#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል
ያዕቆብ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
²-³ ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት
⁴ ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።
⁵ ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።
⁶ ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።
⁷-⁸ ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው።
⁹-¹⁰ የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና።
¹¹ ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።
¹² በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።
¹³ ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።
¹⁴ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።
¹⁵ ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።
¹⁶ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ።
¹⁷ በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
¹⁸ ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።
¹⁹ ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤
²⁰ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።
²¹ ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።
²² ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።
²³ ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤
²⁴ ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል።
²⁵ ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።
²⁶ አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።
²⁷ ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

👍4
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ለጻድቅ ያለው ጥቂት ከብዙ ከኃጢአተኞች ሀብት ይበልጣል።”
መዝሙር 37፥16
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ለጻድቅ ያለው ጥቂት ከብዙ ከኃጢአተኞች ሀብት ይበልጣል።”
መዝሙር 37፥16
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5❤2
ሐዋርያው ጳውሎስ የሮሜን መልእክት ሲጽፍ በመጻፍ ያገዘው ማን ነው?
Anonymous Quiz
22%
ሀ. እራሱ ጳውሎስ ነው የጻፈው
14%
ለ. ጢሞቴዎስ
12%
ሐ. አፍሮዲጡ
11%
መ. አቂላና ጵርስቅላ
28%
ሠ. ጤርጥዮስ
9%
ረ. በርናባስ
4%
ሰ. ሲላስ
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“የጽድቅም ሥራ ሰላም፥ የጽድቅም ፍሬ ለዘላለም ጸጥታና መታመን ይሆናል።”
ኢሳይያስ 32፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“የጽድቅም ሥራ ሰላም፥ የጽድቅም ፍሬ ለዘላለም ጸጥታና መታመን ይሆናል።”
ኢሳይያስ 32፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2❤1
#እራሳችንን_እንመርምር
እግዚአብሔር ከባርነት ለምን አወጣን? ከሞት ወደ ሕይወትስ ለምን አሻገረን? ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ለምን መጣን?
“እስራኤል የበኵር ልጄ ነው፤ ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኵር ልጅህን እገድላለሁ ትለዋለህ።”
ዘጸአት 4፥23

