HaqCheck
429 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
ባሳለፍነው ሳምንት በተለያዩ ሚድያዎች ሲዘዋወሩ ከነበሩ መረጃዎች ውስጥ አወዛጋቢ እና ሃሰተኛ የሆኑ መረጃዎች እንዲሁም ስለ ፕሮግራማችን አጠቃላይ ይዘት አንስተን በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር/Beyond disinfo ፕሮግራማችን ተወያይተናል።

ይከታተሉን👇
https://youtu.be/a_hEFZ6bRJ4
👍21
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Deepfake" ማለት አርቴፊሻል ኢንቴሌጀንስ (Ai) በመጠቀም የሰዎችን ምስል ፣ ቪድዮ እና ድምፅ በማስመሰል ለተለያዩ አላማ የማዋል ሂደት ነው።  በአለማችን የተለያዩ ሃገራት  መሪዎችን እና ታዋቂ ሰዎችን ድምፅና ምስል በመጠቀም እነሱ እንደተናገሩትና ድርጊቱን እንደፈፀሙት በማስመሰል አሳሳች መረጃዎችን መመልከት የተለመደ ሆኗል፣ በሃገራችንም  ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በ Ai  የተቀነባበሩ ቪድዮችን ተመልከተናል።
ቪድዮውን ይመልከቱ 👆🏻

✍️ ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍4🙏21
ቪድዮው በደብረ ማርቆስ በፋኖ የተማረከ ሂሊኮፕተርን አያሳይም

ከ46,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስ ቡክ ገፅ እ.ኤ.አ. በ ነሐሴ 28/ 2023 በአንድ ቪዲዮ በደብረ ማርቆስ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር በፋኖ ታጣቂዎች የተማረከ እንደሆነ ከሚገልጽ ጹሑፍ ጋር አጋርቷል። የፌስቡክ ልጥፉ ይህ ጽሑፍ እስከተዘጋጀበት ድረስ ወደ 300 የሚጠጉ ግብረ ምላሾችን እና ከሰባት ሺህ በላይ ሰዎች ተመልክተውታል። 

የፌድራል መንግስት የክልል ልዩ ሃይልን አፈርሳለሁ ማለቱን ተከትሎ የተነሳው አለመግባባት በተለይም በነሀሴ ወር መጀመሪያ አካባቢ የፋኖ ታጣቂዎች በርካታ ከተሞችን እና አካባቢዎችን ሲቆጣጠሩ ግጭቱ ተባብሶ ቀጥሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከተሞቹን መልሶ ለመያዝ  መከላከያ ሰራዊትን በማሰማራት አብዛኞቹን ዋና ዋና ከተሞች መልሶ ይዟል ነገር ግን ግጭቱ በአንዳንድ አካባቢዎች እንደቀጠለ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይህን ተከትሎ  የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር በደብረ ማርቆስ በፋኖ ታጣቂዎች መማረኩን ከሚገልጽ የጹህፍ መግለጫ ጋር ቪድዮው ተጋርቷል።

ሀቅቼክ እንዳጣራው ቪዲዮው የቆየና ወቅታዊ እንዳልሆነ ማረጋገጥ ችሏል። ዋናው ቪዲዮ ሚያዝያ 26 ቀን 2019 በአንድ የፌስቡክ ገጽ ላይ የተለጠፈ ሲሆን የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ (ሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ) ንብረት የሆነው ሄሊኮፕተር በሞተር ብልሽት ምክንያት ተከስክሶ እንደነበር የተያያዘው  መግለጫው ይገልጻል። ሙሉ ጹሁፍን ለማንበብ👇

https://haqcheck.org/does-the-image-show-fano-militants-downed-an-ethiopian-helicopter-in-debre-markos/?amp=1
👍3
ይህ የምትመለከቱት የሂሊፕተር ምስል ወታደሮችን ወደ አማራ ክልል ሲያጓጉዝ አያሳይም።

