በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር ፕሮግራማችን:-
❓የተባበሩት መንግስታት የባህር ህግ ስምምነት ኢትዮጵያ የባህር በር የባለቤትነት ይዞታን እንድትጠይቅ ዋስትና ይሰጣል?፣
❓ የኢትዮጵያ ጠቅላል የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ባለፉት አምሥት ዓመታት በእጥፍ አድጓል?፣
❓ኢትዮጵያ አሜሪካንን ጨምሮ ዓለምን በስለላ እያስጨነቀች ነው? 🤔 የሚሉትን ሃሰተኛና አሳሳች መረጃዎችን እና
✍ ኢሰመኮ ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎ የተፈጠረውን ውዝግብ እንዲሁም ከውጭ
❓ቱርክ ፍልስጤማውያንን ለመረዳት የጦር መርከቦቿን ወደ ጋዛ እያጓጓዘች ነው?
የሚሉትን በባለፈዉ ሳምንት በመደበኛና በማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት ሲዘዋወሩ የነበሩትን መረጃዎች እንፈትሻቸዋለን።
ይከታተሉን👇👇👇
https://youtu.be/NFIl8ukJh5E?si=EfUxfzLbPsu91Mok

🤔4
Ethiopia’s GDP did not double in five years in terms of real GDP. While nominal GDP showed substantial growth, this was largely due to inflation. When adjusted for inflation, the real GDP growth did not meet the doubling claim.
Read the full article here:
👉👉https://bit.ly/3QojhKT
Read the full article here:
👉👉https://bit.ly/3QojhKT
👍1👏1
📢 በየሳምንቱ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች በኢሜል እንዲደርስዎ ይመዝገቡ።
✔️ሳምንታዊ የሃሰተኛ መረጃ ማጠቃለያ (weekly disinformation summary)
✔️ ትንታኔዎች (analysis) እና የሚድያ አጠቃቀም ክህሎት ለማሳዳግ የሚጠቅሙ ሃሳቦችን (media literacy tips) እና ሌሎችንም መረጃዎች በየሳምንቱ በኢሜል አድራሻዎ እንዲደርስዎ 👉https://bit.ly/3rl8vwn ላይ ይመዝገቡ ወይም በድህረ ገጽ 👉www.HaqCheck.org ላይ በመግባት መመዝገብ (ሰብስክራይብ) ማድረግ ይችላሉ።

👍4🔥1
November week one disinformation summary
Last week HaqCheck debunked false claims that U.S. Secretary of State Antony Blinken called for ENDF withdrawal from the Amhara region, Eritrea deployed troops to the Ethiopian border, and Chief of Staff Birhanu Jula said ENDF is exhausted by Fano militants. All claims were found to be FALSE. Read the details here: https://bit.ly/3QNZDJr #Ethiopia #haqcheck
👍3❤1
በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር ፕሮግራማችን
❓አሜሪካ መከላከያ ሰራዊት ከአማራ ክልል እንዲወጣ ጠይቃለች?
❓ኤርትራ ሰራዊቷን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አስጠግታለች ስለሚለው መረጃ?
❓ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መከላከያ በፋኖ እንደተዳከመባቸው ተናግረዋል?
የሚሉትን ሃሰተኛ መረጃዎች እና
✍ ጠንካራ የይለፍ ቃል እንዲኖረን ምን ማድረግ ይኖርብናል? እንዲሁም ሌሎችንም መረጃዎች ይዘናል።
ይከታተሉን. 👉 https://youtu.be/TX5X4Qlq8iU

