ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.38K photos
61 videos
333 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች፣ #መጻሕፍትን_እንመርምር በሚል ርዕስ በሚቀርበው ዝግጅት ሊነሱ ወይም ሊብራሩ ይገባል የምትሉትን መጻሕፍ ቅዱሳዊ አሳብ ወይም ጥያቄ ካላችሁ በነጻነት እንድታቀርቡ ትበረታታላችሁ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ጢሞቴዎስም የመጣ እንደ ሆነ በእናንተ ዘንድ ያለ ፍርሃት እንዲኖር ተጠንቀቁ፤ እንደ እኔ ደግሞ የጌታን ሥራ ይሠራልና፤ እንግዲህ ማንም አይናቀው።”
          1ኛ ቆሮንቶስ 16፥10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እነርሱም አሉት፦ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንዳለ በእርግጥ አየን፤ ስለዚህም፦ በእኛና በአንተ መካከል መሐላ ይሁን እኛ አንተን እንዳልነካንህ፥ በጎነትንም ብቻ እንዳሳየንህ፥ በደኅናም እንደ ሰደድንህ፥ አንተም ክፉ እንዳትሠራብን ቃል ኪዳን ከአንተ ጋር እናድርግ አልን አንተ አሁን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተባረክህ ነህ።”
           ዘፍጥረት 26፥28-29




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3🥰2👍1
የ12ቱ ደቀ መዛሙርት(ሐዋርያት)  አጭር ታሪክ 


፩. ጴጥሮስ(ስሞኦን) 

በመጀመሪያ ስሞኦን ተባለ በኋላ ኢየሱስ ኬፋ አለው። በአረማይክ ኬፋ በግሪክ ጴጥሮስ ሁለቱም አለት ማለት ነው። የትውልድ ቦታው ቤተ ሳይዳ ነበር። ጴጥሮስ እንደ አይሁድ ሊቃውንት የተማረ አልነበረም። ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በቅፍርናሆም አሳ በማጥመድ ይኖር ነበር። ሚስት ነበረችው(ማር። ፩፡፳፱-፴)። ጴጥሮስን በመጀመሪያ ከኢየሱስ ጋር ያስተዋወቀው እንድርያስ ነበር(ዮሐ. ፩፡፵፩-፵፫)። ይህ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለኢየሱስ በተለየ ሁኔታ ቅርብ ነበር። መንፈስ ቅዱስ ከወረደም በኋላ መሪ ሆኖም አገልግሏል።በተጨማሪም ጴጥሮስ ሁለት መልእክቶችን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ጽፏል። አሟሟቱም በመጽሐፍ ቅዱስም ባይጻፍም በመስቀል ተዘቅዝቆ እንደ ሞተ የቤ.ክ ታሪክ ይናገራል።

፪. ዮሐንስ

የያዕቆብ ወንድም የዘብዴዎስ ልጅ ነው እናቱም ሰሎሜ ሳትሆን አትቀርም ይባላል። ዮሐንስ ማለት የስሙ ትርጉም እግዚኣብሔር ጸጋ ነው ማለት ሲሆን ወላጆቹ ሃብታሞች ነበሩ። የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር እንደሆነ ይገመታል(ዮሐ. ፩፡፴፭-፵፪)። ከወንድሙና ከአባቱ ጋር አሳ እያጠመዱ ሳሉ ኢየሱስ ወንድሙንና እርሱን ጠራው። ሁለቱም ወንድማማቾች ሃይለኞች ስለነበሩ ኢየሱስ "ቦአኔርጌስ" ብሎ ጠርቷቸዋል። ትርጉሙም የነገድጓድ ልጆች ማለት ነው።ዮሐንስ አንድ ወንጌል ሶስት መልእክቶችን እና ራእይን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ጽፏል። በተጨማሪም ዮሐንስ እራሱን በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ይወደው የነበረ ደቀ መዝሙር በማለት ይገልጻል። በመጨረሻም ከኤፌሶን ተሰዶ ፍጥሞ በምትባል ደሴት ኖረ(ራእ. ፩፡፱)።

፫. ያዕቆብ

የዘብዴዎስ ልጅ የዮሐንስ ታላቅ ወንድም ነው። የስሙ ትርጉም ተረከዝን ይይዛል ማለት ነው። ከደቀ መዛሙርት መካከል ቀድሞ የሞተው እርሱ ሲሆን ሄሮድስ በሰይፍ አስገደለው።

፬. ያዕቆብ(የእልፍዮስ ልጅ)

