ቅዱሳት መጻሕፍት
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት ሮሜ 8፥5-8 ፭. ኃጢአትን ሰውሮ በኃጢአት መመላለስ ወይም መጽናት በአማኝ ሕይወት ውስጥ አዲሱ የሕይወት መንፈስ ሕግ በስፋት ጎልብቶ ፍሬ እንዳያፈራ እንቅፋት ከሚሆነው ነገር ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው በኃጢአት መጽናት፤ ከጥፋት ላለመመለስ ደግሞ ኃጢአትን እየሰወሩ መኖር ነው። ኃጢአት ሁልጊዜ በደጃችን ታደባለች ታዲያ በመንፈሳዊ ሕይወት ለምልመን ለመኖር ከወሰንን ኃጢአትን…
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ሮሜ 8፥5-8
ከዚህ በፊት ዳግመኛ በተወለደ የአማኝ ሕይወት ውስጥ አዲሱ የሕይወት መንፈስ ሕግ በስፋት ፍሬ እንዳያፈራ እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን አይተናል። ዛሬ ደግሞ መፍትሄውን እንመለከታለን።
🔑መፍትሄ፦ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ ማስተዋል።
“በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።”
ማቴዎስ 13፥23
በመንፈሳዊ ሕይወታችን ፍሬያማ እና ውጤታማ እንዲሆን ከፈለግን የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ብቻ ሳይሆን ማስተዋልም ይጠበቅብናል። ማስተዋል የመንፈሳዊ ሰው ትልቁ ሃብቱ እና መለያው ነው። አንድ ሰው ማስተዋል እንዳለው የምናውቀው የእግዚአብሔርን ቃል በተግባር ሲያውለው ነው። ማስረጃ፦
“እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፤ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።”
መዝሙር 111፥10 (አዲሱ መ.ት)
“ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ።”
መዝሙር 119፥104
“ብቻ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ሕግ ትጠብቅ ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን ይስጥህ፥ በእስራኤልም ላይ ያሠልጥንህ።”
1 ዜና 22፥12
“ሰውንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ነው አለው።”
ኢዮብ 28፥28
“ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ።”
ያዕቆብ 3፥13
✍ማስተዋል እንዴት ይገኛል?
👉ከእግዚአብሔር ዘንድ በመጸለይ
“አቤቱ፥ ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትቅረብ፤ እንደ ቃልህም አስተዋይ አድርገኝ።”
መዝሙር 119፥169
👉 በመስማት እና በማድመጥ
“እናንተ ልጆች፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤”
ምሳሌ 4፥1
“ሕዝቡንም ጠርቶ፦ ስሙ አስተውሉም፤”
ማቴዎስ 15፥10
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot

👍3🔥2❤1🥰1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ዳዊትም በአካሄዱ ሁሉ አስተውሎ ያደርግ ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።”
1ኛ ሳሙኤል 18፥14

