የቀጠለ...
📜መጽሐፍ ቅዱሳችን እንዴት ተፃፈ
መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት ሁሉ ልዩ የሆነበት ምክንያት ምንድነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት ልዩ የሆነበት ምክንያት፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲያንን እግዚአብሔር ራሱ በቀጥታ በተለየ መንገድ ስለመራቸው ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች እግዚአብሔር እንዲጽፉ የፈለገውን ነገር የጻፉት በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መሪነት ነበር (2ጢሞ. 3፥16፤ 2ጴጥ. 1፥21)። መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ቃል ብቻ አይደለም። ነገር ግን የእግዚአብሔር የራሱ ቃል ነው።
ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ቃሉን እንዲጽፉ በሰዎች ተጠቅሞአል። እግዚአብሔር እያንዳንዱን ቃል በመናገር እንዲጻፍ አላደረገም፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በራሳቸው አእምሮ ተጠቅመው ስለ ጻፉት የግለሰብ ስብእናቸውና ጠባያቸው በጽሑፎቻቸው ውስጥ ሊታይ ይቻላል። ልክ ኢየሱስ ራሱ በአንድነት እግዚአብሔርም ሰውም እንደነበረ፥ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲሁ በአንድነት የእግዚአብሔርም ቃል፥ የሰውም ቃል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው የእግዚአብሔርን ሀሳብ በተለየ መንገድ በሚያውቁ ሰዎች ነው። እግዚአብሔር አሳቡን ገለጠላቸው፤ እነርሱም እግዚአብሔር በገለጠላቸው መሠረት ጻፉት። ሌሎች ክርስቲያን ጸሐፊዎች በአጠቃላይ በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው እግዚአብሔርን የሚያስደስቱ መጻሕፍትን መጻፋቸው እርግጥ ነው። ነገር ግን እነርሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ፀሐፊዎች የነበራቸውን የእግዚአብሔርን ሃሳብ በተለየ መንገድ የማወቅ ችሎታ አልነበራቸውም። ከዚህም የተነሣ መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት ሁሉ የተለየ ነው። የተገለጠና ሥልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ሙሉ በሙሉ እውነት ነው፤ ምንም ስሕተት የለበትም። አንዳንድ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ «በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አገኘን» ይላሉ። በኋላ ግን የተሳሳቱት ራሳቸው እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ እንዳልነበረ ይረዳሉ። በተደጋጋሚ ጊዜያት በታሪካዊና በከርሰ ምድር ምርመራ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችን እውነት አረጋግጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ በታሪክም ሆነ በሳይንስ በሁሉ አቅጣጫ ተመርምሮ እውነተኛነቱ ተረጋግጦአል።
ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን የታሪክ ወይም የሳይንስ መጽሐፍ እንደምናነበው ማንበብ ብቻ በቂ አይደለም። በአእምሮአችን ብቻ ተጠቅመን መጽሐፍ ቅዱሳችንን ማንበብ በቂ አይሆንም። መጽሐፍ ቅዱስን በመንፈሳችን ጭምር ማንበብ ይኖርብናል፤ አለበለዚያ ግን የመጽሐፍ ቅዱሱን ጥቅል መንፈሳዊ እውነት ለማወቅ አንችልም። መጽሐፍ ቅዱስን በምናነብበት ጊዜ በትሕትና ራሳችንን ዝቅ አድርገን የእግዚአብሔርን እውነት ለመቀበል የተከፈተ አእምሮ ሊኖረን ያስፈልጋል። እግዚአብሔር መንፈሳዊ ማስተዋል እንዲሰጠን መጸለይ ይኖርብናል። ይህንንም በእምነት በምናደርግበት ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ለእኛ ሕያው ይሆናል፤ ሕይወታችንንም ይለውጠዋል።
መጽሐፍ ቅዱስን ሕያው ሊያደርግና በአንባቢው ልብ ውስጥ ኃይለኛ ሊያደርገው የሚችል መንፈስ ቅዱስ ነው (2ቆሮ. 3፥6)። መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው የሚኖር ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛና ሕያው የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ በውስጣቸው ሊረዱ ይችላሉ። ከመጽሐፍ ቅዱስም እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ወይም ክርስቶስ ማን እንደሆነ በእርግጠኝነት ሊያውቁ ይችላሉ። እግዚአብሔር ያደረገውንም ነገር ከመጽሐፍ ቅዱሳቸው ሊያውቁ ይችላሉ። ብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ሰዎችን ለመገናኘት ያደረገውንና የሰዎችንም እምቢተኛነትና ኃጢአት መዝግቦ የያዘ ነው። ብሉይ ኪዳን በግልጥ የሚያሳየው ሰዎች ኃጢአተኞች መሆናቸውንና አዳኝም እንደሚያስፈልጋቸው ሲሆን አዲስ ኪዳን ገልጦ የሚያሳየው ደግሞ ሰዎችን የወደደ አምላክ መኖሩን ነው። ይህ አምላክ ሰዎችን በጣም ከመውደዱ የተነሣ ራሱ ወደ መሬት መጣ፣ የመጣውም በሰው አምሳል ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ ሆኖ ሰዎችን ከኃጢአታቸው ለማዳንና የዘላለም ሕይወትን ለመስጠት ነው። መከራ ተቀበለ፥ ሞተም።
አንባቢ ይህንን መጽሐፍ በሚያጠናበት ጊዜ እግዚአብሔር ከቅዱሳት መጽሐፍ ያስተምረው ዘንድ ራሱን እንደሚያዘጋጅ ይታመናል። እንግዲህ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ብቻ ሳይሆን እንኖርበትም ዘንድ ግድ ነው።
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 91-92
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

