HaqCheck
429 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
የምስል መመርመሪያ መገልገያዎች/ image verification tools

የአንድን ምስል ምንጭ ወይም ከዚህ በፊት በማን፣ ለምን እና መቼ ጥቅም ላይ እንደዋለ ለማውቅ የሚረዱን በርካታ ድረ-ገፆችና መተግበሪያዎች አሉ።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ያለምንም ከፍያ በነፃ ፎቶዎችን ለመመርመር የሚረዱን መግልገያዎች  ናቸው።

Google reverse images
TinEye
FotoForensics
Yandex
InVID
Bing

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2👏1
✍️ በደብረ ኤልያስ ወረዳ ጓይ ቀበሌ ህዝቡ  ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር በመሆን መንግስትን ከሚደግፉ የአካባቢው ሚሊሻዎች እና ፖሊሶች ላይ ከ15 በላይ ትጥቅ  መውሰዳቸውን የሚገልጽ ምስል እና መግለጫ የያዘ የፌስ ቡክ ጽሁፍ ሐምሌ 03 ቀን 2015 ተለቋል።
✍️ በጽሁፉ መሰረት የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶስት ኦራል እና አንድ አውቶብስ ተጠቅመው ደብረ ኤሊያስ ወረዳ እንደገቡ ይገልጻል። በተጨማሪም መሳሪያዎቹ የተያዙት በአካባቢው የሚገኙ ታጣቂዎች የመከላከያ ሰራዊት አባላትን እየመሩ ፋኖን ለማስመታት ተዘጋጅተው ይጠብቁ እንደነበረ ይገልጻል፡፡

ሃቅቼክ እንዳጣራው:
✍️የፌዴራል መንግስት በሚያዝያ 2023 ልዩ ሃይሎችን ትጥቅ ለማስፈታት ከወሰነ ጊዜ ጀምሮ በአማራ ክልል ተቃውሞ ሲካሄድ ቆይቷል። የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች እና መደበኛ ያልሆኑ ታጣቂዎ ግጭት ውስጥ ገብተዋል፡፡
✍️በተቀሰቀሰው ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን መረጃዎች ያመለክታሉ።
✍️በጎጃም ደንበጫ፣ ጅጋ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች ህዝባዊ አመጽ ሰሞኑን እንደነበረ መረጃዎች ያሳያሉ። በመቀጠልም ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች እና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል ውጊያ ተካሂዶ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ20 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።
✍️ይህንን ሁኔታ በመከተል ሐምሌ 03 ቀን 2015 ዓም በደብረ ኤልያስ ወረዳ የፋኖ ታጣቂዎች ከ15 በላይ ትጥቅን ከአካባቢው ሚሊሻዎች እና መንግስትን ከሚደግፉ ታጣቂዎች መማረካቸውን የሚገልጽ የፌስቡክ ጽሁፍ ወጣ።
✍️ነገር ግን፣ ከልጥፉ ጋር ያለው ምስል ሁኔታውን የማይገልጽና ዋናው ምስል ለመጀመሪያ ጊዜ የተለጠፈው በአሚኮ ድህረ ገጽ ላይ ጥቅምት 2021 እአአ እንደሆነ ያሳያል። በመሆኑም ሀቅቼክ ይህን የፌስቡክ ልጥፍ ትክክለኛ ያልሆነ ምስል በመጠቀሙ ሃሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
በአዲስ አበባ ለምትገኙ ጋዜጠኞች

ኢንፎርም አፍሪካ ከአፍሪካ ቼክ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የሁለት ቀናት የ Fact checking and verification ስልጠና ላይ መሳተፍ ለምትፈልጉ ውስን ቦታ ስላለን መመዝገብ ትችላላችሁ።

🔶ስልጠናው የሚሰጠው በአካል በመገኘት ነው
🔶የስልጠናው ቀን ከሐምሌ 13-14, 2015
🔶ቦታ ፣ ወደፊት ይገለጻል
🔶ምዝገባ የሚያበቃው ነገ ሐምሌ 8, 2015
🔶ለመመዝገብ ከታች ያለውን ጉግል ፎርም ሞልተው ይላኩልን

https://ggle.io/61D5
ያገኙትን መረጃ ከማጋራትዎ በፊት መረጃውን ማጣራት መቻል ላይ ምን ያህል በራስዎ ይተማመናሉ?
Anonymous Poll
74%
በራሴ በጣም እተማመናለሁ
21%
በራሴ በመጠኑ እተማመናለሁ
0%
በራሴ በጣም አልተማመንም
5%
ጭራሽ አልተማመንም
ሳምንቱን እውነትን በማሰብና እና ትክክለኛ መረጃን ለሌሎች በማጋራት እንጀምረው።
መልካም ሳምንት ይሁንልዎ!

