#እራሳችንን_እንመርምር
ስለወንጌል ሁሉን እናደርጋለን ወይስ ለጥቅማችን ስንል ሁሉን እናደርጋለን? ኧረ እንዲህማ አይሆንም ይሄማ ከባድ ተቃርኖ ነው። የሚል አይጠፋም እስቲ አሳቡን ጠበብ እናድርገው። ስለወንጌል ሁሉን እናደርጋለን ወይስ ወንጌል እየሰበክን ስለወንጌል ጥቅማችንን መተው ይከብደናል? ወንጌልን ለምንድነው የምንሰብከው? ባንሰብክስ? ወንጌልን ለመስበክ ምን ያህል ርቀት እንጓዛለን? ወንጌልን ስንሰብክ በአእምሯችን ምን እናገኛለን ብለን ነው? ወንጌልን መስበክ ግዴታ ወይስ መብት?
"እንደዚሁም የወንጌልን ቃል የሚያስተምሩ መምህራንም ፥ ለኑሮአቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ከምዕመናን እንዲቀበሉ ጌታ ፈቅዶላቸዋል። እኔ በበኩሌ ግን በዚህ መብቴ አልተጠቀምኩበትም። አሁንም ይህን መጻፌ በዚሁ መብት ለመጠቀም ፍላጐት ኖሮኝ አይደለም። ወንጌልን ያለምንም ዋጋ ስለሰበክሁላችሁ ያገኘሁት ደስታ ይህ ነው አይባልም። ስለዚህ ይህን ከማጣ በረሃብ ብሞት ይሻለኛል። ወንጌልን በመስበኬም ልመካበት አልችልም። ልመካበት የማልችለውም የምሰብከው ጌታ ኢየሱስ ስላዘዘኝ በመሆኑ ነው። ጌታ እንዳዘዘኝ የወንጌሉን ቃል ሳልሰብክ ብቀር ግን ወዮልኝ። ይህን ወንጌል በፍቃደኝነትና በውዴታ ብሰብክ ለድካሜ ዋጋ አለኝ። ነገር ግን ያለፈቃደኝነት ባደርገው ኃላፊነቴንና ግዴታዬን ብቻ መወጣቴ ይሆናል። እን ዲህ ከሆነ ታዲያ ደመወዜ ምንድን ነው? የእኔስ ደመወዝ ወንጌልን በነፃ እየሰበክሁ ፥ ላገኝ የሚገባኝን ጥቅም በመተው የማገኘው ደስታ ብቻ ነው።"
1ኛ ቆሮ 9፥14-18 (ሕያው ቃል)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot

❤1👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ፦ አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው አለ።”
ማርቆስ 9፥24

❤5👍1
“ድምጽ ነኝ!”
“አንተ ማን ነህ?” ቢሉት ማዕረጉን ፍለጋ
ሰባኪዉ ዝም ጭጭ መልስ የለም እርሱ ጋ
“በል ባክህ ንገረን
ደግሞ እንቸኩላለን
ለሚጠባበቁን ወሬ እናደርሳለን፤
እንዲህ የሆነ እንደሁ ዝናህም ይወጣል
አገር ጉድ እያለ በክብር ያጅብሃል።”
ጠብ የሚል ሲጠፋ የሚደረድረዉ
የማዕረግ አይነት የሚከናነበዉ
እንደነበር ሲቆም በአንክሮ እያያቸዉ
አማራጭን ሰጡት እንዲመርጥላቸዉ።
“ክርስቶስ ነህ ኤልያስ ወይስ ነቢዩ ነህ?
ምንስ ነዉ ማዕረግህ ማን ብለን እንጥራህ?
እባክህ ንገረን ክብር ደረጃህን
ስምና መለያ የሚመጥንህን”
ያን ጊዜ ከበደዉ መታገስ አቃተዉ
ማድመጥም አልቻለ እንኳን ሊደርበዉ
የሚጯጯሁትን ቀና ብሎ አየና
“ድምጽ ነኝ”! አላቸዉ እጅጉን ጮኸና
ያመጡትን ኮከብ የሚለጥፉትን
አራግፎ ከላዩ ሰዉ ሠራሽ ማዕረግን
እንዲህ ሲል ቀጠለ ሰባኪው ጩኸቱን፡-
“ድምጽ ነኝ፣ ድምጽ ነኝ ያዉም የበረሀ
መንገድ የሚያቀና እንዲያልፍበት ዉሀ
እንደልቡ እንዲሔድ ሕይወት ሰጭዉ ጅረት
ጥርጊያዉን አቅኝ ነኝ በሚሰጠኝ ምህረት
በሉ አትነዝንዙኝ ማንነቴ ይህ ነው
ሌላ ምንም የለኝ ስለራሴ እምለዉ
ኋላዬ ያለዉ ግን ባለማዕረግ ነዉ
ከሰማይ የመጣዉ ክርስቶስ ጌታዬ
ከሁሉ በላይ ነዉ።”
(ዮሐ 1፧19-28)
ምንጭ፦ mamushafenta.com
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
“አንተ ማን ነህ?” ቢሉት ማዕረጉን ፍለጋ
ሰባኪዉ ዝም ጭጭ መልስ የለም እርሱ ጋ
“በል ባክህ ንገረን
ደግሞ እንቸኩላለን
ለሚጠባበቁን ወሬ እናደርሳለን፤
እንዲህ የሆነ እንደሁ ዝናህም ይወጣል
አገር ጉድ እያለ በክብር ያጅብሃል።”
ጠብ የሚል ሲጠፋ የሚደረድረዉ
የማዕረግ አይነት የሚከናነበዉ
እንደነበር ሲቆም በአንክሮ እያያቸዉ
አማራጭን ሰጡት እንዲመርጥላቸዉ።
“ክርስቶስ ነህ ኤልያስ ወይስ ነቢዩ ነህ?
ምንስ ነዉ ማዕረግህ ማን ብለን እንጥራህ?
