📢 ገዱ አንዳርጋቸው ወልቃይትን ሸጠዋል ስለሚለው ቪድዮ፣ በድብረ ማርቆስ በፋኖ ተማረኩ ስለተባሉት ሄሊኮፕተሮች፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሰዎችን ድምፅ እና ምስል በማስመሰል እየወጡ ያሉ መረጃዎችን በተመለከተ ፣ በ BBC ስም ስለወጣው ሃሰተኛ መረጃ እንዲሁም ከትዊተር ማረጋገጫ ጋር ተያይዞ ስላሉ እውነታዎች አንስተን በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር Beyond disinfo ፕሮግራማችን ላይ በሰፊው ተወያይተናል።
ቪድዮውን ለማየት👇
https://youtu.be/PYQ5a1ohLiM
ቪድዮውን ለማየት👇
https://youtu.be/PYQ5a1ohLiM
❤2🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በቪድዮው ላይ የሚታዩት ባንዲራዎች የኦሮሚያ ክልል መሆናቸው እና በዚያ አካባቢ ያሉት ሰዎች የሚያወሩት ቋንቋ ኦሮሚኛ መሆኑ የመረጃውን ሐሰተኛነት ያመለክታሉ።
ሙሉ ቪዲዮውን ለማየት👇
https://youtu.be/PYQ5a1ohLiM
ሙሉ ቪዲዮውን ለማየት👇
https://youtu.be/PYQ5a1ohLiM
👍2👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌻እንኳን ለ 2016 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም አዲስ ዓመት!💐
መልካም አዲስ ዓመት!💐
🎉2🔥1
📢 የቢንግ የተገላቢጦሽ ምስል መፈለጊያን(Bing reverse image search) በመጠቀም እንዴት ምስልን ማረጋገጥ እንችላለን?
✍️ የአንድን ምስል ምንጭ ከዚህ በፊት በማን ፣ለምን እና መቼ ጥቅም ላይ እንደዋለ ለማወቅ የሚረዱን ድህረ ገፆችና መተግበሪያዎች ያሉ ሲሆን፣ ለዛሬ የምናየው የማይክሮሶፍት ውጤት የሆነውን የቢንግ የተገላቢጦሽ ምስል መፈለጊያን በመጠቀም እንዴት ምስልን መመርመር እንደምንችል ነው።
✍️ ሊፈትሹት ወይም ሊያረጋግጡ የፈለጉትን ምስል ያውርዱ(save/download) ያድርጉ ወይም ምስሉ የሚገኝበትን የድር አግራሻውን(URL address) ይቅዱ (copy) ያድርጉ
✍️ Bing.com ድህረ ገጽን ይክፈቱ
✍️ በመፈለጊያ ቦታ ላይ የሚገኘውን የካሜራ ምስል በመጫን መመርመር የምንፈልገውን ምስል ወይም የምስሉን መዳረሻ (link)ማስገባትና መፈለግ
✍ የሚጠቀሙት በስልክ ከሆነና በማስፈንጠሪያ (link) ለመፈለግ የስልኮዎን browser ወደ desktop እይታ መቀየር ይኖርብዎታል፣ በምስል ለመፈልግ ከሆነ ባይቀይሩትም ይሰራል።
✍️ ውጤቶቹ ምስሉ ከተጋራ ምን ያህል ጊዜ እንደሆነው እንዲሁም አካባቢውን፣ የምስሉን አውድ እና የመሳሰሉትን ሌሎች መረጃዎችን ይሰጥዎታል።
✍️ ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇
TikTok|Facebook|website|Twitter

✍ በአማራ ክልል ያለውን ግጭት ተከትሎ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ ብዛት ያላቸው ሰዎች ለእስር እንደተዳረጉ መረጃዎች ያሳያሉ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እዝ መምሪያም በተለያዩ ማቆያ ቦታዎች 764 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎችን እንዳሰረ ገልጿል።
✍ ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚድያዎች ላይ "በአማራ ብሔር ላይ በተለያዩ ማቆያ ቦታዎች እየደረሱ ያሉ በደሎች እንደሆኑ የሚገልጹ መረጃዎች እና ምስሎች" በስፋት እየተዘዋወሩ ነው። በሌላ በኩል እነዚህን ምስሎች የቆዩና ወቅታዊ እንዳልሆኑ ለማሳየት በማህበራዊ ሚድያ ፣ በተለይም በፌስቡክ ላይ ቆየት ያሉ ልጥፎችን ኤዲት በማድረግና ከሰሞኑ የሚዘዋወሩ ምስሎችን በመተካት፣ ሰሞናዊ መረጃውን ሃሰተኛ እና የቆየ እንደሆነ ለማሳየት የሚጥሩ አካላት እንዳሉ መመልከት ችለናል።
ሀቅቼክ የቆዩ ልጥፎችን ኤዲት በማድረግ እየተሰራጩ ባሉ ሃሰተኛ መረጃዎች ዙሪያ ያዘጋጀውን ጹሑፍ ያንብቡ👇
https://haqcheck.org/editing-old-posts-a-tactic-of-disinformation-in-the-midst-of-amhara-conflict/

HaqCheck
Editing Old Posts: A Tactic of Disinformation in the Midst of Amhara Conflict - HaqCheck
The armed conflict in the Amhara region of Ethiopia has intensified in recent months. The immediate cause of the conflict was the Ethiopian government’s decision to dissolve regional special police forces. Since then, the Amhara region has been engulfed in…
