Health Science Library
1.34K subscribers
238 photos
204 files
41 links
For any fields of Health Science, Giudelines,Books,Lecture notes and Research PDFs are available Here.
Download Telegram
Malaria 2022.pdf
4.1 MB
Share Malaria 2022.pdf
❤2
የኮንዶም ዋና ዋና ጥቅሞችን ያውቃሉ ?


1. በግብረሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን (STIs) መከላከል

ኮንዶም በግንኙነት ወቅት ከሰውነት የሚወጡ ፈሳሾች እና የቆዳ ንክኪን ስለሚገታ የሚከተሉትን በሽታዎች ለመከላከል አስተማማኝ መንገድ ነው፦

✔ ኤች.አይ.ቪ (HIV/AIDS)

✔ ቂጥኝ (Syphilis)፣ ጨብጡ (Gonorrhea) እና ክላሚዲያ (Chlamydia)

✔ የብልት ኪንታሮት (HPV) እና የብልት ሄርፒስ (Herpes)

2. ያልተፈለገ እርግዝናን መከላከል

ኮንዶም በትክክል ከተጠቀሙበት ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል በጣም ውጤታማ ከሆኑ የእርግዝና መከላከያ መንገዶች አንዱ ነው። የወንድ የዘር ፍሬ (Sperm) ወደ ማህፀን እንዳይገባ ሙሉ በሙሉ ይከላከላል።

3.ሁለት ጥቅም ጥበቃ (Dual benefits ) መስጠቱ ፦

ሌሎች የእርግዝና መከላከያዎች (ለምሳሌ ክኒን፣ መርፌ ወይም የምጥን መርፌ) እርግዝናን ብቻ ነው የሚከላከሉት። ኮንዶም ግን እርግዝናን እና የአባላዘር በሽታዎችን በአንድ ላይ መከላከል የሚችል ብቸኛው ዘዴ ነው።

4. ከሆርሞን የጎንዮሽ ጉዳት (Side Effects) ነፃ መሆኑ

እንደ መርፌ ወይም ክኒን ያሉ መከላከያዎች በሴቶች አካል ውስጥ የሆርሞን መዛባትን ሊፈጥሩ ይችላሉ። ኮንዶም ግን ምንም ዓይነት የሆርሞን ኬሚካል ስለሌለው ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት አያመጣም።

5. የአእምሮ ሰላም እና መረጋጋት መስጠቱ

ስለ እርግዝና ወይም ስለ በሽታ መያዝ የሚኖረውን ስጋት እና ጭንቀት ስለሚቀንስ፣ ሁለቱም ተጓዳኞች ሙሉ በሙሉ ተረጋግተው እና ተዝናንተው ግንኙነት እንዲያደርጉ ይረዳል።

6. በቀላሉ እና በቅናሽ ዋጋ መገኘቱ

ኮንዶምን ለማግኘት የሐኪም ማዘዣ (Prescription) አያስፈልግም። በግል ፋርማሲዎች በቀላል ዋጋ ፣ በመንግሥት የጤና ተቋማት ደግሞ በነጻ ማግኘት እየተቻለ ብዙዎች ግን በቸለልተኝነት ሳይጠቀሙ ይቀራሉ።


ማሳሰቢያ ፦
እነዚህን ጥቅሞች ሙሉ በሙሉ ለማግኘት ኮንዶሙ ሳይበላሽ (ኤክስፓየር ሳያደርግ)፣ በትክክለኛ መንገድ እና ከግንኙነቱ መጀመሪያ ጀምሮ ጥቅም ላይ መዋል አለበት።

መረጃው ጠቃሚ ሁኖ ካገኙት ለጓድኛዎ share ያድርጉ ።
❤1
Forwarded from Health Science Library
Information Guide for Students.pdf
3.6 MB
Share Information Guide for Students.pdf
የሚገበውን የAdvertise Bot አትንኩት፤ እለፉት።
❤1
🫀 #የደረት_ህመም

✌️ የደረት ህመም በራሱ በሽታ ሳይሆን የተለያዩ ችግሮች ምልክት ነው።
✌️ህመሙ ከልብ፣ ከሳንባ፣ ከጡንቻና አጥንት፣ ከሆድ/የምግብ መተላለፊያ ወይም ከጭንቀት ሊመጣ ይችላል።
#ምክንያቶች

