HaqCheck
429 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
ሳምንቱን እውነትን በማሰብና እና ትክክለኛ መረጃን ለሌሎች በማጋራት እንጀምረው።
መልካም ሳምንት ይሁንልዎ!

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
1👍1
ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚድያ በተለይም በፌስቡክ ላይ “ድምፃዊት ራሄል ጌቱ እምነት በመቀየር ጥምቀትን ፈፅማለች የሚሉ የተለያዩ ፖስቶች ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። በዚህም አንዳንዶች ደስተኛ ሲሆኑ ሌሎች የተለያዩ ስድቦችን ሲፅፉ ተመልክተናል።

ይሁን እንጂ ድምፃዊቷ ስትጠመቅ የሚያሳየው ምስል ከሁለት አመት ከ6ወር በፊት (በፈረንጆቹ ጃንዋሪ 2020) በአንድ የፌስቡክ ገፅ ላይ “ድምፃዊት ራሄል ጌቱ(ጥሎብኝ) በእየሩሳሌም ተጠመቀች ራሄል ጥምቀትን በቅድስቲቱ እየሩሳሌም በዚህ መልኩ ስርዓቱን ፈፅማለች።” በሚል ፅሁፍ ስር ተጋርቶ አግኝተነዋል። በዚህም ሀቅቼክ ምስሉ የቆየ እንደሆነ አረጋግጧል።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2👌1
የሐምሌ ወር የሁለተኛ ሳምንት ዳሰሳ

በአማራ ክልል እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን በሚመለከት በርካታ የሀሰት መረጃዎች እና አወዛጋቢ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ተሰራጭተዋል። ከተሰራጩት መረጃዎች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

የፋኖ ታጣቂዎች መሳሪያ ማረኩ የሚል የሃሰት ክስ

በደብረ ኤልያስ ወረዳ ጓይ ቀበሌ ህዝቡ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር በመሆን መንግስትን ከሚደግፉ የአካባቢው ሚሊሻዎች እና ፖሊሶች ላይ ከ15 በላይ ትጥቅ መውሰዳቸውን የሚገልጽ ምስል እና መግለጫ የያዘ የፌስ ቡክ ጽሁፍ ሐምሌ 03 ቀን 2015 ተለቋል።
ነገር ግን፣ ሀቅቼክ እንዳረጋገጠው ከልጥፉ ጋር ያለው ምስል ሁኔታውን የማይገልጽና ዋናው ምስል ለመጀመሪያ ጊዜ የተለጠፈው በአሚኮ ድህረ ገጽ ላይ እ.አ.አ ጥቅምት 2021 እንደሆነ ያሳያል። በመሆኑም ሀቅቼክ ይህን የፌስቡክ ልጥፍ ትክክለኛ ያልሆነ ምስል በመጠቀሙ ሃሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በአማራ ክልል ወሎ አካባቢ ግጭት እንዳለ በማህበራዊ ድህረ ገጾች በሰፊው ሲዘገብ ነበር

በወሎ በተለይም በቆቦ ከተማ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል ውጊያ እንደተካሄደ በማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት ተሰራጭቷል።

ነገር ግን፣ ከእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች መካከል አንዳንዶቹ አላስፈላጊ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን መጠቀምን ጨምሮ አሳሳች መረጃዎችን ይዘዋል። ስለ ጉዳዩ የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች መበራከታቸው በመሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ለመረዳት አስቸጋሪ አድርጎታል።

ምክሮች

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ስሜታዊ ሊያደርጉ የሚችሉ ዜናዎች ሲያጋጥሟቸው ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ይህን አይነት ይዘት ያላቸውን ከማጋራት ወይም ከመለጠፍዎ በፊት ትክክለኛነቱን መጠራጠር እና የምንጩን ታማኝነት ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።

የመንግስት ተቋማት ወቅታዊ መረጃዎችን እና ማብራሪያዎችን ለህዝብ እና ሚዲያዎች መስጠት አለባቸው። ትክክለኛ መረጃን በመደበኛነት ማካፈል የተሳሳቱ መረጃዎችን ስርጭት ለመከላከል ይረዳል። የመንግስት ተቋማት የዜጎችን ሙሉ መረጃ የማግኘት መብታቸውን ማክበር አለባቸው።