👍2❤1🥰1👏1
#መጻሕፍትን_እንመርምር
አማኝ ወይም የዳነ ሰው ድነቱን ሊያጣ ይችላል ወይስ አይችልም?
ክፍል-4
የሰው ምላሽ
ሰዎች ራሳቸውን ማዳን ከቶ አይችሉም። ሰዎች መዳን የሚችሉት በእግዚአብሔር ምሕረትና ጸጋ ብቻ ነው። እንዲህ ሲባል ግን ሰዎች በደኅንነት ሥራ ውስጥ ምንም ድርሻ የላቸውም ማለት አይደለም። ምንም እንኳን ኢየሱስ የዓለምን ሁሉ ኃጢአት በመስቀል ላይ ቢያስወግድም (ዮሐ. 1፥29) ሁሉ ሰው ግን አልዳነም። እግዚአብሔር የሰጠንን ደኅንነት ለመቀበል አንድ ነገር ብቻ ያስፈልጋል በኢየሱስ ማመን (ዮሐ. 3፥16–18፤ የሐዋ. 16፥31)።
በኢየሱስ ማመን ማለት ኢየሱስ መሲሕ ወይም ክርስቶስ እንደሆነና የእግዚአብሔርም ልጅ እንደሆነ ማመን ማለት ብቻ አይደለም (ዮሐ. 8፥24)፤ ወደ ሕይወታችንና ወደ ልባችንም መቀበልና (ማቴ. 10፥40፤ ዮሐ. 1፥12፤ ራእ. 3፥20) በእርሱም ሙሉ በሙሉ መታመን ማለትም ነው (2ጢሞ. 1፥12)። እምነት ማለት ኢየሱስን ማወቅ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ለእርሱ ከልባችን መሰጠት ማለት ነው። እውነተኛ እምነት ያለን ከሆነ፥ ኃጢአታችንን እንናዘዛለን (1ዮሐ. 1፥9)፥ ከኃጢአታችንም ተመልሰን ንስሓ እንገባለን (ሉቃ. 13፥3፤ 5፤ የሐዋ. 2፥38)። በእርግጥ እውነተኛ እምነት ካለን፥ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በሰዎች ፊት በግልጽ እንመሰክራለን እንጂ ክርስቲያን መሆናችንን አንሸሽግም (ማቴ. 10፥32 33፤ ሮሜ 10፥9–10)። እንዲሁም ኢየሱስ ተጠመቁ ሲል የሰጠውን ትዕዛዝ እንፈጽማለን (ማቴ. 28፥19 20፣ ማር. 16፥15–16፤ የሐዋ. 2፥38)።
ምንም እንኳን ደኅንነት እግዚአብሔር በክርስቶስ ሞት አማካይነት በመስቀል ላይ የፈጸመልን ሥራ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ብቻ በሠራው ደኅንነት ማመንና መደገፍ አለብን። ደኅንነት ከእኛ አልተገኘም። የደኅንነት መገኛና ምንጭ እግዚአብሔር ነው። ከጸጋው የተነሣ እንዲያው በነፃ ሰጠን። ደኅንነትን በራሳችን ኃይልና ጥረት ወይም ደግሞ በመልካም ሥራችን ማግኘት አንችልም (ሮሜ 9፥16)። እምነት በእግዚአብሔርና በሰጠንም ጸጋ መታመን ማለት ነው (ሮሜ 4፥5)።
ይህም በመሆኑ ነው ጳውሎስ ደኅንነትና ከእርሱም ጋር የምናገኘው በረከት ሁሉ በእምነት አማካይነት በጸጋው የምናገኘው ነገር መሆኑን የተናገረው (ኤፌ. 2፥8)። በሌላ ቦታ ደግሞ «በእምነት አማካይነት በጸጋው» የሚለውን «በእምነት» በማለት አሳጥሮ ጽፎአል። በእምነት ወይም በእምነት አማካይነት ጻድቃን (ሮሜ 3፥27–28፤ ገላ. 2፥15–16) ወይም ቅዱሳን ሆነናል (የሐዋ. 16፥18፤ ገላ. 3፥1–5)። በእምነትም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሆነናል (ዮሐ. 1፥12–13)። ሆኖም እምነት ራሱ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። በእኛ ዘንድ የምንመካበት አንዳች ነገር የለም (የሐዋ. 3፥16፤ ኤፌ. 2፥9፤ ፊል. 1፥29፤ 2ጢሞ. 2፥25)። የእምነታችን አመንጪና ጀማሪ ኢየሱስ ራሱ ነው። እንዲሁም እርሱ የእምነታችን ፈጻሚም ነው (ዕብ. 12፥2)።
መስኮት የሚሰጠውን አገልግሎት ለአብነት ያህል የወሰድን እንደሆን በጸጋና በእምነት መካከል ያለውን ተዛምዶ ሊያስረዳን ይችላል። የፀሐይን ብርሃን የምናገኘው በመስኮት በኩል ነው። ሆኖም መስኮት ስላለን ብቻ የፀሐይን ብርሃን አናገኝም። ጸጋ ልክ እንደ ፀሐይ ብርሃን ነው፤ እምነት ደግሞ እንደ መስኮት ነው። የእግዚአብሔርን ጸጋ የምናገኘው በእምነት አማካይነት ነው። ነገር ግን እምነት ስላለን ብቻ የእግዚአብሔርን ጸጋ አናገኝም። የእግዚአብሔር ጸጋ ወደ ሕይወታችን ገብቶ እንዳይለውጠን ጸጋውን ባለማመን ልናዳፍነው እንችላለን። ደኅንነትን ለማግኘት እግዚአብሔርን መታመን አስፈላጊ ነገር ቢሆንም እምነት በራሱ የደኅንነት ምንጭ ሊሆን አይችልም።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 21-22

❤1👍1👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
"ልባሞች ስለምትሆኑ በደስታ ሞኞችን ትታገሣላችሁና፤ ማንም ባሪያዎች ቢያደርጋችሁ፥ ማንም ቢበላችሁ፥ ማንም ቢቀማችሁ፥ ማንም ቢኮራባችሁ፥ ማንም ፊታችሁን በጥፊ ቢመታችሁ ትታገሣላችሁና።"
2ኛ ቆሮ 11፥19-20

❤3👍3🔥1👏1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም።
¹⁰ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው።
¹¹ ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።
ሮሜ 8 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ እናንተ ግን፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ የሚኖር ከሆነ፣ በሥጋ ሳይሆን በመንፈስ ናችሁ። ማንም የክርስቶስ መንፈስ ከሌለው፣ እርሱ የክርስቶስ አይደለም።
¹⁰ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጣችሁ ካለ፣ ሰውነታችሁ ከኀጢአት የተነሣ የሞተ ቢሆንም፣ መንፈሳችሁ ከጽድቅ የተነሣ ሕያው ነው።
¹¹ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ የሚኖር ከሆነ፣ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው፣ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈሱ ሟች ለሆነው ሰውነታችሁ ሕይወትን ይሰጣል።
ሮሜ 8 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ እናንተ ግን እንደዚህ አይደላችሁም። የእግዚአብሔር መንፈስ ያደረባችሁ ስለሆነ ለሥጋዊ ፈቃድ አትገዙም። የክርስቶስ መንፈስ የማያድርበት ሰው የክርስቶስ ወገን ሊሆን አይችልም።
¹⁰ ሥጋችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ቢሆንም ፥ ክርስቶስ በውስጣችሁ ካደረ መንፈሳችሁ ከጽድቅ የተነሣ ሕያው ይሆናል።
¹¹ ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረባችሁ ፥ ይኸው መንፈሱ የሚሞተው ሥጋችሁን ሕይወት ያለው ያደርገዋል።
Romans 8 (The Message)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ But if God himself has taken up residence in your life, you can hardly be thinking more of yourself than of him. Anyone, of course, who has not welcomed this invisible but clearly present God, the Spirit of Christ, won't know what we're talking about.
¹⁰ But for you who welcome him, in whom he dwells - even though you still experience all the limitations of sin - you yourself experience life on God's terms.
¹¹ It stands to reason, doesn't it, that if the alive-and-present God who raised Jesus from the dead moves into your life, he'll do the same thing in you that he did in Jesus, bringing you alive to himself? When God lives and breathes in you (and he does, as surely as he did in Jesus), you are delivered from that dead life. With his Spirit living in you, your body will be as alive as Christ's!

