HaqCheck
428 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
A Facebook page with more than 700 thousand followers shared a video on Oct 5, 2022, captioned, “Please have a look at this video showing how the Abiy regime [Federal Government] is sending its airforce commandos from Debre Zeit air force base to Asmara[Eritrea], it is not fair to deploy soldiers while talking about peace.
Whatsoever, the Army of TDF [Tigray Defense Forces] will not be inattentive.”
However, HaqCheck inspected the video and rendered it False.

https://bit.ly/3rL7MkB
ይህ ቪድዮ መንግስት ወታደሮቹን ከደብረዘይት አየር ሀይል ወደ አስመራ ሲያጓጉዝ ያሳያል?

ከ700ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም “የአብይ መንግስት ወደ አስመራ ከደብረዘይት አየር ሀይል ግቢ በአንቶኖቭ ወታደሮችን ሲያመላልስ የሚያሳይ ቪድዮ ተመልከቱ። ስለ ሰላም እያወራን ወታደር ማሰማራት ትክክል አየደለም ለማንኛውም ሰራዊታችን TDF አይዘናጋም።” የሚል ፅሁፍ በማያያዝ አንድ የ25 ሰከንድ ርዝመት ያለው ቪድዮ አጋርቶ ነበር።”ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ የፌስቡክ ፖስት ከ11ሺህ በላይ እይታን ማግኘት ችሏል።

ሀቅቼክ በፌስቡክ ገፁ ላይ የተጋራውን ቪድዮ ለማጣራት ባደረገው ጥረት ነሀሴ 23 ፤ 2014 ዓ.ም የ4 ደቂቃ ከ5 ሴኮንድ ርዝመት ባለው ቪድዮ ውስጥ አግኝቶታል። ይህ ቪድዮም ከ9ሺህ በላይ ተከታይ ባለው የፌስቡክ ገፅ ላይ “የኢፌዴሪ የአየር ሀይል ልምምድን ተመልከቱ” በሚል የፅሁፍ መግለጫ ተጋርቶ ተገኝቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ሀቅቼክ በሁለቱ ቪድዮዎች ውስጥ ያሉ ተመሳሳይ ምስሎችን ማግኘት የቻለ ሲሆን በነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ሀቅቼክ በፌስቡክ ገፁ የተጋራውን ቪድዮ ሀሰት ብሎታል።

https://bityl.co/F0BX
👍2
አንጋፋው የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ የሆነው አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል የሚሉ የተለያዩ የፌስቡክ ፖስቶች ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። አርቲስቱ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ያለ ሲሆን ሀቅቼክ ስለሁኔታው ለማጣራት ባደረገው ጥረት  አርቲስቱ ከዚህ አለም በሞት ተለየ የሚለው ወሬ ሀሰት መሆኑን ሀቅቼክ ማረጋገጥ ችሏል።
1
Week two summary of social and mainstream media information disorder during the month of October.

https://haqcheck.org/october-week-two-summary/
Does the image show the new national palace being built in Addis Ababa?
ከ40 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የትዊተር አካውንትን ጨምሮ የተለያዩ የማህበራዊ ገፆች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) እየተባለ የሚጠራውን ቡድን ባንዲራ የተሸከሙ አዛውንትን ምስል ነው ተብሎ ሲያጋሩ ቆይተዋል።

ይህ ምስል ከዚህ ቀደምም በሌሎች ሀገሮችም ሰራጭቶ የነበረ ሲሆን ለምሳሌ ያክል ከዚህ ቀደም በአፍጋኒስታን በታሊባን ታጣቂዎች እና በአፍጋኒስታን መንግስት መካከል ተከስቶ በነበረው ግጭት ላይ እኚህ አዛውንት የአፍጋኒስታን መንግስትን ብሄራዊ ባንዲራን እንደተሸከሙ ተደርጎ በስፋት ሲዘዋወር ነበር።

ነገር ግን ሀቅቼክ ምስሉን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ትክክለኛ ምስሉን በአንድ የትዊተር አካውንት ላይ ተጋርቶ ያገኘው ሲሆን የያዙት ባንዲራም የታሊባን (በነጭ ባንዲራ ላይ በጥቁር ፅሁፍ ያረፈበት) እንደሆነ የተረጋገጠ ሲሆን በምስሉ ላይ የታዩት ግለሰብ ከተሸከሙት ነጭ ባንዲራ ጋር የሚያሳይ እና በትክክል የት ቦታ እንደተቀረጸ የማይታወቅ ቪድዮ ተገኝቷል። https://bit.ly/3Un5J2Z

