HaqCheck
428 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
ከApril’s fool ቀን ጋር ተያይዘው ከሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች ይጠንቀቁ

እንደ አውሮፓዉያን አቆጣጠር የሚያዚያ ወር መግቢያ ማለትም April 1, የ ኤፕሪል ዘፉል (April’s fool) ቀን ተደርጎ በብዙዎች ዘንድ ይከበራል፡፡ ይህን ተከትሎ የሚስተዋሉ ቀልዶች እና ፕራንኮች የሚያዝናኑ ቢሆኑም፣ ነገር ግን ሃሰተኛ ሆነው ሳለ እንደ እዉነተኛ ተደርገው በኦንላየን ላይ ከሚሰራጩ መረጃዎች መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

ምንግዜም ቢሆን መረጃዎች ሲያጋጥሙን

✍️ መረጃውን ከማመን በፊት ሌሎች አስተማማኝ የመረጃ ምንጮች ላይ ማረጋገጥ
✍️ የመረጃ ምንጩን መፈተሽ- እምነት የሚጣልበት ወይስ ለማሳሳት የሚሞክር?
✍️ በጣም እውነት የሚመስሉ እንኳን ቢሆኑም እውነት ላይሆኑ እንደሚችሉ ከግምት ዉስጥ ማስገባት ያስፈልጋል

ሁል ጊዜም ቢሆን መረጃን ከማጋራታችን በፊት እናጣራ!

ለተጨማሪ መረጃ 👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
4👍1🔥1
🌍 Today is International Fact-Checking Day!

🔍 Let's celebrate the power of truth and accuracy! Join us in the fight against misinformation and share reliable information.

🔎 At HaqCheck, we are committed to promoting fact-checking and debunking false claims. Together, we can build a more informed world.

🙌 Spread the word and stand up for the truth!

For more, visit our website and social media:

Website: www.haqcheck.org
Twitter: www.twitter.com/HaqCheck
TikTok: www.tiktok.com/@haqcheck
LinkedIn: www.linkedin.com/haqcheck
Facebook: https://www.facebook.com/HaqCheck

#InternationalFactCheckingDay #HaqCheck
🎉4🔥1
የሚስብ አርእስት ያላቸው መረጃዎች ሲያጋጥሙን ምን እናድርግ?
-------------------------
፩: ሙሉ መረጃውን ማንብብ/መመልከት

መረጃውን እውነት አድርጎ ከመቀበል በፊት ከርዕሱ በተጨማሪ በጹሑፍ ወይም በቪድዮው ውስጥ ያለውን መረጃ ማንብብ እና መመልከት ያስፈልጋል።

፪: የመረጃውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ

አጠቃላይ የመረጃውን ይዘት ከተረዳን በኋላ እውነት መሆን አለመሆኑን የተለያዩ የመረጃ ማጣሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም ፣ መፈተሽና መበየን።

፫: አጠራጣሪ ከሆነ ከማጋራት መቆጠብ

ከላይ እንደተገለጸው መረጃውን በአትኩሮት አጣርተን አጠራጣሪ ወይም ሃሳተኛ ሆኖ ካገኘነው መረጃውን አለማጋራት እና ምንም አይነት ግብረ መልስ አለመስጠት ይኖርብል።

ብዙ ጊዜ ርእሱን በጣም ሳቢ እና ማራኪ በማድረግ መረጃን የሚያሰራጩ አካላት ብዙ ተመልካች ለማግኝት እና ያንንም ዝና እና ገንዘብ ለማግኘት እንደሚጠቀሙበት መገንዘብ ያስፈልጋል።

ምንጊዜም ቢሆን መረጃን ከማጋራታችን በፊት እናጣራ!

ℹ️ ለተጨማሪ መረጃ: 👇


Website: www.haqcheck.org
Twitter: www.twitter.com/HaqCheck
TikTok: www.tiktok.com/@haqcheck
LinkedIn: www.linkedin.com/haqcheck
Facebook: https://www.facebook.com/HaqCheck

#HaqCheck #medialitracy #disinformation
👍4
✈️ Leaving Dire Dawa, Queen of the Desert, with enlightened minds and hearts full! 🌟 Inform Africa, alongside Addis Ababa University and the US Embassy in Addis, has just concluded an exhilarating fact-checking training. A giant leap towards truth in an era of misinformation, empowering voices with the skills to discern and debunk.