👉👉❤️ ከልብ የሚመጣ ህመም (Angina )
የልብ ጡንቻ በቂ ደምና ኦክሲጅን ሳያገኝ ይከሰታል። ብዙ ጊዜ በመራመድ፣ በመሮጥ ወይም በከባድ ስራ ጊዜ ይጀምራል፤ እረፍት ሲደረግ ሊቀንስ ይችላል።
📌📌Heart attack (Myocardial infarction) ግን የልብ ደም ስር በመዘጋቱ የልብ ጡንቻ ክፍል መጎዳት ነው። ከባድ የደረት መጫን/መጨናነቅ፣ ላብ፣ ማቅለሽለሽ፣ ድካም እና ህመሙ ወደ እጅ፣ ጀርባ፣ አንገት ወይም መንጋጋ መስፋፋት ሊኖር ይችላል።
👉👉🫁 ከሳንባ የሚመጣ
እንደ ሳንበ ምች፣ የሳንብ ሽፋን መቆጣት ፣ በሳንባ ከረጢት ውስጥ ደም ፣ አየር መከማቸት እና የሰንባ ደም መላሸ መሰመሮቾ መዘጋት ያሉ ችግሮች የደረት ህመም ሊያመጡ ይችላሉ።
በተለይ ህመሙ በጥልቅ መተንፈስ ወይም በሳል ሲባባስ ከሳንባ/pleura ጋር የተያያዘ መሆኑ ሊጠረጠር ይችላል።
👉👉💪 ከጡንቻና ከደረት ግድግዳ
ከባድ ስራ፣ እቃ መሸከም፣ ስፖርት ወይም ጉዳት በኋላ የደረት ጡንቻ ሊወጠር ይችላል። Costochondritis ደግሞ የጎድን አጥንትና የደረት አጥንት መገናኛ አካባቢ እብጠት/ህመም ነው።
እንዲህ ዓይነቱ ህመም በመንካት ወይም በአንዳንድ እንቅስቃሴ ሊባባስ ይችላል።
👉👉🔥 ከሆድ አሲድ — GERD
የሆድ አሲድ ወደ የምግብ መተላለፊያ ሲመለስ የደረት ማቃጠል (heartburn) ሊያመጣ ይችላል። ብዙ ጊዜ ከምግብ በኋላ፣ በመተኛት ጊዜ ወይም በመጎንበስ ይባባሳል።
👉👉😟 ከጭንቀት ወይም panic attack
ከፍተኛ ጭንቀት የደረት መጨናነቅ፣ ፈጣን የልብ ምት፣ መንቀጥቀጥ፣ ላብ እና እስትንፋስ እንደሚያጥር ስሜት ሊያመጣ ይችላል። ነገር ግን የደረት ህመምን በቀጥታ በጭንቀት ላይ ማስቀመጥ አይገባም—በተለይ ከባድ የልብ ወይም የሳንባ ችግር ምልክቶች ካሉ።

🚨 #መቼ_አስቸኳይ_ነው?

🎤🎤የደረት ህመም፦

🚫በድንገት ከጀመረ
🚫ከባድ መጨናነቅ/መጫን ከሆነ
🚫ወደ እጅ፣ ጀርባ፣ አንገት ወይም መንጋጋ ከተሰራጨ
🚫ከእስትንፋስ ማጣት ጋር ከሆነ
🚫ከብዙ ላብ፣ ማቅለሽለሽ፣ ማዞር ወይም ራስን መሳት ጋር ከሆነ አስቸኳይ የህክምና ምርመራ ያስፈልጋል።
💊 #መፍትሔውስ?

👉👉የደረት ህመም ሁሉ በአንድ መድሀኒት አይታከምም። መጀመሪያ ምክንያቱን መለየት ነው ዋናው ነገር። ለምሳሌ GERD ከሆነ የአሲድ መቀነሻ ህክምና ሊሰጥ ይችላል፤ የጡንቻ ህመም ከሆነ የተለየ አቀራረብ ይፈልጋል፤ የልብ ድንገተኛ ጥቃት ግን አስቸኳይ የሆስፒታል ህክምና ይፈልጋል።
ስለዚህ “የደረት ህመም አለኝ” ብቻ በመስማት መድሀኒት መጀመር አይገባም። የህመሙ ቦታ፣ ባህሪ፣ መጀመሪያ ጊዜ፣ ከእንቅስቃሴ/ምግብ/መተንፈስ ጋር ያለው ግንኙነት እና ተያያዥ ምልክቶች መጠየቅ ያስፈልጋል።