❤1👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።”
ዮሐንስ 13፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።”
ዮሐንስ 13፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2❤1
ኢየሱስና የመከራ ሕይወት
በእግዚአብሔር ሕልውና የማያምኑ ሰዎች “እግዚአብሔር የለም” ለማለት በየዘመናቱ ከሚያነሧቸው ጥያቄዎች አንዱ በምድር ላይ የመከራ መኖር ነው፡፡ ʻእግዚአብሔር ቢኖር ይህ ሁሉ ጥፋት በሰዎች ላይ ለምን ይደርሳል?ʼ ይላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚያምኑ ሰዎችም ጥያቄውን ደጋግመው ያነሡታል፡፡ ሰዎች መከራን በተለያየ መልኩ ሲጋፈጡ በእግዚአብሔር ሕልውና፣ በእግዚአብሔር መልካምነት ወይም በእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ላይ ጥያቄ ይፈጠርባቸዋል፡፡ የመከራ ሕይወትና የእግዚአብሔር ሕልውና የተጋመዱ ናቸው፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ አውግስጢኖስ፣ “እግዚአብሔር ከሌለ ይህ ሁሉ መልካም ነገር እንዴት ይኖራል? እግዚአብሔር ካለስ እንዴት ይህ ሁሉ ክፋት ይኖራል?” ሲል የጠየቀው፡፡
ጥያቄው ተገቢ ነው፡፡ ቅዱሱ መጽሐፍም እንዲህ ያሉ ተቃውሞዎችንና ክርክሮችን በታማኝነት ዘግቦ ስላቈየልን ቅዱሳን አባቶቻችን ከእግዚአብሔር ጋር ሲሟገቱና ጥያቄ ሲያነሡ እናያለን፡፡ ለምሳሌ፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ለምን ደረሰብን?” የሚለው የጌዴዮን ጥያቄ ነው (መሳ. 6፥13)፤ ዕንባቆም ደግሞ “ሰዎችንም … አለቃ እንደሌላቸው ተንቀሳቃሾች ለምን ታደርጋቸዋለህ?” ሲል እግዚአብሔርን ይሞግታል (ዕን. 1÷14)፡፡ ኤርምያስ በተራው “እንዳንቀላፋ ሰው፣ ያድንም ዘንድ እንደማይችል ኀያል ለምን ትሆናለህ?” በማለት እግዚአብሔርን ይጠይቃል (ኤር. 14፥9)፡፡ በተለይ መዝሙረ ዳዊትን ማጥናት ለዚህ በቂ ማስረጃ ይሰጣል፤ ምክንያቱም የመዝሙራቱ ይዘት ስድሳ በመቶው ሰቆቃና እንጉርጉሮን የያዘ ነውና። ስለዚህ መዝሙረኛውም፣ “አቤቱ፣ ንቃ ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፣ ለዘወትርም አትጣለን” ሲል ለምኗል (መዝ. 44፥22)፤ “በጩኸት ደከምሁ፤ ጕሮሮዬም ሰለለ፤ አምላኬን ስጠብቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ (መዝ. 69፥3) በማለት ሲናገር፣ ጌታ ኢየሱስም “አምላኬ አምላኬ ስለ ምን ተውኸኝ?”በማለት የተናገረው ከዚሁ የመዝሙር መጽሐፍ ወስዶ ነው (ማቴ. 27፥46፤ መዝ. 22፥1)፡፡
በተለይ መከራ ሲነሣ ኢዮብን አለማንሣት አይቻልም፡፡ ሆኖም ኢዮብም ሆነ ከላይ የጠቀስናቸው ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች ባለቤት የሆኑት ሰዎች ግን የእግዚአብሔርን ሕልውና አልካዱም፤ በእግዚአብሔር ማመናቸውም ግን ተቃውሞአቸውንና ሙግታቸውን ከማቅረብ አልከለከላቸውም፡፡ እምነት ለጥያቄና ለተቃውሞ ቦታ አለውና!