አንዳንድ ጊዜ ታናሹ ያእቆብ ይባላል።

፭. የአስቆሮቱ ይሁዳ

ይሁዳ ማለት ማመስገን ሲሆን አስቆሮት ማለት እርሱ የመጣበትን አካባቢ/መንደር ይገልጻል። አስቆሮት በይሁዳ አውራጃ የሚገኝ ቂርያትሐጾር የሚባለው መንደር ይሆናል(ኢያ. ፲፭፡፳፭)። ከዚህ በመነሳት ይሁዳ ከተማ ቀመስ ሰው እንደሆን እንገምታለን። ገንዘብ ያዥ ሆኖ ሳለ ሌባ እንደሆን ወንጌላት ይናገራሉ። በመጨረሻም ሰይጣን ገብቶበት ኢየሱስን ጌታውን ሽጦ በገንዘቡ ሳይጠቀም ታንቆ ሞቷል።

፮. ይሁዳ(የያዕቆብ ልጅ)

ይህኛው ይሁዳ ታዴዎስ የተባለው ልብድዮስ ሳይሆን አይቀርም(ማቴ. ፲፡፫)።

፯. ማቴዎስ

የእልፍዮስ ልጅ ሲሆን ቀራጭና የቅፍርናሆም ነዋሪ ነበር። ማቴዎስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ማቴዎስ ወንጌልን የጻፈ ሲሆን ሉቃስና ማርቆስ በቤተሰቡ ስም ሌዊ እያሉ የሚጠሩት ሲሆን እርሱ እራሱን ደግሞ ቀራጭ እያለ ይጠራ ነበር።

፰. ፊሊጶስ

የቤተ ሳይዳ ሰው ሲሆን ናትናኤልን ወደ ኢየሱስ ያመጣ ደቀ መዝሙር ነበር።

፱. እንድርያስ

የጴጥሮስ ወንድም ሲሆን ከእርሱ ጋር ሆኖ አሳ ሲያጠምድ ኢየሱስ ጠራቸው። እንድርያስ የዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሲሆን ኢየሱስን እንዲከተል ከነገረው በኋላ ኢየሱስ ቤት ውሏል። ጴጥሮስንም ወደ ኢየሱስ ጠራው(ዮሐ. ፩፡፴፭-፵፮)። መጥምቁ ዮሐንስ የሚዜነቱን ስራ በሚገባ እንደተወጣ የእንድርያስ ሕይወት በሚገባ ያሳያል። እንድርያስም ሰውን ወደ ጌታ በማምጣት ይታወቅ ነበር።

፲. ቶማስ

ቶማስ በአረማይክ ዲዲሞስ በግሪክ ሁለቱም ትርጉማቸው መንታ ማለት ነው። ብዙዎች በተጠራጣሪነቱ ቢያውቁትም መንፈስ ቅዱስ ከወረደ በኋላ ግን ስለኢየሱስ ሰብኳል። እንዲያውም የቤ.ክ ታሪክ እንደሚለው ከሆነ ቶማስ በሕንድና በፋርስ ወንጌል እንዳስተማረ ይነገራል።

፲፩. በርተሎሜዎስ

በርተሎሜዎስ ማለት የተሎሜዎስ ልጅ ማለት ነው። ምናልባት በርተሎሜዎስ የተባለው ናትናኤል ሳይሆን አይቀርም።

፲፪. ቀናተኛው ስምኦን

አንዳንዶቹ ናትናኤል ነው ይሉታል።



ምንጭ:- የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ  ቃላት




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍113👏2🔥1🥰1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ልቡም በፊትህ የታመነ ሆኖ አገኘኸው፤ የከነዓናዊውንና የኬጢያዊውን የአሞራዊውንም የፌርዛዊውንም የኢያቡሳዊውንም የጌርጌሳዊውንም ምድር ለእርሱና ለዘሩ ትሰጥ ዘንድ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረግህ፤ አንተም ጻድቅ ነህና ቃልህን ፈጸምህ።”
              ነህምያ 9፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2🔥2👍1👏1
💠የእግዚአብሔርን ፀጋ የምንጥልባቸው አራቱ መንገዶች



እኛን ያቆመን የእግዚአብሔር ፀጋ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ፀጋ ውጭ እኛ ምንም ማድረግ አንችልም፡፡

"ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።" (1ኛ ቆሮ.15፡10)

