HaqCheck
428 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
You can register here!!!

https://forms.gle/hApVfxw9PXPBfaE49
👍3
Interested Applicants Can Register Using The Form Below

https://forms.gle/hApVfxw9PXPBfaE49
#Happeningnow
An online session on fact-checking and media literacy for journalists and human defenders. Learn to distinguish fact from fiction in today's world of misinformation.
#FactChecking #MediaLiteracy #Journalism #HumanRightsDefenders
2
በማህበራዊ ሚድያዎች ከሚዘዋወሩት ሀሰተኛ መረጃዎች መካከል የተቀነባበሩ ወይም የተለወጡ ምስሎች ይገኙበታል። የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መረጃን ለማጣራት እንደሚውሉት ሁሉ መረጃዎችን በማዛባት እና ለውጥ በማድረግ ሌላ ትርጉም እንዲሰጡ በማድረግ ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ። ከሰሞኑ በቱርክ እና በሶርያ ድንበር አካባቢ ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተያይዞ ሀሰተኛ መረጃዎች ሲዘዋወሩ ነበር።

ከሀሰተኛ መረጃዎቹ መካከል ፌስቡክ እና ኢንስታግራምን ጨምሮ በሌሎች የማህበራዊ ሚድያ አማራጮች ላይ “በቱርክ የሚገኙ አንድ ኢማም በፍርስራሽ ውስጥ የነበሩ 3 ሰዎችን ያዳነውን ውሻ እጅ ሲስሙ” በሚል ፅሁፍ ስር አንድ ምስል በስፋት ሲዘዋወር ነበር። ነገር ግን ምስሉ በፈረንጆቹ 2011 ተጋርቶ የነበረና ቶማዝ ጀስኪ (Tomasz Jaeschke) በሚል ስም የሚጠራ የሀይማኖት አስተማሪን የሚያሳይ ነው።
👍1
Types of mis&disinformation
UNESCO, in collaboration with Inform Africa, organized a training session on combating hate speech and disinformation for community radio journalists under the theme "Strengthening the capacity of community radio in peace building, countering hate speech and disinformation." 
1
#የጥንቃቄመልዕክት

በምስሉ ላይ ያለው አጭር የፅሁፍ መልዕክት ቁጥር በአሁኑ ሰዓት ለቦረና እርዳታ ማሰባብሰቢያ የሚውል አይደለም

በመጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ ከ12 ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት አንድ የፌስቡክ ገፅ በቦረና አካባቢ ለተከሰተው ድርቅ የገቢ ማሰባሰቢያ እናድርግ በማለት በኦሮሞ አርቲስቶች ስም ከኢትዮ-ቴሌኮም 655 የሚል አጭር የፅሁፍ መልዕክት ቁጥር አንደተፈቀደ እና በተጨማሪም እሱ 100 ብር ያስገባበትንና የምስጋና መልዕክት እንደደረሰው የሚያሳይ ስክሪን ሾት አብሮ አጋርቶ ነበር። እንዲሁም ሌሎች ይህን ዘመቻ እንዲቀላቀሉት ጠይቋል።

በተጨማሪም Oromoo fi Oromiyaa በሚባል እና ወደ 213ሺህ አባላት ያሉት የፌስቡክ ግሩፕ ላይ መልዕክቱን ተጋርቷል። ይህ የተጋራው ፖስት ብዙ ግብረመልሶችን ማግኘት ችሏል።

ሀቅቼክ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞች አገልግሎት ማዕከል የደወለ ሲሆን ፤ በአሁኑ ሰዓት በዚህ ቁጥር ምንም አይነት እርዳታ እየተሰባሰበ እንዳልሆነ ኢትዮ ቴሌኮን አሳውቆናል። የተባለው ቁጥር መልዕክት ሲላክበት ‘በኋላ ላይ ይሞክሩ’ የሚል መልስ እንደሚሰጥም ሀቅቼክ አረጋግጧል።

በመሆኑም በእንደዚህ አይነት መልዕክቶች ምክንያት ብዙ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች እርዳታውን ሳያገኙ ሊቀሩ ስለሚችሉ ለዕርዳታ የሚዘጋጁ አጭር የመልዕክት መላኪያ ቁጥሮችን ጠንቅቀን ማወቅ፣ ማጣራት እና እራስንም ሆነ ሌሎችን ከተሳሳተ መረጃ መጠበቅ ይኖርብናል።

ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች የዕርዳታ አማራጮችን በመጠቀም ለተቸገሩ ወገኖች መድረስ ይቻላል።

ባጣራነው መረጃ መሠረት በአሁኑ ሰዓት በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እርዳታ ለማድረግ በቀይ መስቀል አጭር የፅሁፍ መልዕክት 9400 ላይ እርዳታ እየተሰባሰበ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።