በእነዚህ ምክንያቶች ሀቅቼክ በማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲዘዋወር የነበረውን ምስል በፎቶሾፕ የተቀናበረ መሆኑን አረጋግጦ ሀሰት ብሎታል።
ሀቅቼክ የህወሓት ታጣቂዎች ያስረከቡት መሳሪያ ተብሎ የተጋራውን ምስል ህዳር 23 ፤ 2013 ዓ.ም በፋና ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ በተጋራ እና “በመቐለ ከተማ በተደረገ ብርበራ የጥፋት ቡድኑ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ዴፖ ተይዟል” የሚል ፅሁፍ ባለው ቪድዮ ውስጥ አግኝቶታል።

bit.ly/3Tsc5g5
👍1
ኢሜይልዎ ወይም የሞባይል ስልክዎ ተጠልፎ ያውቃል?

መልሱን እዚህ ድረገፅ ላይ ማግኘት ይችላሉ (https://haveibeenpwned.com)

በመጀመሪያ
- www.haveibeenpwned.com ወደሚል ድረገፅ ይሄዳሉ።

በመቀጠል - የኢሜይል ወይም የስልክ አድራሻዎን ያስገባሉ።

በመጨረሻም - የድረገፁ የምርመራ ውጤት ሁለት አይነት መልሶችን ሊያሳየን ይችላል

1, የኢሜይል ወይም የስልክ አድራሻዎ ተጠልፎ የሚያውቅ ከሆነ “oh no - pwned” የሚል መልስን የሚያሳየን ሲሆን

2, የኢሜይል ወይም የስልክ አድራሻዎ ተጠልፎ የማያውቅ ከሆነ “Good news - no pwnage found” የሚል መልስን ያሳየናል።
👍3
ከሰሞኑ በተለያዩ የማህበራዊ ገፆች ላይ “ከእንግሊዝ ኤንባሲ ጀርባ ያለውን ተራራማ ጫካ ይዞ ፣ እንጦጦን አካሎ ፣ የሱሉልታን ግርጌ ይዞ ፣ ጣፎ ደርሶ ወዲህ የሚመለስ ግዙፍ ፕሮጀክት” በሚል የፅሁፍ መግለጫ ስር የተለያዩ ምስሎች በስፋት ሲዘዋወሩ ቆይተዋል።

ባሳለፍነው የኢትዮጵያውያን 2014 ዓ.ም የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት 49 ቢልዮን ብር የሚፈጅ አዲስ ቤተመንግስት ሊገነባ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገልፆ የነበረ ሲሆን ከታላቁ የህዳሴ ግድብ በመቀጠል ብዙ ወጪ የሚወጣበት ይህ ፕሮጀክት መንግስት ባስቀመጠው የ10 አመት መሪ የልማት ዕቅድ ውስጥ “የጫካ ፕሮጀክት” በሚል ፕሮጀክት ስር የሚገነባ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች ወጥተው ነበር።

ይሁን እንጂ ከሰሞኑ የቤተመንግስቱ እና በዙሪያው የሚሰራው ፕሮጀክት እንደሆነ ያሳያል በሚል ሲዘዋወር የቆየው ምስል እውን የተባለውን ቤተ መንግስት የሚያሳይ ሳይሆን ስቴፋኖ ቦአሪ በተባለ የጣልያን አርክቴክት በሜክሲኮ ውስጥ የምትገኝና ካንኩን ለምትባል ከተማ (Smart city) ለመገንባት የተነደፈ ንድፍ ሲሆን የሚገነባው ከተማ ወደ 557 ሄክታር እንደሚሸፍን በአርክቴክቱ የተገለፀ ሲሆን በውስጡ ወደ 7.5 ሚልዮን ዛፎች እንዲሁም እፅዋቶች እንዲኖረውም ታስቦ የወጣ ንድፍ ነው።

በዚህም መሰረት ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገነባ ግዙፍ ፕሮጀክት ተብሎ ሲዘዋወር የነበረውን ምስል ሀቅቼክ በመርመር የተሳሳተ እንደሆነ አረጋግጧል።
👍4
የትዊተር ተጠቃሚዎች የተሳሳተ መረጃን እንዲያርሙ የሚያስችል አሰራር አስጀመረ

