ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
333 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት

የቀጠለ ...



ሮሜ 8:18-30


ለክርስቲያኖች ተስፋ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። በዚህ ዓለም ላይ ርስታችንን በሙሉ አንቀበልም፤ ማለትም የተሟላ ደኅንነትን አናገኝም። አሁን የምናገኘው የውርሳችንን የወደፊት መያዛ ብቻ ነው (ኤፌ. 1፥14)። የተሟላ ውርስ ወይም ደኅንነት፥ የሥጋችን መዋጀት በኋላ ይመጣል። ስለዚህ ወደፊት የሚመጣውን ነገር ተስፋ እናደርጋለን።

እኛ የዳነው በዚሁ ተስፋ ነው (ቁ. 24)። ይህም ተስፋ የሥጋችን መዋጀት ተስፋ ነው (ቁ. 23)። ጳውሎስ በእምነት አማካይነት በዚህ ተስፋ እንድናለን ነው የሚለን። እምነት ተስፋ የምናደርገው ነገር እውነት እንደሚሆን ማረጋገጫ ነው (ዕብ. 11፥1)። ተስፋ የሚመጣው ከእምነት ነው፤ እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል እንደሚፈጸም እናምናለን። ስለሆነም ቃል የገባልንን እንደምንቀበል ተስፋ አለን።

መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ከሚያደርግልን ከብዙ ነገሮች መካከል አንዱ፤ እንድንጸልይ መርዳት ነው። አንዳንድ ጊዜ ስለምን መጸለይ እንደሚገባን አናውቅም። እኛ ምንም እንደማያውቅ፤ አባቱን የማይገባውን ወይም የሚጎዳውን ነገር እንዲሰጠው እንደሚጠይቅ ሕፃን ነን። እኛ ብዙ ጊዜ ለራሳችንም ሆነ ለሌሎች መጸለይ የሚገባንን አናውቅም።

ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ በጸሎታችን ሊረዳን የተዘጋጀ በመሆኑ፥ ልናመሰግነው ይገባናል። ልክ ክርስቶስ ለእኛ በሰማይ እንደሚማልድልን (ሮሜ 8፥34፤ ዕብ. 7፥25) ሁሉ፥ መንፈስ ቅዱስም በእኛ ውስጥ በመኖር ቃላት ሊገልጡት በማይችሉት መቃተት ለእኛ ይማልዳል።

እኛው ራሳችን ለመጸለይ ብርቱ ጥረት ካላደረግን መንፈስ ቅዱስ በእርግጥ አይረዳንም። የምንችለውን ያህል መጸለይ አለብን፤ ይህም ማለት ለጸሎት ብዙ ጊዜ መውሰድ ይገባናል።

በ1ዮሐ. 5፥14 ዮሐንስ እንዲህ ብሎ ተጽፎአል፤" . . እንደ ፈቃዱ የሆነውን ማናቸውንም ነገር ብንጠይቅ እርሱ ይሰማናል።" የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ የሚያሳየን መንፈስ ቅዱስ ነው። ከዚህም የተነሣ በእግዚአብሔር ፈቃድ መጸለይ እንችላለን።

ልባችንን የሚመረምረው እርሱ (እግዚአብሔር) የመንፈስን አእምሮ ያውቃል። ይህ መንፈስ የእግዚአብሔር የራሱ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የራሱን መንፈስ "አእምሮ ያውቃል" ማለት ነው። የእግዚአብሔር የራሱ መንፈስ ከመሆኑ የተነሣ መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ መሠረት ይማልድልናል።

እግዚአብሔር በልባችን ውስጥ ያስቀመጥነውን ነገር ሁሉ ያያል፤ ገና እርሱን ሳንለምነው የልብ ፍላጎታችንን ሁሉ ያውቃል። እግዚአብሔር ጸሎታችን በእውነት ክልብ ይሁን ወይም ለማስመሰል ከከንፈራችን ይሁን ያውቃል። በማርቆስ 7፤6 እንደተጻፈው «እነርሱ እግዚአብሔርን የሚያመልኩት በከንፈራቸው ብቻ ነው!» ተብሎ ስለ እኛ አይነገርብን።

ይህ ጥቅስ (ቁ. 28) በአዲስ ኪዳን ከሚገኙት ጥቅሶች በጣም ታላቅ ነው። በዘመናት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ታላላቅ መጽናናትና ተስፋ አግኝተውበታል። «በሁሉ ነገር እግዚአብሔር ለእኛ መልካም ነገር ያደርግልናል»። በሁሉ ነገር የሚለው አነጋገር የሚያጠቃልለው በሕይወታችን መልካምና አስደሳች የሆኑትን ነገሮች ብቻ ሳይሆን፥ ክፉውና የማያስደስት ነገሮችን ክፉው፥ በሽታና ሞትንም ያጠቃልላል። እግዚአብሔር ክፉ ነገሮችንም እንኳ ለእኛ መልካም እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። መልካም የሚያደርገው ግን ለማንም ሰው ሳይሆን “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት...” ነው።



ይቀጥላል ...



ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 369




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ቃል ኪዳኔ ከእርሱ ጋር የሕይወትና የሰላም ቃል ኪዳን ነበረ፤ ይፈራ ዘንድም እነርሱን ሰጠሁት፤ እርሱም ፈራኝ፥ ከስሜም የተነሣ ደነገጠ።”
           ሚልክያስ 2፥5





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ቅዱሳት መጻሕፍት
ኢየሱስና የመከራ ሕይወት በእግዚአብሔር ሕልውና የማያምኑ ሰዎች “እግዚአብሔር የለም” ለማለት በየዘመናቱ ከሚያነሧቸው ጥያቄዎች አንዱ በምድር ላይ የመከራ መኖር ነው፡፡ ʻእግዚአብሔር ቢኖር ይህ ሁሉ ጥፋት በሰዎች ላይ ለምን ይደርሳል?ʼ ይላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚያምኑ ሰዎችም ጥያቄውን ደጋግመው ያነሡታል፡፡ ሰዎች መከራን በተለያየ መልኩ ሲጋፈጡ በእግዚአብሔር ሕልውና፣ በእግዚአብሔር መልካምነት ወይም በእግዚአብሔር…
የቀጠለ...


ኢየሱስና የመከራ ሕይወት



አሳዛኙ ነገር ግን በአደጋው ወቅት አብሮ ያልነበረው ልጁ የነበረበት ሁኔታ ነው፡፡ በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውን የቤተሰቡን አባላት በማስታመም እና ከአባቱ ድንገተኛ ሞት ለመጽናናት በሚጥርበት ወቅት እነዚህ በክርስቲያኖች አንደበት ይነገሩ የነበሩ መላምቶች መጽናናትን ከባድ አድርገውበታል፡፡ የመኪና አደጋ በማንም ሰው ሊደርስ የሚችል ሆኖ ሳለ፣ ይህ ልጅም በዚህ አደጋ ከእግዚአብሔር ጋር የመሟገቱ አይቀሬነት እየታወቀ የየሰዉ ግዴለሽ አስተያየት ኀዘኑን የሚያብስ እንጂ የሚያጽናና አልነበረም፤ በተለይ የቅዱሳንን እገዛ በሚፈልግበት በዚያ ጊዜ! ከብዙ ጊዜ በኋላም ከዚህ ወጣት ጋር ጥቂት ጊዜ ሳሳልፍ በወቅቱ ወገኖች በሚሰነዝሩት መላምት ዛሬም ድረስ ምን ያህል እንደ ተጎዳ ለመረዳት አልከበደኝም፡፡

አደጋ በሚደርስበት ጊዜ ሁሉ መንሥኤውን (ሰበቡን) ፈልገን አንችለውም፡፡ ሰዎች ላይ አደጋ የሚደርሰው ከሌሎች የበለጡ ኀጢአተኞች ስለሆኑ አይደለም፡፡ ጌታ ኢየሱስ የጅምላ አደጋና ሥቃይ መድረሱን ለነገሩት ሰዎች ይህንኑ ነው የመለሰላቸው (ሉቃ 13፥1-5)፡፡ መከራ ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ እርምጃ በሚራመዱ ሰዎችም ላይ ይደርሳል፡፡ ስለዚህ በመከራ የሚያልፉ ሰዎችን ማጽናናት ቀዳሚ ሥራችን መሆን ይኖርበታል፡፡ በተለይ ሰዎች እግዚአብሔር ለምን ጣልቃ ገብቶ እንዳላዳናቸው በጥያቄ ተወጥረው በሚሠቃዩበት ጊዜ በቁስላቸው ላይ ጨው እንዳንነሰንስ መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡ መከራ ሰው አይመርጥም፤ ማንንም አይምርም፤ እግዚአብሔርም ጣልቃ ላይገባ ይችላል፡፡ በብሉይ ኪዳን የምናየው የኀዘን እንጉርጉሮ ብዛት እግዚአብሔር ሁልጊዜም በቀጥታ ጣልቃ እንደሚገባ እርግጠኛ እንዳንሆን ያደርገናል፡፡ ጣልቃ ገብቶ የሚታደግበት ጊዜ አለ፤ የማይገባበትም ጊዜ ሞልቶአል፡፡ ምክንያቱን የሚያውቀው እርሱ ብቻ ነው፡፡ ሙሴ እንዳለው ምስጢሩ ለአምላካችን ነው (ዘዳ. 29፥29)፡፡
ሆኖም ጌታ ኢየሱስ ሲመጣ መከራ በሰው ልጆች ላይ የሚደርስበትን ምስጢር አልነገረንም፤ መከራንም አላስቀረም፡፡ ለምን? ይልቁኑ በመከራ የሚያልፉ ሰዎችን አብሮአቸው በመሆን፣ በማጽናናትና በመፈወስ የእግዚአብሔርን አብሮ ኋኚነትና ሰው ወዳድነት አጸናልን፡፡ እግዚአብሔር ሁልጊዜም ከሕዝቡ ጋር ነው፡፡ በሞት ጥላ መካከል ስንሄድ እርሱ አብሮን አለ (መዝ. 23፥4)፤ በእሳት ውስጥ ስንጣል አብሮ አለ (ዳን. 3፥19-27)፡፡