እባክህ ንገረን ክብር ደረጃህን
ስምና መለያ የሚመጥንህን”
ያን ጊዜ ከበደዉ መታገስ አቃተዉ
ማድመጥም አልቻለ እንኳን ሊደርበዉ
የሚጯጯሁትን ቀና ብሎ አየና
“ድምጽ ነኝ”! አላቸዉ እጅጉን ጮኸና
ያመጡትን ኮከብ የሚለጥፉትን
አራግፎ ከላዩ ሰዉ ሠራሽ ማዕረግን
እንዲህ ሲል ቀጠለ ሰባኪው ጩኸቱን፡-
“ድምጽ ነኝ፣ ድምጽ ነኝ ያዉም የበረሀ
መንገድ የሚያቀና እንዲያልፍበት ዉሀ
እንደልቡ እንዲሔድ ሕይወት ሰጭዉ ጅረት
ጥርጊያዉን አቅኝ ነኝ በሚሰጠኝ ምህረት
በሉ አትነዝንዙኝ ማንነቴ ይህ ነው
ሌላ ምንም የለኝ ስለራሴ እምለዉ
ኋላዬ ያለዉ ግን ባለማዕረግ ነዉ
ከሰማይ የመጣዉ ክርስቶስ ጌታዬ
ከሁሉ በላይ ነዉ።”
(ዮሐ 1፧19-28)
ምንጭ፦ mamushafenta.com
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
❤8👍2🥰1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ጊዜው መልካም ሲሆን፣ ደስ ይበልህ፤ ጊዜው ክፉ ሲሆን ግን ይህን አስብ፤ እግዚአብሔር አንዱን እንዳደረገ፣ ሌላውንም አድርጎአል፤ ስለዚህ ሰው ስለ ወደ ፊት ሁኔታው፣ ምንም ሊያውቅ አይችልም።”
መክብብ 7፥14 (አዲሱ መ.ት)

#መጻሕፍትን_እንመርምር
አማኝ ወይም የዳነ ሰው ድነቱን ሊያጣ ይችላል ወይስ አይችልም?
ክፍል-5
እምነትና ሥራ
አንዳንድ የሃይማኖት ክፍሎች መልካምን ሥራ በማድረግ ደኅንነትን ማግኘት ይቻላል ብለው ያስተምራሉ። የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ደግሞ ክርስቲያኖች መልካምን ሥራ ሲያደርጉ በማየት እነርሱም እንዲህ ያለውን መልካም ሥራ የሚያደርጉት ደኅንነትን ለማግኘት ሲሉ ነው ብለው ያስባሉ። ስለዚህ አያሌ ሰዎች በክርስትናና በሌሎች ሃይማኖቶች መካከል ምንም ልዩነት የለም በማለት ይናገራሉ።
ይሁንና እንዲህ የሚሉ ሰዎች ተሳስተዋል። በክርስትናና በሌሎች ሃይማኖቶች መካከል ያለው ልዩነት እጅግ ታላቅ ነው። ክርስቲያኖች መልካምን ሥራ የሚያደርጉት በቅድሚያ ደኅንነትን ካገኙ በኋላ ነው። መልካምን ሥራ የምናደርገው ደኅንነትን ለማግኘት ስንል አይደለም። መልካምን ሥራ የምናደርገው አስቀድሞ ስለዳንን ነው።
ከዚህም ላይ ቢሆን አንዳንድ ክርስቲያኖች ስህተትን ይፈጽማሉ። ደኅንነትን ካገኙ በኋላ ያገኙትን ደኅንነት ለማጽናት ሲሉ መልካምን ሥራ ማድረግ ያለባቸው ይመስላቸዋል። ሆኖም ሰዎች ደኅንነትን በመልካም ሥራቸው እንደማያገኙ ሁሉ ያገኙትንም ደኅንነት በመልካም ሥራቸው ማጽናት አይችሉም (ገላ. 3፥3)። ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ደኅንነት ያገኘነው በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ያገኘነውም ደኅንነት የሚጸናው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው።
እስከ አሁን ድረስ የተባለው ነገር ሁሉ ትክክል ቢሆንም፥ ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን መታዛዝና እርሱንም ደስ የሚያሰኝ ተግባር መፈጸም አለባቸው። በሕይወታችን ውስጥ መልካም ተግባር የማይታይ ከሆነ እምነታችን ሐሰት ነው ማለት ነው። እውነተኛ እምነት ባለበት ቦታ ሁሉ መልካምም ተግባር አለ (ያዕ. 2፥17)።
የዛፍን ምሳሌ የወሰድን እንደሆን በእምነትና በሥራ መካከል ያለውን ተዛምዶ በሚገባ ሊያስረዳን ይችላል። ፍሬ ለማፍራት (ይኸውም መልካም ተግባር ለማድረግ) በቅድሚያ ሕያዋን መሆን አለብን። የማያምኑና ደኅንነትንም ያልተቀበሉ ሰዎች ግን ሙታን ናቸው። እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መልካም ተግባር ለመፈጸም ኃይል የላቸውም። ሙት ዛፍ ፍሬ እንደማያፈራ ሁሉ በኃጢአትም ምክንያት ሙት የሆኑና ያልዳኑም ሰዎች ልክ እንዲሁ ናቸው። በእግዚአብሔር ሥራ ከመመካት ይልቅ አሁንም የሚታመኑት መልካም ሥራዬ ያድነኛል ብለው ነው (ሮሜ 4፥45)። በጎ ተግባራትን የምንፈጽመው ለራሳችን ጥቅም ሳይሆን ለሌሎች ጥቅምና ፍቅራችንንም ለእግዚአብሔር ለመግለጽ ስንል ነው (ዮሐ. 14፥21)።
በሌላ በኩል ደግሞ ፍሬ የሚያፈራ ሕያው ዛፍ ሁሉ ፍሬን ማፍራት አለበት። ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ ፍሬ የማያፈራ ከሆነ እንደ ሙት ዛፍ ወይም ሊሞት እንደተቃረበ ዛፍ መሆኑን እናውቃለን። እናምናለን እያልን መልካምን ተግባር የማናደርግ ከሆነ ሐሰተኞች ነን (ማቴ. 7፥21፤ 1ዮሐ. 2፥4)። እምነት እንዳለን የምናረጋግጠው በመልካም ተግባራችን ነው። ምክንያቱም እውነተኛ እምነት የሚገለጠው በመልካም ሥራ ነው።
እንግዲህ እንደ ሌሎች ሃይማኖቶች ከሆነ ሰዎች ሙት ዛፍ ናቸው፤ ሕይወትን ለመቀበል ተስፋ የሚያደርጉት ፍሬ በማፍራት ነው። እንደ ክርስትና ሃይማኖት ግን ፍሬ ማፍራት የምንችለው ሕይወትን ካገኘን በኋላ ነው።
ይህ የሚያሳየን እንግዲህ በእምነት «አማካይነት»፥ «በእምነት በኩል» ወይም «እምነታችንን በመጠቀም» ኃጢአትን መካድና እግዚአብሔርን መታዘዝ ያለብን መሆኑን ነው። እውነተኛ እምነት ያለን ከሆነ ባሕርያችንና አኗኗራችን ፍጹም ይቀየራል (ሮሜ 8፥13፤ 1ቆሮ. 6፥9–11፤ ገላ. 5፥19–26)። ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ እንዲህ ለማድረግ የሚያስችል ኀይል ስለሰጠን ነው። እግዚአብሔር አዲስ ሕይወት ሰጠን፤ አዲስ ኅሊና ሰጠን፤ አዲስም ተፈጥሮ ሰጠን፤ እንዲህም በመሆኑ እርሱን ደስ የሚያሰኝ ሕይወትን ለመኖር እንችላለን። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ሲል ያሳስባል፥ «ወዳጆች ሆይ! . . . እያንዳንዳችሁ ያላችሁን ደኅንነት ፍጹም ለማድረግ በፍርሃትና በአክብሮ ተግታችሁ ሥሩ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ፈቃደኛነትንና ታዛዥነትን ለእናንተ እየሰጠ ዓላማውን ከፍጻሜ ለማድረስ በእናንተ ውስጥ ይሠራል» (ፊል. 2፥12–13)።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 22-23

