#መጻሕፍትን_እንመርምር
አማኝ ወይም የዳነ ሰው ድነቱን ሊያጣ ይችላል ወይስ አይችልም?
ክፍል-3
ይሁንና እግዚኣብሔር እንደ ጻድቃን ብቻ አልቆጠረንም። ደግሞም የጽድቅ ሕይወትን ለመኖር የሚያስችል አዲስ ተፈጥሮ ብቻ አልሰጠንም። ከዚህ ሁሉ በላይ ጻድቅ ሆነን እንድንገኝ በእጅጉ አግዞናል። በሌላ አነጋገር «ቀድሶናል» ወይም «ቅዱሳን» አድርጎናል። የራሱንም ቅድስና ሰጥቶናል። ኢየሱስ ሰዎችን የታደገው ከኃጢአት ቅጣት ብቻ ሳይሆን ሕዝቡንም «ከኃጢአታቸው» አንጽቷል (ማቴ. 1፥21፤ ሮሜ 6፥22)። በአንድ በኩል፥ ኢየሱስ አንድ ጊዜ ባቀረበው መሥዋዕት ቅዱሳን ሆነናል (ዕብ. 10፥10)።
እንዲሁም «ቅዱሳን» ተብለን ተጠርተናል (ኤፌ. 1፥1፤ ፊል. 1፥1)። በሌላ በኩል ግን በየዕለቱ የቅድስናን ሕይወት አንለማመድም። በመሆኑም በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ዘወትር የምንቀደስ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል (ሮሜ 7፥24-25፤ 8፥10–11፤ ገላ. 3፥3)።
እንዲሁም እግዚአብሔር «አክብሮናል» (ሮሜ 8፥30)። አከበራቸው የሚለው ቃል አንድ ቀን ከሙታን የሚነሳውን አካላችንንና የምናገኘውንም የዘላለም ሕይወት የሚያሳይ ቃል ነው። ኢየሱስ በአብ ዘንድ ያለውን ክብር ማየት እንድንችል ጸለዮ ነበር (ዮሐ. 17፥24)። ጳውሎስ ደግሞ የዚህ ክብር ተካፋዮች እንደምንሆን ተናግሯል (ሮሜ 8፥17)። አሁን ያለን አካል በከበረ አካል ይለወጣል (1ቆሮ. 15፥4244)። ጳውሎስ እንዳመለከተው ደኅንነት ያገኘነው በዚህ ሕይወት ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ሕይወት ነው። ትንሣኤ ሙታን የተስፋችን ማዕከል ነው (1ቆሮ. 15፥12–20)። የዘላለምም ሕይወት እንደምናገኝ ተስፋ ተሰጥቶናል (ዮሐ. 3፥16፤ 10፥28)።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን ደኅንነት አስፋፍተው የሚገልጡ ሌሎችም ቃላት አሉ። ለምሳሌ በክርስቶስ አማካይነት «ተዋጅተናል» (ኤፌ. 1፥7)። ዋጀ (ወይም ቤዠ) ማለት «እዳን ከፍሎ ገዛ ወይም ታደገ» ማለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ወገኖች እንሆን ዘንድ (የሐዋ. 20፥28፤ ራእ. 5፥9)፤ ከኃጢአት ባርነትና (ቲቶ. 2፥14) ከሕግ እርግማን ተቤዠቶናል (ገላ. 3፥13)። «በዋጋ ተገዝተናል» (1ቆሮ 6፥20)፤ የተገዛነውም ክቡር በሆነው ደሙ ነው (1ጴጥ. 1፥18–19)።
ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን ደኅንነት የሚገልጠው ሌላው ቃል «የእግዚአብሔር ልጆች» ሆነናል የሚለው ቃል ነው። እግዚአብሔር አብ ኢየሱስ ክርስቶስ በሠራው ሥራ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆን ባደረገንና በተቀበልነውም በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት «ልጆቹ እንድንሆን አስቀድሞ ወሰነን» (ኤፌ. 1፥5፤ ሮሜ 8፥14-17፤ ገላ. 4፥57)። አሁን የተቀበልነው ወደፊት ለምንወርሰው እርስት መያዣ የሚሆነንን ብቻ ነው። ይሁንና አዲስ የትንሣኤ አካል በምንለብስበት ዕለት የእግዚአብሔር ልጅነታችንን ሙሉ መብት እንደምንቀበል ጳውሎስ ጽፎአል (ሮሜ 8፥18–25፤ ኤፌ. 1፥13–14)።
እንግዲህ ይህ የሚያሳየን ደኅንነት የሚለው ቃል በሦስት የጊዜ መደብ አጠቃቀም ማለትም በሃላፊ፥ በአሁንና በወደፊት ጊዜ የተገለጸ መሆኑን ነው። ስለዚህ ድነናል (ኤፌ. 2፥5፤ 8፤ 2ጢሞ. 1፥9)፥ እየዳንን ነው (1ቆሮ. 1፥18፤ 2ቆሮ. 2፥15፤ ፊል. 2፥12–13)። ደግሞም እንድናለን (ሮሜ 13፥11፤ 1ተሰ. 5፥9፤ 1ጴጥ. 1፥5)። ቀደም ሲል በተጠቀምንባቸው ስያሜዎች ነገሩን ስናጠቃልለው እንዲህ ማለት ይሆናል፤ በቀደመው ጊዜ «ጸድቀናል»፥ «ተዋጅተናል» እንዲሁም «አዲስ ተፈጥሮ» ተቀብለናል። በአሁኑ ጊዜ «እየተቀደስን» ነው፤ ወደፊት ደግሞ «የእግዚአብሔር ልጅነታችንን» ሙሉ መብት እንቀበላለን፤ በዚያን ጊዜም «እንከብራለን»።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 21-22
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot

❤2👍1👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ ተስፋ ካልቈረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን።”
ገላትያ 6፥9 (አዲሱ መ.ት)

👍6❤2🥰1
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መጪው ዘመን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚሆንበት እና እግዚአብሔር እንደነገረን ብቻ የምንቀሳቀስበትና የምናደርግበት ዘመን ይሁንልን!
“...ብቻ አምላክህ እግዚአብሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።”
ኢያሱ 1፥17
“አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፤”
ዘፍጥረት 12፥4

👍5❤2🥰1👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ጻድቃን መልካም ነገር እንደሚያገኙ ንገሯቸው፤ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና።”
ኢሳይያስ 3፥10 (አዲሱ መ.ት)

👍2❤1🥰1👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ክብሬ በእኔ ዘንድ ታድሶአል፥ ቀስቴም በእጄ ውስጥ ለምልሞአል።”
ኢዮብ 29፥20

❤3🔥2👍1🥰1👏1
አዲሱ አመት በእውነት አዲስ የሚሆንበት ሶስቱ መንገዶች
አመት ሲለወጥ ሁልጊዜ ተስፋችን ይታደሳል አዲስን ነገር ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ነገር ግን ከተረዳነው የአመቱ ወሮችና ቀኖች በራሳቸው አዲስ አይደሉም ካለእኛም በራሳቸው አዲስን ነገር ሊያደርጉልን አይችሉም፡፡ ያው እሁድ ሰኞ ማክሰኞ ሮብ ሃሙስ አርብ ቅዳሜ ናቸው የአመቱም ወሮች ያው መስከረም ጥቅምት ህዳር ታህሳሰ ወዘተ ናቸው፡፡
አዲስን አመት አዲስ የሚያደርገው አዲሱን አመት የሚኖርበት ሰው አዲስ መሆኑና መታደሱ ነው፡፡ ምክንያቱም አሮጌን ነገር በአዲስ ነገር ውስጥ ብንጨምር አይሰራም፡፡ አሮጌ ሰው በአዲስ አመት ውስጥ መኖሩ አመቱን በፍፁም አዲስ አያደርገውም፡፡ አሮጌ ሰው ከአዲስ አመት አዲስን ነገር መጠበቅ ነፋስን እንደመጨበጥ ከንቱ ድካም ነው፡፡
"በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።"
ማቴዎስ 9፡17
ሰውን የሚለውጠው አመት አይደለም፡፡ ሰውን የሚለውጠው እና አዲስና በቀጣይነት የታደሰ የሚያደርገው የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡
የአዲስን አመት ጥቅም ለመጠቀም አዲስን ነገር በአዲስ ነገር ውስጥ መጨመር ግዴታ ነው፡፡ አዲሱን አመት በአዲስነት የምንቀበልበትና በአዲስነት የምናድስባቸው ሶስት መንገዶች፡-
1. አዲስ ፍጥረት መሆን
ሰው ስለሃጢያቱ እንደሞተለት እና የሃጢያቱን ዋጋ ሁሉ እንደከፈለለት በእግዚአብሔር ካላመነ ፣ ኢየሱስን እንደ አዳኙ ካልተቀበለና እግዚአብሔር በኢየሱስ ያዘጋጀለትን የመዳኛ መንገድ ካልተቀበለ የህይወት አዲስነት በፍፁም አይገኝም፡፡ ሰው ኢየሱስን ካልተቀበለ የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም፡፡
"በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።"
ዮሐንስ 3፡36
ኢየሱስን የተቀበለ ሰው ግን እግዚአብሔር ልጅ አድርጎ ይቀበለዋል በክርስቶስም አዲስ ፍጥረት ይሆናል፡፡
"ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።"
2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17
2. አእምሮን ማደስ
አዲሱን አመት በአዲስነት እንድንደሰትበት አሮጌውን አስተሳሰባችንን በእግዚአብሄር ቃል በማደስ እንደ አዲስ ፍጥረትነታችን መኖር ይኖርብናል፡፡
"የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።"
ሮሜ 12፡2
የእግዚአብሔርን ቃል በመቀበል በልባችን ያለውን አለማዊ አስተሳሰብ ካላስወገድን በስተቀር አዲስ አመት አዲስ ይሆንልናል ማለት ዘበት ነው፡፡
"ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።"
ያዕቆብ 1፡21
3. አዲሱን ሰው መልበስ
ምንም እንኳን አዲስ ፍጥረት መሆን ወሳኝ ቢሆንም አዲስን አመት አዲስ የሚያደርገው አዲስ ፍጥረት መሆን ብቻ አይደለም፡፡ በአዲስ ህይወት ለመመላለስ አእምሮን በእግዚአብሄር ቃል ማደስና እንደ እግዚአብሄር ቃል መኖር መመላለስ ይጠይቃል፡፡
"ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።"
ኤፌሶን 4፡22-24
ኢየሱስን ተቀብለን አዲስ ፍጥረት ብንሆን ፣ አእምሮዋችንን በእግዚአብሄር ቃል ብናድስና እንደ አዲስ ፍጥረትነታችንና እንደታደሰ አእምሮ ብንመላለስ አዲሱ አመት በእውነት አዲስ ይሆንልናል፡፡ ህይወታችን እስካልተለወጠ ዘመናችን አይለወጥም፡፡ ህይወታችን በተለወጠ ቁጥር ዘመናችን እየታደሰ ይሄዳል፡፡
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1botሐ