ተጨማሪ ለማንበብ https://haqcheck.org/july-week-three-summary/
👍3🕊1
በእርስዎ አስተያየት የሚዲያ አጠቃቀም ትምህርት በየትኛው የትምህርት ደረጃ ላይ መሰጠት መጀመር ያለበት ይመስሎታል?
Anonymous Poll
38%
በመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት
41%
በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
12%
በመሰናዶ ት/ቤት
9%
በኮሌጅ/ በዩኒቨርሲቲ
#Alert በዘመን ባንክ ስም የተከፈቱ የቴሌግራም አካውንቶች:-

❗️በአሁኑ ሰዓት ሃሰተኛ የማጭበርበሪያ መልክቶች በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያዎች  በስፋት እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።

❗️እነዚህ የማጭበርበሪያ መልክቶች ባብዛኛው የሚተላለፉት በአንዳንድ ታዋቂ ሰዎች፣ በድርጅቶች እና በባንኮች አርማ፣ስምና ፎቶ በመጠቀም በተከፈቱ ሃሰተኛ የማህበራዊ ሚድያ ገጾች ላይ ነው።

 🎤 ለዛሬ ልንጠቁማችሁ የወደድነው በዘመን ባንክ ስም ስለተከፈቱ የቴሌግራም አካውንቶች ነው።

❗️በምስሉ ላይ የምተመለከቷቸው በዘመን ባንክ ስም Zemen Bank S.C. በሚል የተከፈቱ የቴሌግራም ግሩፖች ናቸው። በተመሳሳይ ስምና ምስል በመጠቀም  የተከፈቱት ከ5 በላይ ሲሆኑ በግሩፑ ውስጥ  ብዙ ተከታይ ካላቸው ወስጥ ብናይ ከ 35,000 , ከ 69, 000 ከ109,000 እና ከ122,000 በለይ ተከታዮች ያሏቸው ይገኛሉ።

❗️ የተከታያቸው ቊጥርም በፍጥነት ነው የሚቀየረው። ሁሉም የሚለጥፉት ተመሳሳይ ይዘት ያለው ሲሆን ፣ በቴሌግራም ግሩፕ ውስጥ ይህን ያህል ሰው ላስገባ (add) ላደረገ ይህን ያህል ብር ይሸለማል የሚሉ ብዙ የማጭበርበሪያ መልዕክቶችን ነው፣ እውነት ለማስመሰል የተለያዩ ሃሰተኛ የሆኑ ሰነዶችን እና  የባንኩን ሌሎች  ትክክለኛ የማህበራዊ ገጾች ሊንኮችን አብረው ይጠቀማሉ።

🎤 ሀቅቼክ በዘመን ባንክ ስም የተከፈቱትን የቴሌግራም ገጾች ለማጣራት ዘመን ባንክን ያናገረ ሲሆን፤ ባንኩ ምንም አይነት የቴሌግራም ቻናል እንደሌለው አረጋግጦልናል። ባንኩ ያሉት ትክክለኛ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች ፌስቡክ ፤ ትዊተር ፤ ዩትዩብ እና ሊንክዲን እንደሆነ ከይፋዊ ድረ-ገፁ ላይ ማረጋገጥ ችለናል።

ስለዚህ እነዚህ የቴሌራም ግሩፓች ትክክለኛ ስላልሆኑ ጥንቃቀቄ እንድታደርጉ መልክታችን ነው፣

ሁልጊዜም ቢሆን መረጃን ከማጋራታችን በፊት እናጣራ!
👍1
📢 ኢንፎርም አፍሪካ ከአፍሪካ ቼክ ጋር በመተባበር ለጋዜጠኞች ያዘጋጀው ሁለተኛ ዙር የሀቅ ማጣራት እና ማረጋገጥ (Fact Checking and Verification) ስልጠና ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል። ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በስልጠናው ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች የመጡ ጋዜጠኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የስልጠናው አላማ በሃገራችን እየተሰራጩ ያሉ የሃሰት መረጃዎችን ከመከላከል አንጻር ጋዜጠኛች ትክክለኛውን መረጃ ለማህበረሰቡ ማቅረብ የሚችሉበትን አቅም መፍጠር ነው፣

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
🔥1
📢 የጉግል የተገላቢጦሽ ምስል መፈለጊያን(Google reverse image search) በመጠቀም እንዴት ምስልን እናረጋግጣለን?

