ሂዳያ (ቅኑ መንገድ)
172 subscribers
54 photos
40 videos
1 file
78 links
ወደ አላህ መንገድ የምንጣራበት፣ ቁርኣንና ሱናን የምንማማርበት ቻናል ነው። አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን።"
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
اللَّهُ أَكْبَرُ، اللَّهُ أَكْبَرُ، اللَّهُ أَكْبَرُ،

     لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ،

       اللَّهُ أَكْبَرُ، اللَّهُ أَكْبَرُ،

         وللَّهِ الحمد

@Al_Furqan_Islamic_Studio
በያላችሁበት!
~
ዒዱን ሙባረክ!
تقبل الله منا ومنكم
🌙 ለኛ ለሙስሊሞች ኢዳችን ነው!🌙

ረሱል (▫️) እንዲህ ብለዋል፦

‍﴿يومُ عرَفةَ ويومُ النَّحْرِ وأيّامُ التَّشريقِ عِيدُنا- أهلَ الإسلامِ- وهي أيّامُ أكلٍ وشُرْبٍ﴾

“የአረፋ ቀን፣ የእርድ ቀን፣ የተሽሪቅ ቀናቶች ለኛ ለኢስላም ሰዎች ኢዳችን ነው። እነሱ የመብያና የመጠጫ ቀናቶች ናቸው።”

📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ 773

✔️ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️Telegeram 📞 Whatsup

👤Facebook  📸Instagram

💬X 🎥Youtube 🎵Tik tok
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ።

​እንኳን ለዒድ ማግስት (ለሁለተኛው የዒድ ቀን) በሰላም አደረሳችሁ! ትላንትና የበዓሉ የመጀመሪያ ቀን በደስታና በተክቢራ አልፏል። ዛሬ ደግሞ የዒድ ደስታችንን የምንቀጥልበት፣ ወዳጅ ዘመድን የምንጠይቅበትና ዝምድናን የምናጠናክርበት ውብ ቀን ነው።ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም! (አላህ መልካም ስራችንን በሙሉ ይቀበለን!)



​የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዳሉት የዒድ ቀናት የመብያ፣ የመጠጫና አላህን በብዛት ማውሻ ቀናት ናቸው። ስለዚህ ዛሬም ቀናችን በፈገግታ፣ በይቅርታና በአላህ ዚክር የደመቀ ይሁን።
​የዛሬውንም የተባረከ ቀን ከምትወዷቸው ሰዎች ጋር በፍቅርና በሰላም አሳልፉ! 🕌🐑✨
Forwarded from Islamic post
ያ الله እድሉን ላላገኘነውና ልባችን በናፍቆት ለሚቃጠለው በሙሉ በሚቀጥለው ዓመት በታላቁ ዐረፋ ተራራ ላይ የምንቆም አድርገን🥹🤲

@islamic_post17
Forwarded from Islamic post (𝐌𝐔𝐁𝐀 𝐉𝐑)
ለአንድ ባሪያ ምርጡ ቀን ማለት ወደ አላህ ከልቡ የተመለሰበት ቀን ነዉ ይላሉ"

ኢብኑል ጀዉዚ ረሂመሁላህ

@islamic_post17
​🚨 የዘመናችን አደገኛ ፈተና — "ቁርኣኒያህ" (የሐዲስ አስተባባሪዎች) ማንነታቸውና አደገኛ አካሄዳቸው! ⚠️
​بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
ውድ የሂዳያ ቤተሰቦች!
​ዛሬ በዲናችን ላይ በስውርም ሆነ በግልፅ እየተስፋፋ ስላለውና የትውልዱን እምነት እያበላሸ ስላለው "ቁርኣኒያህ" (ቁርኣን ብቻ) ስለሚባለው አደገኛ እሳቤ ጥቂት እንላለን።
​🔍 "ቁርኣኒያህ" (قُرْآنِيَّة) ምንድን ነው?
​ትርጉም፦ "ቁርኣን ብቻ ይበቃል" በማለት የተወዳጁ ነቢያችንን (ﷺ) ትክክለኛ ሐዲሶች ሆነ የቀደምት ሰለፎችን (የሰሓባዎችን፣ የታቢዒዮችንና የታቢዑ አት-ታቢዒንን) አረዳድ ሙሉ በሙሉ ውድቅ የሚያደርግ አፈንጋጭ እሳቤ ነው። ይህንን እሳቤ የሚያራምዱ ሰዎች "ቁርኣኒይ" (قُرْآنِيّ) ይባላሉ።