👍2❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ከፀሐይ በታች በደከመበት ድካም ሁሉና በልቡ አሳብ የሰው ጥቅም ምንድር ነው?”
መክብብ 2፥22

👍2❤1🥰1🤔1
በደቡብ ያለው መናገሻውን ኢየሩሳሌም ያደረገው መንግሥት የትኛው ወገን ነበረበት?
Anonymous Quiz
35%
ሀ. ይሁዳ
10%
ለ. ብንያም
7%
ሐ. ኤፍሬም
7%
መ. ጋድ
3%
ሠ. ሁሉም
39%
ረ. ሀ እና ለ
👍3❤2
ከሚከተሉት ውስጥ በጠርሴስ የተወለደ፣ በገማልያል እግር ስር የአይሁድን ሕግ ጠንቅቆ የተማረ ሰው ማን ነው?
Anonymous Quiz
9%
ሀ. አጵሎስ
2%
ለ. ቲቶ
78%
ሐ. ጳውሎስ
9%
መ. ጢሞቴዎስ
3%
ሠ. በርናባስ
❤9👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ ቱሚምህና ኡሪምህ ለቅዱስህ ሰው ነው፥ በማሳህ ለፈተንኸው፥ በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፤”
ዘዳግም 33፥8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ ቱሚምህና ኡሪምህ ለቅዱስህ ሰው ነው፥ በማሳህ ለፈተንኸው፥ በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፤”
ዘዳግም 33፥8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤1👍1🥰1👏1
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#ጴርጋሞን፤
ጴርጋሞን ለሮማ መንግሥት አምልኮ እራሳቸውን ባዘጋጁ በርካታ ቤተመቅደሶች ላይ የምትኮራ ከተማ ነበረች። በሮማውያን ዘመን የቀድሞዋ የትንሿ እስያ (Asia Minor) አስተዳደር ዋና ከተማ የነበረችው የጴርጋሞን ከተማ ወደ ኤፌሶን ተዛወረች። እንደ አብዛኞቹ ዋና ዋና የግሪክ ከተሞች ሁሉ፣ ጴርጋሞን በግሪኮ-ሮማን ዓለም ውስጥ የመደበኛ ሕይወት አካል ከሆኑት ሕንፃዎች መካከል ቲያትር፣ ስታዲየም፣ ቤተ መጻሕፍት እና የአስክሊፒየስ የፈውስ ማዕከል ሆናለች። በጴርጋሞን የሚገኘው የፈውስ ማዕከል (አስክሊፒዮን)፣ ዋና መሥሪያ ቤት እንደሆነ ተደርጎ የሚታሰበው፣ በሮማ ግዛት ውስጥ በጣም ትልቅ የሆነ የፈውስ ማዕከሎች አውታረ መረብ አካል ነበር። በሮማ ግዛት ውስጥ በጣም ታዋቂው ሐኪም እና የንጉሠ ነገሥት ማርከስ ኦሬሊየስ የግል ሐኪም ጋለን ለብዙ ዓመታት በዚህ አስክሊፕዮን ውስጥ ሰርቷል። ይህ ሕክምና በእባብ በመነካት የሚገኝ ነው ተብሎ ይታመን ነበር። የነዋሪዎቹ ሃይማኖት ምልክት እባብ ነበረ።
የጴርጋሞን ቤተ መፃህፍት በአሌክሳንድራ ውስጥ ከሚታወቀው ቤተ-መጻሕፍት ቀጥሎ በዓለም በሁለተኛ ደረጃ ይመደብ ነበር። የጴርጋሞን ቤተ መፃህፍት ከ 200,000 በላይ ጥራዞች እንደ ነበሩት ፕሉታርክ ገልጿል። ሌላው ዘገባ ደግሞ የሮማ ወታደራዊ አዛዥ የነበረው ማርክ አንቶኒ በጁሊየስ ቄሳር ለደረሰው የአሌክሳንድርያ ቤተ መጻሕፍት ውድመት ወጪውን እንዲከፍል ለክሊዮፓትራ ውርስ ሰጥቷል። ቤተመቅደሶችን ለንጉሥ የሚሆን ቤተመቅዶሶች ነበሯት። የአማልክት እና የሰው ሁሉ አባት የሚባለው የዜኡስ (በጥሬው "የሰማይ አባት" አምላክ ማለት ነው) መቀመጫ ነበረች። የዜኡስ መሠዊያ በጴርጋሞን ካሉት እጅግ አስደናቂ ሕንፃዎች አንዱ ነበር። የመሠዊያው ደረጃዎች፣ ዓምዶች እና የተቀረጹ ጎኖች አርባ ጫማ (12 ሜትር) ከፍታ ነበራቸው። ዛሬ በበርሊን በሚገኘው የጴርጋሞን ሙዚየም ውስጥ በመሠዊያው መሠረት ዙሪያ ያሉትን ደረጃዎች ብቻ ማየት ይቻላል። በዚህም ምክንያት ከተማዋ የሳይንስ እና የሰይጣን መቀመጫ እንደሆነች ይነገራል። መጽሐፍ ይህን እውነት እንዲህ በማለት ይገልጻል፦
“የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፥ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።”
ራእይ 2፥13
ጳውሎስ በኤፌሶን ሳለ የጴርጋሞን ቤተክርስያን በዚያ የተመሠረተች ይመስላል፤ ሐ.ሥ. 19፥10። በጴርጋሞን ከተማ አማኞች በጽኑ ተፈተኑ፤ ራእ. 1፥11፤ 2፥12-17። ነገር ግን የበለዓምን እና የኒቆላውያንን ትምህርት በመታገሳቸው ተወቀሱ። ጴርጋሞን በነበረበት አጠገብ ትንሽ ከተማ ይገኛል።
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 263፣ https://blog.israelbiblicalstudies.com/jewish-studies/throne-satan-rev-2-2-16/