👍4🔥4❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤”
2ኛ ቆሮ 1፥8

❤4👍2👏1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ሮሜ 8፥9-11
ከዚህ በፊት ሮሜ 8፥5-8 ተመልክተናል። በዚያ ክፍል አዲሱ የሕይወት መንፈስ ሕግ በሕይወታችን በሙላት እንዲሰራ ምን ያስፈልጋል ብለን በዝርዝር አንዱን ርዕስ አይተን ነበር፤ ሌላውን ዛሬ እንጀምራለን። እርሱም መንፈስ ቅዱስ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ማሰላሰልም ሆነ በቃሉ ጸንተን ፍሬ ለማፍራት ያለ መንፈስ ቅዱስ የሚታሰብ አይደለም።
ጳውሎስ እዚህ ላይ (ሮሜ 8፥9-11) ክርስቲያኖችን በመንፈስ ቁጥጥር ሥር እንደሆኑ እንጂ በኃጢአተኛ ባሕሪ ቁጥጥር ሥር እንዳልሆኑ ያስታውሳቸዋል። በዚህ ጥቅስ ላይ (ቁ. 9) መንፈስ፥ የእግዚአብሔር መንፈስና፥ የክርስቶስ መንፈስ የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት እንዱን መንፈስ ነው፤ ያውም መንፈስ ቅዱስን ነው (1ቆሮ. 3፥16፤ 8፥19)።
በእግዚአብሔር አብ፥ በክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ስላለው ግኑኝነት ለመረዳት፤ የውሃን ምሳሌነት ብንጠቀም መልካም ነው። አብ የውሃው ምንጭ ማለትም የውሃው መፍለቂያ ነው እንበል፥ ክርስቶስ ደግሞ ውሃውን ወደ መሬት የሚያመጣው ቧንቧ ወይም ቦይ ነው እንበል፥ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ከአብ አንሥቶ በክርስቶስ ውስጥ ወደ እኛ የሚመነጨው ራሱ ውሃው ነው እንደ ማለት ነው። የክርስቶስ መንፈስ በውስጣችን ሲኖር ብቻ ነው የክርስቶስ ነን ለማለት የምንችለው በእርግጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ መጥቶ አማኞች ያልሆኑትን ሊጠራቸው ይችላል። ነገር ግን በውስጣቸው መኖሪያ ቦታ ሊያገኝ አይችልም። መንፈስ በሰው ውስጥ ሊገባና መኖሪያ ቦታ አግኝቶ ሊኖር የሚችለው፤ ሰው ልቡን ከፍቶ መንፈስ ቅዱስን ሲጋብዘው ብቻ ነው (ራእ. 3፥20)።
ነገር ግን ክርስቶስ (የክርስቶስ መንፈስ) በውስጣችሁ ቢኖር ሥጋችሁ፥ (አሮጌው ኃጢአተኛ ሥጋችሁ) የሞተ ነው፤ ከእንግዲህ ወዲህ አሮጌው ሥጋችሁ ጌታችሁ ሊሆን አይገባውም (ሮሜ 6፥6)።
የክርስቶስ መንፈስ በውስጣችሁ ቢኖር፥ ሥጋችሁ የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን ሕያው ነው ይህም አዲሱ መንፈሳዊ አካላችሁ ሕያው ነው ማለት ነው (ሮሜ 6፥11፤ ገላ. 2፥20)።
ሰውነታችን፥ ማለትም አሮጌው ሥጋችን በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፤ መንፈሳችን ግን በጽድቅ ምክንያት፥ ያውም በክርስቶስ ጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው።
ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው እግዚአብሔር አብ ነው። በውስጣችን በሚኖረው በመንፈሱ አማካይነት እግዚአብሔር ለሟች አካላችን ሕይወት፤ ይሄውም መንፈሳዊ ሕይወት ይሰጠናል። እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ለእኛ የሚሰጠን አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት ብቻ ሳይሆን፥ ልክ ክርስቶስን ከሞት እንዳስነሣው እኛንም በዓለም መጨረሻ ላይ ከሞት ያስነሣናል። ከእርሱም ጋር ለዘላለም እንድንኖር ያደርገናል። በዚህ ጥቅስ ላይ(ቁ.11) ሥጋችን ከሞት እንደሚነሣ ተስፋ ተሰጥቶናል (1ቆሮ. 15፥42-49፤ ፊል. 3፥20-21)።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 367

👍3❤1🔥1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
"ጨለማ በወረሰው አስፈሪ ሸለቆ ውስጥ እንኳ ባልፍ ፥ አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንክ አደጋ ይደርስብኛል ብዬ አልፈራም። በትርህ ስለሚመራኝ ፥ ምርኵዝህም ስለሚደግፈኝ እየተጽናናሁ እጓዛለሁ።"
መዝሙር 23፥4 (ሕያው ቃል)

👍4❤1🥰1👏1
Follow the ቅዱሳት መጻሕፍት channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaA94PKFsn0ejWkJe012
ቅዱሳት መጻሕፍትን በዋትስአፕ መከታተል ለሚፈልጉ
ቅዱሳት መጻሕፍትን በዋትስአፕ መከታተል ለሚፈልጉ
👍2❤1
ቅዱሳት መጻሕፍት pinned «Follow the ቅዱሳት መጻሕፍት channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaA94PKFsn0ejWkJe012 ቅዱሳት መጻሕፍትን በዋትስአፕ መከታተል ለሚፈልጉ»
📜መጽሐፍ ቅዱሳችን እንዴት ተፃፈ
ብሉይ ኪዳን
ብሉይ ኪዳን የተጻፈው በአንድ ሺ ዓመታት ዘመን ውስጥ ነው፤ ይህም በግምት ከ1400 እስከ 400 ከክርስቶስ ልደት በፊት መሆኑ ነው። የብሉይ ኪዳን የመጀመሪያዎቹ አምስት መጻሕፍት፥ አንዳንድ ጊዜ የሕግ መጻሕፍት ወይም የሙሴ ሕግ ተብለው የሚጠሩት አብዛኛዎቹ የተጻፉት በሙሴ ሲሆን እነርሱም የተጻፉት 1400 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነበር። የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው መጽሐፍ የተጻፈው በነቢዩ ሚልኪያስ ሲሆን እርሱም የተጻፈው በ400 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነበር።
