HaqCheck
428 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከሰሞኑ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አውታሮች ላይ “የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሁለተኛ ጊዜ በህዝብ ፊት በጥፊ እንደተመቱ እንደሚያሳይ ተነግሮ አንድ ቪድዮ ሲዘዋወር ነበር።”

አንዳንድ በውጭ ሀገር የሚገኙ የፌስቡክ ገፆችን ጨምሮ በሀገራችን ከ30ሺህ በላይ ተከታይ እስካላቸው ገፆች ድረስ ፕሬዝዳንቱን በድጋሚ በጥፊ የተመታችው በአንዲት እንስት እንደሆነ በመናገር ሲዘግቡ ቆይተዋል።
(https://t.me/alzarkawihabib/5235 ,
https://fb.watch/gZMgzjg4BJ/)

ሰኔ 8 ቀን 2021 እ.አ.አ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በደቡባዊ ፈረንሳይ ጉብኝት በሚያደርጉበት ወቅት እርሳቸውን ለመመልከት ከተሰበሰቡ ህዝቦች መሃል ዴምየን ታረል የተባለ ግለሰብ ፕሬዝዳንቱን በጥፊ እንደመታቸው የሚያሳዩ የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ተለቀዋል ( https://fb.watch/gZM8Ozj0SD/ ) ። የዚህን ግለሰብ ድርጊት ተከትሎ የፈረንሳይ ፍ/ቤት በግለሰቡ ላይ የ18 ወራት እስር ፈርዶበት የነበረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የእስር ጊዜውን ወደ 4 ወራት ቀንሶለት ነበር።

ሀቅቼክ በቅርቡ የተሰራጨውን ቪድዮ ለማጣራት ባደረገው ጥረት ቪድዮው የዛሬ አመት በፕሬዝዳንቱ ላይ የተፈፀመው ድርጊት መሆኑን አረጋግጧል። ሃቅቼክ በሁለቱ ቪድዮዎች ውስጥ ያሉትን ግለሰቦች፣ የነበሩበትን አካባቢ እና በቦታው የነበሩ ነገሮችን አጥንቶ ቪድዮው በወቅቱ በተለየ አቅጣጫ የተቀረፀ እንደሆነ ማረጋገጥ ችሏል።
👍1
A Facebook page with more than 38 thousand followers shared a post, claiming that the pictures are of a design of a satellite town to be built in Addis Ababa. The post also states that the satellite town (aka the Chaka Project) covers a large swath of land stretching from around Entoto to Tafo.

However, HaqCheck inspected the images and rendered them as False.

http://bit.ly/3gwo0Ms
👍1
ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚድያ አካውንቶች (ቦቶችን) መለየት ከምንችልባቸው መንገዶች መካከል ፦

የአካውንቱን ስም በጥንቃቄ መመልከት

ብዙውን ጊዜ በቦት የሚንቀሳቀሱ የማህበራዊ ሚድያ አካውንት ስሞች የፊደሎች(Spelling) መዘበራረቅ ይታይባቸዋል።

የአካውንቱን የፕሮፋይል ምስል መመልከት

እነዚህ አካውንቶች የፕሮፋይል ምስል የላቸውም? ወይስ ባነሰ ጥራት እና ግለሰቡን ለመለየት የሚያዳግት ነው? እንደዚህ ከሆነ ይጠንቀቁ ምክንያቱም የተመለከቱት አካውንት ቦት ሊሆን ይችላል። ብዙ የሀሰት አካውንቶች ከእውነተኛ ሰዎች ፎቶዎችን ይሰርቃሉ, ይህም ማለት ጽሑፎቻቸውን ስናካፍል የተሳሳቱ መረጃዎችን መጋራት ብቻ ሳይሆን በምስሉ ላይ ያለውን እውነተኛውንም ሰው እየጎዳን ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ ይኖርብናል።

የአካውንቱን እንቅስቃሴ መመልከት

ተጠቃሚው ማህበራዊ ሚድያውን በቅርቡ ነው የተቀላቀለው?

የፕሮፋይል ምስል ፣ የማህበራዊ ሚድያው ልዩ ስያሜ (handle) እና የስክሪን ስሙ መመሳሰሉን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

ታዲያ የእነዚህን የሀሰተኛ የማህበራዊ ሚድያ አካውንቶችን እንቅስቃሴ መርምረው የሚያጣሩ የኦንላይን ሳይቶች ሲኖሩ ከነዚያም መካከል
( https://botometer.osome.iu.edu/ እና https://foller.me/ ) ይጠቀሳሉ።
👍1
#Alert: The image doesn't show a donkey looted by Eritrean troops from Tigray

On Nov 28, 2022, a Facebook post was made sharing a tweet screenshot with an image that shows a donkey in a minivan and a short text implicitly claiming that Eritrean troops looted the donkey in the minivan from Tigray.

The text on the screenshot picture reads, “When there is nothing left to take…” and it used an emoji indicating the minivan’s license plate.

However, HaqCheck confirmed that the image doesn't prove the claim that the donkey shown in the minivan was looted by Eritrean soldiers from Tigray. The license plate of the car was intentionally altered to support the claim.

The image was first published on Reddit with the description, “This donkey getting a ride home in a minivan” on 24 August 2019.

The same image with a similar claim was debunked by HaqCheck back in January 2021. Here is the previous fact-checking article.
👍2
ሙሉ መረጃውን ለማንበብ

ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3ukj4O8
👍1
ሊንክ በመጠቀም የሚደረጉ የመረጃ ምንተፋዎችን እንዴት መከላከል ይቻላል?