እግዚአብሔር ከምናልፍበት መከራ ሁሌ አያስጥለን ይሆናል፤ ሁሌም ግን አብሮን አለ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ራሱን የሚሰውር አምላክ ነውና (ኢሳ. 45፥15) አብሮን መሆኑ አይታወቀን ይሆናል፡፡ ስለዚህ ከመከረኞች ጋር አብረን ስንሆን፣ በሚያልፉበት ነገር ውስጥ አልታያቸው ያለውን እግዚአብሔርን ማሳየት እንችላለን፡፡
በተለይ በምድራችን እዚህም እዚያም እየተረጨ ያለው “የብልጽግና ወንጌል” የተሰኘው አስተምህሮ አማኝነት መከራ እንዳይደርስብን ዋስትና እንደሚሆነን ማስተማሩ ይህ ዐይነቱን አለመግባባት በመፍጠር ውስጥ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡ ስለዚህ ሰዎች በሽታ ወይም ችግር ሲደርስባቸው እምነት እንደጎደላቸው ማሰብ ለብዙዎች ቀላል ነው፡፡ ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎችን ከማጽናናት እና በችግራቸው አብሮ ከመቸገር ይልቅ እምነትን በተግባር ያለ መለማመድ ምሳሌ ሲደረጉ ይታያል፡፡ ስለዚህ እነርሱም የአማኞች አብሮነት እጅግ በሚያስፈልጋቸው በችግራቸው ጊዜ ከአማኞች ለመሸሽ ይገደዳሉ፡፡ በችግር ጊዜ ደራሽና አጽናኝ መሆን የሚጠበቅባቸው አማኞች ችግርን አባባሽ ሆነው ያርፉታል፡፡ ለመሆኑ የኢዮብ “ወዳጆችስ” ከዚህ የተለየ ምን አደረጉ? እግዚአብሔር ደጋግሞ “ጻድቅና ከክፋት የራቀ” በማለት የተናገረለትን ሰው እምነት እንዳጣና ኀጢአት እንደሚለማመድ ስለዚህም መከራው እንደ ደረሰበት መናገር ምን ይባላል? እግዚአብሔር መጨረሻ የገሠጸው ግን እነርሱን ነበር፡፡ ኢዮብን ለማጽናናት ቢመጡም ተጨማሪ ሥቃይ ፈጥረውበት ሄዱ፡፡

አማኞች በሰው የሚደርስ ችግር እንደማይደርስብን ዋስትና አልተሰጠንም፡፡ እንዲያውም መከራ ሲደርስ ሰዎች ከተደጋገፉ ችግሩ ይቀልላቸዋልና እንደ አማኝ ይህን ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡
ጌታ ኢየሱስ በየትኛውም የመከራ ጕዳይ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡ ፈውስና መጽናናትን ፍለጋ ወደ እርሱ የመጡ ሰዎችን “መጀመሪያውኑ ይህ የደረሰባችሁ እምነት ስለ ጎደላችሁ፣ አዎንታዊ ቃል ስላላወጃችሁ፣ ቅርጫት ውስጥ ገንዘብ ስላልወረወራችሁ፣ የተሰበከውን ቃል የራሳችሁ ስላላደረጋችሁ፣ የተደበቀ ኀጢአት ስላለባችሁ ነው” የሚል ትንታኔ አልሰጠም፡፡ መከራ የሰዎች የአርባ ቀን ዕድል በመሆኑ ዐይናቸውን ጨፍነው እንዲቀበሉትም አላግባባም፡፡ ጌታ ኢየሱስ ሲያደርግ የኖረው አንድ ነገር ነው፤ ወደ እርሱ የመጡትን ሕመምተኞች ሁሉ ፈወሳቸው፤ ያዘኑትንም አጽናናቸው፡፡ ወደ እርሱ ያልመጡትንም ወደ እነርሱ እየሄደ ተመሳሳይ ነገር አደረገ፡፡ ፍቅርን በተግባር አስተማረ፡፡ ለነገሩማ “በአዲስ ኪዳን ውስጥ የምናገኘው እያንዳንዱ ስለ መከራ የሚያወራ ምንባብ ከመንሥኤው ይልቅ ለመከራው የሚኖረን ምላሽ ላይ የሚያተኲር ነው፡፡” እኛስ ማንን መምሰል እንፈልጋለን?




                                      በጳውሎስ ፈቃዱ


ይቀጥላል ...