Talking from the heart Blog
አዲሱ አመት በእውነት አዲስ የሚሆንበት ሶስቱ መንገዶች
አመት ሲለወጥ ሁልጊዜ ተስፋችን ይታደሳል አዲስን ነገር ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ነገር ግን ከተረዳነው የአመቱ ወሮችና ቀኖች በራሳቸው አዲስ አይደሉም ካለእኛም በራሳቸው አዲስን ነገር ሊያደርጉልን አይችሉም፡፡ ያው እሁድ ሰኞ ማክሰኞ ሮብ ሃሙስ አርብ ቅዳሜ ናቸው የአመቱም ወሮች ያው መስከረም ጥቅምት ህዳር ታህሳሰ …
👍3❤1🔥1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።”
ሮሜ 11፥33
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።”
ሮሜ 11፥33
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
👍2❤1🥰1👏1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
2ኛ ጢሞቴዎስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።
² ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥
³ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥
⁴ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤
⁵ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።
⁶-⁷ ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና።
⁸ ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው፥ እውነትን ይቃወማሉ።
⁹ ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም።

❤3👍3👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
"ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሄዳሉ፥ የአምልኮን ሥርዓት አያጓድሉም፤ ነገር ግን የሚሰሙትን እውነት በተግባር አያውሉትም። እነዚህን ከመሳሰሉ ሰዎች ራቅ።"
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥5 (ሕያው ቃል)

❤2👍2🔥1👏1
በዮሐንስ ራእይ መልእክት ከተጻፈላቸው 7ቱ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ከጌታ ዘንድ አንድም ሙገሳ ወይም አድናቆት ያልተነገረው ቤተክርስቲያን የቱ ነው?
Anonymous Quiz
17%
ሀ. ትያጥሮን
41%
ለ. ሎዶቅያ
14%
ሐ. ጴርጋሞን
13%
መ. ሰርዴስ
14%
ሠ. ሰምርኔስ
👍3❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ዮቶርም እግዚአብሔር ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ፥ ከግብፃውያንም እጅ ስላዳናቸው ደስ አለው።”
ዘጸአት 18፥9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ዮቶርም እግዚአብሔር ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ፥ ከግብፃውያንም እጅ ስላዳናቸው ደስ አለው።”
ዘጸአት 18፥9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
👍4❤1🔥1🥰1
#እራሳችንን_እንመርምር
ከዚህ በኋላ ምን አይነት ዘመን ይመጣ ይሆን? ቅዱሳት መጻሕፍትስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይሉናል? ታዲያ ዘመኑን እንዴት እንለፈው?
“ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥1
“አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን አሳቤንም እምነቴንም ትዕግሥቴንም ፍቅሬንም መጽናቴንም ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤”
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥10
“አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤”
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥14

