HaqCheck
429 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
የሃሰተኛ መረጃ ዓይነቶች
🛑 ሃሰተኛ መረጃዎች በተለያየ አላማና ይዘት ሊሰራጩ ይችላሉ። መሰረታዊ ልዩነታቸው ያለው ከሚሰራጩበት ጀርባ ያለው ፍላጎት ላይ ነው። የሚሰራጩበትን አላማ መሰረት አድርገን ሃሰተኛ መረጃዎችን በሦስት ከፍለን ማየት እንችላለን

❗️መረጃን ማሳሳት (misinformation)

የዚህን ዓይነት የመረጃ ማሳሳት የሚከሰተው መረጃውን ያሰራጨው አካል መረጃው የተሳሳተ መሆኑን ካለማወቅ እና እውነት ነው ብሎ በማሰብ ወይም ከመሳሳት የተነሳ የድርጊቱ ተሳታፊ ሲሆን ነው። ይህ በሀገራችን በጣም በብዛት የሚታይ የሃሰተኛ መረጃ ዓይነት ነው፡፡

❗️መረጃን ማዛባት (disinformation)

በዚህኛው ምድብ ደግሞ ሰዎች አስበውበት፣ አቅደውበት እና ሆን ብለው ፍላጎታቸውን  ለማስፈጸም ብለው የሚያዘጋጁት የሃሰተኛ መረጃ ዓይነት ነው፡፡

❗️መረጃን መበከል (malinformation)

ይህ ደግሞ አንድ ትክክለኛ የሆነን መረጃን ያለ ተቋሙ ወይም ያለ ግለሰቡ ፍቃድ ጉዳት ለማድረስ፣ ስም ለማጥፋትና ችግር ለመፍጠር መረጃን መጠቀምና ማሰራጨትን የሚያመለክት ነው።

መረጃዎችን ከመጠቀማችንና ለሌሎች ከማጋራታችን በፊት መረጃው እውነት መሆን አለመሆኑን ማጣራት የሁላችንም ሐላፊነት ነው!

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

Telegram|Facebook|website|Twitter
1🙏1
በማህበራዊ ሚድያ ላይ መረጃን ከማጋራትዎ በፊት መረጃው እውነት መሆን አለመሆኑን ምን ያህል ያጣራሉ?
Anonymous Poll
72%
ሁሌም (Always)
17%
አንዳንዴ (Sometimes)
6%
አልፎ አልፎ (Rarely)
6%
በጭራሽ (Never)
ከሰሞኑ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አማራጮች ላይ ይህ ምስል በስፋት ሲዘዋወር ቆይቶ ነበር። አሁን በስፋት በተሰራጨው ምስል ላይ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ ፖስቶች የአፄ ሚኒሊክ ምስል ያለበት ፍሬም ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ሲበረከትላቸው የሚታይ እንደሆነ በመግለፅ በስፋት ሲጋራ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ምስሉ ከሁለት አመት በፊት ተጋርቶ ያገኘነው ሲሆን ምስሉ የተቀናበረ እንደሆነ ማረጋገጥ ችለናል።

ትክከለኛው እና የተቀናበረውን ምስል ይመልከቱ 👀
👍2
በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ ሃቅ ማጣራት (fact-checking) ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች የልምድ ልውውጥ አደረጉ

ከኢትዮጵያ ፣ ከኡጋንዳ ፣ ከዚምባብዌ ፣ ከሱዳን እና ከኬንያ የተውጣጡ ሀቅ አጣሪዎች
(fact-checkers) በቪድዮ ኮንፍረንስ በታገዘ ስብሰባ በቀጠናው ላይ ስላለው የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት መከላከል እና የሚድያ አጠቃቀም ክህሎት ላይ ያተኮረ የልምድ ልዉውጥ አካሂደዋል።

መርሃግብሩን ያዘጋጁት በኢትዮጵያ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት የሚታወቀው ሀቅቼክ እና ሚዳን Meedan ናቸው፡፡