ምንጭ፦ hintset.org




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“አጵሎስ ወደ አካይያ ለመሄድ በፈለገ ጊዜ፣ ወንድሞች አበረታቱት፤ በዚያ የነበሩት ደቀ መዛሙርትም እንዲቀበሉት ደብዳቤ ጻፉለት። እዚያም በደረሰ ጊዜ ከጸጋው የተነሣ አምነው ለነበሩት ትልቅ ረዳት ሆናቸው፤”
         ሐዋርያት 18፥27 (አዲሱ መ.ት)





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
ከሚከተሉት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጥቅስ የጠቀሰው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
28%
ሀ. የዮሐንስ ራእይ
56%
ለ. የዮሐንስ ወንጌል
8%
ሐ. ፊልጵስዩስ
9%
መ. ቆላስይስ
👍8
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ጢሞቴዎስ ልጄ ሆይ፥ አስቀድሞ ስለ አንተ እንደ ተነገረው ትንቢት፥ በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ፤”
        1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥18




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት



#ደብረ_ዘይት፤ የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው። ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ይገኛል። በደብረ ዘይትና በኢየሩሳሌም መካከል የቄድሮን ሸለቆ ይገኛል። ከቤተ መቅደስ አደባባይ ደብረ ዘይት ሰባ አምስት ሜትር ገደማ ከፍ ይላል። ዳዊት ከአቤሴሎም በሸሸ ጊዜ ወደ ደብረ ዘይት ዐቀበት ወጣ፤ 2ሳሙ. 15፥30። ቤተ ፋጌና ቢታንያ ከደብረ ዘይት ተራራ ግርጌ ናቸው፤

👉ኢየሱስ በሆሳዕና ዕለት ከደብረ ዘይት ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፤ ማር. 11፥1።

👉ኢየሱስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ስለ ኢየሩሳሌም መፍረስና ስለ ዓለም መጨረሻ አስተማረ፤ ማር. 13፥3።

👉ኢየሱስ ከደብረ ዘይት ግርጌ ባለው በጌቴሴማኒ በአይሁድ ጭፍሮች ተያዘ፤ ማቴ. 26፥30:36።

👉 ኢየሱስ ከደብረ ዘይት ወደ ሰማይ ዐረገ (ሉቃ. 24፥51:52፤ ሐ.ሥ. 1፥12)፤

👉እንደገናም በዓለም ፍጻሜ በደብረ ዘይት ይወርዳል የሚል ትንቢት ተነግሯል፤ ዘካ. 14፥4።




ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 228





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ሎጥ ከተለየው በኋላም እግዚአብሔር አብራምን አለው፦ ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ፤”
              ዘፍጥረት 13፥14




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
#እራሳችንን_እንመርምር



የእግዚአብሔር ፈቃድ ሕይወታችንን እንዲቆጣጠረው እና በብርሃኑ መውጣት እና መግባት እንፈልጋለን? የእግዚአብሔርስ አፍ መሆንስ? ስለዚህ ምን ላድርግ?



“ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ ቱሚምህና ኡሪምህ ለቅዱስህ ሰው ነው፥ በማሳህ ለፈተንኸው፥ በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፤”
ዘዳግም 33፥8

“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።”
ኤርምያስ 15፥19




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።”
             መዝሙር 43፥3




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?



1ኛ ጢሞቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ።
³-⁴ ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።
⁵ አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
⁶ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤
⁷ እኔም ለዚህ ነገር አዋጅ ነጋሪና ሐዋርያ በእምነትና በእውነትም የአሕዛብ አስተማሪ ለመሆን ተሾምሁ፤ እውነት እናገራለሁ፤ አልዋሽም።
⁸ እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቍጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሱ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ደግሞ ሰው የሚመስል ዳሰሰኝ፥ አበረታኝም።”
           ዳንኤል 10፥18




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3
‹‹ዕርቅ - የጥበብ መንገድ››
    


                         በንጉሤ ቡልቻ

እኛ በክርስቶስ የምናምን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች አንድነትና ስምምነት አጥተን ስንጣላ የሚሆነው ነገር ምን ይመስላል ቢባል፣ በታላቅ ጥበብና ጥንቃቄ በተባለው የሸራ ቅብ ላይ አሮጌ የቀለም ጣሳ ቀድደን ድፍድፉን ቀለም ማፍሰስ ነው፣ ለመብላት ያሰፈሰፉ ሰዎች ዐይኖች በሚቋምጡት በወግ የተሰናዳ የእንጀራ ገበታ ላይ አሸዋ መድፋት ነው፤ ለድል አንድ ምዕራፍ የቀረውን ሯጭ ቋንጃ በስለት መበጠስ ነው፡፡ ጠብ የዓለም ሁሉ ሰቀቀን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቤተሰብ መካከል ጠብ ጉልበት ካገኘ ለምድርዓለም የተሰጣት የተስፋ ብርሃን ተስለመለመ ማለት ነው፡፡
 