👏2❤1👍1🥰1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን በመጠን እንኑር፤”
1ኛ ተሰሎንቄ 5፥8

ቅዱሳት መጻሕፍት
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት ሮሜ 8፥5-8 ፭. ኃጢአትን ሰውሮ በኃጢአት መመላለስ ወይም መጽናት በአማኝ ሕይወት ውስጥ አዲሱ የሕይወት መንፈስ ሕግ በስፋት ጎልብቶ ፍሬ እንዳያፈራ እንቅፋት ከሚሆነው ነገር ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው በኃጢአት መጽናት፤ ከጥፋት ላለመመለስ ደግሞ ኃጢአትን እየሰወሩ መኖር ነው። ኃጢአት ሁልጊዜ በደጃችን ታደባለች ታዲያ በመንፈሳዊ ሕይወት ለምልመን ለመኖር ከወሰንን ኃጢአትን…
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ሮሜ 8፥5-8
ከዚህ በፊት ዳግመኛ በተወለደ የአማኝ ሕይወት ውስጥ አዲሱ የሕይወት መንፈስ ሕግ በስፋት ፍሬ እንዳያፈራ እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን አይተናል። ዛሬ ደግሞ መፍትሄውን እንመለከታለን።
🔑መፍትሄ፦ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ ማስተዋል።
“በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።”
ማቴዎስ 13፥23
በመንፈሳዊ ሕይወታችን ፍሬያማ እና ውጤታማ እንዲሆን ከፈለግን የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ብቻ ሳይሆን ማስተዋልም ይጠበቅብናል። ማስተዋል የመንፈሳዊ ሰው ትልቁ ሃብቱ እና መለያው ነው። አንድ ሰው ማስተዋል እንዳለው የምናውቀው የእግዚአብሔርን ቃል በተግባር ሲያውለው ነው። ማስረጃ፦
“እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፤ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።”
መዝሙር 111፥10 (አዲሱ መ.ት)
“ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ።”
መዝሙር 119፥104
“ብቻ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ሕግ ትጠብቅ ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን ይስጥህ፥ በእስራኤልም ላይ ያሠልጥንህ።”
1 ዜና 22፥12
“ሰውንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ነው አለው።”
ኢዮብ 28፥28
“ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ።”
ያዕቆብ 3፥13
✍ማስተዋል እንዴት ይገኛል?
👉ከእግዚአብሔር ዘንድ በመጸለይ
“አቤቱ፥ ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትቅረብ፤ እንደ ቃልህም አስተዋይ አድርገኝ።”
መዝሙር 119፥169
👉 በመስማት እና በማድመጥ
“እናንተ ልጆች፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤”
ምሳሌ 4፥1
“ሕዝቡንም ጠርቶ፦ ስሙ አስተውሉም፤”
ማቴዎስ 15፥10

