የራስ ምታት አይነቶች እና ህክምናዎቻቸው
( types of headache and their treatments) ፦
1. የውጥረት / የጭንቀት ራስ ምታት (Tension Headache)
• ምልክቶች (Typical Features)፦
• በራስ ዙሪያ የመጨናነቅ ወይም ማሰሪያ እንደታሰረበት ዓይነት ስሜት።
• ብዙውን ጊዜ በሁለቱም የራስ ጎኖች ላይ ይከሰታል።
• ህክምና (Common Treatment)፦
• ፓራሴታሞል (Paracetamol) / አሴታሚኖፌን (Acetaminophen)።
• የህመም ማስታገሻዎች (NSAIDs - ለምሳሌ ኢቡፕሮፌን)።
• የጭንቀት እና የእንቅልፍ ሁኔታን ማስተካከል (Stress & sleep management)።
——————————
2. ማይግሬን (Migraine)
• ምልክቶች (Typical Features)፦
• መካከለኛ እስከ ከፍተኛ የሆነ ተወርዋሪ/የሚመታ ዓይነት የህመም ስሜት።
• ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ።
• ለብርሃን እና ለድምፅ ተጋላጭ መሆን (ብርሃን/ድምፅ አለመቻል።
• አውራ/Aura (ከህመሙ በፊት የእይታ ለውጦች መታየት)።
• ህክምና (Common Treatment)፦
• NSAIDs ወይም ፓራሴታሞል (Paracetamol)።
• ትሪፕታንስ / Triptans (ለሚስማማቸው ታካሚዎች)።
• ህመሙ ተደጋጋሚ ከሆነ መከላከያ ሕክምናዎች (Preventive therapy)።
——————————
3. የክላስተር / የመደጋገም ራስ ምታት (Cluster Headache)
• ምልክቶች (Typical Features)፦
• በአንድ በኩል ብቻ ያለ ከበድ ያለ ህመም።
• በዓይን ዙሪያ የሚከሰት።
• የዓይን እንባ ማፍሰስ፣ መቅላት እና የአፍንጫ መታፈን/ፈሳሽ መኖር።
• ህክምና (Common Treatment)፦
• 100% ኦክስጅን (በከፍተኛ ፍሰት መስጠት)።
• ፈጣን አሰራር ያለው ትሪፕታን (Rapid-acting triptan)።
• በልዩ ባለሙያ የሚሰጥ መከላከያ ሕክምና።
——————————
4. የሳይነስ ራስ ምታት (Sinus-related Headache)
• ምልክቶች (Typical Features)፦
• በፊት አካባቢ የሚሰማ ጫና እና ህመም።
• የአፍንጫ መታፈን እና የፈሳሽ መውጣት።
• ወደ ታች/ወደ ፊት ሲያጎንቡ ህመሙ ይብሳል።
• ህክምና (Common Treatment)፦
• ዋናውን የሳይነስ በሽታ ማከም።
• የህመም ማስታገሻዎች (እንደ አስፈላጊነቱ)።
• የአፍንጫ መታፈን ማስታገሻዎች (Decongestants) / የጨው ውሃ (Saline)።
——————————
5. የመድኃኒት አጠቃቀም ብዛት የሚመጣ ራስ ምታት (Medication-Overuse Headache)
• ምልክቶች (Typical Features)፦
• የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን ሁልጊዜ አብዝቶ በመውሰድ የሚከሰት ተደጋጋሚ ራስ ምታት።
• ህክምና (Common Treatment)፦
• የሚወሰደውን መድኃኒት መቀነስ ወይም ማቆም።
• በሕክምና ባለሙያ ጥብቅ መመሪያ እና ክትትል ማድረግ።
——————————
6. ሁለተኛ ደረጃ ራስ ምታት (Secondary Headache)
• ምልክቶች (Typical Features)፦
• በሌላ የጤና ችግር ምክንያት የሚመጣ (ለምሳሌ፡ ኢንፌክሽን፣ ደም መፍሰስ፣ የአንጎል ጉዳት ወይም በጣም ከፍተኛ የደም ግፊት)።
• ህክምና (Common Treatment)፦
• የህመሙን ዋና መንስኤ በአስቸኳይ ማከም።
——————————
⚠️ ቀይ ባንዲራዎች / አስቸኳይ ትኩረት የሚሹ ምልክቶች (Red Flags)
(እነዚህ ምልክቶች ካሉ አስቸኳይ የሕክምና ምርመራ ያስፈልጋል!)
• በድንገት የሚመጣ በጣም አሰቃቂ/ከባድ ራስ ምታት።
• አዲስ የመጣ ራስ ምታት ከሰውነት ድካም ወይም ከግራ መጋባት ጋር።
• ትኩሳት እና የአንጎል/የአንገት መገተር (መወጠር)።
• የራስ/አንጎል ጉዳት።
• በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ አዲስ የሚጀምር ራስ ምታት።
• ከፍተኛ የእይታ ለውጦች መከሰት።

❤2
#ቃሪያ_ለጤና_ያለው_ጥቅም
በምድራችን ላይ ከ200 በላይ የተለያየ አይነት የቃሪያ አይነቶች አሉ፡፡ ቃሪያ ውስጥ ያለው ዋናው ንጥረ ነገር ካፕሲን ይባላል፡፡ ይሄ ንጥረ ነገር ለልብ፤ለደም ግፊት እና ለመተንፈሻ አካላችን ጤና ይጠቅማል፡፡ በተጨማሪም ቃሪያ የተለያዩ ቫይታሚኖች በውስጡ ስለያዘ ቃሪያን ብሉ ብለን እንመክሮታለን፡፡
👉👉 የቃሪያ ጥቅሞች
✅✅ 1. ጉንፋን ወይም ሳይነስ ይከላለላ፡- በተለምዶ ጉንፋን የያዘውን ሰው ቃሪያ ብላ ወይም የሚያቃጥል ነገር ብላ ይባላል፡፡ይሄ ነገር ሳይንስም ይደግፈዋል፡፡ ቃሪያ ውስጥ ያለው ካፕሲን አፍንጫችን ውስጥ ያለውን ሚውከስ ሜምብሬን ያነቃቃዋል፡፡አፍንጫችን ውስጥ ያለው የደም ዝውውር በማፋጠን ከአፍንጫችን የሚወጣው ፈሳሽ አንዲቀጥን ያደርገዋል፡፡ ይሄ ማለት ከጉንፋን ወይም ሳይነስ በሽታ ቶሎ እንድናገግም ይረዳናል ማለት ነው፡፡
✅✅ 2. የበሽታ መከላከል አቅማችንን ያሳድጋል፡- ቃሪያ በውስጡ ከያዛቸው ቫይታሚኖች ዋነኛው ቫይታሚን ሲ ነው፡፡ ቫይታሚን ሲ ሰውነታችን ራሱን ከበሽታ እንዲከላከል እና ጤነኛ ሆነን እንድንቆይ ይረዳናል፡፡ በተጨማሪም ቃሪያ ፀረ-ባክቴሪያ የመሆን ባህሪ አለው፡፡ በዚህ ምክንያት በሰውነታችን ውስጥ በተለያየ ምክንያት የተፈጠሩ ፍሪ ራዲካል የሚባሉትን ጎጂ ነገሮችን ያፀዳል፡፡
✅✅ 3. ቃሪያ መብላት ያነቃቃል፡- ቃሪያ ውስጥ ያለው ካፕሲን የተባለው ንጥረ ነገር ሰውነታቸን ኢንዶርፊን የተባለውን ሆርሞን እንዲያመነጭ ያደርገዋል፡፡ ይሄ ሆርሞን ጥሩ ስሜት እንዲሰማን እና ደስተኛ እንድንሆን ያደርገናል፡፡