👍3❤2🥰2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እርሱም፦ በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ነው ሕዝቡን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር ትገዛላችሁ አለ።”
ዘጸአት 3፥12

❤3👍2🔥1🥰1
በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ያሉ ሰባቱ ምልክቶች
ማርቆስ ኢየሱስ የፈጸማቸውን ተአምራት የኃይል መግለጫዎች ወይም ተአምራት ብሎ ሲጠራ፣ ዮሐንስ ግን «ምልክቶች» ማለትን መርጧል። ምልክት ወደ ሌላ ነገር የሚያመላክት ክስተት ነው። ኢየሱስ የፈጸማቸው ተአምራት ሁሉ መለኮታዊነቱንና መሢሕነቱን የሚያሳዩ ነበሩ።
ሰባቱ ምልክቶች:-
👉ውኃን ወደ ወይን መለወጥ (ዮሐ 2፡1-11)።
👉የሹሙን ልጅ መፈወስ (ዮሐ 4፡46-54)፡፡
👉በቤተ ሳይዳ መጠመቂያ፥ ለሠላሳ ስምንት ዓመት ታሞ የኖረ ሰው መፈወስ (ዮሐ 5፡1-15)፡፡
👉አምስት ሺህ ሰዎችን መመገብ (ዮሐ 6፡1-15)፡፡
👉በውኃ ላይ መራመድ (ዮሐ 6፡16-21)፡፡
👉ዐይነ ስውሩን መፈወስ (ዮሐ 9፡1-7)፡፡
👉አልዓዛርን ከሞት ማስነሣት (ዮሐ 11፡17-44)፡፡