ከሰሞኑ ከ50,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር አካውንት በአማራ ክልል ያለውን ግጭት ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊቱን በሄሊኮፕተር ወደ አማራ ክልል ሲጓጉዝ የሚያሳይ ምስል እንደሆነ በመግለጽ አጋርቷል። ልጥፉ ወደ 61 ጊዜ የተጋራ ሲሆን ከ 88 በላይ ግብረ መልሶችን አግኝቷል።

የፌዴራል መንግስት የክልል ልዩ ሃይል ፓሊስን አፈርሳለሁ ማለቱን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞና ግጭት እስካሁን ከመቀጠሉ ጋር ተያይዞ ብዙ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።  ከነዚህም ውስጥ ከላይ የጠቀስነው የትዊተር ልጥፍ ይገኝበታል።

ሀቅቼክ እንዳረጋገጠው ምስሉ ወቅታዊ  ያልሆነ እና የቆየ እንደሆነ ማረጋገጥ ችሏል ። ዋናው ምስል በፌስቡክ ነሐሴ 2 ቀን 2021 በተሰራጨ ቪዲዮ ላይ ተጋርቶ እንደነበር ማረጋገጥ ተችሏል።

በአማራ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ብዛት ያላቸው መረጃዎች እየተዘዋወሩ ስለሆነ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ከማመናችን በፊት ማጣራትና ምረጋገጥ ይኖርብናል።

ሙሉ ጹሑፍን ለመማንበብ 👇👇👇
https://haqcheck.org/does-the-image-show-a-plane-transporting-soldiers-to-the-amhara-region/
👍2👎1
#የሀሰተኛ_መረጃ_ጥቆማ

ከሰሞኑ የህዝብ ተወካዩ እና የአብን ፓርቲ የቀድሞ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ክርስትያን ታደለ ከእስር እንደተፈቱ የሚገልጹ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚድያው ላይ ተመልክተናል። ከነዚህ መካከል አንዱ በቲክቶክ ላይ ‘አቶ ክርስትያን ታደለ ከእስር ተፈተዋል” ከሚል ጽሁፍ ጋር አንድ ቪድዮ ተሰራጭቶ ነበር።

ይሁን እንጂ አቶ ክርስትያን ከእስር መፈታታቸው ያሳያል የተባለው ቪድዮ ከ3 አመት በፊት ተሰራጭቶ የነበረ ሲሆን ቪድዮው ከ3 አመት በፊት የአብን የፖለቲካ ጉዳዮች ሀላፊ የነበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለ “አንድ አማራ ለሁሉም አማራ" በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ በተዘጋጀው ህዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ ካስተላለፉት መልእክት የተወሰደ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።

አቶ ክርስትያን በአማራ ክልል የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ከታወጀ በኋላ ታስረው አዋሽ አርባ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል።
👍21🙏1
📢 ገዱ አንዳርጋቸው ወልቃይትን ሸጠዋል ስለሚለው ቪድዮ፣ በድብረ ማርቆስ በፋኖ ተማረኩ ስለተባሉት ሄሊኮፕተሮች፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሰዎችን ድምፅ እና ምስል በማስመሰል እየወጡ  ያሉ መረጃዎችን በተመለከተ ፣ በ BBC ስም ስለወጣው ሃሰተኛ መረጃ እንዲሁም ከትዊተር ማረጋገጫ ጋር ተያይዞ ስላሉ እውነታዎች አንስተን በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር Beyond disinfo ፕሮግራማችን ላይ በሰፊው ተወያይተናል።

ቪድዮውን ለማየት👇
https://youtu.be/PYQ5a1ohLiM
2🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በቪድዮው ላይ የሚታዩት ባንዲራዎች የኦሮሚያ ክልል መሆናቸው እና በዚያ አካባቢ ያሉት ሰዎች የሚያወሩት ቋንቋ ኦሮሚኛ መሆኑ የመረጃውን ሐሰተኛነት ያመለክታሉ።

ሙሉ ቪዲዮውን ለማየት👇
https://youtu.be/PYQ5a1ohLiM
👍2👌1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው 'ወልቃይትን ለትግራይ እንደሸጡ' የሚያሳይው ቪድዮ ከየት ተገኘ ?

