🪔የንጉሡ የኢየሱስ ልደት (ማቴ. 1፡18-2፡23)
የክርስቶስን ልደት የሚገልጹ ወንጌላት ሁለት ብቻ ናቸው። ከእነዚህ ሁለቱ መካከል፥ ሉቃስ ስለ ክርስቶስ ልደት ሰፊ ምርምር ኣካሂዷል። ሉቃስ የክርስቶስን ልደት ከማርያም እይታ አንጻር ሲመለከት፥ ማቴዎስ ግን ከዮሴፍ እይታ አንጻር ይመለከታል።
የክርስቶስ ልደት የሆነው ዮሴፍና ማርያም ተጫጭተው ባሉበት ወቅት ነበር። እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ፥ የአይሁድ መተጫጨት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች ስለ ነበሩ፥ መቋረጥ የሚችሉት በፍች ነበር። በሚተጫጩበት ወቅት ማርያም «በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች» (ማቴ. 1፡18)።
ማርያም ስለሆነው ነገር ለዮሴፍ ገልጻለት ይሆናል። ስለዚህ የተጠቀሰ ነገር የለም። ነገር ግን ዮሴፍ በሆነ መንገድ ደርሶበታል። ነገር ግን ዮሴፍ የዋህ ሰው ስለ ነበር፥ ከሌላ ወንድ ለማርገዟ በይፋ ሊወቅሳት አልፈለገም። ስለሆነም ለእርሷ ሳይነግራት በስውር ሊተዋት አሰበ። እግዚአብሔር ግን ማርያም በትክክል ከመንፈስ ቅዱስ እንደፀነሰች ለዮሴፍ ለመንገር መልአኩን ላከ። ማርያም ከሌላ ሰው ጋር አላመነዘረችም ነበር። ምንም እንኳ ማርያም በማርግዟ ቢቀልዱባትም፥ ዮሴፍ እግዚአብሔርን ታዝዞ ማርያምን ወሰዳት።
እግዚአብሔር በዚህ መሢሑን ወደ ዓለም በመላኩ ሂደት ማርያምን ብቻ ሳይሆን ዮሴፍንም አክብሯል። እንደ ባልና የቤት ራስ ሁሉ፥ እግዚአብሔር ዮሴፍ ለልጁ ስም እንዲያወጣ መብት ሰጠው። ለክርስቶስ ስም በማውጣቱ፥ ዮሴፍ ሕጋዊ ኣባትነቱን እያረጋገጠ ነበር።
እግዚአብሔር ዮሴፍ ልጁን «ኢያሱ» (ዕብራዊ ስም) ወይም «ኢየሱስ» (ግሪካዊ ስም) ብሎ እንዲጠራ ነገረው። የሁለቱም ስሞች ፍች «እግዚእብሔር ደኅንነት ነው» የሚል ነው። ይህም የመሢሑ ቀዳሚ ተግባር ድል ነሺ ንጉሥ መሆን ሳይሆን፥ አዳኝ እንደሆነ የሚያመለክት ነው። ክርስቶስ «ሕዝቡን ከኃጢአታቸው የሚያድን» መንፈሳዊ አዳኝ እንጂ ፖለቲካዊ ነፃ አውጪ እንዳልሆነ ማቴዎስ ገልጾአል።
ማቴዎስ፥ የድንግሊቱ መውለድና የክርስቶስ ልደት ዝርዝር ጉዳዮች ሁሉ፥ በእግዚአብሔር በጥንቃቄ እንደታቀዱና በብሉይ ኪዳን እንደተተነበዩ አስረድቷል። ማርያም በሚያስደንቅ መንገድ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ስለ ወለደች፥ ኢየሱስ ሰውም አምላክም ሆኗል። ይህም እርሱ ብቻ «አማኑኤል» ማለትም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆኖኣል (ኢሳ. 