የአንድን ምስል ምንጭ ከዚህ በፊት በማን ፣ለምን እና መቼ ጥቅም ላይ እንደዋለ ለማወቅ የሚረዱን ድህረ ገፆችና መተግበሪያዎች ያሉ ሲሆን፣ ለዛሬ  የምናየው  የጉግል የተገላቢጦሽ ምስል መፈለጊያን በመጠቀም እንዴት ምስልን መመርመር እንደምንችል ነው።

ሊፈትሹት ወይም ሊያረጋግጡ የፈለጉትን ምስል ያውርዱ(save/download)  ያድርጉ ወይም ምስሉ የሚገኝበትን የድር አግራሻዉን(URL address) ይቅዱ (copy) ያድርጉ

Images.google.com ድህረ ገጽን ይክፍቱ፣

በመፈለጊያ ቦታ ላይ የሚገኘውን የካሜራ ምስል በመጫን መመርመር የምንፈልገውን ምስል ወይም የምስሉን መዳረሻ (link)ማስገባትና መፈለግ፣

ውጤቶቹ ምስሉ ከተጋራ ምን ያህል ጊዜ እንደ ሆነው እንዲሁም አካባቢዉን፣ የምስሉን አዉድ እና የመሳሰሉትን ሌሎች መረጃውችን ይሰጥዎታል።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በዛሬው የሀቅ ማጣራትና ማረጋገጥ ስልጠና ላይ፣ ተሳታፊ ጋዜጠኞች ሃቅን ለማጣራት ከምንጠቀምበት ዘዴ አንዱ የሆነውን ቦታን ማጣራት(geolocation) ላይ ሲለማመዱ የሚያሳይ ቪድዮ።
👍2👌1
📢 የሁለተኛ ዙር የሀቅ ማጣራት እና ማረጋገጥ (Fact Checking and Verification) ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።

ስልጠናው በዋናነት የመረጃ መዛባት ምንነትና አይነቶች፣የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስል፣ ሃሰተኛ  መረጃን የሚያሰራጩ አካላት የሚጠቀሙት ዘዴ እና በመጨረሻም ሃሰተኛ መረጃን እንዴት መከላከል እንደሚቻልና ሃሰተኛ መረጃዎችን የተለያዩ ነጻ መተግበሪያዎችንና ድህረ ገጾችን በመጠቀም እንዴት ማረጋገጥና ማጣራት እንደሚቻል ሰልጣኞች በተግባር የተደገፈ ክህሎት ያዳበሩበት ነበር።

ተሳታፊ ጋዜጠኞችም በስልጠናው እጅግ ጠቃሚ የሆነ ክህሎትና ግንዛቤን እንዳገኙ የገለጹ ሲሆን በጋዜጠኝነት ሙያቸዉ ለማህበረሰቡ እውነተኛና ትክክለኛ መረጃን በማቅረብ ፣ የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሀቅቼክ መረጃን አጣርቶ ለማህበረሰቡ ከቅርብ በተጨማሪ እያንዳንዱ ዜጋ የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት እንዲኖረው፣ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር መሰል ስልጠናዎችን ማዘጋጀቱን ይቀጥላል።
🔥1👏1
የመረጃ መንታፊዎች ማስፋንጠርያ ሊንኮችን በመላክ የግል መረጃን ይመነትፋሉ።

አንድ ሊንክ ሲላክሎት ወይም ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲመለከቱ ሊንኩ መረጃን ለመመንተፍ የተሰራ ሊሆን ስለሚችል በጥንቃቄ መመልከት  ያስፈልጋል።