✅✅ 4. እይታችንን ያስተካክላል፡- ቃሪያ ቫይታሚን ኤ እና ሲ በውስጡ ይዟል፡፡ እነዚህ
ቫይታሚኖች የአይናችን ጤና ይጠብቃሉ በተጨማሪም እንደ ሞራ ያሉ የአይን ችግሮችን ይከላከሉልናል፡፡
✅✅ 5. ቃሪያ ለፀጉራችን እና ለጤናችን ይጠቅማል፡- ቃሪያ መብላት ቆዳችንን ጤነኛ እና ጥሩ ወዘና ያለው እንዲሆን ይረዳል፡፡ ቫይታሚን ሲ የተጎዱ የቆዳችን ሴሎች እንዲጠገኑ እና የቆዳችን መሸብሸብ እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ቃሪያ በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠረውን መቆጣት እና እብጠቶች ስለሚቀንስ ብጉርን ይከላከላል፡፡
✅✅6. ቃሪያ አንታይ ኢንፍላማቶሪ ነው፡- ሰውነታችን ውስጥ ከውስጥም ሆነ ከውጭ እብጠት ወይም መቅላት ወይም መቆጣት ይከሳታል፡፡ ይሄ ኢንፍላሜሽን ይባላል፡፡ ቃሪያ በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ስለሆነ ይሄ ችግር እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡ ከተከሰተም ቶሎ እንዲድን ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡
✅✅ 7. ቁስል ቶሎ ያሽራል፡- ቃርያ ውስጥ ያለው ቫይታሚን ሲ በቆዳችን ላይ የሚፈጠሩ ቁስሎችን ቶሎ እንዲድኑ ያደርጋል፡፡ቫይታሚን ሲ ቆዳችን የሚሰራበትን ኮላጅን ቶሎ እንዲመረት ያደርጋል ስለዚህም ቁስሉ ቶሎ እና ጠባሳው ሳይበዛ እንዲድን ያደርገዋል፡፡
✅✅ 8. ቃሪያ ለልብ ይጠቅማል፡- ቃሪያ ካፕሲን ስላለው ለልባችን ጤና የተለያዩ ጥቅሞች ይሰጣል፡፡ በደማችን ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል መጠን ያስተካክላል፡፡በደም ቧንቧችን ውስጥ የተጠራቀመውን ኮሌስትሮል ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የደም እንቅስቃሴ ያሻሽላል ይሄም በልባችን ላይ ያለውን ጫና ይቀንሳል፡፡
✅✅ 9. ቃሪያ በውስጡ ብዙ ካልሲየም ይዟል፡- ቃሪያ በውስጡ ብዙ ካልሲየም እና ቫይታሚን ኬ ስላለው ለአጥንታችን እና ለጥርሳችን ጤና ይጠቅማል፡፡በአደጋ ጊዜ የሚደርሰውን የደም መፍሰስም ይቀንሳል፡፡
📍📍 ማሳሰቢያ
በአንድ ጊዜ ብዙ ቃሪያ መብላት የቆዳ እና የጨጓራ ችግር ሊያመጣ ይችላል፡፡
ቃሪያ በአንዳንድ ሰዎች ላይ የሆድ ቁርጠት እና ተቅማጥ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የስኳር ህመም መሰረታዊ ትምህርቶች
ትርጓሜ፦ የስኳር ህመም ማለት በደማችን ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን መጨመር ማለት ነው።
የህመሙ ስርጭት፦ በአለማችን ብሎም በሀገራችን በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ በአማካኝ ከ አስር ሰወች አንድ ሰው የስኳር ህመም አለበት ተብሎ ይገመታል።3/4 የሚሆነው ታማሚ በታዳጊ ሀገሮች ይገኛል። ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ህመሙ እንዳለባቸው አያቁም።
የስኳር ህመም አይነቶች
1) አይነት አንድ የስኳር ህመም
2) አይነት ሁለት የስኳር ህመም
3) በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የስኳር ህመም
4) ሌሎች የስኳር ህመሞች
የህመሙ ምልክቶች፦ ምንም አይነት ምልክት ሳይኖረው በደም ምርመራ ብቻ ሊታወቅ ይችላል። ቶሎ ቶሎ ውሀ የመጥማት ፣ቶሎ ቶሎ የመሽናት ፣ የረሀብ ስሜት ፣ ክብደት መቀነስ ፣የድካም ስሜት እና በሌሎች ኢንፌክሽን የመጋለጥ ምልክቶች ይኖራቸዋል ። በጣም ከፍተኛ የስኳር መጠን ደግሞ ራስን እስከመሳት ሊያደርስ ይችላል። እንዲሁም ስኳር በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ማለትም የልብ፣ የኩላሊት፣ ስትሮክ ፣ የአይን ፣ የእግር ቁስለት ጉዳት ካደረሰ በኋላ ሊታወቅ ይችላል።
ቅድመ ምርመራ የሚያስፈልጋቸው ሰወች
1) ማንኛውም ከ40 አመት እድሜ በላይ ያለው
2) ከልክ በላይ ውፍረት
3) የደም ግፊት ህመም ያለባቸው
4) በደማቸው ውስጥ ከፍተኛ የስብ መጠን መኖር
5) በህክምና የታወቀ የጭንቅላት ወይም የልብ የደም ስር መጥበብ
6) የ ኤች አይ ቪ ህመም ያለባቸው
7) ከ 4 ኪ.ግ ክብደት በላይ የሚመዝን ህፃን የወለደች እናት
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ነጥቦች ያለባቸው ሰወች በየሶስት አመት የስኳር መጠን እንዲመረመሩ ይመከራል። ነገር ግን መጠነኛ መጨመር ካሳየ በየአመቱ እንዲለካ ይደረጋል።
የስኳር ህመም ምርመራ ማረጋገጫ
1) ከምግብ በፊት(ለ 8 ሰዓት ምግብ ሳይወሰድ)- 126 እና ከዚያ በላይ
2)የ3 ወር የስኳር አማካይ ምርመራ(HGA1c) -6.5 እና ከዚያ በላይ
3)75 ግራም ስኳር ከወሰዱ 2 ሰዓት በኋላ ያለው ልኬት- 200 እና ከዚያ በላይ
ወይም
4) የስኳር ምልክት የታየባቸው ከሆነ በማንኛውም ሰዓት የሚለካ የስኳር መጠን- 200 እና ከዚያ በላይ ከሆነ የስኳር ህመም አለ ይባላል።
የስኳር ምርመራ ለሁለተኛ ጊዜ በድጋሜ ከሌላ ወይም ከተመሳሳይ የደም ናሙና መለካት እና መረጋገጥ ይኖርበታል።
የስኳር ህመም ህክምናወች
1) አጠቃላይ ጤና አጠበባባቅ
፨ በሳምንት 150 ደቂቃ መካከለኛ እንቅስቃሴ (የፍጥነት ጉዞ፣ እርሻ...) ማድረግ (ሁለት ተከታታይ ቀናት ሳይሰሩ ማሳለፍ አይመከርም)
፨ ከእንቅስቃሴ በፊት የስኳር መጠን መለካት ሊያስፈልግ ይችላል