7፡14)። በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር የክብር ደመናውን በሰዎች መካከል ያኖረ ሲሆን፥ አሁን ግን እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በሰዎች መካከል አድሯል። ክርስቶስ ወደ ሰማይ ከመመለሱ በፊት፥ ለደቀ መዛሙርቱ አሁንም አማኑኤል እንደሚሆን፥ ማለትም እስከ መጨረሻው አብሯቸው እንደሚሆን ገልጾአል (ማቴ. 28፡18-20) ማቴዎስ ክርስቶስ የብሉይ ኪዳንን ትንቢት በመፈጸም በቤተልሔም እንደ ተወለደ ተናግሯል።
ለአይሁዶች እግዚአብሔር ለአሕዛብም ዕቅድ እንዳለው ማቴዎስ አመልክቷል። እንዲሁም መጀመሪያ ክርስቶስን ያከበሩትና ያመለኩት ሰብዓ ሰገል መሆናቸውን ገልጾአል። ማቴዎስ እነዚህ ሰብዓ ሰገል ከየት እንደ መጡ ወይም ስንት እንደሆኑ አልጠቀሰም። በክርስትና ትውፊት ሦስት ሰዎች እንደሆኑ የሚታመነው ካበረከቱት ስጦታ በመነሣት ነው። ለእነዚህ ሰዎች የተሰጠው የግሪክ ስያሜ «ማጂ» (magi) የሚል ነው። ማጂ የልዩ ሃይማኖታዊ ሰዎች ቡድን ሲሆን፥ ብዙ ምሑራን ከፋርስ ወይም ከሳውዲ ዓረቢያ እንደ መጡ ያምናሉ። እነዚህ ሰዎች በከዋክብት ጥናት ይካኑ እንጂ፥ ስለ እግዚአብሔርም በቂ ግንዛቤ የነበራቸው ይመስላል። ያዩት አዲስ ኮከብ ለአይሁዶች ልዩ ንጉሥ እንደ ተወለደ የሚያመለክት መሆኑን የተረዱ ይመስላል። ለመስገድ መፈለጋቸው ደግሞ ይህ ንጉሥ ከተራ ንጉሥ በላይ መሆኑን እንደ ተገነዘቡ ያሳያል። የአይሁዶች መዲና ወደሆነችው ኢየሩሳሌም እስኪደርሱ ድረስ ለብዙ ወራት ኮከቡን ተከትለው ተጓዙ። ንጉሡ በቤተ መንግሥት ይወለዳል ብለው ስለ ገመቱ፥ ወደ ንጉሥ ሄሮድስ ሄደው ኣዲስ ስለ ተወለደው ንጉሥ ጠየቁ።
ቀደም ሲል ዙፋኔን ይነጥቁብኛል በሚል ስጋት ከቤተሰቡ አባላት መካከል ብዙ ሰዎችን የፈጀው ንጉሥ ሄሮድስ፥ ይህን ሲሰማ ደነገጠ። በመጀመሪያ፥ የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎችን ሰብስቦ ጠየቃቸው። እነዚህ ሰዎች በብሉይ ኪዳን እንደተነገረው መሢሑ ከኢየሩሳሌም ሰባት ኪሎ ሜትር ወጣ ብላ በምትገኘው በቤተልሔም እንደሚወለድ ያውቁ ነበር። ሄሮድስ ያለበትን ስፍራ አይተው እንዲነግሩት በማዘዝ ሰብዓ ሰገልን ወደ ቤተልሔም ላካቸው። ምንም እንኳ ሄሮድስ ሕጻኑን ንጉሥ ለማክበር እንደፈለገ ቢነግራቸውም፥ እውነተኛ ፍላጎቱ ግን ሕጻኑን መግደል ነበር። ኮከቡ እንደገና ለሰብዓ ሰገል ተገልጦ፥ ኢየሱስ ወደነበረበት ወደ ቤተልሔም መራቸው።
