ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
333 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#እራሳችንን_እንመርምር



የእግዚአብሔር ፈቃድ ሕይወታችንን እንዲቆጣጠረው እና በብርሃኑ መውጣት እና መግባት እንፈልጋለን? የእግዚአብሔርስ አፍ መሆንስ? ስለዚህ ምን ላድርግ?



“ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ ቱሚምህና ኡሪምህ ለቅዱስህ ሰው ነው፥ በማሳህ ለፈተንኸው፥ በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፤”
ዘዳግም 33፥8

“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።”
ኤርምያስ 15፥19




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።”
             መዝሙር 43፥3




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?



1ኛ ጢሞቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ።
³-⁴ ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።
⁵ አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
⁶ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤
⁷ እኔም ለዚህ ነገር አዋጅ ነጋሪና ሐዋርያ በእምነትና በእውነትም የአሕዛብ አስተማሪ ለመሆን ተሾምሁ፤ እውነት እናገራለሁ፤ አልዋሽም።
⁸ እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቍጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሱ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ደግሞ ሰው የሚመስል ዳሰሰኝ፥ አበረታኝም።”
           ዳንኤል 10፥18




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3
‹‹ዕርቅ - የጥበብ መንገድ››
    


                         በንጉሤ ቡልቻ

እኛ በክርስቶስ የምናምን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች አንድነትና ስምምነት አጥተን ስንጣላ የሚሆነው ነገር ምን ይመስላል ቢባል፣ በታላቅ ጥበብና ጥንቃቄ በተባለው የሸራ ቅብ ላይ አሮጌ የቀለም ጣሳ ቀድደን ድፍድፉን ቀለም ማፍሰስ ነው፣ ለመብላት ያሰፈሰፉ ሰዎች ዐይኖች በሚቋምጡት በወግ የተሰናዳ የእንጀራ ገበታ ላይ አሸዋ መድፋት ነው፤ ለድል አንድ ምዕራፍ የቀረውን ሯጭ ቋንጃ በስለት መበጠስ ነው፡፡ ጠብ የዓለም ሁሉ ሰቀቀን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቤተሰብ መካከል ጠብ ጉልበት ካገኘ ለምድርዓለም የተሰጣት የተስፋ ብርሃን ተስለመለመ ማለት ነው፡፡
 
ምን ያጣላናል? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ቢሆንም ለጊዜው ለምን እርቅ ያስቸግረናል? የሚለውን መመራመር ሳይሻል አይቀርም፡፡ የዕርቅና የአንድነት እንቅፋቶች ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ፈጥጠው የሚታዩኝን አራት ጭራቆች ብቻ ላንሳ፡፡

#አንደኛው፣ ጠብ የሚያመጣውን አደጋ አለመፍራት ነው፡፡ “የመጣው ይምጣ” የሚል ሥጋዊ ድፍረት ነው፡፡ “ኧረ ይህ ነገር ውሎ ያደረ እንደሆነ ክፉ ጣጣ አለው” ሲባል፡፡ “ምን ይመጣል ቢበዛ መለያየት ነው” የሚል መንፈሳዊ ድንዛዜ ከክርስቶስ የአንድነት ጸሎት እንዴት የራቀ እንደሆነ መገንዘብ አያዳግትም፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱን እንዲህ ብሎ ለመነው፡፡ “አንተ እንደላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ….እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ፡፡” ይህ እጅግ አሳሳቢ ጸሎት ነው እንደጌታችን አመለካከት እኛ አንድ ካልሆንን ዓለም የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛነት ለማመን ይከብዳታል ማለት ነው፡፡ የተራቀቀ የወንጌል ስርጭት ስልታችን፣ የፈረጠመው አደረጃጀታችን ወይም የካበተ ልምዳችን ሰውን ሊያሳምን አይችልም ማለት ነው፡፡