👍6🔥2
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ከታወጀበት ከሐምሌ 28 ፤ 2015 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ የፌደራሉ መንግስት የአማራ ብሄር ተወላጆችን ጨምሮ ፖለቲከኞችን ፤ ጋዜጠኞችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን አስሯል።
እንደ መንግስት ሚድያዎች የዜና ዘገባ ከሆነ የፌደራሉ መንግስት 764 የሚሆኑ በክልሉ ያለውን የትጥቅ እንቅስቃሴ ይደግፋሉ ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ይፋ አድርጓል።
ይሁን እንጂ የተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ ሪፖርቶች መንግስት የአማራ ብሄር ተወላጆችን ኢላማ አድርጎ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች በሚገኙ የእስር ማቆያ ቦታዎች እንዳሰራቸው እየተናገሩ ይገኛሉ።
ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዘው እየወጡ ያሉ የማህበራዊ ሚድያ ላይ ፖስቶች በመንግስት እስር ላይ የሚገኙ የአማራ ብሄር ተወላጆችን የሚያሳዩ ናቸው በመባል እየተሰራጩ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል እነዚህን መረጃዎች ሃሰተኛ እና መንግስት ያሰራቸውን የአማራ ክልል ተወላጆች እንደማያሳዩ ለማሳየት የቆዩ የማህበራዊ ሚድያ ልጥፎች ላይ አርትዖት በመስራት ጭምር መረጃውን ሃሰት ነው የሚሉ አካላትም እንዳሉ መመልከት ችለናል።
በዚህ ዙሪያ ሀቅቼክ በአማርኛ ያዘጋጀውን ሙሉ ጹሑፍን ያንብቡ
https://bityl.co/L95i

የቆዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክቶች ላይ አርትዖት መስራት ፤ አዲሱ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ስልት - HaqCheck
የፌደራሉ መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን ትጥቅ በማስፈታት እንደፍላጎታቸው ወደመከላከያ ፤ ፌደራል እና የክልል ፖሊስ እንዲቀላቀሉ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ በአማራ ክልል ግጭት መከሰቱ ይታወሳል። ይህ በክልሉ የተከሰተው ግጭት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይበልጥ እየተባባሰ እና ጉዳት እያስከተለ መምጣቱን የሚያሳዩ ሪፖርቶች እየወጡ ይገኛሉ። ይህን ተከትሎ አማራ ክልል በፌደራል መንግስት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል…
👍5
📢 በሀቅቼክ እየተዘጋጀ በየሳምንቱ ወደ አንባብያን የሚደርሰውን ሳምንታዊ የሃሰተኛ መረጃ ማጠቃለያ እንዲሁም ትንታኔዎችን እና መረጃዎችን ለማጣራት ጠቃሚ የሆኑ ምክሮችን በየሳምንቱ በኢሜል አድራሻዎ እንዲደርስዎ በ https://bit.ly/3rl8vwn ላይ ይመዝገቡ ወይም በድህረ ገጽ www.HaqCheck.org ላይ በመግባት ሰብስክራይብ ማድረግ ይችላሉ።
✍️ ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇
TikTok|Facebook|website|Twitter
✍️ ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇
TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2
ከአማራ ብሔር ተወላጆች እስር ጋር ተያይዞ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ፣ የክርስቲያን ታደለ ከእስር እንደተለቀቀ ያሳያል ተብሎ የወጣው ቪድዮ ፣ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በፋኖ መሳርያ እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል ስለሚለው ቪድዮ፣ የህዳሴ ግድብ አራተኛ ሙሌትን ተከትሎ የተፈጠሩት አወዛጋቢ መረጃዎች እና በቆዩ ምስሎች ላይ አርትዖት በመስራት ዙሪያ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር ፕሮግራማችን ይዘንላችሁ ቀርበናል ይከታተሉን👇
https://youtu.be/kfibXxTYQY8?si=q9bmK6-4Nh3msbAJ
https://youtu.be/kfibXxTYQY8?si=q9bmK6-4Nh3msbAJ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አቶ ክርስትያን ታደለ ከእስር ተፈቷል?
