Health Science Library
1.35K subscribers
238 photos
204 files
41 links
For any fields of Health Science, Giudelines,Books,Lecture notes and Research PDFs are available Here.
Download Telegram
አብዛኛውን ጊዜ የሰውነት በሽታ መከላከል አቅማቸው ደህና የሆኑ እና ብዙም 'ያልተጎዱ' ሰዎች ከሽታው በራሳቸው ከአንድ እስከ ሁለት ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገግማሉ

በተጨማሪም የተለያዩ መድሀኒቶች ምችን ለማከም ሊታዘዙ የሚችሉ ሲሆን ፤ህክምናውም በዋነኝነት በተቻለ አቅም በፍጥነት የህመሙን ስሜቶች ቁስለቶችን እና ደረጃ መቀነስ እና ማጥፋት ነው

እንዲሁም አንዳንዴ ምች በጣም በተደጋጋሚ የሚያስቸግራቸው ሰዎች ከቅድመ ጥንቃቄዎች በተጨማሪ አነስተኛ መጠን ያለው ፀረ ቫይረስ መድሃኒት በየቀኑ አንዴ መውሰዱ (Suppressed therapy ) ድግግሞሹን ለመቀነስ ሊረዳቸው ይችላል።

እንዴት መከላከል ይቻላል?

1. የምች ምልክት ከሚያሳዩ ግለሰቦች ጋር ቀጥታ የአፍ ንክኪን መቀነስ (መሳሳም: የገራ መጠጫዎች...

2. የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እና የሰውነት ጤናን መጠበቅ

3. በቂ ፈሳሽ መውሰድ

4. በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ

5. ጭንቀት:ድባቴ... መቀነስ

6. በ'አርጅኒን' ይዘት ባላቸው ምግቦች ምክንያት የሚመጣን የቫይረስ መነቃቃት ለመቀልበስ 'ላይዚን' በተባለው ፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን (እርጎ :አይብ: አፕል: አሳ...) ማዘውተር ወይም የላይዚን ሰፕልመንት ፒልሶችን መጠቀም።

7. እለንዲሁም ለፀሀይ ጨረር በመጋለጥ ምክንያት ምች በተደጋጋሚ ለሚያጠቃቸው በተቻለ መጠን ራስን ከቀጥታ የፀሀይ ጨረር ተጋላጭነት ማራቅ እና የፀሀይ መከላከያዎችን (Sunscreens) መጠቀም ይመከራል።

በመጨረሻም ፥ 'ምች አይምታቹ'

*ማጣቀሻ መፀሀፍት መረጃዎች

1. World Health Organization (WHO)
https://www.who.int

2. National Institutes of Health (.gov)
https://pmc.ncbi.nlm.nih.gov
Treatment and prevention of herpes labialis
❤2
🌸 የቤተሰብ ዕቅድ (Family Planning) 👨‍👩‍👧‍👦

የቤተሰብ ዕቅድ ማለት ቤተሰብ የሚፈልገውን የልጆች ብዛትና የእርግዝና ጊዜ በራሱ መወሰን እና ይህንን ለማሳካት የተለያዩ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም ነው።

💚 የቤተሰብ ዕቅድ ጥቅሞች

• ያልታቀደ እርግዝናን ይቀንሳል።
• በእርግዝናዎች መካከል በቂ ጊዜ እንዲኖር ይረዳል።
• የእናትንና የሕፃንን ጤና ለመጠበቅ ይረዳል።
• ቤተሰብ የሚፈልገውን የልጆች ብዛትና የቤተሰብ ወጪ ለማቀድ ያግዛል።
• በቅርብ የሚከሰቱ እርግዝናዎችን በመቀነስ አንዳንድ የጤና ችግሮችን ይቀንሳል።

⚠️ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች ሊያስከትሉ የሚችሉ ጎንዮሽ ተፅዕኖዎች

ጎንዮሽ ተፅዕኖው እንደ ዘዴው ይለያያል።

1️⃣ ኪኒን (Pill) 💊
• የጭንቅላት ህመም
• የወር አበባ ለውጥ

2️⃣ የሶስት ወር መርፌ (Depo/Injection) 💉
• የወር አበባ መዛባት
• የወር አበባ ሊቆም ይችላል
• የሰውነት ክብደት ሊጨምር ይችላል

