ሂዳያ (ቅኑ መንገድ)
172 subscribers
54 photos
40 videos
1 file
78 links
ወደ አላህ መንገድ የምንጣራበት፣ ቁርኣንና ሱናን የምንማማርበት ቻናል ነው። አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን።"
Download Telegram
Forwarded from Zeynu 🖤
​🚸 "ልጆቻችንን በኢስላማዊ ተርቢያ እናሳድግ! — ከዛሬው የጁመዓ ኹጥባ የተወሰደ መልዕክት" ✨
​بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
​ውድ የቻናላችን ተከታዮች!
​ልጆች አላህ በእጃችን ላይ ያስቀመጣቸው ትልቅ አደራዎች (አማና) ናቸው። ነገ በአላህ ፊት የምንጠየቅበት የነገው ኡማችን መሠረቶች በመሆናቸው፣ ዛሬ ላይ የምንሰጣቸው ተርቢያ (አስተዳደግ) የህይወታቸውን አቅጣጫ ይወስነዋል።
​ነቢያችን (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
​“ሁላችሁም እረኞች ናችሁ፤ እያንዳንዳችሁም በምትጠብቁት ነገር (አደራ) ትጠየቃላችሁ። ሰውየው በቤተሰቦቹ ላይ እረኛ ነው፤ በእነሱም ይጠየቃል።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

​📌 ዛሬ ለልጆቻችን ቀድመን ልናስተምራቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነገሮች፦
​☝️ ስለ አላህ ታላቅነትና ተውሂድ፦ ልክ ታላቁ ሉቅማን ልጃቸውን "ልጄ ሆይ! በአላህ ላይ አታሻርክ" ብለው እንደመከሩት፤ በልጆቻችን ልብ ውስጥ መጀመሪያ የአላህን ፍቅር፣ ፍርሃትና ታላቅነት መዝራት አለብን።
​💚 ስለ ነቢያችን (ﷺ) ማንነትና ሱና፦ ስለ ውቡ ስነ-ምግባራቸው፣ ስለ እዝነታቸውና ስለ አስተማሪነታቸው በመንገር የእሳቸውን ፈለግ እንዲከተሉና እንዲወዱ ማድረግ።
​⚔️ ስለ ሰሓባዎች ጀግንነትና ታሪክ፦ ዛሬ ልጆቻችን የዱንያ ሰዎችንና የፊልም ገጸ-ባህሪያትን አርአያ (Role Model) ከማድረግ ይልቅ፣ የዲን ባለውለታ የሆኑትን የሰሓባዎችን ታሪክና ጀግንነት እያወቁ እንዲያድጉ ማስተማር።
​💎 ስለ እውነትና እውነተኝነት፦ ከውሸትና ከማታለል የጸዳ፣ ሁልጊዜም እውነትን የሚናገርና በታማኝነት የሚራመድ ትውልድ እንዲሆኑ በተግባር ማሳየት።
​ውድ ወላጆችና ታላላቆች ሆይ!
ልጆችን በቁሳቁስና በዱንያ ትምህርት ብቻ ማርካት ተርቢያ አይደለም። እውነተኛው ስኬት በዲን ኮትኩቶ፣ በጥሩ አህላቅና በተቅዋ ማሳደግ ነው። ዛሬ የምንዘራው መልካም ዘር፣ ነገ ለእኛም የአኺራ ሰደቃ ጃሪያ (የማይቋረጥ አጅር) ይሆንልናል።
​አላህ ልጆቻችንን የዓይናችን ማረፊያ፣ የኢስላም ጋሻና የሱና አርበኞች ያድርግልን! አሚን።
​"መልካምን ነገር ያመለከተ ሰው ልክ እንደሰራው ሰው አጅር አለው።" (ነቢያችን ﷺ)
ይህንን ወሳኝ የኹጥባ ማስታወሻ ለሁሉም ወላጆች ሼር (Share) በማድረግ የአደራችንን ክብደት እናሳስብ!
​🌐 [https://t.me/Hidaya_Path]
​📚 "የዕውቀት ልቅና እና የኡለማዎች ክብር! — ከዛሬው የጁመዓ ኹጥባ የተወሰደ መልዕክት" 💎
​بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
​ውድ የቻናላችን ተከታዮች!
​ዛሬ በተደረገው የጁመዓ ኹጥባ ላይ፣ ዲናችን እስልምና ለዕውቀትና ለዓሊሞች የሰጠውን እጅግ ከፍ ያለና የማይነጥፍ ክብር በጥልቀት ተመልክተናል። ዕውቀት የልብ ብርሃን፣ ዓሊሞች ደግሞ የዚህ ኡማ መብራቶች ናቸው።
​አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣኑ ላይ አዋቂዎችና አላዋቂዎች በፍጹም እኩል ሊሆኑ እንደማይችሉ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦
​“በል፦ እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ እኩል ይሆናሉን? የሚገሰጹት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው።” (አል-ዙመር፡ 9)

