ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
333 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት

#ቃዴስ

ቃዴስ፤ ቅዱስ ማለት ነው። ከከነዓን በስተደቡብ ያለ ምድረ በዳ ስፍራ፤ መዝ. 29፥8። ቃዴስ በርኔ ተብሎም ይጠራል፤ ዘኍ. 32፥8 :: እስራኤላውያን ከግብጽ አገር ወደ ከነዓን ሲጓዙ በቃዴስ ሰፈሩ። ዐሥራ ሁለቱ ሰላዮች ከከነዓን ከተመለሱ በኋላ፥ ሕዝቡ እግዚአብሔር ወደ አገራቸው ሊያደርሳቸው እንደሚችል የተነገራቸውን ስለተጠራጠሩ እስከ ሠላሳ ሰባት ዓመት ድረስ በቃዴስ እንዲቀመጡ ተፈረደባቸው፤ ዘዳ. 1፥46። የሙሴ እኅት ማርያም በቃዴስ ሞተች። ሙሴም በዚህ ቦታ ድንጋዩን በመምታት እግዚአብሔርን አሳዘነው፤ ዘኍ. 20፥1-13።




ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 93




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤”
               2ኛ ቆሮ 2፥14



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
Zondervan Illustrated Bible Dictionary ( PDFDrive.com ).pdf
45.8 MB
📔Title፦ Zondervan Illustrated Bible Dictionary
👤Author፦ J.D Douglas and Merrill C.Tenney
🖋Revised By:- Moises Silva
📃Page፦ 3,263
💾Size፦45.8MB



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ራሱ ሊያደርግ ያለውን ያውቅ ነበርና ሊፈትነው ይህን ተናገረ።”
            ዮሐንስ 6፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
#እራሳችንን_እንመርምር


ብዙ ጊዜ ወደፊት ምን ይሆን ይሆን? እሺ፣ እንደዚያ ባይሆንስ እያልን ነገሮችን በስሌት እያወጣን እና እያወረድን የምንከርም ስንቶቻችን ነን? ወደፊት ስለሚሆነው ነገር ሁሉ ማወቅ ለእኛ ተሰጥቶናል? ታዲያ እኛ ምን እናድርግ?


“ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው።”
ዘዳግም 29፥29




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔርስ ከወደደን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል።”
              ዘኍልቁ 14፥8




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1
#መጻሕፍትን_እንመርምር


የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በሙሉ ስለጌታችን እና ስለመድኃኒታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚናገር የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ይናገራሉ። ስለሆነም በብሉይ ኪዳን ያለውን በዝርዝር ከመመልከታችን በፊት እስቲ አንዳንድ ስለኢየሱስ የተነገሩትን ትንቢቶች እንመልከት።


1. መሲሕ የሚወለደው ከሴት ነው።

(ዘፍጥረት 3:15፤ ማቴዎስ 1:20፤ ገላትያ 4-4)

2. መሲሕ የሚወለደው በቤተልሔም ነው። (ሚክያስ 5: 2፤ ማቴዎስ 2: 1፤ ሉቃስ 2: 4-6)

3. መሲሕ ከድንግል ይወለዳል

(ኢሳይያስ 7:14ማቴዎስ 1: 22-23፤ ሉቃስ 1: 26-31)

4. መሲሕ የሚመጣው ከአብርሃም ዘር ነው

ዘፍጥረት 12፥3፤ ዘፍጥረት 22:18፤ ማቴዎስ 1፥1፤ ሮሜ 9፥5

5. መሲሕ ከይስሐቅ ዘር ይሆናል።

ዘፍጥረት 17፥19፤ ዘፍጥረት 21፥12፤ ሉቃስ 3፥34

6. መሲሕ የያዕቆብ ዘር ይሆናል።

(ዘኍልቍ 24፥17፤ ማቴዎስ 1፥ 2)

7. መሲሑ የመጣው ከይሁዳ ነገድ ነው።

(ዘፍጥረት 49፥10፤ ሉቃስ 3፥33፤ ዕብራውያን 7፥14


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ https://am.eferrit.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
እንደ ግሪጎሪያን ካላንደር መሠረት የጌታችንን እና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ለምታከብሩ፣ እንኳን አደረሳችሁ! ዛሬ ማታ የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ይዘን እንጠብቃችኋለን። መልካም በዓል!