3️⃣ ኢምፕላንት (Implant)
• የወር አበባ መዛባት ወይም ያልተለመደ ደም መፍሰስ
• የጭንቅላት ህመም

4️⃣ የማህፀን ውስጥ መሳሪያ (IUD)
• አንዳንድ የIUD አይነቶች የወር አበባን ሊያበዙ እና የሆድ ቁርጠትን ሊያስከትሉ ይችላሉ።
• ሆርሞን ያለው IUD ግን የወር አበባን ሊያሳንስ ይችላል።

5️⃣ ኮንዶም (Condom) 🛡️
• ከእርግዝና በተጨማሪ ከብዙ የጾታ ግንኙነት በሽታዎች ለመከላከል ይረዳል።
• አንዳንድ ሰዎች ላይ የቆዳ መቆጣት ወይም አለርጂ ሊያመጣ ይችላል።
• በትክክል ካልተጠቀሙበት የእርግዝና እድል ሊኖር ይችላል።

6️⃣ ቋሚ የመከላከያ ዘዴ (Sterilization)
• ቋሚ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ነው።
• ከተደረገ በኋላ ወደ ኋላ መመለስ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

📌 ማስታወሻ: አንድ የቤተሰብ ዕቅድ ዘዴ ለአንድ ሰው ተስማሚ ሲሆን ለሌላ ሰው ላይሆን ይችላል። ስለዚህ ዘዴ ከመምረጥዎ በፊት ከጤና ባለሙያ ጋር መማከር ይመከራል።
❤2
መሰረታዊ የአእምሮ ሕመም ምልክቶች
የጭንቀት ደረጃዎች ከሰው ወደ ሰው ቢለያዩም ፣ ከደካማ የአእምሮ ጤንነት ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ አንዳንድ የተለመዱ ምልክቶች አሉ ፡፡

መሠረታዊ የአእምሮ ጤንነት ደካማ እንደሆነ የሚያመለክቱ ማስጠንቀቂያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
🖊 ብዙ አካላዊ የሆኑ የሕመም ቅሬታዎች (እንደ፦ ራስ ምታት እና የሆድ ሕመም)
🖊 አፅዕኖት ያላቸው ኑሮን የሚጎዱ የሕይወት ክስተቶች (ሥራ ማጣት ፣ ወዘተ)
🖊 አደገኛ የወሲብ ባህሪ
🖊የተራዘመ አፍራሽ (አሉታዊ)ስሜት
🖊ስለሞት ወይም ራስን ስለማጥፋት ማሰብ ወይም በሃሳብ መጠመድ
🖊አልኮል እና/ ወይም አደንዛዥ ዕፅ አላግባብ መጠቀም
🖊በንጽህና ላይ ያለ ለውጥ፤ ራስን የመንከባከብ ጉድለት
🖊 የታዘዘ መድሃኒት ስለምግብ ፣ ስለክብደት ፣ ስለአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም ስለአካል ምስል በሃሳብ መጠመድ
🖊 ራስን መጉዳት ወይም ራስን የሚያጠፋ ባህሪ። (ማለትም፦ አካልን መቁረጥ ፣ አካልን ማቃጠል ፣ ፀጉር መንጨት ወዘተ)
🖊 ተደጋጋሚ የቁጣ ጩኸት ፣ ጠበኝነት

የአዕምሮ ሕመም ሕክምና

ብዙዎቹን የአእምሮ ሕመሞች ማከም ይቻላል። የአእምሮ ሕመም ሲጀምር የሚታዩ ምልክቶችን ለይቶ ማወቅና አስቀድሞ ሕክምና መሻት ጠቃሚ
ነው። ህክምና ቶሎ ከጀመሩ የመዳን እድልዎ ከፍ ያለ ነው።