፨ ከ 30 ደቂቃ በላይ ምንም ሳይንቀሳቀሱ ቁጭ አለማለት (የተወሰነ እንቅስቃሴ በመካከል ያስፈሊጋል)
፨ኮምፕሌክስ ካርቦሀይድሬት ያላቸው(ድንች ፣ፖስታ፣ ዳቦ፣ መኮረኒ...)መካከለኛ ማድረግ
፨ የአትክልት ምግቦችን ማዘውተር
፨ ስኳር ቶሎ ሚጨምሩ(ስኳር፣ለስላሳ፣ማር፣ ኬክ ..)አለመመገብ
፨ ጎጅ ስብ ያለባቸው (ቅቤ፣የረጋ ዘይት..) መቀነስ
፨ ጨው ፣አልኮል መቀነስ እና ሲጋራ/ትምባሆ አለማጨስ
፨ ከፍተኛ ውፍረትን ቢያንስ በ 5 % መቀነስ
፨በቂ እንቅልፍ መተኛት
፨ ኮቪድ 19 እና ሌሎች ክትባት መውሰድ
2) መድሀኒት በመውሰድ
፨ የሚዋጥ መድሀኒት- ለአይነት ሁለት ስኳር ህመም የሚሰጡ መድሀኒቶች ናቸው።
፨ መርፌ(ኢንሱሊን)- ይህ ደግሞ ለአይነት አንድ ስኳር ፣ በእርግዝና ጊዜ እና በመድሀኒት መቆጣጠር ያልተቻለ ወይም የስኳር መጠኑ በጣም የጨመረ አይነት ሁለት የሰኳር ህመም እንዲወስዱ ይደረጋል። ኢንሱሊን በፍሪጅ ወይም አሸዋ ውስጥ ውሀ በመጨመር ማስቀመጥ ይኖርብናል። ኢንሱሊን የሚወጋበትን የሰውነት ክፍል( ትክሻ፣ሆድ ፣ጭን ) በየጊዜው መቀያየር አለብን።
ህክምና ላይ እያሉ የሚፈለገው የስኳር መጠን
1) ምግብ ሳይበሉ (ላለፉት 8 ሰዓታት) የሚለካ መጠን ከ 80-130 ሚ.ግ/ዴ.ሊ
2) ምግብ ከተበላ 2 ሰዓት በኋላ የሚለካው መጠን ከ 180 ሚ.ግ/ዴ.ሊ በታች እና
3) የሶስት ወር አማካኝ ምርመራ ልኬት ለአብዛኛው ማህበረሰብ ከ 7% በታች መሆን ይኖርበታል።
በእርግዝና ጊዜ የሚደረግ የስኳር መጠን ክትትል
1) ምግብ ከመመገብ በፊት( ለ8 ስዓት) የሚለካው መጠን ከ 95 ሚ.ግ/ዴ.ሊ በታች
2) ከምግብ 1 ሰአት በኋላ የሚለካው መጠን ከ 140 ሚ.ግ/ዴ.ሊ በታች
3) እና ከምግብ 2 ሰአት በኋላ የሚለካው መጠን ከ 120 ሚ.ግ/ዴ.ሊ በታች መሆን ይኖርበታል ።
ማስታወሻ ፦ ከእርግዝና በፊት የሶስት ወር አማካይ የስኳር መጠን ልኬት ከ6.5 % በታች መሆን ይኖርበታል። ስለዚህ ሀኪምዎን ከእርግዝና በፊት ማማከር ይኖርብዎታል።
የስኳር መጠን ክትትል
፨ እንደ ስኳር መጠኑ በየወሩ ወይም በየ ሶስት ወር ክትትል ያስፈልጋል።
፨ በቤት ውስጥ መለካት የሚችሉ ከሆነ
፨ ኢንሱሊን ለሚወስዱ- ምግብ ሳይበሉ ጥዋት ፣ከምግብ በፊት፣ የስኳር መጠን መቀነስ ምልክት ሲኖር እና ከምግብ 2 ሰዓት በኋላ በተቻለ መጠን መለካት
፨ የሚዋጥ መድሀኒት ለሚወስዱ - የምግብ፣ የእንቅስቃሴ ወይም የመድሀኒት ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ መለካት ያስፈልጋል።
፨ የሶስት ወር አማካይ ምርመራ ደግሞ በአመት ከ 2-4 ጊዜ መለካት ይመከራል።
ሌሎች በየክትትል ጊዜ መከናወን ያለባቸው ነገሮች
፨ የግፊት ምርመራ
፨ የእርግዝና ሁኔታ
፨የልብ ህመም ቅድመ መከላከል
፨ የደም ውስጥ የስብ ክምችት መጠን (እንደ አስፈላጊነቱ)
፨ የውፍረት መጠን(ክብደትና ቦርጭ)
፨ የቫይታሚን ቢ 12 መጠን (እንደ አስፈላጊነቱ)
በየአመቱ መደረግ ያለባቸው ክትትል
እነዚህ ክትትሎች የሚያስፈልጋቸው ለአይነት ሁለት ታካሚወች ስኳር ህመም ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ሲሆን ለ አይነት አንድ ደግሞ ስኳር ህመም ከታወቀበት 5 አመት በኋላ ይጀመራል።
፨ የእግር ቁስለት(በሀኪም የመረመር)
፨ የአይን ምርመራ(የመጀመሪያው ምርመራ ጤነኛ ከሆነ በየ 2 ወይም 3 አመት ማድረግ ይቻላል)
፨ የሽንትና ኩላሊት ምርመራ
፨ የልብ ህመም ክትትል
የእግር ቁስለት ለመከላከል መደረግ ያለባቸው
፨ በየቀኑ መከታተል
፨ ለብ ባለ እንጅ በሞቀ ውሀ አለመታጠብ
፨ እንዳይሰነጣጠቅ ቅባት መቀባት
፨ ጥፍርን በጥንቃቄ መቁረጥ
፨ ካልስ በየጊዜው ወቀየር
፨ ጫማ ከመልበስ በፊት ጠጠር ወይም ሌላ ጎጅ ነገር አመኖሩን ውስጡን በደንብ ማየት
፨ በባዶ እግር አለመንቀሳቀስ
፨ የስኳር መጠንን መቆጣጠር እና አለማጨስ ይኖርብናል።
የስኳር መጠን መቀነስ
ይህ ህመም አደገኛ ሲሆን የስኳር መጠን ከ70 ሚ.ግ/ዴ.ሊ በታች ሲሆን ይከሰታል። ምክንያቶቹ ደግሞ በቂ ምግብ ባለመውሰድ፣የመድኃኒት መጠን መብዛት ፣ከባድ እንቅስቃሴ በመስራት እና ተያያዥ የኩላሊት ወይም የጉበት ህመም ሲኖር ሊከሰት ይችላል።
የስኳር መቀነስ ምልክቶች ራስ ምታት፣ ረሀብ፣ ጭንቀት፣ ልብ በፍጥነት መምታት፣ ላብ፣ የሰውነት መንቀጥቀጥ እና ራስ መሳት ናቸው። እነዚህ ምልክቶች ከተሰሙ ወዲያውኑ 4 የሻይ ማንኪያ ስኳር ወይም 4 ከረሚላ ወይም ግማሽ ብርጭቆ ለስላሳ መውሰድ ያስፈልጋል። ከ 15 ደቂቃ በኋላ ምልክቶች ከቀጠሉ ድጋሜ መውሰድ እና ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል።
ዶ/ር ክብረት እንየው ፤ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት

❤1
"ምች" - Oral Herps /Cold Sores
በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከንፈራችን ላይ፣ አፋችን አካቢቢ እና ውስጥ በድንገት የህመም ስሜት ያላቸው ትንንሽ ውሃ የቋጠሩ ሚመስሉ አይነት እብጠቶች ወይም ቁስለት ሲያጋጥመን 'ምች መቶኝ ነው' የሚል የተለመደ የህመም አገላለፅ አለን።
በተለይ' የተወሰኑ ምግቦችን ከተጠቀምኩ ቡሀላ አፌን በደንብ ሳልታጠብ ወደ ፀሀይ ስወጣ... ነው ምች ያገኘኝ' እንላለን።
'ፀሀይ ላይ ምግብ አትብላ ምች ይመታሀልም' ስንባል ያደግንም ብዙዎች ነን።
'ምች ይደጋገምብኛል : ይፀናብኛል: ያስቸግረኛል... እያሉ 'የሚናገሩም ብዙ ሰዎች አሉ።
'ምች ይምታህ' .. የሚለው ቃል ደግሞ የልጅነት የእርግማን ወይም ስድብ ትዝታችን ነው
ምች ምንድነው?