እውን እግዚአብሔር እያለ ለምን ይህ ሁሉ ግፍና ሰቆቃ ይደርሳል? በእርግጥ በዚህ የመከራ ጥያቄ ላይ ብዙ ተነግሯል፣ ብዙ ተጽፏል፤ ብዙ ተሰብኳል፤ ነገር ግን ጥያቄው “ዐሥሬ ተጠይቆ፣ ዐሥሬ መልስ አግኝቶ ዳግመኛ ዐሥሬ የሚጠየቅ” ዐይነት በመሆኑ ዛሬም ልናነሣው ግድ ይሆናል፤ ወይም አንድ ቁርጥ ያለ መልስ አይኖረው ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ለዚህ ጥያቄ ምን ምላሽ እንደሚኖረው ማወቅ የምንችለው የእግዚአብሔር ነቢያት ምን እንደ ተናገሩ በመመልከት ቢሆንም፣ ከሁሉ በላይ ግን እግዚአብሔርን ያሳየንን ጌታ ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ የእግዚአብሔርን መልክ በኢየሱስ ዐይተነዋልና፡፡ ታዲያ ጌታ ኢየሱስ ምን አደረገ? ለመከራ ምን ምላሽ ነበረው?
የምድር ኑሮ ብርቱ ሰልፍ ነው፡፡ ሰዎች ዕድሜአቸው ከዘጠኝ መቶ ዓመታት በላይ ይደርስ በነበረበት በዚያ “የድንጋይ ዳቦ ዘመን” እንኳ ሰዎች ከዚህች “እግዚአብሔር ከረገማት ምድር” ማረፍን እጅግ ይናፍቁ ነበር (ዘፍ. 5፥29)፡፡ ሞትና ሥቃይ፣ ኀዘንና ልቅሶ የበዛባት ይህች ምድር መቼም የዕረፍት ስፍራ ሆና አታውቅም፡፡ ጌታ ኢየሱስም ሲወለድ ይኸው ነበር የገጠመው፡፡ በእርሱ መወለድ ብዙ ሕፃናት ሞቱ፤ የእርሱንም ነፍስ ለማትረፍ ቤተ ሰቦቹ በስደት አገር ለቅቀው መሄድ ነበረባቸው (ስደቱን የፈጸሙት ዛሬ በየዜና ማሰራጫው እንደምንከታተለው በእግር እና በጀልባ ይሆን?) (ማቴ. 2፥13-18)፡፡
ጌታችን አገልግሎቱን ሲጀምር ሰይጣን በቀላሉ ስኬትን የማግኘት ግብዣ አቅርቦለት ነበር፤ እርሱ ግን ግብዣውን ወዲያ ብሎ የመከራን መንገድ መርጧል (ማቴ. 4፥1-11)፡፡ በየቀኑ የሚገጥሙት ሰዎችም ግፍ፣ በሽታ፣ ኀዘን እና ሞት የደቆሳቸው ነበሩ፡፡ የኢዮብ “ወዳጆች” ኢዮብን ከማጽናናት ይልቅ ስለ መከራ አመጣጥ ለማስተንተን እንደ ሞከሩት ሁሉ፣ የጌታ ደቀ መዛሙርትም አንዳንድ ሰዎች ላይ ስለሚደርሰው መከራ መንሥኤ ማወቅ ይፈልጉ ነበር (ዮሐ. 9፥2)፤ እርሱ ግን አቋሙ ከዚህ የተለየ ነበር፡፡ የመከራውን መንሥኤ ሲጠየቅ ማብራሪያ ከመስጠት ይልቅ በሽታ የደቆሰውን ሰው መፈወስና ማጽናናትን ይመርጣል፡፡
አንድ ጊዜ አንደ የታወቀ አገልጋይ መኪና ሲያሽከረክር በደረሰበት አደጋ ሲሞት፣ አብረውት የነበሩ የቤተ ሰቡ አባላት ላይም ከባድ አደጋ ደረሰ፡፡ በጊዜው ስለ አሟሟቱ ብዙ መላምቶች በአማኞች ይሰነዘሩ ጀመር፡፡ ለአንዳንዶቹ፣ አገልጋዩ በተሰጠው ጸጋ መታበይ ስለ ጀመረ ነው አደጋ የደረሰበት፤ ለሌሎች ደግሞ ጥፋቱ የተገልጋዩ ሕዝብ ነበር፤ ዐይናቸውን በአገልጋዩ ላይ ስላደረጉ እግዚአብሔር ለክብሩ ቀንቶ ወሰደው፡፡ አደጋው የደረሰው ከእርሱ ጋር አብረው በነበሩት የቤተ ሰቡ አባላትም ላይ ነበር፡፡ ታዲያ “ኀጢአቱ” የእርሱ ብቻ ነበር ወይስ አብረውት የነበሩ ቤተ ሰቦቹም ጭምር? ወይስ፣ “ለኀጥአን የወረደ ለጻድቃን ይተርፋል”?
በጳውሎስ ፈቃዱ
ይቀጥላል ...
ምንጭ፦ hintset.org

