#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#ኢያሪኮ
ኢያሪኮ፤ ከጨው ባሕር በስተሰሜን 15፥ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ 25 ኪ.ሜ. ርቆ የሚገኝ ከተማ ነው። ሦስት ከተማዎች ኢያሪኮ ተብለዋል፤ እነርሱም፦
1. በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረ ከተማ፥
2. በክርስቶስ ዘመን የነበረ ከተማ እና
3. አሁንም ያለው ከተማ ናቸው።
ሦስቱም ቦታዎች ይቀራረባሉ። ይህም ከተማው ፈርሶ በሌላ ቦታ ሲቆረቆር በቀደመ ስሙ ተጠርቷል ማለት ነው። ኢያሪኮ ማለት የጨረቃ ከተማ ማለት ነው፡፡ በኢያሪኮ የኖሩ የጥንት ሰዎች ጨረቃን ሲያመልኩ ኖረዋል። ኢያሪኮ 250 ሜትር ከባሕሩ ጠለል ዝቅ ስለሚል፥ ከዓለም ከተሞች ሁሉ ዝቅተኛ ነው። በዙሪያው ብዙ ምንጮች ስላሉ 7000 ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ ሰዎች በኢያሪኮ መኖር ጀምረዋልቶ ዘዳ 34፥3። ኢያሱ የፊተኛውን ከተማ አፈረሰ (ኢያሱ 6) አኪኤል እንደገና ሠራው፤ 1ነገ. 16፥34። ሄሮድስ በኢያሪኮ ሞተ። ክርስቶስ በምድር ሳለ ብዙ ካህናት በኢያሪኮ ነበሩ፤ ሉቃ 10፥30፡31። ኢየሱስ በኢያሪኮ የበርጤሜዎስን ዓይን አበራ (ማር. 10፥46-52)፥ በዘኬዎስም ቤት ዋለ፤ ሉቃ 19፥1-10። ሮማውያን ኢያሪኮን በ67 ዓ.ም. አፈረሱ።
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 168
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

👍3❤2👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ትዕግሥት ታላቁን ኃጢአት ጸጥ ያደርጋልና የገዢ ቍጣ የተነሣብህ እንደ ሆነ ስፍራህን አትልቀቅ።”
መክብብ 10፥4

👍5❤4🔥1👏1
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ "ሃሌ ሉያ" የሚለው ቃል በየትኛው መጽሐፍ ውስጥ ይገኛል?
Anonymous Quiz
55%
ሀ. መዝሙረ ዳዊት
0%
ለ. ኤፌሶን
1%
ሐ. ኢሳይያስ
5%
መ. የዮሐንስ ራእይ
6%
ሠ. ሁሉም
33%
ረ. ሀ እና መ
👏6❤2👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።”
1ኛ ዮሐንስ 3፥18
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።”
1ኛ ዮሐንስ 3፥18
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2❤1🥰1👏1
#እራሳችንን_እንመርምር
በየትኛው ጊዜ እንደክርስቲያን ምን ማድረግ አለብኝ? የእግዚአብሔርስ ፈቃድ ምን ይሆን? በዚህ አስቸጋሪ ዘመን ምን ላድርግ? ምንስ አላድርግ? ቅዱሳት መጻሕፍትስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ? እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ምን ያስፈልገኝ ይሆን?
“እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር።”
1 ዜና 12፥32

👍8❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥1

👍5❤2👏1
የመንፈሳዊ ራብ በረከት
መንፈሳዊ ራብ ጌታን መናፈቅን፣እሱን ለማግኘት መጓጓትን፣ወደ እሱ ለመጠጋት ማሰብን ወዘተ ያመለክታል፡፡
በግለሰብ ይሁን በወል ደረጃ መንፈሳዊ ራብና ጥማት ለእግዚአብሔር መለኮታዊ ጉብኝት እጅግ ወሳኝ ናቸው፡፡አውነተኛ የሆነ መንፈሳዊ ራብና ጥማት እግዚአብሔርን እንድንሻው፣ እንድንፈልገውና እንድንጠጋው ኃይል ይሆኑናል፡፡ ቃሉ “ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው” (ማቴዎስ 5፡6) የሚለን ለዚህ ነው፡፡ “ብፁዓን” የሚለውን ቃል አምሊፋይድ መጽሐፍ ቅዱስ (Amplified Bible) ደስተኞች፣ በመንፈስ ባለጸጋ የሆኑ፣ የረኩ፣ የተባረኩ ወዘተ ብሎ ነው የሚገልጸው፡፡
ሐና መንፈሳዊ ራብ ያላቸው ሰዎች በጌታ ፊት ዋጋ ያላቸውና የማይረሱ እንደ ሆነ ስትናገር “ተርበው የነበሩ ከራብ አርፈዋል” (1 ሳሙኤል 2:5) ብላለች፤ አምላኳ የሚያረካ፣የሚያጠግብና የሚያሳርፍ መሆኑን በማወደስ፡፡
መንፈሳዊ ራብ በራሱ ትልቅ በረከት ነው፤ ወደ ፊት እንድንዘረጋ፣ እንድንቃትት፣ ፊቱን አንድንፈልግ ያደርገናል፡፡ የምር የሆነ መንፈሳዊ ራብ የሚመነጨው ደግሞ ያለንበትን ሁኔታ የእግዚአብሔር መንፈስ ሲያሳየንና ያለንበትን አዘቅት ስንጠላው ነው፡፡ መንፈሳዊ ራብ ይጐተጉተናል፣ አያስተኛንም፤ ቃሉ “የሠራተኛ ራብ ለርሱ ይሠራል አፉ ይጐተጉተዋል” (ምሳሌ 16፡26) ይላልና ፡፡ “ለርሱ ይሠራል” የሚለውን አስምሩልኝ፡፡ለማን? ለርሱ! አያስተኛውማ! ሳያገኝ አያሳርፈውማ! ለዚህ ነው መንፈሳዊ ራብ በራሱ የሚጓጓለት በረከት የሆነው፡፡
መንፈሳዊ ራብ ልክ እንደ ኤርምያስ ጌታን በትጋት እንድንፈልገው ያደርገናል፡፡ኤርምያስ ከብዙ ፍለጋ በኋላ ሕይወት የሚሰጠውን፣ መንፈስ የሆነውን፣ የጊዜውን ቃል ሲያገኝ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦
“ቃልህ ተገኝቷል እኔም በልቼዋለሁ፤አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃል ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ”
(ኤርምያስ 15፡16)
ከዚህ ምንባብ በጥቂቱ እንደምንረዳው፣ ኤርምያስ ቃሉን በትጋትና በተራበ መንፈስ ሲፈልግ የቆየ ይመስላል፡፡ ባገኘውም ጊዜ ከነበረው ናፍቆት የተነሣ ለመብላት ፋታ ያገኘም አይመስልም፡፡ እናም እስከሚረካና በሐሤት እስኪጥለቀለቅ ድረስ በላው፡፡
ንጉሥ ዳዊት እውነተኛ መንፈሳዊ ራብ ያላቸውን ሰዎች እግዚአብሔር እንዴት እንደሚባርክ ሲገልጽ፦ “የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፤ የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና” (መዝ 107፡9) ብሎ ተናግሯል፡፡ አዎ መንፈሳዊ ራብ የገባበት ሰው ሲቆፍር፣ ሲፈልግ፣ ሲቃትት ወዘተ ያድራል፤ ዕረፍት አይኖረውም ያንን ራብ ሳያስታግስ፡፡ ራቡ ጐትጓች ነውና፣ አያስተኛውምና፡፡
ይህን መንፈሳዊ ራብ የሚያቀጣጥሉ ሦስት የታወቁ ነገሮች አሉ፡፡እነሱም፡-
1⃣የእግዚአብሔር ቃል አብዝቶ ማጥናትና ማሰላሰል
2⃣ደጋግሞ ለረጅም ጊዜ መጾም
3⃣በጌታ ፊት በውሳኔ መውደቅ
ጌታ እንደ ተስፋ ቃሉ መንፈሳዊን ነገር በሚራቡና በሚጠሙ ሰዎች ሕይወት፣ ከብዙ መሻት በኋላ ሲገለጥ አስደናቂ ነገር የሚሆነው፡፡ለዚህ ነው ሰፋ ካለ መንፈሳዊ መነቃቃት በፊት በቤተ ክርስትያን እርሱን የሚራቡና የሚጠሙ፣ እናም በጓዳ እሱን የሚሹና የሚፈልጉ ሰዎች አስቀድሞ የሚያስነሣው፡፡
አንድ ክርስትያን ይህ ራብ በውስጡ ለረጅም ጊዜ ከጠፋ፣ ለመውደቅ እየተንሸራተተ እንደ ሆነ ሊያስብ ይገባዋል፡፡
መንፈሳዊ ራቡ ልባችንን ባሰፋነው መጠን ያድጋል፡፡ አብዝተን እንድንቃትት ያደርገናል፡፡አብዝተን ስንጸልይ ደግሞ ጸሎቱ ሌላ ከፍ ያለ መንፈሳዊ ራብን ይወልዳል፡፡የሚመጣው መንፈሳዊ ራብ ደግሞ አብዝተን እንድንጸልይ ያደርገናል፡፡ወገኖቼ አንዱ አንዱን እየጨመረ ማብቂያ የሌለው አስደናቂ ነገር ውስጥ ነው የምንገባው፤ እኛ በሥጋዊ አካሄዶች መንፈስን እስካላጠፋን ድረስ፡፡
ጌታ ሆይ ከፍ ያለ አንተን የሚሻና የሚፈልግ ልብ ስጠን !