 #ሁለተኛው፣ በራስ አመለካከትና አቋም መዋጥ፣ የሌላውን ለማየት አለመቻል፣ አለመፈለግም፣ የሌላውን ወንድም ወይም ወገን የአስተሳሰብ መንገድ መናቅ፣ ማጣጣል፣ መጠራጠር፣ አዛብቶ መተርጎም፣ ይህንንም የሚመስል የራስ አስተሳሰብ ደሴተኛነት ነው፡፡ በራስ እንደመታሰር ያለ ግዞት የትም የለ፡፡

“ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር” ያለው ሐዋርያ ምሳሌ አድርጎ የሚያቀርብልን ራሱን ባዶ ያደረገውን ኢየሱስን ነው፡፡ የባልንጀራውን የአባቱን ፈቃድና አሳብ አስበልጦ ወደደ፣ የሚያስከፍለውን ከፍሎ የኋላ ሽልማቱን በክብር ተጎናጸፈ፡፡ የሌሎችን አሳብ መቀበል ኪሣራ ከመሰለን የኢየሱስ ወንድሞች ነን ለማለት እንዴት እንደፍራለን?

#ሦስተኛው፣ “አንዴ ብያለሁ፣ አሳቤን አልለውጥም” የሚል ዕቡይነት፣ ለተሻለ ነገርም ቢሆን ማፈግፈግን አለመውደድ፣ ቢያዋጣም ባያዋጣም የያዝኩትን አቋም እገፋበታለሁ የሚል ቂልነት ነው፡፡ ሞኝ ካመረረ፣ በግ ከበረረ፡፡

የጠፋው ልጅ የተሞኘው ስሜቱን ብቻ አዳምጦ ከቤት የወጣ ቀን ነው እንጂ ውድቀቱን አይቶ በልቡ የተጸጸተ ቀን አይደለም አቅጣጫ ቀይሮ ወደተገቢው ቦታ መመለስ ልባምነት ነው እንጂ ፈሪነት አይደለም፡፡ በጨለማ መንገድ መፈርጠጥ ነው ሥጋዊነት፣ መመለስ መንፈሳዊነት ነው፡፡

#አራተኛው ጭራቅ ምንድነው የተባለ እንደሆነ፣ “የታረቅሁ እንደሆነ የተስማማሁ እንደሆነ ይህ ይቀርብኛል፣ ይህ ይጎድልብኛል” የሚል የሞኝ ስስት ነው፡፡ ሽማግሌ/አስታራቂ ሰምቼ እሺ ብል ማንነቴ ይደበዝዛል፣ ክብሬ ይስለመለማል፣ ጥቅሜ ይቀናነሳል ተደማጭነቴ ዝቅ ይላል የሚል አጉል ፍርሃት በአስር በትር እንድንደባደብ ያደርገናል፡፡ የፈሪ ዱላ አሥር ነው፡፡ ዕርቅና አንድነት ያበለፅጋል እንጂ አያደኸይም፤ ለመኖርና ለመክበር ዋስትናችን የከበበን ጭፍራ ብዛት ሳይሆን የሚወደንና የሚያስብልን የእውነት ዳኛ እግዚአብሔር ነው፡፡ እውነተኛ ዕርቅ ከድርድር ሰነዱ ይልቅ በጻድቅ አምላክ ላይ ባለን እምነት የምንወስነው የጀግንነት ውሳኔ ነው፡፡




ምንጭ:- semayawithought.com
                



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይሰበሰቡም፥ የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል።”
          ኤርምያስ 51፥44




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👏2👍1
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈበት ጊዜ አንጻር የመጀመሪያው እና የመጨረሻው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
58%
ሀ. ዘፍጥረት እና የዮሐንስ ራእይ
5%
ለ. መዝሙረ ዳዊት እና የዮሐንስ ራእይ
31%
ሐ. መጽሐፍ ኢዮብ እና የዮሐንስ ራእይ
6%
መ. ዘፍጥረት እና ሚልክያስ
👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን?”
          1ኛ ቆሮንቶስ 3፥3