​📌 የታሪኩ መነሻና የረሻድ ኸሊፋህ ውሸት
​ይህንን እሳቤ በዘመናዊ መልኩ የጀመረው ግብፃዊውና አሜሪካዊው ረሻድ ኸሊፋህ (1933–1990) ነው። ግለሰቡ መጀመሪያ ላይ "እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ" ብሎ አወጀ።
​ዐሊሞች (ሊቃውንት) ቁርኣንን ጠቅሰው፦ "ሙሐመድ (ﷺ) የነቢያት መደምደሚያ (خَاتَمَ النَّبِيِّينَ) ነው" (አል-አሕዛብ፡ 40) ሲሉት፣ እርሱ ግን አሳሳች ምላሽ በመስጠት፦ "ቁርኣኑ 'የነቢያት' አለ እንጂ 'የመልእክተኞች' መደምደሚያ አላለም፣ ስለዚህ እኔ ነቢይ ሳልሆን መልእክተኛ ነኝ" አለ።
​ዐሊሞችም "ነቢይ ሳይሆኑ መልእክተኛ መሆን አይቻልም" በማለት በሐዲስ ሞገቱት።
​💎 እውነታው ከነቢያችን (ﷺ) አንደበት
​ነቢያችን (ﷺ) ከእሳቸው በኋላ ምንም ዓይነት ነቢይም ሆነ መልእክተኛ እንደማይመጣ እንቅጩን ፍርጥ አድርገው ነግረውናል፦
​የመልእክተኛነት መዘጋት፦ ​"በእርግጥም መልእክተኛነትና ነቢይነት ተዘግቷል። ከእኔ በኋላ መልእክተኛም ነቢይም የለም።" (ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ፡ 2272)
​"በእርግጥም መልእክተኛነትና ነቢይነት ተዘግቷል። ከእኔ በኋላ መልእክተኛም ነቢይም የለም።" (ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ፡ 2272)

​ስለ 30ዎቹ ደጃሎች (ቀጣፊዎች) ማስጠንቀቂያ፦ ​"የመጨረሻይቱ ሰዓት አትቆምም፤ ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች (ቀጣፊዎች) ተነስተው ‘እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ’ ብለው ቢናገሩ ቢሆን እንጂ።" (ኢማም ሙስሊም፡ 108) "ከእኔ ኡማህ ውስጥ ሠላሳ የሚያህሉ ቀጣፊዎች ‘ነቢይ ነኝ’ ብለው ይነሳሉ፤ ነገር ግን እኔ የነቢያት መደምደሚያ ነኝ። ከእኔ በኋላ ነቢይ የለም።" (ሱነን አቢ ዳውድ፡ 13)
​"የመጨረሻይቱ ሰዓት አትቆምም፤ ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች (ቀጣፊዎች) ተነስተው ‘እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ’ ብለው ቢናገሩ ቢሆን እንጂ።" (ኢማም ሙስሊም፡ 108)
"ከእኔ ኡማህ ውስጥ ሠላሳ የሚያህሉ ቀጣፊዎች ‘ነቢይ ነኝ’ ብለው ይነሳሉ፤ ነገር ግን እኔ የነቢያት መደምደሚያ ነኝ። ከእኔ በኋላ ነቢይ የለም።" (ሱነን አቢ ዳውድ፡ 13)