Our journey included a memorable visit to the Dire Dawa community radio studio, amplifying our impact.

Here’s to nurturing a well-informed society, one fact at a time.Farewell, Dire Dawa, until next time. 📚🔍🎙️ #FactChecking #InformAfrica #DireDawa #CommunityRadio
👍32
📢 Join Us:
Part-Time Finance Manager.

Hello, At Inform Africa, we're battling disinformation and boosting credible media across the continent. We're scouting for a Finance Manager with savvy financial skills and a passion for impact. Sound like you?

Your Role:

✍️ Manage our finances and navigate Ethiopian tax laws.
✍️ Leverage your expertise to boost our funds and reach.

You'll Need:

✍️ Degree in Finance/Accounting (CPA/CMA is a bonus).
✍️ 3+ years in finance, with Ethiopian taxation know-how.
✍️ Expert in finance software, Excel, and based in Addis Ababa.
✍️ Flexible hours, meaningful work.Impact media integrity in Ethiopia and beyond.

Interested? Send your CV and a brief cover letter to haqcheck@gmail.com Subject: “Finance Manager – Your Name”.

Deadline April 23, 2024

Let’s Make a Difference Together!

#wearehiring #finance #manager #jobopportunity #hiring #openposition #jobopening #jobs
👍3🙏1
🎉 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

ኢድ ሙባረክ !
👍2
በማህበራዊ ሚድያ ላይ የጥላቻ ንግግር ወይም ሆን ተብለው የተጋሩ ሃሰተኛ መረጃዎች ሲያጋጥምዎት የሚወስዱት እርምጃ ምንድነዉ?
Anonymous Poll
41%
ልጥፉን ሪፖርት አደርጋለሁ
5%
ሪፖርት ማድረግን አልመርጥም
32%
ችላ ብዬ ነው የማልፈዉ
22%
አዉንታዊ በሆነ መልኩ ሃሳብ እሰጣለሁ
Fact-checking training in action! 💡

Our team is currently in Arba Minch🇪🇹 , empowering undergraduate and postgraduate students of Arba Minch University to combat mis/disinformation through fact-checking.

Did you know that "Arba Minch" means "40 Springs," originating from the presence of more than 40 springs. The city has several tourist attractions, including Chamo and Abaya Lakes 🏞, Nech Sar National Park 🌳 and more.

Join us as we work together to promote truth and accuracy in the digital age!
#factchecking #misinformation #disinformation #haqcheck
👍32
5ቱ ለሃሰተኛ መረጃ ተጋላጭ በመሆናችን ምክንያት የሚመጡ አሉታዊ ውጤቶች

1️⃣ የእምነት መሸርሸር

ለሃሰተኛ መረጃ ተጋላጭነታችን እየጨመረ ሲመጣ እና እነዚህን መረጃዎች መቀበል ስንጀምር ታማኝ በሆኑ የዜና ምንጮች እና ባለሙያዎች ላይ ያለንን እምነት ይሸረሽራል።

2️⃣ የተሳሳተ ውሳኔ መስጠት
በሃሰተኛ መረጃ ተመስርተው በተለያዩ የሕይወት ዘርፎች ላይ ማለትም በጤና፣ በፋይናንስ እንዲሁም በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የተሳሳተ እና ጎጂ ውሳኔዎች ላይ ሊያደርሰን ይችላል።

3️⃣ አድሎአዊ ያደርጋል
ለተዛባ መረጃ መጋለጥ አድሎአዊነትን  ያስከትላል ፣ ይህም መረጃን በትክክል ለመገምገም እና ለመለየት አስቸጋሪ ያደርገዋል።

4️⃣ ጽንፈኝነትና እና ክፍፍልን ያመጣል
ሃሰተኛ መረጃ ጥቃቅን አሉታዊ  እምነቶችን ያጠናክራል ፣ ጽንፈኝነትን ያቀጣጥላል እንዲሁም ገንቢ የሆኑ ውይይቶች እንዳይኖሩ ያደርጋል፡፡

5️⃣ ስነ ልቦናዊ ውጥረት ያስከትላል
ለሃሰተኛ መረጃ በየጊዜው መጋለጥ ጭንቀትን እና ውጥረትን ይጨምራል ይህም በጊዜ ሂደት የአዕምሮ ደህንነትን ያዳክማል።


ምንጊዜም ቢሆን መረጃን ከማጋራታችን በፊት እናጣራ!


