' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በውስጥ ሰውነታችሁ እንድትጠነክሩ፣ ከክብሩ ባለጠግነት በመንፈሱ በኩል ኀይል እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤”
ኤፌሶን 3፥16 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤5👍3
#መጻሕፍትን_እንመርምር
ቅዱሳት መጻሕፍት በሙሉ ስለጌታችን እና መድኃኒታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይናገራሉ። በተለይ ብሉይ ኪዳን ስለእርሱ የመናገሩን ጉዳይ ብዙዎች ይጠራጠራሉ። ስለዚህ #መጻሕፍትን_እንመርምር ክፍላችን ከዚህ በኋላ ከዘፍጥረት ጀምረን ስለኢየሱስ የሚናገረውን ማየት እንጀምራለን። ስለሆነም ማንኛውም አስተያየት፣ ጥያቄ ወይም የተለየ ምልከታን እንደተለመደው በነጻነት ማቅረብ ይቻላል። ጸጋ ይብዛላችሁ!
“ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።”
ሉቃስ 24፥27

👍6❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።”
ሮሜ 13፥14

❤2👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... ኢየሱስና የመከራ ሕይወት አሳዛኙ ነገር ግን በአደጋው ወቅት አብሮ ያልነበረው ልጁ የነበረበት ሁኔታ ነው፡፡ በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውን የቤተሰቡን አባላት በማስታመም እና ከአባቱ ድንገተኛ ሞት ለመጽናናት በሚጥርበት ወቅት እነዚህ በክርስቲያኖች አንደበት ይነገሩ የነበሩ መላምቶች መጽናናትን ከባድ አድርገውበታል፡፡ የመኪና አደጋ በማንም ሰው ሊደርስ የሚችል ሆኖ ሳለ፣ ይህ ልጅም…
የቀጠለ...
ኢየሱስና የመከራ ሕይወት
በቅርቡ በኒውዚላንድ (አውስትራሊያ) ባለች “ክራይስት ቸርች” የተባለች ከተማ ተደጋጋሚ ርዕደ መሬት ደርሶ ነበር፡፡ ሰዎች ሞተዋል፤ የቤተ ክርስቲያንን ሕንጻ ጨምሮ ንብረት ወድሟል፡፡ ዜናውን በቀረበባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ “በክርስቶስ ስም በተሰየመች ከተማ እንኳ ይህ ይደርሳል? ይህች ከተማ ከአደጋው ብትተርፍ ኖሮ ለወንጌል ምስክርነት መልካም አይሆንም ነበር?” ብዬ ዐስቤአለሁ፡፡ በእርግጥ የተለያየ አደጋ ተራፊዎች በየአጋጣሚው የሚያቀርቡልን ምስክርነት ከአደጋው በተአምር ስለ መዳናቸው በመሆኑ ሁሌም ተመሳሳይ ተአምር እንዲከሰት እንድንጠብቅ አድርገውናል፡፡ በየአደጋው የሚሞቱትስ ሰዎች እምነት ስለ ጎደላቸው ነው ወይስ ይበልጥ ኀጢአተኛ ስለ ሆኑ ነው ያልተረፉት?