ማቴዎስን ከሉቃስ ትረካ ጋር በማነጻጸር እንደምንገነዘበው፥ ኢየሱስ ከተወለደ የተወሰነ ጊዜ አልፎ ነበር። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ከተወለደበት ግርግም ወደ ቤት ተዛውሮ ነበር። ይህም የዘመድ ቤት ወይም እነዮሴፍ የተከራዩት ቤት ሳይሆን አይቀርም። ኢየሱስ ከተወለደ ምን ያህል ጊዜ እንዳለፈ አናውቅም። ሄሮድስ ከሰብዓ ሰገል ኮከቡ መጀመሪያ የታየበትን ጊዜ ተረድቶ እስከ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ሕጻናት ሁሉ ስለ ገደለ፥ ኢየሱስ ከተወለደ ሁለት ዓመታት ሳይሞላው ኣይቀርም ተብሎ ይገመታል። ሰብዓ ሰገል ስጦታዎችን በመስጠትና እንደ አምላክ በማምለክ ክርስቶስን አክብረውታል።
እግዚአብሔርም ለሰብዓ ሰገል ያዩትን ለሄሮድስ ሳይናገሩ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል። በዚህ ታሪክ ማቴዎስ እግዚአብሔር የአይሁዶች ብቻ አምላክ እንዳልሆነና አሕዛብም የዕቅዱ አካል መሆናቸውን አመልክቷል። ክርስቶስ መሢሕ እንደሆነ በመጀመሪያ ከተገነዘቡት ሰዎች አንዳንዶቹ አሕዛብ ነበሩ። ዓለም ስለ እነርሱ ምንም ዐይነት አመለካከት ቢኖረውም ወንጌሉን ብዙውን ጊዜ እናውቃለን ከሚሉት የተሰወረው እውነት ልባቸውን ለከፈቱት ተገልጧል።
ከመሢሑ ታሪክ በስተጀርባ መንፈሳዊ ውጊያ አለ፡፡ ሰይጣን መሢሑን ለማጥፋት ፈልጎ ነበር። ይህንንም ያደረገው በዓለም ላይ ያለውን ኃይሉን እንደሚሽርበት ስለ ተገነዘበ ነበር። እግዚአብሔር ግን ልጁ ዕቅዶቹን ፈጽሞ፥ በመስቀል ላይ እንዲሞት ወስኖ ነበር። ስለዚህ ሰይጣን ኢየሱስን ለመግደል በሄሮድስ ልብ ውስጥ ያሴር እንደነበረ እግዚአብሔር በመገንዘብ፥ ዮሴፍ በመጀመሪያ ወደ ግብፅ ይዞት እንዲወርድ ከዚያም ወደ ናዝሬት ይዞት እንዲመለስ አዘዘው። ከዚያም ሄሮድስ ወደ ቤተልሔም ተጉዞ እስከ ሁለት ዓመት ዕድሜ የሆናቸውን ሕጻናት ሁሉ አስገደለ። ይህም ሰብዓ ሰገል ኢየሱስን ለማየት የመጡት ቢያንስ ከኣንድ ዓመት ተኩል እስከ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ ሳይሆን አይቀርም ወደሚል ድምዳሚ ይመራናል። በክርስቶስ ልደት ዙሪያ በተከናወኑት በእነዚህ ክስተቶች ሁሉ፥ የእግዚአብሔር እጅ እንደ ነበረበት ማቴዎስ ያውቅ ነበር። የሕጻናቱ መገደል፥ የክርስቶስ ከግብፅና በኋላም ከናዝሬት መምጣት፥ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተተንብዮአል።
ምንጭ:- ethiopiansite-com
(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ አይ ኤም ከታተመውና የዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

