HaqCheck
428 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
#Akeekkachiisaa

Dhiheenya kana akkaawuntiin TikToki hordoftoota kuma 244 ol qabu tokko lammiileen Itiyoophiyaa ta’an dhalattoota Oromoo Somaaliyaa gadhiisanii akka ba’an dirqisiifamaa jiruu jechudhan viidiyoo qoodera.

Odeeffannoo kanaan wal qabatee akkaawuntiin X Somaaliya nawu jedhamu tokko, ummanni Oromoo Somaaliyaa keessa jiraachuun isaanii jiruu keenyaaf balaa waan ta’eef, buqqisuu jalqabuu qabna jechudhan qodeera.

Jeequmsi akkanaa miidiyaa hawaasaa irratti tatamsa’aa jiraatus; Garuu viidiyoon qooddame kun viidiyoo ummanni Oromoon Soomaaliya keessa gadhiisanii yeroo bahan hin agarsiisuu.

Haqcheck dhuggumma viidiyoo kana akka sakkata’eeti kanan duraa bara 2016 ji’a Muddee keessatti marsariitii oduu NonStop Local jedhamu irratti ergaa barreeffamaa waa’ee godaantota kumaatamaan lakkaa’aman gara daangaa Ameerikaa deeman jedhu wajjin akka qoodame ture argatera.

#Factchecking #HaqCheck #Ethiopia
👏2👍1
የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎት(Digital literacy) አስፈላጊ የሆነባቸው 3 ምክንያቶች

1️⃣ እድሎችን ለማግኘት

በአሁኑ የዲጂታል አለም ዉስጥ የተለያዩ እድሎች ማለትም የትምህርት፣ የስራ፣ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት እና ከሌሎች ጋር ለመገናኘት ጥሩ የሆነ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎት ያስፈልጋል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎት ቴክኖሎጂን አዘውትረው ከሚጠቀሙ ሰዎች ጋር በአዲሱ የዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያስችሎታል።

2️⃣ እውነታውን ለመለየት

አሁን ላይ መረጃን በቀላሉ በእጃችን ባሉ የቴክኖሎጂይ ውጤቶች ማግኘት እንችላለን ሆኖም የመረጃውን እዉነታነት ማጣራት መሰረታዊ ነገር ነው። ይሁን እንጂ የዲጂታል ቴክኖሎጂይ አጠቃቀም ክህሎት ካለን የመረጃውን እዉነታ በቀላሉ እንድንለይ ያግዘናል።

3️⃣ የዲጂታል ደህንነትዎን ለመጥበቅ

ቴክኖሎጂን የሚጠቀመው የአለም ህዝብ እየጨመረ እንደመምጣቱ ሁሉ በዛዉ ልክ በኦንላይን ላይ የምንመለከታቸው የማጭበርበር ፣ የግላዊ መረጃዎች ምንተፋ፣ የጥላቻ ንግግሮች እና መሰል ሁነታዎች በእጅጉ እየጨመሩና ብዙ ሰዎችም የዚህ ሰለባ ሲሆኑ ይታያል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎት ያለዉ ሰዉ የእነዚህ ጥቃቶች ሰላባ እንዳይሆን የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የኦንላይን ላይ ደህንነቱን የሚጠብቅበት ክህሎት ይኖረዋል፡፡

ስለዚህ በዛሬው የዲጂታል ዓለም ውስጥ ያሉ እድሎችን ለመጠቀም፣ እዉነተኛ መረጃን ይከሀሰተኛዉ ለመለየት እና የኦንላይን ደህንነታችንን ጠብቀን ተወዳዳሪ ሆነን ለመገኘት የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎት እንዲኖረን በተለያየ መንገድ መማር እና ማወቅ ይኖርብናል።

#HaqCheck #digitalliteracy
👍51
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአማራ ክልል ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ ከ 30ሺ በላይ ተከታይ ያለው የ ቲክቶክ አካውንት በፋኖ እጅ የተማረኩ የመከላከያ ሰራዊት በማለት ቪዲዮ አጋርቷል።

ነገር ግን ሀቅቼክ እንዳጣራው ቪድዮው ህዳር ወር 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ መንግስት እና በህውሃት መካከል በነበረው ግጭት ወቅት በአንድ የትዊተር (X) አካውንት ላይ "ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ ወደ ጦር ግንባር መዝመታቸዉን ተከትሎ የትግራይ ሃይሎች የተማረኩ የኢትዮጵያ ጦር እስረኞችን የሚያሳይ ቪድዮ ለቀቁ" ከሚል ጽሁፍ ጋር ተጋርቶ አግኝቶታል።

