገረ መለኮት በብዙ ቃላት ያሸበረቀ ነው። “ተወለደ” ከሚለው ዕሳቤ በተጨማሪ፣ በአዲስ ኪዳን እኩል አጽንዖት ተሰጥቷቸው የምናገኛቸው ተጨማሪ ነገረ መለኮታዊና ሙያዊ የሆኑ ገለጻዎች አሉ። በእነዚህ ገለጻዎች የነገረ ትሥጉት ግንዛቤያችን ሊዳብር ይገባዋል።
የዚህ ዐጭር ጽሑፍ ዐላማ፣ ስለ ልደቱ (ስለ ገና) በግል በአምልኮ ጊዜ ስናሰላስል ይሁን፣ በኅብረት ስንዘምረው፣ በስብከታችን ስናውጅ ወይም በአስተምህሮ ስናብራራ፣ የዳበረና የፋፋ የነገረ ትሥጉት መረዳት እንዲኖረን ይረዳን ሐሳብ ለማቀበል ነው።
የአዲስ ኪዳን የነገረ ትሥጉት ትርክት በሚከተሉት ቃላት/ሐረጎች ያሸበረቀ ነው፦

👉“ተወለደ” (ሉቃ 2፥10)

👉“ሥጋ ሆነ” (ዮሐ 1፥14)

👉“በመካከላችን ዐደረ” (ዮሐ 1፥14)

👉“ራሱን ባዶ አደረገ”

👉“ተገለጠ” (1ዮሐ 3፥8)

👉“ከሰማይ ወረደ” (ዮሐ 3፥11–13)

👉“ተላከ” (ገላ 4፥4፤ ሮሜ 8፥3)

👉“የባሪያን መልክ ያዘ” (ፊል 2፥5–7)

👉“መጣ” (1ጢሞ 1፥15)

👉“በሥጋና በደም ተካፈለ” (ዕብ 2፥24–25)

👉“በኀጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ” (ሮሜ 8፥3) ወዘተ.

እነዚህን ቃላት/ሐረጎች በሦስት መደብ እናስቀምጣቸው፦

የመጀመሪያው መደብ ተጸንሶ ከመወለዱ አንጻርና እና የሰውን ባሕርይ ሙሉ ገንዘቡ አድርጎ መውሰዱን የሚያስገነዝቡን ናቸው (ተወለደ፣ ሥጋ ሆነ፣ የባሪያን መልክ ያዘ፣ በሰው አምሳል ሆነ፣ በኀጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ…)።

ሁለተኛው መደብ ከሞላ ጎደል፣ ሰው ከመሆኑ በፊት ስለ ነበረው ቅድመ ሕላዌ የሚያስገነዝቡን ናቸው (ከሰማይ ወረደ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፣ ተገለጠ፣ በመካከላችን ዐደረ…)።

ሦስተኛው መደብ ደግሞ የመወለዱን ዐላማ ያሳዩናል (ተላከ፣ መጣ…)።
እነዚህ መደቦች “ለምን ተወለደ?” የሚለውን ጥያቄ የሚመልሱ ሲሆን፣ ነገረ ትሥጉትን እና ነገረ ድነት የተያያዙ መሆናቸውን ያመለክቱናል።

ተወለደ (τίκτω, γεννάω)

“መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፤ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።” (ሉቃ 2፥10–11)።

የገና በዓል በደረሰ ጊዜ፣ ስለ ሕፃኑ ኢየሱስ ከሚመጡልን ምስሎች የተለመደ ሆኖ የሚነገረው፣ “በግርግም የተኛ” ሕፃን የሚለው ነው። ይህ በርግጥ አስደናቂ እውነት ነው። ለዘመናት የሚጠበቀው የምሥራች ቃል አሁን ታወጀ። ምድር ደስ ይበልሽ፤ የዓለም መድኃኒት የሆነ “ሕፃን”፣ እርሱም የዳዊት ልጅ ክርስቶስ ተወልዷልና። የንጋት ጎህ ቀደደ። ተስፋው ተገለጠ።