ሙሉ ቪዲዮውን ለማየት👇
https://youtu.be/PYQ5a1ohLiM
👍2🔥1👏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌻እንኳን ለ 2016 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም አዲስ ዓመት!💐
🎉2🔥1
📢 የቢንግ የተገላቢጦሽ ምስል መፈለጊያን(Bing reverse image search) በመጠቀም እንዴት ምስልን ማረጋገጥ እንችላለን?

✍️ የአንድን ምስል ምንጭ ከዚህ በፊት በማን ፣ለምን እና መቼ ጥቅም ላይ እንደዋለ ለማወቅ የሚረዱን ድህረ ገፆችና መተግበሪያዎች ያሉ ሲሆን፣ ለዛሬ  የምናየው የማይክሮሶፍት ውጤት የሆነውን የቢንግ የተገላቢጦሽ ምስል መፈለጊያን በመጠቀም እንዴት ምስልን መመርመር እንደምንችል ነው።

✍️ ሊፈትሹት ወይም ሊያረጋግጡ የፈለጉትን ምስል ያውርዱ(save/download)  ያድርጉ ወይም ምስሉ የሚገኝበትን የድር አግራሻውን(URL address) ይቅዱ (copy) ያድርጉ

✍️  Bing.com  ድህረ ገጽን ይክፈቱ

✍️ በመፈለጊያ ቦታ ላይ የሚገኘውን የካሜራ ምስል በመጫን መመርመር የምንፈልገውን ምስል ወይም የምስሉን መዳረሻ (link)ማስገባትና መፈለግ

የሚጠቀሙት በስልክ ከሆነና በማስፈንጠሪያ (link) ለመፈለግ የስልኮዎን browser ወደ desktop እይታ መቀየር ይኖርብዎታል፣ በምስል ለመፈልግ ከሆነ ባይቀይሩትም ይሰራል።

✍️ ውጤቶቹ ምስሉ ከተጋራ ምን ያህል ጊዜ እንደሆነው እንዲሁም አካባቢውን፣ የምስሉን አውድ እና የመሳሰሉትን ሌሎች መረጃዎችን ይሰጥዎታል።

✍️ ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2👌1
በአማራ ክልል ያለውን ግጭት ተከትሎ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ ብዛት ያላቸው ሰዎች ለእስር እንደተዳረጉ መረጃዎች ያሳያሉ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እዝ መምሪያም በተለያዩ ማቆያ ቦታዎች 764 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎችን እንዳሰረ ገልጿል።

ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚድያዎች ላይ "በአማራ ብሔር ላይ በተለያዩ ማቆያ ቦታዎች እየደረሱ ያሉ በደሎች እንደሆኑ የሚገልጹ  መረጃዎች እና ምስሎች" በስፋት እየተዘዋወሩ ነው። በሌላ በኩል እነዚህን ምስሎች የቆዩና ወቅታዊ እንዳልሆኑ ለማሳየት በማህበራዊ ሚድያ ፣ በተለይም በፌስቡክ ላይ ቆየት ያሉ ልጥፎችን ኤዲት በማድረግና ከሰሞኑ የሚዘዋወሩ ምስሎችን በመተካት፣ ሰሞናዊ መረጃውን ሃሰተኛ እና የቆየ  እንደሆነ ለማሳየት የሚጥሩ አካላት እንዳሉ መመልከት ችለናል።

ሀቅቼክ የቆዩ ልጥፎችን ኤዲት በማድረግ እየተሰራጩ ባሉ ሃሰተኛ መረጃዎች ዙሪያ ያዘጋጀውን ጹሑፍ  ያንብቡ👇
https://haqcheck.org/editing-old-posts-a-tactic-of-disinformation-in-the-midst-of-amhara-conflict/
👍6🔥2
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ከታወጀበት ከሐምሌ 28 ፤ 2015 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ የፌደራሉ መንግስት የአማራ ብሄር ተወላጆችን ጨምሮ ፖለቲከኞችን ፤ ጋዜጠኞችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን አስሯል።