የዝግጅቱ ዋና አላማ አሃጉራዊ ውይይቶችን ማበረታታት እና ሃሰተኛ መረጃውችን በማጥራት ሂደት ያሉ ተሞክሮዎችን እና በየሀገሩ የተለዩትን ወቅታዊ የሀሰት መረጃ አዝማሚያዎችን በተመለከተ ጠቃሚ ሃሳቦችን ማካፈል ነበር።

ተሳታፊዎች በመስኩ ላይ ብዙ ልምድ ካካበቱ ባለሙያዎች ጋር ምርጥ ተሞክሮዎችን እንዲለዋወጡ አስችሏል።

በውይይቱ የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላክለ በየሃገሩ ያሉ ጥሩ አጋጣሚዎች ናቸው ያሏቸዉንና አስቸጋሪ ወይም መሰናክል የሆኑ ጉዳዮችን አንስተዋል። ተጨማሪ ለማንበብ ይህን ይጫኑ

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍1
ከውሸቱ ባሻገር - Beyond Disinfo

በሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት፣ በንግግር ነፃነት እና ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ የሚያጠነጥን የፖድካስት ጨዋታ።

ዛሬ ማታ 3ሰዓት ላይ በትዊተር ስፔስ እንገናኝ ስለ ሀሰተኛ መረጃዎች ብዙ ነገር እናወራለን 👇🏽👇🏽

https://twitter.com/i/spaces/1kvJpmAOYyLxE
👍2
❗️ያገኙትን መረጃ  እውነት መሆኑን ሳያጣሩ ለሌሎች ባለማጋራት የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን በጋራ እንከላከል።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍1👌1
ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍1👌1
በእርስዎ አመለካከት፣ የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን መቀነስ በዋናነት የማን ኃላፊነት ነው?
Anonymous Poll
14%
የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች
17%
የዜና ተቋማት
60%
እያንዳንዱ ግለሰብ
9%
ሌሎች (እባክዎ በኮሜንት መስጫው ላይ ይጥቀሱ)
የምስል መመርመሪያ መገልገያዎች/ image verification tools

የአንድን ምስል ምንጭ ወይም ከዚህ በፊት በማን፣ ለምን እና መቼ ጥቅም ላይ እንደዋለ ለማውቅ የሚረዱን በርካታ ድረ-ገፆችና መተግበሪያዎች አሉ።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ያለምንም ከፍያ በነፃ ፎቶዎችን ለመመርመር የሚረዱን መግልገያዎች  ናቸው።

Google reverse images
TinEye
FotoForensics
Yandex
InVID
Bing

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2👏1
✍️ በደብረ ኤልያስ ወረዳ ጓይ ቀበሌ ህዝቡ  ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር በመሆን መንግስትን ከሚደግፉ የአካባቢው ሚሊሻዎች እና ፖሊሶች ላይ ከ15 በላይ ትጥቅ  መውሰዳቸውን የሚገልጽ ምስል እና መግለጫ የያዘ የፌስ ቡክ ጽሁፍ ሐምሌ 03 ቀን 2015 ተለቋል።
✍️ በጽሁፉ መሰረት የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶስት ኦራል እና አንድ አውቶብስ ተጠቅመው ደብረ ኤሊያስ ወረዳ እንደገቡ ይገልጻል። በተጨማሪም መሳሪያዎቹ የተያዙት በአካባቢው የሚገኙ ታጣቂዎች የመከላከያ ሰራዊት አባላትን እየመሩ ፋኖን ለማስመታት ተዘጋጅተው ይጠብቁ እንደነበረ ይገልጻል፡፡