ሙሉ ቪድዮውን ይመልከቱ https://ytube.io/3kG5
✍️ ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇
TikTok|Facebook|website|Twitter
ሙሉ ቪድዮውን ይመልከቱ https://ytube.io/3kG5
✍️ ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇
TikTok|Facebook|website|Twitter
👍3👌1
የባለፈው ሳምንት ዳሰሳ
...........
1: ምስሉ የኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎች በሶማሌ መንደሮች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ አያሳይም
ከሰሞኑ አንድ የትዊተር አካውንት "በኦሮሚያ ክልል መንግስት ድጋፍ የታጠቁ የኦሮሞ ታጣቂዎች በጅጅጋ አቅራቢያ በሚገኘው ትልቁ የሶማሌ ስደተኞች ካምፕ ቆላጂ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ከሚገልጽ ጹሑፍ ጋር ሁለት ፎቶዎችን በማያያዝ አጋርቶ ነበር። " ፖስቱ ከ 294 ጊዜ በላይ የተጋራ ሲሆን ከ428 በላይ ግብረ መልሶችን አግኝቷል።
ከሰሞኑ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ድንበር አካባቢ ያለውን ግጭት ተከትሎ በማህበራዊ ሚድያ ላይ የተለያዩ መረጃዎች እየተጋሩ ነው። ከነዚህም ውስጥ በመግቢያ ላይ የጠቀስነው የቲውተር መረጃ ይገኝበታል።
ሀቅቼክ እንዳጣራው መርጃውን ለመደገፍ የተጠቀመው ምስል የቆየና አንደኛው ፎቶ መጀመሪያ ላይ የተለጠፈው እ.ኤ.አ. ነሃሴ 19, 2019 በዛው አካባቢ ያለ ሁኔታን በሚገልጽ ጹሑፍ ስር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በግንቦት 27, 2018 በካልፎርኒያ የተከሰተ ሰደድ እሳትን ተከትሎ የተጋራ ምስል እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል። ስለዚህ ይህ መረጃ ሃሰተኛ ነው።
2: ቪድዮው በአማራ ክልል በመከላከያ የተፈጸመን ድብደባ አያሳይም
ሌላው ከሰሞኑ በአማራ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በትዊተር ላይ "የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ሰዎችን እየደበድቡ እንደሆነ ከሚገልጽ ጹሑፍ ጋር ሲዘዋወር ነበር"። ቪድዮው ከ 379 በላይ ሲጋራ ከ 329 በላይ ግብረ መልስ አግኝቷል፣
ነገር ግን ቪድዮው ከሰሞኑ በአማራ ክልል እንደተፈጸመ አያሳይም። ቪድዮው መጀመሪያ ከሁለት አመት በፊት "መከላከያ በትግራይ ክልል ሰዎችን እየደበደበ እንደሆነ ከሚገልጽ ጹሑፍ ጋር ተጋርቶ እንደነበር ያሳያል። ስለዚህ መረጃው ሃሰተኛ ነው።
ሙሉ መርጃውን በዚህ ሊንክ ያንብቡ

👍4🙏1
ሃሰተኛ መረጃን ከመከላከል አንጻር የኢትዮጵያ መንግስት መስሪያ ቤቶች ምላሽ ሰጪነት በሚል ርዕስ አንድ አዲስ ጥናት ከሰሞኑ ለህትመት በቅቷል። ጥናቱን ያደረጉት ድርጅታችን ኢንፎርም አፍሪካ እና ሚዳን የተባለ አለም አቀፍ ተቋም በጋራ በመሆን ነው።