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
1👍1
ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚድያ በተለይም በፌስቡክ ላይ “ድምፃዊት ራሄል ጌቱ እምነት በመቀየር ጥምቀትን ፈፅማለች የሚሉ የተለያዩ ፖስቶች ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። በዚህም አንዳንዶች ደስተኛ ሲሆኑ ሌሎች የተለያዩ ስድቦችን ሲፅፉ ተመልክተናል።

ይሁን እንጂ ድምፃዊቷ ስትጠመቅ የሚያሳየው ምስል ከሁለት አመት ከ6ወር በፊት (በፈረንጆቹ ጃንዋሪ 2020) በአንድ የፌስቡክ ገፅ ላይ “ድምፃዊት ራሄል ጌቱ(ጥሎብኝ) በእየሩሳሌም ተጠመቀች ራሄል ጥምቀትን በቅድስቲቱ እየሩሳሌም በዚህ መልኩ ስርዓቱን ፈፅማለች።” በሚል ፅሁፍ ስር ተጋርቶ አግኝተነዋል። በዚህም ሀቅቼክ ምስሉ የቆየ እንደሆነ አረጋግጧል።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2👌1
የሐምሌ ወር የሁለተኛ ሳምንት ዳሰሳ

በአማራ ክልል እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን በሚመለከት በርካታ የሀሰት መረጃዎች እና አወዛጋቢ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ተሰራጭተዋል። ከተሰራጩት መረጃዎች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

የፋኖ ታጣቂዎች መሳሪያ ማረኩ የሚል የሃሰት ክስ

በደብረ ኤልያስ ወረዳ ጓይ ቀበሌ ህዝቡ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር በመሆን መንግስትን ከሚደግፉ የአካባቢው ሚሊሻዎች እና ፖሊሶች ላይ ከ15 በላይ ትጥቅ መውሰዳቸውን የሚገልጽ ምስል እና መግለጫ የያዘ የፌስ ቡክ ጽሁፍ ሐምሌ 03 ቀን 2015 ተለቋል።
ነገር ግን፣ ሀቅቼክ እንዳረጋገጠው ከልጥፉ ጋር ያለው ምስል ሁኔታውን የማይገልጽና ዋናው ምስል ለመጀመሪያ ጊዜ የተለጠፈው በአሚኮ ድህረ ገጽ ላይ እ.አ.አ ጥቅምት 2021 እንደሆነ ያሳያል። በመሆኑም ሀቅቼክ ይህን የፌስቡክ ልጥፍ ትክክለኛ ያልሆነ ምስል በመጠቀሙ ሃሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በአማራ ክልል ወሎ አካባቢ ግጭት እንዳለ በማህበራዊ ድህረ ገጾች በሰፊው ሲዘገብ ነበር

በወሎ በተለይም በቆቦ ከተማ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል ውጊያ እንደተካሄደ በማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት ተሰራጭቷል።

ነገር ግን፣ ከእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች መካከል አንዳንዶቹ አላስፈላጊ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን መጠቀምን ጨምሮ አሳሳች መረጃዎችን ይዘዋል። ስለ ጉዳዩ የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች መበራከታቸው በመሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ለመረዳት አስቸጋሪ አድርጎታል።

ምክሮች

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ስሜታዊ ሊያደርጉ የሚችሉ ዜናዎች ሲያጋጥሟቸው ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ይህን አይነት ይዘት ያላቸውን ከማጋራት ወይም ከመለጠፍዎ በፊት ትክክለኛነቱን መጠራጠር እና የምንጩን ታማኝነት ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።

የመንግስት ተቋማት ወቅታዊ መረጃዎችን እና ማብራሪያዎችን ለህዝብ እና ሚዲያዎች መስጠት አለባቸው። ትክክለኛ መረጃን በመደበኛነት ማካፈል የተሳሳቱ መረጃዎችን ስርጭት ለመከላከል ይረዳል። የመንግስት ተቋማት የዜጎችን ሙሉ መረጃ የማግኘት መብታቸውን ማክበር አለባቸው።

ተጨማሪ ለማንበብ https://haqcheck.org/july-week-three-summary/
👍3🕊1
በእርስዎ አስተያየት የሚዲያ አጠቃቀም ትምህርት በየትኛው የትምህርት ደረጃ ላይ መሰጠት መጀመር ያለበት ይመስሎታል?
Anonymous Poll
38%
በመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት
41%
በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
12%
በመሰናዶ ት/ቤት
9%
በኮሌጅ/ በዩኒቨርሲቲ
#Alert በዘመን ባንክ ስም የተከፈቱ የቴሌግራም አካውንቶች:-

❗️በአሁኑ ሰዓት ሃሰተኛ የማጭበርበሪያ መልክቶች በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያዎች  በስፋት እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።