ከተለመዱት አንዳንድ የአእምሮ
ሕመም ሕክምናዎች መካከል የሚከተሉትን ያካትታሉ ;-

👉የስነልቦና ህክምና (psychotherapy)
👉የማህበረሰብ ድጋፍ ማግኘት
👉 መልሶ ማቋቋም
👉 ች ግ ሩን ከሚ ያ ባብሱ
ነ ገሮች መራቅ፤ አልኮል ከመጠጣት እና ከአደንዛዝ መድሓኒቶች/ዕፆች
👉 እራስን የማከምና ጥሩ ሕይወትን
በሚገባ መምራት ላይ ማተኮር።

https://t.me/HealthLib
❤3
የአስም በሽታ አጠቃላይ ሕክምና እና እንክብካቤ (Asthma Management & Treatment)

አስም የአየር ቧንቧዎች መጥበብ፣ ማበጥና ከመጠን ያለፈ ንፍጥ ማመንጨት ምክንያት የመተንፈስ ችግር የሚያስከትል ሥር የሰደደ የጤና እክል ነው። የአስም ሕክምና ዋና ዓላማ ምልክቶቹን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር፣ ድንገተኛ የአስም ጥቃትን (Asthma attack) መከላከል እና የሳንባን ጤና መጠበቅ ነው።

——————————

1. የመድኃኒት ሕክምና (Medical Treatments)

የአስም መድኃኒቶች በዋናነት በሁለት ይከፈላሉ፦

ሀ. ፈጣን እፎይታ ሰጪ መድኃኒቶች (Reliever / Rescue Medications)

እነዚህ መድኃኒቶች ድንገተኛ የትንፋሽ ማጠር፣ ሳል ወይም ፉጨት በሚከሰትበት ጊዜ ወዲያውኑ እፎይታ ለመስጠት ያገለግላሉ።

• አሠራራቸው፦ የተኮማተሩትን የአየር ቧንቧ ጡንቻዎች በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በማዝናናት አየር በቀላሉ እንዲገባና እንዲወጣ ያደርጋሉ።

• ዋና ዋናዎቹ፦

• ሳልቡታሞል (Salbutamol / Albuterol - SABA) በኢንሄለር (በአፍ በሚሳብ) መልክ።

• አጠቃቀም፦ አስም ሲቀሰቀስ ወይም ድንገተኛ ችግር ሲያጋጥም ብቻ የሚወሰዱ ናቸው።

ለ. የረጅም ጊዜ ተቆጣጣሪ መድኃኒቶች (Controller / Preventer Medications)

እነዚህ መድኃኒቶች ሕመሙ እንዳይቀሰቀስና የአየር ቧንቧ እብጠት እንዳይከሰት በየቀኑ በቋሚነት የሚወሰዱ ናቸው (ምልክት ባይኖርም እንኳ መወሰድ አለባቸው)።

• አሠራራቸው፦ በአየር ቧንቧ ውስጥ ያለውን እብጠትና ንዴት በመቀነስ ቧንቧው ስሜታዊ እንዳይሆን ያደርጋሉ።

• ዋና ዋናዎቹ፦

• በአፍ የሚሳቡ ስቴሮይዶች (Inhaled Corticosteroids - ICS)፦ እንደ Budesonide, Fluticasone, Beclomethasone የመሳሰሉት።

• የተቀናጁ መድኃኒቶች (ICS + LABA)፦ እብጠትን የሚቀንሱ እና የረጅም ሰዓት የአየር ማስፊያዎችን በአንድ ላይ የያዙ (ምሳሌ፡ Symbicort / Budesonide+Formoterol, Seretide / Fluticasone+Salmeterol)።

• (Tablets)፦ እንደ ሞንቴሉካስት (Montelukast) ያሉ የአለርጂ ምላሽን የሚቀንሱ መድኃኒቶች።

ሐ. ድንገተኛ የፅኑ አስም ሕክምና (Emergency / Severe Asthma Treatment)