​⚠️ የቁርኣኒያዎች ዋና ዋና አደገኛና ክፉ አቋሞች
​እነዚህ አካላት "ቁርኣን የተብራራ ነው፣ ማንም ማብራራት አይገባውም" ይሉና መልሰው ግን እራሳቸው ቁርኣንን እንደፈለጉ ይተረጉማሉ። ጥቂት የማይባሉ አቋሞቻቸው የሚከተሉት ናቸው፦
​የዲን ህግጋትን ማፍረስ፦ ሶላት ወደ ኢባዳ መዳረሻ እንጂ እራሱ ኢባዳ አይደለም ይላሉ።
​የታሪክ ክህደት፦ ተውራት ለሙሳ አልተወረደም፣ እስራኤል ያዕቆብ አይደለም ይላሉ።
​የመጨረሻውን ዘመን ክስተቶች መካድ፦ ዒሳ (ዐ.ሰ) ሆነ መሲሁድ-ደጃል አይመጡም፣ ዒሳ በአካል አላረገም ይላሉ።
​የስነ-ምግባር ብልሽት (ኢኽቲላጥ)፦ ወንድና ሴትን በትምህርት፣ በጉባኤና በአምልኮ ቦታዎች ላይ ያለምንም ገደብ ደባልቆ ማስተማርን (ኢኽቲላጥን) ያስፋፋሉ።
​💡 የዛሬው የሂዳያ መልዕክት ምክር፦
ይህ አደገኛ ፈሳድ (ብልሽት) በሀገራችንም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጭንብሉን አውልቆ በግልፅ እየተስፋፋ ይገኛል። እኛ ይህንን የምናስጠነቅቀው ትውልዱ ከእሳት እራትነት እንዲድን እንጂ የሰዎችን ግላዊ ስብዕና ለመንካት አይደለም። አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በዚህ እሳቤ የተጠለፉትን አላህ ሂዳያውን ይወፍቃቸው፤ እኛንም ከቁርኣኒያህ ፈሳድና ኒፋቅ (መናፍቅነት) ይጠብቀን! አሚን።
​✍️ ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
🌐 [https://t.me/Wahidcom]
​📢 የቻናላችን መልዕክት፦
🌐 [https://t.me/Hidaya_Path]
ባለፈው መልዕክታችን ስለ "ቁርኣኒያህ" አደገኛ እሳቤ መነጋገራችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ በኡማው ውስጥ የራሳቸውን የተሳሳተ ፈለግ በማስፋፋት ላይ ስለሚገኙት ስለ "ኢኽዋን" እና "አሕባሽ" ቡድኖች የታላላቅ የሱና ዐሊሞች (እንደ ሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ/ለጅናህ፣ ሼኽ ቢን ባዝ እና ሌሎችም) የሰጡትን ማብራሪያ በአጭሩ እናካፍላችኋለን።
ስለ "ኢኽዋኑል ሙስሊሚን" ቡድን በሰፊው
​🚨 የኢኽዋኑል ሙስሊሚን (የአንጃው) ታሪክ፣ ስውር አካሄድና አደገኛ ስህተቶች በሰፊው! ⚠️
​بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
ውድ የሂዳያ ቤተሰቦች!
​ዛሬ በዓለማችን ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ካላቸውና በርካታ ወጣቶችን በስሜት ከመሰረቱት የሱና መስመር ካራቁ አንጃዎች መካከል ስለ "ኢኽዋኑል ሙስሊሚን" ቡድን በሰፊው እንመለከታለን።
​🔍 1. መነሻና መስራቹ
​ይህ ቡድን በ1928 ዓ.ም (እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር) በግብፅ ሀገር በሐሰን አል-በና አማካኝነት የተመሰረተ ድርጅት ነው። መጀመሪያ ላይ የዳዕዋና የማህበራዊ ስራዎች መልክ ይዞ ቢነሳም፣ ዋናውና ትልቁ ግቡ ግን ፖለቲካዊ ስልጣን ላይ መውጣትና መንግስትን መቆጣጠር ነው።
​🛑 2. የታላላቅ ዐሊሞች ፈትዋ (ፍርድ)
​የሳውዲ አረቢያ ታላላቅ ዐሊሞች ምክር ቤት (ለጅናህ አድ-ዳኢማህ)፣ ሼኽ አብዱልዓዚዝ ቢን ባዝ፣ ሼኽ አልባኒ እና ሼኽ ሷሊህ አል-ፈውዛንን ጨምሮ በርካታ ሊቃውንት ይህንን ቡድን በተመለከተ ግልፅ መግለጫ አውጥተዋል። ዐሊሞቹ እንዲህ ይላሉ፦
​"ኢኽዋኑል ሙስሊሚን አህሉስ ሱናን ወል ጀማዓን አይወክሉም፤ ይልቁኑ ስልጣን ለማግኘት ሲሉ ዲንን የሚጠቀሙ፣ ኡማውን የሚከፋፍሉና ከቀጥተኛው መንገድ የወጡ አፈንጋጭ አንጃዎች ናቸው።"

​⚠️ 3. ዋና ዋና አደገኛ ስህተቶቻቸው (በሰፊው)
​ተውሂድን ችላ ማለት (ቅድሚያ አለመስጠት)፦ ነቢያት በሙሉ (ኑህ፣ ኢብራሂም፣ ሙሳ፣ ዒሳና ሙሐመድ ﷺ) ጥሪያቸውን የጀመሩት "አላህን በብቸኝነት አምልኩ፣ ጣዖታትን ራቁ" በሚለው በተውሂድ ስራ ነው። ኢኽዋኖች ግን ለፖለቲካ ጥንካሬ ሲሉ ሰዎችን በአቂዳ (በእምነት) ላይ ከማንጽ ይልቅ ስብስብና ቁጥር ላይ ያተኩራሉ። በውስጣቸው ቀብር የሚያመልኩ፣ የቢድዓ ባለቤቶችና የተሳሳተ አቂዳ ያላቸው ሰዎች ቢኖሩም ዝም ይላሉ።
​የ"አል-በና" መርህ (የአቂዳ መደባለቅ)፦ መስራቻቸው ሐሰን አል-በና ያስቀመጠው አንድ አደገኛ መርህ አለ፦ "ባስማማን ነገር ላይ አብረን እንሰራለን፣ ባልተስማማንበት ላይ ይቅርታ እንደራረጋለን" ይላል። ይህ መርህ የሱናንና የቢድዓን መስመር ያጠፋል፤ ለስልጣን ሲባል ከአንጃዎች ሁሉ ጋር (ከሺዓዎችም ጭምር) ጥምረት እንዲፈጥሩ በር ከፍቷል።
​ወጣቶችን በስሜት መንዳትና ማክፈር (ተክፊር)፦ በኢኽዋን አስተሳሰብ ውስጥ ካደጉት መካከል እንደ ሰይድ ቁጥብ ያሉ ፀሃፊዎች ሙስሊም ማህበረሰቦችንና መሪዎችን በጅምላ "ጃሂሊያ" (ከእስልምና የወጡ) አድርገው በመግለጻቸው፣ በዘመናችን ላሉት አክራሪና ተዋጊ (ኸዋሪጅ) ቡድኖች መፈልፈያ ሰበብ ሆኗል።
ይቀጥላል....
​⚠️ በጅምላ "ሙብተዲዕ" የማለትን በሽታ በተመለከተ — የታላላቅ የሱና ዐሊሞች ምክርና መመሪያ! 🚨

سْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

​ውድና የተከበራችሁ የሂዳያ ቤተሰቦች!
​ዛሬ በዳዕዋው መስክ ላይ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚታይ አንድ እጅግ አደገኛና ስውር ፈተና አለ። እርሱም፦ በጥናት፣ በማስረጃና በዐሊሞች ፈትዋ ላይ ያልተመሰረተ፣ ሰዎችን በጅምላ "ሙብተዲዕ" (የቢድዓ ሰው) ወይም "ሙመይዕ" እያሉ ስም የማጥፋትና የመክፈል አባዜ ነው።
​አንዳንዶች "ከእገሌ ጋር አውርተሃል፣ እገሌን አልተቃወምክም፣ ስለዚህ አንተም ሙብተዲዕ ነህ" በማለት ሰንሰለታማ ፍረጃ ውስጥ ይገባሉ። ይህ አካሄድ የሰለፎች መንገድ ሳይሆን የበቅሎ ፍልስፍና ነው።
​📌 1. የሰለፎች (የቀደምቶች) ሚዛናዊ መርህ 💎
​የሰለፎች መንገድ ሰዎችን በማውገዝ ላይ የተቸኮለ ሳይሆን እውነትን በማውጣትና ሰዎችን በመምከር ላይ የተመሰረተ ነው። ታላቁ ሊቅ ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
​"አህሉስ ሱናህ ማለት እውነትን የሚያውቁና ለሰዎች ደግሞ እጅግ አዛኝ የሆኑት ናቸው።"


​አንድን ሙስሊም ወይም የሱና ሰውን ከሱና ክበብ ማስወጣት (ተብዲዕ ማድረግ) የሰፈር ጉልበተኝነት ሳይሆን የታላላቅ ዐሊሞችና የሸሪዓ ፍርድ ቤት ስራ ነው።
​🔍 2. የሰንሰለታማ ፍረጃ (ማንኪያ) አደጋ
​"የሙብተዲዕ ጓደኛ ሙብተዲዕ ነው፣ እሱን ያልተከላከለ ሙብተዲዕ ነው..." እያሉ ሰንሰለት መዘርጋት ኡማውን የሚበትን ከንቱ ስራ ነው። ነቢያችን (ﷺ) ሰዎችን ያለ አግባብ ስም ከመስጠትና ከመወንጀል አስጠንቅቀውናል፦
​"አንድ ሰው ወንድሙን 'አንተ ካፊር/ፋሲቅ' ቢለውና ወንድሙ ያ ካልሆነ፣ ንግግሩ ወደ ተናጋሪው ይመለሳል።" (ቡኻሪና ሙስሊም)