በመጀመሪያ ይህ “ተወለደ” የሚለው ቃል አስረግጦ የሚያሳየን፣ የሕፃኑ መወለድ በአንድ እጅ አስቀድሞ እግዚአብሔር ከሰጠው የድነት ታሪክ ፍጻሜ ጋር መያያዙን ነው። ለዚህ ነው በሉቃስ ወንጌል ላይ ከክርስቶስ መወለድ ጋር ተያይዞ “ተስፋው ተፈጸመ” የሚለው ዕሳቤ እንደ አዝማች የሚደረደረው።

• የማርያም መዝሙር፤ "ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፣ ለአብርሃምና ለዘሩ ያለውን ለዘላለም ለመጠበቅ ነው።” (ሉቃ 1፥55)፤

• የዘካርያስ ትንቢት፤ “ጥንት በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረው … ይህንም ያደረገው ለአባቶቻችን ምሕረቱን ለማሳየት፣ ቅዱስ ኪዳኑን ለማስታወስ፣ ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሓላ ለማሰብ ...” (1፥72–73)፤

• የስምዖን ባርኮት፤ “ዐይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና”፤
የነቢዪቱ ሐና ስብከት፤ “የኢየሩሳሌምንም መቤዠት ለሚጠባበቁ” ሁሉ ስለ ሕፃኑ ተናገረች፤
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ “ተወለደ” የሚለው ቃል ኢየሱስ ፍጹም ሕፃን ልጅ መሆኑን ያሳየናል፤ “በጥበብና በቁመት፣ በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት” ማደግ ያስፈልገው ነበር። በሰው ስም “ኢየሱስ” ተብሎ ተሰይሟል። ትውልዱ በዳዊትም ቤት ተቆጥሯል። እንደ ማኛውም ሕፃን ጡት ጠብቷል፤ ፊደል ቆጥሯል፤ ተርቧል፤ አልቅሷል...። ሕፃኑ ለዐደጋ ግሉጥ ከመሆኑ የተነሣ፣ ዮሴፍ ወደ ግብፅ ይዞት ሊሰደድ የተገባ ነበር።
የማይወሰነው አምላክ ተወሰነ። ይህ ሕፃን በአንድ እጅ እንደ ማንም ሕፃን እንደ ነበር፣ ደግሞም በሌላ እጅ ‘ልዩ ሕፃን’ ይህም “መለኮታዊ” መሆኑን ማቴዎስ ሲያሳየን፣ “የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነው … እርሱ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋል” ይላል። ይህ ሕፃን ሰው ብቻ ሳይሆን፣ “አዳኝም” ጭምር ነው።
ሉቃስ ደግሞ ይህንን ውጥረት፣ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል” በማለት ሕፃኑን “የእግዚአብሔር ልጅ” ይለዋል (ከመሲሓዊ ስያሜው ባለፈ)። እንዴት ሁለቱ በአንድ ጊዜ እውነት ሆኑ? “ምሥጢር! ምሥጢር!” ብለን ከመጮህ የዘለለ እውቀት የለንም።



ይቀጥላል ...



ምንጭ:- hintset.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።”
            1ኛ ዮሐንስ 4፥9




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ቅዱሳት መጻሕፍት
ለምን ተወለደ?                  በሳምሶን ጥላሁን ‘ለምን ተወለደ?’ የሚለው ጥያቄ የሕይወት ጥያቄ ነው። ሆኖም ግን በአዲስ ኪዳን “ተወለደ” የሚለው ቃል፣ ወልድ ፍጹም ሰው ስለ መሆኑ (ስለ ነገረ ትሥጉት/incarnation) ከሚነግሩን ገለጻዎች አንዱና ዋነኛው ይሁን እንጂ፣ “ብቸኛው” ግን አይደለም። በአዲስ ኪዳን የትሥጉት ነገረ መለኮት በብዙ ቃላት ያሸበረቀ ነው። “ተወለደ” ከሚለው…
...የቀጠለ

ለምን ተወለደ?