Israel Institute of Biblical Studies
What is the Throne of Satan?
Revelation 2 mentions the Throne of Satan. What could this be and what does the author mean by it? Is it one of pagan temples or something else more subtle?
👍2❤1👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤”
ዕብራውያን 1፥3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤”
ዕብራውያን 1፥3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤2👍1🥰1👏1
#እራሳችንን_እንመርምር
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ ፍላጎት አለን? ታዲያ በፈቃዱ ለመመላለስ የእኛ ድርሻ ምንድነው? አሁንስ ምን እያደረግን ነው?
“አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።”
መዝሙር 40፥8

👍6❤2🥰1👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እነርሱም የተናገራቸውን ቃል በልባቸው አሳደሩት፤ ነገር ግን፣ 'ከሙታን መነሣት' ምን ማለት እንደሆነ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር።”
ማርቆስ 9፥10 (አዲሱ መ.ት)

👍3❤1🤔1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ኢየሱስም፦ ገና ጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው። ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም።”
ዮሐንስ 12፥35

❤2👍1🔥1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ዕብራውያን 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።
³ በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኃጢአተኞች በደረሰበት እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን አስቡ።
⁴ ከኃጢአት ጋር እየተጋደላችሁ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም፤
⁵-⁶ እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር፦ ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል።
⁷ ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?
⁸ ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።
⁹ ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
¹⁰ እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።
¹¹ ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል።
¹² ስለዚህ የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጉልበቶች አቅኑ፤
¹³ ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ።
¹⁴ ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።
¹⁵ የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥
¹⁶ ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ።
¹⁷ ከዚያ በኋላ እንኳ በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና፤ በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘምና።
¹⁸ ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም ወደ ጨለማም ወደ ዐውሎ ነፋስም ወደ መለከት ድምፅም ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና፤
¹⁹ ያንም ነገር የሰሙት ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው ለመኑ፤
²⁰ እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ ተወግሮ ይሙት የምትለውን ትእዛዝ ሊታገሡ አልቻሉምና፤
²¹ ሙሴም፦ እጅግ እፈራለሁ እንቀጠቀጥማለሁ እስኪል ድረስ የሚታየው እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤
²² ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥
²³ በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥
²⁴ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።
²⁵ ለሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላስረዳቸው እምቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፥ ከሰማይ ከመጣው ፈቀቅ የምንል እኛስ እንዴት እናመልጣለን?
²⁶ በዚያም ጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጠ፥ አሁን ግን፦ አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል።
²⁷ ዳሩ ግን፦ አንድ ጊዜ ደግሜ የሚል ቃል፥ የማይናወጡት ጸንተው እንዲኖሩ፥ የሚናወጡት የተፈጠሩ እንደሚሆኑ ይለወጡ ዘንድ ያሳያል።
²⁸ ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤
²⁹ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።

❤4👍2🔥1🥰1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ብዙ ጊዜም በብዙ ነገር መርምረን ትጉ እንደ ሆነ ያገኘነውን፥ አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ የሚሆነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር እንልካለን።”
2ኛ ቆሮ 8፥22

❤3👍1🔥1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው። አቤቱ፥ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ።”
መዝሙር 4፥6