​🤝 3. የነቢያዊው መንገድ (ዳዕዋ) አላማ
​የዳዕዋ አላማ ሰዎችን ወደ ጀሀነም መግፋትና ስም መለጠፍ ሳይሆን፣ ሰዎችን በጥበብና በመልካም ምክር ወደ ቀጥተኛው መንገድ (ሂዳያ) መመለስ ነው።
​ስህተት ያለበት ሰው ካለ ተለይቶ ይመከራል እንጂ ስሙ አይጠፋም።
​ከአንድ ሰው ጋር መገናኘት ወይም መወያየት በራሱ ያንን ሰው መምሰል አይደለም፤ ነቢያችንም (ﷺ) ካፊሮችንና ሙናፊቆችን ጭምር ይመክሩና ያነጋግሩ ነበር።
​💡 የዛሬው የሂዳያ መልዕክት ማጠቃለያ፦
ወንድሞችና እህቶች! በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስም በማጥፋት ራሳችሁን የአላህ ፍርድ ቤት አታድርጉ። የሂሳብ ቀን አውቆም ይሁን ሳያውቁ በሰዎች ስም ላይ ለቀጠፉት ጥያቄ አለው።
​አላህ ምላሳችንን የሰዎችን ስጋ ከመብላት (ከማማት) ይጠብቅልን! እውነትን አውቀው በሱና ላይ የሚፀኑ፣ ሰዎችንም በፍቅርና በእውቀት ወደ ዲን የሚጠሩ ያድርገን። አሚን።
​"መልካምን ነገር ያመለከተ ሰው ልክ እንደሰራው ሰው አጅር አለው።" (ነቢያችን ﷺ)
እርስዎም ይህንን ትምህርታዊ መልዕክት ሼር በማድረግ የኡማውን አንድነት ይጠብቁ!
​የአላህ ሰላምና እዝነት በእናንተ ላይ ይሁን! 🕌✨
​🌐 [https://t.me/Hidaya_Path]
Forwarded from Islamic post
የአሹራ ቀን ፆም!

ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
﴿صيامُ يومِ عاشوراءَ، إنِّي أحتَسِبُ على اللَّهِ أن يُكَفِّرَ السَّنةَ الَّتي قبلَهُ﴾

“የአሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አመት ኃጢአት እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ።”
ሙስሊም ዘግበውታል: 1162



በሌላ ሀዲስ
ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
﴿فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ - إِنْ شَاءَ اللَّهُ - صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ﴾

“የሚቀጥለው ዓመት ከደረስኩ በአላህ ፍቃድ የአሹራን ቀን ፆም ዘጠነኛውን ጨምሬ እፆማለሁ።”
ሙስሊም ዘግበውታል: 1134


➲ ዘጠነኛው ቀን እሮብ 17/10/2018
➲ አስረኛው ቀን ሀሙስ 18/10/2018

አላህ በሰላም አድርሶን ከሚፆሙ ያድርገን



@Islamic_post17
👍1
ታላቅ መንፈሳዊ የዳዕዋ ፕሮግራም — እንዳያመልጥዎ! 📢🕋
​بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
​ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ ۖ وَجَادِلْهُم بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِالْمُهْتَدِينَ
​"ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የኾኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው፡፡" (አል-ነሕል: 125)