የማህበራዊ መገናኛ ድርጅቱ ትዊተር የትስስሩ ተጠቃሚዎች የተሳሳተ መረጃን እንዲያርሙ የሚያስችል አሰራር አስጀምሯል። አሰራሩ ትዊተር ላይ የሚለቀቁ መረጃዎችን እውነትነት በፍቃደኛ ተጠቃሚዎች እንዲጣራ የሚፈቅድ ነው።

በአዲሱ አሰራር መሠረት የትዊተር ተጠቃሚዎች በማህበራዊ ትስስሩ ገፅ የሚለጠፉ መረጃዎች ስር አጭር የአውድ ማስታወሻ ወይም ተጨማሪ የማስተካከያ መረጃ እንዲፅፉና እንዲፃፍ ሀሳብ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል። አንድ ማስታወሻ ከተፃፈ በኋላ ደግሞ አጋዥ መሆኑ እና አለመሆኑ በፍቃደኛ አባላቶቹ በሚሰጥ ደረጃ ወይም ሬቲንግ ይወሰናል።

እሄን በተጠቃሚዎች አጭር የአውድ ማስታወሻ በመፃፍ የመረጃን እውነትነት የማጣራት ዘዴ በተለይ በአሜሪካን ሀገር እያደገ እየመጣ ያለው መረጃ-አጣሪዎችን ያለማመን ሁኔታ መልስ ይሆናል ተብሏል።

አሜሪካዊዊው ቱጃሩ ባለሀብት ኤሎን ማስክ ትዊተርን በ44 ቢልየን ዶላር ከገዙት በኋላ የተለያዩ ማሻሻያዎች እንዳደረጉ ሲዘገብ ቆይቷል።

እሄንን አሰራር ከአንድ አመት በፊት የተጠነሰሰ ቢሆንም በቅርቡ ትዊተር ላው ተግባራዊ ሆኗል።
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከሰሞኑ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አውታሮች ላይ “የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሁለተኛ ጊዜ በህዝብ ፊት በጥፊ እንደተመቱ እንደሚያሳይ ተነግሮ አንድ ቪድዮ ሲዘዋወር ነበር።”

አንዳንድ በውጭ ሀገር የሚገኙ የፌስቡክ ገፆችን ጨምሮ በሀገራችን ከ30ሺህ በላይ ተከታይ እስካላቸው ገፆች ድረስ ፕሬዝዳንቱን በድጋሚ በጥፊ የተመታችው በአንዲት እንስት እንደሆነ በመናገር ሲዘግቡ ቆይተዋል።
(https://t.me/alzarkawihabib/5235 ,
https://fb.watch/gZMgzjg4BJ/)

ሰኔ 8 ቀን 2021 እ.አ.አ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በደቡባዊ ፈረንሳይ ጉብኝት በሚያደርጉበት ወቅት እርሳቸውን ለመመልከት ከተሰበሰቡ ህዝቦች መሃል ዴምየን ታረል የተባለ ግለሰብ ፕሬዝዳንቱን በጥፊ እንደመታቸው የሚያሳዩ የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ተለቀዋል ( https://fb.watch/gZM8Ozj0SD/ ) ። የዚህን ግለሰብ ድርጊት ተከትሎ የፈረንሳይ ፍ/ቤት በግለሰቡ ላይ የ18 ወራት እስር ፈርዶበት የነበረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የእስር ጊዜውን ወደ 4 ወራት ቀንሶለት ነበር።

ሀቅቼክ በቅርቡ የተሰራጨውን ቪድዮ ለማጣራት ባደረገው ጥረት ቪድዮው የዛሬ አመት በፕሬዝዳንቱ ላይ የተፈፀመው ድርጊት መሆኑን አረጋግጧል። ሃቅቼክ በሁለቱ ቪድዮዎች ውስጥ ያሉትን ግለሰቦች፣ የነበሩበትን አካባቢ እና በቦታው የነበሩ ነገሮችን አጥንቶ ቪድዮው በወቅቱ በተለየ አቅጣጫ የተቀረፀ እንደሆነ ማረጋገጥ ችሏል።
👍1