በዚህም ምክንያት በፋኖ ተማረኩ መከላከያ ሰራዊት ከሚል መልክት ጋር የተጋራው ቪዲዮ የቆየና ሃሰተኛ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።
👍2🙏2
ከሰሞኑ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ ገጾቻችን ላይ በተለያየ መልኩ በኦንላይን ስለሚደረጉ ማጭበርበሮች ተከታዮቻችን ያላቸውን ተሞክሮ እንዲያካፍሉን፤ ከየትኛው ጋር በተተያያዘ አጭበርባሪዎች አጋጥመዎት ወይም ተጭበርብረው ያውቃሉ? ስንል ጠይቀን ነበር፡፡ አጠቃላይ 44 ግለሰቦች የተሳተፉ ሲሆን አስተያየታቸዉም ከታች ያለዉን ይመስላል፡


👉ከሀሰተኛ የኦንላይን ስራ ጋር በተያያዘ 21 ምላሽ ሰጪዎች ወይም (47.7%) የሚሆኑት አጭበርባሪዎች አጋጥመውኝ ወይም ተጭበርብሬ አውቃለሁ ብለዋል፡፡

👉ከዲጂታል ከረንሲ (cryptocurrency) 6 ምላሽ ሰጪዎች ወይም (13.6%) የሚሆኑት አጭበርባሪዎች አጋጥመውኝ ወይም ተጭበርብሬ አውቃለሁ ብለዋል፡፡


👉ከውጭ ሀገር ስራና ትምህርት 7 ምላሽ ሰጭዎች ወይም (15.9%) የሚሆኑት አጭበርባሪዎች አጋጥመውኝ ወይም ተጭበርብሬ አውቃለሁ ብለዋል፡፡


👉 ከሞባይል ባንኪንግ ጋር ተያይዞ 3 ምላሽ ሰጪዎች ወይም (6.8%) የሚሆኑት አጭበርባሪዎች አጋጥመውኝ ወይም ተጭበርብሬ አውቃለሁ ብለዋል፡፡


👉ምንም አይነት አጭበርባሪ አጋጥሞኝ አያውቅም 7 ምላሽ ሰጪዎች ወይም (15.9%) የሚሆኑት በማጭበርበር ምንም ችግር እንደሌለ ጠቁመዋል።


ይህ የተመልካቾች አስተያየት እንደሚያሳየዉ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተሳታፊዎች አጭበርባሪዎች አጋጠሟቸው ወይም እንደተጭበረበሩ ገልጸዋል፡፡ ይህ የሚያሳየዉ ብዙ ሰዉ በተለያየ መንገድ ለአጭበርባሪዎች የተጋለጠና ቀጥተኛ ተጠቂም እንደሆነ ነው
👍4🙏3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ሶማሊያውያን ፋኖን እየደገፉ ነዉ" በማለት ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተሰራጨ ስላለዉ ቪድዮ #HaqCheck
👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል ይሁንላችሁ 🎉
#HaqCheck
2👍1🔥1
የህዝብ ዋይፋይን (Public Wi-Fi) ስንጠቀም ልናደርጋቸዉ የሚገቡ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶች

1️⃣ VPN መጠቀም፡ በምትጠቀሙበት ስልክ ወይም ኮምፒውተር እና በኢንተርኔቱ መካከል የሚኖረው ግንኙነት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሚስጥራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣ ይህም መረጃዎ በሳይበር ወንጀለኞች እንዳይመነተፍ ያግዛል። 🔒

2️⃣ የይለፍ ቃል ያለዉን ኔትዎርክ ይጠቀሙ፡ ፓስዎርድ የማያስፈልጋቸው ዋይፋይ ኔቶርኮችን አለመጠቀም። ፓስዋርድ የሌላቸዉ አንዳንዴ በ ሳይበር ወንጀለኞች መረጃዎችን ለመመንተፍ የተዘጋጁ ሊሆኑ ይችላሉ። 🚫

3️⃣ የሁለተኛ ዙር የደህንነት ማረጋገጫ መጠቀም፡ ባጋጣሚ የይለፍ ቃልዎ ቢሰረቅ እንኳን ወደ እናንተ አካዉንት እንዳይገቡ የሁለተኛ ዙር የደህንነት ማረጋገጫ ( Two step verification) መጠቀም ይመከራል🔒

4️⃣ መሳሪያዎን (devices) ማዘመን፡- የምትጠቀሙት መሳሪያዎች እና ሶፍትዌሮች አዳዲስ የደህንነት መጠበቂያዎች እንዳሏቸው እና ወቅታዊ መሆናቸውን ያረጋግጡ። ጊዜው ያለፈበት ሶፍትዌር ለጥቃት ተጋላጭ ያደርገዎታል።