​ውድና የተከበራችሁ የኢስላም ልጆች! የሂዳያ ቻናል ተከታዮችና የመላው ሙስሊም ኡማ በሙሉ!
​ልባችን በኢማን ብርሃን የሚታደስበት ዕውቀታችን የሚጨምርበትና ከመንፈሳዊው ማዕድ የምንቋደስበት እጅግ ታላቅና ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቆታል የወቅቱን ፈተናዎች የምንመክትበትና ወደ አላህ የምንቃረብበት ውብ ዕለት!
​🎙️ የዕለቱ የተከበሩ እንግዶቻችን (ኡስታዞች)
1️⃣ ሼኽ ሀሩን ጡምሶ
2️⃣ ኡስታዝ ረህመቶ ሱካሮ
3️⃣ ኡስታዝ ሸምሱዲን ጀማል
4️⃣ ኡስታዝ አቡ ረኡፍ ናስር
(+ ስማቸው ያልተጠቀሱ ሌሎች ታላላቅ መሻኢኾችና ኡስታዞች ይገኛሉ)
​📌 የፕሮግራሙ ዋና ዋና ይዘቶች፦
💎 ልብን የሚያርሱና መንፈስን የሚያድሱ ድንቅ ዳዕዋዎች
❓ ወቅታዊና አንገብጋቢ ለሆኑ ጥያቄዎች ምላሾች
🤝 የወንድማማችነትና የእህትማማችነት ልዩ መድረክ
​📅 የፕሮግራሙ አድራሻና ሰዓት
📍 ቦታ በፎንቆ ከተማ  በኡመቲ ኡመቲ መስጅድ
📆 ቀን፦ እሁድ ሰኔ 21 ቀን (21/10/2018 ዓ.ል)
⏰ ሰዓት ከጠዋቱ ጀምሮ
​💡 ማሳሰቢያ
​ለሴት እህቶቻችንም በቂና ምቹ ቦታ ተዘጋጅቷል
​መሪ ቃል፦ ተውሂድ የነቢያት መንገድ ነው
​አዘጋጅ አስሃቡል የሚን እስላማዊ ማህበር
​መልካምን ነገር ያመለከተ ሰው ልክ እንደሰራው ሰው አጅር አለው።" (ነቢያችን ﷺ)
​ስለዚህ ይህንን መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ በፌስቡክ (FB)፣ በቴሌግራም (TG)  ላይ ሼር (Share) በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ! እርስዎም ቀድመው ቦታዎን ይያዙ።
​የአላህ ሰላምና እዝነት በእናንተ ላይ ይሁን! 🕌✨
Forwarded from DEEN MODE
Audio
ጁመዓ የእዝነትና የበረከት ዕለት ✨
​بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
​"ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ፤ ነገሬንም አግራልኝ።" (ጧሃ፡ 25-26)
​ውድና የተከበራችሁ የኢስላም ልጆች!
​ሳምንቱን ሙሉ በዱንያ ሩጫ የደከመው ልባችን በዱዓ፣ በዚክርና በሰለዋት የሚታደስበት፣ የወንጀል ማጠቢያ የሆነው ታላቁ የጁመዓ ዕለት መጣ። አላህ ካደረሰን ምርጥ ቀናት መካከል።
​📌 በዚህ በተባረከ ዕለት ልንገበያይባቸው የሚገቡ ትርፋማ ስራዎች፦
​📿 በነቢያችን (ﷺ) ላይ ሰለዋት ማብዛት፦ “በጁመዓ ዕለት በእኔ ላይ ሰለዋትን አብዙ፤ እርሱ እኔ ዘንድ ይቀርባልና።” (ሐዲስ)
​📖 ሱረቱል ካህፍን መቅራት፦ ከዚህ ጁመዓ እስከ ቀጣዩ ጁመዓ ድረስ ያለውን ህይወታችንን በብርሃን ይሞላዋል።
​🤲 የዱዓ ተቀባይነት ሰዓትን መጠባበቅ፦ በተለይ ከአስር በኋላ ባሉት ውብ ሰዓታት ዱዓችንን ማበርከት።
​አላህ በዚህ በተባረከ ቀን ዱዓችንን የሚቀበል፣ ጭንቀታችንን የሚያቀል፣ ህመማችንን የሚፈውስ እና ሀገራችንን ሰላም የሚያደርግልን ያድርገን።
​መልካም፣ የተባረከ እና የሰላም ጁመዓ ይሁንላችሁ! 🕋✨
​"መልካምን ነገር ያመለከተ ሰው ልክ እንደሰራው ሰው አጅር አለው።" (ነቢያችን ﷺ)
ይህንን የጁመዓ ስጦታ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር (Share) በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!
​🌐 [https://t.me/Hidaya_Path]
Forwarded from Islamic post
ሕይወትህ ግራ ሲጋባብህና መውጫው ሲጠፋህ ጥበብን ፍለጋ ወደ ሰው አትሩጥ፤ ይልቁኑ ጥበበኛ ከሆነው አላህ ወደ ወረደው ቁርኣን ተመለስ

እያንዳንዱ አንቀጽ ለልብህ ፈውስና መመሪያ አድርገው


@Islamic_post17
❤2
Forwarded from Al-Fattah_Media🕊
🌱 ምናልባት እኮ ከአላህ ያራቀህ ምንም ትኩረት ያሰጠሃት ትንሽ ወንጀል ትሆናለች !

•
Forwarded from Al-Fattah_Media🕊
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

"የአላህን ውሳኔ ምንም አይመልሰውም (ዱዓእ) ቢሆን እንጂ ፤ ዕድሜም አይጨምርም 'በመልካም' ስራ ቢሆንጂ።
     
     ☘ቲርሚዚ ዘግበውታል (2139)
Forwarded from Zeynu 🖤
​🚸 "ልጆቻችንን በኢስላማዊ ተርቢያ እናሳድግ! — ከዛሬው የጁመዓ ኹጥባ የተወሰደ መልዕክት" ✨
​بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
​ውድ የቻናላችን ተከታዮች!
​ልጆች አላህ በእጃችን ላይ ያስቀመጣቸው ትልቅ አደራዎች (አማና) ናቸው። ነገ በአላህ ፊት የምንጠየቅበት የነገው ኡማችን መሠረቶች በመሆናቸው፣ ዛሬ ላይ የምንሰጣቸው ተርቢያ (አስተዳደግ) የህይወታቸውን አቅጣጫ ይወስነዋል።
​ነቢያችን (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
​“ሁላችሁም እረኞች ናችሁ፤ እያንዳንዳችሁም በምትጠብቁት ነገር (አደራ) ትጠየቃላችሁ። ሰውየው በቤተሰቦቹ ላይ እረኛ ነው፤ በእነሱም ይጠየቃል።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