እንደ መንግስት ሚድያዎች የዜና ዘገባ ከሆነ የፌደራሉ መንግስት 764 የሚሆኑ በክልሉ ያለውን የትጥቅ እንቅስቃሴ ይደግፋሉ ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ይፋ አድርጓል።  

ይሁን እንጂ የተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ ሪፖርቶች መንግስት የአማራ ብሄር ተወላጆችን ኢላማ አድርጎ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች በሚገኙ የእስር ማቆያ ቦታዎች እንዳሰራቸው እየተናገሩ ይገኛሉ።

ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዘው እየወጡ ያሉ የማህበራዊ ሚድያ ላይ ፖስቶች በመንግስት እስር ላይ የሚገኙ የአማራ ብሄር ተወላጆችን የሚያሳዩ ናቸው በመባል እየተሰራጩ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል እነዚህን መረጃዎች ሃሰተኛ እና መንግስት ያሰራቸውን የአማራ ክልል ተወላጆች እንደማያሳዩ ለማሳየት የቆዩ የማህበራዊ ሚድያ ልጥፎች ላይ አርትዖት በመስራት ጭምር መረጃውን ሃሰት ነው የሚሉ አካላትም እንዳሉ መመልከት ችለናል።

በዚህ ዙሪያ ሀቅቼክ በአማርኛ ያዘጋጀውን ሙሉ ጹሑፍን  ያንብቡ

https://bityl.co/L95i
👍5
📢 በሀቅቼክ እየተዘጋጀ በየሳምንቱ ወደ አንባብያን የሚደርሰውን ሳምንታዊ የሃሰተኛ መረጃ ማጠቃለያ እንዲሁም ትንታኔዎችን እና  መረጃዎችን ለማጣራት ጠቃሚ የሆኑ  ምክሮችን በየሳምንቱ በኢሜል አድራሻዎ እንዲደርስዎ በ https://bit.ly/3rl8vwn ላይ ይመዝገቡ ወይም በድህረ ገጽ www.HaqCheck.org ላይ በመግባት  ሰብስክራይብ ማድረግ ይችላሉ።

✍️ ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇
TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2
ከአማራ ብሔር ተወላጆች እስር ጋር ተያይዞ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ፣ የክርስቲያን ታደለ ከእስር እንደተለቀቀ ያሳያል ተብሎ የወጣው ቪድዮ ፣ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በፋኖ መሳርያ እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል ስለሚለው ቪድዮ፣ የህዳሴ ግድብ አራተኛ ሙሌትን ተከትሎ የተፈጠሩት አወዛጋቢ መረጃዎች እና በቆዩ ምስሎች ላይ አርትዖት በመስራት ዙሪያ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል በዛሬው ከውሸቱ ባሻገር ፕሮግራማችን ይዘንላችሁ ቀርበናል ይከታተሉን👇

https://youtu.be/kfibXxTYQY8?si=q9bmK6-4Nh3msbAJ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አቶ ክርስትያን ታደለ ከእስር ተፈቷል?

ሙሉ ቪድዮውን ይመልከቱ https://ytube.io/3kG5

✍️ ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇
TikTok|Facebook|website|Twitter
👍3👌1
የባለፈው ሳምንት ዳሰሳ
    ...........

1: ምስሉ የኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎች በሶማሌ መንደሮች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ አያሳይም

ከሰሞኑ አንድ የትዊተር አካውንት "በኦሮሚያ ክልል መንግስት ድጋፍ የታጠቁ የኦሮሞ ታጣቂዎች በጅጅጋ አቅራቢያ በሚገኘው ትልቁ የሶማሌ ስደተኞች ካምፕ ቆላጂ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ከሚገልጽ  ጹሑፍ ጋር ሁለት ፎቶዎችን በማያያዝ አጋርቶ ነበር። " ፖስቱ ከ 294 ጊዜ በላይ የተጋራ ሲሆን ከ428 በላይ ግብረ መልሶችን አግኝቷል።