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።”
ማቴዎስ 1፥23




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ።”
         ሐዋርያት 13፥23




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትክክለኛው የልደት በዓል ቀን የቱ ነው?
Anonymous Quiz
8%
ሀ. ዲሴንበር 25 (ዛሬ ፈረንጆች እያከበሩ ያሉት)
26%
ለ. ጃንዋሪ 7 (ታህሳስ 28/29)
6%
ሐ. ጃንዋሪ 6
60%
መ. ቀኑ በትክክል አይታወቅም
👍2
🪔የንጉሡ የኢየሱስ ልደት (ማቴ. 1፡18-2፡23)



የክርስቶስን ልደት የሚገልጹ ወንጌላት ሁለት ብቻ ናቸው። ከእነዚህ ሁለቱ መካከል፥ ሉቃስ ስለ ክርስቶስ ልደት ሰፊ ምርምር ኣካሂዷል። ሉቃስ የክርስቶስን ልደት ከማርያም እይታ አንጻር ሲመለከት፥ ማቴዎስ ግን ከዮሴፍ እይታ አንጻር ይመለከታል።

የክርስቶስ ልደት የሆነው ዮሴፍና ማርያም ተጫጭተው ባሉበት ወቅት ነበር። እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ፥ የአይሁድ መተጫጨት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች ስለ ነበሩ፥ መቋረጥ የሚችሉት በፍች ነበር። በሚተጫጩበት ወቅት ማርያም «በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች» (ማቴ. 1፡18)።

ማርያም ስለሆነው ነገር ለዮሴፍ ገልጻለት ይሆናል። ስለዚህ የተጠቀሰ ነገር የለም። ነገር ግን ዮሴፍ በሆነ መንገድ ደርሶበታል። ነገር ግን ዮሴፍ የዋህ ሰው ስለ ነበር፥ ከሌላ ወንድ ለማርገዟ በይፋ ሊወቅሳት አልፈለገም። ስለሆነም ለእርሷ ሳይነግራት በስውር ሊተዋት አሰበ። እግዚአብሔር ግን ማርያም በትክክል ከመንፈስ ቅዱስ እንደፀነሰች ለዮሴፍ ለመንገር መልአኩን ላከ። ማርያም ከሌላ ሰው ጋር አላመነዘረችም ነበር። ምንም እንኳ ማርያም በማርግዟ ቢቀልዱባትም፥ ዮሴፍ እግዚአብሔርን ታዝዞ ማርያምን ወሰዳት።
እግዚአብሔር በዚህ መሢሑን ወደ ዓለም በመላኩ ሂደት ማርያምን ብቻ ሳይሆን ዮሴፍንም አክብሯል። እንደ ባልና የቤት ራስ ሁሉ፥ እግዚአብሔር ዮሴፍ ለልጁ ስም እንዲያወጣ መብት ሰጠው። ለክርስቶስ ስም በማውጣቱ፥ ዮሴፍ ሕጋዊ ኣባትነቱን እያረጋገጠ ነበር።

እግዚአብሔር ዮሴፍ ልጁን «ኢያሱ» (ዕብራዊ ስም) ወይም «ኢየሱስ» (ግሪካዊ ስም) ብሎ እንዲጠራ ነገረው። የሁለቱም ስሞች ፍች «እግዚእብሔር ደኅንነት ነው» የሚል ነው። ይህም የመሢሑ ቀዳሚ ተግባር ድል ነሺ ንጉሥ መሆን ሳይሆን፥ አዳኝ እንደሆነ የሚያመለክት ነው። ክርስቶስ «ሕዝቡን ከኃጢአታቸው የሚያድን» መንፈሳዊ አዳኝ እንጂ ፖለቲካዊ ነፃ አውጪ እንዳልሆነ ማቴዎስ ገልጾአል።
ማቴዎስ፥ የድንግሊቱ መውለድና የክርስቶስ ልደት ዝርዝር ጉዳዮች ሁሉ፥ በእግዚአብሔር በጥንቃቄ እንደታቀዱና በብሉይ ኪዳን እንደተተነበዩ አስረድቷል። ማርያም በሚያስደንቅ መንገድ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ስለ ወለደች፥ ኢየሱስ ሰውም አምላክም ሆኗል። ይህም እርሱ ብቻ «አማኑኤል» ማለትም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆኖኣል (ኢሳ. 7፡14)። በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር የክብር ደመናውን በሰዎች መካከል ያኖረ ሲሆን፥ አሁን ግን እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በሰዎች መካከል አድሯል። ክርስቶስ ወደ ሰማይ ከመመለሱ በፊት፥ ለደቀ መዛሙርቱ አሁንም አማኑኤል እንደሚሆን፥ ማለትም እስከ መጨረሻው አብሯቸው እንደሚሆን ገልጾአል (ማቴ. 28፡18-20) ማቴዎስ ክርስቶስ የብሉይ ኪዳንን ትንቢት በመፈጸም በቤተልሔም እንደ ተወለደ ተናግሯል።