❤2👍2🥰1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።”
ዮሐንስ 5፥21

❤6🔥1🥰1
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#ሎዶቅያ
በሎዶቅያ ያለችው ቤተ ክርስቲያን የተቋቋመችው ጳውሎስ በኤፌሶን በሚኖርበት ጊዜ ነው (የሐዋ. 19፥10)። ኤፓፍራ የሚባል የሎዶቅያ ስው ወንጌልን በኤፌሶን ከነበረው ከጳውሎስ ከሰማ በኋላ ከዚያ ተመልሶ በሎዶቅያ ቤተክርስቲያንን እንዳቋቋመ የሚያምኑ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት አሉ (ቆላ. 4፥12)። ጳውሎስ በሎዶቅያ ለምትገኘው ቤተክርስቲያን ደብዳቤ ጻፈ፤ ነገር ግን ያ ደብዳቤ ጠፍቶአል (ቆላ. 4፥15)።
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 20-21፣ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 637፣ https://wowcappadocia.com/laodicea-ancient-city.html#:~:text=Laodicea%20came%20under%20Pergamum's%20rule,fabrics%2C%20sandals%2C%20and%20medicine.
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
#ሎዶቅያ
ሎዶቅያ በሊከስ ወንዝ ሸለቆ ውስጥ ከሚገኙት ከሦስቱ ጥንታዊ ሰፈሮች አንዷ ነበረች። ከቆላስይስ በምስራቅ 9 ማይል እና በሰሜን በኩል ደግሞ ከሄራፖሊስ 6 ማይል ርቀት ላይ ትገኛለች። የሎዶቅያ ከተማ በአንድ ወቅት ከሊከስ ዳርቻ አንድ ማይል ርቆ በሚገኘው ከሸለቆው ወለል 100 ጫማ ርቀት ላይ በሚገኝ ስኩዌር አካባቢ ላይ ቆሞ ነበር።
በመጀመሪያ በ286-246 ከክርስቶስ ልደት በፊት ዲዮስፖሊስ እና ሮአስ ትባል ነበር። ከተማይቱ በሦርያ ገዥ አንቲዮከስ 2ኛ ቴዎስ (የሶርያ ገዢ) ለሚስቱ ለሎዶቅ ክብር ሎዶቅያ ተባለ።
ሎዶቅያ በጴርጋሞን አገዛዝ ሥር በ190 ከክርስቶስ ልደት በፊት እና በኋላ በ133 ከክርስቶስ ልደት በፊት በሮም ቁጥጥር ሥር ወደቀች። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት መገባደጃ ላይ ሎዶቅያ በትንሿ እስያ ከሚገኙት ዋና ዋና ከተሞች አንዷ ሆና ነበር። በጨርቃ ጨርቅ፣ በጫማ እና በመድኃኒት ዝነኛ ነበረች።
በተጨማሪም ሲሴሮ እንኳን ወደ ትውልድ አገሩ ወደ ኪሊሺያ የሚወስደውን ረቂቅ ገንዘብ የሚያወጣበት ዋና የባንክ ማእከል ነበር። በ1ኛው ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ፣ ሎዶቅያ የግሪክኛ ተናጋሪ ሶርያውያን፣ ግሪኮች፣ ሮማውያን እና ሮማናዊ ተወላጆች እንዲሁም የአይሁድ ቀኝ ተገዢዎች ነበሩባት። እነዚህ አይሁዶች በኢየሩሳሌም ላለው ቤተመቅደስ የወርቅ መዋጮ አዘውትረው ይልኩ ነበር፣ እና በ62 ከክርስቶስ ልደት በፊት ሮማዊው ገዥ ፍላከስ 20 ፓውንድ ወርቅ ወሰደባቸው። ዛሬ ሎዶቅያ በቱርክ ውስጥ ከኤፌሶን ቀጥላ ሁለተኛዋ ትልቅ ጥንታዊ ከተማ ነች። በሊከስ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን ሌሎች ከተሞች ባጠፋው የመሬት መንቀጥቀጥ ብትተርፍም፣ ከተማዋ በመጨረሻም ወድቃለች። በቱርክ ውስጥ የምትገኝ ጥንታዊቷ ሎዶቅያ በርካታ ታሪካዊና አርኪኦሎጂያዊ ቦታዎች አሏት። ከእነዚህ ቦታዎች አንዱ በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክርስቲያን ምዕመናንን ይስብ የነበረው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅሪት ነው። የቤተክርስቲያኑ መድረክ እና የመቅደስ ክፍሎች ዛሬም ይታያሉ። ሌላው ትኩረትን የሚስበው የዚውስ ቤተመቅደስ ሲሆን ቁፋሮው ለብዙ አመታት ሲካሄድ ቆይቷል። አርኪኦሎጂስቶች 11 ሜትር ከፍታ ያላቸው እና እያንዳንዳቸው 15 ቶን የሚመዝኑ ግዙፍ የአዕማድ ጋለሪዎችን አግኝተዋል።
በዚች ከተማ ለልብስ የሚሆን ጥቁር ሱፍ በብዛት ይገኝ ነበር። ዝነኛ የሆነ የዓይን መድኃኒትም በሎዶቅያ ይሠራ ነበር። ከከተማይቱ ራቅ ብሎ ከሚገኘው ጠበል ተነሥቶ በድንጋይ ቧምቧ ስለሚመጣ የከተማይቱ ውኃ ከከተማይቱ ሲደርስ ለብያለ ነበረ። ዮሐንስ ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን መልእክት ሲጽፍ እነዚህን ነገሮች ምሳሌ አድርጎ በመጥቀስ መንፈሳዊ ትምህርት ይሰጣል።
በቅርቡ የታሪክ ምሁራን በሎዶቅያ የ1600 ዓመት ዕድሜ ያለው የጨርቃጨርቅ ንጣፍ በማግኘታቸው የክልሉን የሽመና ባህል ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት እንደነበረ ያሳያል።
በመጽሐፍ ቅዱስ የራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ከተጠቀሱት ሰባት አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ሎዶቅያ ለክርስትናም ትልቅ ቦታ ነች። ከ 4 ኛው መቶ ዓመት ጀምሮ ከተማዋ ለክርስቲያኖች የተቀደሰ የአምልኮ ማዕከል ሆና ቆይታለች።በሎዶቅያ ያለችው ቤተ ክርስቲያን የተቋቋመችው ጳውሎስ በኤፌሶን በሚኖርበት ጊዜ ነው (የሐዋ. 19፥10)። ኤፓፍራ የሚባል የሎዶቅያ ስው ወንጌልን በኤፌሶን ከነበረው ከጳውሎስ ከሰማ በኋላ ከዚያ ተመልሶ በሎዶቅያ ቤተክርስቲያንን እንዳቋቋመ የሚያምኑ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት አሉ (ቆላ. 4፥12)። ጳውሎስ በሎዶቅያ ለምትገኘው ቤተክርስቲያን ደብዳቤ ጻፈ፤ ነገር ግን ያ ደብዳቤ ጠፍቶአል (ቆላ. 4፥15)።
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 20-21፣ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 637፣ https://wowcappadocia.com/laodicea-ancient-city.html#:~:text=Laodicea%20came%20under%20Pergamum's%20rule,fabrics%2C%20sandals%2C%20and%20medicine.
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
Wowcappadocia
Denizli - Laodicea Ancient City
Laodicea was one of three ancient settlements in the valley of the Lycus River, a tributary of the Meander. Colossae is 9 miles to the east, and Hierapolis is 6 miles north.
❤2👍2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በሚስያም አንጻር በደረሱ ጊዜ ወደ ቢታንያ ይሄዱ ዘድን ሞከሩ፥ የኢየሱስ መንፈስም አልፈቀደላቸውም፤”
ሐዋርያት 16፥7
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በሚስያም አንጻር በደረሱ ጊዜ ወደ ቢታንያ ይሄዱ ዘድን ሞከሩ፥ የኢየሱስ መንፈስም አልፈቀደላቸውም፤”
ሐዋርያት 16፥7
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
❤3👍1👏1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
1ኛ ቆሮንቶስ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እኔ ነጻ አይደለሁምን? ሐዋርያስ አይደለሁምን? ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስንስ አላየሁትምን? እናንተስ በጌታ ሥራዬ አይደላችሁምን?
² የሐዋርያነቴ ማኅተም በጌታ እናንተ ናችሁና ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን ለእናንተስ ምንም ቢሆን ሐዋርያ ነኝ።
³-⁴ ለሚመረምሩኝ መልሴ ይህ ነው። ልንበላና ልንጠጣ መብት የለንምን?
⁵ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንደ ኬፋም፥ እኅት ሚስታችንን ይዘን ልንዞር መብት የለንምን?
⁶ ወይስ ሥራን ለመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?
⁷ ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይስ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የማይጠጣ ማን ነው?
⁸ ይህን በሰው ሥልጣን ብቻ እላለሁን?
⁹ ሕግስ ደግሞ ያን አይልምን? የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር ተብሎ በሙሴ ሕግ ተጽፎአልና። እግዚአብሔርስ ስለ በሬዎች ይገደዋልን?
¹⁰ ይህን የሚለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይደለምን? የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ የሚያበራይም እንዲካፈል በተስፋ ሊያበራይ ስለሚገባው በእውነት ስለ እኛ ተጽፎአል።
¹¹ እኛ መንፈሳዊን ነገር የዘራንላችሁ ከሆንን የእናንተን የሥጋዊን ነገር እኛ ብናጭድ ትልቅ ነገር ነውን?
¹² ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን መብት የሚካፈሉ ከሆኑ እኛማ ይልቁን እንዴታ? ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ በዚህ መብት አልተጠቀምንም።
¹³ በመቅደስ ነገር የሚያገለግሉ ከመቅደስ የሆነውን ነገርን እንዲመገቡ፥ በመሠዊያውም የሚጸኑ ከመሠዊያው እንዲካፈሉ አታውቁምን?
¹⁴ እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል።
¹⁵ እኔ ግን ከእነዚህ ሁሉ ምንም አልተጠቀምሁም። እንዲህ እንዲሆንልኝ ይህን አልጽፍም፤ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና።
¹⁶ ወንጌልን ብሰብክ እንኳ የምመካበት የለኝም፤ ግድ ደርሶብኝ ነውና፤ ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ።
¹⁷ ይህን በፈቃዴ ባደርገው ደመወዝ አለኝና፤ ያለ ፈቃዴ ግን ባደርገው መጋቢነት በአደራ ተሰጥቶኛል።
¹⁸ እንግዲህ ደመወዜ ምንድር ነው? ወንጌልን እየሰበክሁ በወንጌል ካለኝ መብት በሙሉ እንዳልጠቀም ወንጌልን ያለ ዋጋ ብናገር ነው።
¹⁹ ከሰው ሁሉ አርነት የወጣሁ ስሆን የሚበልጡትን እንድጠቅም እንደ ባሪያ ራሴን ለሁሉ አስገዛለሁ።
²⁰ አይሁድንም እጠቅም ዘንድ ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ፤ ከሕግ በታች ያሉትን እጠቅም ዘንድ፥ እኔ ራሴ ከሕግ በታች ሳልሆን፥ ከሕግ በታች ላሉት ከሕግ በታች እንዳለሁ ሆንሁ፤
²¹ ሕግ የሌላቸውን እጠቅም ዘንድ፥ ያለ እግዚአብሔር ሕግ ሳልኖር ነገር ግን በክርስቶስ ሕግ በታች ሳለሁ፥ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደ ሌለኝ ሆንሁ፤
²² ደካሞችን እጠቅም ዘንድ ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንሁ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ።
²³ በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።
²⁴ በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ።
²⁵ የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።
²⁶ ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤
²⁷ ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ።