የእግዚአብሔርን ፀጋ ስንጥል ማደግ እናቆማለን፡፡ የእግዚአብሔርን ፀጋ ከጣልን መውደቃችን አይቀሬ ነው፡፡

የእግዚአብሄርን ፀጋ የምናጣበት ሃይል አልባ የሚያደርጉን አራቱ መንገዶች

1. ትህትናን መጣል  

ሰው ትህትናን ከጣለ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እንደሚወድቅ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ሰው እግዚአብሔር ከሰጠው ደረጃ በላይ ራሱን ከፍ አድርጎ ሲያይ ከእግዚአብሔር ጋር ይተላለፋል፡፡ እግዚአብሔር ፀጋን መስጠትና ማንሳት ከፍ ማድረግ እየፈለገ በራሱ ነገሮችን ማድረግ እንደሚችል የሚያስበውን ትእቢተኛን ሰው ግን ከመቃወም ውጭ ምንም ሊያደርገው አይችልም፡፡  

"ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣልይላል።" (ያዕ. 4፡6)

2. እውቀትን መጣል

ሰው ከመሬት ተነስቶ አውቆ የጨረሰ ከመሰለው በህይወቱ ማደግና መለወጥ አቁሟል ማለት ነው፡፡ ይህ ሰው ለአዲስ ተግዳሮት በእውቀት ራሱን ካላስታጠቀ መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡ ይህ ሰው ያወቀና የጨረሰ ከመሰለው እጅግ አሰቃቂ ነው፡፡

"ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋም፥ ሁላችን እውቀት እንዳለን እናውቃለን። እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል። ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤" (1ኛ ቆሮ. 8፡1-2)

"ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤" (ሆሴ. 4፡6)

"በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።"( 2ኛ ጴጥ. 1፡2)

3. እምነትን መጣል

ሰው በእግዚአብሔር ላይ መደገፍን ትቶ በራሱ ስራ ላይ ሲደገፍ ከእግዚአብሔር ፀጋ ይጎድላል፡፡ ሰው ለመዳንም ሆነ ከዳነ በኋላ ለመቀደስ ፣ ለእግዚአብሔር መንግስት ለመስራትና እግዚአብሔርን ለማስደሰት በራሱ ጉልበትና ቅልጥፍና ላይ ሲደገፍ ከእግዚአብሔር ፀጋ ይጎድላል፡፡

"በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል።" (ገላ. 5፡4)

"ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።" (1ኛ ቆሮ.1፡30-31)

4. ምስጋናን መጣል

ሰው ምንም ከማይወጣለት መልካም አምላክ ጋር እየኖረ ካጉረመረመና ማመስገን ካቃተው ከእግዚአብሔር ፀጋ ይጎድላል፡፡ ሰው በእግዚአብሔር አሰራር ላይ አቃቂር ማውጣት ከቻለ የሆነ የሳተው ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር በላይ የሚያውቅ ከመሰለው የሆነ የተዛባ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሔር አሰራር ካልታመነ ከእግዚአብሔር ጋር በየዋህነት መኖር ፣ ራሱን መስጠት ፣ ለእግዚአብሔር በየዋህነት መስራትና ፍሬያማ መሆን ያቅተዋል፡፡   

"አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።"(ማቴ. 25፡24-25)

"ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደጠፉ አታንጐርጕሩ።" (1ኛ ቆሮ. 10፡10)



ምንጭ:- አብይ ዋቁማ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍41👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።”
           ኤፌሶን 2፥10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍1🔥1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት

የቀጠለ...


ሮሜ 8፥12-17


ልጅነት፣ የልጅነት መብት በመስጠት ቤተሰብ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህም በአዲስ ኪዳን ውስጥ በተለያዩ አራት ቦታዎች ተጠቅሶአል (ቍ 23፤ 9፥4፣ ገላ 4፥5፤ ኤፌ 1፥5 )፡፡ ከአብራክ ያልተገኘን ልጅ እንደ ራስ ልጅ አድርጎ ማሳደግና ሀብት የመውረስ መብቱ እንዲጠበቅለት ማድረግ፣ በግሪኮችና በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ነበር። ክርስቲያኖችም የልጅነትን መብት ያገኙት በጸጋ ነው:: ክርስቶስ ግን የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ነው:: አባ አባት ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ልዩ የሆነ ኅብረት ያመለክታል፡፡

መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅነታችንን ያረጋግጥልናል። መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ከሆነ ለእግዚአብሔር ልጅነታችን ምንም ዓይነት ጥርጣሬ ሊኖረን አይገባም (ገላ. 4፥67፤ 1ዮሐ 3÷1)።