​📌 ከዛሬው ኹጥባ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች
​👑 ዓሊሞች የነቢያት ወራሾች ናቸው፦ ነቢያችን (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ “ዓሊሞች (የዕውቀት ባለቤቶች) የነቢያት ወራሾች ናቸው ነቢያት ዲናርንም ሆነ ድርሃምን አላወረሱም፤ ያወረሱት ዕውቀትን ብቻ ነው። ይህንን ዕውቀት የያዘ ሰው ታላቅ ዕድልን አገኘ (አቡ ዳውድና ቲርሚዚ)
​🛑 የኡለማዎችን ክብር መጠበቅ ዛሬ ላይ በሶሻል ሚዲያም ሆነ በተለያየ መድረክ የዲን ዓሊሞችን ማጥላላት ስም መስጠትና መሳደብ አደገኛ መርዝ ነው የሰለፎች መንገድ ዓሊሞችን ማክበርና እውቀታቸውን መቅሰም ነው
​🚨 የመጨረሻው ታላቅ አደራ (ለወላጆች) የዱንያ ትምህርት ብቻውን ለልጆቻችን በቂ አይደለም! ልጆቻችን የዶክተርነት የኢንጂነርነት ወይም ሌላ የዱንያ ክብር ላይ ቢደርሱ እንኳ የዱንያው ትምህርት ከአኺራ ጥፋት ሊያድናቸው አይችልም ቀድመን ዲናቸውን ተውሂዳቸውንና ሱናን ልናስተምራቸው ግድ ይላል
​ውድ ወላጆች ሆይ!
ልጆቻችንን የአላህን መንገድ ሳናስተምር ሶላትና ስነ-ምግባር ሳይኖራቸው ለዱንያ ስኬት ብቻ መጣር አደራን ማጉደል ነው ነገ በአላህ ፊት እንዳናፍር ዛሬውኑ ልጆቻችንን በዲን እውቀት እንኮትኩታቸው
​አላህ እውነተኛውን እውቀት ጨምሮልን በተግባር የምንውል ያድርገን! ዓሊሞቻችንን ይጠብቅልን ልጆቻችንንም የዲን አርበኞች ያድርግልን አሚን
​"መልካምን ነገር ያመለከተ ሰው ልክ እንደሰራው ሰው አጅር አለው። (ነቢያችን ﷺ)
ይህንን ወሳኝ የጁመዓ መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር (Share) በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!
https://t.me/Hidaya_Path
Forwarded from Islamic post
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምሽት ሽንቅ🫀

​اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ
اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد

القارئ الشيخ علاء بن ابراهيم المزجاجي
Instagram ➲3ala_mizjaji
🥰1
​🤝 "እውነተኛ ጓደኛ — የዱንያ ስንቅ፣ የአኺራ ጥላ!" ✨

​بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

​ውድ የቻናላችን ተከታዮች!

​በዚህች ፈታኝ በሆነች የዱንያ ህይወት ውስጥ፣ ከእውነተኛ እና ለአላህ ብሎ ከሚወድ ጓደኛ (ሶሊህ ጓደኛ) የበለጠ ትልቅ ጸጋ የለም። እውነተኛ ጓደኛ ማለት በሳቅና በደስታ ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ በችግርና በጭንቀት ሰዓት ከጎንህ የማይጠፋ ነው።

​ነቢያችን (ﷺ) ስለ ጓደኛ ምርጫ ሲመክሩን እንዲህ ብለዋል፦

​“ሰውየው በጓደኛው ዲን (መንገድ) ላይ ነው፤ ስለዚህ አንዳችሁ ማንንም ጓደኛ እንደሚያደርግ ይመልከት።” (አቡ ዳውድና ቲርሚዚ)


​📌 የእውነተኛ ጓደኛ መገለጫዎች፦
​☝️ አላህን ያስታውሰሃል፦ ስትዘናጋ ወደ አላህ መንገድ ይመልስሃል፤ ለኸይር ስራ ያነሳሳሃል።​
🛡️ ነውርህን ይሸፍናል፦ ስህተትህን በግልጽ አደባባይ ላይ ከማውጣት ይልቅ፣ በምስጢርና በእዝነት ይመክርሃል