ይህች ምድር የኖኅ አባት እንዳለው የተረገመች ምድር ናት (ዘፍ. 5፥29)፤ በኀጢአት ምክንያት እርግማን ደርሶባታል፡፡ ስለዚህ ብዙ ኀዘን፣ ብዙ እንባ፣ ብዙ ሥቃይ፣ ብዙ ጥያቄ አለባት፡፡ የምንወዳቸው ሰዎች ድንገት ይታመማሉ፤ አደጋ ይደርስባቸዋል፤ ይሞታሉ፤ የተፈጥሮ አደጋም በየቦታው ይደርሳል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚናገረው ፍጥረት በመቃተትና በምጥ ተይዟል (ሮሜ 8፥22)፤ እኛም የፍጥረቱ አካል ነንና በተመሳሳይ ሁኔታ ነው የምንኖረው፡፡ ይህች ምድር የኀዘን ስፍራ ናት፡፡ እዚህ በምንም ሁኔታ ውስጥ ከኀዘን ነጻ መሆን አይቻልም፡፡ ይልቁኑ ኀዘን የሌለባትን “አዲሲቷን ምድር” እየናፈቅን መኖሩ ነው የሚያዋጣን፡፡ ሞት አንድ ቀን ይሸነፋል፤ “የታባቱ ሞትም ይሙት” ሲሉ መፎከር ሳያዋጣ አይቀርም፡፡ ሞት የሚሸነፍበት ቀን መኖሩን ቅዱሱ መጽሐፍ ይናገራል፡፡ ስለዚህ እርሱን ማወጅ ይበጃል፡፡
ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ እንዳደረገው ችግርና አደጋ ሲደርስ ለችግሩ ተጋላጮች መጸለይ ተገቢ ክርስቲያናዊ ኀላፊነት ነው፡፡ ከዚያ በላይ ግን ጌታም እንዳደረገው ፈጥነን መድረስና ማገዝ፣ ማጽናናት ይጠበቅብናል፡፡ ክርስቲያን በምንም ዐይነት አደጋ ውስጥ ለሚያልፉና በየትኛውም ቦታ በሚገኙ የአደጋ ሰለባዎች ፈጥኖ ደራሽ መሆን አለበት፡፡ ክርስቲያን ወደ ልቅሶና ኀዘን ቤት ለመድረስ መፍጠን አለበት፡፡ ክርስቲያን ከሚያለቅሱ ጋር ማልቀስ አለበት፡፡ በዚህ ሁሉ ግን ጥንቃቄ ማድረግ ግድ ነው፤ ጌታችን ሰዎችን ሲዳስስ እንጂ የችግሩን መንስኤ ሲያብራራ አላየንምና!
በእርግጥ ወደ እግዚአብሔር መጮኽም እንችላለን፤ እግዚአብሔር በሕዝቡ ጒዳይ ግድየለሽ አይደለምና፡፡ እንዲያውም እግዚአብሔር በሕዝቡ ጭንቀት ይጨነቃል (ኢሳ. 63፥9)፤ መከራችን ያሳዝነዋል (ዮሐ. 11፥33-35)፡፡ መከራ ከሚቀበሉ እና ከሚሠቃዩ ጋር እግዚአብሔር አብሮ መኖሩንና አብሮ መከራ መቀበሉን አለመቀበልና እግዚአብሔርን የዳር (የሩቅ) ተመልካች ማድረግ ስድብ ነው፡፡
እግዚአብሔር ግን የታሪክን መጋረጃ እስኪገልጥ ወይም ታሪክ እስከሚጠቀለልበትና ዘመኑ እስከሚዘጋበት ድረስ ሁኔታዎች አይለወጡ ይሆናል፡፡ ያኔ ግን በግልጥ ሁሉን እናያለን፡፡ እስከዚያው ድረስ በምድር ሁሌም ችግር ይኖራል! ሆኖም በሰዎች ላይ በሚደርሱ አደጋዎችና ችግሮች ላይ ተቃውሞአችንን መግለጽ እንችላለን፡፡ ግፍን መቃወም እንችላለን፤ ነቢያቱ ተቃውሞአቸውን እንደ ገለጡ፣ እኛም መቃወም እንችላለን፤ ክርስትና ግፍን ዐይተን እንዳላየ እንድናልፍ ምንም ዐይነት ፈቃድ አይሰጠንም፡፡ ለምሳሌ፣ የተፈጥሮ ሙቀት መጨመርና የአየር ብክለት ብዙ ጥፋቶችን እያደረሰ ነው፤ ሚዛናዊ የሀብት ክፍፍል አለመኖሩና የኑሮ ውድነቱ ብዙ ድኾችንና ራብተኞችን እየፈጠረ ነው፤ የፍትሕ መታጣት የብዙ ስብራትና ኀዘን እርሾ ነው፤ ይህን መቃወም ክርስቲያናዊ ኀላፊነት ነው፡፡ እንዲያውም ይህን ማድረግ ያለባቸው አማንያን ናቸው፤ ምክንያቱም ሚሮስላቭ ዎልቭ እንዳለው “የዚህን ምድር ክፋት መቃወም የሚቻለው በመልካም አምላክ መኖር ካመኑ ብቻ ነው፤ አሊያ ተቃውሞው ትርጒም አይኖረውም፡፡”
ምንጭ፦ hintset.org