👍3❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ።”
ዕብራውያን 12፥13

❤9
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።”
2ኛ ቆሮ 9፥8-9

❤2👍1
sparks.pdf
1.7 MB
📔ርዕስ፦ በዚያን ጊዜ
👤ደራሲ፦ ተስፋዬ ጋቢሶ
🖨አሳታሚ፦ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
👉የዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ የሕይወት ታሪክ።
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👤ደራሲ፦ ተስፋዬ ጋቢሶ
🖨አሳታሚ፦ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
👉የዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ የሕይወት ታሪክ።
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4👏2❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤”
1ኛ ጴጥሮስ 4፥10

❤2
ቅዱሳት መጻሕፍት
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት ከፍርሃት ነፃ ወጥተናል- መለየት የለም (8:31-39) ኩነኔ የማይኖርብን ከእግዚአብሔር ጽድቅ ስለምንካፈል እና ሕግ ሊኮንነን ስለማይችል ነው፡፡ ሥጋን አሸንፈን ለእግዚአብሔር እንድንኖር የእግዚአብሔር መንፈስ ስላለን ዕዳ የለብንም፡፡ ተስፋ መቁረጥም የለም፡፡ ምክንያቱም የተባረከ ተስፋችን በሆነው በክርስቶስ መመለስ የእግዚአብሔርን ክብር እንካፈላለንና፡፡ የእግዚአብሔርን ፍቅር…
የቀጠለ...
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ከፍርሃት ነፃ ወጥተናል- መለየት የለም (8:31-39)
መ) ክርስቶስ ስለ እኛ ይማልዳል (8:34)
እጥፍ ምልጃ አማኝን በክርስቶስ ዋስትና ይሰጠዋል፡፡ መንፈስ ይማልዳል (8:26-27)፣ የእግዚአብሔር ልጅም ይማልድልናል (8:34):: ለእኛ የሞተልን ያው ጌታ አሁን በሰማያት ይማልድልናል፡፡ ሊቀ ካህናችን በመሆኑ ፈተናን መወጣት የምንችልበትን ጸጋና ጠላትን የምንረታበትን ጉልበት ይሰጠናል (ዕብ. 4:14-16)። ጠበቃችን ስለሆነና፣ ኃጢአታችንን ይቅር ብሎ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ኅብረት ያድሳል (1ኛ ዮሐ. 1:9-2፡2)። ምልጃ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እኛን ወክሎ ስላለ ራሳችንን መወከል አያሻንም ማለት ነው፡፡
በሮሜ 5:9-10 ባለው ክፍል ጳውሎስ የምልጃን አገልግሎት ጠቁሟል፡፡ የዳንነው በሞቱ ብቻ ሳይሆን በሕይወቱም ነው፡፡ «ስለ እነርሱም ሊማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል» (ዕብ. 7፡25)፡፡ ጴጥሮስ በጌታ ላይ ኃጢአት ሠርቶ ነበር፣ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአቱ ተፋቀለት ኅብረቱም ታደሰለት፡፡ «ስምዖን ስምዖን ሆይ፣ እነሆ፣ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ» (ሉቃስ 22፥31-32)። ስለ እያንዳንዳችን ይማልዳል ይህም አገልግሎቱ እያንዳንዳችን ዋስትና ያለን ስለመሆኑ ያረጋግጥልናል፡፡
ሠ) ክርስቶስ ይወድደናል (8:35-39)
ከቁጥር 31-34 ጳውሎስ እግዚአብሔር እንደማይተወን አረጋግጧል:: ነገር ግን እኛ ልንተወው እንችላለን? ከዚያስ? ጳውሎስ ይህንን ችግር በዚህ በመጨረሻው ክፍል ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ነገር እንደ ሌለ ያብራራል፡፡
ለመንፈሳዊ ዕድገታችን የሚያስፈልጉን ስለሆነ ብሎ (ሮሜ 5:3-5) እግዚአብሔር ከሕይወት ውጣ ውረዶች አያስጠልለንም፡፡ በሮሜ 8:28 እንደተናገረው የሕይወት ውጣ ውረዶች ለበጎ እንደሚሆኑልን እንጂ እንደማያጠፉን አረጋግጦልናል፡፡ ለራሳችን በጎነትና ለራሱ ክብር ሲል እግዚአብሔር ፈተናን ይፈቅዳል፡፡ ስለ እርሱ ብለን ፈተናን እንታገሳለን (8:36):: ይህንን በማድረጋችን እግዚአብሔር የሚተወን ይመስላችኋል? በፍጹም! ይልቁንም በሕይወት ፈተና ስናልፍ የበለጠ ይጠጋናል፡፡
በተጨማሪም፣ የምናሸንፍበትን ኃይል ይሰጠናል (ቁ. 37)። በክርስቶስ «ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::» በድል ላይ ድልን ይሰጠናል፡፡ ሕይወትንም፣ ሞትንም፣ ያለውንም፣ የሚመጣውንም አንፈራም። ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ይወድደናል፣ ድልንም ይሰጠናል:: ይህ የተስፋ ቃል በእኛ ጥረት ላይ የተመሠረተ አይደለም፣ «እንዲህ ብታደርጉ፣ እንዲህ አደርጋለሁ» አላለም፡፡ ይህ ዋስትናችን የጸና እውነት ነው፡፡ እኛ የክርስቶስ ስለሆንን ዋስትናው የራሳችን መሆኑን እናውጃለን፡፡ ከእርሱ ፍቅር ምንም ሊለያችሁ አይችልም:: እመኑና በእርሱ ሐሴት አድርጉ!
የዚህ አስደናቂ ምዕራፍ ግምገማ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ባለድል መሆኑን ያሳያል፡፡ ክርስቶስ ስለሞተልን ከፍርድ ነፃ ነን፡፡ የእርሱም ጽድቅ አለን፡፡ ክርስቶስ በመንፈሱ በእኛ ውስጥ ስለሚኖርና በሕይወቱ ስለምንካፈል፣ ከሽንፈት ነፃ ነን፡፡ ክርስቶስ ስለሚመጣና በክብሩ ስለምንካፈል ከተስፋ መቁረጥ አርነት ወጥተናል፡፡ ክርስቶስ ስለሚማልድልንና ከእርሱ ፍቅር ሊለየን የሚችል ማንም ስለሌለ፣ ከፍርሃት ነፃ ነን፡፡
ኩነኔ የለብንም! ዕዳ የለብንም! ተስፋ አንቆርጥም! ከእርሱ አንለይም!
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ማን ይቃወመናል?
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ተስማማ፤ ገጽ 90-91