👍4❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ወንድሞች ሆይ፤ የሰበክሁላችሁ ወንጌል ሰው ሠራሽ አለመሆኑን እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤”
ገላትያ 1፥11 (አዲሱ መ.ት)

❤1👍1
#እራሳችንን_እንመርምር
ስለወንጌል ሁሉን እናደርጋለን ወይስ ለጥቅማችን ስንል ሁሉን እናደርጋለን? ኧረ እንዲህማ አይሆንም ይሄማ ከባድ ተቃርኖ ነው። የሚል አይጠፋም እስቲ አሳቡን ጠበብ እናድርገው። ስለወንጌል ሁሉን እናደርጋለን ወይስ ወንጌል እየሰበክን ስለወንጌል ጥቅማችንን መተው ይከብደናል? ወንጌልን ለምንድነው የምንሰብከው? ባንሰብክስ? ወንጌልን ለመስበክ ምን ያህል ርቀት እንጓዛለን? ወንጌልን ስንሰብክ በአእምሯችን ምን እናገኛለን ብለን ነው? ወንጌልን መስበክ ግዴታ ወይስ መብት?
"እንደዚሁም የወንጌልን ቃል የሚያስተምሩ መምህራንም ፥ ለኑሮአቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ከምዕመናን እንዲቀበሉ ጌታ ፈቅዶላቸዋል። እኔ በበኩሌ ግን በዚህ መብቴ አልተጠቀምኩበትም። አሁንም ይህን መጻፌ በዚሁ መብት ለመጠቀም ፍላጐት ኖሮኝ አይደለም። ወንጌልን ያለምንም ዋጋ ስለሰበክሁላችሁ ያገኘሁት ደስታ ይህ ነው አይባልም። ስለዚህ ይህን ከማጣ በረሃብ ብሞት ይሻለኛል። ወንጌልን በመስበኬም ልመካበት አልችልም። ልመካበት የማልችለውም የምሰብከው ጌታ ኢየሱስ ስላዘዘኝ በመሆኑ ነው። ጌታ እንዳዘዘኝ የወንጌሉን ቃል ሳልሰብክ ብቀር ግን ወዮልኝ። ይህን ወንጌል በፍቃደኝነትና በውዴታ ብሰብክ ለድካሜ ዋጋ አለኝ። ነገር ግን ያለፈቃደኝነት ባደርገው ኃላፊነቴንና ግዴታዬን ብቻ መወጣቴ ይሆናል። እን ዲህ ከሆነ ታዲያ ደመወዜ ምንድን ነው? የእኔስ ደመወዝ ወንጌልን በነፃ እየሰበክሁ ፥ ላገኝ የሚገባኝን ጥቅም በመተው የማገኘው ደስታ ብቻ ነው።"
1ኛ ቆሮ 9፥14-18 (ሕያው ቃል)

“ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ፦ አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው አለ።”
ማርቆስ 9፥24