👍2❤1🥰1👏1
#መጻሕፍትን_እንመርምር
አማኝ ወይም የዳነ ሰው ድነቱን ሊያጣ ይችላል ወይስ አይችልም?
ክፍል-8
በኢየሱስ ከማመናችን በፊት የኃጢአትና «የሰይጣን» ባርያዎች ነበርን (ሮሜ 6፥17)። ካመንን በኋላ ግን የጽድቅ ባርያዎች ሆነናል (ሮሜ 6፥18)። እንዲህ ሲባል የእግዚአብሔርን ጸጋ መቃወምና ደኅንነታችንን ማጣት አይቻልም ማለት ነውን?
በርካታ ክርስቲያኖች ያመኑ ሰዎች ሁሉ ደኅንነታቸውን ማጣት አይችሉም ብለው ያስባሉ። እነዚህ ክርስቲያኖች እንደሚሉት፥ ያመኑ ሰዎች ኃጢአት ሊሠሩና የካዱም ሊመስሉ ይችላሉ ነገር ግን እግዚአብሔር ሁሉጊዜ ወደ ጸጋው ይመልሳቸዋል። ይህንንም «የዘላለም ዋስትና» ብለው ይጠሩታል። እንዲህ ሲሉ «አንዴ የዳነ ሠርክ ድኗል» ማለታቸው ነው።
ሌሎች አያሌ ክርስቲያኖች ግን፥ ያመኑ ሰዎች በእርግጥ እግዚአብሔርን ሊክዱና ደኅንነታቸውንም ሊያጡ ይችላሉ ብለው ያስባሉ። እግዚአብሔር ሊመልሳቸው ይችላል፤ ሆኖም በክህደታቸው ከጸኑ ግን ዳግም ደኅንነትን እንዲቀበሉ አያስገድዳቸውም።
ዋስትና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
ቅዱሳት መጻሕፍት የዘላለም ዋስትናን አስመልክቶ ለሚነሱ ጥያቄዎች ግልጽ መልስ አይሰጡም። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ደኅንነታችንን እንደማናጣ የሚናገሩ ይመስላሉ፤ ሌሎች ክፍሎች ደግሞ ደኅንነታችንን እንደምናጣ የሚናገሩ ይመስላሉ።
ያመኑ ሰዎች እግዚአብሔርን መካድና ደኅንነታቸውንም ማጣት አይችሉም ብለው የሚያስቡት ክርስቲያኖች ሁሉጊዜ የሚያቀርቡት ማስረጃ፥ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት እንደሰጠ የሚናገሩትን ጥቅሶች ነው (ዮሐ. 3፥16፤ 6፥54፤ 11፥26)። ኢየሱስ ሲናገር የእርሱ ለሆኑት በጎች የዘላለምን ሕይወት ሰጥቷቸዋል፤ ስለዚህ ከቶ አይጠፉም፤ "ከእኔ እጅ ማንም ነጥቆ አይወስዳቸውም" ብሏል (ዮሐ 10፥28)። እንዲሁም ወደ እርሱ የሚመጣውን ሁሉ «ወደ ውጪ አላባርረውም» ደግሞም አብ የሚሰጠኝን ሁሉ አንድ እንኳ አላጠፋም ብሏል (ዮሐ. 6፥37፤ 39)። ጳውሎስ በበኩሉ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም ነገር እንደሌለና (ሮሜ 8፥38–39) «የርስታችን መያዣ» በሆነው በመንፈስ ቅዱስ እንደታተምንም ተናግሯል (ኤፌ. 1፥14)። በሌላም ቦታ «ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ሕይወት ውስጥ የጀመረ አምላክ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ በሚመለስበት ቀን ወደ ፍጻሜ እንደሚያደርሰው እርግጠኛ ነኝ» ብሏል (ፊል. 1፥6)። እግዚአብሔር የሰጠነውን ዐደራ መጠበቅ የሚችል ነው (2ጢሞ. 1፥12)፤ ከፈተና ሊታደገንና (2ጴጥ. 2፥9) እንዳንወድቅም ሊያደርገን የሚችል ነው (ይሁዳ 24)። ከእነዚህ ጥቅሶች እንደምንረዳው አማኞች የዘላለም ዋስትና አላቸው።