በአብዛኛው ማህበረሰባችን ዘንድ' ምች ተብሎ' ተብሎ የሚታወቀው ፦በአፍ ውስጥ ከንፈር እና አካባቢው የሚከሰት እና በትንንሽ ህመም ያላቸው ውሃ የቋጠሩ ሚመስሉ እብጠቶች ወይም ቁስለት ምልክቶቹ በዋናነት የሚገለፀው ሲሆን ፥በሳይንሳዊ መጠሪያው 'Oral Herps/Cold sores' ወይም አንዳንዴ ከንፈረ ላይ ብቻ ሲወሰን 'Herps labialis' ተብሎ ከሚጠራው የቫይረስ ኢንፌክሽን ጋር የሚስተካከል ህመም ነው።
ሆኖም ግን ሌሎች ከ Herps ቫይረስ ውጪ ባሉ ምክንያቶች የሚከሰቱ የአፍ ውስጥ እና አካባቢው ቁስለቶችም አንዳዴ በምልክት መመሳሰል የተነሳ በሰዎች ዘንድ ምች ተብለው ሊገለፁ እንደሚችሉም ማስተዋል ያስፈልጋል።
እናም በዚህ ፅሁፍ ላይ' ምች' ስል ለመገልፅ እየሞከርኩ ያለሁት በ herps ቫይረስ ሚከሰተውን እና ከአብዛኛው ማህበረሰባችን የምች ምልክቶች አገላለፅ ጋር የሚጣጣመውን 'Oral Herps' መሆኑን ቀድሜ ላስገነዝብ እፈልጋለሁ።
ምች/Oral Herps
ይህ 'Herps simplex virus 1 (HSV-1) ተብሎ በሚታወቅ የቫይረስ አይነት የሚመጣ በአፍ ውስጥ ስጋዎች (ምላስ : ድድ...): ከንፈር እና አካባቢው ባለው ቆዳ ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን ነው።
ሁለት አይነት የ HSV አይነቶች ሲኖሩ HSV-1 አፋ እና አካባቢውን ሲያጠቃ HSV-2 ተመሳሳይ ኢንፌክሽን በመራቢያ አካላት ላይ ያስከትላል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 3.8 ቢሊየን (64%) እድሜያቸው ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች የOral Herps (ምች) የሚያመጣው ቫይረስ ተጠቂዎች ናቸው።
ቫይረሱ እንዴት ነው የሚሰራው?
ምች (Oral herps) በከፍተኛ ሁኔታ ተላላፊ ኢንፌክሽን ሲሆን በዋነኝነትም በቀጥታ የበሽታው ምልክት (ቁስለት : እብጠት : ምራቅ..) ጋር በሚደረግ ቀጥተኛ ንክኪ ይተላለፋል።
አንዳንድ ጊዜ ምንም ምልክቱ ከማይታይባቸው (ከሌለባቸው) የቫይረሱ ተሸካሚ ሰዎችም ጋር በሚደረጉ የጠበቁ ንክኪዎች (በመሳሳም : በምራቅ...) ሊተላለፍ ይችላል።
አንድ ሰው አንዴ በዚህ ቫይሰረስ (HSV-1) ከተጠቃ (ቫይረሱ ወደ ሰውነቱ ከገባ) ቡሀላ; ቫይረሱ እድሜ ልኩን አብሮት የሚኖሮ ሲሆን ፤ አብዛኛውን ወቅት ላይ ግን ምንም አይነት ምልክቶችን (ህመሞችን) አያሳይም።
ቫይረሱ አንዴ ወደሰውነታችን ከገባ ቡሀላ አብዛኛው ጊዜውን ፊታችን አካባቢ በሚገኝ ነርቭ ህዋስ (Trigeminal ganglion) ውስጥ ተደብብቆ(ፀጥ ብሎ/አድፍጦ/Dormant/inactive) የሚቀመጥ ሲሆን ፤ ምቹ አጋጣሚዎችን ሲያገኝ ግን ከመጠን በላይ በመራባት እና በመሰራጨት ጥቃት መፈፀሙን ጀምሮ ጉዳቶቹን/ምልክቶችን በአፍ ውስጥ ከንፈር እና አካባቢው ላይ ያሳያል። የዚያኔ 'ምች መታኝ' ወይም Oral Herps ተከሰተ እንላለን።
ምልክቶቹ
1. የህመም ስሜት ያለቸው ውሀ የቋጠሩ ሚመስሉ ትንንሽዬ እብጠቶች
2. የተላጠ ቁስለት (እብጠቶቹ ፈንድተው ሊፈጠር ሚቾል ቁስለት አይነት)
3. በተጨማሪም ማቃጠል: ማሳከክ: መውጋት: የመቅላት... አይነት ስሜቶች ሊኖሩ ይችላሉ
እንዲሁም ኢንፌክሽኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ የተከሰተው ከቁስለቶቹ እና እብጠቶች በተጨማሪ የሰውነት ህመም : ትኩሳት :ራስ ምታት :የጉሮሮ ህመም እና አንገት አካባቢ ያሉ ንፍፊቶች (cervical lymphnodes) እብጠት ሊኖር ይችላል።
ምች አንድ ሰው ላይ ለምን በየጊዜው ይመላለስ? (Recurrent Oral herps)
ምች ድንገት ወይም ደግሞ በተለያዩ አጋላጭ ነገሮች ምክንያት ሊነሳ ይችላል
ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው አንዴ ሰውነታችን ከገባ ቡሀላ የማይወጣ እና አፍ አካባቢ በሚገኝ ነርቭ ህዋሳችን ውስጥ በትንሽ መጠን ራሱን ደብቆ በአብዛኛው ምንም ምልክት ሳያሳይ (ጉዳት ሳያደርስ) አጋጣሚዎችን እየጠበቀ የሚኖር ሲሆን ፤ ራሱን ለማውጣት አቅም በሚያገኝበት እና ይበልጥ መራባት የሚችልበት እድል ሲያገኝ የተለመደው የአፍ እና አካቢው ቁስለቶች እብጠቶች እና ህመሙን ያስከትላል።
ለቫይረሱ አቅም ማግኘት እና ድጋሚ ህመም የመፍጠር ብቃትን የሚሰጡት ነገሮች ምንድናቸው?
1. አጠቃላይ የሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም ሲኖር
2. የተለያዩ የሰውነት ህመሞች ወይም ትኩሳት ሲኖር
3. ቀጥታ ፊታችንን ለፀሀይ ጨረር በምንጋለጥበት ወቅት
4. ከፋተኛ ጭንቀት: ድባቴ:.. በሚኖርበት ወቅት
5. የወር አበባ እና የሆርሞን መቀያየር ሲኖር
6. አፍ አካባቢ አደጋ ወይም ቀዶ ህክምናዎች
እነዚህ ከላይ የተገለፁ አጋላጭ ምክንያቶች በሚኖሩበት ወቅት በዋነኝነት የሰውነታችን አጠቃላይ በሽታን የመከላከለ አቅም ስለሚዳከም አካባቢያዊ ምክንያቶችም ተዳብለው ቫይረሱ በቀላሉ ከተደበቀበት ወጥቶ በመራባት እና በመሰራጨት አፋችን እና አካባቢው ላይ ጉዳቶቹን (ህመመሞቹን) ያስከትላል።
እውን እንዳንድ ምግቦች ምችን ያስከትላሉ?