በጥናቱም የኢትዮጵያ መንግስት 🔍📰 ለመገናኛ ብዙኃን በቂ መረጃ አለመስጠቱ፣ ወቅታዊ መግለጫዎችን በሰዓቱ አለመስጠቱ እና ከመንግስት ጋር ግንኙነት ላላቸው ሚዲያዎች ያለው አድልአዊ የመረጃ አቅርቦት ትክክለኛ የመረጃ ፍሰት እንዳይኖር በማድረግ የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንደዳባባሰ ያሳያል። 📉🔥
ጥናቱ መንግስት ማዕከላዊ የመረጃ ስርዓት ሊኖረው እንደሚገባ፣ ንቁ የማህበራዊ ሚዲያ ተሳትፎ ማድርግ እንዳለበት፣ መደበኛ የፕሬስ መግለጫዎች መስጠት እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ወቅታዊ መረጃዎችን በግልጽ ለሚዲያ በመስጠት የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመከላከል ዙሪያ አውንታዊ አስተዋጽኦ ሊኖርው እንደሚችል ይጠቁማል💬👥
ሙሉውን የጥናት ጹሑፍ በዚህ ሊንክ ያንብቡ፡ https://bit.ly/46w9Z5E

🙏5🔥1
#የሀሰተኛ_መረጃ_ጥቆማ❗️
ከሰሞኑ በአቢሲንያ ባንክ ስም በተከፈተ የቲክቶክ አካውንት ለአሸናፊዎች የ10,000 ብር የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትበት ነው በሚል ላይክ ያደረጉና ኮፒሊንክ ያደረጉ ሰዎች እጩ የሚሆኑበት ‘10 ሺ ቻሌንጅ’ በሚል ስያሜ ያገኘ ቪድዮ በስፋት ሲጋራ ነበር።
ይህ አካውንት ባለቤትነቱ የአቢሲንያ ባንክ ያልሆነና ባንኩ ይህ ጽሁፍ እስከታተመበት ጊዜ ድረስ ይፋዊ ቴሌግራም፤ ፌስቡክ፤ ኤክስና (ትዊተር) ሊንክዲን አካውንቶችን ብቻ ለማህበራዊ ሚድያ ተደራሸነት እንደሚጠቀም ከባንኩ ከተገኘ መረጃ ለማረጋገጥ ተችሏል። ‘10 ሺ ቻሌንጅ’ በሚል የቀረበውም የይሳተፉ ይሸለሙ ጥሪ ሀሰትና ከባንኩ እውቅና ውጭ መሆኑ ተረጋግጧል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተስፋፉ የመጡት እንደዚህ አይነት ማጭበርበሪያ መንገዶች የታዋቂ ሰዎች ስምና የድርጅቶች ስያሜዎች በመጠቀም የአካውንቱን ተከታዮች በማብዛት አካውንቱን በገበያ ላይ ለማዋል የሚጠቀሙበት መንገድ ነው። ስለሆነም ማህበረሰቡ ይፋዊ የሆኑ ገጾችን ብቻ በመከተል ይህንን ከሚመስሉ የማጭበርበሪያ ዘዴዎች ራሱን መጠበቅ አለበት።

👍5🙏1👌1
#የሀሰተኛ_መረጃ_ጥቆማ
ከሰሞኑ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስም የተከፈተ የቴሌግራም ቦት ለአሸናፊዎች የ3000 ብር የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትበት ነው በሚል ቻናሉን ለተቀላቀሉና ለሌሎች ያጋሩ ሰዎች የሚሸለሙበት ነው በማለት በስፋት ተጋርቷል።
ይህ አካውንት ባለቤትነቱ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እንዳልሆነ ሀቅቼክ አረጋግጧል። የኩባንያው የቴሌግራም አካውንት በድህረገጹ ላይ የተጠቀሰ እና በአሁኑ ወቅት ከ22 ሺህ በላይ ተከታዮች ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።
ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ በሚል የቀረበውም የይጋብዙ ይሸለሙ ጥሪ ሀሰትና ከኩባንያው እውቅና ውጭ መሆኑ ተረጋግጧል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በይበልጥ እየተስፋፉ የመጣው የማጭበርበሪያ መንገድ የአካውንቱን ተከታዮች በማብዛት አካውንቱን በገበያ ላይ ለማዋል የታዋቂ ሰዎች ስምና የድርጅቶች ስያሜዎች በመጠቀም የሚደረግ ነው።
ስለሆነም የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ይፋዊ የሆኑ ገጾችን ብቻ በመከተል ይህንን ከሚመስሉ የማጭበርበሪያ ዘዴዎች ራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው።

👍3🔥1🙏1
በማህበረዊ ሚድያ ላይ በምስል የተደገፉ መረጃዎች ሲያጋጥሙን ማድረግ ያሉብን ነገሮች:
✍ በምስሉ ላይ የሚታዩ ፅሁፎች ካሉ የተጻፉበት ቋንቋ ምን እንደሆነ እና ምልክቶችም ካሉ ምንነታቸውን ማየትና መለየት
✍ ሰንደቅ አላማ፣ አርማ ወይም ሌሎች ማንነት ገለጫ ነገሮችን በምስሉ ውስጥ መፈለግ
✍ የመኪና ታርጋዎች፣ መንገዶች እና የመንገድ ምልክቶችን ማስተዋል
✍ ህንጻዎችን፣ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ እና አከባቢውን መቃኘት
እነዚህን ከላይ የጠቀስናቸውን በመመልከት ስለ ምስሉ ፍንጭ ሰጪ መረጃዎችን ልናገኝ እንችላለን፣ በተጨማሪም የምስል መመርመሪያ መሳሪያዎች ስላሉ እንሱን መጠቀም ይኖርብናል።

📢 ኢትዮጵያ በቢዝነስ በጣም አዋጭ እንዲሁም በጣም አክሳሪ ሀገሮች ዝርዝር ዉስጥ ስለመካተቷ ፤ በጎንደር የእሳት ቃጠሎ እንደደረሰ ስለሚያሳየው ቪድዮ ፤ በኮምቦልቻ ፋኖ ሙስሊሙን አይወክልም ብለው ሰልፍ እንዳደረጉ ስለሚያሳየው ቪድዮ እና ሌሎችንም የሃገር ዉስጥና ከሃገር ውጪ በስፋት ሲዘዋወሩ የነበሩ መረጃዎችን በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር ፕሮግራማችን ይዘን ቀርበናል ይከታተሉን፡፡
👇👇👇
https://youtu.be/YPfMInW620E?si=WvByr1coX6yFDtNQ

👍4🔥1
📢 በአፍሪካ እውነትን ማጣራት(fact Checking) ላይ የሚሰሩ ተቋማት ዓመታዊ ጉባዔያቸውን በሞሪሽየስ ዩኒቨርስቲ ማካሄድ ጀምረዋል። በጉባኤው ላይ የተለያዩ ሀቅን የሚያጣሩ ድርጅቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ይህ ስብሰባ የተዛቡ መረጃዎችን በመዋጋት ረገድ ተባብሮ መሥራትንና መልካም ተሞክሮን ማሳደግ ላይ የሚያተኩር እንደሚሆን ተገልጿል። በኢትዮጵያም ሀሰተኛ መረጃን ማጣራት ላይ የሚሰራው ሀቅቼክ በጉባኤው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
#Haqcheck #AfricaFactSummit23 #FactChecking #Disinformation

👍5👏1
ከአጭበርባሪዎች እራሳችንን እንዴት እንከላከል?