❤5👍1
“ድምጽ ነኝ!”
“አንተ ማን ነህ?” ቢሉት ማዕረጉን ፍለጋ
ሰባኪዉ ዝም ጭጭ መልስ የለም እርሱ ጋ
“በል ባክህ ንገረን
ደግሞ እንቸኩላለን
ለሚጠባበቁን ወሬ እናደርሳለን፤
እንዲህ የሆነ እንደሁ ዝናህም ይወጣል
አገር ጉድ እያለ በክብር ያጅብሃል።”
ጠብ የሚል ሲጠፋ የሚደረድረዉ
የማዕረግ አይነት የሚከናነበዉ
እንደነበር ሲቆም በአንክሮ እያያቸዉ
አማራጭን ሰጡት እንዲመርጥላቸዉ።
“ክርስቶስ ነህ ኤልያስ ወይስ ነቢዩ ነህ?
ምንስ ነዉ ማዕረግህ ማን ብለን እንጥራህ?
እባክህ ንገረን ክብር ደረጃህን
ስምና መለያ የሚመጥንህን”
ያን ጊዜ ከበደዉ መታገስ አቃተዉ
ማድመጥም አልቻለ እንኳን ሊደርበዉ
የሚጯጯሁትን ቀና ብሎ አየና
“ድምጽ ነኝ”! አላቸዉ እጅጉን ጮኸና
ያመጡትን ኮከብ የሚለጥፉትን
አራግፎ ከላዩ ሰዉ ሠራሽ ማዕረግን
እንዲህ ሲል ቀጠለ ሰባኪው ጩኸቱን፡-
“ድምጽ ነኝ፣ ድምጽ ነኝ ያዉም የበረሀ
መንገድ የሚያቀና እንዲያልፍበት ዉሀ
እንደልቡ እንዲሔድ ሕይወት ሰጭዉ ጅረት
ጥርጊያዉን አቅኝ ነኝ በሚሰጠኝ ምህረት
በሉ አትነዝንዙኝ ማንነቴ ይህ ነው
ሌላ ምንም የለኝ ስለራሴ እምለዉ
ኋላዬ ያለዉ ግን ባለማዕረግ ነዉ
ከሰማይ የመጣዉ ክርስቶስ ጌታዬ
ከሁሉ በላይ ነዉ።”
(ዮሐ 1፧19-28)
ምንጭ፦ mamushafenta.com
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
“አንተ ማን ነህ?” ቢሉት ማዕረጉን ፍለጋ
ሰባኪዉ ዝም ጭጭ መልስ የለም እርሱ ጋ
“በል ባክህ ንገረን
ደግሞ እንቸኩላለን
ለሚጠባበቁን ወሬ እናደርሳለን፤
እንዲህ የሆነ እንደሁ ዝናህም ይወጣል
አገር ጉድ እያለ በክብር ያጅብሃል።”
ጠብ የሚል ሲጠፋ የሚደረድረዉ
የማዕረግ አይነት የሚከናነበዉ
እንደነበር ሲቆም በአንክሮ እያያቸዉ
አማራጭን ሰጡት እንዲመርጥላቸዉ።
“ክርስቶስ ነህ ኤልያስ ወይስ ነቢዩ ነህ?
ምንስ ነዉ ማዕረግህ ማን ብለን እንጥራህ?
እባክህ ንገረን ክብር ደረጃህን
ስምና መለያ የሚመጥንህን”
ያን ጊዜ ከበደዉ መታገስ አቃተዉ
ማድመጥም አልቻለ እንኳን ሊደርበዉ
የሚጯጯሁትን ቀና ብሎ አየና
“ድምጽ ነኝ”! አላቸዉ እጅጉን ጮኸና
ያመጡትን ኮከብ የሚለጥፉትን
አራግፎ ከላዩ ሰዉ ሠራሽ ማዕረግን
እንዲህ ሲል ቀጠለ ሰባኪው ጩኸቱን፡-
“ድምጽ ነኝ፣ ድምጽ ነኝ ያዉም የበረሀ
መንገድ የሚያቀና እንዲያልፍበት ዉሀ
እንደልቡ እንዲሔድ ሕይወት ሰጭዉ ጅረት
ጥርጊያዉን አቅኝ ነኝ በሚሰጠኝ ምህረት
በሉ አትነዝንዙኝ ማንነቴ ይህ ነው
ሌላ ምንም የለኝ ስለራሴ እምለዉ
ኋላዬ ያለዉ ግን ባለማዕረግ ነዉ
ከሰማይ የመጣዉ ክርስቶስ ጌታዬ
ከሁሉ በላይ ነዉ።”
(ዮሐ 1፧19-28)
ምንጭ፦ mamushafenta.com
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
❤8👍2🥰1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ጊዜው መልካም ሲሆን፣ ደስ ይበልህ፤ ጊዜው ክፉ ሲሆን ግን ይህን አስብ፤ እግዚአብሔር አንዱን እንዳደረገ፣ ሌላውንም አድርጎአል፤ ስለዚህ ሰው ስለ ወደ ፊት ሁኔታው፣ ምንም ሊያውቅ አይችልም።”
መክብብ 7፥14 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ጊዜው መልካም ሲሆን፣ ደስ ይበልህ፤ ጊዜው ክፉ ሲሆን ግን ይህን አስብ፤ እግዚአብሔር አንዱን እንዳደረገ፣ ሌላውንም አድርጎአል፤ ስለዚህ ሰው ስለ ወደ ፊት ሁኔታው፣ ምንም ሊያውቅ አይችልም።”
መክብብ 7፥14 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
❤5👍1
#መጻሕፍትን_እንመርምር
አማኝ ወይም የዳነ ሰው ድነቱን ሊያጣ ይችላል ወይስ አይችልም?
ክፍል-5
እምነትና ሥራ
አንዳንድ የሃይማኖት ክፍሎች መልካምን ሥራ በማድረግ ደኅንነትን ማግኘት ይቻላል ብለው ያስተምራሉ። የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ደግሞ ክርስቲያኖች መልካምን ሥራ ሲያደርጉ በማየት እነርሱም እንዲህ ያለውን መልካም ሥራ የሚያደርጉት ደኅንነትን ለማግኘት ሲሉ ነው ብለው ያስባሉ። ስለዚህ አያሌ ሰዎች በክርስትናና በሌሎች ሃይማኖቶች መካከል ምንም ልዩነት የለም በማለት ይናገራሉ።