​🤲 በዱዓ አይረሳህም፦ በህይወትህም ሆነ ከሞትክ በኋላ፣ በሩቅ ሆኖ ለአንተ ዱዓ ያደርግልሃል
​🤝 እስከ አኺራ አብሮህ ይጓዛል፦ ጓደኝነቱ ለዱንያ ጥቅም ሳይሆን ለአላህ ብሎ ስለሆነ፣ በቂያማ ቀን በአላህ ጥላ ስር አብረው ከሚሆኑት ውስጥ ያደርጋችኋል

​ታላቁ ሊቅ ሐሰኑል በስርይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦

​አማኝ የሆኑ ጓደኞችን ያብዛ፤ ምክንያቱም በቂያማ ቀን (አላህ ሲፈቅድላቸው) ምልጃ (ሸፋዓ) ያደርጋሉና


​ወንድም እህቶቼ ሆይ! የያዝናቸውን ጓደኞች እንመርምር ወደ ጀነት የሚጎትተን ጓደኛ ካለን አጥብቀን እንያዘው ምክንያቱም እውነተኛ ጓደኛ ማግኘት ከባድ ነውና።

​አላህ (ሱ.ወ) ለአላህ ብለው ከሚዋደዱት በመልካም ከሚተጋገዙትና በጀነተል ፊርደውስ አብረው ከሚገቡት ያድርገን! አሚን

​"መልካምን ነገር ያመለከተ ሰው ልክ እንደሰራው ሰው አጅር አለው።" (ነቢያችን ﷺ)

ይህንን መልዕክት ለምትወዱትና አብሯችሁ ጀነት እንዲገባ ለምትመኙት እውነተኛ ጓደኛ ሼር (Share) በማድረግ ፍቅራችሁን ግለጹ!

​🌐 [https://t.me/Hidaya_Path]
የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሒመሁላህ) ንግግር
​"አላህ ዘንድ በክብር ሀገሩ (በጀነት) ውስጥ ከፍተኛ የሆኑ ደረጃዎች አሉ። እነዚያንም ደረጃዎች የመከራና የፈተና ባለቤቶች (ታጋሾች) እንጂ ማንም አያገኛቸውም።"
​ምንጭ፦ ጃሚዕ አል-መሳኢል (3/92)
Forwarded from Islamic post
'ዱዓ'

​ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን የዓይን ማረፊያን ለእኛ ስጠን፤ ለፈራህያን (ለጥንቁቆቹ) መሪ አድርገን። (ሱረቱ አል-ፉርቃን 74)

አላህ መልካም አድርጎ ከመልካሙ ባሪያው ጋ ያጣምረን🤲

@Islamic_post17
@Islamic_post17
🥰2
Forwarded from Islamic post
አላህ እራሱ አድርጎት መላኢኮችን አስከትሎ እኛን ያዘዘበት ብቸኛ ዒባዳ ሰለዋት ነው

إن الله وملائكته يصلون على النبي يأيها الذين آمنوا صلوا عليه وسلموا تسليما



اللهم صل وسلم على نبينا

የጁመዓ ብርሃንን እንድናገኝም ሱረቱል ከህፍን እንቅራ

@Islamic_post17
Forwarded from Islamic post
ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (🤎)
እንዲህ ይላሉ:- 

🔁ከሴቶች አስቀያሚ ማለት
በወንድ ልጅ ላይ ደፋር የሆነች
(ሀያእ የሌላት) ሴት ነች። 


@islamic_post17🌙
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Islamic post
ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ  : -
«ችግርን እና ህመምን መደበቅ የብልሆች መገለጫ ነው።»