                          በሳምሶን ጥላሁን


ሥጋ ሆነ (γίνομαι)

“ቃልም ሥጋ ሆነ…”። የዮሐንስ ወንጌል፣ እንደ ማቴዎስ፣ አሊያም እንደ ሉቃስ በውስጡ “የልደት” ትረካን አያካትትም። በዮሐንስ ሕፃን ሲወልድ አናይም። የምናገኘው “ቃል” ከተሰኘና ቅድመ ሕላዌ ካለው አካል ጀምሮ፣ ወደ ነገረ ትሥጉቱ የሚሄድ እንቅስቃሴ ነው። ይህ ከላይ ወደታች የሚሄድ የአተራረክ ዘዬ፣ ዮሐንስን ከሌሎቹ ወንጌላውያን ይለየዋል። በቅድመ ትሥጉት ማንነቱ፣ ቃል “ነበረ” ይለናል። የሚጠቀመው “ሆነ” የሚለውን የመሆን ግሥ ሲሆን፣ ይህም ‘በመጀመሪያ ቃል የሆነ፤ እግዚአብሔር የሆነ…'፣ ሳይሆን “ነበር” የሚለውን የመሆን ግሥ በመጠቀም ነው። ይኸውም፣ “በመጀመሪያ ቃል ነበረ … ቃልም ከእግዚአብሔርም ጋር ነበረ … ቃልም እግዚአብሔርም ነበረ።” “ነበር”፣ “ነበር”፣ “ነበር”! ሆኖም ግን ቁጥር 14 ላይ ሲደርስ፣ ዮሐንስ የመሆን ግሡን ከ“ነበረ” ወደ “ሆነ” ይለውጠዋል፤ ‘ቃልም ሥጋ ነበረ' ከማለት ይልቅ፣ “ቃልም ሥጋ ሆነ” በማለት። “ሆነ … ዐደረ”።

ይህ ገለጻ አስረግጦ የሚያመለክተን ቁም ነገር፣ “ቃል” በሁለት መደብ በአንድ ጊዜ የሚመደብ መሆኑን ነው። በአንድ በኩል ቃል በመለኮት መደብ ይኖራል። እርሱ አማክሎተ ፍጥረት ነው (Agent of Creation)፤ አማክሎተ ድነት ነው (Agent of Redemption)፤ ቃል አማክሎተ አስተርዮ ነው (Agent of Revelation)። በሌላ በኩል ደግሞ ቃል ከዚህ ቀደም “ያልነበረውን” ነገር ወሰደ፤ “ሥጋ ሆነ”።

በቁጥር 1 ላይ፣ “እግዚአብሔር” የሚለውን ቃል ዮሐንስ በሁለት ዐይነት መንገድ ይጠቀመዋል። አንድኛው አብን የሚወክል የመለኮት አካል ስም ሆኖ ጥቅም ላይ ሲውል፣ “ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበር” እርሱም አብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ፣ “እግዚአብሔር” የሚለው ቃል የመለኮት ባሕርይን ገላጭ ሆኖ ጥቅም ላይ ውሏል፤ “ቃልም እግዚአብሔር ነበረ”። ስለዚህ ይህ መለኮታዊ ባሕርይ ገንዘቡ ሆኖ ይኖር የነበረው፣ እንዲሁም መለኮታዊ ከሆነው ከሌላኛው አካል ፊት ለፊት ሕልው ሆኖ ይኖር የነበረው ቃል፣ መለኮታዊ ባሕርይውን ሳይለቅቅ፣ ከዚህ ቀደም ያልነበረውን “ሰብዓዊ ባሕርይ” ገንዘቡ አደረገ።
እንቅስቃሴው ከላይ ከምጡቅ ሕልውናው ይጀምርና ወደ ምድር ሰብዓዊ ማንነቱ ይዘልቃል።

ቃል “ሥጋ” አልመሰለም፤ ቃል ሥጋ ሆነ እንጂ!
ይህ አቅጣጫ በዮሐንስ ትረካ ኋላ እየዳበረ ይመጣል። ይህ ሕይወትና ብርሃን የሆነው ቃል (ዮሐ 1፥4-5)፣ ሥጋ ሆኖ ተገልጦ (1፥14)፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር በተለይ በመስቀል ሞቱ ተርኮልን (3፥16) ወደ ነበረበት በክብር ይመለሳል።

እግዚአብሔር ሕይወት፣ ብርሃን፣ ፍቅር ነው። የፍቅሩ፣ የሕይወቱና የብርሃኑ መገለጫ ሞገድ፣ የክብሩም መንጸባረቂያ ሥፍራ ‘ትሥጉቱ’ ነው። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ነው። ዮሐንስ የክርስቶን ልደት “ተወለደ” በሚለው ቃል ሳይሆን፣ “ሆነ” በሚለው ስለተረከልን፣ ነገረ ትሥጉቱን ከሌላና ከምጡቅ ገጽታው አንጻር እንድናይ ረድቶናል።


መልካም በዓል!