👍5
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ቅጥር እንደሌላት እንደ ፈረሰች ከተማ፥ መንፈሱን የማይከለክል ሰው እንዲሁ ነው።”
ምሳሌ 25፥28

👍2❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ሁሉንም ፍርሃት ያዛቸውና፦ ታላቅ ነቢይ በእኛ መካከል ተነሥቶአል፥ ደግሞ፦ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጐበኘ እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።”
ሉቃስ 7፥16

#እራሳችንን_እንመርምር
እግዚአብሔር የመረጠልንን መንገድ ለመከተል እውቀት ለማግኘት ምን ማድረግ አለብን?
"እንግዲህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማነው? ለእርሱ የተመረጠለትን መንገድ እንዲከተል እግዚአብሔር ዕውቀቱን ይሰጠዋል፤"
መዝሙር 25፥12 (ሕያው ቃል)

❤3
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ስለ ምን ሕመሜ አዘወተረኝ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ። አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆነኛለህን?”
ኤርምያስ 15፥18

❤1👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር የጊዜ ስሌት ለምትጠቀሙ የቻናላችን ቤተሰቦች መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ!
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“አንተን በሚረዳህ በአባትህ አምላክ፣ በሚባርክህ፣ ሁሉን ማድረግ በሚችል አምላክ፣ ከላይ ከሰማይ በሚገኝ ረድኤት፣ ከምድር ጥልቅ በሚገኝ በረከት፣ ከማሕፀንና ከጡት በሚገኝ ምርቃት ይባርክሃል።”
ዘፍጥረት 49፥25 (አዲሱ መ.ት)

❤7👍4
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
መዝሙር 84
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ ማደሪያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው!
² ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትወድዳለች ትናፍቅማለች፤ ልቤም ሥጋዬም በሕያው አምላክ ደስ ተሰኘ።
³ ወፍ ለእርስዋ ቤትን አገኘች፥ ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች፤ የሠራዊት አምላክ ንጉሤም አምላኬም ሆይ፥ እርሱ መሠዊያህ ነው።
⁴ በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፤ ለዓለምና ለዘላለምም ያመሰግኑሃል።
⁵ አቤቱ፥ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት፥ በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው።
⁶ በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰነው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።
⁷ ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፤ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።
⁸ የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ አድምጥ።
⁹ አቤቱ፥ መታመናችንን እይልን፥ ወደ ቀባኸውም ፊት ተመልከት።
¹⁰ ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ።
¹¹ እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም።
¹² የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በአንተ የታመነ ሰው ምስጉን ነው።