ምን ያጣላናል? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ቢሆንም ለጊዜው ለምን እርቅ ያስቸግረናል? የሚለውን መመራመር ሳይሻል አይቀርም፡፡ የዕርቅና የአንድነት እንቅፋቶች ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ፈጥጠው የሚታዩኝን አራት ጭራቆች ብቻ ላንሳ፡፡

#አንደኛው፣ ጠብ የሚያመጣውን አደጋ አለመፍራት ነው፡፡ “የመጣው ይምጣ” የሚል ሥጋዊ ድፍረት ነው፡፡ “ኧረ ይህ ነገር ውሎ ያደረ እንደሆነ ክፉ ጣጣ አለው” ሲባል፡፡ “ምን ይመጣል ቢበዛ መለያየት ነው” የሚል መንፈሳዊ ድንዛዜ ከክርስቶስ የአንድነት ጸሎት እንዴት የራቀ እንደሆነ መገንዘብ አያዳግትም፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱን እንዲህ ብሎ ለመነው፡፡ “አንተ እንደላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ….እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ፡፡” ይህ እጅግ አሳሳቢ ጸሎት ነው እንደጌታችን አመለካከት እኛ አንድ ካልሆንን ዓለም የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛነት ለማመን ይከብዳታል ማለት ነው፡፡ የተራቀቀ የወንጌል ስርጭት ስልታችን፣ የፈረጠመው አደረጃጀታችን ወይም የካበተ ልምዳችን ሰውን ሊያሳምን አይችልም ማለት ነው፡፡

 #ሁለተኛው፣ በራስ አመለካከትና አቋም መዋጥ፣ የሌላውን ለማየት አለመቻል፣ አለመፈለግም፣ የሌላውን ወንድም ወይም ወገን የአስተሳሰብ መንገድ መናቅ፣ ማጣጣል፣ መጠራጠር፣ አዛብቶ መተርጎም፣ ይህንንም የሚመስል የራስ አስተሳሰብ ደሴተኛነት ነው፡፡ በራስ እንደመታሰር ያለ ግዞት የትም የለ፡፡

“ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር” ያለው ሐዋርያ ምሳሌ አድርጎ የሚያቀርብልን ራሱን ባዶ ያደረገውን ኢየሱስን ነው፡፡ የባልንጀራውን የአባቱን ፈቃድና አሳብ አስበልጦ ወደደ፣ የሚያስከፍለውን ከፍሎ የኋላ ሽልማቱን በክብር ተጎናጸፈ፡፡ የሌሎችን አሳብ መቀበል ኪሣራ ከመሰለን የኢየሱስ ወንድሞች ነን ለማለት እንዴት እንደፍራለን?

#ሦስተኛው፣ “አንዴ ብያለሁ፣ አሳቤን አልለውጥም” የሚል ዕቡይነት፣ ለተሻለ ነገርም ቢሆን ማፈግፈግን አለመውደድ፣ ቢያዋጣም ባያዋጣም የያዝኩትን አቋም እገፋበታለሁ የሚል ቂልነት ነው፡፡ ሞኝ ካመረረ፣ በግ ከበረረ፡፡

የጠፋው ልጅ የተሞኘው ስሜቱን ብቻ አዳምጦ ከቤት የወጣ ቀን ነው እንጂ ውድቀቱን አይቶ በልቡ የተጸጸተ ቀን አይደለም አቅጣጫ ቀይሮ ወደተገቢው ቦታ መመለስ ልባምነት ነው እንጂ ፈሪነት አይደለም፡፡ በጨለማ መንገድ መፈርጠጥ ነው ሥጋዊነት፣ መመለስ መንፈሳዊነት ነው፡፡

#አራተኛው ጭራቅ ምንድነው የተባለ እንደሆነ፣ “የታረቅሁ እንደሆነ የተስማማሁ እንደሆነ ይህ ይቀርብኛል፣ ይህ ይጎድልብኛል” የሚል የሞኝ ስስት ነው፡፡ ሽማግሌ/አስታራቂ ሰምቼ እሺ ብል ማንነቴ ይደበዝዛል፣ ክብሬ ይስለመለማል፣ ጥቅሜ ይቀናነሳል ተደማጭነቴ ዝቅ ይላል የሚል አጉል ፍርሃት በአስር በትር እንድንደባደብ ያደርገናል፡፡ የፈሪ ዱላ አሥር ነው፡፡ ዕርቅና አንድነት ያበለፅጋል እንጂ አያደኸይም፤ ለመኖርና ለመክበር ዋስትናችን የከበበን ጭፍራ ብዛት ሳይሆን የሚወደንና የሚያስብልን የእውነት ዳኛ እግዚአብሔር ነው፡፡ እውነተኛ ዕርቅ ከድርድር ሰነዱ ይልቅ በጻድቅ አምላክ ላይ ባለን እምነት የምንወስነው የጀግንነት ውሳኔ ነው፡፡