ሕመሙ በጣም ሲበረታና በተለመደው ኢንሄለር ሳይሻል ሲቀር በሆስፒታል ደረጃ የሚሰጥ፦

• በኔቡላይዘር (Nebulizer) ማሽን አማካኝነት መድኃኒት በእንፋሎት መልክ መስጠት።

• በደም ሥር ወይም በጡንቻ የሚሰጡ ስቴሮይዶች (Hydrocortisone/Dexamethasone) ወይም የአፍ ኪኒኖች (Prednisolone)።

• የኦክስጅን ድጋፍ (Oxygen therapy) መስጠት።

——————————

2. አስምን የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መከላከል (Trigger Avoidance)

የአስም መድኃኒት ከመውሰድ ባልተናነሰ ሕመሙን ከሚቀሰቅሱ ነገሮች መራቅ ወሳኝ ነው፦

1. አቧራና ጭስ፦ ከእንጨት፣ ከከሰል፣ ከሲጋራ ጭስ እንዲሁም ከመኪና ጢስ መራቅ።

2. ሽቶና ኬሚካሎች፦ ጠንካራ መዓዛ ካላቸው ሽቶዎች፣ የጽዳት ሳሙናዎችና ኬሚካሎች መራቅ።

3. ቀዝቃዛ አየር፦ በማለዳና በምሽት ቀዝቃዛ አየር ሲኖር አፍና አፍንጫን በሻርፕ መሸፈን።

4. የቤት እንስሳት፦ የድመት፣ የውሻ ፀጉር ወይም ፎረፎር አለርጂክ ለሆኑ ሰዎች ሕመሙን ስለሚቀሰቅስ ከቤት ማራቅ።

5. ኢንፌክሽኖች፦ ጉንፋን፣ ሳይነስ እና የደረት ኢንፌክሽን አስምን ስለሚያባብሱ ወቅታዊ የጉንፋን ክትባቶችን መውሰድና ከታመሙ ሰዎች መራቅ።

6. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፦ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት አስም የሚነሳ ከሆነ ከስፖርት በፊት የሚወሰደውን አዳኝ ኢንሄለር (Salbutamol) በሐኪም ትዕዛዝ አስቀድሞ መውሰድ።

——————————

3. ኢንሄለርን (Inhaler) በትክክል የመጠቀም መመሪያ

መድኃኒቱ ወደ ሳንባ በሚገባ እንዲደርስ አጠቃቀሙን ማወቅ አስፈላጊ ነው፦

1. ኢንሄለሩን በደንብ ማወዛወዝ።

2. በውስጥ ያለውን አየር ሙሉ በሙሉ ወደ ውጭ ማውጣት (መተንፈስ)።

3. የመድኃኒቱን አፍ በአፍ ውስጥ አስገብቶ ከንፈርን በጥብቅ መዝጋት።

4. መድኃኒቱን እየጫኑ ወደ ውስጥ በረጅሙና በዝግታ መሳብ።

5. አየርን ከሳቡ በኋላ ትንፋሽን ከ 5 እስከ 10 ሰከንድ ያህል አምቆ ማቆየት፤ ከዚያም በዝግታ መልቀቅ።

6. ስቴሮይድ ያለበትን ኢንሄለር ከተጠቀሙ በኋላ የአፍ ውስጥ ቁስለት ወይም ፈንገስ እንዳይከሰት አፍን በውሃ መጉመጥመጥና መትፋት።

——————————

4. ወደ ድንገተኛ ሕክምና ክፍል መሄድ የሚገባው መቼ ነው?

• ኢንሄለር (Salbutamol) ወስደው ምንም እፎይታ ካልተሰማዎት።

• አረፍ ብለው እንኳን በከፍተኛ ሁኔታ ትንፋሽ ካጠረዎት።

• በሚናገሩበት ወቅት ሙሉ ዓረፍተ ነገር ሳይጨርሱ ትንፋሽ የሚያጥርዎት ከሆነ።

• የከንፈር ወይም የጥፍር ጫፎች ወደ ሰማያዊነት ከተቀየሩ ወዲያውኑ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።