👍4❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በእኔ ደስ ተሰኝተህ ከሆነ፣ አንተን ዐውቅህና ያለ ማቋረጥ በፊትህ ሞገስ አገኝ ዘንድ መንገድህን አስተምረኝ፤ ይህ ሕዝብ የአንተ ሕዝብ መሆኑን አስታውስ።”
ዘጸአት 33፥13 (አዲሱ መ.ት)

❤4
🌟የገና በዓል ታሪካዊ አመጣጥ
ክፍል-፩
በጳውሎስ ካሱ
የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በየዓመቱ በደማቅ (በተለየ የአሜሪካና አውሮፓ) ሁኔታ ከሚያከብሯቸው በዓላት አንዱ ገና ነው፡፡የገና በዓል አከባበር በየአገሩ መጠነኛ ልዩነት ቢኖረውም በየዓመቱ አዳዲስ መሻሻሎች እየተደረገበት ደማቅነቱ እንደቀጠለ መጥቷል፡፡
ይህንኑ ተከትሎም የበዓሉን አጀማመርና ታሪክ ለማግኘት ብዙ ጥናቶች ተደርገዋል:: የጥናቶቹ ግኝትም ብዙዎቹን እርግጥ ይህ በዓል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን? ብለው እንዲጠይቁ ሲያደርግ ብዙዎቹን ግን በዓሉን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማድረግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በመጥቀስ ትክክለኛነቱን ለማሳየት ይሞክራሉ፡፡የተቀሩት ደግሞ ትኩረታቸውን ከበዓሉ በሚገኘው ደስታ ላይ ብቻ በማድረግ የአያገባኝም አቋም ወስደዋል፡፡ እርግጥ የገና በዓል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው? መልሱ በሚከተሉት የጥናት ግኝቶች ውስጥ ይገኛል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው በእርግጥ በፈረንጆቹ ዲሴምበር 25 ወይም በኢትዮጵያዊያን ታኅሣሥ 29 ነውን? አዲስ ኪዳን ኢየሱሰ ክርስቶስ የተወለደበትን ቀን በትክክል አይናገርም::
ከወንጌላቱ ሁሉ መጀመርያ እንደተጻፈ የሚታመነው የማርቆስ ወንጌል ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ65 ዓ.ም. የተጻፈ ሲሆን፣ ታሪኩን የሚጀምረው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ነው። ይህም የሚጠቁመው የመጀመርያዎቹ ክርስቲያኖች የክርስቶስን የልደት ቀን እንደማያውቁ ለማወቅም ፍላጎት እንዳልነበራቸው ነው፡፡ ይህም አንድ ጥያቄ ማስነሳቱ አልቀረም፤ ክርስቶስ በዲሴምበር 25 ወይም ታኅሣሥ 29 ተወለደ ብሎ የጻፈው ማነው? እንዴትስ አወቀ? ታሪክ እንደሚናገረው ጌታ ተወለደ ተብሎ የሚታመንበትን ዓመት የወሰነው ዲዮኒሲየስ ኤግዚገስ (Dionysisus Exiguus) የተባለ የካቶሊክ መነኩሴ ነው፡፡
ክርስቶስ የተወለደበትን ዓመት ለመወሰን የተጠቀመው ቀመርም የሚከተለውን ይመስላል፡-
በቅድመ ክርስትና ሮም ዓመታት የሚቆጠሩት "ከአበ አርበ ኮንዲታ" (ab Urbe Condita) ማለትም ሮም ከተመሠረተችበት ቀን ጀምሮ ነው፤ ይህም AUC ይባላል እንደኛ ዓ.ም. ማለት ነው፡፡ ስለዚህ 1 AUC ሮም የተመሠረተችበትን ቀን ይወክላል፡፡ 5 AUC የሮምን ግዛት አምስተኛ ዓመት ይወክላል ወዘተ.