ምንጭ:- hintset.com





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ።”
                ሮሜ 8፥3-4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
2👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።”
            ዮሐንስ 3፥17




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
በመጽሐፍ ቅዱስ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስጦታ ይዘው የመጡት ሰብአ ሰገል ቁጥራቸው ስንት ነው
Anonymous Quiz
51%
ሀ. 3
11%
ለ. 7
1%
ሐ. 10
5%
መ. 12
32%
ሠ. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቁጥራቸው አልተጠቀሰም
👍9
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤”
          ገላትያ 4፥4




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ምድርም ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች። የምድርን ጥልቅ ስፍራ ሁሉ ጨለማ ውጦት ነበር። የእግዚአብሔርም (ኤሎሂም) መንፈስ በውሆች ላይ ይረብብ ነበር።”
          ዘፍጥረት 1፥2 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
የገና በዓል ታሪካዊ  አመጣጥ
         

                   ክፍል-፪


                     በጳውሎስ ካሱ


       🎄የገና  በዓል አመጣጥ🎄

ድሮ ሰዎች ፀሐይ አምላክ ናት ብለው ያምኑና ያመልኳት ነበር፡፡ ክረምት የሚመጣውም ፀሐይ ስትታመም ወይም ስትደክም ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ በምድራችን በሰሜን ንፍቀ ክበብ አካባቢ አጭር የሚባለው ቀን የሚውለው እ.ኤ.አ. በዲሴምበር (ታኅሣሥ) 21 ወይም 22 ነው፡፡ ይህንንም ጊዜ የክረምት ሶልስቲስ ይሉታል (ፀሐይ የድካሟ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የምትደርስበት ማለት ነው)፡፡ ፀሐይ ከመጨረሻ ድካሟ በኋላ ወደ ቀድሞ ጥንካሬዋ ስለምትመለስ ይህ ወቅት በልዩ ሁኔታ ይከበር ነበር፡፡ ይህ በዓል በተለያዩ አገሮች በተለያየ ሁኔታ ይከበር ነበር፡፡ ለምሳሌ ግብፃውያን ራ ብለው የሚጠሩት ፀሐይን እንደ ኮፍያ ያጠለቀ አምላካቸውን የሚያስቡበትና የሚያከብሩበት በዓል ሲሆን፣ የጥንት ሮማውያን ደግሞ ሳተርን የሚሉትን የእርሻ አምላክ ለማክበር በዓሉን ሳቱርናሊያ (Saturnalia) ብለው ያከብሩ ነበር፡፡ ቀጥሎ የሚመጣውን አረንጓዴነት በማሰብም ቤተ መቅደሳቸውንና ቤታቸውን በአረንጓዴ ዕፀዋት ያስጌጡ ነበር፡፡

ለዛሬው ገና ዋና መሠረቱ የሮማ አረማውያን ሳቱርናልያ የሚባለውና ከዲሴምበር (ታኅሣሥ)17 እስከ 25 የሚቆይው የአንድ ሳምንት ሕግ አልባ ክብረ በዓል ነው። በዚህ ሳምንት የሮማ ፍርድ ቤቶች በሙሉ ይዘጉ ነበር፡፡ የሮማ ሕግም በዚህ ሳምንት ውስጥ ንብረት ያጠፋም ሆነ ሰው ያቆሰለ እንደማይቀጣ ይደነግጋል፡፡ ሳምንት የሚቆየው በዓል የሚጀምረው  የሮማ ባለሥልጣኖች የሮማውያን ጠላት ብለው የሚሰይሙትና የመጥፎ መንግሥት ጌታን የሚወክለውን ሰው/ሰዎች ከመረጡ በኋላ ነው፡፡ እነዚህ የሚመረጡት ሰዎች ምንም ጥፋት ያላጠፉ ንፁኃን ሰዎች ነበሩ። እያንዳንዱ የሮማ ማኅበረሰብ የየራሱን የሮማውያን ጠላት ይመርጥና ሳምንቱን ሙሉ እነዚህን ንፁኃን ሰዎች ከመጠን በላይ እንዲበሉ፣ እንዲጠጡና እንዲዳሩ ያስገድዷቸዋል፡፡ ሮማውያኑም በዓሉን  የሚያከብሩት ከመጠን በላይ በመብላት፣በመጠጣት፣በመዳራትና በመዋጋት ነበር። በበዓሉ የመጨረሻ ቀንም ማለትም ዛሬ የክርስቶስ የልደት ቀን ነው ተብሎ በሚታመንበት ዲሴምበር 25 እነዚህን ሳምንቱን ሙሉ የተሰቃዩ ንፁኃን ወንዶችና ሴቶች በመግደል ሮማውያን  ጠላቶቻቸውን እንዳጠፉ በመቁጠር ይኩራሩ ነበር፡፡ 