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።”
           1ኛ ዮሐንስ 3፥22




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
ቅዱሳት መጻሕፍት
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት የቀጠለ ... ሮሜ 8:18-30 ለክርስቲያኖች ተስፋ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። በዚህ ዓለም ላይ ርስታችንን በሙሉ አንቀበልም፤ ማለትም የተሟላ ደኅንነትን አናገኝም። አሁን የምናገኘው የውርሳችንን የወደፊት መያዛ ብቻ ነው (ኤፌ. 1፥14)። የተሟላ ውርስ ወይም ደኅንነት፥ የሥጋችን መዋጀት በኋላ ይመጣል። ስለዚህ ወደፊት የሚመጣውን ነገር ተስፋ እናደርጋለን። እኛ የዳነው…
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት

የቀጠለ ...



ሮሜ 8:18-30


እኛን ደስ ሲለንና ነገሮች እየተቃኑ በሚሄዱበት ጊዜ ከዚህ ጥቅስ ጋር ለመስማማት ቀላል ነው። ችግር በሚበዛበት ጊዜ ግን ይህ ጥቅስ ሊረዱት የማይቻል ይሆናል። ለማመንም በጣም ያስቸግራል። በመልካም ጊዜም ቢሆን፥ ይህን ጥቅስ በቀላሉ ልናየው አይገባም።

እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ይነሣል። በሁሉ ነገር እግዚአብሔር ለእኛ የሚያደርገው መልካም ከሆነ «ሁሉ ነገር» የሚለው አባባል ሰይጣንንም ይጨምራል? ማለትም እግዚአብሔር ሰይጣንንም ለእኛ መልካም ለማድረግ ይጠቀምበታል? ይህ ጥያቄ በጣም አስፈላጊ ነው። አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ሊከራክር ይችላል፤ የሰይጣንን ሥራ ለእኛ መልካም እንዲሆን የምንጠቀምበት ከሆነ፥ ሰይጣን ወዳጃችን እንጅ ጠላታችን አይደለም ማለት ነው!

ይሁን እንጂ፥ ሰይጣን ጠላታችን እንደሆነ፥ ያውም ኀይለኛና አሠቃቂ ጠላት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በሚገባ ያስተምረናል። በዚህ ዓለም የሰይጣን ሥራ ለእኛ ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ነው። ሕይወት ዘመናቸውን በወህኒ ቤት የገፉ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች፥ የተገደሉ፤ በእሳት ተቃጥለው የሞቱ፥ የተሰቀሉ፥ አንበሶች እንዲበሉአቸው የተደረጉ፥ ሁሉ ነገር ለመልካም ሆኖላቸዋል እንዴት ማለት እንችላለን? በጭራሽ አንችልም። ታዲያ ይህን ጥቅስ እንዴት ልንረዳ ይገባል? በዚህ