የብሉይ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት በአይሁዳውያን ጸሐፊዎች በጥንቃቄ በእጅ በመገልበጥ፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፉ መጥተዋል። አንድ ጸሐፊ የቅዱሳት መጻሕፍትን አንድ አዲስ ግልባጭ በሚገለብጥበት ጊዜ አሮጌውን ግልባጭ ያጠፋዋል፤ ከዚህም የተነሣ ብዙ ዘመን የቆዩትን የብሉይ ኪዳን ግልባጮች በአሁኑ ዘመን ማግኘት አይቻልም። ዛሬ የሚገኘው ብዙ ዘመን የተቆጠረለት የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ በጣም በሩቅ ጊዜ የተገለበጠ ነው ቢባል ከክርስቶስ ልደት በኋላ በዐሥረኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተገለበጠ ነው (1000 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በኋላ ነው)።
ይሁን እንጂ በ1947 ዓ.ም. ብዙ ዘመን የቆዩ የቆዳ የጽሑፍ ጥቅልሎች በእስራኤል አገር በአንድ እረኛ ልጅ ተገኝተዋል። ልጁም ያገኛቸው ከኢያሪኮ ከተማ በስተደቡብ 8 ማይል ርቆ በሙት ባሕር አጠገብ በሚገኝ በአንድ ዋሻ ውስጥ ነው። ስለዚህም «የሙት ባሕር የጽሑፍ ጥቅልሎች» በመባል ይታወቃሉ። በጥቅልሎቹም ውስጥ ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አብዛኛዎቹ ይገኙባቸዋል። የሙት ባሕር የጽሑፍ ጥቅልሎች የተገለበጡት ከክርስቶስ ልደት በፊት በአንደኛውና በሁለተኛው መቶ ዓመት ውስጥ ነው። በጣም ጥቃቅን የሆኑ የሆሄያትና የአፃፃፍ ዘይቤ ልዩነት ከመያዛቸው በቀር ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ግልባጭ ከተገኘው ከአሁኑ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ግልባጭ ጋር ቀጥታ ተመሳሳይ ናቸው። ይህም የአይሁድ ጸሐፊዎች መጻህፍትን ይገለብጡ የነበረው በታላቅ ጥንቃቄና ፍጹምነት እንደነበረ ማስረጃ ነው። በመሆኑም በቅርብ ጊዜ የተገለበጡት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት (ዘመናዊ መጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደባቸው) በጥንት ጊዜ ብሉይ ኪዳንን ከጻፉት ሰዎች መጻህፍት ጋር ሙሉ በሙሉ ትክክል እንደሆኑ እርግጠኛ መሆን እንችላለን። ይህ በጣም አስፈላጊ ነው ብለን የምናምንበት ምክንያት ቀጥሎ እንደምንመለከተው፥ የመጀመሪያዎቹ ጸሐፊዎች በልዩ መንገድ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርተው፥ እግዚአብሔር እንዲጻፉ የፈለገውን ስለፃፈ ነው። ስለዚህ፥ የእነርሱ ጽሑፍ ቅጂ በታማኝነትና ያለምንም ስህተት በዓመታት መካከል ወደ እኛ ተላልፈዋል ብለን መተማመን እንችላለን።
አብዛኛዎቹ የብሉይ ኪዳን ጽሑፎች የተጻፉት የአይሁዳውያን የጥንት ቋንቋ በሆነው በዕብራይስጥ ቋንቋ ነበር። ይሁን እንጂ በክርስቶስ ዘመን ዕብራይስጥ ቋንቋ በተራው ሕዝብ የሚነገር አልነበረም፤ በዕብራይስጥ ቋንቋ የሚጠቀሙት የአይሁድ ካህናትና የሃይማኖት ጠበብት ነበሩ። በክርስቶስ ዘመን በመካከለኛው ምሥራቅ የተለመደ ቋንቋ አረማይክ ሲሆን፤ ክርስቶስም ይናገር የነበረው በዚህ ቋንቋ ነበር።
ይሁን እንጂ በክርስቶስ ዘመን የሚጠቀሙበት ሌላ ዋና ቋንቋ ነበር። እርሱም የግሪክ ቋንቋ ነው። ግሪክ በሜድትራኒያን ባሕር ዙሪያ የሚገኙ አገሮች ሁሉ የሚጠቀሙበት ቋንቋ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ብዙ የተማሩ ሰዎች የሚያውቁት ቋንቋ ነበር። ዕብራይስጥ የሚያውቁ ሰዎች ጥቂት ስለነበሩ፥ ብሉይ ኪዳን ከክርስቶስ ልደት በፊት 200 ዓመት በግሪክ ቋንቋ ተተረጎመ። የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ከብሉይ ኪዳን ሲጠቅሱ ብዙውን ጊዜ የሚጠቀሙት ከዚህ ከግሪክ ትርጉም እንጂ ጥንት በዕብራይስጥ ከተጻፈው አልነበረም።
ብሉይ ኪዳን የያዘው ሠላሳ ዘጠኝ መጻሕፍትን ሲሆን እነርሱም በብዙ ደራሲያን የተጻፉ ነበሩ።
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 89
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ዋትስአፕ፦ Follow the ቅዱሳት መጻሕፍት channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaA94PKFsn0ejWkJe012

👍4❤1👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።”
ቲቶ 3፥6-7
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
Follow the ቅዱሳት መጻሕፍት channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaA94PKFsn0ejWkJe012
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።”
ቲቶ 3፥6-7
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
Follow the ቅዱሳት መጻሕፍት channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaA94PKFsn0ejWkJe012
❤2👍1🔥1🥰1
ከሚከተሉት ውስጥ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ወይም ቤተክርስቲያንን እንዲጠነቀቁ ያዘዛቸው ትምህርት የቱ ነው?