ሉሲያን (Lucian) የተባለ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊና ባለቅኔ በጊዜው የሳቱርናልያ በዓል በግሪክ እንዴት ይከበር እንደነበር ሲጽፍ እንደ ሮማውያኑ ሰዎችን ከመሰዋት በተጨማሪ ከቅጥ ያለፈ መጠጥ ወይም ስካር፣ እርቃን ሆኖ ከቤት ቤት እየሄዱ መዝፈን (እንደ ኢትዮጵያውያን እንቁጣጣሽና ሆያ ሆዬ)፣ ሴቶችን መድፈርና ሌሎች የልቅ ወሲብ ድርጊቶችና በሰው ቅርፅ የተሠሩ ብስኩቶችን መብላት (እነዚህ ብስኩቶች አሁንም በገና ወቅት በእንግሊዝና በጀርመን ይዘጋጃሉ) የበዓሉ ዋና ገጽታዎች እንደነበሩ ገልጿል፡፡

 በአራተኛው ክፍለ ዘመን የቤተክርስቲያን መሪዎች እነዚህን አረማውያን አባል ለማድረግ በማሰብ ክርስትናን ከተቀበሉ በኋላም ሳቱርናልያን ማክበር መቀጠል እንደሚችሉ በማሳመን የክርስትናን እምነት እንዲቀበሉና ሳቱርናልያና ወደ ቤተክርስቲያን ይዘው እንዲገቡ ፈቀዱላቸው፡፡ ሆኖም ሳቱርናልያንና ክርስትናን የሚያገናኛቸው አንድም ነገር አልነበረም፡፡ ይህን ችግር ለመፍታትና ሳቱርናልያን ክርስቲያናዊ  ለማስመሰል የወቅቱ የቤተክርስቲያን መሪዎች የሳቱርናልያን የመዝጊያ ቀን (ዲሴምበር 25) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን ብለው  በመሰየም በዓሉ እንዲቀጥል አደረጉ። ሳቱርናልያም ክሪስማስ (ገና) ተባለ፡፡የሚያሳዝነው እነዚህ የስመ ክርስቲያን መሪዎች በበዓሉ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ለውጥ ለማድረግ አለመቻላቸው ነው፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት ይህ ‹‹የክርስቶስ ልደት ቀን›› የሚከበረው ልክ እንደ ሳቱርናልያ በመጠጣት፣ በመዳራትና፣ በራቁት የጎዳና ላይ ዳንስ (የክሪስማሰ ካሮል መሠረቱ ይኼ ነው) ነበር፡፡

ኢንከሪዝ ማዘር የተባሉ አሜሪካዊ በ1687 ዓ.ም. ባሳተሙት ጽሑፍቸው ላይ ‹‹ዲሴምበር 25ን የክርስቶስ የልደት ቀን ነው ብለው ማክበር የጀመሩት ክርስቲያኖች ቀኑን የሚያከብሩት ክርስቶስ በዚህ ቀን ተወልዷል በሚል እምነት ላይ ተመሥርተው አልነበረም፡፡ የአረማውያኑ ሳቱርናልያ የሚከበረው በተመሳሳይ ወቅት ስለነበረ በዓሉ ወደ ቤተ ክርስቲያን አንዲገባ ፍቃደኛ ስለሆኑ ብቻ ነበር፤›› በማለት አብራርተዋል፡፡ በዚሁ ግልጽ የሆነ አረማዊ መሠረቱ ምክንያት ቀደም ባሉት ጊዜያት በአንዳንድ አክራሪዎች ዘንድ የገናን በዓል ማክበር በሕግ የተከለከለ ነበር፡፡