ምንጭ:- semayawithought.com
                



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይሰበሰቡም፥ የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል።”
          ኤርምያስ 51፥44




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👏2👍1
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈበት ጊዜ አንጻር የመጀመሪያው እና የመጨረሻው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
58%
ሀ. ዘፍጥረት እና የዮሐንስ ራእይ
5%
ለ. መዝሙረ ዳዊት እና የዮሐንስ ራእይ
31%
ሐ. መጽሐፍ ኢዮብ እና የዮሐንስ ራእይ
6%
መ. ዘፍጥረት እና ሚልክያስ
👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን?”
          1ኛ ቆሮንቶስ 3፥3




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።”
           1ኛ ዮሐንስ 3፥22




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
ቅዱሳት መጻሕፍት
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት የቀጠለ ... ሮሜ 8:18-30 ለክርስቲያኖች ተስፋ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። በዚህ ዓለም ላይ ርስታችንን በሙሉ አንቀበልም፤ ማለትም የተሟላ ደኅንነትን አናገኝም። አሁን የምናገኘው የውርሳችንን የወደፊት መያዛ ብቻ ነው (ኤፌ. 1፥14)። የተሟላ ውርስ ወይም ደኅንነት፥ የሥጋችን መዋጀት በኋላ ይመጣል። ስለዚህ ወደፊት የሚመጣውን ነገር ተስፋ እናደርጋለን። እኛ የዳነው…
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት

የቀጠለ ...



ሮሜ 8:18-30


እኛን ደስ ሲለንና ነገሮች እየተቃኑ በሚሄዱበት ጊዜ ከዚህ ጥቅስ ጋር ለመስማማት ቀላል ነው። ችግር በሚበዛበት ጊዜ ግን ይህ ጥቅስ ሊረዱት የማይቻል ይሆናል። ለማመንም በጣም ያስቸግራል። በመልካም ጊዜም ቢሆን፥ ይህን ጥቅስ በቀላሉ ልናየው አይገባም።

እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ይነሣል። በሁሉ ነገር እግዚአብሔር ለእኛ የሚያደርገው መልካም ከሆነ «ሁሉ ነገር» የሚለው አባባል ሰይጣንንም ይጨምራል? ማለትም እግዚአብሔር ሰይጣንንም ለእኛ መልካም ለማድረግ ይጠቀምበታል? ይህ ጥያቄ በጣም አስፈላጊ ነው። አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ሊከራክር ይችላል፤ የሰይጣንን ሥራ ለእኛ መልካም እንዲሆን የምንጠቀምበት ከሆነ፥ ሰይጣን ወዳጃችን እንጅ ጠላታችን አይደለም ማለት ነው!

ይሁን እንጂ፥ ሰይጣን ጠላታችን እንደሆነ፥ ያውም ኀይለኛና አሠቃቂ ጠላት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በሚገባ ያስተምረናል። በዚህ ዓለም የሰይጣን ሥራ ለእኛ ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ነው። ሕይወት ዘመናቸውን በወህኒ ቤት የገፉ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች፥ የተገደሉ፤ በእሳት ተቃጥለው የሞቱ፥ የተሰቀሉ፥ አንበሶች እንዲበሉአቸው የተደረጉ፥ ሁሉ ነገር ለመልካም ሆኖላቸዋል እንዴት ማለት እንችላለን? በጭራሽ አንችልም። ታዲያ ይህን ጥቅስ እንዴት ልንረዳ ይገባል? በዚህ

መንገድ እናስተውለው፥ በዚህ ምድር ስንኖር በእኛ ላይ የሚደርሰውን ማናቸውንም ነገር፥ እግዚአብሔር በመንግሥተ ሰማይ ለመልካም ያደርግልናል። ከቁ. 18-25 ጳውሎስ ስለ ወደፊት ተስፋችንና ስለ ወደፊት ክብራችን ነግሮናል። ስለዚህ በዚህ ጥቅስ ጳውሎስ የሚንግረን መልካም ነገር ሰማያዊ መልካም ነገር እንጂ ምድራዊ መልካም ነገር አይደለም። በምድር ላይ የሰይጣን ኀይል ታላቅ ነው፤ በመንግሥተ ሰማይ ግን ምንም ኀይል የለውም። በመንግሥተ ሰማይ የሰይጣን ምድራዊ ክፋቶች ሁሉ ተለውጠው ለእኛ መልካም ይሆናሉ። ነገር ግን ይህንን ካልን በኋላ፥ እግዚአብሔር ለዚህ ምድራዊ ሕይወታችን ሁሉን ነገር መልካም ለማድረግ የሚጨነቅልን መሆኑም እውነት ነው፡፡ ለሰውነታችን፥ ለጤንነታችን፥ ለምግባችንና ለልብሳችንም ቢሆን ያስብልናል። ኢየሱስም እንዲህ ብሎኣል፥ «...በመጀመሪያ መንግሥቱንና (የእግዚአብሔርን) ጽድቁን ፈልጉ ሌላውም ሁሉ ነገር ምግብም፥ ልብስም የቀረውም በተጨማሪነት ይሰጡአችኋል» (ማቴ. 6፥33)። እግዚአብሔር በሕይወታችን ችግር እንዲመጣ የሚፈቅድ ከሆነ፥ ብዙውን ጊዜ ያንን ችግር ተጠቅሞ በዚሁ በምድር ላይ በሕይወታችን መልካም ነገር እንዲመጣ ያደርጋል (ሮሜ 5፥3-41 ያዕ. 1፥2-4 )። እምነታችን የሚፈተነውና የሚጠነክረውም በችግር ነው (1ጴጥ. 1፥6-7)። በተለያዩ ችግሮች እግዚአብሔር እኛን ሥርዓት በማስተማር ሕይወታችንን ወደ ጽድቅ ይመራዋል (ዕብ. 12፥7፤10-11)። ምንም እንኳ የሰይጣን ኀይል ታላቅ ቢሆንም፥ የእግዚአብሔር ኀይል ከሰይጣን ኀይል ይበልጥ ታላቅ መሆኑን ሁልጊዜ ማስታወስ ይኖርብናል። እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያቀደውን፥ ሰይጣን ሊለውጠው አይችልም።