الفـوائـد【32】

@Islamic_post17
💯1
ዛሬ ጁምዓ ነዉ ሰሉ አለ ነቢይ🤍
  اللهم صل وسلَّم على نبينا محمد

@Islamic_post17
አሠለሙ አላይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ የተከበራችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች!
​ዛሬ በነበረን የጁምዓ ኹጥባ የተማርነውን እና የዲናችንን መሠረት የሆነውን ጠቃሚ ትምህርት በአጭሩ ላጋራችሁ ፦
​📖 ዲናችን ሙሉ ነው! (ቁርአንና ሀዲስ በቂ ናቸው)
​ወገኖች ሆይ! ዲናችን የተሟላ እንጂ አንዳች ነገር የሚጨመርበት ጎደሎ አይደለም። አላህ (ሱ.ወ) በቁርአኑ ዲናችንን ሙሉ አድርጎ ሰጥቶናል። ስለዚህም መመዘኛችን የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ እና የቁርአን ብርሃን ብቻ ሊሆን ይገባል።
​"ዲናችንን በትክክል እንረዳ፤ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና ሶሀባዎች በቆሙበት ጽኑ መሠረት እንቁም!"
​⛓️ ቁርአንና ሀዲስን አጥብቆ መያዝ (ተመሱክ)
​ኢስላም ማለት በሰው አስተሳሰብ የሚለዋወጥ ሳይሆን፣ በቁርአንና በሀዲስ የታጠረ ነው። እንደ አንድ ሙስሊም ትልቁ ድላችን እና ጽናታችን ያለው ቁርአንንና ሀዲስን አጥብቆ በመያዝ ላይ ነው። በየዓመቱ የሚፈጠሩ አዳዲስ ልማዶች (ቢድዓዎች) ዲናችንን ከማጎልበት ይልቅ የሚሸረሽሩ ናቸው። ስለዚህ ዲናችንን ከቢድዓ ንፅህና ለመጠበቅ፣ ቁርአንንና ሀዲስን በጽናት መያዝ እና በዚያ ላይ መፅናት (ተመሱክ) ብቸኛው የኢማን መገለጫችን ነው።
​⚠️ ከቢድዓ (አዲስ ፈጠራ) እንርቅ!
​በዲን ውስጥ ከእስልምና መሠረት ውጪ የሚደረጉ አዳዲስ ፈጠራዎች ሁሉ ተመላሾች (ውድቅ) ናቸው። የዲናችንን ንፅህና የምንጠብቀው በቁርአንና በሀዲስ ብርሃን ስንጓዝ እና በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መንገድ ላይ ስንፀና ብቻ ነው።
​💡 ልብ ይበሉ፦
ትክክለኛው መንገድ የሰለፎች (የቀደምት ሶሊሆች) መንገድ ነው። አዲስ ፈጠራን በመተው በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና በሶሀባዎች ፈለግ መጓዝ የኩራትና የድል መሠረት ነው
​📌 (የተከበራችሁ ቤተሰቦች በየዓመቱ የሚሰሩትን እና ከዲን ውጪ ያሉ አዳዲስ ፈጠራዎችን በተለይም «ስለመውሊድ» ያለውን ትክክለኛ የሸሪዓ አቋም በቀጣዩ በሰፊው የምንመለከት ይሆናል፤ አብራችሁን ቆዩ!)
Forwarded from Yasin Nuru fan's
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❤️ የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ ❤️

🌙 ሰባኹል ኸይር / ሰባኹል ኑር



📖🎧 #ቁርኣን  || PART ❷❻⓪

⭐️ Yasin Nuru fan's || SHARE 😊
Forwarded from QURAN || قرآن
‏﴿إِنَّ اللَّهَ وَ مَلائِكَتَهُ يُصَلُونَ عَلَى النَّبيِّ يَا أَيُّها الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسلِّمُوا تَسْلِيماً﴾
➽ስለ መውሊድ አራቱ አኢማዎች ምን ብለዋል???
ኢማሙ አህመድ፣ኢማሙ ሻፊ ዒይ፣ኢማሙ ማሊክእና አቡ ኸኒፋ
💫 ኢማሙ አህመድ
ምንም አለሉም።
💫 ኢማሙ ማሊክ
ምንም አላሉም።
💫 ኢማሙ ሻፊዒይ
ምንም አላሉም።
💫 አቡ ኸኒፋ
ምንም አላሉም።

አራቱ አኢማዎች ስለ መውሊድ ምንም አላሉም።
ምክንያቱም
👇
👉በዘመናቸው መውሊድ አልነበረም።።
💫ነብዩ ሰ ዐ ወ አላዘዙበትም።
💫ሰሓባዎች አላከበሩትም።
💫ታቢዒዮች አላከበሩትም።
💫የታቢዒዮች ተከታይ አላከበሩትም።
💫አራቱም አኢማዎች አያውቁትም።