❗️በውጭው ዓለም በስፋት የሚዘወተሩት የኦንላይን የማጭበርበር ዘዴዎች የተለመዱና የታወቁ ናቸው። አሁን አሁን በሃገራችንም ብዙ ሰዎች ለተለያዩ አጭበርባሪዎች ሰላባ እየሆኑ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
❗️እንዚህ አጭበርባሪዎች በዋናነት የሚጠቀሙት ዘዴ:- ከዲጂታል ከረንሲይ (ከክሪፕቶ ከረንሲይ) ፣ ከ ኦንላይን ስራ እና ከኦንላየን ንግድ ጋር የተያያዙ የማጭበርበሪያ መልክቶችን በመላክ እና በማህበራዊ ሚድያ ላይ በማስተዋወቅ ነው።
❓የምናያቸውን መልክቶች እና ማስታወቂያዎች እንዴት በቀላሉ ማጭበርበሪያ መሆናቸውን ማውቅ እንችላለን? 👇👇👇
✍ ያገኘነው መልክት ወይም በማህበራዊ ሚድያ ላይ የተመለከትነው ማስታወቂያ እጅግ በጣም አጓጊና በቀላሉ ያለ ድካም ትርፋማ መሆን እንደሚቻል የሚገልጽ ከሆነ፣
✍ ከማናውቀው ሰው በማህበራዊ ሚድያ የውስጥ መልክት ከተላከልን፣ አለማመን ፣ መጠራር ፣ ለምን ብሎ መጠየቅ ይኖርብናል
✍ የግል መረጃን እና ቅድመ ክፍያ የሚጠይቁ ከሆነ፣ ህጋዊ ተቋማት ስራ ለማስጀመር ቀድመዉ ቅድመ ክፍያን እንደመስፈርት አድርገው አይጠይቁም፡፡
✍ በቂ መረጃ የማይሰጡ ከሆነና ግልጽ ካልሆኑ፣ እነሱ የሚሉትን ብቻ እንድናደርግ የሚፈልጉ ከሆነ
✍ ነገሮችን በፊጥነት እንድናደርግ እና እንድንወስን የሚያቻኩሉን ከሆነ
✍ የተቋሙን ድህረ ገጽ ቢልኩልን እንኳን ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
እንዚህን ከላይ የጠቀስናቸውን ካገኘንባቸው አጭበርባሪዎች እንደሆኑ ማወቅ እንችላለን።
"There is no free money"

🔥3🙏2👌1
#የሀሰተኛ_መረጃ_ጥቆማ
ከሰሞኑ በአማራ ባንክ ስም በተከፈተ የቲክቶክ አካውንት ለአሸናፊዎች የ10,000 ብር የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትበት ነው በሚል ላይክ ያደረጉና ኮፒሊንክ ያደረጉ ሰዎችን እጩ የሚሆኑበት ቻሌንጅ በሚል አንድ ቪድዮ በስፋት ተጋርቷል።
ሀቅቼክ ባደረገው ማጣራት ይህ የቲክቶክ አካውንት የአማራ ባንክ አይደለም። ባንኩ ይፋዊ ቴሌግራም፤ ፌስቡክ፤ ኤክስና (ትዊተር) እና ሊንክዲን አካውንቶችን ብቻ ለማህበራዊ ሚድያ ተደራሸነት እንደሚጠቀምና እነዚህም ሊንኮች ይፋዊ ገጹ ላይ እንደሚገኙ ከባንኩ ከተገኘ መረጃ ለማረጋገጥ ተችሏል።
ባንኩ ለሀቅቼክ እንዳሳወቀው በባንኩ ስም የተከፈቱ ሃሰተኛ አካውንቶች እንደሚገኙና 10 ሺ ብር ያሸልማል በሚል በቲክቶክ የሚሰራጨውም የይሳተፉ ይሸለሙ ጥሪ ሀሰትና ከባንኩ እውቅና ውጭ መሆኑ ተረጋግጧል።
የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ይፋዊ የሆኑ ገጾችን ብቻ በመከተል ይህንን ከሚመስሉ የማጭበርበርያ መልእክቶችና ጥሪዎች ራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው።
