HaqCheck
428 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አለምን ያወዛገቡ አስር የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻዎች እና ጉዳታቸው

በታሪክ አጋጣሚዎች ውዝግብ ለመፍጠር፣ የህብረተሰቡን አስተሳሰብ ለመቀየር፣ እንዲሁም ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ አለመረጋጋትን ለመፍጠር በማሰብ ሀሰተኛ መረጃዎች ሆን ተብለው ይሰራጫሉ።
👍3
አሳሳች ፡ የደቡብ አፍሪካ ነፃነት ታጋዮች ንግግር ተብሎ በማህበራዊ ሚድያ የተሰራጨው የሀሰት መረጃ

በደቡብ አፍሪካ በአንድ የፌስቡክ ግሩፕ ላይ የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፖለቲከኞች የሆኑት ክሪስ ሃኒ ፤ ኦሊቨር ታምቦ እና ኔልሰን ማንዴላ የተናገሩት ንግግር በማለት ፅሁፎችን ተጋርቶ ነበር።

ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች በኋላ በፈረንጆቹ ሚያዝያ 27 ቀን 1994 ብሄራዊ ምርጫ አካሂዳ ነበር። ይህ ቀንም በደቡብ አፍሪካውያን ዘንድ የነፃነት ቀን ተብሎ በየአመቱ ይከበራል። ይህ የፌስቡክ ገፅም የዚህን አመታዊ ክብረ በዓል ተከትሎ ይህን መረጃ አጋርቶ ነበር።

ይህ የፌስቡክ ፖስት በእነዚህ ሦስት ጥቅሶች ውስጥ የፀረ-አፓርታይድ አክቲቪስቶች የነበሩት የፖለቲካ መሪዎች የደቡብ አፍሪካን አሁናዊ የፖለቲካ ሁኔታ አስቀድመው እንደተነበዩት ለማሳየት ሞክሯል።
ይህ የፌስቡክ ፖስት “ስለ ንግግራቸው ብዙ ጊዜ አስብ ነበር ... ምን አይተው ነበር?” የሚል የመግለጫ ፅሁፍን ከምስሎቹ ጋር አያይዞ አጋርቶ ነበር።

ከነዚያ መካከል የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ገዢ ፓርቲ 'የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ’ ፕሬዝደንት የነበሩት ኦሊቨር ታምቦ “በሙስና የተዘፈቀ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ከአፓርታይድ አገዛዝ ይልቅ የከፋ ነው።” ብለው ተናግረዋል የሚለው ንግግር ቀድሞም በማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት ሲዘዋወር የነበረ ነው።

በደቡብ አፍሪካ የሚገኝ አፍሪካ ቼክ የተባለ የመረጃ አጣሪ ተቋም በፈረንጆቹ 2019 በዚህ የኦሊቨር ታምቦ ነው ተብሎ በተሰራጨው ንግግር ላይ ምርመራ አድርጎ፡ ታምቦ ይህን እንደተናገሩ የሚያሳይ ምንም ፍንጭ ማግኘት አልቻለም።
የቀጠለ.......

ሌላኛው ደግሞ ከቀድሞ የነፃነት ታጋይ እና ፖለቲከኛ ኔልሰን ማንዴላ የተናገሩት ተብሎ የተሰራጨ ነው።
“የአፓርታይድ አገዛዝ እና መንግስት ላይ ያደረጋችሁትን በአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ላይ አርጉ” የሚል ሲሆን አፍሪካ ቼክ በዚህ አባባል ላይ ጥልቅ የሆነ ጥናትን ያካሄዱ ሲሆን ንግግሩ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንጆቹ 1994 5ተኛው የደቡብ አፍሪካ የንግድ ህብረት ብሄራዊ ኮንግረስ ስብሰባ ላይ ኔልሰን ማንዴላ ካደረጉት ንግግር ላይ የተወሰደ ነው።

ከዚያ በኋላ ግን ንግግሩ እየተነካካ እና እየተቀየረ እዚህ ላይ መድረሱ ተረጋግጧል። ነገር ግን ኔልሰን ማንዴላ ደጋፊዎቻቸውን “የአፓርታይድ አገዛዝ እና መንግስት ላይ ያደረጋችሁትን በአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ላይ አርጉ” ለማለታቸው ምንም አይነት ተጨባጭ የሆነ መረጃ መገኘት አልተቻለም።