ጳውሎስ እዚህ ላይ የሚለው፤ መንፈስ ራሱ፥ እርሱም መንፈስ ቅዱስ ከእኛ መንፈስ ማለትም ከራሳችን ሰብአዊ መንፈስ ጋር በመሆን ይመሰክራል። ሰብአዊ መንፈስ ምንድን ነው? ሰብአዊ መንፈስ የሰው መንፈሳዊ ክፍል ነው። በክርስቶስ በምናምንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሕይወት የሚሰጠው የእኛነታችን ክፍል ነው። አንዳንድ ሰዎች ሰብአዊ መንፈስ ማለት የሰው ውስጣዊ ሕያውነት ወይም ኅሊና ነው ይላሉ (ሮሜ 7፥22)። ሰው በሦስት ክፍል ይመደባል፥ መንፈስ፥ ነፍስና ሥጋ (1ተሰ. 5፥23)። በሰብአዊ መንፈሳችን በኩል የእግዚአብሔርን መኖርና የመንፈስ ቅዱስን በረከት በሕይወታችን እንረዳለን።

ልጆች ከሆንን ወራሾችም ነን በውስጣችን ያለው መንፈስ ቅዱስ ወደፊት በመንግሥተ ሰማይ ለሚኖረን ውርስ መያዣ ወይም ዋስትናችን ነው (2ቆሮ. 5፥5፤ ኤፌ. 1፥13–14)።

ጳውሎስ ግን እዚህ ላይ በጣም ጠቃሚ የሆነ ማስታወሻ ይሰጠናል። ከክርስቶስ ጋር አብረን የምንወርስ ስለሆነን፤ የሕይወቱ ወይም የክብሩ ተካፋዮች ብቻ ሳንሆን፥ የመከራውም ተካፋዮች ነን። የመከራው ተካፋዮች መሆን የማንፈልግ ከሆነ የክብሩም ተካፋዮች መሆን ከቶ አንችልም (2ጢሞ. 2፥11-12፤ 3፥12፤ 1ጴጥ. 4፥1214)።

ክርስቲያኖች ሁለት ዓይነት መስቀል አላቸው።

1. አንደኛው መስቀል አሮጌው ሰውነታችን የተሰቀለበት መስቀል ሲሆን (ሮሜ 6፥6)፤

2. ሁለተኛው መስቀል ክርስቶስን በመከተል ምክንያት የሚመጣብን መከራና ስደት ነው።

የመጀመሪያውን መስቀል ክርስቶስ ራሱ ተሸክሞልናል፤ ሁለተኛውን መስቀል ለእርሱ ስንል እኛ መሸከም አለብን። ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ለመሆንና አብረነው ለመንገሥ የምንፈልግ ከሆነ፥ ይህን ሁለተኛውን መስቀል መሸከም ይኖርብናል (ማር. 8፥34)።




ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 368፣ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጹሑፍ ጋር፤ ገጽ 1718





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32🔥1👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ ካወቃቸው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመታዘዝ በደሙ ለተረጩትና በመንፈስ አማካይነት ለተቀደሱት፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።”
           1ኛ ጴጥሮስ 1፥2 (አዲሱ መ.ት)





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1🥰1👏1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


መዝሙር 115
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ለእኛ አይደለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይደለም፥ ነገር ግን ለስምህ ስለ ምሕረትህ ስለ እውነትህም ምስጋናን ስጥ።
² አሕዛብ፦ አምላካቸው ወዴት ነው? አይበሉ።
³ አምላካችንስ በላይ በሰማይ ነው፤ በሰማይም በምድርም የፈቀደውን ሁሉ አደረገ።
⁴ የአሕዛብ ጣዖታቶች የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው።
⁵ አፍ አላቸው አይናገሩምም፤ ዓይን አላቸው አያዩምም፤
⁶ ጆሮ አላቸው አይሰሙምም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፤
⁷ እጅ አላቸው አይዳሰሱምም፤ እግር አላቸው አይሄዱምም፤ በጕሮሮአቸውም አይናገሩም።
⁸ የሚሠሩአቸውም የሚያምኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።
⁹ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ ረድኤታቸውና መታመኛቸው እርሱ ነው።
¹⁰ የአሮን ቤት ሆይ፥ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ ረድኤታቸውና መታመኛቸው እርሱ ነው።
¹¹ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፥ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ ረድኤታቸውና መታመኛቸው እርሱ ነው።
¹² እግዚአብሔር አሰበን ይባርከንማል፤ የእስራኤልን ቤት ይባረካል፥ የአሮንንም ቤት ይባረካል።
¹³ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፥ ትንንሾችንና ትልልቆችን ይባርካል።
¹⁴ እግዚአብሔር በላያችሁ፥ በላያችሁና በልጆቻችሁ ላይ ይጨምር።
¹⁵ እናንተ ሰማይንና ምድርን ለሠራ ለእግዚአብሔር የተባረካችሁ ናችሁ።
¹⁶ የሰማያት ሰማይ ለእግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።
¹⁷ አቤቱ፥ ሙታን የሚያመሰግኑህ አይደሉም፥ ወደ ሲኦልም የሚወርዱ ሁሉ፤
¹⁸ እኛ ሕያዋን ግን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔርን እንባርካለን። ሃሌ ሉያ።