ለአይሁዶች እግዚአብሔር ለአሕዛብም ዕቅድ እንዳለው ማቴዎስ አመልክቷል። እንዲሁም መጀመሪያ ክርስቶስን ያከበሩትና ያመለኩት ሰብዓ ሰገል መሆናቸውን ገልጾአል። ማቴዎስ እነዚህ ሰብዓ ሰገል ከየት እንደ መጡ ወይም ስንት እንደሆኑ አልጠቀሰም። በክርስትና ትውፊት ሦስት ሰዎች እንደሆኑ የሚታመነው ካበረከቱት ስጦታ በመነሣት ነው። ለእነዚህ ሰዎች የተሰጠው የግሪክ ስያሜ «ማጂ» (magi) የሚል ነው። ማጂ የልዩ ሃይማኖታዊ ሰዎች ቡድን ሲሆን፥ ብዙ ምሑራን ከፋርስ ወይም ከሳውዲ ዓረቢያ እንደ መጡ ያምናሉ። እነዚህ ሰዎች በከዋክብት ጥናት ይካኑ እንጂ፥ ስለ እግዚአብሔርም በቂ ግንዛቤ የነበራቸው ይመስላል። ያዩት አዲስ ኮከብ ለአይሁዶች ልዩ ንጉሥ እንደ ተወለደ የሚያመለክት መሆኑን የተረዱ ይመስላል። ለመስገድ መፈለጋቸው ደግሞ ይህ ንጉሥ ከተራ ንጉሥ በላይ መሆኑን እንደ ተገነዘቡ ያሳያል። የአይሁዶች መዲና ወደሆነችው ኢየሩሳሌም እስኪደርሱ ድረስ ለብዙ ወራት ኮከቡን ተከትለው ተጓዙ። ንጉሡ በቤተ መንግሥት ይወለዳል ብለው ስለ ገመቱ፥ ወደ ንጉሥ ሄሮድስ ሄደው ኣዲስ ስለ ተወለደው ንጉሥ ጠየቁ።

ቀደም ሲል ዙፋኔን ይነጥቁብኛል በሚል ስጋት ከቤተሰቡ አባላት መካከል ብዙ ሰዎችን የፈጀው ንጉሥ ሄሮድስ፥ ይህን ሲሰማ ደነገጠ። በመጀመሪያ፥ የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎችን ሰብስቦ ጠየቃቸው። እነዚህ ሰዎች በብሉይ ኪዳን እንደተነገረው መሢሑ ከኢየሩሳሌም ሰባት ኪሎ ሜትር ወጣ ብላ በምትገኘው በቤተልሔም እንደሚወለድ ያውቁ ነበር። ሄሮድስ ያለበትን ስፍራ አይተው እንዲነግሩት በማዘዝ ሰብዓ ሰገልን ወደ ቤተልሔም ላካቸው። ምንም እንኳ ሄሮድስ ሕጻኑን ንጉሥ ለማክበር እንደፈለገ ቢነግራቸውም፥ እውነተኛ ፍላጎቱ ግን ሕጻኑን መግደል ነበር። ኮከቡ እንደገና ለሰብዓ ሰገል ተገልጦ፥ ኢየሱስ ወደነበረበት ወደ ቤተልሔም መራቸው።

ማቴዎስን ከሉቃስ ትረካ ጋር በማነጻጸር እንደምንገነዘበው፥ ኢየሱስ ከተወለደ የተወሰነ ጊዜ አልፎ ነበር። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ከተወለደበት ግርግም ወደ ቤት ተዛውሮ ነበር። ይህም የዘመድ ቤት ወይም እነዮሴፍ የተከራዩት ቤት ሳይሆን አይቀርም። ኢየሱስ ከተወለደ ምን ያህል ጊዜ እንዳለፈ አናውቅም። ሄሮድስ ከሰብዓ ሰገል ኮከቡ መጀመሪያ የታየበትን ጊዜ ተረድቶ እስከ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ሕጻናት ሁሉ ስለ ገደለ፥ ኢየሱስ ከተወለደ ሁለት ዓመታት ሳይሞላው ኣይቀርም ተብሎ ይገመታል። ሰብዓ ሰገል ስጦታዎችን በመስጠትና እንደ አምላክ በማምለክ ክርስቶስን አክብረውታል።
እግዚአብሔርም ለሰብዓ ሰገል ያዩትን ለሄሮድስ ሳይናገሩ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል። በዚህ ታሪክ ማቴዎስ እግዚአብሔር የአይሁዶች ብቻ አምላክ እንዳልሆነና አሕዛብም የዕቅዱ አካል መሆናቸውን አመልክቷል። ክርስቶስ መሢሕ እንደሆነ በመጀመሪያ ከተገነዘቡት ሰዎች አንዳንዶቹ አሕዛብ ነበሩ። ዓለም ስለ እነርሱ ምንም ዐይነት አመለካከት ቢኖረውም ወንጌሉን ብዙውን ጊዜ እናውቃለን ከሚሉት የተሰወረው እውነት ልባቸውን ለከፈቱት ተገልጧል።