እስካሁን ባለው ተጨባጭ የትኛውም አይነት ምግብ በቀጥታ ምች (Oral herps) ያመጣል ተብሎ አይታሰብም።
ሆኖም ግን አንዴ ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ገብቶ ከተደበቀ ቡሀላ አንዳንድ የምግብ አይነቶች ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች ቫይረሱ እንዲነቃቃ እንዲራበ እና ህመም እንዲፈጥር ሊያደርጉት ይችላሉ።
አመጋገባችን ታድያ በሁለት አይነት መንገድ ቫይረሱን ጉልበት እንዲያገኝ (እንዲነቃቃ) ሊያደርገው ይችላል
1. አመጋገባችን በቂ እና ተመጣጣኝ ሳይሆን ሲቀር እና የሰውነት የመከላከል አቅማችንን መደገፍ ሲሳነው
2. አንዳንድ የምግብ አይነቶች በውስጣቸው የያዙት ኬሚካል (አርጂኒን የተባለ ፕሮቲን) የቫይረሱን የመራባት እና የመስራት አቅም ስለሚጨምር
ጥናቶች እንደሚያሳዩት 'አርጂኒን 'የተባለው በተለያዩ የምንመገባቸው መአዶች ውስጥ የሚገኝ ፕሮቲን(አሚኖ አሲድ) የተወሰኑ ቫይረስ አይነቶች እድገትን በሰውነታችን ውስጥ የሚያነቃቃ እና የሚደግፍ ሲሆን ከእነሱም አንዱ ደግሞ ምች የሚስከትለው ቫይረስ HSV1 ነው።
ሰለሆነም አንዳንድ ሰዎች የተመረጡ ምግቦችን በልተው ለፀሀይ ሲጋለጡ በተደጋጋሚ ወዲያው ምች ይመታናል የሚሉት አንዱም ምክንያት ;ምን አልባትም ምግባቸው ከፍተኛ አርጂኒን ይዘት ያለው ሆኖ :፤ ቫይረሱ ፀሀይ እና አርጂኒኑ አንድ ላይ ድንገት ተገጣጥመውለት በአንዴ ከፍተኛ ጉልበት አግኝቶ ተጠቅሞበት ሊሆን ይችላል።
ምች ይታከማልን?

አብዛኛውን ጊዜ የሰውነት በሽታ መከላከል አቅማቸው ደህና የሆኑ እና ብዙም 'ያልተጎዱ' ሰዎች ከሽታው በራሳቸው ከአንድ እስከ ሁለት ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገግማሉ
በተጨማሪም የተለያዩ መድሀኒቶች ምችን ለማከም ሊታዘዙ የሚችሉ ሲሆን ፤ህክምናውም በዋነኝነት በተቻለ አቅም በፍጥነት የህመሙን ስሜቶች ቁስለቶችን እና ደረጃ መቀነስ እና ማጥፋት ነው
እንዲሁም አንዳንዴ ምች በጣም በተደጋጋሚ የሚያስቸግራቸው ሰዎች ከቅድመ ጥንቃቄዎች በተጨማሪ አነስተኛ መጠን ያለው ፀረ ቫይረስ መድሃኒት በየቀኑ አንዴ መውሰዱ (Suppressed therapy ) ድግግሞሹን ለመቀነስ ሊረዳቸው ይችላል።
እንዴት መከላከል ይቻላል?
1. የምች ምልክት ከሚያሳዩ ግለሰቦች ጋር ቀጥታ የአፍ ንክኪን መቀነስ (መሳሳም: የገራ መጠጫዎች...
2. የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እና የሰውነት ጤናን መጠበቅ
3. በቂ ፈሳሽ መውሰድ
4. በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ
5. ጭንቀት:ድባቴ... መቀነስ
6. በ'አርጅኒን' ይዘት ባላቸው ምግቦች ምክንያት የሚመጣን የቫይረስ መነቃቃት ለመቀልበስ 'ላይዚን' በተባለው ፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን (እርጎ :አይብ: አፕል: አሳ...) ማዘውተር ወይም የላይዚን ሰፕልመንት ፒልሶችን መጠቀም።
7. እለንዲሁም ለፀሀይ ጨረር በመጋለጥ ምክንያት ምች በተደጋጋሚ ለሚያጠቃቸው በተቻለ መጠን ራስን ከቀጥታ የፀሀይ ጨረር ተጋላጭነት ማራቅ እና የፀሀይ መከላከያዎችን (Sunscreens) መጠቀም ይመከራል።
በመጨረሻም ፥ 'ምች አይምታቹ'
*ማጣቀሻ መፀሀፍት መረጃዎች
1. World Health Organization (WHO)
https://www.who.int
2. National Institutes of Health (.gov)
https://pmc.ncbi.nlm.nih.gov
Treatment and prevention of herpes labialis

www.who.int
World Health Organization (WHO)
The United Nations agency working to promote health, keep the world safe and serve the vulnerable.
❤2
🌸 የቤተሰብ ዕቅድ (Family Planning) 👨👩👧👦
የቤተሰብ ዕቅድ ማለት ቤተሰብ የሚፈልገውን የልጆች ብዛትና የእርግዝና ጊዜ በራሱ መወሰን እና ይህንን ለማሳካት የተለያዩ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም ነው።
💚 የቤተሰብ ዕቅድ ጥቅሞች
• ያልታቀደ እርግዝናን ይቀንሳል።
• በእርግዝናዎች መካከል በቂ ጊዜ እንዲኖር ይረዳል።
• የእናትንና የሕፃንን ጤና ለመጠበቅ ይረዳል።
• ቤተሰብ የሚፈልገውን የልጆች ብዛትና የቤተሰብ ወጪ ለማቀድ ያግዛል።
• በቅርብ የሚከሰቱ እርግዝናዎችን በመቀነስ አንዳንድ የጤና ችግሮችን ይቀንሳል።
⚠️ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች ሊያስከትሉ የሚችሉ ጎንዮሽ ተፅዕኖዎች
ጎንዮሽ ተፅዕኖው እንደ ዘዴው ይለያያል።
1️⃣ ኪኒን (Pill) 💊
• የጭንቅላት ህመም
• የወር አበባ ለውጥ
2️⃣ የሶስት ወር መርፌ (Depo/Injection) 💉
• የወር አበባ መዛባት
• የወር አበባ ሊቆም ይችላል
• የሰውነት ክብደት ሊጨምር ይችላል
3️⃣ ኢምፕላንት (Implant)
• የወር አበባ መዛባት ወይም ያልተለመደ ደም መፍሰስ
• የጭንቅላት ህመም
4️⃣ የማህፀን ውስጥ መሳሪያ (IUD)
• አንዳንድ የIUD አይነቶች የወር አበባን ሊያበዙ እና የሆድ ቁርጠትን ሊያስከትሉ ይችላሉ።
• ሆርሞን ያለው IUD ግን የወር አበባን ሊያሳንስ ይችላል።
5️⃣ ኮንዶም (Condom) 🛡️
• ከእርግዝና በተጨማሪ ከብዙ የጾታ ግንኙነት በሽታዎች ለመከላከል ይረዳል።
• አንዳንድ ሰዎች ላይ የቆዳ መቆጣት ወይም አለርጂ ሊያመጣ ይችላል።
• በትክክል ካልተጠቀሙበት የእርግዝና እድል ሊኖር ይችላል።
6️⃣ ቋሚ የመከላከያ ዘዴ (Sterilization)
• ቋሚ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ነው።
• ከተደረገ በኋላ ወደ ኋላ መመለስ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።
📌 ማስታወሻ: አንድ የቤተሰብ ዕቅድ ዘዴ ለአንድ ሰው ተስማሚ ሲሆን ለሌላ ሰው ላይሆን ይችላል። ስለዚህ ዘዴ ከመምረጥዎ በፊት ከጤና ባለሙያ ጋር መማከር ይመከራል።

መሰረታዊ የአእምሮ ሕመም ምልክቶች
የጭንቀት ደረጃዎች ከሰው ወደ ሰው ቢለያዩም ፣ ከደካማ የአእምሮ ጤንነት ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ አንዳንድ የተለመዱ ምልክቶች አሉ ፡፡
