ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.38K photos
61 videos
333 files
809 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ።”
          ኢሳይያስ 40፥25




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures

Follow the ቅዱሳት መጻሕፍት channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaA94PKFsn0ejWkJe012
2👍1👏1
📜ርዕስ፦ "ለታማኝ አገልጋይነት የሚጠቅሙ ባሕርያት"
🖨አሳታሚ:- SIM ማተሚያ ቤት
📅የታተመበት ዓ.ም፦  1983
🔢የገጽ ብዛት፦ 99



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures

Follow the ቅዱሳት መጻሕፍት channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaA94PKFsn0ejWkJe012
3👍1🥰1
CFS_01.pdf
630.9 KB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures

Follow the ቅዱሳት መጻሕፍት channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaA94PKFsn0ejWkJe012
3👍3
               📜📜📜===📜📜📜  
               📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
               📜📜📜===📜📜📜
“የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።”
           2ኛ ተሰሎንቄ 3፥16




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3🥰2👍1
ቤት ውስጥ ምን ያህል መጽሐፍ ቅዱሶች አሉዎት? አብዛኞቻችን ብዙ መጽሐፍ ቅዱሶች አሉን። የእንግሊዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ አባት ተብሎ የሚጠራው ዊልያም ቲንደል ዛሬ ለእንግሊዝኛ ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ መኖር ዋነኛው ሰው ነው። ምንም እንኳን 90% የኪንግ ጀምስ ቨርዥን(KJV) እና 75% የተሻሻለው ስታንዳርድ ቨርሽን(RSV) ምንጭ የሆነው የዊልያም ቲንደል የእንግሊዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ቢሆንም ቲንደል በዚህ ቀን ኦክቶበር 6፣ በ1536 መጽሐፍ ቅዱስ ስለተረጎመ በአደባባይ በእንጨት ላይ በእሳት ተቃጥሏል። በእጃችን ላይ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ ዋጋውን እንድንረዳው እግዚአብሔር ይርዳን!


ምንጭ፦ biblestudytools.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1🔥1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል።”
                   ምሳሌ 16፥32




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1🔥1👏1
#እራሳችንን_እንመርምር


ለመሆኑ እግዚአብሔርን የምናስበው ሁልጊዜ ለእኛ መልካም አሳብ የሚያስብ አምላክ አድርገን ነው ወይስ አልፎ አልፎ የሚጎዳንን ነገር የሚያደርግ አምላክ ብለን? ቁጣው እና ተግሳጹን፣ ቅጣቱን እና ማስጨነቁን እንደጉዳት ቆጥረነው ይሆን?


“ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።”
ኤርምያስ 29፥11





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21🥰1👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን።”
                     ኤፌሶን 1፥5




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32🔥1🥰1
#መጻሕፍትን_እንመርምር

አማኝ ወይም የዳነ ሰው ድነቱን ሊያጣ ይችላል ወይስ አይችልም?



                        ክፍል-7


እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ ጠርቷልን?

እግዚአብሔር የሚፈልገው እያንዳንዱ ሰው ደኅንነትን እንዲያገኝ ነው ወይስ ጥቂቶች ብቻ? በማቴዎስ 22፥14 ላይ ኢየሱስ ሲናገር፥ «የተጠሩ ብዙዎች ናቸው፤ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው» ብሏል። ኢየሱስ የዓለም አዳኝ እንደሆነና (ዮሐ. 4፥42፤ 1ዮሐ. 4፥14) የዓለምንም ኃጢአት ለማስወገድ ሲል እንደሞተ በግልጽ መረዳት ይቻላል (ዮሐ. 1፥29፤ 1ዮሐ. 2፥2)። ከዚህ በተጨማሪ ጳውሎስ ሲናገር እግዚአብሔር «ሰዎችን ሁሉ» እንዲድኑ እግዚአብሔር ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል (ሮሜ 11፥32፤ 1ጢሞ. 2፥46፤ 2ጴጥ. 3፥9)። ግን «ሰዎችን ሁሉ» ማለት ምን ማለት ነው? «ሰዎችን ሁሉ» የሚለውስ ሐረግ ምንን ያመለክታል?