ከመሢሑ ታሪክ በስተጀርባ መንፈሳዊ ውጊያ አለ፡፡ ሰይጣን መሢሑን ለማጥፋት ፈልጎ ነበር። ይህንንም ያደረገው በዓለም ላይ ያለውን ኃይሉን እንደሚሽርበት ስለ ተገነዘበ ነበር። እግዚአብሔር ግን ልጁ ዕቅዶቹን ፈጽሞ፥ በመስቀል ላይ እንዲሞት ወስኖ ነበር። ስለዚህ ሰይጣን ኢየሱስን ለመግደል በሄሮድስ ልብ ውስጥ ያሴር እንደነበረ እግዚአብሔር በመገንዘብ፥ ዮሴፍ በመጀመሪያ ወደ ግብፅ ይዞት እንዲወርድ ከዚያም ወደ ናዝሬት ይዞት እንዲመለስ አዘዘው። ከዚያም ሄሮድስ ወደ ቤተልሔም ተጉዞ እስከ ሁለት ዓመት ዕድሜ የሆናቸውን ሕጻናት ሁሉ አስገደለ። ይህም ሰብዓ ሰገል ኢየሱስን ለማየት የመጡት ቢያንስ ከኣንድ ዓመት ተኩል እስከ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ ሳይሆን አይቀርም ወደሚል ድምዳሚ ይመራናል። በክርስቶስ ልደት ዙሪያ በተከናወኑት በእነዚህ ክስተቶች ሁሉ፥ የእግዚአብሔር እጅ እንደ ነበረበት ማቴዎስ ያውቅ ነበር። የሕጻናቱ መገደል፥ የክርስቶስ ከግብፅና በኋላም ከናዝሬት መምጣት፥ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተተንብዮአል።


ምንጭ:- ethiopiansite-com
(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ አይ ኤም ከታተመውና የዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ።”
          ዕብራውያን 12፥13




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።”
              2ኛ ቆሮ 9፥8-9




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
sparks.pdf
1.7 MB
📔ርዕስ፦ በዚያን ጊዜ
👤ደራሲ፦ ተስፋዬ ጋቢሶ
🖨አሳታሚ፦ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን

👉የዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ የሕይወት ታሪክ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4👏21
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤”
           1ኛ ጴጥሮስ 4፥10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ቅዱሳት መጻሕፍት
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት ከፍርሃት ነፃ ወጥተናል- መለየት የለም (8:31-39) ኩነኔ የማይኖርብን ከእግዚአብሔር ጽድቅ ስለምንካፈል እና ሕግ ሊኮንነን ስለማይችል ነው፡፡ ሥጋን አሸንፈን ለእግዚአብሔር እንድንኖር የእግዚአብሔር መንፈስ ስላለን ዕዳ የለብንም፡፡ ተስፋ መቁረጥም የለም፡፡ ምክንያቱም የተባረከ ተስፋችን በሆነው በክርስቶስ መመለስ የእግዚአብሔርን ክብር እንካፈላለንና፡፡ የእግዚአብሔርን ፍቅር…
የቀጠለ...


#የሮሜ_መልእክት_ጥናት




ከፍርሃት ነፃ ወጥተናል- መለየት የለም (8:31-39)



መ) ክርስቶስ ስለ እኛ ይማልዳል (8:34)

እጥፍ ምልጃ አማኝን በክርስቶስ ዋስትና ይሰጠዋል፡፡ መንፈስ ይማልዳል (8:26-27)፣ የእግዚአብሔር ልጅም ይማልድልናል (8:34):: ለእኛ የሞተልን ያው ጌታ አሁን በሰማያት ይማልድልናል፡፡ ሊቀ ካህናችን በመሆኑ ፈተናን መወጣት የምንችልበትን ጸጋና ጠላትን የምንረታበትን ጉልበት ይሰጠናል (ዕብ. 4:14-16)። ጠበቃችን ስለሆነና፣ ኃጢአታችንን ይቅር ብሎ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ኅብረት ያድሳል (1ኛ ዮሐ. 1:9-2፡2)። ምልጃ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እኛን ወክሎ ስላለ ራሳችንን መወከል አያሻንም ማለት ነው፡፡