መሠረታዊ የአእምሮ ጤንነት ደካማ እንደሆነ የሚያመለክቱ ማስጠንቀቂያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
🖊 ብዙ አካላዊ የሆኑ የሕመም ቅሬታዎች (እንደ፦ ራስ ምታት እና የሆድ ሕመም)
🖊 አፅዕኖት ያላቸው ኑሮን የሚጎዱ የሕይወት ክስተቶች (ሥራ ማጣት ፣ ወዘተ)
🖊 አደገኛ የወሲብ ባህሪ
🖊የተራዘመ አፍራሽ (አሉታዊ)ስሜት
🖊ስለሞት ወይም ራስን ስለማጥፋት ማሰብ ወይም በሃሳብ መጠመድ
🖊አልኮል እና/ ወይም አደንዛዥ ዕፅ አላግባብ መጠቀም
🖊በንጽህና ላይ ያለ ለውጥ፤ ራስን የመንከባከብ ጉድለት
🖊 የታዘዘ መድሃኒት ስለምግብ ፣ ስለክብደት ፣ ስለአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም ስለአካል ምስል በሃሳብ መጠመድ
🖊 ራስን መጉዳት ወይም ራስን የሚያጠፋ ባህሪ። (ማለትም፦ አካልን መቁረጥ ፣ አካልን ማቃጠል ፣ ፀጉር መንጨት ወዘተ)
🖊 ተደጋጋሚ የቁጣ ጩኸት ፣ ጠበኝነት
የአዕምሮ ሕመም ሕክምና
ብዙዎቹን የአእምሮ ሕመሞች ማከም ይቻላል። የአእምሮ ሕመም ሲጀምር የሚታዩ ምልክቶችን ለይቶ ማወቅና አስቀድሞ ሕክምና መሻት ጠቃሚ
ነው። ህክምና ቶሎ ከጀመሩ የመዳን እድልዎ ከፍ ያለ ነው።
ከተለመዱት አንዳንድ የአእምሮ
ሕመም ሕክምናዎች መካከል የሚከተሉትን ያካትታሉ ;-
👉የስነልቦና ህክምና (psychotherapy)
👉የማህበረሰብ ድጋፍ ማግኘት
👉 መልሶ ማቋቋም
👉 ች ግ ሩን ከሚ ያ ባብሱ
ነ ገሮች መራቅ፤ አልኮል ከመጠጣት እና ከአደንዛዝ መድሓኒቶች/ዕፆች
👉 እራስን የማከምና ጥሩ ሕይወትን
በሚገባ መምራት ላይ ማተኮር።
https://t.me/HealthLib

Telegram
Health Science Library
For any fields of Health Science, Giudelines,Books,Lecture notes and Research PDFs are available Here.
❤3
የአስም በሽታ አጠቃላይ ሕክምና እና እንክብካቤ (Asthma Management & Treatment)
አስም የአየር ቧንቧዎች መጥበብ፣ ማበጥና ከመጠን ያለፈ ንፍጥ ማመንጨት ምክንያት የመተንፈስ ችግር የሚያስከትል ሥር የሰደደ የጤና እክል ነው። የአስም ሕክምና ዋና ዓላማ ምልክቶቹን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር፣ ድንገተኛ የአስም ጥቃትን (Asthma attack) መከላከል እና የሳንባን ጤና መጠበቅ ነው።
——————————
1. የመድኃኒት ሕክምና (Medical Treatments)
የአስም መድኃኒቶች በዋናነት በሁለት ይከፈላሉ፦
ሀ. ፈጣን እፎይታ ሰጪ መድኃኒቶች (Reliever / Rescue Medications)
እነዚህ መድኃኒቶች ድንገተኛ የትንፋሽ ማጠር፣ ሳል ወይም ፉጨት በሚከሰትበት ጊዜ ወዲያውኑ እፎይታ ለመስጠት ያገለግላሉ።
• አሠራራቸው፦ የተኮማተሩትን የአየር ቧንቧ ጡንቻዎች በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በማዝናናት አየር በቀላሉ እንዲገባና እንዲወጣ ያደርጋሉ።
• ዋና ዋናዎቹ፦
• ሳልቡታሞል (Salbutamol / Albuterol - SABA) በኢንሄለር (በአፍ በሚሳብ) መልክ።
• አጠቃቀም፦ አስም ሲቀሰቀስ ወይም ድንገተኛ ችግር ሲያጋጥም ብቻ የሚወሰዱ ናቸው።
ለ. የረጅም ጊዜ ተቆጣጣሪ መድኃኒቶች (Controller / Preventer Medications)
እነዚህ መድኃኒቶች ሕመሙ እንዳይቀሰቀስና የአየር ቧንቧ እብጠት እንዳይከሰት በየቀኑ በቋሚነት የሚወሰዱ ናቸው (ምልክት ባይኖርም እንኳ መወሰድ አለባቸው)።
• አሠራራቸው፦ በአየር ቧንቧ ውስጥ ያለውን እብጠትና ንዴት በመቀነስ ቧንቧው ስሜታዊ እንዳይሆን ያደርጋሉ።
• ዋና ዋናዎቹ፦
• በአፍ የሚሳቡ ስቴሮይዶች (Inhaled Corticosteroids - ICS)፦ እንደ Budesonide, Fluticasone, Beclomethasone የመሳሰሉት።
• የተቀናጁ መድኃኒቶች (ICS + LABA)፦ እብጠትን የሚቀንሱ እና የረጅም ሰዓት የአየር ማስፊያዎችን በአንድ ላይ የያዙ (ምሳሌ፡ Symbicort / Budesonide+Formoterol, Seretide / Fluticasone+Salmeterol)።
• (Tablets)፦ እንደ ሞንቴሉካስት (Montelukast) ያሉ የአለርጂ ምላሽን የሚቀንሱ መድኃኒቶች።
ሐ. ድንገተኛ የፅኑ አስም ሕክምና (Emergency / Severe Asthma Treatment)
ሕመሙ በጣም ሲበረታና በተለመደው ኢንሄለር ሳይሻል ሲቀር በሆስፒታል ደረጃ የሚሰጥ፦
• በኔቡላይዘር (Nebulizer) ማሽን አማካኝነት መድኃኒት በእንፋሎት መልክ መስጠት።
• በደም ሥር ወይም በጡንቻ የሚሰጡ ስቴሮይዶች (Hydrocortisone/Dexamethasone) ወይም የአፍ ኪኒኖች (Prednisolone)።
• የኦክስጅን ድጋፍ (Oxygen therapy) መስጠት።
——————————
2. አስምን የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መከላከል (Trigger Avoidance)
የአስም መድኃኒት ከመውሰድ ባልተናነሰ ሕመሙን ከሚቀሰቅሱ ነገሮች መራቅ ወሳኝ ነው፦
1. አቧራና ጭስ፦ ከእንጨት፣ ከከሰል፣ ከሲጋራ ጭስ እንዲሁም ከመኪና ጢስ መራቅ።
2. ሽቶና ኬሚካሎች፦ ጠንካራ መዓዛ ካላቸው ሽቶዎች፣ የጽዳት ሳሙናዎችና ኬሚካሎች መራቅ።
3. ቀዝቃዛ አየር፦ በማለዳና በምሽት ቀዝቃዛ አየር ሲኖር አፍና አፍንጫን በሻርፕ መሸፈን።
4. የቤት እንስሳት፦ የድመት፣ የውሻ ፀጉር ወይም ፎረፎር አለርጂክ ለሆኑ ሰዎች ሕመሙን ስለሚቀሰቅስ ከቤት ማራቅ።
5. ኢንፌክሽኖች፦ ጉንፋን፣ ሳይነስ እና የደረት ኢንፌክሽን አስምን ስለሚያባብሱ ወቅታዊ የጉንፋን ክትባቶችን መውሰድና ከታመሙ ሰዎች መራቅ።
6. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፦ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት አስም የሚነሳ ከሆነ ከስፖርት በፊት የሚወሰደውን አዳኝ ኢንሄለር (Salbutamol) በሐኪም ትዕዛዝ አስቀድሞ መውሰድ።
——————————
3. ኢንሄለርን (Inhaler) በትክክል የመጠቀም መመሪያ
መድኃኒቱ ወደ ሳንባ በሚገባ እንዲደርስ አጠቃቀሙን ማወቅ አስፈላጊ ነው፦
1. ኢንሄለሩን በደንብ ማወዛወዝ።
2. በውስጥ ያለውን አየር ሙሉ በሙሉ ወደ ውጭ ማውጣት (መተንፈስ)።