👍2
ከሚከተሉት መካከል ስለአራቱ ወንጌላት ትክክል የሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
9%
ሀ. የማቴዎስ ወንጌል ሲጻፍ በዋናነት የተጻፈው ለአይሁድ ነው
3%
ለ. የሉቃስ ወንጌል በመጀመሪያ የተጻፈው ለግሪካዊያን ነው
3%
ሐ. የማርቆስ ወንጌል የመጀመሪያ ተደራሲ ሮማውያን ናቸው
19%
መ. የዮሐንስ ወንጌል ሲጻፍ ለሰው ሁሉ እንዲደርስ የታቀደ ነው።
13%
ሠ. ሀ እና ለ
54%
ረ. ሁሉም
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትድኚ ዘንድ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ አሳብ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው?”
ኤርምያስ 4፥14
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትድኚ ዘንድ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ አሳብ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው?”
ኤርምያስ 4፥14
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤3
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ያዕቆብ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን?
² ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤
³ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም።
⁴ አመንዝሮች ሆይ፥ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።
⁵ ወይስ መጽሐፍ፦ በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን?
⁶ ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል።
⁷ እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤
⁸ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።
⁹ ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ።
¹⁰ በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።

❤5👍2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።”
1ኛ ጴጥሮስ 2፥2-3

👍4❤1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ከፍርሃት ነፃ ወጥተናል- መለየት የለም (8:31-39)
ኩነኔ የማይኖርብን ከእግዚአብሔር ጽድቅ ስለምንካፈል እና ሕግ ሊኮንነን ስለማይችል ነው፡፡ ሥጋን አሸንፈን ለእግዚአብሔር እንድንኖር የእግዚአብሔር መንፈስ ስላለን ዕዳ የለብንም፡፡ ተስፋ መቁረጥም የለም፡፡ ምክንያቱም የተባረከ ተስፋችን በሆነው በክርስቶስ መመለስ የእግዚአብሔርን ክብር እንካፈላለንና፡፡ የእግዚአብሔርን ፍቅር ስለምንለማመድ መለየት የለም:- «ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል?» (ሮሜ 8:35)።
የዚህ ምእራፍ የመጨረሻ ክፍል አጽንኦት የአማኞችን ዋስትና በተመለከተ ነው:: በክርስቶስ ፍቅር ስለተጠበቅን ትናንትን፣ ዛሬንና ነገን ልንፈራ አይገባንም፡፡ በአማኝና በጌታ መካከል መለያየት አለመኖሩን ለማስረዳት ጳውሎስ አምስት ሙግቶችን አቅርቧል::
ሀ) እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው (8:31)