አንዳንድ አፀያፊ የሳቱርናልያ አከባበር ገጽታዎች በጥንቷ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አማካይነት በ1466 ዓ.ም. አንደ አዲስ አንዲከበሩና ዕውቅና እንዲያገኙ እንደተሞከረ አንዳንድ የታሪክ ምንጮች ይጠቅሳሉ፡፡ ለምሳሌ በ1466 ዓ.ም. የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ሁለተኛው ጳውሎስ የሮማን ዜጎች  ለማስደሰት ሲል አይሁዶች እርቃናቸውን በጎዳና እንዲሮጡ ማድረግ እንደጀመረ የታሪክ ማስረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሩጫውን ከባድ  ለማድረግና ሕዝብን የበለጠ ለማሳቅ ሲባልም ሯጮቹ ከመጠን በላይ እንዲመገቡ ይደረግ እንደነበር እነዚሁ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ ጳጳሱም  ከሕዝቡ ጋር ተቀምጦ በሩጫው ይስቅ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ ዛሬ ‹‹የክርስቶስ ልደት›› እየተባለ የሚከበረው በዓል መሠረቱ ይኼ ነው፡፡ 

የገና ዛፍ፣ የገና ስጦታዎች አመጣጥና የገና አባት...


ይቀጥላል...



ምንጭ:- ethiopianreporter.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍71🔥1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ጌታም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ቢሰጥህም አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፤ ዓይኖችህ ግን አስተማሪህን ያያሉ፥”
           ኢሳይያስ 30፥20




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?



ምሳሌ 27
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ቀን የሚያመጣውን ምን እንደ ሆነ አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ።
² ሌላ ያመስግንህ እንጂ አፍህ አይደለም፤ ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይደለም።
³ ድንጋይ ከባድ ነው አሸዋም ሸክሙ ጽኑ ነው፤ ከሁለቱ ግን የሰነፍ ቍጣ ይከብዳል።
⁴ ቍጣ ምሕረት የሌለው ነው፥ መዓትም እንደ ጎርፍ ነው፤ በቅንዓት ፊት ግን ማን ይቆማል?
⁵ የተገለጠ ዘለፋ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።
⁶ የወዳጅ ማቍሰል የታመነ ነው፤ የጠላት መሳም ግን የበዛ ነው።
⁷ የጠገበች ነፍስ የማር ወላላ ትረግጣለች፤ ለተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር ሁሉ ይጣፍጣታል።
⁸ ስፍራውን የሚተው ሰው ቤቱን ትቶ እንደሚበርር ወፍ ነው።
⁹ ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤ እንዲሁ ነፍስ በወዳጁ ምክር ደስ ይላታል።
¹⁰ ወዳጅህንና የአባትህን ወዳጅ አትተው፤ በመከራህም ቀን ወደ ወንድምህ ቤት አትግባ፤ የቀረበ ወዳጅ ከራቀ ወንድም ይሻላል።
¹¹ ልጄ ሆይ፥ ጠቢብ ሁን፥ ልቤንም ደስ አሰኘው፥ ለሚሰድበኝ መልስ መስጠት ይቻለኝ ዘንድ።
¹² ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፤ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይጐዳሉ።
¹³ ለማያውቀው ከተዋሰ ሰው ልብሱን ውሰድ፥ ለእንግዳ የተዋሰውንም እርሱን አግተው።
¹⁴ ባልንጀራውን በታላቅ ቃል ማለዳ የሚባርክ ሰው እንደሚራገም ያህል ነው።
¹⁵ በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው፤
¹⁶ እርስዋንም መከልከል ነፍስን መከልከልና ዘይትን በቀኝ እጅ መጨበጥ ነው።
¹⁷ ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን ይስላል።
¹⁸ በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።
¹⁹ ፊት በውኃ ላይ ለፊት እንደሚታይ፥ እንዲሁ የሰው ልብ ለሰው ይታያል።
²⁰ ሲኦልና ጥፋት እንዳይጠግቡ፥ እንዲሁ የሰው ዓይን አይጠግብም።
²¹ ብር በከውር ወርቅም በማቅለጫ ይፈተናል፤ ሰውም በሚያመሰገኑት ሰዎች አፍ ይፈተናል።
²² ሰነፍን በሙቀጫ ውስጥ ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠው፥ ስንፍናው ከእርሱ አይርቅም።
²³ የበጎችህን መልክ አስተውለህ እወቅ፥ በከብቶችህም ላይ ልብህን አኑር፤
²⁴ ባለጠግነት ለዘላለም አይኖርምና፥ ዘውድም ለትውልድ ሁሉ አይጸናምና።
²⁵ ደረቅ ሣር በታጨደ ጊዜ፥ አዲስ ለምለም በታየ ጊዜ፥ ከተራራውም ቡቃያ በተሰበሰበ ጊዜ፥
²⁶ በጎች ለልብስህ ፍየሎችም የእርሻ ዋጋ ይሆናሉ።
²⁷ ለሲሳይህ ለቤተ ሰቦችህም ሲሳይ ለገረዶችህም ምግብ የፍየል ወተት ይበቃል።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍52
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል።”
             ምሳሌ 14፥15