​📌 ዛሬ ለልጆቻችን ቀድመን ልናስተምራቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነገሮች፦
​☝️ ስለ አላህ ታላቅነትና ተውሂድ፦ ልክ ታላቁ ሉቅማን ልጃቸውን "ልጄ ሆይ! በአላህ ላይ አታሻርክ" ብለው እንደመከሩት፤ በልጆቻችን ልብ ውስጥ መጀመሪያ የአላህን ፍቅር፣ ፍርሃትና ታላቅነት መዝራት አለብን።
​💚 ስለ ነቢያችን (ﷺ) ማንነትና ሱና፦ ስለ ውቡ ስነ-ምግባራቸው፣ ስለ እዝነታቸውና ስለ አስተማሪነታቸው በመንገር የእሳቸውን ፈለግ እንዲከተሉና እንዲወዱ ማድረግ።
​⚔️ ስለ ሰሓባዎች ጀግንነትና ታሪክ፦ ዛሬ ልጆቻችን የዱንያ ሰዎችንና የፊልም ገጸ-ባህሪያትን አርአያ (Role Model) ከማድረግ ይልቅ፣ የዲን ባለውለታ የሆኑትን የሰሓባዎችን ታሪክና ጀግንነት እያወቁ እንዲያድጉ ማስተማር።
​💎 ስለ እውነትና እውነተኝነት፦ ከውሸትና ከማታለል የጸዳ፣ ሁልጊዜም እውነትን የሚናገርና በታማኝነት የሚራመድ ትውልድ እንዲሆኑ በተግባር ማሳየት።
​ውድ ወላጆችና ታላላቆች ሆይ!
ልጆችን በቁሳቁስና በዱንያ ትምህርት ብቻ ማርካት ተርቢያ አይደለም። እውነተኛው ስኬት በዲን ኮትኩቶ፣ በጥሩ አህላቅና በተቅዋ ማሳደግ ነው። ዛሬ የምንዘራው መልካም ዘር፣ ነገ ለእኛም የአኺራ ሰደቃ ጃሪያ (የማይቋረጥ አጅር) ይሆንልናል።
​አላህ ልጆቻችንን የዓይናችን ማረፊያ፣ የኢስላም ጋሻና የሱና አርበኞች ያድርግልን! አሚን።
​"መልካምን ነገር ያመለከተ ሰው ልክ እንደሰራው ሰው አጅር አለው።" (ነቢያችን ﷺ)
ይህንን ወሳኝ የኹጥባ ማስታወሻ ለሁሉም ወላጆች ሼር (Share) በማድረግ የአደራችንን ክብደት እናሳስብ!
​🌐 [https://t.me/Hidaya_Path]
​📚 "የዕውቀት ልቅና እና የኡለማዎች ክብር! — ከዛሬው የጁመዓ ኹጥባ የተወሰደ መልዕክት" 💎
​بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
​ውድ የቻናላችን ተከታዮች!
​ዛሬ በተደረገው የጁመዓ ኹጥባ ላይ፣ ዲናችን እስልምና ለዕውቀትና ለዓሊሞች የሰጠውን እጅግ ከፍ ያለና የማይነጥፍ ክብር በጥልቀት ተመልክተናል። ዕውቀት የልብ ብርሃን፣ ዓሊሞች ደግሞ የዚህ ኡማ መብራቶች ናቸው።
​አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣኑ ላይ አዋቂዎችና አላዋቂዎች በፍጹም እኩል ሊሆኑ እንደማይችሉ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦
​“በል፦ እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ እኩል ይሆናሉን? የሚገሰጹት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው።” (አል-ዙመር፡ 9)

​📌 ከዛሬው ኹጥባ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች
​👑 ዓሊሞች የነቢያት ወራሾች ናቸው፦ ነቢያችን (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ “ዓሊሞች (የዕውቀት ባለቤቶች) የነቢያት ወራሾች ናቸው ነቢያት ዲናርንም ሆነ ድርሃምን አላወረሱም፤ ያወረሱት ዕውቀትን ብቻ ነው። ይህንን ዕውቀት የያዘ ሰው ታላቅ ዕድልን አገኘ (አቡ ዳውድና ቲርሚዚ)
​🛑 የኡለማዎችን ክብር መጠበቅ ዛሬ ላይ በሶሻል ሚዲያም ሆነ በተለያየ መድረክ የዲን ዓሊሞችን ማጥላላት ስም መስጠትና መሳደብ አደገኛ መርዝ ነው የሰለፎች መንገድ ዓሊሞችን ማክበርና እውቀታቸውን መቅሰም ነው
​🚨 የመጨረሻው ታላቅ አደራ (ለወላጆች) የዱንያ ትምህርት ብቻውን ለልጆቻችን በቂ አይደለም! ልጆቻችን የዶክተርነት የኢንጂነርነት ወይም ሌላ የዱንያ ክብር ላይ ቢደርሱ እንኳ የዱንያው ትምህርት ከአኺራ ጥፋት ሊያድናቸው አይችልም ቀድመን ዲናቸውን ተውሂዳቸውንና ሱናን ልናስተምራቸው ግድ ይላል
​ውድ ወላጆች ሆይ!
ልጆቻችንን የአላህን መንገድ ሳናስተምር ሶላትና ስነ-ምግባር ሳይኖራቸው ለዱንያ ስኬት ብቻ መጣር አደራን ማጉደል ነው ነገ በአላህ ፊት እንዳናፍር ዛሬውኑ ልጆቻችንን በዲን እውቀት እንኮትኩታቸው
​አላህ እውነተኛውን እውቀት ጨምሮልን በተግባር የምንውል ያድርገን! ዓሊሞቻችንን ይጠብቅልን ልጆቻችንንም የዲን አርበኞች ያድርግልን አሚን
​"መልካምን ነገር ያመለከተ ሰው ልክ እንደሰራው ሰው አጅር አለው። (ነቢያችን ﷺ)
ይህንን ወሳኝ የጁመዓ መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር (Share) በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!
https://t.me/Hidaya_Path
Forwarded from Islamic post
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምሽት ሽንቅ🫀

​اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ
اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد

القارئ الشيخ علاء بن ابراهيم المزجاجي
Instagram ➲3ala_mizjaji
🥰1
​🤝 "እውነተኛ ጓደኛ — የዱንያ ስንቅ፣ የአኺራ ጥላ!" ✨

​بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

​ውድ የቻናላችን ተከታዮች!

​በዚህች ፈታኝ በሆነች የዱንያ ህይወት ውስጥ፣ ከእውነተኛ እና ለአላህ ብሎ ከሚወድ ጓደኛ (ሶሊህ ጓደኛ) የበለጠ ትልቅ ጸጋ የለም። እውነተኛ ጓደኛ ማለት በሳቅና በደስታ ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ በችግርና በጭንቀት ሰዓት ከጎንህ የማይጠፋ ነው።

​ነቢያችን (ﷺ) ስለ ጓደኛ ምርጫ ሲመክሩን እንዲህ ብለዋል፦

​“ሰውየው በጓደኛው ዲን (መንገድ) ላይ ነው፤ ስለዚህ አንዳችሁ ማንንም ጓደኛ እንደሚያደርግ ይመልከት።” (አቡ ዳውድና ቲርሚዚ)


​📌 የእውነተኛ ጓደኛ መገለጫዎች፦
​☝️ አላህን ያስታውሰሃል፦ ስትዘናጋ ወደ አላህ መንገድ ይመልስሃል፤ ለኸይር ስራ ያነሳሳሃል።​
🛡️ ነውርህን ይሸፍናል፦ ስህተትህን በግልጽ አደባባይ ላይ ከማውጣት ይልቅ፣ በምስጢርና በእዝነት ይመክርሃል

​🤲 በዱዓ አይረሳህም፦ በህይወትህም ሆነ ከሞትክ በኋላ፣ በሩቅ ሆኖ ለአንተ ዱዓ ያደርግልሃል
​🤝 እስከ አኺራ አብሮህ ይጓዛል፦ ጓደኝነቱ ለዱንያ ጥቅም ሳይሆን ለአላህ ብሎ ስለሆነ፣ በቂያማ ቀን በአላህ ጥላ ስር አብረው ከሚሆኑት ውስጥ ያደርጋችኋል

​ታላቁ ሊቅ ሐሰኑል በስርይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦

​አማኝ የሆኑ ጓደኞችን ያብዛ፤ ምክንያቱም በቂያማ ቀን (አላህ ሲፈቅድላቸው) ምልጃ (ሸፋዓ) ያደርጋሉና


​ወንድም እህቶቼ ሆይ! የያዝናቸውን ጓደኞች እንመርምር ወደ ጀነት የሚጎትተን ጓደኛ ካለን አጥብቀን እንያዘው ምክንያቱም እውነተኛ ጓደኛ ማግኘት ከባድ ነውና።

​አላህ (ሱ.ወ) ለአላህ ብለው ከሚዋደዱት በመልካም ከሚተጋገዙትና በጀነተል ፊርደውስ አብረው ከሚገቡት ያድርገን! አሚን

​"መልካምን ነገር ያመለከተ ሰው ልክ እንደሰራው ሰው አጅር አለው።" (ነቢያችን ﷺ)

ይህንን መልዕክት ለምትወዱትና አብሯችሁ ጀነት እንዲገባ ለምትመኙት እውነተኛ ጓደኛ ሼር (Share) በማድረግ ፍቅራችሁን ግለጹ!

​🌐 [https://t.me/Hidaya_Path]