ስለዚህ ጥቅስ ማስታወስ የሚገባን በጣም አስፈላጊ ነገር፤ እዚህ ላይ የተሰጠው ተስፋ እግዚአብሔርን ለሚወዱና እንደፈቃዱም ለተጠሩ ሰዎች ብቻ መሆኑን ነው። እግዚአብሔርን የምንወድና እንደ ፈቃዱም የተጠራን ከሆነ፥ ሁሉን ነገር ለእኛ ለመልካም እንደሚያደርግልን በሙሉ ልባችን ልንተማመንበት እንችላለን። ተስፋችን በእግዚአብሔር ነው፤ እርሱም ታማኝ ነው፤ የሰጠውንም የተስፋ ቃል ለመፈጸም የሚቻለው ነው (ዕብ. 10፥23)።

እግዚአብሔርን የማንወድ ከሆነና እንደ ፈቃዱም ያልተጠራን ከሆነ፥ የዚህ ጥቅስ ተስፋ ለእኛ አይደለም። እዚህ ላይ እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ለጥቅማችን የማድረጉን ዋና ዓላማ እናያለን። እግዚአብሔር ለእኛ ለአማኞች ያለው የመጨረሻ ዓላማ የልጁን መልክ እንድንመስል ነው። እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ያውቀናል (ኤፌ. 1፥4-5)። ዓለም ራሱ ሳይፈጠር በፊት እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ዕቅድ ነበረው። ይህም እቅድ ልጁን ኢየሱስን መስለን መገኘት ሲሆን፤ እግዚአብሔር ልጁን ኢየሱስን የማስመሰል ሥራ የጀመረው በመጀመሪያ እንዳመንን ነው። ሥራውንም የሚያቆመው ዳግም ሰውነታችን ትንሣኤን አግኝቶ በመንግሥተ ሰማይ ሲገኝ ነው። እግዚአብሔርን የምንወድና እንደ ዓላማውም የተጠራን ከሆነ፥ በዚህ ምድር ላይ የሚደርስብን ነገር ሁሉ፤ የቱንም ያህል ክፉ ቢሆን በመጨረሻ ኢየሱስን እንድንመስል በውስጣችን ይሠራል።

ኢየሱስን ስንመስል የኢየሱስ ወንድሞች እንሆናለን፤ የእግዚአብሔርም ምኞት ኢየሱስ በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ሆኖ እንዲገኝ ነው። እዚህ ላይ ጳውሎስ የሚናገረው ስለ ቤተ ክርስቲያን ነው። ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን የተሠራችው በብዙ ወንድሞች (እኅቶችም ጭምር) ሲሆን፥ ከእነርሱም መካከል ኢየሱስ በኩር ነው።

እግዚአብሔር ዐይኖቹን በእኛ ላይ ያተኮረው ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ነው። እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ዘላለማዊ ዓላማ ጨርሶ ሊሻር አይችልም። እርሱ ገና ከመወለዳችን በፊት ያውቀናል (ቁ. 29)፡፡ ከመወለዳችን በፊት አስቀድሞ ወሰነን፥ ጠራንም። የእግዚአብሔርን ጥሪ ሰምተን በክርስቶስ አመንን፤ በእምነትም የክርስቶስን ጽድቅ ወረስን። እግዚአብሔር ነፃ አወጣን። እግዚአብሔር ልጆቹ ማለትም የኢየሱስ ወንድሞችና እኅቶች በማድረግ አከበረን። ወደ መንግሥተ ሰማይ ስንገባ ሰውነታችንን በማስነሣትና ሙሉ በሙሉ ኢየሱስን እንድንመስል በማድረግ ያከብረናል። ስለሆነም በመንግሥተ ሰማይ ክብራችን የተሟላ ይሆናል (ቁ. 18)።