ይሁንና እንዲህ የሚሉ ሰዎች ተሳስተዋል። በክርስትናና በሌሎች ሃይማኖቶች መካከል ያለው ልዩነት እጅግ ታላቅ ነው። ክርስቲያኖች መልካምን ሥራ የሚያደርጉት በቅድሚያ ደኅንነትን ካገኙ በኋላ ነው። መልካምን ሥራ የምናደርገው ደኅንነትን ለማግኘት ስንል አይደለም። መልካምን ሥራ የምናደርገው አስቀድሞ ስለዳንን ነው።
ከዚህም ላይ ቢሆን አንዳንድ ክርስቲያኖች ስህተትን ይፈጽማሉ። ደኅንነትን ካገኙ በኋላ ያገኙትን ደኅንነት ለማጽናት ሲሉ መልካምን ሥራ ማድረግ ያለባቸው ይመስላቸዋል። ሆኖም ሰዎች ደኅንነትን በመልካም ሥራቸው እንደማያገኙ ሁሉ ያገኙትንም ደኅንነት በመልካም ሥራቸው ማጽናት አይችሉም (ገላ. 3፥3)። ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ደኅንነት ያገኘነው በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ያገኘነውም ደኅንነት የሚጸናው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው።
እስከ አሁን ድረስ የተባለው ነገር ሁሉ ትክክል ቢሆንም፥ ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን መታዛዝና እርሱንም ደስ የሚያሰኝ ተግባር መፈጸም አለባቸው። በሕይወታችን ውስጥ መልካም ተግባር የማይታይ ከሆነ እምነታችን ሐሰት ነው ማለት ነው። እውነተኛ እምነት ባለበት ቦታ ሁሉ መልካምም ተግባር አለ (ያዕ. 2፥17)።
የዛፍን ምሳሌ የወሰድን እንደሆን በእምነትና በሥራ መካከል ያለውን ተዛምዶ በሚገባ ሊያስረዳን ይችላል። ፍሬ ለማፍራት (ይኸውም መልካም ተግባር ለማድረግ) በቅድሚያ ሕያዋን መሆን አለብን። የማያምኑና ደኅንነትንም ያልተቀበሉ ሰዎች ግን ሙታን ናቸው። እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መልካም ተግባር ለመፈጸም ኃይል የላቸውም። ሙት ዛፍ ፍሬ እንደማያፈራ ሁሉ በኃጢአትም ምክንያት ሙት የሆኑና ያልዳኑም ሰዎች ልክ እንዲሁ ናቸው። በእግዚአብሔር ሥራ ከመመካት ይልቅ አሁንም የሚታመኑት መልካም ሥራዬ ያድነኛል ብለው ነው (ሮሜ 4፥45)። በጎ ተግባራትን የምንፈጽመው ለራሳችን ጥቅም ሳይሆን ለሌሎች ጥቅምና ፍቅራችንንም ለእግዚአብሔር ለመግለጽ ስንል ነው (ዮሐ. 14፥21)።
በሌላ በኩል ደግሞ ፍሬ የሚያፈራ ሕያው ዛፍ ሁሉ ፍሬን ማፍራት አለበት። ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ ፍሬ የማያፈራ ከሆነ እንደ ሙት ዛፍ ወይም ሊሞት እንደተቃረበ ዛፍ መሆኑን እናውቃለን። እናምናለን እያልን መልካምን ተግባር የማናደርግ ከሆነ ሐሰተኞች ነን (ማቴ. 7፥21፤ 1ዮሐ. 2፥4)። እምነት እንዳለን የምናረጋግጠው በመልካም ተግባራችን ነው። ምክንያቱም እውነተኛ እምነት የሚገለጠው በመልካም ሥራ ነው።
እንግዲህ እንደ ሌሎች ሃይማኖቶች ከሆነ ሰዎች ሙት ዛፍ ናቸው፤ ሕይወትን ለመቀበል ተስፋ የሚያደርጉት ፍሬ በማፍራት ነው። እንደ ክርስትና ሃይማኖት ግን ፍሬ ማፍራት የምንችለው ሕይወትን ካገኘን በኋላ ነው።
ይህ የሚያሳየን እንግዲህ በእምነት «አማካይነት»፥ «በእምነት በኩል» ወይም «እምነታችንን በመጠቀም» ኃጢአትን መካድና እግዚአብሔርን መታዘዝ ያለብን መሆኑን ነው። እውነተኛ እምነት ያለን ከሆነ ባሕርያችንና አኗኗራችን ፍጹም ይቀየራል (ሮሜ 8፥13፤ 1ቆሮ. 6፥9–11፤ ገላ. 5፥19–26)። ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ እንዲህ ለማድረግ የሚያስችል ኀይል ስለሰጠን ነው። እግዚአብሔር አዲስ ሕይወት ሰጠን፤ አዲስ ኅሊና ሰጠን፤ አዲስም ተፈጥሮ ሰጠን፤ እንዲህም በመሆኑ እርሱን ደስ የሚያሰኝ ሕይወትን ለመኖር እንችላለን። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ሲል ያሳስባል፥ «ወዳጆች ሆይ! . . . እያንዳንዳችሁ ያላችሁን ደኅንነት ፍጹም ለማድረግ በፍርሃትና በአክብሮ ተግታችሁ ሥሩ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ፈቃደኛነትንና ታዛዥነትን ለእናንተ እየሰጠ ዓላማውን ከፍጻሜ ለማድረስ በእናንተ ውስጥ ይሠራል» (ፊል. 2፥12–13)።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 22-23