1. አንዳንድ ክርስቲያኖች እንደሚሉት «ሰዎችን ሁሉ» ማለት «ከሁሉም የኀብረተሰብ ክፍሎች» ማለት ነው። እንዲህም ሲባል እግዚአብሔር ከሁሉም የኀብረተሰብ ክፍሎች አንዳንድ ሰዎችን ጠርቷል ወይም መርጧል ማለት ነው። እንዲህ የሚሉት ክርስቲያኖች እግዚአብሔር የክርስቶስ ወንጌል በዓለም ሁሉ እንዲዳረስ ፍላጎቱ ነው፤ ይሁንና የእምነትን ስጦታ የሚሰጠው ከእያንዳንዱ የኀብረተሰብ ክፍል ውስጥ ለጥቂቶች ብቻ ነው ይላሉ።

2. እንደ ሌሎች ክርስቲያኖች አባባል ግን «ሰዎችን ሁሉ» ማለት «አንድም ሳይቀር ሁሉንም ሰዎች» ማለት ነው። ምንም እንኳን እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ ቢጠራም፥ አማኞች ብቻ ናቸው «የተመረጡ» ተብለው መጠራት ያለባቸው ይላሉ (በግሪኩ ንባብ ላይ ሁለቱም ፍቺዎች ያስኬዳሉ)።'

የሆነ ሆኖ ስለ ኢየሱስ ምንም ያልሰሙ ሰዎች እንዴት ይሆናሉ? የሚድኑበትስ መንገድ ይኖራልን? አያሌ ክርስቲያኖች ከቶ አይድኑም ይላሉ። ሰዎች ሁሉ በተፈጥሮዋቸው ኃጢአተኞች ናቸው። ሁሉም ሰው ሞት ይገባዋል (ሮሜ 3፥10–12፤ 6፥23)። በክርስቶስ ካልሆነ በቀር በሌላ በምንም መንገድ መዳን አይቻልም (ዮሐ. 14፥6፤ የሐዋ. 4፥12)። ስለዚህ ጳውሎስ በሮሜ 10፥13–14 ላይ ሲጽፍ እንዲህ ብሏል፥ «የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል ተብሎ ተጽፎአል። ነገር ግን ሳያምኑበት እንዴት ሊጠሩት ይችላሉ?። ስለ እርሱስ ሳይሰሙስ እንዴት ያምናሉ? የምሥራቹን ቃል የሚያበሥርላቸው ሳይኖርስ እንዴት ሊሰሙ ይችላሉ?» እግዚአብሔር ስለ ኢየሱስ ምንም ላልሰሙ ሰዎች ምሕረቱን ሊያሳይ ይችላል (ሉቃ. 12፥47-48፤ ሮሜ 2፥12)፤ ነገር ግን ይህ የእግዚአብሔር ውሣኔ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ምንም ስላልሰሙ ሰዎች ግልጽ የሆነ ትምህርት የለውም። ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ የመመስከር ኃላፊነት እንዳለብን በግልጽ ያወሳል።

በዚህ ክፍል የተነሱት ጥያቄዎች አስቸጋሪዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች ሁሉ ቁርጥ መልስ አይሰጠንም። የእግዚአብሔር አሳብ እኮ ፍጹም ምስጢር ነው! ጥበቡና ዕውቀቱም እጅግ ጥልቅ ነው! (ሮሜ 11፥33–36)። ምናልባት እነዚህ ሁሉ አማራጮች በከፊል እውነትነት ይኖራቸዋል። ዮሐንስ ሲጽፍ፥ «እግዚአብሔር አስቀድሞ ስላፈቀረን እኛም እናፈቅራለን» (1ዮሐ. 4፥19) ብሏል። ምናልባትም እንዲህ ማለት ይቻላል፥ «እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለመረጠን እኛም እርሱን መረጥነው» ደኅንነት የእግዚአብሔር ሥራ ቢሆንም እኛም ግን ድርሻ ያለን ይመስላል። ጳውሎስ እነዚህን ሁለት ሀሳቦች አያይዞ ሲጽፍ፥ «እያንዳንዳችሁ ያላችሁን ደኅንነት ፍጹም ለማድረግ በፍርሃትና በአክብሮት ተግታችሁ ሥሩ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ፈቃደኛነትንና ታዛዥነትን ለእናንተ እየሰጠ ዓላማውን ከፍጻሜ ለማድረስ በእናንተ ውስጥ ይሠራል» ብሏል (ፊል. 2፥12–13)።


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 26





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ኢያሱም በጋይ የሚኖሩትን ሁሉ ፈጽሞ እስኪያጠፋ ድረስ ጦር የዘረጋባትን እጁን አላጠፈም።”
           ኢያሱ 8፥26




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21🔥1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?