ℹ️ ለተጨማሪ መረጃ: 👇


Website: www.haqcheck.org
Twitter: www.twitter.com/HaqCheck
TikTok: www.tiktok.com/@haqcheck
LinkedIn: www.linkedin.com/haqcheck
Facebook: https://www.facebook.com/HaqCheck

#HaqCheck #medialitracy #combatingdisinformation
👍6🙏1
መለያ ገፅዎን(Account) በ2ተኛ ዙር የደህንነት ማረጋገጫ ይጠብቁ

ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ ያድርጉ
- ወደ አካውንቶ ሲገቡ (Log in) ሲሉ ተጨማሪ የማረጋገጫ ኮድ በስልክ ወይም በኤሜል እንዲደርስዎ ያድርጉ

ከመንታፊዎች እራሶን ይጠብቁ
- ሌሎች ሰዎች የይለፍ ቃልዎን (password) ቢያገኙ እንኳን ወደ መለያ ገፅዎ በቀላሉ ለመግባት (login) ለማለት አይችሉም፡፡

✍️ ለተጨማሪ መረጃ: 👇

Website: www.haqcheck.org
Twitter: www.twitter.com/HaqCheck
TikTok: www.tiktok.com/@haqcheck
LinkedIn: www.linkedin.com/haqcheck
Facebook: https://www.facebook.com/HaqCheck

#HaqCheck #medialitracy #disinformation #medialiteracy #digitalliteracy
2👍1
Monday reminder.

❗️Misinformation spreads beyond screens and pages.

❗️ Ensure accuracy when speaking to your loved ones and colleagues evey day.


ℹ️ For more: 👇


Website: www.haqcheck.org
Twitter: www.twitter.com/HaqCheck
TikTok: www.tiktok.com/@haqcheck
LinkedIn: www.linkedin.com/haqcheck
Facebook: https://www.facebook.com/HaqCheck

#HaqCheck #medialitracy #combatingdisinformation
🔥3👍2
ሃሰተኛ የማህበራዊ ገጾች ጉዳይ

የታዋቂ ግለሰቦችና ድርጅቶችን ስም ፣ፎቶ እና መለያ ሎጎን በመጠቀም የሚከፈቱ የማህበራዊ ሚድያ ገጾች እየተበራከቱ መጥተዋል፣ በዚህ መልኩ የሚከፈቱት ሃሰተኛ አካውንቶች ብዙ ተከታይ ለማግኘት ሲሉ የተለያዩ አጓጊ የስጦታ እይነቶችን እንደሚሰጡ ቃል በመግባት ብዙሃኑን እያጭበረበሩ እንደሆነ መመልከት ይቻላል።

እነዚህን ገጾች ጥሩ ተከታይ ካፈሩባቸው በኋላ ደግሞ ለሽያጭ እንደሚያቀርቧቸውም ተመልክተናል። ለምሳሌ 55,000 ተከታይ ያለውና በትምህርት ሚንስቴር ስም እና አርማ የተከፈተ የቴሌግራም ገጽ በ 26,000 ብር ለሽያጭ እንደቀረበ ከተያያዘው ምስል ላይ ወይም በዚህ ሊንክ መመልከት ይችላሉ

ከሰሞኑ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲቢኢ ብር የተከፈቱ  ሃሰተኛ የቴሌግራም ገጾች ስላሉ ይጠንቀቁ ሲል መልዕክቱን በማህበራዊ ገጹ አጋርቶናል።

ንግድ ባንክ እንደገልውጸው ሃሰተኛ ገጾቹ አባላትን ወደ ቻናሉ ስታስገቡ (add member) ሽልማት ታገኛላችሁ በሚል  የማጭበርበሪያ መልዕክት የተከታዮቻቸውን ቁጥር በማሳደግ ላይ እንደሆኑ ገልጿል።

በተጨማሪም ባንኩ በሲቢኢ ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገጽ እንደሌለው ገልጻል።

✍️ ለተጨማሪ መረጃ: 👇

Website: www.haqcheck.org
Twitter: www.twitter.com/HaqCheck
TikTok: www.tiktok.com/@haqcheck
LinkedIn: www.linkedin.com/haqcheck
Facebook: https://www.facebook.com/HaqCheck

#HaqCheck #medialitracy #disinformation #medialiteracy #digitalliteracy
👍5