ሶስተኛው በክሪስ ሃኒ የተነገረ የተባለው አባባል “እኔ የምፈራው ደቡብ አፍሪካን ነፃ ያወጡ ሰዎች በከተማው መሀል ማርቼዲስ እና ቤንዝ እየነዱ እና የሀገሪቱን ሀብት እየበዘበዙ በቅንጡ ቤተ-መንግስት ውስጥ እየኖሩ ሀብትን እንዳያካብቱ ነው።” የሚል ነበር።

ይህ ንግግር ትክክለኛው መሆኑ ተረጋግጧል። ይህም በፖለቲከኛው በፈረንጆቹ ጥቅምት 29 ቀን 1992 ዓ.ም የተነገረ እንደሆነ ሲረጋገጥ፡ የደቡብ አፍሪካው ኮሙኒስት ፓርቲ አመራር የሆኑት ክሪስ ሃኒ ከመገደላቸው ከ6 ወር በፊት የተናገሩት እንደሆነ ተረጋግጧል።
#የተለወጠ_ምስል
ምስሎች የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ፣ ስሜትን ለመኮርኮር እንዲሁም ሀሳብን ለማስቀየር ይውላሉ። ከዚህ ባለፈ ሰዎችን የማሳመን እና የማደናገር ሚናቸው ከፍተኛ ነው። ይህን ተከትሎ አውዳቸውን የሳቱ፣ የተቀናበሩ እና የተቀየሩ ምስሎች ሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎችን ለማሰራጨት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

መረጃዎችን ከማጋራታችን በፊት እውነት መሆናቸውን እናረጋግጥ!
👍1
#የጥንቃቄ_መልዕክት
#Alert

ከትላንት ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በማህበራዊ ሚድያ በተለይም በፌስቡክ ላይ “የፌደራል መንግስት በአማራ ክልል ላይ በፈፀመው የአየር ድብደባ እንስሳት በዚህ መልኩ ተቃጥለዋል” በሚል ፅሁፍ ስር ይህ ምስል በስፋት ሲዘዋወር ቆይቷል።

ነገር ግን ምስሉ ሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም “በጨንቻ ዙሪያ ወረዳ በዶኮ ካሌ ቀበሌ በልዩ ስሙ ኤተሎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቀን 23/08/2015 ዓ/ም ከምሽቱ ሦስት ሠዓት አካባቢ የተከሰተ የእሳት አደጋ በእንሰሳትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።" በሚል ፅሁፍ ስር ከሌሎች ምስሎች ጋር ተጋርቶ ነበር።

ስለዚህ በአማራ ክልል ግጭት እንዳለ ቢነገርም ይሄንን ምስል በክልሉ የአየር ድብደባ እየተደረገ እንደሆነ አያሳይም።
👍1
📣 Calling all Ethiopian journalists! 📰🎙
Inform Africa, in partnership with @Africa Check, proudly presents a transformative workshop: "Fact-checking and Verification Masterclass for Journalists." 🌍🔎

📅 Dates: 22 to 23 June 2023
Time: 9 am to 4 pm
📍 Venue: To be confirmed

Seize this incredible opportunity to enhance your fact-checking skills and become a trusted source of information in the world of journalism. 📚
🔒Limited Spaces Available! Only committed participants who can attend the full two-day session should apply.

✍️: Fill this form now
https://docs.google.com/forms/d/1EgpiTS82mv-71pxVGefmrKZjBQ0Szl7Pul2tc2X_TwA/edit
👎1
Opportunities are still open for participants from Addis Ababa.

Inform Africa, in collaboration with Africa Check, is delighted to announce an empowering workshop: Fact-checking and Verification Masterclass for Journalists. We have limited slots remaining for individuals from Addis Ababa. Don't delay, register today!
The workshop will take place
Dates: 22 to 23 June 2023
Time: 9 am to 4 pm
Venue: Best Western Plus Pearl Addis
Register Now: https://lnkd.in/eWNGJZSD
1