ነገር ግን ያመኑ ሰዎች ደኅንነታቸውን ሊያጡ ይችላሉ ብለው የሚናገሩት ክርስቲያኖች፣ ደኅንነታችንን ልናጣ እንደምንችል የሚያስጠነቅቁ ንባቦችን ለምሳሌ፥ «እስከ መጨረሻ በትዕግስት የሚጸና ግን ይድናል» የሚሉትን እንድናይ ይጠቁሙናል (ማር. 13፥13)። ከዚህ በተጨማሪ 1ቆሮ. 15፥12፤ ቆላ. 1፥21-23፤ ዕብ. 3፥6፤ 12፤ 10፥35–36 እንድንመለከት ይጋብዙናል። እንዲሁም ኢየሱስ በዮሐንስ 15፥1–6 ላይ «በእኔ ጸንቶ የማይኖር ሁሉ እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ተጥሎ ይደርቃል ወደ እሳት ይጣልና ይቃጠላል» በማለት የተናገረውንም እንድናጤን ያሳስባሉ። ጳውሎስ በሮሜ 11፥22 ላይ ሲናገር፥ በእግዚአብሔር ምሕረትና ጸጋ ጸንተው የማይኖሩ አረማውያንን «እናንተም ተቆርጣችሁ ትወድቃላችሁ» ብሏል። እንዲሁም የገላትያን ሰዎች ሲያሳስብ ወደ ብሉይ ኪዳን ሕግ የሚመለሱ አማኞችን «ከጸጋው ወድቃችኋል» ብሏል (ገላ. 5፥1–4)። ኢየሱስ ራሱ የዘሪውን ምሳሌ እያብራራ ሳለ «እነርሱ የሚያምኑት ለጊዜው ነው... በፈተና ጊዜ ወዲያውኑ ይክዳሉ» (ሉቃ. 8፥13) በማለት ተናግሯል። ጳውሎስ ሲያስታውቅ «አንዳንድ ሰዎች ሃይማኖትን ይክዳሉ» (1ጢሞ. 4፥1) ብሏል። የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ደግሞ «የመንፈስ ቅዱስ ተካፋዮች» የነበሩ ሰዎች ወይም በክርስቶስ ደም «የተቀደሱ» ሰዎች ክርስቶስን ሊክዱ እንደሚችሉ ጠቁሟል (ዕብ. 6፥4-6፤ 10፥28–29፤ 39)። አዲስ ኪዳን ሌሎችንም ማስጠንቀቂያዎች ይሰጣል (2ጴጥ. 2፥20–21፤ ራእ. 3፥5፤ 22፥19)። እነዚህ ክርስቲያኖች ደኅንነታችንን የማናጣ ከሆነ እነዚህ ማስጠንቀቂያዎች ለምን ተሰጡ? በማለት ይጠይቃሉ።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 28

👍3❤1👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው? ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣ ብርሃንም ከሌለው፣ በእግዚአብሔር ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ።”
ኢሳይያስ 50፥10 (አዲሱ መ.ት)