ምንጭ:-Divine Wisdom4

👍8
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“የእግዚአብሔርንም ሕግ መጽሐፍ አነበቡ፤ ዕዝራም እግዚአብሔርን ማወቅ ያስተምርና ያስታውቅ ነበር፥ ሕዝቡም የሚነበበውን ያስተውሉ ነበር።”
ነህምያ 8፥8

❤2👍1
የእግዚአብሔርን ቃል እየተማርን ውጤት የማናመጣ ከሆነ ምን ይከተለናል?
የእግዚአብሔርን ቃል እየተማርን እውነትን ወደ ማወቅ የማንደርስ ከሆነ ማለትም ሰምተን በተግባር የማንለውጠው ከሆነ፦
1. በኃጢአት ላይ ኃጢአት እየጨመርን በኃጢአት ውስጥ በሙላት እንዘፈቃለን
2. በክፉ ምኞት በቀላሉ እንወሰዳለን
3. መንፈሰ ደካማ ወይም ሞኝ ሆነን እንቀራለን
4. የሐሰተኛ አስተማሪዎች ወይም ነቢያት መጫወቻ እንሆናለን
“ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥6-7
"እነርሱም በየቤቱ ሾልከው እየገቡ የኀጢአት ብዛት የተጫናቸውን፣ በተለያየ ክፉ ምኞት ውስጥ ገብተው የሚዋልሉ መንፈሰ ደካማ ሴቶችን የሚያጠምዱ ናቸው፤ እንደነዚህ ያሉ ሴቶች ሁል ጊዜ ይማራሉ፤ ነገር ግን እውነትን ወደ ማወቅ ፈጽሞ ሊደርሱ አይችሉም።"
2ኛ ጢሞቴዎስ 3 (አዲሱ መ.ት)

❤5👍2👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤”
ሮሜ 1፥28

❤2👍2
የዮሐንስ ራእይ ወይም በእንግሊዝኛው "Revelation (በግሪኩ 'Apokalupsis')" መጽሐፍ፣ በግሪኩ (መጀመሪያ በተጻፈበት ቋንቋ) የስሙ ትርጉም ምንድነው?