ማንኛውም አይነት ማስፈንጠርያ ወይም ሊንክ ሲላክልዎ ወይም ሲያጋጥምዎ በጥድፍያ አለመንካት ያስፈልጋል። ሊንኩን በጥንቃቄ መመርመር ተገቢ ነው። ያንን ሊንክ ከሚያውቁት ሰው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በማህበራዊ ሚድያ በውስጥ መስመር ሊላክሎት ይችላል። ማንኛውንም ሊንክ ማመን የለብዎትም፤ ሊንኩ ከየት እንደተላከ በጥንቃቄ ማየት ይኖርብዎታል።

ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሰዎችን ቀልብ ለመሳብ የተለየዩ ፅሁፍ የያዙ መንታፊ ሊንኮች ይታያሉ። በፅሁፍ ከላይ የሚነበበው እና ማስፈንጠርያ ሊንኩ የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ።

ለምሳሌ ከላይ ያለው ፅሁፍ ስለሽልማት ፣ ስለትምህርት እድል ወዘተ ሊሆን ይችላል። ይህ አሰራር ሰዎች ከላይ በሚያነቡት ፅሁፍ ተሸውደው ሊንኩን በጥድፍያ እንዲነኩ ለማስጎምጀት ታልሞ የተዘጋጀ ነው።

ስለዚህ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሊንክ ሲያዩ ከመንካትዎ በፊት በፅሁፉ የሚነበበው ሀሳብ እና ሊንኩን አንድ አይነት መሆኑን ማመሳከር ይኖርቦታል።

የኢሜይል አድራሻዎ ፣ የይለፍ ቃል ወይም ፓስዋርድ ፣ የባንክ አካውንት ፣ የማህበራዊ ሚድያ አካውንት የመሳሰሉ የግል መረጃዎች እንዲሰጡ ሲጠየቁ ሊንኩ እውነተኛ መሆኑን ሳያረጋግጡ መስጠት የለብዎትም።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👌21👍1
"ሀቅ ችላ ስለተባለች መኖሯን አታቆምም"

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
🔇 በማህበራዊ ሚዲያ፣ በተለያዩ ጽሁፎች፣ በቪዲዮዎች እና በዜና ዘገባዎች ላይ ያገኛችሁት መረጃ እውነት መሆኑ ካጠራጠራችሁ፣ ጥያቄ ከፈጠረባችሁ፣ ወደ ሀቅቼክ መረጃውን ያገኙበትን ምንጭ አያይዘው ይላኩልን። የመረጃውን እውነትነት አጣርተን መልሰን ለእናንተው እናቀርባለን።

መረጃ ለመላክ:-
   በ ኢሜል: claims@haqcheck.org
   በድህረ ገጽ : Haqcheck.org ላይ ገብተው  ሪፖርት የሚለውን በመጫን መላክ ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍1🕊1
ከሰሞኑ በቲክቶክ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአማራ ህዝባዊ ኃይል በአማራ ክልል ራያ ቆቦ ላይ የመንግስትን የጦር አውሮፕላን መተው እንደጣሉ የሚገልጽ የጹሕፍ፣ ምስልና ድምጽ ቅንብር በስፋት እየተዘዋወረ ይገኛል። ይህ ቪድዮ ከ10 ሺህ በላይ ላይክና ከ 500 በላይ አስተያየት አግኝቷል።

በአማራ ክልል በመንግስት እና በክልሉ ባሉ  ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንዳለ ይታወቃል።
ሀቅ ቼክ ምስሉን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ምስሉ ከ10 ዓመት በፊት በፈረንጆቹ ሚያዝያ 2013 ላይ ከደቡብ ኮርያ ጦር ጋር በመሆን ልምምድ ሲያደርግ የነበረ የአሜሪካ ሄሊኮፕተር በሰሜን ኮሪያ ድንበር አካባቢ መከስከሱን ከሚያሳይ ጹሑፍ ጋር ዴይሊ ሜል በሚባለው ድህረ ገጽ ላይ ተጋርቶ እንደነበር ማረጋገጥ ችሏል።

በዚህም ምክንያት መረጃውን ለመደገፍ የተጠቀሙት ምስል የተሳሳት ነው። 

ተጨማሪ ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ

ሁልጊዜም ቢሆን መረጃን ከማጋራታችን በፊት እናጣራ።
👍2🔥1