HaqCheck
429 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
ከመረጃ መንታፊዎች እራሳችንን እንዴት እንጠብቅ?

👩‍💻 መረጃ መንታፊዎች መረጃን ለመመንተፍ የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። ከነዚህም ውስጥ ሃሰተኛ የኦንላየን ስራና የኦንላየን ንግድ ማስታወቂያዎችን በማውጣት በቀጥታ ሰዎች መርጃቸውን እንዲልኩላቸው በማድረግ እና ማስፋንጠርያ ሊንኮችን በማህበራዊ ሚድያና በመልእክት መላላኪያ አማራጮች በመላክ መረጃዎችን ይወስዳሉ፡፡

✍️ አንድ ሊንክ ሲላክሎት ወይም ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲመለከቱ ሊንኩ መረጃን ለመመንተፍ የተሰራ ሊሆን ስለሚችል በጥንቃቄ መመልከት እና በጥድፍያ አለመንካት ያስፈልጋል። ያንን ሊንክ ከሚያውቁት ሰው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሊላክሎት ስለሚችል ማመን የለብዎትም። ለኦንላየን ስራና ንግድም ቢሆን አስቀድመው የግል መረጃ የሚጠየቁ ከሆነ መጠርጠር ያስፈልጋል፡፡

✍️ ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሰዎችን ቀልብ ለመሳብ የተለያየ ጹሁፍ የያዙ መንታፊ ሊንኮች ይታያሉ። በፅሁፍ ከላይ የሚነበበው እና ማስፈንጠርያ ሊንኩ የተለያዩ ናቸው። ከላይ ያለው ፅሁፍ ስለ ብድር፣ ስለሽልማት ፣ ስለትምህርት እድል እና ስለ ስራ ወዘተ ሊሆን ይችላል። ይህ አሰራር ሰዎች ከላይ በሚያነቡት ፅሁፍ ተሸውደው ሊንኩን በጥድፍያ እንዲነኩ ለማስጎምጀት፣ ለማጓጓት ታልሞ የተዘጋጀ ነው።

✍️ ስለዚህ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሊንክ ሲያዩ ከመንካትዎ በፊት በፅሁፉ የሚነበበው ሀሳብ እና ሊንኩ አንድ አይነት መሆኑን ማመሳከር እና የሊንኩን ደህንነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

✍️ የኢሜይል፣ የባንክ እና የማህበራዊ ሚድያ አካውንት የግል መረጃዎችን እንዲሰጡ ወይም እንዲሞሉ ከተጥየቁ እውነት መሆኑን ሳያረጋግጡ መስጠት አያስፈልግም፡፡ በተጨማሪም የግል አካውንታችንን በሁለተኛ ዙር የደህንነት ማረጋገጫ (Two step verification) በመጠቀም መረጃዎቻችንን መጠበቅ ይኖርብናል፡፡
🔥2🙏1
📢 ሀቅቼክ ከአሜሪካ ኢምባሲ ጋር በመተባበር መሰረታዊ የሀቅ ማጣራትና ማረጋገጥ (Fundamentals of Fact-Checking and verification) ስልጠና ይስጣል።

መቼ? ረቡዕ ጥቅምት 7/2015 ዓ.ም
የት ? በ Satchmo American Center
ሰዓት? ከቀኑ 8:00 -10:00 ሰዓት

በፕሮግራሙ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ባሉት ሊንኮች ይመዝገቡ👇

Register for the event here: https://bit.ly/counteringmisdisinfo . Access to the Satchmo Center is by membership only. Please sign up for membership: https://bit.ly/SatchmoCenterMembership
4🔥2👍1👏1
እንዲጣራ የሚፈልጉትን መረጃ ይላኩልን

👩‍💻 በተለያዩ የሚድያ አማራጮች ላይ የተመለከታችሁት ወይም ያገኛችሁት መረጃ እውነት መሆኑ ካጠራጠራችሁ፣ ጥያቄ ከፈጠረባችሁ፣ መረጃውን ያገኙበትን ምንጭ አያይዘው ይላኩልን፤ የመረጃውን እውነትነት አጣርተን እና አረጋግጠን መልሰን ለእናንተው እናቀርባለን።

✍️ መረጃ ለመላክ:-
   በቴሌግራም: @haqcheckbot ላይ ይላኩልን።
4🔥1
የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች (check mark) አሰጣጥና የሚያመጡት ተፅዕኖ