❤3👍1🔥1🥰1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
የቀጠለ...
ሮሜ 8፥9-11
የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በአማኝ ሕይወት ውስጥ
ነገር ግን አያሌ ክርስቲያኖች እንደሚያምኑት፥ ቅድስና ጊዜ የሚወስድና በሞትንም ጊዜ እንኳ ፍጻሜ የማያገኝ ረጅም ሂደት ነው። እንዲህ የሚሉት ክርስቲያኖች ለቅድስና ልዩ የሆነ ልምምድ አለ የሚለውን አባባል አይቀበሉም። ከዚህ ይልቅ መጻሕፍት ፍጹማን «ሆነናል» (ገላ. 3፥3፤ ዕብ. 10፥14፤ 12፥10–11) ወይም ኃጢአትን እየታገልን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ በማለት የሚያስተምሩትን እንድናነብ ይጠቁሙናል (ዕብ. 12፥12)። በርካታ አዲስ ኪዳናዊ ንባባት ሰውነታችንን «እንድናለማምድ»፥ ራሳችንን «መሥዋዕት አድርገን እንድናቀርብ»፥ ሩጫችንን በትዕግስት «እንድንሮጥና» እንደሚገባም «እንድንታገል» ያሳስቡናል። ከእነዚህ ንባባት እንደምንረዳው ገና ፈጽሞ ቅዱሳን አልሆንም።
ራሱ ጳውሎስ እንደተናገረው ምንም እንኳን በመንፈሳዊ ሕይወት ከበሰሉት መካከል ቢሆንም (ፊል. 3፥15) ፍጹም ቅዱስ እንዳልሆነና ወደዚያ ቅድስና ለመድረስ ግን እንደሚጣጣር (ፊል. 3፥12-14) አስታውቋል። አንዳንዶች ደግሞ ዮሐንስ፥ በ1ኛ ዮሐንስ 1፥8 ላይ «ኃጢአት የለብንም ብንል እውነተኞች አይደለንም» በማለት የተናገረውን ያመለክቱናል። በክርስቶስ «የበሰሉ» ሰዎች እየሆንን በመጣን ቁጥር ኃጢአታችንንና ደካማነታችንን የበለጠ እየተረዳን እንመጣለን። ጳውሎስ ወደ ሕይወቱ ማብቂያ ግድም ላይ ከኃጢአተኞች ሁሉ «የባስሁ» ኃጢአተኛ ነበርኩ በማለት ተናግሯል (1ጢሞ. 1፥15)። ይህን ሁለተኛውን አመለካከት የሚቀበሉ ክርስቲያኖች እንደሚናገሩት፥ ሮሜ ምዕራፍ 7 የሚያስተምረው በዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ከኃጢአት ጋር ስለሚታገሉ ክርስቲያኖች ነው። አንድ ክርስቲያን በሮሜ ምዕራፍ 8 ላይ የተገለጠውን የድል ሕይወት መለማመድ የሚጀምረው ቀስ በቀስ ነው። ይሁንና በዚህ ዓለም ከአሮጌው የሥጋ ፈቃድ ጋር የሚያደርገው ፍልሚያ ከቶ ፍጻሜ አያገኝም።
የእያንዳንዱ ክርስቲያን ልምምድ ለየቅል ነው። በርካታ ክርስቲያኖች ይህን «ሁለተኛ በረከት» ወይም ልዩ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት እንደተቀበሉ ይናገራሉ። አንዳንድ ክርስቲያኖች በየጊዜው ወይም ቀስ በቀስ ከሚለማመዱት ቅድስና በተጨማሪ ድንገት የሚለማመዱት ቅድስናም እንዳለ ይናገራሉ። እግዚአብሔር በተለያዩ ሰዎች ሕይወት ውስጥ በተለያየ መንገድ ይሠራል። የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በእኛ ውሱን ልምምድ መወሰን የለብንም።
ስለ ቅድስና ልምምድ ያለን አመለካከት የቱንም ያህል ቢለያይ፥ አንድ ግልጽ የሆነ ኀላፊነት ግን አለብን። ይኸውም ቅዱሳን እንድንሆን ታዘናል። ጴጥሮስ ሲጽፍ እንዲህ ብሏል፥ «… በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ» (1ጴጥ. 1፥15)። «ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ፤ በቅድስናም ለመኖር ትጉ፤ ምክንያቱም ያለ ቅድስና ማንም እግዚአብሔርን ማየት አይችልም» (ዕብ. 12፥14)።
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 33