6️⃣ ጥንቃቄ የሚፈልጉ (sensitive) ተግባራትን አለማድረግ፡ እንደ የኦንላይን ባንኪንግ ወይም ሌሎች የኢንተርኔት ግብይቶችን የመሳሰሉትን ከማድረግ ይቆጠቡ። እነዚህ እንቅስቃሴዎች በሳይበር ወንጀለኞች ከተጠለፉ ጉዳታቸው ከፍ ያለ ሊሆን ስለሚችል

ከላይ የተጠቀሱትን ጥንቃቄዎች በማድረግ በተለይም የህዝብ ዋይፋይ ሲጠቀሙ የግል መረጃዎን እና ደህንነትዎን መጠበቅ ይችላሉ።
4👍1🔥1👏1
በዛሬዉ ከውሸቱ ባሻገር የምዕራፍ ሁለት ፕሮግራማችን፡

👉የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያዉያን ከሶማሊያ እንዲወጡ እየተደረገ ነው?፣

👉 በፋኖ እጅ የተማረኩ የመከላከያ ሰራዊትን ያሳያል ስለተባለው ቪድዮ፣

👉 ሶማሊያውያን ፋኖን እየደገፉ ነዉ? ፣

👉በመንግስት የድሮን ጥቃት ከ 500 ሰዎች በላይ ሞቱ? በማለት ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት ሲሰራጩ የነበሩትን እና ከሃገር ውጪ ያገኘናቸዉን መረጃዎች እንፈትሻለን::

ይከታተሉን👉https://youtu.be/UJizNvpNo70?si=sBMsqDzTtV8-JFyv
👍3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"በጎጃም በድሮን ጥቃት ከ 500 በላይ ሰዎች ሞተዋል" በማለት ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲሰራጭ የነበረዉ ቪድዮ ሃሰተኛ እና ከ9 ዓመት በፊት በአማራ ክልል ያለዉን የለቅሶ ስነ ስርአት ለማሳየት ታስቦ የተጋራ እንደነበር ሀቅቼክ ማረጋገጥ ችሏል፡፡
👍3
ሃሰተኛ የሆነ ቪዲዮን እንዴት መለየት እንችላለን?

በመልክአ ምድራዊ እይታ: በቪዲዮው ውስጥ ከዋናው ሁነት በስተጀርባ እና በአካባቢው ላይ የሚታዩትን የመሬት ገጽታዎችን ልብ ብሎ መመልከት እና ማመስከር።

በተሽከርካሪ ታርጋዎች፡- በቪዲዮው ላይ ተሽከርካሪዎች የሚታዩ ከሆነ የሰሌዳ ቁጥራቸውን እና የየት ሀገር ታርጋ እንደሆነ መለየት። 

በሰንደቅ አላማ፡ በቪዲዮው ውስጥ ሰንደቅ አላማ ወይም ብሄራዊ ምልክቶችን መፈለግ፤ ዲዛይናቸውን፣ ቀለሞቻቸውን እና የቦታ አቀማመጠቸውን በትኩርት መመልከት

በቪድዮ ውስጥ በሚሰሙ ድምጾች፡- ከዋናው ድምጽ ውጭ ያሉትን በትኩረት ማድመጥና መለየት፣ እንዲሁም የቪድዮውን የድምጽ ጥራት እና ወጥነት በትኩረት መመልከት።

በምልክቶች፡ በቪዲዮው ላይ የሚታዩትን ምልክቶች ወይም አርማዎችን መመልከት፣ የመንገድ ዳር ምልክቶችን፣ የተሰቀሉ ባነሮችን በመመልከት ከመረጃው ይዘት ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ።

በቀን ፡ በቪዲዮው ላይ የተጠቀሰ ወይም የሚታይ ቀን ካለ እሱን በትኩረት መመልከት እና ከመረጃው ጋር ማመሳከር።

👉 እንዚህን ከላይ የጠቀስናቸውን ፍንጭ ሰጭ መረጃዎችን ከለየን በኃላ የተለያዩ መሳሪያዎችን እንደ(Geo location, Invid ) እና ሌሎችንም በመጠቀም ማረጋገጥ እንችላለን።
👍6🔥1
💡 Start your week off right with a dose of positive and motivated notes! Remember, the #truth is powerful, so speak it loudly and embrace the power of #facts. 💯 They are the foundation of wisdom and progress.

#Haqcheck #medialiteracy #digitalliteracy #MondayMotivation
🔥2🥰2👍1👏1
Do you want to enhance your skills in distinguishing between fact and fiction?

Join us for a rigorous training program co-hosted by the United States Embassy in Addis Ababa, Addis Ababa University, and Inform Africa/HaqCheck. This opportunity is designed to elevate your fact-checking and verification abilities, empowering you to confidently navigate the intricate landscape of information. Ensure your participation by registering now through the provided barcode or by accessing the Google form link.