Anonymous Quiz
54%
ሀ. የፈሪሳውያን እና የሰዱቃዊያን ትምህርት
1%
ለ. የበለዓም ትምህርት
5%
ሐ. የኒቆላውያን ትምህርት
3%
መ. የአርዮስ ትምህርት
35%
ሠ. ሀ፣ለ እና ሐ
👍3❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ልጆቹ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፥ የሚበሉትም አጥተው ሲቅበዘበዙ፥ ለቍራ መብልን የሚሰጠው ማን ነው?”
ኢዮብ 38፥41
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
Follow the ቅዱሳት መጻሕፍት channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaA94PKFsn0ejWkJe012
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ልጆቹ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፥ የሚበሉትም አጥተው ሲቅበዘበዙ፥ ለቍራ መብልን የሚሰጠው ማን ነው?”
ኢዮብ 38፥41
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
Follow the ቅዱሳት መጻሕፍት channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaA94PKFsn0ejWkJe012
👍4❤1🥰1👏1
#መጻሕፍትን_እንመርምር
አማኝ ወይም የዳነ ሰው ድነቱን ሊያጣ ይችላል ወይስ አይችልም?
ክፍል-6
ሰው በደኅንነት ጉዳይ ላይ ምርጫ ወይም ፈቃድ አለውን?
ክርስቲያኖች ለዚህ ጥያቄ የሚሰጡት መልስ በጣም የተለያየ ነው። አንዳንድ ክርስቲያኖች እንደሚሉት ሰዎችን የሚመርጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ሰው የኃጢአት ባርያ በመሆኑ የምርጫ ነፃነት የለውም። እግዚአብሔር የዓለምን ሰዎች በሙሉ ሳይሆን ጥቂቶችን ብቻ ነው የመረጠው፤ ሌሎቹን ግን ለጥፋት መድቧቸዋል በማለትም ይናገራሉ። እንዲህ የሚሉት ክርስቲያኖች ኢየሱስ፥ «የተጠሩ ብዙዎች ናቸው፤ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው» (ማቴ. 22፥14) በማለት የተናገረውን፥ እንዲሁም ጳውሎስ አንዳንድ ዕቃዎች ለጥፋት ሌሎች ደግሞ ለክብር እንደተዘጋጁ የሚናገርበትን ቦታ እንድንመለከት ይጠቁሙናል። በሮሜ 9፥22– 23 ላይ ጳውሎስ ሲጽፍ «እግዚአብሔር የሚፈልገውን ይምረዋል፤ የሚፈልገውንም እልኸኛ ያደርገዋል» ብሏል። በሌላ ቦታ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች ለዘለዓለም ሕይወት ‹‹እንደተመረጡ» (የሐዋ. 13፥48)፥ ሌሎች ደግሞ ለውድቀትና : ላለመታዘዝ እንደተመደቡ ተጽፎአል (1ጴጥ. 2፥8)። እንዲህ በማለት የሚናገሩት ክርስቲያኖች እግዚአብሔር የሚድኑትን ሰዎች ከመረጠ በኋላ ወደ ንስሀና (2ጢሞ. 2፥25) ወደ እምነትም የሚያደርስ ኀይል ሰጥቷቸዋል ብለው ያምናሉ (ፊል. 1፥29)። የተመረጡ ሰዎች በራሳቸው የምርጫ ነፃነት የሌላቸውና እግዚአብሔርንም «አይሆንም» ለማለት የማይችሉ ናቸው።
ሌሎች አያሌ ክርስቲያኖች ደግሞ በደኅንነት ጉዳይ ላይ የእግዚአብሔር ምርጫ ብቻ ሳይሆን የእኛም ድርሻ አለበት ይላሉ። በብሉይ ኪዳን የነበሩ የአይሁድ ሕዝቦች አንዳች መልካምነት ሳይኖራቸው በእግዚአብሔር የተመረጡ ቢሆኑም እግዚአብሔርን የመከተልና ያለመከተል ምርጫ ግን ተሰጥቷቸው ነበር (ዘዳ. 30፥19፤ ኢያ. 24፥15)። በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ሲናገር፥ «የላከኝን ፈቃድ ማድረግ የሚፈልግ ቢኖር» የእግዚአብሔርን ትምህርት ይቀበላል ብሏል (ዮሐ 7፥17)። ደኅንነትን ለማግኘት ኃጢአታችንን መናዘዝና (የሐዋ. 2፥38) በኢየሱስ ክርስቶስም ማመን (ሮሜ 10፥9–10) እንዳለብን ትእዛዝ ተሰጥቶናል። እንዲህ የሚሉት ክርስቲያኖች እግዚአብሔር በመጀመሪያ ጠርቶናል፤ ይሁንና የእግዚአብሔርን ጥሪና ደኅንነት መቃወም እንችላለን ይላሉ።
ከዚህ ከሁለተኛው ቡድን ውስጥ አንዳንድ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር አንድን የማያምንና የኃጢአት ባርያ የሆነን ሰው ነፃ ምርጫ ማድረግ እንዲችል ከኃጢአቱ ነፃ ያደርገዋል ብለው ይናገራሉ። ነፃ የወጣው ሰው እግዚአብሔርን የሚፈልግ ከሆነ ድኗል ማለት ነው። ሆኖም «ሰይጣንን» የመረጠ እንደሆን ግን ተመልሶ ወደ ኃጢአት ባርነት ውስጥ ይወድቃል፥ የተኮነነም ይሆናል። ሌሎች ደግሞ ሰዎች ሁሉ በኃጢአት በጽኑ የታሠሩ በመሆናቸው እግዚአብሔርን ከቶ ሊፈልጉ አይችሉም ይላሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር ለደኅንነት የሚያበቃ ምርጫ ሲያደርግ፤ ሰው ግን ለርግማን የሚያበቃውን ምርጫ ያደርጋል ብለው ይናገራሉ። በሌላ አነጋገር እግዚአብሔር አንድን ሰው እንዲድን ከመረጠውና ያም ሰው እግዚአብሔርን የማይቃወም ከሆነ ድኗል ማለት ነው። ነገር ግን ይህ ሰው እግዚአብሔርን የሚቃወም ከሆነ እግዚአብሔር በግድ መዳን አለብህ ብሎ አያስገድደውም። ሰውየው ግን በራሱ ምርጫ ፍርድን ይቀበላል።
