HaqCheck
428 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
A Facebook page with more than 130 thousand followers shared a post, captioned, “ two tanks were destroyed by an air raid at Alamata which were being loaded to Kobo.” However, HaqCheck inspected the image used to support the claim and rendered it False.

https://bit.ly/3eU7dlj
A Twitter account shared a post on Sep 13, 2022, captioned, "Ethiopian drones attacked Mekelle and that one key leader of Tigray People’s Liberation Front (TPLF) was executed."
by the time this article is published The post had more than 700 retweets.
However, HaqCheck inspected the image and rendered it False.

https://bit.ly/5qwert
ቪዲዮው ዳግም በተቀሰቀሰው ጦርነት የተማረኩ የመከላከያ ሰራዊቶችን ያሳያል?
ከ 7 ሺ በላይ ተከታይ ያለው የቲውተር አካውንት መስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም በስፋት ሲዘዋወር የነበረ አንድ ቪዲዮ አጋርቷል። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ዳግም በተቀሰቀሰው ጦርነት ኢትዮጵያውያን የጦር እስረኞች ለሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኃይሎች እጃቸውን ሲሰጡ በማለት ተጋርቷል።
ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ ቪዲዮ ከ6 መቶ ጊዜ በላይ የተጋራ ሲሆን በትዊተር ገጽ ላይ ብቻ ከ63 ሺህ በላይ ሰዎች ተመልክተውታል።
ሀቅቼክ ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል ከዚህ ቀደም ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም በአሜርካ ድምጽ አማርኛ የፌስቡክ ገጽ ላይ “የትግራይ ክልል መንግሥት የጦር ምርኮኞች እንዲለቀቁ መወሰኑን አስታወቀ” በሚል ዜና ስር ጥቅም ላይ የዋለ መሆኑን አረጋግጧል።
ስለሆነም ሀቅቼክ የቲውተር ፖስቱ መረጃውን እንዲደግፍለት የተጠቀመው ቪዲዮ የቆየ በመሆኑ ሀሰት ብሎታል።

https://bityl.co/EgRs
ከ120 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ ነሀሴ 28 ፤ 2014 ዓ.ም ላይ “በራያ ግንባር ከጠላት የተማረከ 430 ክላሽንኮቭ እና 3 ዲሽቃ ፤ ጠላት የጥምር ጦሩ ብርቱ ክንድ መቋቋም ያልቻለው ሀይል እየተማረከ ነው” የሚል ፅሁፍ በማያያዝ አንድ ምስልን አጋርቶ ነበር።

ሀቅቼክ ምስሎቹን ትክክለኛነት ለማጣራት ባደረገው ጥረት ምስሎቹን በአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን የዩቲዩብ ቻናል ላይ ጥር 25 ፤ 2014 ዓ.ም በቀረበ የዜና ቪድዮ ላይ አግኝቷቸዋል። ይህ ጽሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ የዩቲዩብ ቪድዮው ከ150ሺህ ጊዜ በላይ ታይቷል።

የዜና ቪድዮው፣ “በመከላከያ ሰራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ጥምር ሃይል አማካኝነት በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ላይ በተወሰደው ርምጃ ከ100 በላይ የሚሆኑ አባላቱ ተደምስሰዋል” በሚል ርዕስ የቀረበ ሲሆን በተጨማሪም በቪድዮው ተማረኩ ያላቸውን የሽብር ቡድኑን አባሎች ያሳያል። በዚህም መሰረት መረጃውን ለመደገፍ ከፖስቱ ጋር የተያያዙትን ምስሎች ሀቅቼክ ሀሰት ብሏቸዋል።