3. የመድኃኒቱን አፍ በአፍ ውስጥ አስገብቶ ከንፈርን በጥብቅ መዝጋት።
4. መድኃኒቱን እየጫኑ ወደ ውስጥ በረጅሙና በዝግታ መሳብ።
5. አየርን ከሳቡ በኋላ ትንፋሽን ከ 5 እስከ 10 ሰከንድ ያህል አምቆ ማቆየት፤ ከዚያም በዝግታ መልቀቅ።
6. ስቴሮይድ ያለበትን ኢንሄለር ከተጠቀሙ በኋላ የአፍ ውስጥ ቁስለት ወይም ፈንገስ እንዳይከሰት አፍን በውሃ መጉመጥመጥና መትፋት።
——————————
4. ወደ ድንገተኛ ሕክምና ክፍል መሄድ የሚገባው መቼ ነው?
• ኢንሄለር (Salbutamol) ወስደው ምንም እፎይታ ካልተሰማዎት።
• አረፍ ብለው እንኳን በከፍተኛ ሁኔታ ትንፋሽ ካጠረዎት።
• በሚናገሩበት ወቅት ሙሉ ዓረፍተ ነገር ሳይጨርሱ ትንፋሽ የሚያጥርዎት ከሆነ።
• የከንፈር ወይም የጥፍር ጫፎች ወደ ሰማያዊነት ከተቀየሩ ወዲያውኑ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።
(ማሳሰቢያ፦ ማንኛውንም የአስም መድኃኒት መጠንና ዓይነት ከመቀየርዎ ወይም ከመውሰድዎ በፊት ከሐኪምዎ ጋር መማከር አስፈላጊ ነው።)

የstroke (የአንጎል የደም ስር ችግር) 9 ምልክቶች
አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ የሚሹ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች
——————————
1. የፊት መዛባት (Face Drooping)
• ከአንዱ የፊት ክፍል በድንገት መስቀል ወይም ወደ ታች መንሸራተት።
2. የእጅ ድካም (Arm Weakness)
• አንዱ እጅ ሊደክም ወይም ወደ ታች ሊንሸራተት/ሊወርድ ይችላል።
3. የመናገር ችግር (Slurred Speech)
• ንግግር ግልጽ ያልሆነ ወይም ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።
4. በአንድ በኩል በድንገት የመደንዘዝ ስሜት (Sudden Numbness on One Side)
• ፊት፣ እጅ ወይም እግር በድንገት የመደንዘዝ ስሜት ሊኖረው ይችላል።
5. በድንገት የመራመድ ችግር (Sudden Trouble Walking)
• መራመድ መረጋጋት ማጣት ወይም ከባድ ሊሆን ይችላል።
6. ድንገተኛ የማዞር ስሜት ወይም ሚዛን ማጣት (Sudden Dizziness or Loss of Balance)
• በድንገት ሚዛን የማጣት ወይም የማዞር ስሜት ሊሰማዎት ይችላል።
7. ድንገተኛ የማየት ችግር (Sudden Vision Problem)
• እይታ ብዥ ሊል ወይም በአንዱ ወይም በሁለቱም ዓይኖች ማየት ሊሳን ይችላል።
8. ድንገተኛ የመደናገር ስሜት (Sudden Confusion)
• ነገሮችን መረዳት ወይም ምላሽ መስጠት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።
9. ከባድና ድንገተኛ የራስ ምታት (Severe Sudden Headache)
• በድንገት የሚመጣ በጣም ከባድ የራስ ምታት የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል።

አጣዳፊ ወይም ድንገተኛ የሆድ ሕመም (Acute Abdominal Pain) መንስኤዎችን፣ መለያ ምልክቶችን እና ህክምና ፦
1. የሆድ ሕመም መንስኤዎች በመገኛ ቦታ (Common Causes by Location)
የሆድ ክፍል ሕመም የሚሰማበት ቦታ ትክክለኛውን በሽታ ለመለየት ትልቅ ፍንጭ ይሰጣል፡
• በቀኝ በኩል የላይኛው የሆድ ክፍል (RUQ): የሐሞት ከረጢት እብጠት/ቁርጠት፣ የጉበት ብግነት (Hepatitis)
• በግራ በኩል የላይኛው የሆድ ክፍል (LUQ): የጨጓራ ብግነት/ቁስለት፣ የጣፊያ ብግነት (Pancreatitis)፣ የሳንባ ምች (የሳንባ የታችኛው ክፍል)።
• የመሃል የላይኛው ክፍል (Epigastric): የጨጓራ ቁስለት በሽታ (Peptic ulcer)፣ የጨጓራ አሲድ ወደ ላይ መመለስ (GERD)፣ የጣፊያ ብግነት።
• በቀኝ በኩል የታችኛው የሆድ ክፍል (RLQ): የትርፍ አንጀት እብጠት (Appendicitis)፣ የሽንት ቱቦ ጠጠር፣ ወይም የማህፀንና የእንቁላል ከረጢት ችግሮች።
• በግራ በኩል የታችኛው የሆድ ክፍል (LLQ): የአንጀት ግድግዳ ከረጢት ኢንፌክሽን (Diverticulitis)፣ ከባድ የሆድ ድርቀት፣ የሽንት ቱቦ ጠጠር።
• በመላው ሆድ የሚሰራጭ ሕመም (Diffuse): የጨጓራና አንጀት ኢንፌክሽን፣ የአንጀት መዘጋት/መታጠፍ፣ የሆድ ዕቃ ሽፋን ብግነት (Peritonitis)።
——————————
2. አስደንጋጭ ወይም አስቸኳይ ቀዶ ጥገና የሚሹ ምልክቶች (Red Flags)
እነዚህ ምልክቶች ከታዩ ታካሚው በአስቸኳይ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ አለበት፡
• የሆድ መደንደል ወይም መሸከርከር (ሆድ ሲነካ እጅግ በጣም መለብለብና ጠንካራ መሆን)።
• ቢጫ ወይም አረንጓዴ መግል የመሰለ ነገር ማስመለስ።
• ከሆድ ዕቃ ደም መፍሰስ (በአፍ ማስታወክ ወይም በፊንጢጣ ደም መውጣት)።
• እርጉዝ ሴት ላይ የሚከሰት ድንገተኛ የሆድ ሕመም።
• የደም ግፊት መውረድ እና የልብ ምት እጅግ በጣም መጨመር።
——————————
3. ዋና ዋና የሕክምና እርምጃዎች (Management Principles)
1. ታካሚውን ማረጋጋት: በደም ስር ፈሳሽ (IV fluids) መስጠት።
2. ምግብና ውሃ በአፍ አለመስጠት (NPO): ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግ ስለሚችል በአፍ ምንም ነገር እንዳይወሰድ ማድረግ።
3. የሕመም ማስታገሻ መስጠት።
4. የቀዶ ጥገና ሐኪም ማማከር።

❤5
የሆድ ህመም - የማስጠንቀቂያ ምልክቶች፦
እንደ ህመሙ ቦታ የተከፋፈሉ ዓይነቶች፡
• የላይኛው የሆድ ክፍል (Upper Abdomen)፦
• የጨጓራ እብጠት (Gastritis)
• የጨጓራ ቁስለት (Ulcer)
• የጣፊያ እብጠት (Pancreatitis)
• የሐሞት ከረጢት ድንጋይ (Gallstones)
• የታችኛው የሆድ ክፍል (Lower Abdomen)፦
• የትርፍ አንጀት ህመም (Appendicitis)
• የሽንት ትቦ ኢንፌክሽን (UTI)
• አንጀት ህመም (IBS)
• የማህፀን / የስነ-ተዋልዶ ህመም ችግሮች (Gynecological issues)
• በመላው ሆድ የሚሰራጭ ህመም (Generalized Pain)፦
• የምግብ አለመፈጨት (Indigestion)
• የሆድ ውስጥ ኢንፌክሽን (Infection)
• የምግብ መመረዝ (Food poisoning)
✅ ሐኪም ማየት የሚገባዎት መቼ ነው?