✍️ የማህበራዊ ሚድያ ባለቤቶች የተጠቃሚዎችን ህጋዊነት እና ትክክለኛነት ለማሳየት በሚል ማረጋገጫ ወይም መለያ ምልክት ይሰጣሉ።

✍️ የማህበራዊ ሚድያ መለያ (check mark) ለማግኘት የተለያዩ መስፈርቶች የሚጠየቁ የነበረ ቢሆንም አሁን አሁን ግን አንዳንዶቹ የማህበራዊ ሚድያ ባለቤቶች ያስቀመጡትን ወርሃዊ ክፍያ መክፈል ለቻሉ አመልካቾች ሁሉ ማረጋገጫውን የሚሰጡበት ሁኔታ እንዳለ መርጃዎች ያሳያሉ፡፡

✍️ የሰማያዊው መደብ ምልክት በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ከማግኘት እና ትክክለኛ ከመሆን ጋር ተያይዞ የሚፈጥረው አዎንታዊ ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው። አንድ አካውንት ሰማያዊ ምልክት ሲኖረው ሰዎች በዛ አካውንት የሚተላለፈው ሃሳብ ወይም መረጃ ትክክለኛ ነው ብለው የማሰብ እና የማመን ሁኔታ አለ።

✍️ ይሁን እንጂ የባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም ሰማያዊው ምልክት ያለው አካውንት የሚያጋራው መረጃ ሃሰተኛና የተሳሳተ ሊሆን ስለሚችል በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል

ሀቅቼክ የማህበራዊ ሚድያ ባለቤቶች ማረጋገጫ የሚሰጡበትን ሁኔታ እና ተፅእኖውን በተመለከተ ያዘጋጀውን ጹሑፍ ያንብቡ 👉 bit.ly/3QlI7Mo
👍2
#Scam_alert

ከሰሞኑ በተለይም ለፌስቡክ ገፆች በውስጥ መስመር እየተላከ ያለ አንድ መልዕክት አለ። ይህ ለእነዚህ የፌስቡክ ገፆች የሚላከው መልዕክት “ገፆቹ የፌስቡክን ህግ እንደጣሱ እንዲሁም ተገቢ ያልሆኑ መረጃዎችን እንደሚያሰራጩ እና የኮፒ መብትን (Copyright) ህግን እየጣሱ እንደሆነ ከሚገልፅ መረጃ ጋር መልዕክቱ ይደርሳቸዋል።

ነገር ግን ይህ መልዕክት ከዚህ በመቀጠል ገፆቹ ይህንን ድርጊት እኛ አልፈፅምንም እና ይግባኝ ማለት እንፈልጋለን የሚሉ ከሆነ በዚህ ሊንክ በመግባት መጠየቅ እንደሚችሉ ገልፆ ይህ ካልሆነ ግን የፌስቡክ ገፁ በ24 ሰዓት ውስጥ ይዘጋል የሚል ይዘት ያለው መረጃን አብሮ ያስነብባል”።

ይህ መልዕክት ከፌስቡክ ወይም Meta የተላከ ለማስመሰል በአሁኑ ሰዓት meta የሚጠቀምበትን አርማ እና ምስል ተጠቅሟል።

ሀቅቼክ ይህንን ከመልዕክቶቹ ጋር የሚላከውን ማስፈንጠርያ (ሊንክ) ያጣራ ሲሆን ሊንኩ አደገኛ እና እነዚህን የፌስቡክ ገፆች እሰከማስጠለፍ ድረስ የሚደርስ እንደሆነ አረጋግጧል።
👍51🙏1
📢 በአፋር የሚገኙ ታጣቂዎች ፋኖን ደግፈው በአማራ ክልል ያለውን የትጥቅ ትግል ተቀላቅለዋል፣ ኤርትራ ጦሯን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አስጠግታለች እና ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ አትገቡም ተብሏል በማለት ከሰሞኑ በተለያዩ ሚድያዎች ሲዘዋወሩ የነበሩ መረጃዎችን፣ እንዲሁም ከውጭ ከእስራኤል እና ፍልስጤም ጦርነት ጋር ተያይዞ የተሰራጩ ሃሰተኛ መረጃዎችን በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር ፕሮግራማችን ተመልክተናቸዋል።