ከሰሞኑ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ድንበር አካባቢ ያለውን ግጭት ተከትሎ በማህበራዊ ሚድያ ላይ የተለያዩ መረጃዎች እየተጋሩ ነው። ከነዚህም ውስጥ በመግቢያ ላይ የጠቀስነው የቲውተር መረጃ ይገኝበታል።

ሀቅቼክ  እንዳጣራው መርጃውን ለመደገፍ የተጠቀመው ምስል የቆየና አንደኛው ፎቶ መጀመሪያ ላይ የተለጠፈው እ.ኤ.አ. ነሃሴ 19, 2019 በዛው አካባቢ ያለ ሁኔታን በሚገልጽ ጹሑፍ ስር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በግንቦት 27, 2018 በካልፎርኒያ የተከሰተ ሰደድ እሳትን ተከትሎ የተጋራ ምስል እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል። ስለዚህ ይህ መረጃ ሃሰተኛ ነው።

2: ቪድዮው በአማራ ክልል በመከላከያ የተፈጸመን ድብደባ አያሳይም

ሌላው ከሰሞኑ በአማራ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በትዊተር ላይ "የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ሰዎችን እየደበድቡ  እንደሆነ ከሚገልጽ ጹሑፍ ጋር ሲዘዋወር ነበር"። ቪድዮው ከ 379 በላይ ሲጋራ ከ 329 በላይ ግብረ መልስ አግኝቷል፣ 

ነገር ግን ቪድዮው ከሰሞኑ በአማራ ክልል እንደተፈጸመ አያሳይም። ቪድዮው መጀመሪያ ከሁለት አመት በፊት "መከላከያ በትግራይ ክልል ሰዎችን እየደበደበ እንደሆነ ከሚገልጽ ጹሑፍ ጋር ተጋርቶ እንደነበር ያሳያል። ስለዚህ መረጃው ሃሰተኛ ነው።

ሙሉ መርጃውን በዚህ ሊንክ ያንብቡ
👍4🙏1
ሃሰተኛ መረጃን ከመከላከል አንጻር የኢትዮጵያ መንግስት መስሪያ ቤቶች ምላሽ ሰጪነት በሚል ርዕስ አንድ አዲስ ጥናት ከሰሞኑ ለህትመት በቅቷል። ጥናቱን ያደረጉት ድርጅታችን ኢንፎርም አፍሪካ  እና ሚዳን የተባለ አለም አቀፍ  ተቋም በጋራ በመሆን ነው።

በጥናቱም የኢትዮጵያ መንግስት 🔍📰 ለመገናኛ ብዙኃን በቂ  መረጃ አለመስጠቱ፣ ወቅታዊ መግለጫዎችን በሰዓቱ አለመስጠቱ እና ከመንግስት ጋር ግንኙነት ላላቸው ሚዲያዎች ያለው አድልአዊ የመረጃ አቅርቦት ትክክለኛ የመረጃ ፍሰት እንዳይኖር በማድረግ የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንደዳባባሰ ያሳያል። 📉🔥

ጥናቱ መንግስት ማዕከላዊ የመረጃ ስርዓት ሊኖረው እንደሚገባ፣ ንቁ የማህበራዊ ሚዲያ ተሳትፎ ማድርግ እንዳለበት፣ መደበኛ የፕሬስ መግለጫዎች መስጠት እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ወቅታዊ መረጃዎችን በግልጽ ለሚዲያ በመስጠት የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመከላከል ዙሪያ አውንታዊ አስተዋጽኦ ሊኖርው እንደሚችል ይጠቁማል💬👥

ሙሉውን የጥናት ጹሑፍ በዚህ ሊንክ ያንብቡ፡ https://bit.ly/46w9Z5E
🙏5🔥1
#የሀሰተኛ_መረጃ_ጥቆማ❗️

ከሰሞኑ በአቢሲንያ ባንክ ስም በተከፈተ የቲክቶክ አካውንት ለአሸናፊዎች የ10,000 ብር የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትበት ነው በሚል ላይክ ያደረጉና ኮፒሊንክ ያደረጉ ሰዎች እጩ የሚሆኑበት ‘10 ሺ ቻሌንጅ’ በሚል ስያሜ ያገኘ ቪድዮ በስፋት ሲጋራ ነበር።