ሐጌ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ አለቃ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤል፥ ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦
² የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ ይህ ሕዝብ፦ ዘመኑ አልደረሰም፥ የእግዚአብሔር ቤት የሚሠራበት ዘመን አልደረሰም ይላል ብሎ ተናገረ።
³ የእግዚአብሔርም ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ እንዲህ ሲል መጣ፦
⁴ በውኑ ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በተሸለሙ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?
⁵ አሁንም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ።
⁶ ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፤ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፤ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ።
⁷ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ።
⁸ ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
⁹ እናንተ ብዙ ነገርን ተስፋ አደረጋችሁ፥ እነሆም፥ ጥቂት ሆነ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አልሁበት። ይህ ስለ ምንድር ነው? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ሁሉ ወደ እየቤታችሁ እየሮጣችሁ የእኔ ቤት ፈርሶ ስለ ተቀመጠ ነው።
¹⁰ ስለዚህ ሰማያት በላያችሁ ጠልን ከልክለዋል፥ ምድሪቱም ፍሬዋን ከልክላለች።
¹¹ እኔም በምድርና በተራሮች፥ በእህልና በወይንም፥ በዘይትና ምድርም በምታበቅለው ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶችም ላይ፥ እጅም በሚደክምበት ሁሉ ላይ ድርቅን ጠርቻለሁ።
¹² የሰላትያልም ልጅ ዘሩባቤል፥ ታላቁም ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ሕዝብ ሁሉ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ድምፅ የነቢዩንም የሐጌን ቃል፥ አምላካቸው እግዚአብሔር እንደ ላከው ሁሉ ሰሙ፤ ሕዝቡም በእግዚአብሔር ፊት ፈሩ።
¹³ የእግዚአብሔርም መልእክተኛ ሐጌ በእግዚአብሔር መልእክት ሕዝቡን፦ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር ብሎ ተናገረ።
¹⁴-¹⁵ እግዚአብሔርም የይሁዳን አለቃ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፥ የታላቁንም ካህን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስ፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አስነሣ፤ በንጉሡም በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በሀያ አራተኛው ቀን መጡ፥ የአምላካቸውንም የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቤት ሠሩ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ጥበብንና ኃይልን የሰጠኸኝ፥ እኛም የለመንንህን ነገር አሁን ያስታወቅኸኝ፥ አንተ የአባቶቼ አምላክ ሆይ፥ የንጉሡን ነገር አስታውቀኸኛልና እገዛልሃለሁ አመሰግንህማለሁ።”
              ዳንኤል 2፥23





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32🥰1👏1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት

የቀጠለ...


ሮሜ 8፥9-11



የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በአማኝ ሕይወት ውስጥ


የእግዚአብሔርን ቅጣት እየተቀበልን (ዕብ. 12፥9–11) በመንፈሳዊ ነገር ራሳችንን ማለማመድ አለብን።

"በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ። የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን። ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤ ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ።"
1ኛ ቆሮንቶስ 9፥24-27


“ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።”
1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥7

እንቅፋት የሚሆንብንን ኃጢአት «እያስወገድን»

“እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።”
2ኛ ቆሮ 7፥1

(ዕብ. 12፥1–2) ሰውነታችንንና ኅሊናችንን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገን ማቅረብ አለብን (ሮሜ 6፥13፤ 19፤ 12፥12)። መጽሐፍ ቅዱስን ዘወትር ማንበብና (2ጢሞ. 3፡16) ማሰላሰል

“አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።”
መዝሙር 119፥11

(2ጴጥ. 1፥4)፥ የመጻሕፍቱም ትምህርት ባሕሪያችንን እንዲለውጥ ራሳችንን ዝግጁ ማድረግ አለብን። እግዚአብሔር ካስቀመጣቸውም መሪዎች አንዳንድ ምክርንና እርዳታን ማግኘት እንችላለን (ኤፌ. 4፥11–13)። ከዚህ ሁሉ በላይ እግዚአብሔር እንዲያግዘን መጸለይ ይኖርብናል (ቆላ. 1፥9–10፤ 1ተሰ. 3፥12–13፤ 5፥23)። አልያ ግን ልንወድቅ እንችላለን።