👍3🙏1
የአንድ ሊንክ ወይም የድር አድራሻ (URL Address) ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ለማወቅ
✍ የድር አድራሻው (URL Address) በ"https://" መጀመር ይኖርበታል ፣ በ "http://" ብቻ ከሆነ ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም።
✍ ከድር አድራሻው በፊት የቁልፍ ምልክት ይኖረዋል (have a lock icon in the address bar)
✍ የድር አድራሻ አወቃቀሩን (URL structure) በጥንቃቄ ይመልከቱ፡ ደህንነታቸው ያልተጠበቁ የድር አድራሻዎች የፊደል ስህተት እንዲሁም ተጨማሪ ቁጥሮችን ወይም ፊደሎችን በሚታወቁ አድራሻዎች ላይ በመጨመር ወይም በመቀነስ ሊጠቀሙ ይችላሉ። ለምሳሌ ትክክለኛውን "paypal.com" አመሳስለው ለማሳሳት "paypa1.com" L ፊደልን በ 1 ቁጥር በመቀየር ወይም "paypal-login.xyz" በማድረግ አድራሻውን በጥንቃቄ ያልመረመረን ሰው የ paypal.com መስሎት ሊሸወድ ይችላል።
✍ ሊንኩ ባጭሩ የተቀመጠ (shortened URLs) ከሆነ ትክክለኛውን አድራሻ ላያሳይ ይችላል። ሊንኩ የሚያጠራጥር ከሆነ "Unshorten.it" ወይም "LongURL" ያሉትን ኦንላይን ዌብሳይቶች በመጠቀም ዋናውን የድር አድራሻ በማግኘት መመልከት ይቻላል፡፡
✍ የደህንነት መጠበቂያ ሶፍትዌሮችን መጠቀም(Use security software)፡ እንደ ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ማልዌር (antivirus and anti-malware software) ያሉትን የደህንነት ሶፍትዌሮችን መጫን ደህንነቱ ያልተጥበቀ ሊንክ ወይም ዌብሳይት ሲገጥመን እነዚህ ሶፍትዌሮች ማስጠንቀቂያ ይሰጡናል።

👍5❤1🔥1
በኦንላየን ያገኙትን መረጃ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ብዙ መጻህፍት ማንበብና ማገላበጥ አይጠበቅብዎትም። የሚያስፈልገው ነገር ምክንያታዊ የሆኑ ጥቂት ጥያቄዎችን መጠየቅ ብቻ ነው
በመስመር(online) ላይ የምናያቸዉን መረጃዎች ከማመናችን በፊት፦
👉የመረጃው ምንጭ ማነው?
👉መረጃውን ያጋራው ግለሰብ ወይም ተቋም አድልዊ አመለካከት አለው?
👉መረጃዉ ማስረጃ አለው፣ ማስረጃውስ ተጠቅሷል?
👉መረጃዉ በሌሎች ሚድያዎች ተጋርቷል? የሚሉትን እና ሌሎች መሰል ጥያቄዎችን በመጠየቅ የመረጃዉን እዉነትነት ማጣራት ይቻላል፡፡

👌4❤1👍1🔥1
#ሀሰተኛ_ምስል
📢 ይህ ከላይ የምትመለከቱት ምስል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ይፋዊ ድህረገጽን ጨምሮ ሌሎች ዋና ዋና የሚድያ አውታሮች ሰሞኑን በመከላከያ አማካኝነት በቄለም ወለጋ ዞን በተደረገ ኦፕሬሽን ከኦነግ ሸኔ የተማረኩ መሳሪያዎችን ያሳያል በማለት ከዜናዎቻቸው ጋር አጋርተውታል፡፡
✍ በእነዚህ የዜና ድረ-ገፆች ላይ ብቻ ሳይሆን የመከላከያ ሰራዊት ይፋዊ የፌስቡክ ገፅም ይህን ምስል ከሌሎች ምስሎች ጋር በቄለም ወለጋ ዞን በተደረገ ኦፕሬሽን በኦነግ ሸኔ ላይ የተደረገ ድንገታዊ ጥቃትን በሚያሳይ ፅሁፍ ስር አጋርቶታል።
✍ ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ይህን ምስል ከዚህ በፊት ‘በሰሜን ሸዋ ዞን የህብረተሰቡን ሰላም ለማናጋት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 25 የጥፋት ቡድን አባላት ከነትጥቃቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ’ በሚል መግለጫ ፋናን ዋቢ በማደረግ አዲስ ዜና በተባለ ድህረገፅ ላይ በሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ተጋርቶ አግኝቶታል፡፡
✍ አሁን ደግሞ ይህ ምስል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በኦሮምያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የ‘ኦነግ ሸኔ’ ታጣቂዎች ላይ ድንገታዊ እርምጃ እንደወሰዱ የሚገልጽ ዜና ለመደገፍ እንደገና ጥቅም ላይ ውሏል።
✍ ስለዚህ ይህ በኢቢሲ ድህረገጽ እና በመከላከያ ሰራዊት ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ ከቀረበው መራጃ ጋር የተያያዘው ምስል መከላከያ በቄለም ወለጋ የማረከው መሳርያን እንደማያሳይ ሀቅቼክ አረጋግጧል።

