HaqCheck
429 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
ሳምንታዊ ዳሰሳ

በአማራ ክልል በመንግስትና በአካባቢው ባሉ ታጣቂዎች መካክል ያለው ግጭት እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ ብዙ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ሲዘዋወሩ ከርመዋል።

ከእነዚህ መረጃዎች ውስጥ አንዳዶቹ የቆዩ ምስልና ቪዲዮዎችን እንደ አዲስ በማስመሰል የተጋሩ ናቸው። 

በሳምንቱ የነበረውን የሃሰተኛ መረጃ ሁኔታ ሙሉውን ያንብቡ:https://haqcheck.org/august-week-one-summary/?amp=1
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሃሰተኛ ዜናዎችን የምንለይባቸው መንገዶች


✍️ ምንጩን ማረጋጋጥ: በሚድያ ላይ የምናገኘውን ማንኛውንም ዜና ከማመንናችን በፊት ዜናው በማን እንደተዘጋጀ ማወቅ ይኖርብናል፣ ታዋቂ የዜና ድርጅት ነው ወይስ ያልተረጋገጠ ግለሰብ ወይም ቡድን?

✍️ በሌሎች ሚድያዎች መዘገቡን ማረጋጥ፡ መረጃውን ከብዙ ታማኝ የዜና ምንጮች ጋር ያረጋግጡ። መረጃው በአንድ ሚድያ ላይ ብቻ የሚገኝ ከሆነ እና ሌላ ቦታ ከሌለ፣ ሐሰት ሊሆን ይችላል።

✍️ ቀኑን እና ዝርዝር መረጃውን መመርመር፡ የተሳሳተ መረጃ ብዙውን ጊዜ የተሳሳቱ ቀኖች ወይም የተቀየሩ ዝርዝሮችን ይይዛል። እነዚህን ነገሮች በጥንቃቄ ይፈትሹ

✍️ አድሏዊ አለመሆኑን ያረጋግጡ፡ ለአንድ ቡድን ወይም ግለሰብ የሚጠቅም ዜና ከሆነ ምናልባት የተዛባ ወይም ሐሰት ሊሆን ይችላል። ሁልጊዜ ገለልተኝነታቸውን ከሚጠብቁ ምንጮች ዜና ይፈልጉ።

✍️ የመረጃ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ይጠቀሙ፡ የውሸት ዜናዎችን ለመለየት የሚረዱ ብዙ መመርመሪያ መሳሪያዎች ስላሉ እነሱን መጠቀም።

መረጃውን ከማጋራት በፊት ጊዜ ወስዶ ማረጋገጥ ምንጊዜም ቢሆን የተሻለ ነው። የውሸት ዜናዎችን ማሰራጨት ከባድ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2🔥1
#Alert❗️

ከሰሞኑ በአማራ ክልል በፌደራል መንግስት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንዳለ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ ከ190ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ 'የኢትዮጵያ መንግስት በደብረብርሃን ከተማ ላይ ባደረገው የድሮን ጥቃት ከመቶ በላይ ሰዎች እንደተገደሉ' የሚገልፅ ፅሁፍን በማያያዝ አምስት ምስሎችን አጋርቶ ነበር።

ሀቅቼክ መረጃውን ለመደገፍ የቀረቡትን ምስሎች እንዳጣራው ሁለቱ ምስሎች ከሁለት አመት በፊት  በአጣዬ እና አካባቢው ከነበሩት ግጭቶች ጋር የተያያዙ ሲሆኑ አንደኛው ምስል ደግሞ በፈረንጆቹ 2015 የሩሲያ የአየር ሀይል ከአሜሪካ አየር ሀይል ጋር በመቀናጀት በሶሪያ ኮባኒ ያደረሱትን የአየር ጥቃት እንደሚያሳይ ማረጋገጥ ተችሏል። የተቀሩት ሁለቱ ምስሎች በአማራ ክልል ካለው ግጭት ይገናኙ አይገናኙ ማረጋገጥ አልተቻለም።

በማህበራዊ ሚድያ ላይ መሰል ይዘት ያላቸው መረጃዎች እየተጋሩ ስለሆነ መረጃዎችን በጥንቃቄ መመልከት አስፈላጊ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
ከውሸቱ ባሻገር/ Beyond disinfo.

📢 በሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ፣ በንግግር ነፃነት እና በቴክኖሎጂ ላይ የሚያጠነጥን አዲስ ፕሮግራም

ሐሙስ ከምሽቱ 12:30 ላይ ይጠብቁን👇

https://youtube.com/c/AddisZeybe
👍2👌1
ሀሰት : ይህ ምስል አሁን በአማራ ክልል ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ በአማራ ክልል በታጣቂዎች የተማረኩ የጦር መሳሪያዎችን አያሳይም

ይህ በግራ በኩል የምትመለከቱት ምስል በፋኖ አማካኝነት ከመከላከያ የተማረኩ መሳሪያዎች በሚል የመግለጫ ፅሁፍ ስር በማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት ሲዘዋወር ቆይቷል።

ነገር ግን ሀቅቼክ ምስሉን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ምስሉን ከሁለት አመት በፊት በፈረንጆቹ 2021 ላይ ጎልጉል የሚል ስያሜ ባለው ድረገጽ ወስጥ "ባጠናቀቅነው ነሀሴ ወር በቁጥጥር ስር የዋሉ የጦር መሳሪያዎች"  በሚል ፅሁፍ ስር ተጋርቶ አግኝቶታል።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
በአማራ ክልል በነበረው ግጭት በፋኖ ታጣቂዎች የተማረከ የኢትዮጵያ መከላከያ  እንደሆነ የሚያሳይ ምስል ሰሞኑን በፌስቡክ በስፋት ሲሰራጭ ነበር።  ሀቅቼክ እንዳጣራው መረጃውን ለመደገፍ የቀረበው ምስል  ሃሰተኛ መሆኑን አረጋግጣል።

ሙሉውን ያንብቡ👇

https://bityl.co/KOKO
👍1
#የሀሰተኛ_መረጃ_ጥቆማ

ከሰሞኑ በአማራ ክልል ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ ዘመነ ካሴ በቁጥጥር ስር ውሏል የሚሉ የተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ መረጃዎችን ተመልክተናል።

ለምሳሌ ያክል ከ62ሺህ በላይ ተከታይ ያለው አንድ የፌስቡክ ገፅ “ሰበር ዜና ዘመነ ካሴ ሀትሪክ ሰራ!!! ለሦስተኛ ጊዜ በቁጥጥር ስር ውሏል” የሚል የመግለጫ ፅሁፍን በመጠቀም ይህን ምስል አጋርቷል።

ሀቅቼክ የምስሉን ወቅታዊነት ለማረጋገጥ ባደረገው ጥረት በመስከረም ወር 2015 ዓ.ም ዘመነ ካሴ ባህርዳር ላይ በክልሉ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲውል ከተነሱት ምስሎች ውስጥ ተጋርቶ አግኝቶታል።

በዚህም ምክንያት ዘመነ ካሴ በቁጥጥር ስር ስለመዋሉ የሚናገሩ የማህበራዊ ሚድያ ፖስቶች ቢኖሩም ይህ ምስል ግን የቆየ መሆኑ ተረጋግጧል።
መልካም  ዜና

በሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ፣ በንግግር ነፃነት እና በቴክኖሎጂ ላይ የሚያጠነጥነው  አዲሱ ፕሮግራም፣  ከውሸቱ ባሻገር  በአዲስ ዘይቤ ዩቲዩብ ቻናል  ዛሬ ሐሙስ ማቅረብ እንደምንጀምር መግለፃችን ይታወቃል። ነገር ግን ፕሮግራሙን  ለብዙኃኑ ተደራሽ እንዲሆን በማሰብ  ከሀገሬ ቲቪ ጋር በመስማማታችን በዚህ ሳምንት አይኖረንም፡፡ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በቴለቪዠን መስኮት በሀገሬ ቲቪ እና በዩቱብ መተላለፍ እንደሚጀምር እንገልፃለን፡፡

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መረጃን ማጣራት መቻል ፣ ትክክኛ እና ሃሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም የመረጃ ምንጮችን በቀላሉ እንድንለይ ያስችለናል። በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ሰው በእያንዳንዱ ርዕስ ላይ የመሰለውን የሚናገርበትና የሚጽፍበት በመሆኑ መረጃን ማጣራት ቀላል ስራ አይደለም።

መረጃን ማጣራት የሚያስገኘው ጥቅም

✍️ የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎትን ያሳድጋል፡
✍️ አድሏዊ ግንዛቤን ይቀንሳል
✍️ ብስለታዊ አስተሳሰብን ያዳብራል
✍️ የተሻለ ጸሐፊ እንዲሆኑ ያግዝዎታል


ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
1👍1
#Alert

ከ30 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ ከላይ ያልውን ምስል በመጠቀም "የፋኖ ታጥቂዎች በሰሜን ወሎ የደላንታ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን ወገልጤና ከተማን ጨምሮ ሙሉ ወረዳውን እንደገና ተቆጣጠረዋል የሚል መረጃ አሰራጭቶ ነበር።"

ይሁን እንጂ ምስሉ ከአንድ ወር በፊት ሰኔ ላይ በማህበራዊ መገናኛ ተሰራጭቶ የነበረ ነው። በወቅቱም አዲስ ማለዳ የተባለ የሚድያ ተቋም ምስሉ በድህረገጹ ላይ "በደላንታ ወረዳ የስምንት ዓመት ሕጻን ልጅ መደፈሯን ተከትሎ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉን" ከሚገልጽ ዜና ጋር አጋርቶት ነበር።
👍2🔥1🙏1
#የሀሰተኛ_መረጃ_ጥቆማ

ከ11ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ "የኦህዴድ ወራሪው ሀይል መሬት ተንሸራቶ በርካቶች ሲሞቱ ከፊሎቹ ቆሰሉ። በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሰፍሮ የነበረው የብልጽግና ሰራዊት ወደ አማራ ክልል ሲጓጓዝ ካራ ተብላ በምትጠራ ቦታ ሲደርስ መሬቱ ከታች በምትመላከቱት መልኩ ተንሸራቶ በርካቶች የሞቱ ሲሆን ከፊሎቹ ስለመቁሰላቸዉ ከቦታው መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።"

የሚል የመግለጫ ፅሁፍ በማያያዝ ይህን ምስል አጋርቶ ነበር። ሀቅቼክ የምስሉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ባደረገው ጥረት ምስሉን ነሀሴ 2 ፤ 2015 ዓ.ም Paukphaw.org በተሰኘ ድረገጽ ላይ ተጋርቶ አግኝቶታል።

የተጋራው ዜና በኤዠያ ውስጥ የሚገኝ እና ከከባድ ዝናብ የተነሳ የፈረሰ መንገድን እንደሚያሳይ ሀቅቼክ ማረጋገጥ ችሏል።

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2
በአማራ ክልል ያለውን ግጭት ተከትሎ ብዛት ያላቸው መረጃዎች በማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት እየተሰራጩ ነው። አንዳንዶቹ የቆዩና የሌላ ጊዜ ምስልና ቪድዮችን፣ የቅርብ እና አሁን ባለው ውቅታዊ ሁኔታ የተፈጠሩ በማስመሰል እያጋሩ ይገኛሉ።

ከሰሞኑ በፍኖተ ሰላም መንግስት በወሰደው የድሮን ጥቃት ሰዎች እንደተገደሉ የሚያሳዩ የተለያዩ መረጃዎች በማህበራዊ ሚድያ እና በአንዳንድ ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት እየተገለጹ ነው።

ይህን ተከትሎ ከ 40ሺ በላይ ተከታይ ያሉት የፌስቡክ ገፅ በፍኖተ ሰላም መንግስት በወሰደው የድሮን ጥቃት 270 ንጹሃን ዜጎች፣ ህጻናትን ጨምሮ እንደሞቱ የሚገልጽ ጹሑፍ እና ምስል ለጥፎ በስፋት ሲዘዋወር ነበር።

ሀቅቼክ እንዳጣራው መርጃውን ለመደገፍ የተጠቀሙበት ምስል የቆየና ከአሁን በፊት በሌላ ፌስቡክ ግጽ ተለጥፎ የነበረ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል።

ሙሉውን ያንብቡ 👇👇👇
https://bityl.co/KV64
በማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚያጋጥሙህን/ሽን ምስሎች ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የምስል ማረጋገጫ መሳሪያዎችን ተጠቅመህ/ሽ ታውቃለህ/ቂያለሽ?
Anonymous Poll
13%
አዎ ሁል ጊዜ
23%
አዎ አልፎ አልፎ
20%
አይ ስለ ምስል ማረጋገጫ መሳርያዎች ምንም አላውቅም
43%
አላውቅም ግን ስለ ምስል ማረጋገጫ መሳሪያዎች መማር እፈልጋለሁ
በአማራ ክልል ያለውን የትጥቅ ግጭት ተከትሎ
ከ46 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ "በታንክ ታጅቦ የመጣ ሃይል በሞጣ ፋኖ ዶግ አመድ ተደርጓል" በሚል የመግለጫ ጹሑፍ ስር የምትመለከቱትን ምስል ለጥፎ ፣ ብዙ ግብረ መልሶችንም አግኝቷል።

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ የኢትዮጵያ ወታደሮች እና ታንኮች መመታታቸውንም ልጥፉ አክሎ ገልጿል።

የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ  ሃይሎችን ለመበተን መወሰኑን በመቃወም የተጀመረው አለመግባባት በአማራ ክልል ከሰሞኑ ብዙ ሂወትን የቀጠፈ ግጭትን አስከስትሏል።

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ በሰው አልባ አውሮፕላን በደረሰ ጥቃት 26 ሰዎች መሞታቸውን በቅርቡ እየወጡ ያሉ ዜናዎች ያሳያሉ።

ሀቅቼክ መረጃውን ለመደገፍ የተጠቀሙበትን  ምስል እንዳጣራው ምስሉ ቀደም ሲል  በትዊተር ላይ በነሐሴ 8 ቀን 2022  'የሩስያ ጦር በቅርቡ ባደረገው ጦርነት የዩክሬን መድፍ ተሽከርካሪዎችን እንዳወደመ' ከሚገልጽ የመግለጫ ጽሁፍ ጋር የተጋራ እንደነበር ማረጋገጥ ተችሏል።

መሉውን ጹሑፍ ለማንበብ https://tinyurl.com/3yzw5cbt
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሀቅቼክ በቲክቶክ ላይ “አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ አሁን ሀገሪቱ ያለችበትን ችግር ቀድሞ ተንብዮ ነበር።” በሚል መግለጫ ስር ተጋርቶ የነበረን አንድ ቪድዮ አጣርቷል።

ቪድዮውን ይመልከቱ 👆🏻

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🎉 መልካም  ዜና

ከውሸቱ ባሻገር/ Beyond disinfo የተሰኘ አዲስ ፕሮግራም ይዘን መጥተናል

ፕሮግራሙ በሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ፣ በንግግር ነፃነት እና በቴክኖሎጂ ላይ የሚያጠነጥን ነው።

ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 1: 30 ላይ በሀገሬ ቲቪ ይጠብቁን📺
1👏1
በማህበራዊ ሚድያ ላይ ያገኘነውን መረጃ ከመማመናችን በፊት ልንጠይቃቸው የሚግቡ 5 ጥያቄዎች

ምንጩ ማን ነው? 🕵️‍♂️
    የመረጃው ምንጭ ተአማኒነት እና በመረጃው ላይ ያለውን እውቀት መለየት ያስፈልጋል። እምነት የሚጣልበት ነው? አድልዎ ወይም ሌላ አጀንዳ የለውም?

ምን ማስረጃ ቀርቧል? 📚
   የቀረበውን መረጃ  የሚያረጋግጡ ደጋፊ ማስረጃዎችን ወይም ማጣቀሻዎችን ማካተቱን ልብ ይበሉ።

መረጃው ወቅታዊ ነው?
    መረጃው የታተመበት ወይም የተለጠፈብትን ቀን ያረጋግጡ።

መረጃው አማራጭ እይታዎች አሉት ? 🔄
  መረጃው በተለያዩ አመለካከቶች ወይም እይታዎች ምን እንድሚመስል መገምገም ያስፈልጋል።

መረጃው ከታማኝ ምንጮች ጋር ይጣጣማል?
መረጃውን ከሚያምኗቸው ታዋቂ ምንጮች ጋር ያገናዝቡ። በአስተማማኝ ምንጮች ላይ መረጃው መሰራጨቱን ያረጋግጡ።

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2👌1
በመንግስትና በአማራ ክልል በሚገኙ ታጣቂዎች መካክል ያለውን ግጭት ተከትሎ ፣ በማህበራዊ ሚድያ ላይ ብዙ መረጃዎች እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።

ከሰሞኑ ይህን የምትመለከቱትን ምስል የፋኖ ታጣቂዎች የመንግስትን ሄሊኮፕተር መተው እንደጣሉና ጉዳት እንዳደረሱ ከሚገልጽ ጹሑፍ ጋር በፌስቡክ በስፋት ሲዘዋወር ነበር።

ነገር ግን ሀቅቼክ የመረጃውን እውነትነት እንዳጣራው፣ መረጃውን ለመደገፍ የተጠቀሙት  ምስል በፈረንጆቹ 2022 የሮማንያ ሄሊኮፕተር ስትከሰከስ ከሚያሳይ የጹሑፍ መግለጫ ጋር ተጋርቶ አግኝቶታል።

ሙሉ ጹሑፉን ለማንበብ 👇

ሙሉውን ያንብቡ http://bit.ly/3OJYIYl

TikTok|Facebook|website|Twitter
በአሁኑ ሰዓት የጥላቻ ንግግርን በዋናነት በመፍጠር ወይም መጀመርያ በመናገር ወደ ማህበረሰቡ ማስረጽ የሚፈልግ አካል ማን ነው ብለው ያስባሉ?
Anonymous Poll
5%
የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች
22%
ግለሰቦች
24%
የማህበረሰብ አንቂዎች
49%
የመንግስት ባለስልጣኖች
ኢንተርኔትን በሐላፊነት የሚጠቀሙ  ሰዎች

🤝  አካታች ናቸው
በኦንላየን ላይ ከሌሎች ጋር የአክብሮት እና ጥሩ ስሜት ያለው ግንኙነት ያላቸው ናቸው።

ℹ️  አገናዛቢ ናቸው
የኦንላይን መረጃዎችን ትክክለኛነት፣ እና እርግጠኛነት  መገምገም የሚችሉ ናቸው።

🧑‍💻 ቴክኖሎጂን ለበጎ አላማ ያውላሉ
ቴክኖሎጂን ለዜጎች ጠቃሚ ለሆኑ ነገሮች የሚጠቀሙ ናቸው።

ሚዛናዊ ናቸው
በኢንተርኔት ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜና በሌላው የህይወታቸው እንቅስቃሴ ላይ የተመጣጠነ ጊዜን ያሳልፋሉ

⚠️ ንቁ ናቸው
የኦንላይን እንቅስቃሴ ደህንነታቸውን ይጠብቃሉ እንዲሁም ለሌሎች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2🙏1
ቢጣራ የሚሉትን መረጃ ይላኩልን

🔊 በማህበራዊ ሚዲያ፣ በተለያዩ ጽሁፎች፣ በቪዲዮዎች እና በዜና ዘገባዎች ላይ ያገኛችሁት መረጃ እውነት መሆኑ ካጠራጠራችሁ፣ ጥያቄ ከፈጠረባችሁ፣ ወደ ሀቅቼክ መረጃውን ያገኙበትን ምንጭ አያይዘው ይላኩልን። የመረጃውን እውነትነት አጣርተን መልሰን ለእናንተው እናቀርባለን።

መረጃ ለመላክ:-
   በቴሌግራም: @haqcheckbot ላይ ገብተው መላክ ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍1👌1