https://bityl.co/Ekwj
ከሰሞኑ ፌስቡክ እና ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አውታሮች የተጋራ አንድ ቪድዮ “የፌደራል መንግስt ወታደራዊ ድሮኖችን በመጠቀም በህወሓት አመራሮች ላይ ጥቃት ሲፈፅም የሚያሳይ ቪድዮ” በሚል መግለጫ ሲዘዋወር ተስተውሏል።
ፌስቡክ ላይ ተጋርቶ የነበረው ቪድዮ ከግማሽ ሚልዮን በላይ ተመልካች ሲያገኝ በዩቲዩብ ላይ ተጋርቶ የነበረው ቪድዮ ከመቶ ሺህ በላይ እይታ ማግኘት ችሏል።የፊደራል መንግስት እየወሰደ ያለውን ወታደራዊ እርምጃ ተከትሎ በፌደራል መንግስት አማካኝነት እየተደረገ ያለ የድሮን ጥቃት በማለት የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች [ቪድዮውች] ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። ይህ በፌስቡክና ዩቲዩብ ጨምሮ የተሰራጨው ቪድዮም ከነዚህ አንዱ ነው።

በቪድዮው መሃል ያለው የቪድዮው ክፍል በፈረንጆቹ 2020 በአዘርባጃን እና በአርሜንያ መካከል የተከሰተውና ናጎርኖ ካራባህ እየተባለ በሚጠራው ጦርነት የቱርክ ድሮኖች የነበራቸውን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ነው። ሀቅቼክ ቪድዮውን ለማግኘት ባደረገው ጥረት የቪድዮውን ክፍል መጋቢት 29 ፤ 2013 ዓ.ም በአንድ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ተጋርቶ አግኝቶታል።

በዚህም ምክንያትም ሀቅቼክ በፌስቡክ እና በዩቲዩብ ላይ ሲዘዋወር የነበረው ቪድዮ ሀሰት መሆኑን አረጋግጧል።

https://bityl.co/Ekx8
👍1
ከ 7 ሺ በላይ ተከታይ ያለው የትዊተር አካውንት መስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም በስፋት ሲዘዋወር የነበረ አንድ ቪዲዮ አጋርቷል። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ዳግም በተቀሰቀሰው ጦርነት ኢትዮጵያውያን የጦር እስረኞች ለሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኃይሎች እጃቸውን ሲሰጡ እንደሚያሳይ በፅሁፍ መግለጫው ይናገራል።

ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ ቪዲዮ ከስድስት መቶ ጊዜ በላይ የተጋራ ሲሆን በትዊተር ላይ ብቻ ከ63 ሺህ በላይ ሰዎች ተመልክተውታል። ነገር ግን ሀቅቼክ መረጃውን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ይህን ተንቀሳቃሽ ምስል ከዚህ ቀደም ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም በአሜሪካ ድምጽ አማርኛ የፌስቡክ ገጽ ላይ “የትግራይ ክልል መንግሥት የጦር ምርኮኞች እንዲለቀቁ መወሰኑን አስታወቀ” በሚል ዜና ስር የተጋራ መሆኑን ሀቅቼክ ማረጋገጥ ችሏል።

ስለሆነም ሀቅቼክ የትዊተር ፖስቱ መረጃውን እንዲደግፍለት የተጠቀመውን ቪዲዮ የቆየና ከተገለፀው ሁነት ጋር ተያያዥነት የሌለው በመሆኑ ሀሰት ብሎታል።

https://bityl.co/ElAn
መስከረም 20 ቀን አንድ የፌስቡክ አካውንት የኢትዮጵያ አየር ሀይል በሽሬ የሚገኘውን የህውሃት የጦር መሳሪያ ማከማቻ አንደመታ በትግረኛ ቋንቋ ከሚገልጽ ጽሁፍ ጋር ሶስት የተለያዩ ምስሎችን አያይዞ አውጥቷል። ይህም መረጃ ከ140 ጊዜ በላይ የተጋራ ሲሆን ከ130 ጊዜ በላይ ግብረ መልስንም ማግኘት ችሏል።

ሀቅቼክ መረጃውን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ምስሎቹ የቆዩ እና በሰሜኑ ክፍል ካለው ጦርነት ጋር ተያያዥነት እንደሌላቸው ያረጋገጠ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ምስሎቹ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በሚገኘው ጦርነት ላይ የተነሱ መሆናቸውን አረጋግጧል።