👍3🔥2❤1🥰1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ዳዊትም በአካሄዱ ሁሉ አስተውሎ ያደርግ ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።”
1ኛ ሳሙኤል 18፥14
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ዳዊትም በአካሄዱ ሁሉ አስተውሎ ያደርግ ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።”
1ኛ ሳሙኤል 18፥14
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አስተያየት መስጫ፦ @HolyScriptures1bot
👍2❤1🥰1👏1
#መጻሕፍትን_እንመርምር
አማኝ ወይም የዳነ ሰው ድነቱን ሊያጣ ይችላል ወይስ አይችልም?
ክፍል-4
የሰው ምላሽ
ሰዎች ራሳቸውን ማዳን ከቶ አይችሉም። ሰዎች መዳን የሚችሉት በእግዚአብሔር ምሕረትና ጸጋ ብቻ ነው። እንዲህ ሲባል ግን ሰዎች በደኅንነት ሥራ ውስጥ ምንም ድርሻ የላቸውም ማለት አይደለም። ምንም እንኳን ኢየሱስ የዓለምን ሁሉ ኃጢአት በመስቀል ላይ ቢያስወግድም (ዮሐ. 1፥29) ሁሉ ሰው ግን አልዳነም። እግዚአብሔር የሰጠንን ደኅንነት ለመቀበል አንድ ነገር ብቻ ያስፈልጋል በኢየሱስ ማመን (ዮሐ. 3፥16–18፤ የሐዋ. 16፥31)።
በኢየሱስ ማመን ማለት ኢየሱስ መሲሕ ወይም ክርስቶስ እንደሆነና የእግዚአብሔርም ልጅ እንደሆነ ማመን ማለት ብቻ አይደለም (ዮሐ. 8፥24)፤ ወደ ሕይወታችንና ወደ ልባችንም መቀበልና (ማቴ. 10፥40፤ ዮሐ. 1፥12፤ ራእ. 3፥20) በእርሱም ሙሉ በሙሉ መታመን ማለትም ነው (2ጢሞ. 1፥12)። እምነት ማለት ኢየሱስን ማወቅ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ለእርሱ ከልባችን መሰጠት ማለት ነው። እውነተኛ እምነት ያለን ከሆነ፥ ኃጢአታችንን እንናዘዛለን (1ዮሐ. 1፥9)፥ ከኃጢአታችንም ተመልሰን ንስሓ እንገባለን (ሉቃ. 13፥3፤ 5፤ የሐዋ. 2፥38)። በእርግጥ እውነተኛ እምነት ካለን፥ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በሰዎች ፊት በግልጽ እንመሰክራለን እንጂ ክርስቲያን መሆናችንን አንሸሽግም (ማቴ. 10፥32 33፤ ሮሜ 10፥9–10)። እንዲሁም ኢየሱስ ተጠመቁ ሲል የሰጠውን ትዕዛዝ እንፈጽማለን (ማቴ. 28፥19 20፣ ማር. 16፥15–16፤ የሐዋ. 2፥38)።
ምንም እንኳን ደኅንነት እግዚአብሔር በክርስቶስ ሞት አማካይነት በመስቀል ላይ የፈጸመልን ሥራ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ብቻ በሠራው ደኅንነት ማመንና መደገፍ አለብን። ደኅንነት ከእኛ አልተገኘም። የደኅንነት መገኛና ምንጭ እግዚአብሔር ነው። ከጸጋው የተነሣ እንዲያው በነፃ ሰጠን። ደኅንነትን በራሳችን ኃይልና ጥረት ወይም ደግሞ በመልካም ሥራችን ማግኘት አንችልም (ሮሜ 9፥16)። እምነት በእግዚአብሔርና በሰጠንም ጸጋ መታመን ማለት ነው (ሮሜ 4፥5)።
ይህም በመሆኑ ነው ጳውሎስ ደኅንነትና ከእርሱም ጋር የምናገኘው በረከት ሁሉ በእምነት አማካይነት በጸጋው የምናገኘው ነገር መሆኑን የተናገረው (ኤፌ. 2፥8)። በሌላ ቦታ ደግሞ «በእምነት አማካይነት በጸጋው» የሚለውን «በእምነት» በማለት አሳጥሮ ጽፎአል። በእምነት ወይም በእምነት አማካይነት ጻድቃን (ሮሜ 3፥27–28፤ ገላ. 2፥15–16) ወይም ቅዱሳን ሆነናል (የሐዋ. 16፥18፤ ገላ. 3፥1–5)። በእምነትም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሆነናል (ዮሐ. 1፥12–13)። ሆኖም እምነት ራሱ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። በእኛ ዘንድ የምንመካበት አንዳች ነገር የለም (የሐዋ. 3፥16፤ ኤፌ. 2፥9፤ ፊል. 1፥29፤ 2ጢሞ. 2፥25)። የእምነታችን አመንጪና ጀማሪ ኢየሱስ ራሱ ነው። እንዲሁም እርሱ የእምነታችን ፈጻሚም ነው (ዕብ. 12፥2)።
መስኮት የሚሰጠውን አገልግሎት ለአብነት ያህል የወሰድን እንደሆን በጸጋና በእምነት መካከል ያለውን ተዛምዶ ሊያስረዳን ይችላል። የፀሐይን ብርሃን የምናገኘው በመስኮት በኩል ነው። ሆኖም መስኮት ስላለን ብቻ የፀሐይን ብርሃን አናገኝም። ጸጋ ልክ እንደ ፀሐይ ብርሃን ነው፤ እምነት ደግሞ እንደ መስኮት ነው። የእግዚአብሔርን ጸጋ የምናገኘው በእምነት አማካይነት ነው። ነገር ግን እምነት ስላለን ብቻ የእግዚአብሔርን ጸጋ አናገኝም። የእግዚአብሔር ጸጋ ወደ ሕይወታችን ገብቶ እንዳይለውጠን ጸጋውን ባለማመን ልናዳፍነው እንችላለን። ደኅንነትን ለማግኘት እግዚአብሔርን መታመን አስፈላጊ ነገር ቢሆንም እምነት በራሱ የደኅንነት ምንጭ ሊሆን አይችልም።

❤1👍1👏1