“በፍርድ ዓመፃ አታድርጉ፤ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በእውነት ፍረድ።”
ዘሌዋውያን 19፥15

❤6
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“የዚያንም የመሬታዊውን መልክ እንደ ለበስን የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን።”
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥49

❤2👍1
በአዲስ ኪዳን "ጽድቅ" የሚለውን ቃል ደጋግሞ በመጠቀም የሚታወቀው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
21%
ሀ. ዕብራውያን
6%
ለ. ማቴዎስ
10%
ሐ. ገላትያ
61%
መ. ሮሜ
2%
ሠ. ዮሐንስ
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እንደዚህ ከእምነት የሆኑት ካመነው ከአብርሃም ጋር ይባረካሉ።”
ገላትያ 3፥9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እንደዚህ ከእምነት የሆኑት ካመነው ከአብርሃም ጋር ይባረካሉ።”
ገላትያ 3፥9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤3
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ሮሜ 8:18-30
እንደ ጳውሎስ ከባድ የሥቃይ ሕይወት የደረሰባቸው ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው (2ቆሮ. 6፥4–10፤ 11፥23-28)። ይህም ቢሆን ከሚመጣው ክብር ጋር ሲወዳደር የተቀበለው ሥቃይ ከቁም ነገር የሚቆጠር አይደለም (2ቆሮ. 4፥17)።
ጳውሎስ እዚህ ላይ በእኛ ውስጥ ስለሚገለጠው ክብር ይናገራል። በእኛ ውስጥ የሚገለጠው ክብር የማን ክብር ነው? የክርስቶስ ክብር ነው። እኛ ከክርስቶስ ጋር ስንነሣ የእርሱን ክብር እንቀበላለን፤ ልክ እርሱን እንመስላለን (1ዮሐ. 3፥2)። በመንፈስ ቅዱስ ለሚመሩ ሰዎች፥ ይህ ክብር አስቀድሞ በዚህ ምድር ላይ ጀምሮአል (2ቆሮ 3፥18)።
በዚህ ጥቅስ ላይ ፍጥረት የሚለው ቃል እንስሳትንና ተክሎችን ጨምሮ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች በሙሉ ያጠቃልላል። ፍጥረት በሙሉ የእግዚአብሔርን ልጆች (በክርስቶስ ያመኑትን) መገለጥ (መክበር) ይጠባበቃል። መቼ ነው እነርሱ የሚገለጡት? ያለ እግዚአብሔር ይህንን ሊያውቅ የሚችል ማንም የለም። ይሁን እንጂ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መሠረት በዓለም መጨረሻ ላይ ይገለጣሉ፤ ይህም ጊዜ ክርስቶስ በክብሩ ሊነግሥ የሚመጣበት ጊዜ ነው (ማር. 13፥23-27 31-32 2. 3፥13 ራእ. 21:1-4)። ያንን ቀን ፍጥረት በሙሉ ይጠባበቀዋል፤ ምክንያቱም በዚያን ቀን የሚገለጡት (የሚከብሩት) አማኞች ብቻ አይደሉም፤ ነገር ግን ፍጥረት ራሱም በልዩ ሁኔታ አዲስ ይሆናል።
ዓለምን ስንመለከት ያለችበት ሁኔታ በአንዳንድ መንገድ ከንቱ ነው፤ የምታደርገው ነገር ሁሉ ከንቱ ነው። ሁሉም ነገር የሚኖረው ለአጭር ጊዜ ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ ሁሉ ሕመምተኛ ሆኖ ይሞታል፤ እንደዚህ በቶሎ የሚቀጠፍ ከሆነ የሕይወት ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው? ፍጥረት በመጀመሪያ እንደዚህ አልነበረም።
እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረ በኋላ፥ የፈጠረውን ሁሉ አየ፥ እጅግ መልካም መሆኑንም ተመለከተ (ዘፍ. 1፥31)። በእግዚአብሔር የተፈጠረው ነገር ሁሉ መልካምና ውብ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር የፈጠረው ነገር ሁሉ በመጀመሪያዎቹ ወንድና ሴት፥ ማለትም በአዳምና በሔዋን ኃጢአት ምክንያት ተበላሸ (ዘፍ. 3፥1-6)። እግዚአብሔር እነርሱን እንዲህ አላቸው፥ «በእናንተ ምክንያት ምድር ተረገመች» (ዘፍ. 3፥17-18)፡፡ ስለዚህ በአንድ መንገድ በሰው ኃጢአት ምክንያት የሰው ዘር ብቻ ሳይሆን፥ መላው ፍጥረት ለፍርሃት፥ ለሞትና ለመበስበስ ተላልፎ ተሰጠ። አሳልፎ የሰጠውም እግዚአብሔር ነበር። ነገር ግን ፍጥረቱ በሙሉ በእንዲህ ዓይነት ተስፋ መቁረጥና ጭንቀት ውስጥ እንዲቀር የእግዚአብሔር ዕቅድ አልነበረም። እርሱ ፍጥረቱን አሳልፎ የሰጠው ለመደናቀፍና ለተስፋ መቁረጥ ብቻ ሳይሆን ለተስፋም ነበር። ይህም ተስፋ ወደፊት ፍጥረት ራሱ ከመበስበስ፥ ከሕመምና፥ ከሞት እስራት ነፃ እንደሚወጣ ነው (ቁ. 21)