መንገድ እናስተውለው፥ በዚህ ምድር ስንኖር በእኛ ላይ የሚደርሰውን ማናቸውንም ነገር፥ እግዚአብሔር በመንግሥተ ሰማይ ለመልካም ያደርግልናል። ከቁ. 18-25 ጳውሎስ ስለ ወደፊት ተስፋችንና ስለ ወደፊት ክብራችን ነግሮናል። ስለዚህ በዚህ ጥቅስ ጳውሎስ የሚንግረን መልካም ነገር ሰማያዊ መልካም ነገር እንጂ ምድራዊ መልካም ነገር አይደለም። በምድር ላይ የሰይጣን ኀይል ታላቅ ነው፤ በመንግሥተ ሰማይ ግን ምንም ኀይል የለውም። በመንግሥተ ሰማይ የሰይጣን ምድራዊ ክፋቶች ሁሉ ተለውጠው ለእኛ መልካም ይሆናሉ። ነገር ግን ይህንን ካልን በኋላ፥ እግዚአብሔር ለዚህ ምድራዊ ሕይወታችን ሁሉን ነገር መልካም ለማድረግ የሚጨነቅልን መሆኑም እውነት ነው፡፡ ለሰውነታችን፥ ለጤንነታችን፥ ለምግባችንና ለልብሳችንም ቢሆን ያስብልናል። ኢየሱስም እንዲህ ብሎኣል፥ «...በመጀመሪያ መንግሥቱንና (የእግዚአብሔርን) ጽድቁን ፈልጉ ሌላውም ሁሉ ነገር ምግብም፥ ልብስም የቀረውም በተጨማሪነት ይሰጡአችኋል» (ማቴ. 6፥33)። እግዚአብሔር በሕይወታችን ችግር እንዲመጣ የሚፈቅድ ከሆነ፥ ብዙውን ጊዜ ያንን ችግር ተጠቅሞ በዚሁ በምድር ላይ በሕይወታችን መልካም ነገር እንዲመጣ ያደርጋል (ሮሜ 5፥3-41 ያዕ. 1፥2-4 )። እምነታችን የሚፈተነውና የሚጠነክረውም በችግር ነው (1ጴጥ. 1፥6-7)። በተለያዩ ችግሮች እግዚአብሔር እኛን ሥርዓት በማስተማር ሕይወታችንን ወደ ጽድቅ ይመራዋል (ዕብ. 12፥7፤10-11)። ምንም እንኳ የሰይጣን ኀይል ታላቅ ቢሆንም፥ የእግዚአብሔር ኀይል ከሰይጣን ኀይል ይበልጥ ታላቅ መሆኑን ሁልጊዜ ማስታወስ ይኖርብናል። እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያቀደውን፥ ሰይጣን ሊለውጠው አይችልም።

ስለዚህ ጥቅስ ማስታወስ የሚገባን በጣም አስፈላጊ ነገር፤ እዚህ ላይ የተሰጠው ተስፋ እግዚአብሔርን ለሚወዱና እንደፈቃዱም ለተጠሩ ሰዎች ብቻ መሆኑን ነው። እግዚአብሔርን የምንወድና እንደ ፈቃዱም የተጠራን ከሆነ፥ ሁሉን ነገር ለእኛ ለመልካም እንደሚያደርግልን በሙሉ ልባችን ልንተማመንበት እንችላለን። ተስፋችን በእግዚአብሔር ነው፤ እርሱም ታማኝ ነው፤ የሰጠውንም የተስፋ ቃል ለመፈጸም የሚቻለው ነው (ዕብ. 10፥23)።

እግዚአብሔርን የማንወድ ከሆነና እንደ ፈቃዱም ያልተጠራን ከሆነ፥ የዚህ ጥቅስ ተስፋ ለእኛ አይደለም። እዚህ ላይ እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ለጥቅማችን የማድረጉን ዋና ዓላማ እናያለን። እግዚአብሔር ለእኛ ለአማኞች ያለው የመጨረሻ ዓላማ የልጁን መልክ እንድንመስል ነው። እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ያውቀናል (ኤፌ. 1፥4-5)። ዓለም ራሱ ሳይፈጠር በፊት እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ዕቅድ ነበረው። ይህም እቅድ ልጁን ኢየሱስን መስለን መገኘት ሲሆን፤ እግዚአብሔር ልጁን ኢየሱስን የማስመሰል ሥራ የጀመረው በመጀመሪያ እንዳመንን ነው። ሥራውንም የሚያቆመው ዳግም ሰውነታችን ትንሣኤን አግኝቶ በመንግሥተ ሰማይ ሲገኝ ነው። እግዚአብሔርን የምንወድና እንደ ዓላማውም የተጠራን ከሆነ፥ በዚህ ምድር ላይ የሚደርስብን ነገር ሁሉ፤ የቱንም ያህል ክፉ ቢሆን በመጨረሻ ኢየሱስን እንድንመስል በውስጣችን ይሠራል።