የመጀመርያው ምስል መጋቢት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ላይ በአንድ የዜና ድህረ ገጽ ላይ በዩክሬን የተመታ የሩሲያን ታንክ ለማሳየት ጥቅም ላይ የዋለ ፎቶ ሲሆን ፣ ሁለተኛው በተመሳሳይ ቀን የተመታን የሩሲያ ወታደራዊ መሳሪያን የሚያሳይ ምስል ሆኖ ተገኝቷል።ሶስተኛው ምስል ሚያዚያ 5 ቀን የዩክሬን ታጣቂ ሀይሎች በሩሲያ ወታደራዊ መሳሪያዎች ላይ ያደረሱትን ጥቃት በሚገልጽ የዜና ጽሁፍ ስር ተካቶ አግኝቶታል።

ስለሆነም ሀቅቼክ የፌስቡክ ፖስቱ ጽሁፉን እንዲደግፍለት የተጠቀማቸው ምስሎች የቀዩ በመሆናቸውና ከተጠቀሰው ሁነት ጋር የማይገናኙ በመሆናቸው የፌስቡክ ፖስቱን ሀሰት ብሎታል።
በከፊል ሀሰት ፡ ምስሎቹ በቅርቡ ከሽብር ቡድኖች የተያዙ የጦር መሳሪያዎችን አያሳይም

ከ50ሺህ እስከ 150ሺህ ድረስ ተከታይ ያላቸው የፌስቡክ ገፆች “በአደባባይ በዓላት ላይ ሁከት በመቀስቀስ ወደ ሀገራዊ ቀውስ እንዲሸጋገር ሲያሴሩ የነበሩ 166 የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።” በሚል ርዕስ አንድ ፅሁፍ በፌስቡክ ገፆቻቸው ላይ አጋርተው ነበር።

በተያያዘው የዜና ፅሁፍ ላይም ከሰሞኑን በኢትዮጵያውያን ከተከበሩት የመስቀል የደመራ ስነ-ስርዓት እና የኢሬቻ የአደባባይ በዓላት ጋር ተያይዞ የሽብር ተግባራትን በመፈፀም ሀገራዊ ቀውስ እንዲፈጠር በህቡዕ ሲያሴሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል እንዳስታወቀ ያስነብባል።

ሀቅቼክ ይህን ከሽብር ቡድን አባላቱ ተያዙ የተባሉትን መሳሪያዎች ያሳያል የተባለውን ምስል ለማጣራት ባደረገው ጥረት የመጀመሪያውን ምስል መስከረም 22 ፤ 2012 ዓ.ም በፋና ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ የእሬቻን በዓል ለማደናቀፍ ፣ የተለያዩ አካላት የራሳቸውን አጀንዳ ለመስፈጸም እና ለጥፋት ሊጠቀሙባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎችና ቦንምቦች ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በሚገልፅ ፅሁፍ ስር አግኝቶታል።

ሁለተኛውን ምስል ኢትዮኒውስ በተሰኘ አንድ ድረ-ገፅ ላይ በአማራ ክልል ገንዳውሃ ተብሎ በሚጠራ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረ ህገወጥ መሳሪያ በፖሊስ መያዙን በሚገልፅ ፅሁፍ ስር አግኝቶታል።

ሶስተኛውን ምስል ሚያዝያ 2 ፤ 2004 ዓ.ም ላይ በላቲን ቋንቋ በተፃፈ እና የሶስት ሀገራት ጥምረት በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ላይ በሚል ርዕስ በታተመ ፅሁፍ ውስጥ ተጋርቶ አግኝቶታል።

በነዚህም ምክንያቶች ሀቅቼክ ምስሎቹን መርምሮ የፌስቡክ ፖስቱን በከፊል ሀሰት ብሎታል።
ሀሰት ፡ ምስሉ በፌደራል እና ጥምር ሀይሎች አንገቱ የተቆረጠ ግለሰብን አያሳይም