👍4🔥4❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤”
2ኛ ቆሮ 1፥8

❤4👍2👏1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ሮሜ 8፥9-11
ከዚህ በፊት ሮሜ 8፥5-8 ተመልክተናል። በዚያ ክፍል አዲሱ የሕይወት መንፈስ ሕግ በሕይወታችን በሙላት እንዲሰራ ምን ያስፈልጋል ብለን በዝርዝር አንዱን ርዕስ አይተን ነበር፤ ሌላውን ዛሬ እንጀምራለን። እርሱም መንፈስ ቅዱስ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ማሰላሰልም ሆነ በቃሉ ጸንተን ፍሬ ለማፍራት ያለ መንፈስ ቅዱስ የሚታሰብ አይደለም።
ጳውሎስ እዚህ ላይ (ሮሜ 8፥9-11) ክርስቲያኖችን በመንፈስ ቁጥጥር ሥር እንደሆኑ እንጂ በኃጢአተኛ ባሕሪ ቁጥጥር ሥር እንዳልሆኑ ያስታውሳቸዋል። በዚህ ጥቅስ ላይ (ቁ. 9) መንፈስ፥ የእግዚአብሔር መንፈስና፥ የክርስቶስ መንፈስ የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት እንዱን መንፈስ ነው፤ ያውም መንፈስ ቅዱስን ነው (1ቆሮ. 3፥16፤ 8፥19)።
በእግዚአብሔር አብ፥ በክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ስላለው ግኑኝነት ለመረዳት፤ የውሃን ምሳሌነት ብንጠቀም መልካም ነው። አብ የውሃው ምንጭ ማለትም የውሃው መፍለቂያ ነው እንበል፥ ክርስቶስ ደግሞ ውሃውን ወደ መሬት የሚያመጣው ቧንቧ ወይም ቦይ ነው እንበል፥ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ከአብ አንሥቶ በክርስቶስ ውስጥ ወደ እኛ የሚመነጨው ራሱ ውሃው ነው እንደ ማለት ነው። የክርስቶስ መንፈስ በውስጣችን ሲኖር ብቻ ነው የክርስቶስ ነን ለማለት የምንችለው በእርግጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ መጥቶ አማኞች ያልሆኑትን ሊጠራቸው ይችላል። ነገር ግን በውስጣቸው መኖሪያ ቦታ ሊያገኝ አይችልም። መንፈስ በሰው ውስጥ ሊገባና መኖሪያ ቦታ አግኝቶ ሊኖር የሚችለው፤ ሰው ልቡን ከፍቶ መንፈስ ቅዱስን ሲጋብዘው ብቻ ነው (ራእ. 3፥20)።
ነገር ግን ክርስቶስ (የክርስቶስ መንፈስ) በውስጣችሁ ቢኖር ሥጋችሁ፥ (አሮጌው ኃጢአተኛ ሥጋችሁ) የሞተ ነው፤ ከእንግዲህ ወዲህ አሮጌው ሥጋችሁ ጌታችሁ ሊሆን አይገባውም (ሮሜ 6፥6)።
የክርስቶስ መንፈስ በውስጣችሁ ቢኖር፥ ሥጋችሁ የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን ሕያው ነው ይህም አዲሱ መንፈሳዊ አካላችሁ ሕያው ነው ማለት ነው (ሮሜ 6፥11፤ ገላ. 2፥20)።
ሰውነታችን፥ ማለትም አሮጌው ሥጋችን በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፤ መንፈሳችን ግን በጽድቅ ምክንያት፥ ያውም በክርስቶስ ጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው።
ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው እግዚአብሔር አብ ነው። በውስጣችን በሚኖረው በመንፈሱ አማካይነት እግዚአብሔር ለሟች አካላችን ሕይወት፤ ይሄውም መንፈሳዊ ሕይወት ይሰጠናል። እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ለእኛ የሚሰጠን አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት ብቻ ሳይሆን፥ ልክ ክርስቶስን ከሞት እንዳስነሣው እኛንም በዓለም መጨረሻ ላይ ከሞት ያስነሣናል። ከእርሱም ጋር ለዘላለም እንድንኖር ያደርገናል። በዚህ ጥቅስ ላይ(ቁ.11) ሥጋችን ከሞት እንደሚነሣ ተስፋ ተሰጥቶናል (1ቆሮ. 15፥42-49፤ ፊል. 3፥20-21)።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 367

👍3❤1🔥1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
"ጨለማ በወረሰው አስፈሪ ሸለቆ ውስጥ እንኳ ባልፍ ፥ አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንክ አደጋ ይደርስብኛል ብዬ አልፈራም። በትርህ ስለሚመራኝ ፥ ምርኵዝህም ስለሚደግፈኝ እየተጽናናሁ እጓዛለሁ።"
መዝሙር 23፥4 (ሕያው ቃል)

👍4❤1🥰1👏1
Follow the ቅዱሳት መጻሕፍት channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaA94PKFsn0ejWkJe012
ቅዱሳት መጻሕፍትን በዋትስአፕ መከታተል ለሚፈልጉ
ቅዱሳት መጻሕፍትን በዋትስአፕ መከታተል ለሚፈልጉ
👍2❤1