ከሰሞኑ በአማራ ባንክ ስም በተከፈተ የቲክቶክ አካውንት ለአሸናፊዎች የ10,000 ብር የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትበት ነው በሚል ላይክ ያደረጉና ኮፒሊንክ ያደረጉ ሰዎችን እጩ የሚሆኑበት ቻሌንጅ በሚል አንድ ቪድዮ በስፋት ተጋርቷል።
ሀቅቼክ ባደረገው ማጣራት ይህ የቲክቶክ አካውንት የአማራ ባንክ አይደለም። ባንኩ ይፋዊ ቴሌግራም፤ ፌስቡክ፤ ኤክስና (ትዊተር) እና ሊንክዲን አካውንቶችን ብቻ ለማህበራዊ ሚድያ ተደራሸነት እንደሚጠቀምና እነዚህም ሊንኮች ይፋዊ ገጹ ላይ እንደሚገኙ ከባንኩ ከተገኘ መረጃ ለማረጋገጥ ተችሏል።
ባንኩ ለሀቅቼክ እንዳሳወቀው በባንኩ ስም የተከፈቱ ሃሰተኛ አካውንቶች እንደሚገኙና 10 ሺ ብር ያሸልማል በሚል በቲክቶክ የሚሰራጨውም የይሳተፉ ይሸለሙ ጥሪ ሀሰትና ከባንኩ እውቅና ውጭ መሆኑ ተረጋግጧል።
የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ይፋዊ የሆኑ ገጾችን ብቻ በመከተል ይህንን ከሚመስሉ የማጭበርበርያ መልእክቶችና ጥሪዎች ራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው።
👍3🔥1🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሃሰተኛ ቪዲዮዎችን እንዴት መለየት እንችላለን?
👉 በመልክአ ምድራዊ እይታ: በቪዲዮው ውስጥ ከዋናው ሁነት በስተጀርባ እና በአካባቢው ላይ የሚታዩትን ሊለዩ የሚችሉ ምልክቶችን፣ ሕንፃዎችን ወይም የመሬት ገጽታዎችን ልብ ብሎ መመልከት እና ማመስከር።
👉 በተሽከርካሪ ታርጋዎች፡- በቪዲዮው ላይ ተሽከርካሪዎች የሚታዩ ከሆነ የሰሌዳ ቁጥራቸውን እና የየት ሀገር ታርጋ እንደሆነ መለየት።
👉በባንዲራ፡ በቪዲዮው ውስጥ ባንዲራ ወይም ብሄራዊ ምልክቶችን መፈለግ። ዲዛይናቸውን፣ ቀለሞቻቸውን እና የቦታ አቀማመጠቸውን በትኩርት መመልከት
👉 በቪድዮ ውስጥ በሚሰሙ ድምጾች፡- ከዋናው ድምጽ ውጭ ያሉትን በትኩረት ማድመጥና መለየት። ከአካባቢው ወይም ከቪዲዮው ይዘት ጋር የማይዛመድ ጫጫታ ወይም ሌላ ድምጽ የሚሰማ ከሆነ ቪድዮው ሃሰተኛ ሊሆን ይችላል።
👉 በድምፅ ጥራት፡- የቪድዮውን ድምጽ ጥራት እና ወጥነትን በትኩረት መመልከት። ድንገተኛ መቆራረጦች፣ ወይም ወጥነት የለሽ ንግግር ካለው፣ የተቀየረ እና አርትኦት የተሰራበት ሊሆን ይችላል።
👉በምልክቶች፡ በቪዲዮው ላይ የሚታዩትን ምልክቶች ወይም አርማዎችን መመልከት፣ የመንገድ ምልክቶችን፣ የተሰቀሉ ባነሮችን በመመልከት ከመረጃው ይዘት ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ።
👉ቀኖች፡ በቪዲዮው ላይ የተጠቀሱ ወይም የሚታዩ ቀኖች ካሉ እነሱን በትኩረት መመልከት። ከተገለጹት ክስተቶች ወይም አውድ ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን ያረጋግጡ።
እንዚህን ከላይ የጠቀስናቸውን ፍንጭ ሰጭ መረጃዎችን ከለየን በኃላ የተለያዩ መሳሪያዎችን እንደ(Geo location, Invid ) እና ሌሎችንም በመጠቀም ማረጋገጥ እንችላለን።

❤3🔥1