በጣም ብርቱ ወይም ድንገተኛ ህመም ሲኖር
✔ ህመሙ ከትፋት፣ ከትኩሳት ወይም ከዓይን/ቆዳ ቢጫ መሆን (ጃውንዲስ) ጋር ሲያጋጥም
✔ በሰገራ ወይም በትፋት ውስጥ ደም ሲኖር
✔ አየር (ጋዝ) ወይም ሰገራ ማውጣት አለመቻል
✔ የሆድ ማበጥ / ማፈፋት
✔ ህመሙ ከ24 ሰዓታት በላይ ሲቆይ
አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ የሚሹ አደገኛ ሁኔታዎች (Red Flag Conditions)፦
✔ የትርፍ አንጀት ህመም (Appendicitis)
✔ ከማህፀን ውጭ ያለ እርግዝና (Ectopic pregnancy)
✔ የሐሞት ከረጢት ድንጋይ (Gallbladder stones)
✔ የኩላሊት ድንጋይ (Kidney stones)
✔ የአንጀት መዘጋት (Intestinal obstruction)
✔ የጣፊያ እብጠት (Pancreatitis)
——————————
ማስታወሻ፦ ሁሉም የሆድ ህመሞች ቀላል አይደሉም — በጊዜ የሚደረግ ምርመራ ሕይወትን ያድናል።
(እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው ከላይ የተጠቀሱትን አደገኛ ምልክቶች የሚያሳይ ከሆነ፣ በአስቸኳይ ወደ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የሕክምና ተቋም በመሄድ የሐኪም እርዳታ ማግኘት ይመከራል።)

#የጤና ባለሙያዎች የሙያ ስያሜ አሰጣጥ
ሀ. የሙያ ስያሜ ደረጃዎች
1. Junior
2. Senior
3. Chief
4. Expert
5. Senior Expert
6. Chief Expert
7. Consultant
ለ. ዝርዝር መስፈርቶች
1. ለባለሙያ የሚሰጠው የሙያ ስያሜ የባለሙያውን የትምህርት ዝግጅት መሰረት ያደረገ ይሆናል።
2. በተ.ቁ 1 ላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለባለሙያው የሚሰጠው የሙያ ስያሜ የአገልግሎት ዘመንን መሰረት በማድረግ Junior, Senior, Chief, Expert, Senior Expert, Chief Expert እና Consultant በሚል ደረጃ ይሆናል።
3. የሙያ ስያሜ ከአንዱ ደረጃ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ለመሸጋገር በሙያው 3 ዓመት ማገልገል ይኖርበታል።
4. የሙያ ስያሜዎቹ በትምህርት ደረጃ (ዲፕሎማ፣ ዲግሪ፣ ማስተርስ፣ ወዘተ) እራሳቸውን ችለው የሚቆሙ ይሆናሉ፤ ከአንደኛው የትምህርት ደረጃ ወደ ሌላኛው ደረጃ የሚሸጋገር የስራ ልምድ አይኖርም።
5. ይህ የሙያ ስያሜ አሰጣጥ ከደመወዝና ከደረጃ እድገት ጋር ግንኙነት የለውም።
6. ማስተርስ፣ ህክምናና ከዚያ በላይ ያሉ ባለሙያዎች ወደ ኮንስልታንት ደረጃ ለመድረስ 15 ዓመት የስራ ልምድ እና ሁለት ጥናት በታወቀ ጆርናል ማሳተም ይጠበቅባቸዋል፤ አተገባበሩም፦
ሀ) በግል ወይም የምርምሩ ባለቤት (principal investigator) ሆኖ ምርምር ሲሰራ፤
ለ) ምርምሩ በታወቀ ጆርናል መታተሙ በጤና ሚኒስቴር የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ተረጋግጦ ማስረጃ ሲቀርብ።
ማሳሰቢያ፦ "ሀ" እና "ለ" ን ያሟሉ ሁለት ጥናቶች እያንዳንዳቸው እንደ አንድ ዓመት የስራ ልምድ ይያዛሉ፤ ሆኖም በአንድ ዓመት ውስጥ ከሁለት በላይ ምርምር ቢታተምም ተጨማሪው እንደ ስራ ልምድ አይያዝም።
7. የሙያ ፈቃድ የሚሰጠው መመዘኛ ግዴታ ለሆነባቸው የሙያ ዘርፎች ብቻ ነው።
8. የብቃት ማረጋገጫ (ብቃት ምዘና) ፈተና መውሰድ የሚገባቸው የጤና ባለሙያዎች፣ የሙያ ፈቃድ የሚያገኙት ፈተናውን ካለፉና በፈታኙ አካል ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
9. በሰብ-ስፔሻሊቲ ወይም በሱፐር-ስፔሻሊቲ ከአንድ ዓመት በታች ተምሮ የተመለሰ ባለሙያ፣ የሰብ-ስፔሻሊቲ/ሱፐር-ስፔሻሊቲ ብቃቱ በሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ተረጋግጦ ማስረጃ ሲቀርብለት የሙያ ስራ ፈቃድ ይሰጠዋል።
10. ሚኒስቴሩ ለሙያ ስያሜ አሰጣጥ አዲስ ሙያ ሲፈጠር፣ ጉዳዩ በሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት ይስተናገዳል።
11. ስለ የሙያ ስያሜ አሰጣጥ ተጨማሪ ዝርዝር በአባሪ 3 ላይ ማየት ይቻላል።