ኢየሱስን ስንመስል የኢየሱስ ወንድሞች እንሆናለን፤ የእግዚአብሔርም ምኞት ኢየሱስ በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ሆኖ እንዲገኝ ነው። እዚህ ላይ ጳውሎስ የሚናገረው ስለ ቤተ ክርስቲያን ነው። ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን የተሠራችው በብዙ ወንድሞች (እኅቶችም ጭምር) ሲሆን፥ ከእነርሱም መካከል ኢየሱስ በኩር ነው።

እግዚአብሔር ዐይኖቹን በእኛ ላይ ያተኮረው ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ነው። እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ዘላለማዊ ዓላማ ጨርሶ ሊሻር አይችልም። እርሱ ገና ከመወለዳችን በፊት ያውቀናል (ቁ. 29)፡፡ ከመወለዳችን በፊት አስቀድሞ ወሰነን፥ ጠራንም። የእግዚአብሔርን ጥሪ ሰምተን በክርስቶስ አመንን፤ በእምነትም የክርስቶስን ጽድቅ ወረስን። እግዚአብሔር ነፃ አወጣን። እግዚአብሔር ልጆቹ ማለትም የኢየሱስ ወንድሞችና እኅቶች በማድረግ አከበረን። ወደ መንግሥተ ሰማይ ስንገባ ሰውነታችንን በማስነሣትና ሙሉ በሙሉ ኢየሱስን እንድንመስል በማድረግ ያከብረናል። ስለሆነም በመንግሥተ ሰማይ ክብራችን የተሟላ ይሆናል (ቁ. 18)።

ይህ ሁሉ እግዚአብሔር ያደረገልንና አሁንም የሚያደርግልን የደኅንነቱ ታላቅ ሥራ ነው። ከቁ. 29-30 ጳውሎስ የደኅንነትን ደረጃዎች ዘርዝሮአል። ከዓለም መፈጠር በፊት ጀምሮ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ዕቅድና ዓላማ፥ ደኅንነትና ዘላለማዊ ሕይወትን እንድናገኝ ነው። ታዲያ በዚህ ባጭር ሕይወታችን የሚደርስብንን ችግር ከዚህ ከታላቅ ደኅንነት ጋር እንዴት ልናወዳድረው እንችላለን? (ቁ. 18)።




ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 369-370




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠነክራል፥ እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።”
            ኢዮብ 17፥9




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት



ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
³² ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
³³ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?
³⁴ የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
³⁵ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?
³⁶ ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
³⁷ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
³⁸ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
³⁹ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።


ሮሜ 8 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ታዲያ ለዚህ ምን እንመልሳለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል?
³² ለገዛ ልጁ ያልሳሳለት፣ ነገር ግን ለሁላችንም አሳልፎ የሰጠው እርሱ፣ ሁሉንስ ነገር ከእርሱ ጋር እንደ ምን በልግስና አይሰጠን?
³³ እግዚአብሔር የመረጣቸውን የሚከስ ማን ነው? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፤
³⁴ ታዲያ የሚኰንን ማን ነው? የሞተው፣ እንዲሁም ከሞት የተነሣው፣ በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠው ክርስቶስ ኢየሱስ፣ ስለ እኛ ይማልዳል።
³⁵ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? ችግር ነው ወይስ ሥቃይ፣ ወይስ ስደት፣ ወይስ ረሀብ፣ ወይስ ዕራቍትነት፣ ወይስ አደጋ ወይስ ሰይፍ?
³⁶ ይህም፣ “ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ ከሞት ጋር እንጋፈጣለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቈጠርን” ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
³⁷ ምንም አይለየንም፤ በዚህ ሁሉ በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
³⁸ ይህን ተረድቻለሁ፤ ሞትም ይሁን ሕይወት፣ መላእክትም ይሁኑ አጋንንት፣ ያለውም ይሁን የሚመጣው፣ ወይም ማንኛውም ኀይል፣
³⁹ ከፍታም ይሁን ጥልቀት፣ ወይም የትኛውም ፍጥረት፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።