ይከታተሉን👇👇👇

https://youtu.be/xaWmwO5c5ok?si=edRxW-4VjwLJnrCa
👍2🔥1
#የሐሰተኛ_መረጃ_ጥቆማ

✍️ ከሰሞኑን ይህ ከላይ የምትመለከቱ ምስል በተለያዩ የፌስቡክ ገፆች ላይ ኦነግ ሸኔ  ከመከላከያ ጋር ከአዲስ አበባ ወደ ደጀን በሚወስደው አውራ ጎዳና ፣ ልዩ ቦታው ሚልኪ ተብሎ በሚጠራው ከተማ ላይ ጦርነት እያካሔደ እንደሆነ ከሚገልጽ ጹሑፍ ጋር በስፋት ሲዘዋወር ነበር።

✍️ በተጨማሪም ከምስሉ ጋር በተያያዘው ፅሁፍ ላይ "መከላከያ ፋኖን እያስታጠቀ ነው" በሚል ኦነግ ሸኔ መከላከያን እያጠቃ እንደሆነ ገልጿል።

✍️ ነገር ግን ሀቅቼክ እንዳጣራው መረጃውን ለመደገፍ የተጠቀሙበት ምስል የቆየ እና ከዚህ በፊት ሃምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም በአንድ የፌስቡክ ገፅ ላይ በሃረርጌ ዙሪያ የነበረን ሁኔታ ከሚገልጽ ጽሑፍ ጋር ተጋርቶ አግኝቶታል።
🛎ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ በዓመት ብዙ ቢሊዮን ዶላር ታወጣለች ፣ የቀድሞ የሕውሃትና የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ መከላከያ እንዲገቡ እየተደረገ ነው፣ መከላከያ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው የሚሉትን እና ከዉጭ በጋዛ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ የተፈጸመ የአየር ጥቃትን በተመለከተ ሲዘዋወሩ የነበሩ ሰሞነኛ መረጃዎችን ፣ በመጨረሻም ከሰሞኑ በፌስቡክ ገጽ በውስጥ መስመር የሚላኩ የማጭበርበሪያ ሊንኮችን ምንነት በዛሬው ከውሸት ባሻገር ፕሮግራማችን እንፈትሻለን።

ይከታተሉን👇👇👇

https://youtu.be/kuc46pandDU?si=Md3ZeKpHhlotB3nk
👍2🔥1
How can we spot AI-generated images?

Even though AI tools are developing quickly, mistakes are still made by this non-human entities.

Here are tips to help you detect AI generated images.

1.Zoom in and take a close look.

Many AI-generated visuals initially seem to be real. hence it's best to examine the images carefully.

2.Find the images source

It is preferable to identify the image source to figure out whether the image is real or artificially created.

3.Be aware of body proportions.

Do the peoples in the images do have the correct body proportion?

4.Keep an eye out for common AI mistakes.

Currently, artificial intelligence methods produce errors in the shape of fingers, teeth, faces, and ears.

5.Does the image looks artificial

Faces of AI generated images looks too pure, closes and textiles looks too harmonious.

6.Examine the background

A closer inspection can help us determine whether or not the background was altered.
🙏3🔥1
📢 በባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ኤምባሲ ግቢ በሚገኘዉ Satchmo American Center መሰረታዊ የሀቅ ማጣራትና ማረጋገጥ (Fundamentals of Fact-Checking and verification) ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናውን የአሜሪካ ኢምባሲ ከሀቅቼክ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን ተሳታፊዎቹም ሃሰተኛ መረጃን ለመለየትና ለመከላከል የሚያስችል እውቀትና ክህሎትን የቀሰሙበት ነበር።

✍🏿 በስልጠናው ላይ የመረጃ መዛባት ምንነት ፣ የተለያዩ የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች እና በኢትዮጵያ ስላለው የሃሰተኛ መረጃ አዝማሚያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። እንዲሁም ሃሰተኛ መረጃዎችንና የውሸት ዜናዎችን መለያ ዘዴዎችን እና የምስል/የቪዲዮ ማረጋገጫ መሳሪያዎችን በተመለከት ለሰልጣኞች መሰረታዊ ግንዛቤ ተሰጥቷል። በመጨረሻም የሀሰተኛ መረጃዎችን እና ሀሰተኛ ዜናዎችን መለየት እና ስርጭታቸውን መከላከል እንዲሁም የሚድያ አጠቃቀም ክህሎትን ማዳበር እንደሚያስፈልግ ተተቁሟል፡፡
👏4👍1
ኢንተርኔት ስንጠቀም ደህንነታችን ለመጠበቅ ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች 