ዲዮኒሲየስ የሮማው ቄሳር አውግስጦስ ለ43 ዓመታት ከገዛ በኋላ በቄሳር ጢባርዩስ ተተካ የሚለውን ታሪክ አምኖ በመቀበል ቀመሩን በዚህ ላይ መሥርቷል፡፡
በሉቃስ ውንጌል ምዕራፍ 3 ቁጥር 1 እና 2 ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ 30 ዓመት ሲሞላው የጢባርዩስ 15ኛ የንግሥ ዓመት እንደሆነ ተመልክቷል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ በጢባርዮስ ዘመነ መንግሥት 30 ዓመቱ ከሆነ በቄሳር አውግስጦስ አገዛዝ ሥር 15 ዓመት ኖሯል ማለት ነው (ይህም የኢየሱስን ልደት በአውግስጦስ 28ኛ የሥልጣን ዓመት ላይ ያደረገዋል)፡፡
አውግስጦስ የነገሠው በ727 AUC ነው::እዚህ ላይ ተመሥርቶ ዲዮኒሲየስ የክርስቶስ ልደት በ754 AUC ነው ብሎ ደመደመ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በሉቃስ 1፥5 ላይ ክርስቶስ የተወለደው በሄሮድስ ዘመነ መንግሥት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ታሪክ እንደሚናገረው ደግሞ ሄርድስ የሞተው በ750 AUC ነው፡፡ ይህም ዲዮኒሲየስ ክርስቶስ ተወለደ ካለበት አራት ዓመታት ቀደም ብሎ ማለት ነው፡፡ ዮሴፍ ፊትዝመየር የተባሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮፌሰር ይህ የዲዮኒሲየስ ቀመር የተሳሳተ እንደሆነና በዚሁ ቀመር ላይ የተመሠረተው ክርስቶስ የተወለደው በ1 ዓ.ም. (የክርስቲያኖች ዓመት መጀመርያ ተብሎ ከሚታመንበት ዓመት) ነው የሚለው እምነትም የተሳሳተ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ እንደ ፕሮፌሰሩ ጥናት ክርስቶስ የተወለደው ሰፕቴምበር(መስከረም) 11 ክርስቶስ ተወለደ ተብሎ ከሚታመንበት ዓመት 3 ዓመት ቀደም ብሎ ነው፡፡ በማን እንደተጻፈ የማይታወቀውና Depaschg Computus በመባል የሚታወቅና ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ243 ዓ.ም. በሰሜን አፍሪካ እንደተጻፈ የሚታመን ጽሑፍ ክርስቶስ በፈረንጆቹ ማርች 28 እንደ ተወለደ ይናገራል፡፡
ከሊመንት የተባለ የአሌክሳንደሪያ ሊቀ ጳጳስ ደግሞ በ215 ዓ.ም. በጻፈው ጽሑፍ ውስጥ ክርስቶስ ኖቨምበር(ኅዳር) 18 አንደተወለደ እንደሚያምን ገልጿል፡፡
ከተደረጉ ጥናቶች አንዱም እንኳን ክርስቶስ ዲሴምበር 25 ወይም ታኅሣሥ 29 ተወለደ የሚል የለም፡፡ ይህም እነዚህ ቀናት የክርስቶስ ልደት ነው የሚለው እምነት ከየት መጣ የሚለውን ጥያቄ ያስነሳሉ፡፡ የገና በዓል፣ የገና ዛፍና የገና አባት ወዘተ. አንድ ላይ የነበሩና በአንድ ጊዜ የመጡ ጉዳዮች ሳይሆኑ በየዘመናቱ የተጨመሩ ነገሮች ናቸው፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ:- ethiopianreporter.com

👍3
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛን ደግሞ ከኢየሱስ ጋር እንዲያስነሣን ከእናንተም ጋር እንዲያቀርበን እናውቃለንና።”
2ኛ ቆሮ 4፥14