መስከረም 26 ፤ 2015 ዓ.ም አንድ የፌስቡክ አካውንት በፌደራል መንግስቱ እና በህወሓት መካከል እየተደረገ ባለው ጦርነት በኢትዮጵያ ጥምር ጦር አንገቱ የተቆረጠ ሰው በማለት አጋርቷል።
ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉን ባደረገው ማጣራት ምስሉን ህዳር 13 ፤ 2013 ዓ.ም Nairaland.com በተሰኘ የናይጄሪያ ድረ-ገጽ ስር በኬንያ ውስጥ የሚፈፀሙ አደገኛ ወንጀሎች እና ግድያዎችን በሚያትት ፅሁፍ ስር ተጋርቶ አግኝቶታል።

በዚህም ምክንያት ሀቅቼክ ምስሉን አጣርቶ ሀሰት ብሎታል
Channel photo updated
A Facebook page with more than 700 thousand followers shared a video on Oct 5, 2022, captioned, “Please have a look at this video showing how the Abiy regime [Federal Government] is sending its airforce commandos from Debre Zeit air force base to Asmara[Eritrea], it is not fair to deploy soldiers while talking about peace.
Whatsoever, the Army of TDF [Tigray Defense Forces] will not be inattentive.”
However, HaqCheck inspected the video and rendered it False.

https://bit.ly/3rL7MkB
ይህ ቪድዮ መንግስት ወታደሮቹን ከደብረዘይት አየር ሀይል ወደ አስመራ ሲያጓጉዝ ያሳያል?

ከ700ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም “የአብይ መንግስት ወደ አስመራ ከደብረዘይት አየር ሀይል ግቢ በአንቶኖቭ ወታደሮችን ሲያመላልስ የሚያሳይ ቪድዮ ተመልከቱ። ስለ ሰላም እያወራን ወታደር ማሰማራት ትክክል አየደለም ለማንኛውም ሰራዊታችን TDF አይዘናጋም።” የሚል ፅሁፍ በማያያዝ አንድ የ25 ሰከንድ ርዝመት ያለው ቪድዮ አጋርቶ ነበር።”ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ የፌስቡክ ፖስት ከ11ሺህ በላይ እይታን ማግኘት ችሏል።

ሀቅቼክ በፌስቡክ ገፁ ላይ የተጋራውን ቪድዮ ለማጣራት ባደረገው ጥረት ነሀሴ 23 ፤ 2014 ዓ.ም የ4 ደቂቃ ከ5 ሴኮንድ ርዝመት ባለው ቪድዮ ውስጥ አግኝቶታል። ይህ ቪድዮም ከ9ሺህ በላይ ተከታይ ባለው የፌስቡክ ገፅ ላይ “የኢፌዴሪ የአየር ሀይል ልምምድን ተመልከቱ” በሚል የፅሁፍ መግለጫ ተጋርቶ ተገኝቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ሀቅቼክ በሁለቱ ቪድዮዎች ውስጥ ያሉ ተመሳሳይ ምስሎችን ማግኘት የቻለ ሲሆን በነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ሀቅቼክ በፌስቡክ ገፁ የተጋራውን ቪድዮ ሀሰት ብሎታል።

https://bityl.co/F0BX
👍2
አንጋፋው የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ የሆነው አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል የሚሉ የተለያዩ የፌስቡክ ፖስቶች ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። አርቲስቱ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ያለ ሲሆን ሀቅቼክ ስለሁኔታው ለማጣራት ባደረገው ጥረት  አርቲስቱ ከዚህ አለም በሞት ተለየ የሚለው ወሬ ሀሰት መሆኑን ሀቅቼክ ማረጋገጥ ችሏል።
1
Week two summary of social and mainstream media information disorder during the month of October.

https://haqcheck.org/october-week-two-summary/
Does the image show the new national palace being built in Addis Ababa?