Anonymous Quiz
47%
ሀ. የተሸፈነን መግለጥ
3%
ለ. መደበቅ ወይም መሸፈን
37%
ሐ. ስለወደፊቱ መናገር
13%
መ. ማየት
👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።”
ራእይ 1፥3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።”
ራእይ 1፥3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2❤1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ሮሜ 8:18-30
ጳውሎስ በዚህ ክፍል መከራንና ሥቃይን ዳስሷል:: ይህንን ክፍል በተሻለ መንገድ ለመረዳት፣ ሦስቱን «መቃተት» መመልከት አስፈላጊ ነው፡፡ ዛሬ ሦስቱን መቃተቶች እንመለከታለን። በቀጣይ ከዚሁ ክፍል በሌላ ርዕስ ሌላ ጉዳይ እንመለከታል።
ሀ) ፍጥረት ይቃትታል (8:18-22)
እግዚአብሔር ፍጥረቱን በፈጸመ ጊዜ ሁሉም መልካም ነበር (ዘፍጥ. 1:31)፤ ነገር ግን ዛሬ ፍጥረት ይቃትታል፡፡ መከራና ሞት አለ፣ ሥቃይ አለ፡፡ ይህ ሁሉ ደግሞ የአዳም ኃጢአት ውጤት ነው፡፡ ፍጥረት በራሱ ችግር ኖሮበት አይደለም:: የፍጥረትን መታወክ ለመግለጽ ጳውሎስ የተጠቀመባቸውን ቃላት አስተውሉ፡፡ ሥቃይ (ቁ. 18)፣ ከንቱነት (ቁ. 20)፣ ባርነት (ቁ. 21)፣ ጥፋት (ቁ. 21) እና መከራ (ቁ. 22) ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህ መቃተት ዋጋ ቢስ አይደለም:: ጳውሎስ ይህን በምጥ ላይ ካለች ሴት ጋር አንጻጽሮታል፡፡ ሕመም ይኖራል፣ ነገር ግን ልጁ ሲወለድ ሥቃዩ ያከትማል፡፡ አንድ ቀን ፍጥረት አርነት ይወጣና የከበረ ፍጥረት ስለሚሆን፣ የፍጥረት መቃተት ያከትማል! አማኝ ዛሬ በሚያየው መከራ ላይ አትኩሮት አይኖረውም፡፡ የነገን ክብር ያያል (ቁ. 18፤ 2ኛ ቆሮ. 4:15-18):: የዛሬው የምጥ ባርነት በነገ የክብር ነጻነት ይለወጣል፡፡
ለ) እኛ አማኞች እንቃትታለን (8:23-25)
የምንቃትትበት ምክንያት «የመንፈስ በኩራት» ስለቀመስን ሲሆን፣ ይህም የመጭው ክብር ቅምሻ ነው:: ሰላዮቹ በተመለሱ ጊዜ እስራኤላውያን የከነዓንን በኩራት እንደቀመሱ (ዘኁል. 13:23-27)፣ እኛ ክርስቲያኖች በመንፈስ አገልግሎት የመንግሥተ ሰማያትን በረከት ቀምሰናል፡፡ ይህም ልናየው እንድንናፍቅ፣ አዲስ አካልን ለመቀበልና ከእርሱ ጋር እየኖርን ለዘለዓለም እንድናገለግለው ያደርጋል:: ክርስቶስ ሲመጣ፣ የሚኖረንን የሥጋችንን መዋጀት እየጠበቅን እንኖራለን (ፊልጵ. 3:20-21)። ይህም በተለወጥን ጊዜ ያገኘነው የእግዚአብሔር ልጅነት ከፍተኛው ደረጃ ላይ መድረስ ሲሆን፣ የልጅነት መንፈስ የልጅነትን ሥልጣን ሰጥቶ ከእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ እንድንቆም አስቻለን። ክርስቶስ ሲመለስ ወደ ሙሉ ርስታችን እንገባለን።
እስከዚያው፣ በተስፋ እንጠባበቃለን፡፡ «በተስፋ ድነናልና» (8:24)፡፡ የምን ተስፋ? «. የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም .. የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ. . .» ነው (ቲቶ 2:13)። የሚሻለው ገና ወደ ፊት ይመጣል! አማኝ በዚህ ዓለም መከራና ሥቃይን ሲያይ ተስፋ አይቆርጥም፡፡ ጊዜያዊው መከራ አንድ ቀን የክብር መግቢያ እንደሚሆን ያውቃል፡፡
ሐ) መንፈስ ቅዱስ ይቃትታል (8:25-30)
እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ መከራ ግድ ይለዋል፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ በሥጋ ሲኖር ኃጢአት በሰዎች ላይ ያደረሰውን ችግር አይቶ ቃትቷል (ማር. 7:34፣ ዮሐ. 11:33-38)። ዛሬም መንፈስ ቅዱስ ድካማችን፣ ሸክማችንና መከራችን እየተሰማው ከእኛ ጋር ይቃትታል፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ከመቃተት የበለጠ ነገር ያደርጋል:: ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን አሳብ አናውቅም፡፡ ሁልጊዜም እንዴት እንደምንጸልይ አናውቅም፣ ነገር በመከራ ፈንታ የእግዚአብሔርን አሳብ እንድናውቅ መንፈስ ስለ እኛ ይማልዳል፡፡ መንፈስ «ድካማችንን ያግዛል»፡፡
እግዚአብሔር በዓለም ላይ እንደሚሠራ እና ፍጹም የሆነ ዕቅድ ለሕይወቱ እንዳለው ስለሚያውቅ (8:28)፣ አማኝ በመከራና በፈተና ሊዝል አይገባውም (8:29)፡፡ እግዚአብሔር በዕቅዱ ሁለት ዓላማዎች አሉት:- እነርሱም የእኛ በጎ መሆንና የእርሱ ክብር ናቸው፡፡ በመጨረሻም፣ ኢየሱስን እንድንመስል ያስችለናል፡፡ ከሁሉ የሚልቀው ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ መከናወኑ ነው፡፡ ሥራውን የጀመረው ከዘለዓለም እኛን በክርስቶሰ በመረጠን ጊዜ ነው (ኤፌ. 1:4-5)፡፡ አንድ ቀን ልጁን እንድንመስል አስቀድሞ ወሰነ፡፡ የመረጣቸውን ጠራቸው (2ኛ ተሰ. 2:13-14ን ተመልከቱ)፣ ለጥሪው ምላሽ ሲሰጡ አጸደቃቻው፣ ከዚያም አከበራቸው:: ይህ የሚያሳየን አማኝ በክርስቶስ የከበረ መሆኑን ነው (ዮሐ. 17:22)፡ የዚህ ክብር መገለጥ ደግሞ የጌታን መመለስ ይጠባበቃል (ሮሜ 8:21-23)።