✍️ የምንጠቀማቸው የይለፍ ቃሎች (passwords) ጠንካራ(Strong)፣ ረጅም(long) እና ልዩ(unique) መሆን አለባቸው። ተመሳሳይ የይለፍ ቃል(passwords) ለተለያዩ አካውንቶች መጠቀም አይመከርም

✍️ የይለፍ ቃሎችን (passwords) በጭራሽ ለሌሎች ሳያጋሩ በሚስጥር መያዝ ያስፈልጋል።

✍️ በጋራ ከሌሎች ጋር  ከምንጠቀምባቸው ኮምፒውተሮችና  እና አፕሊኬሽኖች ውስጥ ስራችንን ስንጨርስ መውጣት (log out) ማለት ይኖርብናል፡፡

✍️ በስልኮች፣ ታብሌቶች እና ኮምፒውተሮች ላይ ያሉ ሁሉንም ሶፍትዌሮች እና አፕሊኬሽኖች ከቅርብ ጊዜ የደህንነት መጠገኛዎች ጋር ማዘመን ያስፈልጋል (up-to-date with the latest security patches)።

✍️ ፐብሊክ Wifi ሲጠቀሙ ጥንቃቄ ማድረግ ከተቻለ VPN መጠቀም ይመከራል።

✍️ የግል አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር ወይም የልደት ቀን የመሳሰሉትን መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በኢሜል ሁሉም ሰው ሊያየዉ በሚችል መልኩ አለማጋራት። 

✍️ በኢንተርኔት ላይ ፎቶዎችን እና አስተያየቶችን ከመለጠፍ በፊት ጊዜ ወስዶ ማሰብ ያስፈልጋል፣ ምክንያቱም የሚጋራው ማንኛውም ነገር ላልተወሰነ ጊዜ ለሁሉም ሰው ይፋ ሊሆን ይችላል ይህ ደግሞ ቆይቶ ሌላ የደህንነት ስጋት ሊሆን ይችላል፡፡ 

✍️ ኦንላየን ላይ ወይም ኢንተርኔት ስንጠቀም ሌሎችን ሳንነካ፣ ሳንሳደብ፣ ሌሎችን በማክበር መሆን አለበት፣ ያ ካልሆነ መልሶ ለራሳችን የኦንላየን ደህንነት አልፎም ለሌሎች ችግሮች ሊያጋልጠን ይችላል።
🔥3🙏1
በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር ፕሮግራማችን:-

የተባበሩት መንግስታት የባህር ህግ ስምምነት ኢትዮጵያ የባህር በር የባለቤትነት ይዞታን እንድትጠይቅ ዋስትና ይሰጣል?፣

የኢትዮጵያ ጠቅላል የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ባለፉት አምሥት ዓመታት በእጥፍ አድጓል?፣

ኢትዮጵያ አሜሪካንን ጨምሮ ዓለምን በስለላ እያስጨነቀች ነው? 🤔 የሚሉትን ሃሰተኛና አሳሳች መረጃዎችን እና

ኢሰመኮ ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎ የተፈጠረውን ውዝግብ እንዲሁም ከውጭ

ቱርክ ፍልስጤማውያንን ለመረዳት የጦር መርከቦቿን ወደ ጋዛ እያጓጓዘች ነው?

የሚሉትን በባለፈዉ ሳምንት በመደበኛና በማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት ሲዘዋወሩ የነበሩትን መረጃዎች እንፈትሻቸዋለን።

ይከታተሉን👇👇👇
https://youtu.be/NFIl8ukJh5E?si=EfUxfzLbPsu91Mok
🤔4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ አሜሪካንን ጨምሮ ዓለምን በስለላ እያስጨነቀች ነው? 🤔
2👍2🔥1
Ethiopia’s GDP did not double in five years in terms of real GDP. While nominal GDP showed substantial growth, this was largely due to inflation. When adjusted for inflation, the real GDP growth did not meet the doubling claim.