🔥4👍1🤔1
📢 መከላከያ ሰራዊት በቄለም ወለጋ በኦነግ ሸኔ ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሷል በማለት ኢቢሲ ያጋራው ሀሰተኛ ምስል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሳኡዲ-አፍሪካ ስብሰባ ላይ አይሳተፉም እየተባለ ሲወጡ ስለነበሩ መረጃዎች ፤ ዋዜማ ሬድዮ ያወጣው የተሳሳተ ዘገባ ፤ የፌደራሉ መንግስት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ላይ የአየር ጥቃት አድርሷል? የሚሉትን መረጃዎችና እና ሌሎችም በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር ፕሮግራም ላይ ተዳሰዋል።
ይከትተሉን https://youtu.be/YeiD8PTQHwc
ይከትተሉን https://youtu.be/YeiD8PTQHwc
👍1🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኦሮሞ ነፃነት ጦር ("ሸኔ") አመራሮች ለድርድር ታንዛንያ መሆናቸውን ተከትሎ በAI ተሰርተው እየወጡ ያሉ ምስሎች ጉዳይ
👍4🙏1
የግል መረጃዎ ለመረጃ መንታፊዎች (hackers)? የተጋለጠ መሆን አለመሆኑን እንዴት ማወቅ ይቻላል?
👨💻 መረጃ መንታፊዎች የግል መረጃዎችን በቀጥታ ከግለሰቡ ከመውሰድ በተጨማሪ የትላልቅ ተቋማትን የመረጃ ቋት በማጥቃት በዛ የመረጃ ቋት ውስጥ የሚገኙትን የግለሰብ መረጃዎች የሚመነትፉበት ሁኔታ አለ፡፡
መረጃችን ለመንታፊውች የተጋለጠ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ :- ✍ በመጀመሪያ -
www.haveibeenpwned.com የሚል ድህረ ገፅን ይክፈቱ።
✍ በመቀጠል - የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡ። በመጨረሻም - የድረገፁ የምርመራ ውጤት ሁለት አይነት መልሶችን ሊያሳየን ይችላል
👉 የግል መረጃችን ለመንታፊዎች (hackers) የተጋለጠ ከሆነ “oh no - pwned” የሚል መልስን የሚያሳየን ሲሆን
👉የግል መረጃችን ለመንታፊዎች (hackers) ተጋልጦ የማያውቅ ከሆነ “Good news - no pwnage found” የሚል መልስን ያሳየናል።
✍ የግል መረጃችን ለመንታፊዎች የተጋለጠ ከሆነ በየትኞቹ ተቋማት በኩል መረጃው እንደሾለከ ፣ መቼና ምን አይነት መረጃዎች ተጋላጭ እንደሆኑ የሚያሳይ ማብራሪያ አለው፡፡
ስለዚህ የግል መረጃችን የተጋላጭነት ምልክቱን ካሳየ :-
👉የይለፍ ቃል መቀየር(change your password & make it strong)
👉ለተለያዩ አካውንቶች ተመሳሳይ የይለፍ ቃል የሚጠቀሙ ከሆነ መቀየር እና
👉የግል አካውንታችንን በሁለተኛ ዙር የደህንነት ማረጋገጫ (Two step verification) በመጠቀም መረጃዎቻችንን መጠበቅ ይኖርብናል፡፡

❤4🙏2🔥1👏1
📊 Is Ethiopia's economy truly bigger than its neighbors combined?
✅Our analysis breaks down Prime Minister Abiy Ahmed's statements on GDP growth and reveals the economic reality. Check out the detailed article for an in-depth look at the numbers and the facts. 👉 https://bit.ly/3SYyXXQ
#EthiopiaEconomy #FactCheck #GDPAnalysis #HaqCheck