ይህ አካውንት ባለቤትነቱ የአቢሲንያ ባንክ ያልሆነና ባንኩ ይህ ጽሁፍ እስከታተመበት ጊዜ ድረስ ይፋዊ ቴሌግራም፤ ፌስቡክ፤ ኤክስና (ትዊተር) ሊንክዲን አካውንቶችን ብቻ ለማህበራዊ ሚድያ ተደራሸነት እንደሚጠቀም ከባንኩ ከተገኘ መረጃ ለማረጋገጥ ተችሏል። ‘10 ሺ ቻሌንጅ’ በሚል የቀረበውም የይሳተፉ ይሸለሙ ጥሪ ሀሰትና ከባንኩ እውቅና ውጭ መሆኑ ተረጋግጧል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተስፋፉ የመጡት እንደዚህ አይነት ማጭበርበሪያ መንገዶች የታዋቂ ሰዎች ስምና የድርጅቶች ስያሜዎች በመጠቀም የአካውንቱን ተከታዮች በማብዛት አካውንቱን በገበያ ላይ ለማዋል የሚጠቀሙበት መንገድ ነው። ስለሆነም ማህበረሰቡ ይፋዊ የሆኑ ገጾችን ብቻ በመከተል ይህንን ከሚመስሉ የማጭበርበሪያ ዘዴዎች ራሱን መጠበቅ አለበት።
👍5🙏1👌1
#የሀሰተኛ_መረጃ_ጥቆማ

ከሰሞኑ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስም የተከፈተ የቴሌግራም ቦት ለአሸናፊዎች የ3000 ብር የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትበት ነው በሚል ቻናሉን ለተቀላቀሉና ለሌሎች ያጋሩ ሰዎች የሚሸለሙበት ነው በማለት በስፋት ተጋርቷል።

ይህ አካውንት ባለቤትነቱ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እንዳልሆነ ሀቅቼክ አረጋግጧል። የኩባንያው የቴሌግራም አካውንት በድህረገጹ ላይ የተጠቀሰ እና በአሁኑ ወቅት ከ22 ሺህ በላይ ተከታዮች ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።

ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ በሚል የቀረበውም የይጋብዙ ይሸለሙ ጥሪ ሀሰትና ከኩባንያው እውቅና ውጭ መሆኑ ተረጋግጧል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በይበልጥ እየተስፋፉ የመጣው የማጭበርበሪያ መንገድ የአካውንቱን ተከታዮች በማብዛት አካውንቱን በገበያ ላይ ለማዋል የታዋቂ ሰዎች ስምና የድርጅቶች ስያሜዎች በመጠቀም የሚደረግ ነው።

ስለሆነም የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ይፋዊ የሆኑ ገጾችን ብቻ በመከተል ይህንን ከሚመስሉ የማጭበርበሪያ ዘዴዎች ራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው።
👍3🔥1🙏1
በማህበረዊ ሚድያ ላይ በምስል የተደገፉ መረጃዎች ሲያጋጥሙን ማድረግ ያሉብን ነገሮች:

በምስሉ ላይ የሚታዩ ፅሁፎች ካሉ የተጻፉበት ቋንቋ ምን እንደሆነ እና ምልክቶችም ካሉ ምንነታቸውን ማየትና መለየት

ሰንደቅ አላማ፣ አርማ ወይም ሌሎች ማንነት ገለጫ ነገሮችን በምስሉ ውስጥ መፈለግ

የመኪና ታርጋዎች፣ መንገዶች እና የመንገድ ምልክቶችን ማስተዋል

ህንጻዎችን፣ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ እና አከባቢውን መቃኘት

እነዚህን ከላይ የጠቀስናቸውን በመመልከት ስለ ምስሉ ፍንጭ ሰጪ መረጃዎችን ልናገኝ እንችላለን፣ በተጨማሪም የምስል መመርመሪያ መሳሪያዎች ስላሉ እንሱን መጠቀም ይኖርብናል።
👍4🙏1