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2👏2🥰1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“የእግዚአብሔር ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን፥ በፊታቸው የሚወጣውን በፊታቸውም የሚገባውን የሚያስወጣቸውንም የሚያስገባቸውንም ሰው የሥጋ ሁሉ መንፈስ አምላክ እግዚአብሔር በማኅበሩ ላይ ይሹመው።”
               ዘኍልቁ 27፥16-17




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1🔥1👏1
#እራሳችንን_እንመርምር

ከእግዚአብሔር ጋር እየዋልን ነው። እርሱንም በሚገባ እየፈለግነው ነው። ከእርሱ ጋር መሆን መልካም ነው። የነፍሳችንም መሻት ይህ ነው። እያልን ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ተላልፈን ይሆን? ከእግዚአብሔር ጋር ከመተላለፍ እግዚአብሔር ይጠብቀን🙏


"ነገር ግን ዕለት ዕለት ይሹኛል መንገዴንም ያውቁ ዘንድ ይወድዳሉ፤ ጽድቅን እንዳደረጉ የአምላካቸውንም ፍርድ እንዳልተዉ ሕዝብ እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወድዳሉ። ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም? ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
ኢሳይያስ 58፥2-3





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን ያፈልሳል፥ ነገሥታትንም ያስነሣል፤ ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል።”
           ዳንኤል 2፥21




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42👏1
በመጽሐፍ ቅዱስ "የእግዚአብሔር ልጅ/ልጆች" ትርጓሜ





በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያዩ ስፍራዎች የቀረቡትን ማስረጃዎች በማጤን “የእግዚአብሔር ልጅ” የሚለው ሐረግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ትርጕሞች እንደሚይዝ መረዳት ይቻላል፤

1) የእግዚአብሔርን የፍጥረት ባለቤትነት ማሳያ ነው።

“በውኑ ለዝናብ አባት አለውን? ወይስ የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው” ከሚለው መረዳት እንደሚቻለው (ኢዮብ 38፥28)፤ የእግዚአብሔር አባትነት እርሱ የፍጥረት ሁሉ ባለቤት መሆኑን የሚያሳይ ዘይቤአዊ አገላለጥ ነው። “የእኛ ዘር ከሌሎች ይበልጣል” በሚል ስሜት የተዋጡት አቴናውያን፣ “እኛም ደግሞ ልጆቹ ነን” በማለት የተናገሩትን ከፈላስፎቻቸው በመውሰድ ሰውን ሁሉ የሚመለከት አድርጎ ሐዋርያው ጳውሎስ ያቀረበው ለዚህ ይመስላል (የሐዋ. 17፥28፤ አ.መ.ት)። የሉቃስ ወንጌል አዳምን “የእግዚአብሔር ልጅ” ማለቱ ምናልባት በዚህ አግባብ የሚታይ ነው (3፥38)። እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ በመሆኑ የፍጥረት ሁሉ አባት ነው። ነገር ግን ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ስለ መሆናቸው መጽሐፍ ቅዱስ እምብዛም የሚናገረው ነገር የለውም።

2) መላእክትን ወይም ሰማያውያን ፍጥረታትን ያመለክታል፤

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋልና (ኢዮብ 1461 2:11 3871 መዝ. 29፥1፤ 82፥6፤ 89፥6)።