🔥3
❓ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአሜሪካን ሀገር ጥገኝነት ጠይቀዋል?
❓ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት ኢኮኖሚ ተደምሮ ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያንሳል ?
❓በሃሰተኛ የስራ ማስታወቂያ ሰበብ ከሰሞኑ እየተስተዋሉ ያሉ ማጭበርበሮች እና ሌሎች ሃሰተኛ መረጃዎችን በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር ፕሮግራማችን እንዳስሳልን።
ይከታተሉን 👉 https://youtu.be/LDpoRJ3HthI?si=2Ioddqm05ti2WEW7

❤2👍2🙏1
#የሀሰተኛ_መረጃ_ጥቆማ (#Alert)
⚠️ ከሰሞኑ የባንኮች ስምና ምልክት በመጠቀም ባንኮቹ በትርፍ ጊዜ በኦንላይን የሚሰሩ ሰራተኞችን እየፈለጉ ነው በሚል የሚከፍሉትን ገንዘብ መጠን ጨምረው የሚጠቅሱ የማህበራዊ ሚድያ መልእክቶች ሲጋሩ አስተውለናል። እነዚህ ማስታወቂያዎች የተጋነነ ክፍያና በቀን ውስጥ ጥቂት ሰዓታት ብቻ በመስራት እንዲሁም ሰዎች ባሉበት ሆነው መስራት የሚችሉት ስራ እንደሆነ በመግለፅ በስፋት ተጋርተዋል። የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እና የአቢሲንያ ባንክ አርማና ስም በመጠቀም ፌስቡክ ላይ የተጋሩት መልእክቶች የማስታወቅያ ክፍያ በመክፈል ብዙ ሰዎች ጋር እንዲዳረሱ ተደርገው አይተናል።
✍ ሀቅቼክ ባደረገው ማጣራት እነዚህ አካውንቶች ባንኮቹን የማይወክሉና ሊንኮቹም ሲከፈቱ ወደ ግል ቴሌግራም አካውንት የሚመሩ ሲሆኑ እነዚህም የግል አካውንቶች ስራ ለማግኘት በመጀመሪያ ቅድመ ክፍያ የሚጠይቁ ናቸው። ባንኮቹ ይፋዊ በሆኑ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር) እና ሊንክዲን አካውንቶችን ብቻ ለማህበራዊ ሚድያ ተደራሸነት እንዲሁም ክፍት የስራ መደብን ለማስተዋወቅ እንደሚጠቀሙ ለማረጋገጥ ተችሏል። የባንኮቹ የማህበራዊ ሚድያ አካውንቶች ማስፈንጠርያዎች በድህረገጾቻቸው ይገኛሉ።
✍ ባንኮቹ ለሀቅቼክ እንዳሳወቁት በባንኮቹ ስም የሚጋሩ ሀሰተኛ መረጃዎች እንደሚገኙና የኦንላይን ስራ በሚል በፌስቡክ የሚሰራጨውም መረጃ ሀሰትና ከባንኮቹ እውቅና ውጭ መሆኑን አረጋግጠዋል። የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ይፋዊ የሆኑ ገጾች ላይ የሚጋሩ መረጃዎችን ብቻ በመከታተል ይህንን ከሚመስሉ የማጭበርበርያ መልዕክቶችና ጥሪዎች ራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው።

👍2🔥1🙏1
✍ While the claim of damage to the Lalibela rock-hewn churches remains unverified, fighting and employment of explosive weapons in the vicinities of the churches could threaten the structures of the centuries-old churches. Read our explainer: bit.ly/47yCsZS
👍4❤1
በእርስዎ አስተያየት በኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ንግግርን ፣ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት እና በኢትዮጵያን እሴትና ባህሎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ከሚኖረው ሚና አንጻር በየትኛው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ልዩ ደንብ ወይም ቁጥጥር ያስፈልጋል ብለህ/ሽ ታምናለህ/ሽ?
Anonymous Poll
53%
ቲክቶክ
7%
ቴሌግራም
31%
ፌስቡክ
10%
ዩቲዩብ