#ሌሎችም_ያጋሩ
❤1
ስለ CGPA እና GPA አሰራር ማብራሪያ

ብዙዎች እንደሚሳሳቱት፣ Cumulative GPA (CGPA) ማለት የ-1st Semester እና የ-2nd Semester Gpaን ደምሮ ለሁለት ማካፈል ማለት አይደለም።❌

የትኛውም የGPA ስሌት የሚሰራው ተማሪው በወሰዳቸው አጠቃላይ Credit Hours ብዛት ላይ ተመስርቶ ነው።

📚 የሴሚስተር GPA አሰራር

የአንድን ተማሪ የሴሚስተር ውጤት (GPA) ለማስላት፣ እያንዳንዱ ትምህርት ያለው የ Credit Hour በዛው ትምህርት የመጣው Grade Point ይባዛል። ከዚያም የሁሉም ትምህርቶች ውጤት በአንድ ላይ ተደምሮ፣ በሴሚስተሩ ለተወሰዱት አጠቃላይ የ Credit Hour ድምር ይካፈላል።

ምሳሌ፦ አንድ ተማሪ በሴሚስተሩ 3 ትምህርቶችን ቢወስድ፡

1ኛ ትምህርት፦ Grade A (4.0) እና Credit Hour 5 ቢሆን ➔ 4.0 x 5 = 20

2ኛ ትምህርት፦ Grade A- (3.75) እና Credit Hour 5 ቢሆን ➔ 3.75 x 5 = 18.75

3ኛ ትምህርት፦ Grade B (3.0) እና Credit Hour 3 ቢሆን ➔ 3.0 x 3 = 9

የተማሪውን GPA ለማግኘት፦

የውጤቶች አጠቃላይ ድምር፦ 20 + 18.75 + 9 = 47.75

የአጠቃላይ Credit Hour ድምር፦ 5 + 5 + 3 = 13

በመጨረሻም፣ የውጤቱን ድምር ለአጠቃላይ ክሬዲት ሰዓቱ ስናካፍለው የሴሚስተሩን GPA እናገኛለን፦
47.75 ÷ 13 = 3.67

ስለዚህ፣ ይህ ተማሪ በሴሚስተሩ 3.67 GPA አመጣ ይባላል።

CGPA ሲሰላም በተመሳሳይ መንገድ የሁሉንም ሴሚስተሮች(የሁሉንም ኮርሶች) አጠቃላይ የውጤት ድምር ለአጠቃላይ የክሬዲት ሰዓት ድምር በማካፈል ነው የሚገኘው።

📌 የ CGPA አሰራር ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ፦
ለምሳሌ የአንድን ተማሪ የሁለት ሴሚስተር የCGPA ውጤት ለማስላት፦
• 1st Semester ላይ፦
የውጤት ድምር = 47.75
የ Credit Hour ድምር = 13
(GPA = 3.67)

• 2nd Semester ላይ፦
የውጤት ድምር = 52.00
የCredit Hour ድምር = 15
(GPA = 3.46)

❌ የተሳሳተው አሰራር፦
የሁለቱን ሴሚስተር GPA ደምሮ ለሁለት ማካፈል (3.67 + 3.46) ÷ 2 = 3.56 (ይህ ስህተት ነው!) የምትወስዱት ኮርስ በጨመረ ቁጥር የተሳሳተ Result ነው የምታገኙት

ትክክለኛው አሰራር (CGPA)፦
የሁለቱንም ሴሚስተር አጠቃላይ የውጤት ድምር ለአጠቃላይ የክሬዲት ሰዓት ድምር ማካፈል፦
• አጠቃላይ የውጤት ድምር፦ 47.75 + 52.00 = 99.75
• አጠቃላይ የCredit Hour ድምር፦ 13 + 15 = 28

ስለዚህ CGPA = 99.75 ÷ 28 = 3.562 (ወደ ሁለት Digit ሲጠጋ 3.56 ይሆናል።)

ውጤቱ ተመሳሳይ ሊሆን የቻለው የሁለቱ ሴሚስተሮች የክሬዲት hr በጣም ስለሚቀራረብ ብቻ ነው፤ የምትወስዷቸው ኮርሶች በበዙ ቁጥር የ ሁለቱ አሰራር ልዩነት ይፈጥራል።
❤4