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1
የገና በዓል ታሪካዊ  አመጣጥ
         

                   ክፍል-፫


                     በጳውሎስ ካሱ



🎄የገና ዛፍ፣ 🎁የገና ስጦታዎች አመጣጥና
🎅የገና አባት

ልክ እንደ በዓሉ ሁሉ የገና ዛፍ፣ ስጦታና የገና አባት መሠረታቸው  አረማውያን ናቸው፡፡

🎄የገና ዛፍ

ከሳቱርናልያ ተከታዮች ጋር በገፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን ከገቡትና ልማዳቸው ክርስቲያናዊ ከተደረገ አረማውያን መካከል የአሸይራ (Asheira) አምላኪዎች ይገኙበታል፡፡ የዛፎች አምልኮ የቆየ ነው፡፡ በቅድመ ክርስቶስ ዘመን አህዛብ በተለይ ትላልቅና ዓመቱን ሙሉ አረንጓዴ እንደሆኑ ለሚቆዩ ዕፀዋት ልዩ ትርጉም ይሰጧቸውና ያመልኳቸው ነበር፡፡ እርኩሳት መናፍስትን፣ አስማተኞችን፣ በሽታን የመሳሰሉትን ይከላከሉ ብለው ስለሚያምኑ ቅርንጫፎቻቸውን እየቆረጡ በበራቸው ላይ ወይም በቤታቸው ውስጥ ይሰቅሉ ነበር፡፡ አይሸራውያን እንደ ብዙ  አረማውያን በደን ውስጥ ያሉ ትላልቅ ዛፎችን ያመልኩ የነበረ ሲሆን ምሳሌዎቻቸውን (ቅርንጫፎቻቸውን) ወደ ቤታቸው በማምጣት ያስጌጧቸው እንደነበረና እነዚህም ቅርጫፎች እርኩሳት መናፍስትን ይከላከላሉ የሚል እምነት እንደነበራቸው ታሪክ ይጠቁማል፡፡ ልክ  እንደ ሳቱርናልያ  ልማዶች  ይህም ልማድ የክርስትና ስም ተሰጥቶት ቤተ ክርስቲያን ገባ፡፡ 

🎁የገና ስጦታዎች አመጣጥ

በቅድመ ክርስትና ሮም ቄሳሮች በሳቱርናልያ በዓል  ወቅት የተናቁ ተገዥዎቻቸው  መስዋትና ስጦታ እንዲያመጡላቸው ያስገድዱ ነበር፡፡ በኋላ ላይም ይህ ግዴታ በሕዝቡ መካከል ተሠራጭቶ እንደ መልካም ልማድ ተቀባይነት ስላገኘ በሳቱርናልያ በዓል ወቅት ሕዝቡ ስጦታ መለዋወጥ ጀመረ። የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ልማድ ቅዱስ ኒኮላስ ይሰጥ ነበር ከሚባለው አፈ ታሪካዊ ስጦታ ጋር በማያያዝ ክርስቲያናዊ አደረጋቸው፡፡

🎅የገና አባት

በ19ኛ ክፍለ ዘመን በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ‹‹ቅዱስ›› የሚል ማዕረግ የተሰጠው በ270 ዓ.ም. በቱርክ እንደተወለደ በቱርክ ሊቀጳጳስ እንደነበረና ታኅሣሥ 6፣345 ዓ.ም. እንደ ሞተ የሚነገርለት ኒኮላስ የተባለ ሰው አለ፡፡ ኒኮላስ በ325 ዓ.ም. በተደረገው የኒቅያ ጉባዔ ላይ ከተገኙ ሊቀጳጳሶች አንዱ እንደ ነበር የታሪክ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ በ1087 ዓ.ም. ለኒኮላስ ከፍተኛ  አክብሮት የነበራቸው መርከበኞች አጽሙን ከቱርክ ወደ ጣሊያን ወስደው ቤሪ በተባለች ስፍራ በሚገኝ መቅደስ ውስጥ አስቀመጡት፡፡ ቀደም ብላ በዚህ መቅደስ ውስጥ የነበረችው ለሕፃናት ስጦታ ትሰጣለች የሚል ታሪክ ያላት ኢፊፋበያ የተባለችው የአረማውያን አማልክትም ከመቅደሱ ተወግዳ በኒኮላስ ተተካች፡፡ ኒኮላስም መቅደሷንም ታሪኳንም ወረሰ፤ ቦታውም የኒኮላስ አምላኪዎች  መሀከል ሆነ፡፡ የኒኮላስ ተከታዮች በየዓመቱ ታኅሣሥ 6ን ሲያከብሩ ስጦታ ይለዋጡ ነበር፡፡ የኒኮላስ አምልኮ በሰሜን እየተስፋፋ በጀርመን አረማውያን ተቀባይነት አገኘ፡፡ እነዚህ የጀርመን አረማውያን ዋደን የተባለ  ነጭ ፂም ያለውና በዓመት አንድ ጊዜ በሰማይ ውስጥ በፈረስ እንደሚጋልብ የሚነገርለት አምላክ ያመልኩ ነበር፡፡ ለዚህ አምላክ የተፈጠረው  ታሪክ ሁሉ ለኒኮላስ ተሰጠ፡፡ ቀደም ብላ እንዳደረገችው አረማውያኑን ለመሳብ ብላ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የኒኮላስን አምላኪዎች ተቀብላ ታሪኩንም እውነት ነው ብላ በማስተማር ስጦታ ከታኅሣሥ 6 ይልቅ በታኅሣሥ 25 እንዲሆን ማስተማር ጀመረች፡፡ የስፓኝ ስሙ ሳንታ ክላውስ (Santa Claus) የበለጠ ዕውቀና እያገኘ መጣ፡፡ አዳዲስ የፈጠራ ታሪኮች ተጨመሩለት፡፡ በ1931 ዓ.ም. የኮካ ኮላ ኩባንያ በሠራው ማስታወቂያ ላይም ሳንታ ቀይ ፀጉራም ልብስ የለበሰ ነጭ ፂም ያለው ወፍራም ሰውዬ ሆኖ ቀረበ፡፡ ይህ ሳንታም ሊቀ ጳጳስ፣ የአረማውያን አምላክና የንግድ ማስታወቂያ ሆኖ እስከ ዛሬ ቀጥሏል፡፡ 

የገና በዓል ብዙ ደጋፊዎች ያሉት በዓል ነው፡፡ ደጋፊዎች በሦስት ይከፈላሉ፡፡ የመጀመርያዎቹ በዓሉ መጸሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው በዓል ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው (ከልባቸውም ይሁን ከአፋቸው)፡፡ ሁለተኛዎቹ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ባይኖረውም የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ እውነት እስከሆነ ድረስ ልደቱን ማክበሩ ክፋት የለውም ብለው የሚያምኑ ናቸው፡፡ ሦስተኛው አካል የሚከራከረው በዓሉ ለንግድና ቤተሰቦችን/ሰዎችን በማቀራረብ  ካለው ጠቀሜታ አኳያ ነው፡፡ 


ተፈፀመ



ምንጭ:- ethiopianreporter.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3