ይቀጥላል. . .
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ተስማማ፤ ገጽ 86-88

“ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤”
2ኛ ቆሮ 3፥5

👍3❤2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል
ያዕቆብ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
²-³ ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት
⁴ ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።
⁵ ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።
⁶ ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።
⁷-⁸ ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው።
⁹-¹⁰ የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና።
¹¹ ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።
¹² በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።
¹³ ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።
¹⁴ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።
¹⁵ ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።
¹⁶ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ።
¹⁷ በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
¹⁸ ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።
¹⁹ ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤
²⁰ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።
²¹ ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።
²² ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።
²³ ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤
²⁴ ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል።
²⁵ ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።
²⁶ አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።
²⁷ ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።

👍4
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ለጻድቅ ያለው ጥቂት ከብዙ ከኃጢአተኞች ሀብት ይበልጣል።”
መዝሙር 37፥16
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ለጻድቅ ያለው ጥቂት ከብዙ ከኃጢአተኞች ሀብት ይበልጣል።”
መዝሙር 37፥16
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5❤2
ሐዋርያው ጳውሎስ የሮሜን መልእክት ሲጽፍ በመጻፍ ያገዘው ማን ነው?
Anonymous Quiz
22%
ሀ. እራሱ ጳውሎስ ነው የጻፈው
14%
ለ. ጢሞቴዎስ
12%
ሐ. አፍሮዲጡ
11%
መ. አቂላና ጵርስቅላ
28%
ሠ. ጤርጥዮስ
9%
ረ. በርናባስ
4%
ሰ. ሲላስ
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“የጽድቅም ሥራ ሰላም፥ የጽድቅም ፍሬ ለዘላለም ጸጥታና መታመን ይሆናል።”
ኢሳይያስ 32፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“የጽድቅም ሥራ ሰላም፥ የጽድቅም ፍሬ ለዘላለም ጸጥታና መታመን ይሆናል።”
ኢሳይያስ 32፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2❤1
#እራሳችንን_እንመርምር
እግዚአብሔር ከባርነት ለምን አወጣን? ከሞት ወደ ሕይወትስ ለምን አሻገረን? ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ለምን መጣን?