❤3👍2🔥1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“የእርሱ ለመሆናችን ማኅተሙን ያተመብን ደግሞም ወደ ፊት ለምናገኘው ነገር የመንፈሱን ዋስትና በልባችን ያኖረ እርሱ ነው።”
2ኛ ቆሮንቶስ 1፥22 (አዲሱ መ.ት)

ከእግዚአብሔር ስሞች መካከል "ጆሆቫ ራፋ" አንዱ ነው። ትርጉሙ ምን ማለት ነው?
Anonymous Quiz
24%
ሀ. እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ
16%
ለ. እግዚአብሔር ዓለማዬ ነው
39%
ሐ. እግዚአብሔር ፈዋሽ
6%
መ. ጌታ
14%
ሠ. እግዚአብሔር ያዘጋጃል
👍3❤1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ዕዳ አለብን፥ እንደ ሥጋ ፈቃድ ግን እንኖር ዘንድ ለሥጋ አይደለም።
¹³ እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ።
¹⁴ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
¹⁵ አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።
¹⁶ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።
¹⁷ ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።
ሮሜ 8 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ ግዴታ አለብን፤ ይሁን እንጂ እንደ ሥጋ እንድንኖር ለሥጋ አይደለም።
¹³ እንደ ሥጋ ብትኖሩ ትሞታላችሁና፤ ክፉ የሆነውን የሥጋ ሥራ በመንፈስ ብትገድሉ ግን፣ በሕይወት ትኖራላችሁ፤
¹⁴ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
¹⁵ እንደ ገና የፍርሀት ባሪያ የሚያደርጋችሁን መንፈስ ሳይሆን፣ “አባ፣ አባት” ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ ተቀብላችኋልና፤
¹⁶ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ሆኖ ይመሰክርልናል።
¹⁷ ልጆች ከሆን ወራሾች ደግሞ ነን፤ የክብሩ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ በርግጥ የመከራው ተካፋዮች ብንሆን፣ የእግዚአብሔር ወራሾች፣ ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።
ሮሜ 8 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ ፥ ለሥጋዊ ፈቃድ ተሸንፋችሁ ልትገዙለት አይገባም።
¹³ ለሥጋ ፈቃዳችሁ ተገዢዎች ከሆናችሁ ትሞታላችሁ። የሥጋ ፈቃዳችሁን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ድል ከነሳችሁት ግን በሕይወት ትኖራላችሁ።
¹⁴ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።
¹⁵ ስለዚህ የተሰጠን መንፈስ በአባቱ እቅፍ እንዳለ ልጅ ፥ 'አባ ፥ አባባ!' ብለን በድፍረት እግዚአብሔርን የምንጠራበት የልጅነት መንፈስ እንጂ ፥ የሚያስፈራና የሚያሸማቅቅ የተገዢነት መንፈስ አይደለም።
¹⁶ በእርግጥም የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ፥ ራሱ መንፈስ ቅዱስም ሆነ የራሳችንም መንፈስ ያረጋግጥልናል።
¹⁷ የእግዚአብ ሔር ልጆች ከሆንን ፥ ወራሾች ነን ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጋር አብረን የርስቱ ተካፋዮች እንሆናለን። ከእርሱ ጋር አብረን መክበር የምንችለውም ፥ የክርስቶስ የመከራው ተካፋዮች ሆነን ስንገኝ ነው።

👍2❤1🔥1👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ለራስሽ የመንገድ ምልክት አድርጊ፥ መንገድንም የሚመሩ ዓምዶችን ትከዪ፥ ልብሽንም ወደ ሄድሽበት መንገድ ወደ ጥርጊያው አቅኚ፤ አንቺ የእስራኤል ድንግል ሆይ፥ ተመለሺ፥ ወደ እነዚህም ወደ ከተሞችሽ ተመለሺ።”
ኤርምያስ 31፥21

❤3👍1👏1
#እራሳችንን_እንመርምር
ከጌታችን እና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረን ወራሽ መሆን እንፈልጋለን? ታዲያ እርሱ ያለፈበትን መንገድ ጠልተን እንዴት ከእርሱ ጋር ወራሽ እንሆናለን? ጌታችን በምን ጎዳና ይሆን ያለፈው?
“ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።”
ሮሜ 8፥17

❤4👍1👏1