ሮሜ 8 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ታዲያ ከዚህ በኋላ ምን የሚጨመር ነገር ይኖራል? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማንስ ሊቃወመን ይችላል?
³² እግዚአብሔር ለገዛ ልጁ እንኳ ሳይራራ ስለ እኛ እንዲሞት አሳልፎ ከሰጠው ፥ ከእርሱ ጋር አብሮ ሁሉንም ነገር እንዴት አትረፍርፎ አይሰጠንም?
³³ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች ማን ሊከሳቸው ይችላል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው።
³⁴ የሚፈርድባቸውስ ማነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈርድባቸዋልን? እንዴት ተደርጎ! ስለ እኛ የሞተውና ከሞት ተነሥቶም በእግዚአብሔር አብ ቀኝ የተቀመጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይማልድልናል።
³⁵ ይህ ከሆነ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ሊለየን ይችላል? መከራ ፥ ጭንቀት ፥ ረሃብ ፥ ስደት፥ መገረፍ ፥ ፍርሃት ፥ የተመዘዘ ሰይፍ ፥ የትኛውም ዓይነት ችግር ፥ ሞትም ቢሆን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን አይችልም።
³⁶ «ስለ አንተ ፍቅር በየቀኑ እንገደላለን። እንደሚታረዱ በጎችም ተቆጥረናል» ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈ ስለሆነ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እንደሚደርሱብን አውቀን እንጠብቃለን።
³⁷ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በሕይወት ዘመናችን ቢያጋጥሙንም ፥ በወደደን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ከድል አድራጊዎች በላይ ነን።
³⁸ ከዚህም የተነሣ ፥ ሞትም ሆነ ሕይወት ፥ መላእክትም ሆኑ መናፍስት ፥ አሁን ያለውም ሆነ ወደፊት የሚመጣው ፥
³⁹ ማንኛውም ፥ 'አለሁ' የሚል ኃይል፥ከፍታም ሆነ፥ ዝቅታ፥ ወይም ማናቸውም ፍጥረት ቢሆን ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካገኘነው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንደማይችል ተረድቻለሁ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ ወደ ግብፅ አትውረድ፥ እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ እንጂ።”
          ዘፍጥረት 26፥2




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
#እራሳችንን_እንመርምር

እግዚአብሔር ወደዚህ ምድር ለምን አመጣኝ? በምንስ ምድብ ላገለግል ተጠርቻለሁ? እግዚአብሔር የቱ ጋ እንድቆም ይፈልጋል? እግዚአብሔርስ ስለ እኔ ምን ይላል? የሚሉትን ጥያቄዎች በሚገባ መመለስ የሚገባን አይመስላችሁም? አለበለዚያ ሰው የሚለንን ሁሉ ነን እያልን እየተደናበርን ማለቃችን እኮ ነው


"እንኪያስ፦ ማን ነህ? ለላኩን መልስ እንድንሰጥ፤ ስለራስህ ምን ትላለህ? አሉት። እርሱም፦ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ፦ የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ አለ።"
ዮሐንስ 1፥22-23




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በውስጥ ሰውነታችሁ እንድትጠነክሩ፣ ከክብሩ ባለጠግነት በመንፈሱ በኩል ኀይል እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤”
           ኤፌሶን 3፥16 (አዲሱ መ.ት)





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍3
#መጻሕፍትን_እንመርምር

ቅዱሳት መጻሕፍት በሙሉ ስለጌታችን እና መድኃኒታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይናገራሉ። በተለይ ብሉይ ኪዳን ስለእርሱ የመናገሩን ጉዳይ ብዙዎች ይጠራጠራሉ። ስለዚህ #መጻሕፍትን_እንመርምር ክፍላችን ከዚህ በኋላ ከዘፍጥረት ጀምረን ስለኢየሱስ የሚናገረውን ማየት እንጀምራለን። ስለሆነም ማንኛውም አስተያየት፣ ጥያቄ ወይም የተለየ ምልከታን እንደተለመደው በነጻነት ማቅረብ ይቻላል። ጸጋ ይብዛላችሁ!


“ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።”
ሉቃስ 24፥27




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።”
         ሮሜ 13፥14




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... ኢየሱስና የመከራ ሕይወት አሳዛኙ ነገር ግን በአደጋው ወቅት አብሮ ያልነበረው ልጁ የነበረበት ሁኔታ ነው፡፡ በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውን የቤተሰቡን አባላት በማስታመም እና ከአባቱ ድንገተኛ ሞት ለመጽናናት በሚጥርበት ወቅት እነዚህ በክርስቲያኖች አንደበት ይነገሩ የነበሩ መላምቶች መጽናናትን ከባድ አድርገውበታል፡፡ የመኪና አደጋ በማንም ሰው ሊደርስ የሚችል ሆኖ ሳለ፣ ይህ ልጅም…
የቀጠለ...


ኢየሱስና የመከራ ሕይወት



በቅርቡ በኒውዚላንድ (አውስትራሊያ) ባለች “ክራይስት ቸርች” የተባለች ከተማ ተደጋጋሚ ርዕደ መሬት ደርሶ ነበር፡፡ ሰዎች ሞተዋል፤ የቤተ ክርስቲያንን ሕንጻ ጨምሮ ንብረት ወድሟል፡፡ ዜናውን በቀረበባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ “በክርስቶስ ስም በተሰየመች ከተማ እንኳ ይህ ይደርሳል? ይህች ከተማ ከአደጋው ብትተርፍ ኖሮ ለወንጌል ምስክርነት መልካም አይሆንም ነበር?” ብዬ ዐስቤአለሁ፡፡ በእርግጥ የተለያየ አደጋ ተራፊዎች በየአጋጣሚው የሚያቀርቡልን ምስክርነት ከአደጋው በተአምር ስለ መዳናቸው በመሆኑ ሁሌም ተመሳሳይ ተአምር እንዲከሰት እንድንጠብቅ አድርገውናል፡፡ በየአደጋው የሚሞቱትስ ሰዎች እምነት ስለ ጎደላቸው ነው ወይስ ይበልጥ ኀጢአተኛ ስለ ሆኑ ነው ያልተረፉት?
ይህች ምድር የኖኅ አባት እንዳለው የተረገመች ምድር ናት (ዘፍ. 5፥29)፤ በኀጢአት ምክንያት እርግማን ደርሶባታል፡፡ ስለዚህ ብዙ ኀዘን፣ ብዙ እንባ፣ ብዙ ሥቃይ፣ ብዙ ጥያቄ አለባት፡፡ የምንወዳቸው ሰዎች ድንገት ይታመማሉ፤ አደጋ ይደርስባቸዋል፤ ይሞታሉ፤ የተፈጥሮ አደጋም በየቦታው ይደርሳል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚናገረው ፍጥረት በመቃተትና በምጥ ተይዟል (ሮሜ 8፥22)፤ እኛም የፍጥረቱ አካል ነንና በተመሳሳይ ሁኔታ ነው የምንኖረው፡፡ ይህች ምድር የኀዘን ስፍራ ናት፡፡ እዚህ በምንም ሁኔታ ውስጥ ከኀዘን ነጻ መሆን አይቻልም፡፡ ይልቁኑ ኀዘን የሌለባትን “አዲሲቷን ምድር” እየናፈቅን መኖሩ ነው የሚያዋጣን፡፡ ሞት አንድ ቀን ይሸነፋል፤ “የታባቱ ሞትም ይሙት” ሲሉ መፎከር ሳያዋጣ አይቀርም፡፡ ሞት የሚሸነፍበት ቀን መኖሩን ቅዱሱ መጽሐፍ ይናገራል፡፡ ስለዚህ እርሱን ማወጅ ይበጃል፡፡
ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ እንዳደረገው ችግርና አደጋ ሲደርስ ለችግሩ ተጋላጮች መጸለይ ተገቢ ክርስቲያናዊ ኀላፊነት ነው፡፡ ከዚያ በላይ ግን ጌታም እንዳደረገው ፈጥነን መድረስና ማገዝ፣ ማጽናናት ይጠበቅብናል፡፡ ክርስቲያን በምንም ዐይነት አደጋ ውስጥ ለሚያልፉና በየትኛውም ቦታ በሚገኙ የአደጋ ሰለባዎች ፈጥኖ ደራሽ መሆን አለበት፡፡ ክርስቲያን ወደ ልቅሶና ኀዘን ቤት ለመድረስ መፍጠን አለበት፡፡ ክርስቲያን ከሚያለቅሱ ጋር ማልቀስ አለበት፡፡ በዚህ ሁሉ ግን ጥንቃቄ ማድረግ ግድ ነው፤ ጌታችን ሰዎችን ሲዳስስ እንጂ የችግሩን መንስኤ ሲያብራራ አላየንምና!