3) እስራኤል የእግዚአብሔር መሆኗን ያመለክታል።

እስራኤል ከምድር ሁሉ ለይቶ የመረጣት በመሆኗ ለእግዚአብሔር የመጀመሪያ ልጅ ናት፤ በዚህ ረገድ እግዚአብሔር ከእርሷ በፊት ልጅ አልነበረውም። ይህንንም ሙሴ በፈርዖን ፊት ቆሞ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- እስራኤል የበኵር ልጄ ነው” በማለት እንዲናገር አድርጎታል (ዘፀ. 4፥22-23)። “እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፤ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና” በማለትም ተጽፏል (ኤር. 31፥9)። ይህ ከእግዚአብሔር የድነት ዕቅድና ከእስራኤል ተልእኮ ጋር ይያያዛል።

እስራኤላውያን በኪዳን ሕዝብነታቸው፣ “እናንተ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ” ተብለዋል (ዘዳ. 14፥1)። በዚህ አገባቡ፡ የእግዚአብሔር ልጅ ማለት የእግዚአብሔር መሆንን እና የእግዚአብሔር ቤተ ሰብነትን ያሳያል። አማኞች የአብርሃም ልጆች የሆኑበትና የእግዚአብሔር የተቀበሉበት አግባብም ይኸው ነው (ሮሜ 9፥6-8 እና 24-31 እንዲሁም 11፥7-26ን ይመለከቷል።)

4) ጻድቃንን ይኸውም የእግዚአብሔር ጠባያት የሚታዩባቸው ሰዎችንም ያመለክታል።

ጠላቶቻቸውን የሚወድዱና መልካም የሚያደርጉ (ሉቃ. 6፥35)፣ የሚያስተራርቁ (ማቴ. 5፥9)፣ ጽድቅን የሚያደርጉ (1ዮሐ. 3፥10) “የእግዚአብሔር ልጆች” ናቸው።

5) ከዳዊት ሥርወ መንግሥት የሚመጣ ንጉሥ የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል።

ዳዊት፣ "ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል። እርሱም፦ ልጅ ይሆነኝ ዘንድ መርጬዋለሁና፥ እኔም አባት እሆነዋለሁና … አለኝ” ሲል የተናገረው ይህንኑ ነው (1ዜና 28፥5-7)።

6) በመጨረሻም፣ “የእግዚአብሔር ልጅ” ወልድ ማለት ነው::

መለኮትነትን ያሳያል። “ከቶውንም እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም፤ ነገር ግን በአብ ዕቅፍ ያለው አንድያ ልጁ የሆነው አምላክ እርሱ ተረከው” (ዮሐ. 1፥18፤ አ.መ.ት)፣ እንዲሁም “ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር” (ዮሐ. 5፥18) የተባለው ለዚህ ነው።



ምንጭ፦ የእግዚአብሔር ልጅ፤ ጳውሎስ ፈቃዱ፤ ገጽ 255-256





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ሙሴ እጆቹን ጭኖበት ነበርና፣ የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ መንፈስ ተሞላ። ስለዚህ እስራኤላውያን አደመጡት፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን አዞት የነበረውንም ሁሉ አደረጉ።”
          ዘዳግም 34፥9 (አዲሱ መ.ት)





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1🔥1👏1
የሙሴ ሕይወት ሲጠቀለል ምን ይመስላል? ሙሴ ምን አይነት ሰው ነበር?

1. ከእግዚአብሔር ጋር

እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ያወቀ

“እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሣም፤”
ዘዳግም 34፥10

2. በጠላቶቹ እና በምድራቸው ላይ

ምልክት እና ድንቅ ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር የላከው

“በግብፅ ምድር በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ ላይ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ምልክትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ላከው ያለ፥”
ዘዳግም 34፥11

3. በቅዱሳን ወይም በእስራኤል ሕዝብ ፊት

ታላቅ ኃይል እና ማስደንገጥ ያሳየ

“በእስራኤል ሁሉ ፊት በጸናች እጅ ሁሉና በታላቅ ማስደንገጥ ሁሉ እንዳደረገው እንደ ሙሴ ያለ አልተነሣም።”
ዘዳግም 34፥12

በአጭሩ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት፣ በእግዚአብሔር ሕዝብ እና በጠላት ሰፈር መሆን እና መኖር እንደሚገባው የኖረ ሰው ነው።


ዘዳግም 34
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሣም፤
¹¹ በግብፅ ምድር በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ ላይ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ምልክትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ላከው ያለ፥
¹² በእስራኤል ሁሉ ፊት በጸናች እጅ ሁሉና በታላቅ ማስደንገጥ ሁሉ እንዳደረገው እንደ ሙሴ ያለ አልተነሣም።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5👏21🥰1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር።”
             ሐዋርያት 6፥8