Registration link is for University staff and students only - https://bityl.co/O9l9

NB: For Addis Ababa participants only
🙏1
Do you want to enhance your skills in distinguishing between fact and fiction?

Join us for a rigorous training program co-hosted by the United States Embassy in Addis Ababa, Addis Ababa University, and Inform Africa/HaqCheck. This opportunity is designed to elevate your fact-checking and verification abilities, empowering you to confidently navigate the intricate landscape of information. Ensure your participation by registering now through the provided barcode or by accessing the Google form link.

Registration link is for journalist's and media professionals only -
https://bityl.co/O9mW

NB: For Addis Ababa participants only
👀21
ከApril’s fool ቀን ጋር ተያይዘው ከሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች ይጠንቀቁ

እንደ አውሮፓዉያን አቆጣጠር የሚያዚያ ወር መግቢያ ማለትም April 1, የ ኤፕሪል ዘፉል (April’s fool) ቀን ተደርጎ በብዙዎች ዘንድ ይከበራል፡፡ ይህን ተከትሎ የሚስተዋሉ ቀልዶች እና ፕራንኮች የሚያዝናኑ ቢሆኑም፣ ነገር ግን ሃሰተኛ ሆነው ሳለ እንደ እዉነተኛ ተደርገው በኦንላየን ላይ ከሚሰራጩ መረጃዎች መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

ምንግዜም ቢሆን መረጃዎች ሲያጋጥሙን

✍️ መረጃውን ከማመን በፊት ሌሎች አስተማማኝ የመረጃ ምንጮች ላይ ማረጋገጥ
✍️ የመረጃ ምንጩን መፈተሽ- እምነት የሚጣልበት ወይስ ለማሳሳት የሚሞክር?
✍️ በጣም እውነት የሚመስሉ እንኳን ቢሆኑም እውነት ላይሆኑ እንደሚችሉ ከግምት ዉስጥ ማስገባት ያስፈልጋል

ሁል ጊዜም ቢሆን መረጃን ከማጋራታችን በፊት እናጣራ!

ለተጨማሪ መረጃ 👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
4👍1🔥1
🌍 Today is International Fact-Checking Day!

🔍 Let's celebrate the power of truth and accuracy! Join us in the fight against misinformation and share reliable information.

🔎 At HaqCheck, we are committed to promoting fact-checking and debunking false claims. Together, we can build a more informed world.

🙌 Spread the word and stand up for the truth!

For more, visit our website and social media:

Website: www.haqcheck.org
Twitter: www.twitter.com/HaqCheck
TikTok: www.tiktok.com/@haqcheck
LinkedIn: www.linkedin.com/haqcheck
Facebook: https://www.facebook.com/HaqCheck

#InternationalFactCheckingDay #HaqCheck
🎉4🔥1
የሚስብ አርእስት ያላቸው መረጃዎች ሲያጋጥሙን ምን እናድርግ?
-------------------------
፩: ሙሉ መረጃውን ማንብብ/መመልከት

መረጃውን እውነት አድርጎ ከመቀበል በፊት ከርዕሱ በተጨማሪ በጹሑፍ ወይም በቪድዮው ውስጥ ያለውን መረጃ ማንብብ እና መመልከት ያስፈልጋል።

፪: የመረጃውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ

አጠቃላይ የመረጃውን ይዘት ከተረዳን በኋላ እውነት መሆን አለመሆኑን የተለያዩ የመረጃ ማጣሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም ፣ መፈተሽና መበየን።

፫: አጠራጣሪ ከሆነ ከማጋራት መቆጠብ

ከላይ እንደተገለጸው መረጃውን በአትኩሮት አጣርተን አጠራጣሪ ወይም ሃሳተኛ ሆኖ ካገኘነው መረጃውን አለማጋራት እና ምንም አይነት ግብረ መልስ አለመስጠት ይኖርብል።

ብዙ ጊዜ ርእሱን በጣም ሳቢ እና ማራኪ በማድረግ መረጃን የሚያሰራጩ አካላት ብዙ ተመልካች ለማግኝት እና ያንንም ዝና እና ገንዘብ ለማግኘት እንደሚጠቀሙበት መገንዘብ ያስፈልጋል።

ምንጊዜም ቢሆን መረጃን ከማጋራታችን በፊት እናጣራ!

ℹ️ ለተጨማሪ መረጃ: 👇


Website: www.haqcheck.org
Twitter: www.twitter.com/HaqCheck
TikTok: www.tiktok.com/@haqcheck
LinkedIn: www.linkedin.com/haqcheck
Facebook: https://www.facebook.com/HaqCheck

#HaqCheck #medialitracy #disinformation
👍4