የአሁኑ ሰማይና ምድር ሲያልፍ፥ መላው ፍጥረት በአንድ መንገድ ትንሣኤ ያገኛል። አዲስም ይሆናል፤ ዳግመኛም መበስበስና ሞት አይኖርም። ጳውሎስ ይህንን አዲስ የትንሣኤ ሁኔታ የእግዚአብሔር ልጆች ክብርና ነፃነት ይለዋል። በቀላሉ የዘላለም ሕይወት ማለት ነው። የዚህን ክብርና ነፃነት ማለትም የዚህ ዘላለማዊ ሕይወት መገለጥ ነው ፍጥረት በሙሉ በታላቅ ተስፋ የሚጠባበቀው (ቁ. 19):: ፍጥረት ሁሉ እስከ ዛሬ ድረስ በምጥ ጭንቀት ተይዞ በመቃተት ላይ መኖሩን እናውቃለን። ከገዛ ሕይወታችን ልምድ ይህ እውነት መሆኑን እናረጋግጣለን። በዚህ ዓለም በምንኖረው በሁላችንም ሕይወት ልፋት፥ ትግል፥ ሐዘን፥ ሕማምና ሞት ሁልጊዜ ይገኛሉ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ችግሮች እንደ ምጥ ጭንቅ ናቸው። አንድ ሕፃን ሲወለድ እናቱ የምጥ ጭንቅ የሚይዛት አዲስ ሕይወት ለመምጣቱ ምልክት ነው። ልክ በዚሁ ዓይነት ይህ ፍጥረት አሁን ታግሦ የሚቀበለው መከራ፤ ለመበስበስ ከታሰረበት ነፃ እንደሚወጣ ምልክት ነው (ቁ. 21)፡፡ ውጤቱም አዲስ ልደት፥ አዲስ ሕይወት፥ አዲስ ፍጥረት ይሆናል።
እኛ አማኞች የእግዚአብሔር ልጆች ነን። እኛ የምንመራውም በእግዚአብሔር መንፈስ ነው። ይሁን እንጂ፥ በውስጣዊ ሕይወታችን እንቃትታለን፡ ሥጋችንም የመበስበስ እስረኛ ነው። የመንፈስን በኩራት፥ ማለትም በክርስቶስ አዲስ ሕይወት ያለን ብንሆንም፥ በሰማይ ተዘጋጅቶ የሚቆየንን ሙሉ ርስት ገና አልተቀበልንም (2ቆሮ. 5፥5፤ ኤፌ. 1፥13- 14)። ያም ውርስ ከመበስበስና ከሞት ነፃ ወጥተን የምንከብርበት የዘላለም ሕይወት ነው (ቁ. 21)
በክርስቶስ ያመኑት ግን አስቀድመው «እግዚአብሔር የተቀበላቸው ልጆች» ሆነዋል (ቁ. 15)። ሙሉ የልጅነት ክብር እንዳንቀበልና ሙሉ መብታችንን እንዳናገኝ ግን ዕድሜአችን ገና አልደረስም ወይም ገና አላደግንም። በዚያን ቀን ሥጋችን ሙሉ ደኅንነትን በሚያገኝበት ጊዜ ወይም ሥጋችን ከሞት በሚነሣበት ጊዜ ሙሉ የልጅነት መብታችንን እንቀበላለን። በዚያን ቀን የደኅንነታችንንና የመዋጀታችንን ሙሉ በረከት እናገኛለን፤ ስለዚህ እኛም ከፍጥረት ሁሉ ጋር ያንን ቀን በናፍቆት እንጠባበቃለን (ኤፌ. 4:30)::
ይቀጥላል ...
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 368-369

👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“የቅዱሳን ልብ በአንተ ስራ ስለ ዐረፈ፥ ወንድሜ ሆይ፥ በፍቅርህ ብዙ ደስታንና መጽናናትን አግኝቼአለሁና።”
ፊልሞና 1፥7

❤2
መዝገበ ቃላት.pdf
57.3 MB
📔ርዕስ፦ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ
ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ
👤አዘጋጅ፦ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
📑የገጽ ብዛት፦ 908 💾መጠን፦57.3MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ
👤አዘጋጅ፦ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
📑የገጽ ብዛት፦ 908 💾መጠን፦57.3MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5❤1🥰1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?”
ያዕቆብ 2፥14

❤7
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ያዕቆብ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?
¹⁵ ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥
¹⁶ ከእናንተ አንዱም፦ በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?
¹⁷ እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።
¹⁸ ነገር ግን አንድ ሰው፦ አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።
¹⁹ እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
²⁰ አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?
²¹ አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?
²² እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?
²³ መጽሐፍም፦ አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።
²⁴ ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።
²⁵ እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?
²⁶ ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።

❤3👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።”
ማቴዎስ 6፥6

❤8👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።”
ሮሜ 4፥5