“እስራኤል የበኵር ልጄ ነው፤ ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኵር ልጅህን እገድላለሁ ትለዋለህ።”
ዘጸአት 4፥23

❤1👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።”
ዮሐንስ 13፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።”
ዮሐንስ 13፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2❤1
ኢየሱስና የመከራ ሕይወት
በእግዚአብሔር ሕልውና የማያምኑ ሰዎች “እግዚአብሔር የለም” ለማለት በየዘመናቱ ከሚያነሧቸው ጥያቄዎች አንዱ በምድር ላይ የመከራ መኖር ነው፡፡ ʻእግዚአብሔር ቢኖር ይህ ሁሉ ጥፋት በሰዎች ላይ ለምን ይደርሳል?ʼ ይላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚያምኑ ሰዎችም ጥያቄውን ደጋግመው ያነሡታል፡፡ ሰዎች መከራን በተለያየ መልኩ ሲጋፈጡ በእግዚአብሔር ሕልውና፣ በእግዚአብሔር መልካምነት ወይም በእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ላይ ጥያቄ ይፈጠርባቸዋል፡፡ የመከራ ሕይወትና የእግዚአብሔር ሕልውና የተጋመዱ ናቸው፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ አውግስጢኖስ፣ “እግዚአብሔር ከሌለ ይህ ሁሉ መልካም ነገር እንዴት ይኖራል? እግዚአብሔር ካለስ እንዴት ይህ ሁሉ ክፋት ይኖራል?” ሲል የጠየቀው፡፡
ጥያቄው ተገቢ ነው፡፡ ቅዱሱ መጽሐፍም እንዲህ ያሉ ተቃውሞዎችንና ክርክሮችን በታማኝነት ዘግቦ ስላቈየልን ቅዱሳን አባቶቻችን ከእግዚአብሔር ጋር ሲሟገቱና ጥያቄ ሲያነሡ እናያለን፡፡ ለምሳሌ፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ለምን ደረሰብን?” የሚለው የጌዴዮን ጥያቄ ነው (መሳ. 6፥13)፤ ዕንባቆም ደግሞ “ሰዎችንም … አለቃ እንደሌላቸው ተንቀሳቃሾች ለምን ታደርጋቸዋለህ?” ሲል እግዚአብሔርን ይሞግታል (ዕን. 1÷14)፡፡ ኤርምያስ በተራው “እንዳንቀላፋ ሰው፣ ያድንም ዘንድ እንደማይችል ኀያል ለምን ትሆናለህ?” በማለት እግዚአብሔርን ይጠይቃል (ኤር. 14፥9)፡፡ በተለይ መዝሙረ ዳዊትን ማጥናት ለዚህ በቂ ማስረጃ ይሰጣል፤ ምክንያቱም የመዝሙራቱ ይዘት ስድሳ በመቶው ሰቆቃና እንጉርጉሮን የያዘ ነውና። ስለዚህ መዝሙረኛውም፣ “አቤቱ፣ ንቃ ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፣ ለዘወትርም አትጣለን” ሲል ለምኗል (መዝ. 44፥22)፤ “በጩኸት ደከምሁ፤ ጕሮሮዬም ሰለለ፤ አምላኬን ስጠብቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ (መዝ. 69፥3) በማለት ሲናገር፣ ጌታ ኢየሱስም “አምላኬ አምላኬ ስለ ምን ተውኸኝ?”በማለት የተናገረው ከዚሁ የመዝሙር መጽሐፍ ወስዶ ነው (ማቴ. 27፥46፤ መዝ. 22፥1)፡፡
በተለይ መከራ ሲነሣ ኢዮብን አለማንሣት አይቻልም፡፡ ሆኖም ኢዮብም ሆነ ከላይ የጠቀስናቸው ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች ባለቤት የሆኑት ሰዎች ግን የእግዚአብሔርን ሕልውና አልካዱም፤ በእግዚአብሔር ማመናቸውም ግን ተቃውሞአቸውንና ሙግታቸውን ከማቅረብ አልከለከላቸውም፡፡ እምነት ለጥያቄና ለተቃውሞ ቦታ አለውና!
እውን እግዚአብሔር እያለ ለምን ይህ ሁሉ ግፍና ሰቆቃ ይደርሳል? በእርግጥ በዚህ የመከራ ጥያቄ ላይ ብዙ ተነግሯል፣ ብዙ ተጽፏል፤ ብዙ ተሰብኳል፤ ነገር ግን ጥያቄው “ዐሥሬ ተጠይቆ፣ ዐሥሬ መልስ አግኝቶ ዳግመኛ ዐሥሬ የሚጠየቅ” ዐይነት በመሆኑ ዛሬም ልናነሣው ግድ ይሆናል፤ ወይም አንድ ቁርጥ ያለ መልስ አይኖረው ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ለዚህ ጥያቄ ምን ምላሽ እንደሚኖረው ማወቅ የምንችለው የእግዚአብሔር ነቢያት ምን እንደ ተናገሩ በመመልከት ቢሆንም፣ ከሁሉ በላይ ግን እግዚአብሔርን ያሳየንን ጌታ ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ የእግዚአብሔርን መልክ በኢየሱስ ዐይተነዋልና፡፡ ታዲያ ጌታ ኢየሱስ ምን አደረገ? ለመከራ ምን ምላሽ ነበረው?