❗️እነዚህ የማጭበርበሪያ መልክቶች ባብዛኛው የሚተላለፉት በአንዳንድ ታዋቂ ሰዎች፣ በድርጅቶች እና በባንኮች አርማ፣ስምና ፎቶ በመጠቀም በተከፈቱ ሃሰተኛ የማህበራዊ ሚድያ ገጾች ላይ ነው።

 🎤 ለዛሬ ልንጠቁማችሁ የወደድነው በዘመን ባንክ ስም ስለተከፈቱ የቴሌግራም አካውንቶች ነው።

❗️በምስሉ ላይ የምተመለከቷቸው በዘመን ባንክ ስም Zemen Bank S.C. በሚል የተከፈቱ የቴሌግራም ግሩፖች ናቸው። በተመሳሳይ ስምና ምስል በመጠቀም  የተከፈቱት ከ5 በላይ ሲሆኑ በግሩፑ ውስጥ  ብዙ ተከታይ ካላቸው ወስጥ ብናይ ከ 35,000 , ከ 69, 000 ከ109,000 እና ከ122,000 በለይ ተከታዮች ያሏቸው ይገኛሉ።

❗️ የተከታያቸው ቊጥርም በፍጥነት ነው የሚቀየረው። ሁሉም የሚለጥፉት ተመሳሳይ ይዘት ያለው ሲሆን ፣ በቴሌግራም ግሩፕ ውስጥ ይህን ያህል ሰው ላስገባ (add) ላደረገ ይህን ያህል ብር ይሸለማል የሚሉ ብዙ የማጭበርበሪያ መልዕክቶችን ነው፣ እውነት ለማስመሰል የተለያዩ ሃሰተኛ የሆኑ ሰነዶችን እና  የባንኩን ሌሎች  ትክክለኛ የማህበራዊ ገጾች ሊንኮችን አብረው ይጠቀማሉ።

🎤 ሀቅቼክ በዘመን ባንክ ስም የተከፈቱትን የቴሌግራም ገጾች ለማጣራት ዘመን ባንክን ያናገረ ሲሆን፤ ባንኩ ምንም አይነት የቴሌግራም ቻናል እንደሌለው አረጋግጦልናል። ባንኩ ያሉት ትክክለኛ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች ፌስቡክ ፤ ትዊተር ፤ ዩትዩብ እና ሊንክዲን እንደሆነ ከይፋዊ ድረ-ገፁ ላይ ማረጋገጥ ችለናል።

ስለዚህ እነዚህ የቴሌራም ግሩፓች ትክክለኛ ስላልሆኑ ጥንቃቀቄ እንድታደርጉ መልክታችን ነው፣

ሁልጊዜም ቢሆን መረጃን ከማጋራታችን በፊት እናጣራ!
👍1
📢 ኢንፎርም አፍሪካ ከአፍሪካ ቼክ ጋር በመተባበር ለጋዜጠኞች ያዘጋጀው ሁለተኛ ዙር የሀቅ ማጣራት እና ማረጋገጥ (Fact Checking and Verification) ስልጠና ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል። ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በስልጠናው ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች የመጡ ጋዜጠኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የስልጠናው አላማ በሃገራችን እየተሰራጩ ያሉ የሃሰት መረጃዎችን ከመከላከል አንጻር ጋዜጠኛች ትክክለኛውን መረጃ ለማህበረሰቡ ማቅረብ የሚችሉበትን አቅም መፍጠር ነው፣

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
🔥1
📢 የጉግል የተገላቢጦሽ ምስል መፈለጊያን(Google reverse image search) በመጠቀም እንዴት ምስልን እናረጋግጣለን?

የአንድን ምስል ምንጭ ከዚህ በፊት በማን ፣ለምን እና መቼ ጥቅም ላይ እንደዋለ ለማወቅ የሚረዱን ድህረ ገፆችና መተግበሪያዎች ያሉ ሲሆን፣ ለዛሬ  የምናየው  የጉግል የተገላቢጦሽ ምስል መፈለጊያን በመጠቀም እንዴት ምስልን መመርመር እንደምንችል ነው።

ሊፈትሹት ወይም ሊያረጋግጡ የፈለጉትን ምስል ያውርዱ(save/download)  ያድርጉ ወይም ምስሉ የሚገኝበትን የድር አግራሻዉን(URL address) ይቅዱ (copy) ያድርጉ

Images.google.com ድህረ ገጽን ይክፍቱ፣

በመፈለጊያ ቦታ ላይ የሚገኘውን የካሜራ ምስል በመጫን መመርመር የምንፈልገውን ምስል ወይም የምስሉን መዳረሻ (link)ማስገባትና መፈለግ፣

ውጤቶቹ ምስሉ ከተጋራ ምን ያህል ጊዜ እንደ ሆነው እንዲሁም አካባቢዉን፣ የምስሉን አዉድ እና የመሳሰሉትን ሌሎች መረጃውችን ይሰጥዎታል።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
1