እግዚአብሔር አብ ከእኛ ጋር መሆኑን ለመግልጽ ልጁን ልኳል (8:32):: ወልድም ከእኛ ጋር ነው (8:34)፣ መንፈስ ቅዱስም ከእኛው ጋር ነው (8:26)፡፡ እግዚአብሔር ሁሉ ነገር ለበጎ እንደሚሆንልን አድርጓል (8:28)። በማንነቱና በአቅርቦቱ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንደ ያዕቆብ እናለቅሳለን፣ «ልጅ አልባ አስቀራችሁኝ» (ዘፍጥ. 42:36)፣ ነገር ግን ሁሉ ነገር ለበጎ ይሆንልናል:: መቋጫው ግልጽ ነው:- «እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ማን ይቃወመናል?»
አማኝ በእያንዳንዱ ቀን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደሆነ በመረዳት መኖር አለበት፡፡ ከእርሱ መልካም ነገርን ለመቀበል የግድ በፈተና ቢያልፉም አፍቃሪ አባታቸው የሚበጀውን ስለሚመኝላቸው፣ መፍራት አያስፈልጋቸውም፡፡ «ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም» (ኤር. 29:11)::
ለ) ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአል (8:32)
እዚህ ላይ ሙግቱ ከአነስተኛ ወደ ታላቅ ነው:: ኃጢአተኞች ሳለን እግዚአብሔር ምርጡን ከሰጠን፣ አሁንማ ልጆቹ ስንሆን የሚያስፈልገንን ሁሉ አይሰጠንምን? ኢየሱስም መሥጋትና መፍራት ሞኝነት መሆኑን ለሕዝቡ ለማስረዳት ሲሞክር ይህን ሙግት ተጠቅሟል፡፡ እግዚአብሔር ለወፎችና ለበጎች እንዲሁም ለሜዳ አበባ ግድ ይለዋል:: ለእኛማ በእርግጥ የበለጠ ያስብልናል፡፡ እግዚአብሔር የእርሱ ከሆኑት ጋር ያለው ተዛምዶ ሕግን የተመረኮዘ ሳይሆን፣ በቀራንዮ ጸጋው ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እግዚአብሔር የራሱ ለሆኑት ሁሉ ሁሉን በነፃ ይሰጣል፡፡
ሐ) እግዚአብሔር አጽድቆናል (8:33)
ይህም በክርስቶስ ውስጥ ጻድቅ አድርጎ ቆጥሮናል ማለት ነው፡፡ ሰይጣን ሊከሰን ይወድዳል (ራእይ 12:10፤ ዘካ. 3፡1-7)፣ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ጻድቅ ሆነን እንቆማለን፡፡ እኛ በክርስቶስ የተመረጥን፣ በክርስቶስ ተቀባይነትን ያገኘን የእግዚአብሔር ምርጦች ነን፡፡ እርሱ ራሱ ስላጸደቀን እግዚአብሔር እኛን አይከስሰንም፡፡ እርሱ የሚከስሰን ከሆነ የሰጠን ደኅንነት ዋጋ ቢስ ነው፡፡ እኛ አሁንም በኃጢአታችን አለን ማለት ነው፡፡
የጽድቅን ትርጉም መረዳት ለልባችን ሰላምን ያመጣል:: እግዚአብሔር አንድን ያመነ ኃጢአተኛ ጻድቅ ብሎ ሲጠራው ዐዋጁ መቼም ቢሆን አይለወጥም፡፡ የክርስትና ልምምዳችን ከቀን ወደ ቀን ሊቀያየር ይችላል፣ ጽድቃችን ግን አይለወጥም:: እኛ ራሳችንን እንከስ ይሆናል፣ ሰዎችም ሊከስሱን ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን ወደ ፍርድ ወንበር ወስዶ ፈጽሞ አይከሰንም፡፡ ኢየሱስ የኃጢአትን ዋጋ ስለ ከፈለ፣ እኛ ተጠብቀናል::
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ተስማማ፤ ገጽ 88-90

👍6❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ቀን የሚያመጣውን ምን እንደ ሆነ አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ።”
ምሳሌ 27፥1

❤4
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#ቃዴስ
ቃዴስ፤ ቅዱስ ማለት ነው። ከከነዓን በስተደቡብ ያለ ምድረ በዳ ስፍራ፤ መዝ. 29፥8። ቃዴስ በርኔ ተብሎም ይጠራል፤ ዘኍ. 32፥8 :: እስራኤላውያን ከግብጽ አገር ወደ ከነዓን ሲጓዙ በቃዴስ ሰፈሩ። ዐሥራ ሁለቱ ሰላዮች ከከነዓን ከተመለሱ በኋላ፥ ሕዝቡ እግዚአብሔር ወደ አገራቸው ሊያደርሳቸው እንደሚችል የተነገራቸውን ስለተጠራጠሩ እስከ ሠላሳ ሰባት ዓመት ድረስ በቃዴስ እንዲቀመጡ ተፈረደባቸው፤ ዘዳ. 1፥46። የሙሴ እኅት ማርያም በቃዴስ ሞተች። ሙሴም በዚህ ቦታ ድንጋዩን በመምታት እግዚአብሔርን አሳዘነው፤ ዘኍ. 20፥1-13።
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 93