በሮሜ 5:9-10 ባለው ክፍል ጳውሎስ የምልጃን አገልግሎት ጠቁሟል፡፡ የዳንነው በሞቱ ብቻ ሳይሆን በሕይወቱም ነው፡፡ «ስለ እነርሱም ሊማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል» (ዕብ. 7፡25)፡፡ ጴጥሮስ በጌታ ላይ ኃጢአት ሠርቶ ነበር፣ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአቱ ተፋቀለት ኅብረቱም ታደሰለት፡፡ «ስምዖን ስምዖን ሆይ፣ እነሆ፣ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ» (ሉቃስ 22፥31-32)። ስለ እያንዳንዳችን ይማልዳል ይህም አገልግሎቱ እያንዳንዳችን ዋስትና ያለን ስለመሆኑ ያረጋግጥልናል፡፡

ሠ) ክርስቶስ ይወድደናል (8:35-39)

ከቁጥር 31-34 ጳውሎስ እግዚአብሔር እንደማይተወን አረጋግጧል:: ነገር ግን እኛ ልንተወው እንችላለን? ከዚያስ? ጳውሎስ ይህንን ችግር በዚህ በመጨረሻው ክፍል ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ነገር እንደ ሌለ ያብራራል፡፡

ለመንፈሳዊ ዕድገታችን የሚያስፈልጉን ስለሆነ ብሎ (ሮሜ 5:3-5) እግዚአብሔር ከሕይወት ውጣ ውረዶች አያስጠልለንም፡፡ በሮሜ 8:28 እንደተናገረው የሕይወት ውጣ ውረዶች ለበጎ እንደሚሆኑልን እንጂ እንደማያጠፉን አረጋግጦልናል፡፡ ለራሳችን በጎነትና ለራሱ ክብር ሲል እግዚአብሔር ፈተናን ይፈቅዳል፡፡ ስለ እርሱ ብለን ፈተናን እንታገሳለን (8:36):: ይህንን በማድረጋችን እግዚአብሔር የሚተወን ይመስላችኋል? በፍጹም! ይልቁንም በሕይወት ፈተና ስናልፍ የበለጠ ይጠጋናል፡፡

በተጨማሪም፣ የምናሸንፍበትን ኃይል ይሰጠናል (ቁ. 37)። በክርስቶስ «ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::» በድል ላይ ድልን ይሰጠናል፡፡ ሕይወትንም፣ ሞትንም፣ ያለውንም፣ የሚመጣውንም አንፈራም። ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ይወድደናል፣ ድልንም ይሰጠናል:: ይህ የተስፋ ቃል በእኛ ጥረት ላይ የተመሠረተ አይደለም፣ «እንዲህ ብታደርጉ፣ እንዲህ አደርጋለሁ» አላለም፡፡ ይህ ዋስትናችን የጸና እውነት ነው፡፡ እኛ የክርስቶስ ስለሆንን ዋስትናው የራሳችን መሆኑን እናውጃለን፡፡ ከእርሱ ፍቅር ምንም ሊለያችሁ አይችልም:: እመኑና በእርሱ ሐሴት አድርጉ!

የዚህ አስደናቂ ምዕራፍ ግምገማ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ባለድል መሆኑን ያሳያል፡፡ ክርስቶስ ስለሞተልን ከፍርድ ነፃ ነን፡፡ የእርሱም ጽድቅ አለን፡፡ ክርስቶስ በመንፈሱ በእኛ ውስጥ ስለሚኖርና በሕይወቱ ስለምንካፈል፣ ከሽንፈት ነፃ ነን፡፡ ክርስቶስ ስለሚመጣና በክብሩ ስለምንካፈል ከተስፋ መቁረጥ አርነት ወጥተናል፡፡ ክርስቶስ ስለሚማልድልንና ከእርሱ ፍቅር ሊለየን የሚችል ማንም ስለሌለ፣ ከፍርሃት ነፃ ነን፡፡

ኩነኔ የለብንም! ዕዳ የለብንም! ተስፋ አንቆርጥም! ከእርሱ አንለይም!

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ማን ይቃወመናል?



ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ተስማማ፤ ገጽ 90-91




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ቅጥር እንደሌላት እንደ ፈረሰች ከተማ፥ መንፈሱን የማይከለክል ሰው እንዲሁ ነው።”
            ምሳሌ 25፥28




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ሁሉንም ፍርሃት ያዛቸውና፦ ታላቅ ነቢይ በእኛ መካከል ተነሥቶአል፥ ደግሞ፦ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጐበኘ እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።”
            ሉቃስ 7፥16




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2