የመረጃ መንታፊዎች ማስፋንጠርያ ሊንኮችን በመላክ የግል መረጃን ይመነትፋሉ።

ስለዚህ አንድ ሊንክ ሲላክሎት ወይም ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲመለከቱ ሊንኩ መረጃን ለመመንተፍ የተሰራ ሊሆን ስለሚችል እነዚህን እርምጃዎች መውሰድ ያስፈልጋል፡-

በጥንቃቄ መመልከት

ማንኛውም አይነት ማስፈንጠርያ ወይም ሊንክ ሲላክልዎ ወይም ሲያጋጥምዎ በጥድፍያ አለመንካት ያስፈልጋል። ሊንኩን በጥንቃቄ መመርመር ተገቢ ነው። ያንን ሊንክ ከምያውቁት ሰው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በማህበራዊ ሚድያ በውስጥ መስመር ሊላክሎት ይችላል። ማንኛውንም ሊንክ ማመን የለብዎትም፤ ሊንኩ ከየት እንደተላከ በጥንቃቄ ማየት ይኖርብዎታል።

ማመሳከር

ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሰዎችን ቀልብ ለመሳብ የተለየ ፅሁፍ የያዙ መንታፊ ሊንኮች ይታያሉ። በፅሁፍ ከላይ የሚነበበው እና ማስፈንጠርያ ሊንኩ የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ከላይ ያለው ፅሁፍ ስለሽልማት ፣ ስለትምህርት እድል ወዘተ ሊሆን ይችላል። ይህ አሰራር ሰዎች ከላይ በሚያነቡት ፅሁፍ ተሸውደው ሊንኩን በጥድፍያ እንዲነኩ ለማስጎምጀት ታልሞ የተዘጋጀ ነው።

ስለዚህ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሊንክ ሲያዩ ከመንካትዎ በፊት በፅሁፉ የሚነበበው ሀሳብ እና ሊንኩን አንድ አይነት መሆኑን ማመሳከር ይኖርቦታል።

የግል መረጃን አለመስጠት

የመረጃ መንታፊዎች እውነተኛ ያልሆኑ ማስፈንጠርያ ሊንኮችን በመላክ የሰዎች የግል መረጃን ይመነትፋሉ። ለምሳሌ አንድ ሊንክ ከነኩ በኋላ ያንን ሊንክ የግል መረጃዎን እንዲያስገቡ ሊጠይቆት ይችላል።

የኢሜይል አድራሻዎ ፣ የይለፍ ቃል ወይም ፓስዋርድ ፣ የባንክ አካውንት ፣ የማህበራዊ ሚድያ አካውንት የመሳሰሉ የግል መረጃዎች እንዲሰጡ ሲጠየቁ ሊንኩ እውነተኛ መሆኑን ሳያረጋግጡ መስጠት የለብዎትም።
👍1
A Facebook page shared a viral video on Dec 4, 2022, claiming that ethnic Amharas were killed in Wollega, Oromia. The video that was published by the post to support the claim shows people transporting dead bodies with stretchers.

Yet, HaqCheck confirmed that the video doesn't show people recently killed in Wollega.

https://bityl.co/G4Lf
👍2
ከ67 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅን ጨምሮ በሌሎች የማህበራዊ ሚድያ አማራጮች ላይ አንድ ምስል በስፋት ሲዘዋወር ቆይቷል። ምስሉ የቀድሞውን የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ የተጣመረ የተቃውሞ የእጅ ምልክት የሚያሳዩበት ምስል የተሰራጨ ሲሆን ይህ የፌስቡክ ገፅ ምስሉን ካሰራጨ ጊዜ ጀምሮ ከ64 ሺህ በላይ ግብረመልስን ሲያገኝ ከ2ሺህ ጊዜ በላይ መጋራት ችሏል።

ይህን እንጂ ምስሉ ትክክለኛ የአቶ ለማ መገርሳ ሳይሆን የተቀናበረ መሆኑን ሀቅቼክ ያረጋገጠ ሲሆን ይህ የፌስቡክ ገጽ ይህን ምስል ካጋራበት ፅሁፍ ስር የ#photoeditingchallenge የሚል መግለጫ ተጠቅሟል። ይህ የሚያሳየው ሀሰተኛ መረጃ የሚሰራጭበት መንገድ እየረቀቀ መምጣቱን ነው። በዚህም ምክንያት ይህን መግለጫ የማያስተውሉ ብዙ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ሰዎች በማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚሰራጩ መረጃዎችን በጥንቃቄ ሊመለከቱ ይግባል።
👍1
Subscribe to HaqCheck's weekly and monthly newsletters. Get our weekly disinformation summaries, monthly analyses, and yearly information disorder trend research for free.

Go to www.HaqCheck.org and click the subscribe button at the bottom of the page
A Facebook page shared an image claiming that the Moroccan national football team displayed the flag of the Ogaden National Liberation Front (ONLF) while celebrating a victory in the FIFA World Cup being held in Qatar. But, the image presented to support the claim was altered. The original image shows the Moroccan team flying the Palestinian flag.

https://bityl.co/GAfn
ታህሳስ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ አንድ የፌስቡክ ገፅ “ወላጅ ልጆቹን ትምህርት እንዲቀስሙለት ትምህርት ቤት ይልካል ባለ ጊዜ እንዲህ ያደርጋል” የሚል ፅሁፍን በማያያዝ አንድ ምስልን አጋርቶ ነበር።
ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ የፌስቡክ ፖስት ከ400 ጊዜ በላይ መጋራት ችሏል።

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉ በቅርቡ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከኦሮሚያ ክልል ባንዲራ ጋር ተነስቶ ከነበረው ግጭት ጋር የሚያያዝ እንዳልሆነ አረጋግጦ ምስሉን ሀሰት ብሎታል።

https://bityl.co/GJtO