❤4👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤”
2ኛ ቆሮ 2፥14

Zondervan Illustrated Bible Dictionary ( PDFDrive.com ).pdf
45.8 MB
📔Title፦ Zondervan Illustrated Bible Dictionary
👤Author፦ J.D Douglas and Merrill C.Tenney
🖋Revised By:- Moises Silva
📃Page፦ 3,263
💾Size፦45.8MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👤Author፦ J.D Douglas and Merrill C.Tenney
🖋Revised By:- Moises Silva
📃Page፦ 3,263
💾Size፦45.8MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ራሱ ሊያደርግ ያለውን ያውቅ ነበርና ሊፈትነው ይህን ተናገረ።”
ዮሐንስ 6፥6

❤1
#እራሳችንን_እንመርምር
ብዙ ጊዜ ወደፊት ምን ይሆን ይሆን? እሺ፣ እንደዚያ ባይሆንስ እያልን ነገሮችን በስሌት እያወጣን እና እያወረድን የምንከርም ስንቶቻችን ነን? ወደፊት ስለሚሆነው ነገር ሁሉ ማወቅ ለእኛ ተሰጥቶናል? ታዲያ እኛ ምን እናድርግ?
“ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው።”
ዘዳግም 29፥29

❤3👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔርስ ከወደደን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል።”
ዘኍልቁ 14፥8

❤5👍1
#መጻሕፍትን_እንመርምር
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በሙሉ ስለጌታችን እና ስለመድኃኒታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚናገር የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ይናገራሉ። ስለሆነም በብሉይ ኪዳን ያለውን በዝርዝር ከመመልከታችን በፊት እስቲ አንዳንድ ስለኢየሱስ የተነገሩትን ትንቢቶች እንመልከት።
1. መሲሕ የሚወለደው ከሴት ነው።
(ዘፍጥረት 3:15፤ ማቴዎስ 1:20፤ ገላትያ 4-4)
2. መሲሕ የሚወለደው በቤተልሔም ነው። (ሚክያስ 5: 2፤ ማቴዎስ 2: 1፤ ሉቃስ 2: 4-6)
3. መሲሕ ከድንግል ይወለዳል።
(ኢሳይያስ 7:14ማቴዎስ 1: 22-23፤ ሉቃስ 1: 26-31)
4. መሲሕ የሚመጣው ከአብርሃም ዘር ነው።
ዘፍጥረት 12፥3፤ ዘፍጥረት 22:18፤ ማቴዎስ 1፥1፤ ሮሜ 9፥5
5. መሲሕ ከይስሐቅ ዘር ይሆናል።
ዘፍጥረት 17፥19፤ ዘፍጥረት 21፥12፤ ሉቃስ 3፥34
6. መሲሕ የያዕቆብ ዘር ይሆናል።
(ዘኍልቍ 24፥17፤ ማቴዎስ 1፥ 2)
7. መሲሑ የመጣው ከይሁዳ ነገድ ነው።
(ዘፍጥረት 49፥10፤ ሉቃስ 3፥33፤ ዕብራውያን 7፥14
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ https://am.eferrit.com

❤3👍2
እንደ ግሪጎሪያን ካላንደር መሠረት የጌታችንን እና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ለምታከብሩ፣ እንኳን አደረሳችሁ! ዛሬ ማታ የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ይዘን እንጠብቃችኋለን። መልካም በዓል!
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።”
ማቴዎስ 1፥23
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።”
ማቴዎስ 1፥23
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤1👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ።”
ሐዋርያት 13፥23