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1🔥1👏1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት


ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።
¹⁹ የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።
²⁰ ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፤
²¹ ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው።
²² ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።
²³ እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።
²⁴ በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል?
²⁵ የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን።
²⁶ እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤
²⁷ ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና።
²⁸ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
²⁹ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
³⁰ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።


ሮሜ 8 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ የአሁኑ ዘመን ሥቃያችን ወደ ፊት ሊገለጥ ካለው ለእኛ ከተጠበቀልን ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም እንዳይደለ እቈጥራለሁ።
¹⁹ ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በናፍቆት ይጠባበቃል።
²⁰ ፍጥረት ሁሉ ለከንቱነት ተዳርጎአል፤ ይኸውም በራሱ ምርጫ ሳይሆን፣ ለተስፋ እንዲገዛ ካደረገው ከፈቃዱ የተነሣ ነው።
²¹ ይህም ፍጥረት ራሱ ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሆነው ወደ ከበረው ነጻነት እንዲደርስ ነው።
²² እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ በምጥ ጊዜ እንዳለው ሥቃይ በመቃተት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን።
²³ እርሱ ብቻ ሳይሆን፣ የመጀመሪያውን የመንፈስ ፍሬ ያገኘን እኛ ራሳችን የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነታችንን በናፍቆት እየተጠባበቅን በውስጣችን እንቃትታለን።
²⁴ በዚህ ተስፋ ድነናል፤ ተስፋው የሚታይ ከሆነ ግን ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል?
²⁵ ነገር ግን ገና ያላየነውን ተስፋ ብናደርግ፣ በትዕግሥት እንጠብቀዋለን።
²⁶ እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ያግዘናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅም፤ መንፈስ ግን በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ይማልድልናል።
²⁷ ልባችንንም የሚመረምረው እርሱ የመንፈስን ሐሳብ ያውቃል፤ ምክንያቱም መንፈስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለቅዱሳን ይማልዳልና።
²⁸ እግዚአብሔር፣ ለሚወዱትና እንደ ሐሳቡ ለተጠሩት፣ ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን።
²⁹ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወሰናቸው፤ ይኸውም ከብዙ ወንድሞች መካከል እርሱ በኵር እንዲሆን ነው።
³⁰ አስቀድሞ የወሰናቸውን ጠራቸው፤ የጠራቸውን አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውን አከበራቸው።


ሮሜ 8 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ይህ አሁን የምንቀበለው መከራ ወደ ፊት ከሚጠብቀን ክብር ታላቅነት ጋር ሊመዛዘን አይችልም።
¹⁹ የእግዚአብሔር ልጆች የሚገለጡበትን ያችን ዕለት ፍጥረት ሁሉ በትዕግሥትና በተስፋ ይጠባበቃል።
²⁰¯²¹ በራሱ ፈቃድ ሳይሆን በእግዚአብሔር ፍርድ ኃጢአትና ሞት የሰፈነበት ፍጥረታዊው ዓለም፥ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተወግደውለት ፥ የእግዚአብሔር ልጆች የሚቀዳጁትን የክብር ነፃነት ተካፋይ ለመሆን በተስፋ ይጠባበቃል።