(ማሳሰቢያ፦ ማንኛውንም የአስም መድኃኒት መጠንና ዓይነት ከመቀየርዎ ወይም ከመውሰድዎ በፊት ከሐኪምዎ ጋር መማከር አስፈላጊ ነው።)
❤1
የstroke (የአንጎል የደም ስር ችግር) 9 ምልክቶች

አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ የሚሹ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች

——————————

1. የፊት መዛባት (Face Drooping)

• ከአንዱ የፊት ክፍል በድንገት መስቀል ወይም ወደ ታች መንሸራተት።

2. የእጅ ድካም (Arm Weakness)

• አንዱ እጅ ሊደክም ወይም ወደ ታች ሊንሸራተት/ሊወርድ ይችላል።

3. የመናገር ችግር (Slurred Speech)

• ንግግር ግልጽ ያልሆነ ወይም ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

4. በአንድ በኩል በድንገት የመደንዘዝ ስሜት (Sudden Numbness on One Side)

• ፊት፣ እጅ ወይም እግር በድንገት የመደንዘዝ ስሜት ሊኖረው ይችላል።

5. በድንገት የመራመድ ችግር (Sudden Trouble Walking)

• መራመድ መረጋጋት ማጣት ወይም ከባድ ሊሆን ይችላል።

6. ድንገተኛ የማዞር ስሜት ወይም ሚዛን ማጣት (Sudden Dizziness or Loss of Balance)

• በድንገት ሚዛን የማጣት ወይም የማዞር ስሜት ሊሰማዎት ይችላል።

7. ድንገተኛ የማየት ችግር (Sudden Vision Problem)

• እይታ ብዥ ሊል ወይም በአንዱ ወይም በሁለቱም ዓይኖች ማየት ሊሳን ይችላል።

8. ድንገተኛ የመደናገር ስሜት (Sudden Confusion)

• ነገሮችን መረዳት ወይም ምላሽ መስጠት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

9. ከባድና ድንገተኛ የራስ ምታት (Severe Sudden Headache)

• በድንገት የሚመጣ በጣም ከባድ የራስ ምታት የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል።
አጣዳፊ ወይም ድንገተኛ የሆድ ሕመም (Acute Abdominal Pain) መንስኤዎችን፣ መለያ ምልክቶችን እና ህክምና ፦

1. የሆድ ሕመም መንስኤዎች በመገኛ ቦታ (Common Causes by Location)

የሆድ ክፍል ሕመም የሚሰማበት ቦታ ትክክለኛውን በሽታ ለመለየት ትልቅ ፍንጭ ይሰጣል፡

• በቀኝ በኩል የላይኛው የሆድ ክፍል (RUQ): የሐሞት ከረጢት እብጠት/ቁርጠት፣ የጉበት ብግነት (Hepatitis)

• በግራ በኩል የላይኛው የሆድ ክፍል (LUQ): የጨጓራ ብግነት/ቁስለት፣ የጣፊያ ብግነት (Pancreatitis)፣ የሳንባ ምች (የሳንባ የታችኛው ክፍል)።

• የመሃል የላይኛው ክፍል (Epigastric): የጨጓራ ቁስለት በሽታ (Peptic ulcer)፣ የጨጓራ አሲድ ወደ ላይ መመለስ (GERD)፣ የጣፊያ ብግነት።

• በቀኝ በኩል የታችኛው የሆድ ክፍል (RLQ): የትርፍ አንጀት እብጠት (Appendicitis)፣ የሽንት ቱቦ ጠጠር፣ ወይም የማህፀንና የእንቁላል ከረጢት ችግሮች።

• በግራ በኩል የታችኛው የሆድ ክፍል (LLQ): የአንጀት ግድግዳ ከረጢት ኢንፌክሽን (Diverticulitis)፣ ከባድ የሆድ ድርቀት፣ የሽንት ቱቦ ጠጠር።

• በመላው ሆድ የሚሰራጭ ሕመም (Diffuse): የጨጓራና አንጀት ኢንፌክሽን፣ የአንጀት መዘጋት/መታጠፍ፣ የሆድ ዕቃ ሽፋን ብግነት (Peritonitis)።