በእርግጥ ግን እግዚአብሔርን በዚህ መንገድ መቃወም እንችላለን? በርካታ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው የሚለውን ነጥብ ያነሳሉ። እግዚአብሔርን የምንቃወም እኛ ማንነን? (ሮሜ 9፥19–21)። ይህም ሆኖ ግን ሌሎች አያሌ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር የምርጫ ነፃነት ሰጥቶናል በማለት ይናገራሉ። እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለመቃወም የሚናገሩ ክፍሎችን እንድናጤናቸው (ማቴ. 23፥37፤ የሐዋ. 7፥51፤ 13:46) እንዲሁም ሌሎች እግዚአብሔርን መቃወም እንደሌለብን የሚያስጠነቅቁ ክፍሎችን
እንድንመለከታቸው ይጋብዙናል (2ቆሮ. 6፥1፤ ዕብ. 3፥8፤ 13፤ 12፥25)።
እንግዲህ ይህ ሁሉ የሚያሳየን ክርስቲያኖች ለዚህ ጥያቄ ሦስት ዋና ዋና መልሶችን የሰጡ መሆኑን ነው፤
1) ሰው በደኅንነትም ሆነ በኩነኔ ጉዳይ ላይ ምንም ምርጫ የለውም፤
2) ሰው በሁለቱም ጉዳዩች ላይ ምርጫ አለው፤
3) ሰው ደኅንነትን መምረጥ አይችልም፤ ይሁንና እግዚአብሔር ከጠራው በኋላ ግን እግዚአብሔርን መቃወምና ኩነኔንም መምረጥ ይችላል።
በደኅንነት ጉዳይ ላይ ምርጫ እንዳለንና እንደሌለን የሚያወሱት እነዚህ ሦስት ዋና ዋና አመለካከቶች ከዚህ በሚከተለው ምሳሌ ሊብራሩ ይችላሉ። አሁን በመንገድ ዳር ስለታሠረ ስለ አንድ ልጅ እስቲ እናስብ። ይህ ልጅ በኃጢአት የታሠረን አንድን የማያምን ሰው ይወክላል። አንድ ሰው ደግሞ በበሬ የሚጎተት ጋሪ ይዞ መጣ። ይህ ደግሞ ሰዎችን ሁሉ ወደ ደኅንነት ሊያመጣ የሚፈልገውን እግዚአብሔርን ይወክላል። በበሬ የሚጎተተውን ጋሪ ይዞ የመጣው ሰው ሦስት አማራጮች አሉት፤
1) ልጁን እንደታሠረ በጋሪው ላይ ጭኖ ሊወስደው ይችላል። ይህም በደኅንነት ጉዳይ ላይ ምንም ምርጫ የለንም፤ እግዚአብሔርንም ደግሞ የመቃወም ኀይል የለንም የሚል አቋም ያላቸውን ሰዎች ይወክላል።
2) ሰውየው ልጁን ሊፈታውና መሄድ ይፈልግ ወይም አይፈልግ እንደሆነ ሊጠይቀው ይችላል። ልጁ መሄድ የሚፈልግ ከሆነ ሰውየው በጋሪው ላይ ሊጭነውና ሊወስደው ይችላል። ይህም እግዚአብሔር ደኅንነትን ወይም ኩነኔን መምረጥ እንድንችል በቅድሚያ ነፃ ያወጣናል የሚል አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ይወክላል።
3) ሰውየው ልጁን በጋሪው ላይ ከጫነው በኋላ ሊፈታው ይችላል። ልጁ ከፈለገ ከጋሪው ላይ ዘሎ ሊወርድ ይችላል። ልጁ ዘሎ ካልወረደ ግን ሰውየው ወደሚሄድበት ይወስደዋል። ይህም እግዚአብሔር መርጦናል ደግሞም ለደኅንነት የሚያስፈልገውን ሁሉ አድርጎልናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን መቃወምና የእርሱንም ሥራ አንፈልግም ማለት እንችላለን የሚል አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ይወክላል።
እስከ አሁን ድረስ የተባለውን ነገር ከዚህ እንደሚከተለው ማጠቃለል ይቻላል። እንደ መጀመሪያዎቹ ሰዎች አመለካከት፥ ለደኅንነትም ሆነ ለኩነኔ ሰዎችን የሚመርጥ እግዚአብሔር ነው። እንደ ሁለተኛዎቹ ሰዎች አመለካከት፥ ደኅንነትን ወይም ኩነኔን ለመምረጥ፥ ለሰዎች የምርጫ ነፃነትን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። እንደ ሦስተኛዎቹ ሰዎች አመለካከት በደኅንነት ጉዳይ ላይ ምርጫዎችን ሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው፤ ሆኖም ሰው እግዚአብሔርን ሊቃወምና ኩነኔን ሊመርጥ ይችላል።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 25-26

❤3👍3🔥1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“አይቼም ተነሣሁ፥ ታላላቆቹንና ሹማምቱንም የቀሩትንም ሕዝብ፦ አትፍሩአቸው ታላቁንና የተፈራውን ጌታ አስቡ፥ ስለ ወንድሞቻችሁም ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻችሁም ስለ ሚስቶቻችሁም ስለ ቤቶቻችሁም ተዋጉ አልኋቸው።”
ነህምያ 4፥14

❤2👍2🔥1
#እራሳችንን_እንመርምር
የምንበላውም ይሁን የምንጠጣው፣ እንዲሁም የምንለብሰው፣ የምንኖርበት ቤት፣ በሰላም ወጥተን መግባት፣ ሁሉ በጎ ነገራችን እግዚአብሔር በቸርነቱ እንዲሁ አድሎን እንደሆነ በሚገባ ተረድተን ይሆን? አንዳንድ ጊዜ ጎደለብን ብለን የምንተክዘው ጎደለን ያልናቸው ነገሮችን እንደ ሕጋዊ ባለቤት እና እንደመብቶቻችን የሙጥኝ ብለን የያዝናቸው አይመስላችሁም? ጌታ አንድን ነገር ቢነሳን ምን ማድረግ እንችላለን? በምክንያት እና በውጤት ቢጠላለፍም ባይጠላለፍም ሰጪው ማን ነው?
"የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤ አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ። አንተ እጅህን ትከፍታለህ፥ ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ። እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።"
መዝሙር 145፥15-17

👍4❤2👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
"ጽኑ፥ አይዞአችሁ ከእኛም ጋር ያለው ከእርሱ ጋር ካለው ይበልጣልና ከአሦር ንጉሥና ከእርሱ ጋር ካለው ጭፍራ ሁሉ አትፍሩ፥ አትደንግጡም። ከእርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳንና የሚዋጋልን አምላካችን እግዚአብሔር ነው ብሎ አጸናናቸው። ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ተጽናና።"
2 ዜና 32፥7-8

❤4👍2🥰1
የቀጠለ...
📜መጽሐፍ ቅዱሳችን እንዴት ተፃፈ
አዲስ ኪዳን
አዲስ ኪዳን የተጻፈው በግሪክ ቋንቋ ሲሆን መጻፍ የተጀመረውም ክርስቶስ ከሞተ ከሃያ ዓመት በኋላ ነበር። ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ የሰጣቸው የመጨረሻ ትእዛዝ፤ ለዓለም በሙሉ ምስክሮቹ እንዲሆኑ ስለነበር (የሐዋ. 1፥8)፤ ከጴንጠቆስጤ ቀን ጀምሮ ደቀመዛሙርቱ ስለ ክርስቶስ ሕይወትና ትምህርት ለሌሎች መንገር ጀመሩ። ክርስቶስ ከሞተ በኋላ ለመጀመሪያዎቹ ሃያ ዓመታት ደቀመዛሙርቱ ወይም ሐዋርያቱ በአፍ እየተናገሩ ቃሉን ያስተምሩ ነበር። ነገር ግን ሐዋርያቱ እያረጁ ሲሄዱ ትምህርታቸው አንዳች ሳይዛነፍ በጹሑፍ ለመጪው ትውልድ መተላለፉ አስፈላጊ ሆነ። ይህም ለወደፊት ዘመናት በትክክል መተላለፉን ለማረጋገጥ ይጠቅም ነበር፤ ስለዚህ ከሐዋርያት አንዳንዶቹና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው ስለ ክርስቶስ ሕይወት መጻፍ ጀመሩ። ሐዋርያው ጴጥሮስ የማርቆስን ወንጌል ለመጻፍ ከማርቆስ ጋር አብሮ ሠራ። ሐዋርያው ማቴዎስ የማቴዎስን ወንጌል ጻፈ። ሐዋርያው ዮሐንስ የዮሐንስን ወንጌል ጻፈ። የሐዋርያው ጳውሎስ የቅርብ ረዳት የነበረው ሉቃስ የሉቃስን ወንጌልና የቀድሞይቱ ቤተክርስቲያን ታሪክ የሆነውን የሐዋርያት ሥራን ጻፈ።
ስለ ክርስቶስ ሕይወት ከመጻፍ በተጨማሪ ሐዋርያቱ ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣበትን ምክንያት አስፋፍተው ለመጻፍ ግድ ሆነባቸው። እንዲሁም በአዳዲስ አብያተክርስቲያናት ዘንድ መብቀል የጀመሩትን አንዳንድ ስሕተቶችና ሐሰተኛ ትምህርቶች ለማረምም መጻፍ ነበረባቸው። ስለዚህ ለመሠረቱአቸው አዳዲስ አብያተክርስቲያናት መልእክት መጻፍ ጀመሩ። ሐዋርያው ጳውሎስ በ50 ዓ.ም. ገደማ ከተፃፈው የገላትያ መልዕክት አንስቶ በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት መልእክቶችን ጻፈ። አንዳንድ ሊቃውንት ከአዲስ ኪዳን መጻሕፍት መካከል በመጀመሪያ የተጻፈው የያዕቆብ ማለትም የኢየሱስ ወንድም መልእክት ነው ብለው ያምናሉ።
ከአዲስ ኪዳን መጻሕፍት መካከል በመጨረሻ የተጻፈው የራእይ መጽሐፍ ነው፤ ይህም መጽሐፍ የተጻፈው በሐዋርያው ዮሐንስ ሲሆን እርሱም የተጻፈው ከ90–95 ዓ.ም. ገደማ ነው። ስለዚህ መላው የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ተጽፈው ያበቁት ከ50 ዓ.ም. እስከ 100 ዓ.ም. መካከል ባለው ዘመን ነው። ከአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ከመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች አብዛኛዎቹ የተጻፉት ፓፒረስ ከሚባል ተክል ከተሠራ ወረቀት ነበር፤ ይህ ፓፒረስ እንደ ዘመኑ ወረቀት ነዋሪ አልነበረም፤ ስለሆነም ለብዙ ጊዜ አይቆይም ነበር። ከዚህም የተነሣ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች በፓፒረስ ጥቅል የጻፉአቸው ጹሑፎች በሙሉ ጠፍተዋል፤ ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን ጹሑፎች ሁሉ ዛሬ የሚገኙት የአዲስ ኪዳን ጹሑፎች የዋናው ቅጅ ማለትም ከፓፒረሱ የተቀዱ ናቸው።