²² እስካሁን ድረስም ፍጥረት ሁሉ በምጥ ጣር ተይዞ እንደሚቃትት እናውቃለን።
²³ የሚቃትተውም ፍጥረት ብቻ አይደለም። ወደ ፊት ተዘጋጅቶ ለሚጠብቀን ክብር መነሻና መሠረት የሆነውን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ የተቀበልን ሁላችን ፥ 'ያች ዕለት ከመቼ መቼ ደርሳ እግዚአብሔር በሰጠን ተስፋ መሠረት፥ ሕመምና ሞት የማይነካውን አዲስ አካል ለብሰን የልጅነት ማዕርጋችንን እንቀበል ይሆን?' ብለን እንቃትታለን፤ እንናፍቃለንም።
²⁴ በዚህ ተስፋ ድነናል። በዓይነ ሥጋ የምናየውንና በእጃችን የገባውን ነገር ገና ወደፊት እንደምናገኘው አድርገን በተስፋ አንጠብቀውም።
²⁵ እግዚአብሔር ይሰጠናል ብለን በተስፋና በትዕግሥት የምንጠብቀው ገና በእጃችን ያልገባውን ነገር ነው።
²⁶ እንደዚሁም በየዕለቱ በሚገጥመን ችግርና በምንጸልይበትም ጊዜ ፥ የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ አይለየንም። ለምንና እንዴት መጸለይ እንደሚገባን በውል ለይተን ስለማናውቅ ፥ መንፈስ ቅዱስ ራሱ ቃላት በትክክል ሊገልጡት በማይቻል ሁናቴ ይጸልይልናል።
²⁷ መንፈስ ቅዱስ ስለ እኛ በሚጸልይበት ጊዜ ስለ ምን እንደሚጸልይልን የሰዎችን ሁሉ ልብ ገልጦ የሚመረምረው እግዚአብሔር ያውቀዋል። ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን የሚጸልየው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ነውና።
²⁸ እግዚአብሔርን የምንወደው ከሆነና እንደ ፈቃዱም የተጠራን ከሆነ ፥ የሚደርስብን ነገር ሁሉ ለእኛው ጥቅም እንደሚሆን እናውቃለን።
²⁹ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር እንዲሆን ፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሁሉ ልጁን እንዲመስሉ ወሰነ።
³⁰ ስለዚህ እግዚአብሔር ቀደም ብሎ የወሰናቸውን ጠራቸው። የጠራቸውንም አጽድቆ የክብሩ ተካፋዮች አደረጋቸው ፡፡




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2👏2
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ።”
               ዘፍጥረት 6፥8




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3🔥1🥰1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ኤርምያስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ፦ ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም፤ ከፊቴ ጣላቸው፤ ይውጡ።
² እነርሱም፦ ወዴት እንውጣ ቢሉህ፥ አንተ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰይፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለምርኮም የሆነ ወደ ምርኮ ትላቸዋለህ።
³ ሰይፍን ለመግደል ውሾችንም ለመጐተት የሰማያትንም ወፎች የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ አራቱን ዓይነት ጥፋት አዝዝባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
⁴ የይሁዳም ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስላደረገው ሁሉ በምድር መንግሥታት ሁሉ መካከል ለመከራ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
⁵ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ይጠይቅ ዘንድ ፈቀቅ የሚል ማን ነው?
⁶ አንቺ እኔን ጥለሻል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጥፍቼሻለሁ፤ ከይቅርታ ደክሜአለሁ።
⁷ በአገርም ደጆች ውስጥ በመንሽ አበጥሬአቸዋለሁ፤ የወላድ መካን አድርጌአቸዋለሁ፥ ሕዝቤንም አጥፍቼአለሁ፤ ከመንገዳቸውም አልተመለሱም።
⁸ መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተውብኛል፤ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፤ ጣርንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።
⁹ ሰባት የወለደች ደክማለች፥ ነፍስዋንም አውጥታለች፤ ቀን ገና ሳለ ፀሐይዋ ገብታባታለች፤ አፍራለች ተዋርዳማለች፤ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ።
¹⁰ እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፤ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።
¹¹ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ በእውነት ለደኅንነትህ አጸናሃለሁ፤ በእውነት በመከራና በጭንቅ ጊዜ ጠላትህ እንዲለምንህ አደርገዋለሁ።
¹² በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን?
¹³ በዳርቻህ ሁሉ ስላለ ኃጢአትህ ሁሉ ባለጠግነትህንና መዝገብህን ለመበዝበዝ በከንቱ እሰጣለሁ።
¹⁴ የምታቃጥላችሁ እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና ከጠላቶችህ ጋር ወደማታውቀው ምድር አሳልፍሃለሁ።
¹⁵ አቤቱ፥ አንተ ታውቃለህ፤ አስበኝ ጐብኘኝም የሚያሳድዱኝንም ተበቀላቸው እንጂ አትታገሣቸው፤ ስለ አንተ ስድብን እንደ ታገሥሁ እወቅ።
¹⁶ ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።
¹⁷ በዋዘኞችና በደስተኞች ጉባኤ አልተቀመጥሁም ቍጣን ሞልተህብኛልና በእጅህ ፊት ለብቻዬ ተቀመጥሁ።
¹⁸ ስለ ምን ሕመሜ አዘወተረኝ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ። አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆነኛለህን?
¹⁹ ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።
²⁰ ለዚህም ሕዝብ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ይዋጉሃል እኔ ግን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም።
²¹ ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፥ ከጨካኞችም ጡጫ እቤዥሃለሁ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።”
                ያዕቆብ 1፥4




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1👏1