——————————

2. አስደንጋጭ ወይም አስቸኳይ ቀዶ ጥገና የሚሹ ምልክቶች (Red Flags)

እነዚህ ምልክቶች ከታዩ ታካሚው በአስቸኳይ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ አለበት፡

• የሆድ መደንደል ወይም መሸከርከር (ሆድ ሲነካ እጅግ በጣም መለብለብና ጠንካራ መሆን)።

• ቢጫ ወይም አረንጓዴ መግል የመሰለ ነገር ማስመለስ።

• ከሆድ ዕቃ ደም መፍሰስ (በአፍ ማስታወክ ወይም በፊንጢጣ ደም መውጣት)።

• እርጉዝ ሴት ላይ የሚከሰት ድንገተኛ የሆድ ሕመም።

• የደም ግፊት መውረድ እና የልብ ምት እጅግ በጣም መጨመር።

——————————

3. ዋና ዋና የሕክምና እርምጃዎች (Management Principles)

1. ታካሚውን ማረጋጋት: በደም ስር ፈሳሽ (IV fluids) መስጠት።

2. ምግብና ውሃ በአፍ አለመስጠት (NPO): ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግ ስለሚችል በአፍ ምንም ነገር እንዳይወሰድ ማድረግ።

3. የሕመም ማስታገሻ መስጠት።

4. የቀዶ ጥገና ሐኪም ማማከር።
❤5
የሆድ ህመም - የማስጠንቀቂያ ምልክቶች፦

እንደ ህመሙ ቦታ የተከፋፈሉ ዓይነቶች፡

• የላይኛው የሆድ ክፍል (Upper Abdomen)፦

• የጨጓራ እብጠት (Gastritis)

• የጨጓራ ቁስለት (Ulcer)

• የጣፊያ እብጠት (Pancreatitis)

• የሐሞት ከረጢት ድንጋይ (Gallstones)

• የታችኛው የሆድ ክፍል (Lower Abdomen)፦

• የትርፍ አንጀት ህመም (Appendicitis)

• የሽንት ትቦ ኢንፌክሽን (UTI)

• አንጀት ህመም (IBS)

• የማህፀን / የስነ-ተዋልዶ ህመም ችግሮች (Gynecological issues)

• በመላው ሆድ የሚሰራጭ ህመም (Generalized Pain)፦

• የምግብ አለመፈጨት (Indigestion)

• የሆድ ውስጥ ኢንፌክሽን (Infection)

• የምግብ መመረዝ (Food poisoning)

✅ ሐኪም ማየት የሚገባዎት መቼ ነው?

በጣም ብርቱ ወይም ድንገተኛ ህመም ሲኖር

✔ ህመሙ ከትፋት፣ ከትኩሳት ወይም ከዓይን/ቆዳ ቢጫ መሆን (ጃውንዲስ) ጋር ሲያጋጥም

✔ በሰገራ ወይም በትፋት ውስጥ ደም ሲኖር

✔ አየር (ጋዝ) ወይም ሰገራ ማውጣት አለመቻል

✔ የሆድ ማበጥ / ማፈፋት

✔ ህመሙ ከ24 ሰዓታት በላይ ሲቆይ

አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ የሚሹ አደገኛ ሁኔታዎች (Red Flag Conditions)፦

✔ የትርፍ አንጀት ህመም (Appendicitis)

✔ ከማህፀን ውጭ ያለ እርግዝና (Ectopic pregnancy)

✔ የሐሞት ከረጢት ድንጋይ (Gallbladder stones)

✔ የኩላሊት ድንጋይ (Kidney stones)

✔ የአንጀት መዘጋት (Intestinal obstruction)

✔ የጣፊያ እብጠት (Pancreatitis)

——————————



ማስታወሻ፦ ሁሉም የሆድ ህመሞች ቀላል አይደሉም — በጊዜ የሚደረግ ምርመራ ሕይወትን ያድናል።



(እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው ከላይ የተጠቀሱትን አደገኛ ምልክቶች የሚያሳይ ከሆነ፣ በአስቸኳይ ወደ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የሕክምና ተቋም በመሄድ የሐኪም እርዳታ ማግኘት ይመከራል።)
❤3
#የጤና ባለሙያዎች የሙያ ስያሜ አሰጣጥ