ሃቅቼክ እንዳጣራው:
✍️የፌዴራል መንግስት በሚያዝያ 2023 ልዩ ሃይሎችን ትጥቅ ለማስፈታት ከወሰነ ጊዜ ጀምሮ በአማራ ክልል ተቃውሞ ሲካሄድ ቆይቷል። የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች እና መደበኛ ያልሆኑ ታጣቂዎ ግጭት ውስጥ ገብተዋል፡፡
✍️በተቀሰቀሰው ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን መረጃዎች ያመለክታሉ።
✍️በጎጃም ደንበጫ፣ ጅጋ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች ህዝባዊ አመጽ ሰሞኑን እንደነበረ መረጃዎች ያሳያሉ። በመቀጠልም ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች እና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል ውጊያ ተካሂዶ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ20 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።
✍️ይህንን ሁኔታ በመከተል ሐምሌ 03 ቀን 2015 ዓም በደብረ ኤልያስ ወረዳ የፋኖ ታጣቂዎች ከ15 በላይ ትጥቅን ከአካባቢው ሚሊሻዎች እና መንግስትን ከሚደግፉ ታጣቂዎች መማረካቸውን የሚገልጽ የፌስቡክ ጽሁፍ ወጣ።
✍️ነገር ግን፣ ከልጥፉ ጋር ያለው ምስል ሁኔታውን የማይገልጽና ዋናው ምስል ለመጀመሪያ ጊዜ የተለጠፈው በአሚኮ ድህረ ገጽ ላይ ጥቅምት 2021 እአአ እንደሆነ ያሳያል። በመሆኑም ሀቅቼክ ይህን የፌስቡክ ልጥፍ ትክክለኛ ያልሆነ ምስል በመጠቀሙ ሃሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
በአዲስ አበባ ለምትገኙ ጋዜጠኞች

ኢንፎርም አፍሪካ ከአፍሪካ ቼክ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የሁለት ቀናት የ Fact checking and verification ስልጠና ላይ መሳተፍ ለምትፈልጉ ውስን ቦታ ስላለን መመዝገብ ትችላላችሁ።

🔶ስልጠናው የሚሰጠው በአካል በመገኘት ነው
🔶የስልጠናው ቀን ከሐምሌ 13-14, 2015
🔶ቦታ ፣ ወደፊት ይገለጻል
🔶ምዝገባ የሚያበቃው ነገ ሐምሌ 8, 2015
🔶ለመመዝገብ ከታች ያለውን ጉግል ፎርም ሞልተው ይላኩልን

https://ggle.io/61D5
ያገኙትን መረጃ ከማጋራትዎ በፊት መረጃውን ማጣራት መቻል ላይ ምን ያህል በራስዎ ይተማመናሉ?
Anonymous Poll
74%
በራሴ በጣም እተማመናለሁ
21%
በራሴ በመጠኑ እተማመናለሁ
0%
በራሴ በጣም አልተማመንም
5%
ጭራሽ አልተማመንም
ሳምንቱን እውነትን በማሰብና እና ትክክለኛ መረጃን ለሌሎች በማጋራት እንጀምረው።
መልካም ሳምንት ይሁንልዎ!

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
1👍1
ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚድያ በተለይም በፌስቡክ ላይ “ድምፃዊት ራሄል ጌቱ እምነት በመቀየር ጥምቀትን ፈፅማለች የሚሉ የተለያዩ ፖስቶች ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። በዚህም አንዳንዶች ደስተኛ ሲሆኑ ሌሎች የተለያዩ ስድቦችን ሲፅፉ ተመልክተናል።

ይሁን እንጂ ድምፃዊቷ ስትጠመቅ የሚያሳየው ምስል ከሁለት አመት ከ6ወር በፊት (በፈረንጆቹ ጃንዋሪ 2020) በአንድ የፌስቡክ ገፅ ላይ “ድምፃዊት ራሄል ጌቱ(ጥሎብኝ) በእየሩሳሌም ተጠመቀች ራሄል ጥምቀትን በቅድስቲቱ እየሩሳሌም በዚህ መልኩ ስርዓቱን ፈፅማለች።” በሚል ፅሁፍ ስር ተጋርቶ አግኝተነዋል። በዚህም ሀቅቼክ ምስሉ የቆየ እንደሆነ አረጋግጧል።

ለተጨማሪ መረጃ: የሀቅቼክ ድህረ ገጽ እና ማህበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ👇

TikTok|Facebook|website|Twitter
👍2👌1