Read the full article here:

👉👉https://bit.ly/3QojhKT
👍1👏1
📢 በየሳምንቱ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች በኢሜል እንዲደርስዎ ይመዝገቡ።

✔️ሳምንታዊ የሃሰተኛ መረጃ ማጠቃለያ (weekly disinformation summary)
✔️ ትንታኔዎች (analysis) እና የሚድያ አጠቃቀም ክህሎት ለማሳዳግ የሚጠቅሙ ሃሳቦችን (media literacy tips) እና ሌሎችንም መረጃዎች በየሳምንቱ በኢሜል አድራሻዎ እንዲደርስዎ 👉https://bit.ly/3rl8vwn ላይ ይመዝገቡ ወይም በድህረ ገጽ 👉www.HaqCheck.org ላይ በመግባት መመዝገብ (ሰብስክራይብ) ማድረግ ይችላሉ።
👍4🔥1
November week one disinformation summary


Last week HaqCheck debunked false claims that U.S. Secretary of State Antony Blinken called for ENDF withdrawal from the Amhara region, Eritrea deployed troops to the Ethiopian border, and Chief of Staff Birhanu Jula said ENDF is exhausted by Fano militants. All claims were found to be FALSE. Read the details here: https://bit.ly/3QNZDJr #Ethiopia #haqcheck
👍31
በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር ፕሮግራማችን

አሜሪካ መከላከያ ሰራዊት ከአማራ ክልል እንዲወጣ ጠይቃለች?

ኤርትራ ሰራዊቷን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አስጠግታለች ስለሚለው መረጃ?

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መከላከያ በፋኖ እንደተዳከመባቸው ተናግረዋል?

የሚሉትን ሃሰተኛ መረጃዎች እና

ጠንካራ የይለፍ ቃል እንዲኖረን ምን ማድረግ ይኖርብናል? እንዲሁም ሌሎችንም መረጃዎች ይዘናል።

ይከታተሉን. 👉 https://youtu.be/TX5X4Qlq8iU
👍3🙏1
የአንድ ሊንክ ወይም  የድር አድራሻ (URL Address) ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ለማወቅ

የድር አድራሻው (URL Address) በ"https://" መጀመር ይኖርበታል ፣ በ  "http://" ብቻ ከሆነ ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም።

ከድር አድራሻው በፊት የቁልፍ ምልክት ይኖረዋል (have a lock icon in the address bar)

የድር አድራሻ አወቃቀሩን (URL structure) በጥንቃቄ ይመልከቱ፡ ደህንነታቸው ያልተጠበቁ የድር አድራሻዎች  የፊደል ስህተት እንዲሁም  ተጨማሪ ቁጥሮችን ወይም ፊደሎችን በሚታወቁ አድራሻዎች ላይ በመጨመር ወይም በመቀነስ ሊጠቀሙ ይችላሉ። ለምሳሌ ትክክለኛውን "paypal.com" አመሳስለው ለማሳሳት "paypa1.comL ፊደልን በ 1 ቁጥር በመቀየር ወይም "paypal-login.xyz" በማድረግ አድራሻውን በጥንቃቄ ያልመረመረን ሰው የ paypal.com መስሎት ሊሸወድ ይችላል።

ሊንኩ ባጭሩ የተቀመጠ (shortened URLs) ከሆነ ትክክለኛውን አድራሻ ላያሳይ ይችላል። ሊንኩ የሚያጠራጥር ከሆነ   "Unshorten.it" ወይም "LongURL" ያሉትን ኦንላይን  ዌብሳይቶች  በመጠቀም ዋናውን የድር አድራሻ በማግኘት መመልከት ይቻላል፡፡

የደህንነት መጠበቂያ ሶፍትዌሮችን መጠቀም(Use security software)፡ እንደ ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ማልዌር (antivirus and anti-malware software) ያሉትን የደህንነት ሶፍትዌሮችን መጫን ደህንነቱ ያልተጥበቀ ሊንክ ወይም ዌብሳይት ሲገጥመን እነዚህ ሶፍትዌሮች ማስጠንቀቂያ ይሰጡናል።
👍51🔥1
በኦንላየን ያገኙትን መረጃ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ብዙ መጻህፍት ማንበብና ማገላበጥ አይጠበቅብዎትም። የሚያስፈልገው ነገር ምክንያታዊ የሆኑ ጥቂት ጥያቄዎችን መጠየቅ ብቻ ነው

በመስመር(online) ላይ የምናያቸዉን መረጃዎች ከማመናችን በፊት፦
👉የመረጃው ምንጭ ማነው?
👉መረጃውን ያጋራው ግለሰብ ወይም ተቋም አድልዊ አመለካከት አለው?
👉መረጃዉ ማስረጃ አለው፣ ማስረጃውስ ተጠቅሷል?
👉መረጃዉ በሌሎች ሚድያዎች ተጋርቷል? የሚሉትን እና ሌሎች መሰል ጥያቄዎችን በመጠየቅ የመረጃዉን እዉነትነት ማጣራት ይቻላል፡፡
👌41👍1🔥1