ከክርስቶስ በኋላ ለመጀመሪያዎቹ ሦስት መቶ ዓመታት አዲስ ኪዳን ጹሑፎች በጥንቃቄና በትክክል በፓፒረስ ጥቅል በጸሐፊዎች አማካይነት የተገለበጡ ናቸው። 1900 ዓመት እንደገባ ወዲያውኑ፥ ከነዚህ ከፓፒረስ ግልባጮች ከነበሩት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ጥቂቶቹ በግብጽ አገር በአሸዋ ውስጥ ተቀብረው ተገኝተዋል። ሌሎቹ ደግሞ በመከላከያ መያዥያዎች በጥንቃቄ ተጣጥፈው ተገኝተዋል። ከነዚህም በጣም ያረጀው ግልባጭ በ135 ዓ.ም. የተሠራ ሲሆን ከዮሐንስ ወንጌል ጥቂቱን ክፍል የያዘ ነበር። በመቀጠል በጣም የቆዩት ጥቅሎች በ200 ዓ.ም. ላይ የተገለበጡና ከአዲስ ኪዳን አብዛኛውን ክፍል የያዙ ነበሩ፤ እነዚህ የጥንት ጥቅሎች በአሁኑ ጊዜ በሙዝየም ውስጥ ተጠብቀው ይገኛሉ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሰዎች ይጠቀሙበት የነበረ ሌላው የወረቀት ዐይነት፤ ብራና ከሚባል በተለየ ሁኔታ ለፍቶና ታሽቶ የተሠራ የፍየልና የበግ ቆዳ ነበር። ብራና ከፓፒረስ ይልቅ በጣም ውድ ሲሆን፤ ከአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ጥቂቶቹ በመጀመሪያ የተጻፉት ከብራና እንደነበረ ይገመታል። ይህ ከሆነ ደግሞ በደንብ ተጠብቀው አልተያዙም ማለት ነው። ሙሉው አዲስ ኪዳን በጣም ያረጀው ግልባጭ የተሠራው በአራተኛው መቶ ዓመት ላይ ነበር። የተጻፈውም በብራና ሲሆን ይህም ያረጀ ግልባጭ የተገኘው በ1800 ዓ.ም. መካከለኛ ላይ በግብጽ አገር በሚገኘው በሲና ተራራ በመነኩሳት ገዳም ውስጥ ነበር። ከዚህም ካረጀ ጥቅል ሌላ የግሪክ አዲስ ኪዳን ግልባጮች የሆኑ በብራና ላይ የተጻፉ ሌላ 270 ግልባጮች በአሁኑ ወቅት ይገኛሉ። የተፃፉትም በአራተኛና በዘጠነኛ መቶ ዓመታት መካከል ነበር።
ከዘጠነኛው መቶ ዓመት እስከ ዐሥራ አምስተኛው መቶ ዓመት በግሪክ ብዙ ቋንቋ አዲስ ኪዳን ግልባጮች ተሠርተዋል፤ ከእነርሱም ከ2700 በላይ የሚሆኑ ግልባጮች እስከ አሁኑ ዘመን ተጠብቀዋል። ከዚያም በኋላ በ1456 ዓ.ም. ጆሐን ጎትንበርግ በተባለ በአንድ ጀርመናዊ አንድ ማተሚያ ተስራ፣ የመጀመሪያው የታተመ መጽሐፍ በመሆን መጽሐፍ ቅዱስ ታተመ። ከዚያ ጊዜ በኋላ መጻሕፍት በእጅ መገልበጣቸው አበቃ፤ በማተሚያ ቤቶች አማካይነት በፍጥነትና በቀላል ዋጋ ሊታተሙ ቻሉ። የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በብዙ ቋንቋዎች ይደረግ ስለነበር፥ አሁን መጽሐፍ ቅዱስ በማንኛውም ተራ ሰው እጅ ሊገኝ ቻለ። በዛሬ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከዓለም ቋንቋዎች 1200 በሚያህሉት ተተርጉሞአል፤ በዓለም ታሪክ ውስጥ ይህን በሚያህል ቋንቋዎች የተተረጎመ ወይም ይህን በሚያህል ሕዝብ የተነበበ ሌላ መጽሐፍ ጨርሶ አይገኝም።
እነዚህ በመቶና በሺ የሚቆጠሩ ጥንታውያን ጽሑፎች እስከ አሁን ጊዜ ድረስ ተጠብቀው መቆየታቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ ከመጀመሪያው የግሪክ ጹሑፎች በትክክል ተገልብጦ ወደ እኛ ለመድረሱ ማረጋገጫ ነው። ምንም እንኳ አንዳንድ ጸሐፊዎች ሲገለብጡ አልፎ አልፎ ስሕተት ማድረጋቸው የሚታወቅ ቢሆንም ብዙዎቹ ጹሑፎች በአንድነት በሚጠኑበት ጊዜ የመጀመሪያዎቹ ጸሐፊዎች በእያንዳንዱ ሁኔታ ምን ለማለት እንደፈለጉ መወሰን ይቻላል። ይህን ያህል የጥንት ግልባጭ ያለው ሌላ የጥንት መጽሐፍ በጭራሽ አይገኝም። የዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች እግዚአብሔር አስቀድሞ ለመጀመሪያዎቹ ፀሐፊዎች የሰጣቸው ቃል ነው ብለን የምንታመነውም ስለዚህ ነው።
ዛሬ የሚገኙ መጽሐፍ ቅዱሶች ትክክለኛ መሆናቸውን የምናረጋግጥበት ሌላም በጣም ጠቃሚ የሆነ ምክንያት አለ። ይኸውም እግዚአብሔር ቃሉን ጠብቆ ለትውልዶች ሁሉ አንዲተላለፍ የሰጠው ተስፋ ነው (መዝ. 119፥89፤152፤160)። እግዚአብሔር ቃሉ እንዳይጠፋና መሠረታዊ ለውጥ እንዳይደረግበት በማድረጉ በጣም ልንተማመን እንችላለን።
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 90-91

❤3👍3👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።”
1ኛ ጴጥሮስ 3፥9

❤4👏2👍1🥰1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
መዝሙር 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?
² በቅንነት የሚሄድ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ፥ በልቡም እውነትን የሚናገር።
³ በአንደበቱ የማይሸነግል፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥ ዘመዶቹንም የማይሰድብ።
⁴ ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም።
⁵ ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘላለም አይታወክም።