በእርግጥ ወደ እግዚአብሔር መጮኽም እንችላለን፤ እግዚአብሔር በሕዝቡ ጒዳይ ግድየለሽ አይደለምና፡፡ እንዲያውም እግዚአብሔር በሕዝቡ ጭንቀት ይጨነቃል (ኢሳ. 63፥9)፤ መከራችን ያሳዝነዋል (ዮሐ. 11፥33-35)፡፡ መከራ ከሚቀበሉ እና ከሚሠቃዩ ጋር እግዚአብሔር አብሮ መኖሩንና አብሮ መከራ መቀበሉን አለመቀበልና እግዚአብሔርን የዳር (የሩቅ) ተመልካች ማድረግ ስድብ ነው፡፡

እግዚአብሔር ግን የታሪክን መጋረጃ እስኪገልጥ ወይም ታሪክ እስከሚጠቀለልበትና ዘመኑ እስከሚዘጋበት ድረስ ሁኔታዎች አይለወጡ ይሆናል፡፡ ያኔ ግን በግልጥ ሁሉን እናያለን፡፡ እስከዚያው ድረስ በምድር ሁሌም ችግር ይኖራል! ሆኖም በሰዎች ላይ በሚደርሱ አደጋዎችና ችግሮች ላይ ተቃውሞአችንን መግለጽ እንችላለን፡፡ ግፍን መቃወም እንችላለን፤ ነቢያቱ ተቃውሞአቸውን እንደ ገለጡ፣ እኛም መቃወም እንችላለን፤ ክርስትና ግፍን ዐይተን እንዳላየ እንድናልፍ ምንም ዐይነት ፈቃድ አይሰጠንም፡፡ ለምሳሌ፣ የተፈጥሮ ሙቀት መጨመርና የአየር ብክለት ብዙ ጥፋቶችን እያደረሰ ነው፤ ሚዛናዊ የሀብት ክፍፍል አለመኖሩና የኑሮ ውድነቱ ብዙ ድኾችንና ራብተኞችን እየፈጠረ ነው፤ የፍትሕ መታጣት የብዙ ስብራትና ኀዘን እርሾ ነው፤ ይህን መቃወም ክርስቲያናዊ ኀላፊነት ነው፡፡ እንዲያውም ይህን ማድረግ ያለባቸው አማንያን ናቸው፤ ምክንያቱም ሚሮስላቭ ዎልቭ እንዳለው “የዚህን ምድር ክፋት መቃወም የሚቻለው በመልካም አምላክ መኖር ካመኑ ብቻ ነው፤ አሊያ ተቃውሞው ትርጒም አይኖረውም፡፡”




ምንጭ፦ hintset.org




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትድኚ ዘንድ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ አሳብ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው?”
            ኤርምያስ 4፥14




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?



ያዕቆብ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን?
² ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤
³ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም።
⁴ አመንዝሮች ሆይ፥ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።
⁵ ወይስ መጽሐፍ፦ በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን?
⁶ ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል።
⁷ እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤
⁸ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።
⁹ ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ።
¹⁰ በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2