ይህ ሁሉ እግዚአብሔር ያደረገልንና አሁንም የሚያደርግልን የደኅንነቱ ታላቅ ሥራ ነው። ከቁ. 29-30 ጳውሎስ የደኅንነትን ደረጃዎች ዘርዝሮአል። ከዓለም መፈጠር በፊት ጀምሮ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ዕቅድና ዓላማ፥ ደኅንነትና ዘላለማዊ ሕይወትን እንድናገኝ ነው። ታዲያ በዚህ ባጭር ሕይወታችን የሚደርስብንን ችግር ከዚህ ከታላቅ ደኅንነት ጋር እንዴት ልናወዳድረው እንችላለን? (ቁ. 18)።




ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 369-370




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠነክራል፥ እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።”
            ኢዮብ 17፥9




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት



ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
³² ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
³³ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?
³⁴ የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
³⁵ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?
³⁶ ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
³⁷ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
³⁸ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
³⁹ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።


ሮሜ 8 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ታዲያ ለዚህ ምን እንመልሳለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል?
³² ለገዛ ልጁ ያልሳሳለት፣ ነገር ግን ለሁላችንም አሳልፎ የሰጠው እርሱ፣ ሁሉንስ ነገር ከእርሱ ጋር እንደ ምን በልግስና አይሰጠን?
³³ እግዚአብሔር የመረጣቸውን የሚከስ ማን ነው? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፤
³⁴ ታዲያ የሚኰንን ማን ነው? የሞተው፣ እንዲሁም ከሞት የተነሣው፣ በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠው ክርስቶስ ኢየሱስ፣ ስለ እኛ ይማልዳል።
³⁵ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? ችግር ነው ወይስ ሥቃይ፣ ወይስ ስደት፣ ወይስ ረሀብ፣ ወይስ ዕራቍትነት፣ ወይስ አደጋ ወይስ ሰይፍ?
³⁶ ይህም፣ “ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ ከሞት ጋር እንጋፈጣለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቈጠርን” ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
³⁷ ምንም አይለየንም፤ በዚህ ሁሉ በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
³⁸ ይህን ተረድቻለሁ፤ ሞትም ይሁን ሕይወት፣ መላእክትም ይሁኑ አጋንንት፣ ያለውም ይሁን የሚመጣው፣ ወይም ማንኛውም ኀይል፣
³⁹ ከፍታም ይሁን ጥልቀት፣ ወይም የትኛውም ፍጥረት፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።



ሮሜ 8 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ታዲያ ከዚህ በኋላ ምን የሚጨመር ነገር ይኖራል? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማንስ ሊቃወመን ይችላል?
³² እግዚአብሔር ለገዛ ልጁ እንኳ ሳይራራ ስለ እኛ እንዲሞት አሳልፎ ከሰጠው ፥ ከእርሱ ጋር አብሮ ሁሉንም ነገር እንዴት አትረፍርፎ አይሰጠንም?
³³ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች ማን ሊከሳቸው ይችላል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው።
³⁴ የሚፈርድባቸውስ ማነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈርድባቸዋልን? እንዴት ተደርጎ! ስለ እኛ የሞተውና ከሞት ተነሥቶም በእግዚአብሔር አብ ቀኝ የተቀመጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይማልድልናል።
³⁵ ይህ ከሆነ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ሊለየን ይችላል? መከራ ፥ ጭንቀት ፥ ረሃብ ፥ ስደት፥ መገረፍ ፥ ፍርሃት ፥ የተመዘዘ ሰይፍ ፥ የትኛውም ዓይነት ችግር ፥ ሞትም ቢሆን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን አይችልም።
³⁶ «ስለ አንተ ፍቅር በየቀኑ እንገደላለን። እንደሚታረዱ በጎችም ተቆጥረናል» ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈ ስለሆነ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እንደሚደርሱብን አውቀን እንጠብቃለን።
³⁷ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በሕይወት ዘመናችን ቢያጋጥሙንም ፥ በወደደን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ከድል አድራጊዎች በላይ ነን።
³⁸ ከዚህም የተነሣ ፥ ሞትም ሆነ ሕይወት ፥ መላእክትም ሆኑ መናፍስት ፥ አሁን ያለውም ሆነ ወደፊት የሚመጣው ፥
³⁹ ማንኛውም ፥ 'አለሁ' የሚል ኃይል፥ከፍታም ሆነ፥ ዝቅታ፥ ወይም ማናቸውም ፍጥረት ቢሆን ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካገኘነው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንደማይችል ተረድቻለሁ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ ወደ ግብፅ አትውረድ፥ እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ እንጂ።”
          ዘፍጥረት 26፥2




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3