የምድር ኑሮ ብርቱ ሰልፍ ነው፡፡ ሰዎች ዕድሜአቸው ከዘጠኝ መቶ ዓመታት በላይ ይደርስ በነበረበት በዚያ “የድንጋይ ዳቦ ዘመን” እንኳ ሰዎች ከዚህች “እግዚአብሔር ከረገማት ምድር” ማረፍን እጅግ ይናፍቁ ነበር (ዘፍ. 5፥29)፡፡ ሞትና ሥቃይ፣ ኀዘንና ልቅሶ የበዛባት ይህች ምድር መቼም የዕረፍት ስፍራ ሆና አታውቅም፡፡ ጌታ ኢየሱስም ሲወለድ ይኸው ነበር የገጠመው፡፡ በእርሱ መወለድ ብዙ ሕፃናት ሞቱ፤ የእርሱንም ነፍስ ለማትረፍ ቤተ ሰቦቹ በስደት አገር ለቅቀው መሄድ ነበረባቸው (ስደቱን የፈጸሙት ዛሬ በየዜና ማሰራጫው እንደምንከታተለው በእግር እና በጀልባ ይሆን?) (ማቴ. 2፥13-18)፡፡
ጌታችን አገልግሎቱን ሲጀምር ሰይጣን በቀላሉ ስኬትን የማግኘት ግብዣ አቅርቦለት ነበር፤ እርሱ ግን ግብዣውን ወዲያ ብሎ የመከራን መንገድ መርጧል (ማቴ. 4፥1-11)፡፡ በየቀኑ የሚገጥሙት ሰዎችም ግፍ፣ በሽታ፣ ኀዘን እና ሞት የደቆሳቸው ነበሩ፡፡ የኢዮብ “ወዳጆች” ኢዮብን ከማጽናናት ይልቅ ስለ መከራ አመጣጥ ለማስተንተን እንደ ሞከሩት ሁሉ፣ የጌታ ደቀ መዛሙርትም አንዳንድ ሰዎች ላይ ስለሚደርሰው መከራ መንሥኤ ማወቅ ይፈልጉ ነበር (ዮሐ. 9፥2)፤ እርሱ ግን አቋሙ ከዚህ የተለየ ነበር፡፡ የመከራውን መንሥኤ ሲጠየቅ ማብራሪያ ከመስጠት ይልቅ በሽታ የደቆሰውን ሰው መፈወስና ማጽናናትን ይመርጣል፡፡
አንድ ጊዜ አንደ የታወቀ አገልጋይ መኪና ሲያሽከረክር በደረሰበት አደጋ ሲሞት፣ አብረውት የነበሩ የቤተ ሰቡ አባላት ላይም ከባድ አደጋ ደረሰ፡፡ በጊዜው ስለ አሟሟቱ ብዙ መላምቶች በአማኞች ይሰነዘሩ ጀመር፡፡ ለአንዳንዶቹ፣ አገልጋዩ በተሰጠው ጸጋ መታበይ ስለ ጀመረ ነው አደጋ የደረሰበት፤ ለሌሎች ደግሞ ጥፋቱ የተገልጋዩ ሕዝብ ነበር፤ ዐይናቸውን በአገልጋዩ ላይ ስላደረጉ እግዚአብሔር ለክብሩ ቀንቶ ወሰደው፡፡ አደጋው የደረሰው ከእርሱ ጋር አብረው በነበሩት የቤተ ሰቡ አባላትም ላይ ነበር፡፡ ታዲያ “ኀጢአቱ” የእርሱ ብቻ ነበር ወይስ አብረውት የነበሩ ቤተ ሰቦቹም ጭምር? ወይስ፣ “ለኀጥአን የወረደ ለጻድቃን ይተርፋል”?
በጳውሎስ ፈቃዱ
ይቀጥላል ...
ምንጭ፦ hintset.org