አንዳንድ ክርስቲያኖች ቅድስናን ለማግኘት ልዩ የሆነ ሌላ መንገድ አለ ብለው ያምናሉ። ከብዙ ጸሎትና ምልጃ በኋላ ልዩ በሆነ ልምምድ ቅድስናን እንቀበላለን፤ የምንፈልገውንም ቅድስና እንደተቀበልን እርግጠኞች መሆን እንችላለን ይላሉ። ይህን የቅድስና ልምምድ «ሁለተኛው የጸጋ ሥራ» በማለት ይጠሩታል (የመጀመሪያው የጸጋ ሥራ ደኅንነታችን ነው)። እነዚህ ክርስቲያኖች እንደሚያስተምሩት ደኅንነትን ስናገኝ ዳግም እንወለዳለን፥ ከዓለምም ተለይተን (1ዮሐ. 5፥4) የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች እንሆናለን (ሮሜ 8፥9)። በክርስቶስም «ሕፃናት» እንሆናለን (1ቆሮ. 3፥1)። ይሁን እንጂ «ሁለተኛው የጸጋ ሥራ»፥ አንዳንድ ጊዜ «ሁለተኛው በረከት» በመባል ይታወቃል፥ ከእኔነት ተለይተን ቅዱሳን እንድንሆንና (ገላ. 2፥20) በመንፈስ ቅዱስም እንድንሞላ ያደርገናል (ኤፌ. 5፥18)። በመሆኑም «የበሰሉና» (ኤፌ. 4፥13) የእግዚአብሔርም ፍቅር በውስጣችን «ፍጹም» የሆኑ ሰዎች እንሆናለን (1ዮሐ. 4፥12፤17)። ከእነዚህ ውስጥ አያሌ ክርስቲያኖች እንደሚያምኑት አውቀንም ሆነ ፈቅደን ኃጢአትን ማድረግ እስከማንችል ድረስ ፍጹም ቅዱሳን መሆን እንችላለን (1ዮሐ. 3፥9)። ሮሜ ምዕራፍ 7 ስላልበሰሉ ክርስቲያኖች ሲናገር ሮሜ ምዕራፍ 8 «ሁለተኛውን በረከት» ስለተቀበሉና ስለበሰሉ ክርስቲያኖች ይናገራል ይላሉ። ለዚህ የቅድስና ልምምድ እንደ ዋቢ የሚጠቅሱት በሐዋርያት ሥራ 2፥4 እና 9፥17 ላይ ያለውን የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ክስተት ነው።



ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 32-33



ይቀጥላል...




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1👏1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች ሚስት፣ ስታታልሉኝ ኖራችኋል፤ ይላል እግዚአብሔር።”
            ኤርምያስ 3፥20 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
የቀጠለ...


📜መጽሐፍ ቅዱሳችን እንዴት ተፃፈ



መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት ሁሉ ልዩ የሆነበት ምክንያት ምንድነው?


መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት ልዩ የሆነበት ምክንያት፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲያንን እግዚአብሔር ራሱ በቀጥታ በተለየ መንገድ ስለመራቸው ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች እግዚአብሔር እንዲጽፉ የፈለገውን ነገር የጻፉት በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መሪነት ነበር (2ጢሞ. 3፥16፤ 2ጴጥ. 1፥21)። መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ቃል ብቻ አይደለም። ነገር ግን የእግዚአብሔር የራሱ ቃል ነው።

ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ቃሉን እንዲጽፉ በሰዎች ተጠቅሞአል። እግዚአብሔር እያንዳንዱን ቃል በመናገር እንዲጻፍ አላደረገም፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በራሳቸው አእምሮ ተጠቅመው ስለ ጻፉት የግለሰብ ስብእናቸውና ጠባያቸው በጽሑፎቻቸው ውስጥ ሊታይ ይቻላል። ልክ ኢየሱስ ራሱ በአንድነት እግዚአብሔርም ሰውም እንደነበረ፥ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲሁ በአንድነት የእግዚአብሔርም ቃል፥ የሰውም ቃል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው የእግዚአብሔርን ሀሳብ በተለየ መንገድ በሚያውቁ ሰዎች ነው። እግዚአብሔር አሳቡን ገለጠላቸው፤ እነርሱም እግዚአብሔር በገለጠላቸው መሠረት ጻፉት። ሌሎች ክርስቲያን ጸሐፊዎች በአጠቃላይ በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው እግዚአብሔርን የሚያስደስቱ መጻሕፍትን መጻፋቸው እርግጥ ነው። ነገር ግን እነርሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ፀሐፊዎች የነበራቸውን የእግዚአብሔርን ሃሳብ በተለየ መንገድ የማወቅ ችሎታ አልነበራቸውም። ከዚህም የተነሣ መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት ሁሉ የተለየ ነው። የተገለጠና ሥልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ሙሉ በሙሉ እውነት ነው፤ ምንም ስሕተት የለበትም። አንዳንድ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ «በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አገኘን» ይላሉ። በኋላ ግን የተሳሳቱት ራሳቸው እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ እንዳልነበረ ይረዳሉ። በተደጋጋሚ ጊዜያት በታሪካዊና በከርሰ ምድር ምርመራ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችን እውነት አረጋግጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ በታሪክም ሆነ በሳይንስ በሁሉ አቅጣጫ ተመርምሮ እውነተኛነቱ ተረጋግጦአል።

ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን የታሪክ ወይም የሳይንስ መጽሐፍ እንደምናነበው ማንበብ ብቻ በቂ አይደለም። በአእምሮአችን ብቻ ተጠቅመን መጽሐፍ ቅዱሳችንን ማንበብ በቂ አይሆንም። መጽሐፍ ቅዱስን በመንፈሳችን ጭምር ማንበብ ይኖርብናል፤ አለበለዚያ ግን የመጽሐፍ ቅዱሱን ጥቅል መንፈሳዊ እውነት ለማወቅ አንችልም። መጽሐፍ ቅዱስን በምናነብበት ጊዜ በትሕትና ራሳችንን ዝቅ አድርገን የእግዚአብሔርን እውነት ለመቀበል የተከፈተ አእምሮ ሊኖረን ያስፈልጋል። እግዚአብሔር መንፈሳዊ ማስተዋል እንዲሰጠን መጸለይ ይኖርብናል። ይህንንም በእምነት በምናደርግበት ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ለእኛ ሕያው ይሆናል፤ ሕይወታችንንም ይለውጠዋል።

መጽሐፍ ቅዱስን ሕያው ሊያደርግና በአንባቢው ልብ ውስጥ ኃይለኛ ሊያደርገው የሚችል መንፈስ ቅዱስ ነው (2ቆሮ. 3፥6)። መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው የሚኖር ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛና ሕያው የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ በውስጣቸው ሊረዱ ይችላሉ። ከመጽሐፍ ቅዱስም እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ወይም ክርስቶስ ማን እንደሆነ በእርግጠኝነት ሊያውቁ ይችላሉ። እግዚአብሔር ያደረገውንም ነገር ከመጽሐፍ ቅዱሳቸው ሊያውቁ ይችላሉ። ብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ሰዎችን ለመገናኘት ያደረገውንና የሰዎችንም እምቢተኛነትና ኃጢአት መዝግቦ የያዘ ነው። ብሉይ ኪዳን በግልጥ የሚያሳየው ሰዎች ኃጢአተኞች መሆናቸውንና አዳኝም እንደሚያስፈልጋቸው ሲሆን አዲስ ኪዳን ገልጦ የሚያሳየው ደግሞ ሰዎችን የወደደ አምላክ መኖሩን ነው። ይህ አምላክ ሰዎችን በጣም ከመውደዱ የተነሣ ራሱ ወደ መሬት መጣ፣ የመጣውም በሰው አምሳል ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ ሆኖ ሰዎችን ከኃጢአታቸው ለማዳንና የዘላለም ሕይወትን ለመስጠት ነው። መከራ ተቀበለ፥ ሞተም።

አንባቢ ይህንን መጽሐፍ በሚያጠናበት ጊዜ እግዚአብሔር ከቅዱሳት መጽሐፍ ያስተምረው ዘንድ ራሱን እንደሚያዘጋጅ ይታመናል። እንግዲህ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት ብቻ ሳይሆን እንኖርበትም ዘንድ ግድ ነው።



ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 91-92




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ከፀሐይ በታች በደከመበት ድካም ሁሉና በልቡ አሳብ የሰው ጥቅም ምንድር ነው?”
               መክብብ 2፥22




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21🥰1🤔1
በደቡብ ያለው መናገሻውን ኢየሩሳሌም ያደረገው መንግሥት የትኛው ወገን ነበረበት?
Anonymous Quiz
35%
ሀ. ይሁዳ
10%
ለ. ብንያም
7%
ሐ. ኤፍሬም
7%
መ. ጋድ
3%
ሠ. ሁሉም
39%
ረ. ሀ እና ለ
👍32
ከሚከተሉት ውስጥ በጠርሴስ የተወለደ፣ በገማልያል እግር ስር የአይሁድን ሕግ ጠንቅቆ የተማረ ሰው ማን ነው?
Anonymous Quiz
9%
ሀ. አጵሎስ
2%
ለ. ቲቶ
78%
ሐ. ጳውሎስ
9%
መ. ጢሞቴዎስ
3%
ሠ. በርናባስ
9👍1