ሀ. የሙያ ስያሜ ደረጃዎች
1. Junior
2. Senior
3. Chief
4. Expert
5. Senior Expert
6. Chief Expert
7. Consultant

ለ. ዝርዝር መስፈርቶች

1. ለባለሙያ የሚሰጠው የሙያ ስያሜ የባለሙያውን የትምህርት ዝግጅት መሰረት ያደረገ ይሆናል።

2. በተ.ቁ 1 ላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለባለሙያው የሚሰጠው የሙያ ስያሜ የአገልግሎት ዘመንን መሰረት በማድረግ Junior, Senior, Chief, Expert, Senior Expert, Chief Expert እና Consultant በሚል ደረጃ ይሆናል።

3. የሙያ ስያሜ ከአንዱ ደረጃ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ለመሸጋገር በሙያው 3 ዓመት ማገልገል ይኖርበታል።

4. የሙያ ስያሜዎቹ በትምህርት ደረጃ (ዲፕሎማ፣ ዲግሪ፣ ማስተርስ፣ ወዘተ) እራሳቸውን ችለው የሚቆሙ ይሆናሉ፤ ከአንደኛው የትምህርት ደረጃ ወደ ሌላኛው ደረጃ የሚሸጋገር የስራ ልምድ አይኖርም።

5. ይህ የሙያ ስያሜ አሰጣጥ ከደመወዝና ከደረጃ እድገት ጋር ግንኙነት የለውም።

6. ማስተርስ፣ ህክምናና ከዚያ በላይ ያሉ ባለሙያዎች ወደ ኮንስልታንት ደረጃ ለመድረስ 15 ዓመት የስራ ልምድ እና ሁለት ጥናት በታወቀ ጆርናል ማሳተም ይጠበቅባቸዋል፤ አተገባበሩም፦
ሀ) በግል ወይም የምርምሩ ባለቤት (principal investigator) ሆኖ ምርምር ሲሰራ፤
ለ) ምርምሩ በታወቀ ጆርናል መታተሙ በጤና ሚኒስቴር የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ተረጋግጦ ማስረጃ ሲቀርብ።
ማሳሰቢያ፦ "ሀ" እና "ለ" ን ያሟሉ ሁለት ጥናቶች እያንዳንዳቸው እንደ አንድ ዓመት የስራ ልምድ ይያዛሉ፤ ሆኖም በአንድ ዓመት ውስጥ ከሁለት በላይ ምርምር ቢታተምም ተጨማሪው እንደ ስራ ልምድ አይያዝም።

7. የሙያ ፈቃድ የሚሰጠው መመዘኛ ግዴታ ለሆነባቸው የሙያ ዘርፎች ብቻ ነው።

8. የብቃት ማረጋገጫ (ብቃት ምዘና) ፈተና መውሰድ የሚገባቸው የጤና ባለሙያዎች፣ የሙያ ፈቃድ የሚያገኙት ፈተናውን ካለፉና በፈታኙ አካል ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

9. በሰብ-ስፔሻሊቲ ወይም በሱፐር-ስፔሻሊቲ ከአንድ ዓመት በታች ተምሮ የተመለሰ ባለሙያ፣ የሰብ-ስፔሻሊቲ/ሱፐር-ስፔሻሊቲ ብቃቱ በሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ተረጋግጦ ማስረጃ ሲቀርብለት የሙያ ስራ ፈቃድ ይሰጠዋል።

10. ሚኒስቴሩ ለሙያ ስያሜ አሰጣጥ አዲስ ሙያ ሲፈጠር፣ ጉዳዩ በሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት ይስተናገዳል።

11. ስለ የሙያ ስያሜ አሰጣጥ ተጨማሪ ዝርዝር በአባሪ 3 ላይ ማየት ይቻላል።

https://t.me/HealthLib
❤2