ታድያ
ከየት መጣ❓ማን ጀመረው ❓ መቼ ጀመረው ❓
ለምን ጀመረው ❓
በበላችጭነት ከተመሰከረላቸው ክፍለ ዘመናት በኋላ
ዘግይተው የመጡ "ዑበይዲዩን"ወይም "ፋጢሚዩን"
የሚበሉት የፈጠሩት አዲስ ፈጠራ ነው።
ለዚህም ፈጠራ ምክንያታቸው
"ክርስቲያኖች የዒሳን ልደት ሲያከብሩ እኛ የረሱል ሰ ዐ ወ
ልደት እንዴት አናከብርም?" በሚል ነበር
#እስልምና_ደሞ_በቁርአንና_በሐዲስ_ድንጋጌ
የሚመራ እምነት እንጂ በሰዎች ራዕይ የሚመራ ተቋም አይደለም።።።
👍1
#ታላቁ_ሸይኽ_ኢብኑ_ባዝ_አላህ_ይዘንላቸው_ስለ_መውልድ_ የሚከተለውን ይላሉ
➽የሱና ሰዎች (አህሉ ሱና) መልዕክተኛው ❴ሰ ዐ ወ❵ ከአላህ
ቀጥሎ ከማንም በላይ የተወደዱ እንደሆኑ ያምናሉ።አህሉ ሱናዎች ዘንድ ከማንም በላይ ተወዳጁ አላህ ነው ።በመቀጠል እነሱ ዘንድ ተወዳጁ ነብዩ ❴ሰ ዐ ወ❵ ናቸው።
ከነፍሳቸው፣ከገንዘባቸው፣ከልጆቻቸው፣እንድሁም ከወላጆቻቸው በላይ አስበልጠው ይወዷቸዋል በመቀጠልም ነብያቶችን ያስከትላሉ እኛም በዚህ እምነት ላይ ነን የእነሱን መንገድ እንከተላለን።ከአላህ ቀጥሎ ከማንም በላይ እርሳቸውን እንደምወድ አላህ ምስክር ነው።ከነፍሶቻችን፣ከገንዘቦቻችን፣ከልጆቻችን እንድሁም ከወላጆቻችን በላይ እርሳቸውን አስበልጠን እንደምወድ አላህ ምስክር ነው!!!!!!!

➦በአላህ ይሁንብህ መውልዲን ደንግገውልን በሆነ ኖሮ እኛም እንሰራው ነበር።ወደርሱም እንጣረ ነበር በአላህ ይሁንብን መውልዲን ደንግገውልን በሆና ኖሮ ወደ እርሱ በተጣራን ነበር( እሱን በማክበር ላይ ባዘዝን ነበር)ስለ እርሱም ብዙ ነገሮችን በፃፊን ነበር ነገር ግን አልደነገጉልንም ።አልተገበሩትም ሶሃባዎችም አለከበሩትም።ነገር ግን አሁን አሁን ከመውሊድ የሚከለክል የሚያስጠነቅቅ ሰው የሰዎች ጠላት ተደርጎ ተቆጥሯል።

✔️አላህ ሱናን አስወድዶ አዳዲስ ተግባሮችን ❪ብዳዓን❫ የምንርቅ ያድርገን አሚን!!!!!!
👍1
✔️መውሊድ በዲን ላይ የተጨመረ የፈጠራ ተግባር ነው!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ما من نبيٍّ بَعثَهُ اللهُ في أُمَّةٍ قبْلِي، إلّا كان لهُ من أُمَّتِه حوارِيُّونَ، وأصحابٌ يأخُذونَ بِسنَّتِه، ويَتقيَّدُونَ بأمْرِهِ، ثمَّ إنَّها تَخُلُفُ من بعدِهِمْ خُلُوفٌ، يقولُونَ ما لا يَفعلُونَ، ويفعلُونَ ما لا يُؤْمَرُونَ، فمَنْ جاهدَهمْ بيدِهِ فهوَ مُؤمِنٌ، ومَنْ جاهدَهمْ بِلسانِه فهوَ مُؤمِنٌ، ومَنْ جاهدَهمْ بقلْبِهِ فهوَ مُؤمنٌ، ليس وراءَ ذلكَ من الإيمانِ حبَّةُ خرْدَلٍ﴾

“ከኔ በፊት አላህ የላከው አንድም ነብይ የለም፣ ከህዝቦቹ ሱንናውን የሚይዙ፣ በትእዛዙ የሚጓዙ ሐዋርያትና ባልደረቦች የኖሩት ቢሆን እንጂ፡፡ ከዚያም ከነሱ በኋላ ክፉ ምትኮች ይተካሉ፡፡ የማይሰሩትን ያወራሉ፡፡ ያልታዘዙትን ይፈፅማሉ፡፡ በእጁ የታገላቸው እሱ አማኝ ነው፡፡ በምላሱ የታገላቸውም እሱ አማኝ ነው፡፡ በልቡ የታገላቸውም እሱ አማኝ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የሰና-ፍጭ ፍሬ ታክል ኢማን የለም።”

📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 5790

🟧🟧🟧🟧🟧🟧🟧

🔸 በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

📱 Telegeram 📱 Whatsup

📱 Facebook  📱 Instagram

📱 X 📱 Youtube 📱 Tik tok
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM