HaqCheck
429 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
አብዛኛውን ጊዜዎን በየትኛው ማህበራዊ ሚድያ ላይ ያሳልፋሉ
Anonymous Poll
50%
በፌስቡክ
31%
በቴሌግራም
9%
በቲክቶክ
9%
በሌሎች(እባክዎ ይጥቀሱ)
👍1
"የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ዓለም አቀፍ ተግዳሮት ነው፣ ያንን ተግዳሮት ለመግታት እንደ ማህበረሰብ  የራሳችንን አቅም ማጎልበት ይኖርብናል፣ የኛ ድርጅት ኢንፎርም አፍሪካ ይህንን ሀገር በቀል አቅም ለመፍጠር ነው እየሞከረ ያለው"

የኢንፎርም አፍሪካ ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር አቤል ዋበላ ከአራዳ ኤፍ ኤም ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ

ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ለመስማት👇

https://ytube.io/3hZa
👍1
✍️ አሁን አሁን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሰዎችን ቀልብ ለመሳብና ብዙ ተመልካች ለማግኘት ሲባል ሳቢ አርዕስት በመስጠት ተጋነው የሚቀርቡ ልጥፎችን በስፋት እናያለን።

✍️ በዚህ ሁኔታ የሚቀርቡ መረጃዎች ሁሉም ትክክለኛ አይደሉም። በተለይም ነባራዊና ወቅታዊ  ሁኔታን ተንተርሰው የሚለቀቁ መረጃዎች ከላይ ሳቢ ይሆኑና ውስጥ ላይ ገብተን ስናያቸው ከርዕሱ ጋር የማይገናኙ ሆነው ልናገኛቸው እንችላለን።

✍️ ስለዚህ እንደነዚህ አይነት መረጃ ሲያጋጥመን መረጃውን አምነን ከመቀበላችን በፊት ሙሉ መረጃውን መስማት ወይም ማንበብ፣ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ እና እውነት መሆኑን ሳናጣራ ለሌሎች አለማጋርት ይኖርብናል።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2🙏1👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እውነታን ማጣራት የጋዜጠኞች ወይም የሀቅ አጣሪ ተቋማት ብቻ ኃላፊነት አይደለም፣ ይልቁንም ስለ እውነት የምንጨነቅ ይሁላችን ሐላፊነት ነው። ይህ የሚጀምረው እርግጠኛ ያልሆነውን መረጃ ለሌሎች ካለማጋርትና ያገኘነውን መረጃ ከአድሏዊ አመለካከት በጸዳ መልኩ ማረጋገጥ ከመቻል ነው።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍3🙏1
በአማራ ክልል ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚድያ በተለይም በፌስቡክና በቲክቶክ ላይ ብዙ መረጃዎች እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።

ከሰሞኑ ይህ የምትመለከቱት  ምስል ከ90 ሺ በላይ ተከታይ ባለው የፌስቡክ ገጽ እና በሌሎችም ላይ “በሸዋ ይፋት ፋኖን ትጥቅ አስጥላለው ብሎ የገባው ሀይል ትጥቁን እየጣለ አምልጧል” ከሚል ጹሑፍ ጋር ተለጥፎ በስፋት ሲዘዋወር ነበር:-

ሀቅቼክ እንዳጣራው፣ ምስሉ ከስድስት ወር በፊት ሩዋንዳ ትሪቡን በሚል ድረ-ገፅ እንዲሁም በትዊተር ላይ ተጋርቶ አግኝቶታል።

የተጋራው መረጃም March 23 ወይም በቅፅል ስማቸው (M23) የተሰኙት የኮንጎለስ ረቮሉሽነሪ አርሚ ወታደሮች በኮንጎ ውስጥ ከሚቀሳቀሱ ከመንግስተና መንግስትን ከሚደግፉ ሌሎች ታጣቂ ሀይሎች ላይ የማረኳቸው መሳሪያዎች እንደሆኑ ማረጋገጥ ተችሏል። ምስሉም ተቆርጦ እንደተወሰድ ማየት ይቻላል።

ሙሉውን ለማንበብ 👉https://rb.gy/d9cvx
👍2
ከማጋራትዎ በፊት ወቅታዊ መረጃ መሆኑን ያረጋግጡ

🎤 በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሃሰተኛ መረጃዎችን ከምንለይባቸው መንገዶች አንደኛው ዘዴ ልጥፉ መጀመሪያ መቼ እንደተለጠፈ ወይም እንደተጻፈ በመለየት ነው፣

🎤 መረጃው ወቅታዊ እና ጠቃሚ መሆኑን ሁልጊዜ ማረጋገጥ ይኖርብናል። ሃሰተኛ መረጃን የሚያሰራጩ አካላት የሚጠቀሙት አንደኛው ስልት ወቅታዊ ያልሆነን ወይም ቀደም ብለው ተለጥፈው የነበሩ መረጃዎችን እንደ አዲስ በማጋራት አሁናዊ መረጃ ማስመሰል ነው።

🎤 ለምሳሌ የምትመለከቱት ምስል ላይ በአዲስ ዘይቤ የትዊተር አካውንት ላይ በሚያዝያ ወር (07 April) ተለጥፎ የነበረውን ምስልና ጹሑፍ ፣ በአማራ ክልል ያለውን አሁናዊ ግጭት እንዳጋጣሚ በመጠቀም በዚህ ሰሞን የተከሰተና ልጥፉም የቅርብ እንደሆነ በማስመሰል በተለያዩ የቲውተር አካውንቶች ላይ እየተጋራ ነው።

🎤 ነገር ግን አስተውለን ካየነው ያጋሩት ልጥፍ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መቼ እንደተለጠፈ ያሳያል ማለትም ምስሉ   07 April ላይ እንደነበር ያሳያል። ነገር ግን መረጃውን አንዱ ዛሬ ከ 4 ሰዓት በፊት እንደተጋራ ሲያሳይ ሌላው ደግሞ ከ አንድ ቀን በፊት እንደተጋራ ያሳያል።

🎤 ስለዚህ የተጋሩ መረጃዎችን ስንመለከት በቀላሉ መረጃዎቹ መጀመሪያ መቼ እንደተለጠፉ በማየት የመረጃውን ውቅታዊነት መለየት እንችላለን።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍1👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት አስፈላጊ የሆነበት ሦስት ምክንያት

✍️ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመወሰን፡-

የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ያለው ሰው ብስለታዊ አስተሳሰብን (critical thinking) ያዳብራል፣ ይህም ሰዎች የመገናኛ ብዙሃን መልዕክቶችን እንዲተነትኑ እና እንዲተረጉሙ ያስችላቸዋል።

✍️ የተዛቡ መረጃዎችን ለመለየት፡-

የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ግለሰቦች ታማኝ የሆኑ የመረጃ ምንጮችን ታማኝ ካልሆኑት በቀላሉ የሚለዩበት ክህሎት እንዲኖራቸው ያደርጋል፣ ይህም ሃሰተኛ መረጃዎችን በቀላሉ መለየት ያስችለዋል።

✍️ ንቁ ዜጋ ለመሆን፡-

ሚዲያን መረዳት የሚችሉ ሰዎች በማህበራዊ ውይይቶች እና በዴሞክራሲያዊ ሂደቶች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2🔥1
በኦንላይን ላይ በቀላሉ ገንዘብ መስራት የሚቻል ይምስሎታል?

አሁን አሁን በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ አምራጮች ላይ በኦንላይን ስራ በመስራት በቀላሉ ጥሩ የሚባል ገንዘብ እንደሚገኝ የሚገልጹ  ማስታወቂያዎችን በስፋት እናያለን። እንደነዚህ አይነት የማህበራዊ ሚድያ ልጥፎች አብዛኞቹ ተመልካቹን ወደ ቴሌግራም ግሩፕ እንዲቀላቀሉ ነው የሚጋበዙት።

ሙያዊ (professional) የሆኑ እና በኦንላይን የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ የታወቀ ነው። ይሁን እንጂ በኛ ሀገር የሚለጠፉት አብዛኞቹ ስራውን ለመስራት ምንም አይነት መስፈርት እንደሌለው እና ማንኛውም ሰው ሰርቶ ጥሩ ገንዘብ ማግኘት እንደሚችል የሚገልጹ ናቸው።

ለዛሬ ሃሳባችሁን እንድታካፍሉን የፈለግነው

፩: በኢትዮጵያ በኦንላይን በቀላሉ ገንዘብ የሚያስገኝና ሙያ የማይጠይቅ ስራ አለ ብለው ያስባሉ?

፪: ከላይ እንጠቀስነው በእንደዚህ አይነት ማስታወቂያዎች ስራ ሰርታችሁ ሳትደክሙ ገንዘብ ያገኛሁበት አጋጣሚ አለ? የተሸወዳችሁበትስ?

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2🔥1
ሳምንታዊ ዳሰሳ

በአማራ ክልል በመንግስትና በአካባቢው ባሉ ታጣቂዎች መካክል ያለው ግጭት እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ ብዙ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ሲዘዋወሩ ከርመዋል።

ከእነዚህ መረጃዎች ውስጥ አንዳዶቹ የቆዩ ምስልና ቪዲዮዎችን እንደ አዲስ በማስመሰል የተጋሩ ናቸው። 

በሳምንቱ የነበረውን የሃሰተኛ መረጃ ሁኔታ ሙሉውን ያንብቡ:https://haqcheck.org/august-week-one-summary/?amp=1
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሃሰተኛ ዜናዎችን የምንለይባቸው መንገዶች


✍️ ምንጩን ማረጋጋጥ: በሚድያ ላይ የምናገኘውን ማንኛውንም ዜና ከማመንናችን በፊት ዜናው በማን እንደተዘጋጀ ማወቅ ይኖርብናል፣ ታዋቂ የዜና ድርጅት ነው ወይስ ያልተረጋገጠ ግለሰብ ወይም ቡድን?

✍️ በሌሎች ሚድያዎች መዘገቡን ማረጋጥ፡ መረጃውን ከብዙ ታማኝ የዜና ምንጮች ጋር ያረጋግጡ። መረጃው በአንድ ሚድያ ላይ ብቻ የሚገኝ ከሆነ እና ሌላ ቦታ ከሌለ፣ ሐሰት ሊሆን ይችላል።

✍️ ቀኑን እና ዝርዝር መረጃውን መመርመር፡ የተሳሳተ መረጃ ብዙውን ጊዜ የተሳሳቱ ቀኖች ወይም የተቀየሩ ዝርዝሮችን ይይዛል። እነዚህን ነገሮች በጥንቃቄ ይፈትሹ

✍️ አድሏዊ አለመሆኑን ያረጋግጡ፡ ለአንድ ቡድን ወይም ግለሰብ የሚጠቅም ዜና ከሆነ ምናልባት የተዛባ ወይም ሐሰት ሊሆን ይችላል። ሁልጊዜ ገለልተኝነታቸውን ከሚጠብቁ ምንጮች ዜና ይፈልጉ።

✍️ የመረጃ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ይጠቀሙ፡ የውሸት ዜናዎችን ለመለየት የሚረዱ ብዙ መመርመሪያ መሳሪያዎች ስላሉ እነሱን መጠቀም።

መረጃውን ከማጋራት በፊት ጊዜ ወስዶ ማረጋገጥ ምንጊዜም ቢሆን የተሻለ ነው። የውሸት ዜናዎችን ማሰራጨት ከባድ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2🔥1
#Alert❗️

ከሰሞኑ በአማራ ክልል በፌደራል መንግስት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንዳለ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ ከ190ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ 'የኢትዮጵያ መንግስት በደብረብርሃን ከተማ ላይ ባደረገው የድሮን ጥቃት ከመቶ በላይ ሰዎች እንደተገደሉ' የሚገልፅ ፅሁፍን በማያያዝ አምስት ምስሎችን አጋርቶ ነበር።

ሀቅቼክ መረጃውን ለመደገፍ የቀረቡትን ምስሎች እንዳጣራው ሁለቱ ምስሎች ከሁለት አመት በፊት  በአጣዬ እና አካባቢው ከነበሩት ግጭቶች ጋር የተያያዙ ሲሆኑ አንደኛው ምስል ደግሞ በፈረንጆቹ 2015 የሩሲያ የአየር ሀይል ከአሜሪካ አየር ሀይል ጋር በመቀናጀት በሶሪያ ኮባኒ ያደረሱትን የአየር ጥቃት እንደሚያሳይ ማረጋገጥ ተችሏል። የተቀሩት ሁለቱ ምስሎች በአማራ ክልል ካለው ግጭት ይገናኙ አይገናኙ ማረጋገጥ አልተቻለም።

በማህበራዊ ሚድያ ላይ መሰል ይዘት ያላቸው መረጃዎች እየተጋሩ ስለሆነ መረጃዎችን በጥንቃቄ መመልከት አስፈላጊ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
ከውሸቱ ባሻገር/ Beyond disinfo.

📢 በሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ፣ በንግግር ነፃነት እና በቴክኖሎጂ ላይ የሚያጠነጥን አዲስ ፕሮግራም

ሐሙስ ከምሽቱ 12:30 ላይ ይጠብቁን👇

https://youtube.com/c/AddisZeybe
👍2👌1
ሀሰት : ይህ ምስል አሁን በአማራ ክልል ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ በአማራ ክልል በታጣቂዎች የተማረኩ የጦር መሳሪያዎችን አያሳይም

ይህ በግራ በኩል የምትመለከቱት ምስል በፋኖ አማካኝነት ከመከላከያ የተማረኩ መሳሪያዎች በሚል የመግለጫ ፅሁፍ ስር በማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት ሲዘዋወር ቆይቷል።

ነገር ግን ሀቅቼክ ምስሉን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ምስሉን ከሁለት አመት በፊት በፈረንጆቹ 2021 ላይ ጎልጉል የሚል ስያሜ ባለው ድረገጽ ወስጥ "ባጠናቀቅነው ነሀሴ ወር በቁጥጥር ስር የዋሉ የጦር መሳሪያዎች"  በሚል ፅሁፍ ስር ተጋርቶ አግኝቶታል።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
በአማራ ክልል በነበረው ግጭት በፋኖ ታጣቂዎች የተማረከ የኢትዮጵያ መከላከያ  እንደሆነ የሚያሳይ ምስል ሰሞኑን በፌስቡክ በስፋት ሲሰራጭ ነበር።  ሀቅቼክ እንዳጣራው መረጃውን ለመደገፍ የቀረበው ምስል  ሃሰተኛ መሆኑን አረጋግጣል።

ሙሉውን ያንብቡ👇

https://bityl.co/KOKO
👍1
#የሀሰተኛ_መረጃ_ጥቆማ

ከሰሞኑ በአማራ ክልል ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ ዘመነ ካሴ በቁጥጥር ስር ውሏል የሚሉ የተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ መረጃዎችን ተመልክተናል።

ለምሳሌ ያክል ከ62ሺህ በላይ ተከታይ ያለው አንድ የፌስቡክ ገፅ “ሰበር ዜና ዘመነ ካሴ ሀትሪክ ሰራ!!! ለሦስተኛ ጊዜ በቁጥጥር ስር ውሏል” የሚል የመግለጫ ፅሁፍን በመጠቀም ይህን ምስል አጋርቷል።

ሀቅቼክ የምስሉን ወቅታዊነት ለማረጋገጥ ባደረገው ጥረት በመስከረም ወር 2015 ዓ.ም ዘመነ ካሴ ባህርዳር ላይ በክልሉ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲውል ከተነሱት ምስሎች ውስጥ ተጋርቶ አግኝቶታል።

በዚህም ምክንያት ዘመነ ካሴ በቁጥጥር ስር ስለመዋሉ የሚናገሩ የማህበራዊ ሚድያ ፖስቶች ቢኖሩም ይህ ምስል ግን የቆየ መሆኑ ተረጋግጧል።
መልካም  ዜና

በሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ፣ በንግግር ነፃነት እና በቴክኖሎጂ ላይ የሚያጠነጥነው  አዲሱ ፕሮግራም፣  ከውሸቱ ባሻገር  በአዲስ ዘይቤ ዩቲዩብ ቻናል  ዛሬ ሐሙስ ማቅረብ እንደምንጀምር መግለፃችን ይታወቃል። ነገር ግን ፕሮግራሙን  ለብዙኃኑ ተደራሽ እንዲሆን በማሰብ  ከሀገሬ ቲቪ ጋር በመስማማታችን በዚህ ሳምንት አይኖረንም፡፡ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በቴለቪዠን መስኮት በሀገሬ ቲቪ እና በዩቱብ መተላለፍ እንደሚጀምር እንገልፃለን፡፡

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መረጃን ማጣራት መቻል ፣ ትክክኛ እና ሃሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም የመረጃ ምንጮችን በቀላሉ እንድንለይ ያስችለናል። በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ሰው በእያንዳንዱ ርዕስ ላይ የመሰለውን የሚናገርበትና የሚጽፍበት በመሆኑ መረጃን ማጣራት ቀላል ስራ አይደለም።

መረጃን ማጣራት የሚያስገኘው ጥቅም

✍️ የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎትን ያሳድጋል፡
✍️ አድሏዊ ግንዛቤን ይቀንሳል
✍️ ብስለታዊ አስተሳሰብን ያዳብራል
✍️ የተሻለ ጸሐፊ እንዲሆኑ ያግዝዎታል


ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
1👍1
#Alert

ከ30 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ ከላይ ያልውን ምስል በመጠቀም "የፋኖ ታጥቂዎች በሰሜን ወሎ የደላንታ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን ወገልጤና ከተማን ጨምሮ ሙሉ ወረዳውን እንደገና ተቆጣጠረዋል የሚል መረጃ አሰራጭቶ ነበር።"

ይሁን እንጂ ምስሉ ከአንድ ወር በፊት ሰኔ ላይ በማህበራዊ መገናኛ ተሰራጭቶ የነበረ ነው። በወቅቱም አዲስ ማለዳ የተባለ የሚድያ ተቋም ምስሉ በድህረገጹ ላይ "በደላንታ ወረዳ የስምንት ዓመት ሕጻን ልጅ መደፈሯን ተከትሎ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉን" ከሚገልጽ ዜና ጋር አጋርቶት ነበር።
👍2🔥1🙏1
#የሀሰተኛ_መረጃ_ጥቆማ

ከ11ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ "የኦህዴድ ወራሪው ሀይል መሬት ተንሸራቶ በርካቶች ሲሞቱ ከፊሎቹ ቆሰሉ። በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሰፍሮ የነበረው የብልጽግና ሰራዊት ወደ አማራ ክልል ሲጓጓዝ ካራ ተብላ በምትጠራ ቦታ ሲደርስ መሬቱ ከታች በምትመላከቱት መልኩ ተንሸራቶ በርካቶች የሞቱ ሲሆን ከፊሎቹ ስለመቁሰላቸዉ ከቦታው መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።"

የሚል የመግለጫ ፅሁፍ በማያያዝ ይህን ምስል አጋርቶ ነበር። ሀቅቼክ የምስሉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ባደረገው ጥረት ምስሉን ነሀሴ 2 ፤ 2015 ዓ.ም Paukphaw.org በተሰኘ ድረገጽ ላይ ተጋርቶ አግኝቶታል።

የተጋራው ዜና በኤዠያ ውስጥ የሚገኝ እና ከከባድ ዝናብ የተነሳ የፈረሰ መንገድን እንደሚያሳይ ሀቅቼክ ማረጋገጥ ችሏል።

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2
በአማራ ክልል ያለውን ግጭት ተከትሎ ብዛት ያላቸው መረጃዎች በማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት እየተሰራጩ ነው። አንዳንዶቹ የቆዩና የሌላ ጊዜ ምስልና ቪድዮችን፣ የቅርብ እና አሁን ባለው ውቅታዊ ሁኔታ የተፈጠሩ በማስመሰል እያጋሩ ይገኛሉ።

ከሰሞኑ በፍኖተ ሰላም መንግስት በወሰደው የድሮን ጥቃት ሰዎች እንደተገደሉ የሚያሳዩ የተለያዩ መረጃዎች በማህበራዊ ሚድያ እና በአንዳንድ ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት እየተገለጹ ነው።

ይህን ተከትሎ ከ 40ሺ በላይ ተከታይ ያሉት የፌስቡክ ገፅ በፍኖተ ሰላም መንግስት በወሰደው የድሮን ጥቃት 270 ንጹሃን ዜጎች፣ ህጻናትን ጨምሮ እንደሞቱ የሚገልጽ ጹሑፍ እና ምስል ለጥፎ በስፋት ሲዘዋወር ነበር።

ሀቅቼክ እንዳጣራው መርጃውን ለመደገፍ የተጠቀሙበት ምስል የቆየና ከአሁን በፊት በሌላ ፌስቡክ ግጽ ተለጥፎ የነበረ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል።

ሙሉውን ያንብቡ 👇👇👇
https://bityl.co/KV64
በማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚያጋጥሙህን/ሽን ምስሎች ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የምስል ማረጋገጫ መሳሪያዎችን ተጠቅመህ/ሽ ታውቃለህ/ቂያለሽ?
Anonymous Poll
13%
አዎ ሁል ጊዜ
23%
አዎ አልፎ አልፎ
20%
አይ ስለ ምስል ማረጋገጫ መሳርያዎች ምንም አላውቅም
43%
አላውቅም ግን ስለ ምስል ማረጋገጫ መሳሪያዎች መማር እፈልጋለሁ