HaqCheck
429 subscribers
324 photos
39 videos
541 links
HaqCheck is an Ethiopia based fact-checking project that verifies media content from social to the mainstream. We fact-check in English and on local languages widely spoken in the Horn of Africa.

https://haqcheck.org
Download Telegram
#የሀሰተኛመረጃጥቆማ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አውታሮች ላይ የሚዘዋወረውን ይህን ምስል ያጋሩ ፖስቶች አሜሪካዊው ቢልየነር ቢልጌትስ በተደረገለት አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ጋዜጠኛዋ ስለ ስኬቱ ሚስጥር በጠየቀችው ጊዜ አንድ ባዶ ቼክ አውጥቶ የፈለገችውን ያህል የገንዘብ መጠን እንድትፅፍ ቢነግራትም ጋዜጠኛዋ በተደጋጋሚ ቼኩን እንደመለሰች ያስነብባሉ። በመጨረሻም አሜሪካዊው ቢልየነር ቢልጌትስ የስኬቱ ሁሉ ሚስጥር እንደሷ ያገኛቸውን እድሎች አለማሳለፉ እንደሆነ እንደነገራትና ሊሰጣት የነበረውን ቼክ ተቀብሏት እንደቀደደው ፅፈዋል።

ይህ መረጃ በሀገራችን ኢትዮጵያ በቻ ሳይሆን በአለም ላይ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች ላይ ሲዘዋወር የቆየ ነው።

ነገር ግን ምስሉ የተወሰደው የተለያዩ ታዋቂ እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በማቅረብ ቃለ-ምልልሶችን በሚያደርገው እና This Morning በተሰኘው የቴሌቪዥን ሾው ላይ የነበረ ሲሆን ቪድዮው ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም በቴሌቪዥኑ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ተጋርቷል።

በፕሮግራሙ ላይም ስለ ቢልየነሩ የግል ጉዳዮች እና ስለሚያወጣቸው ወጪዎች የተጠየቀበት አጭር ፕሮግራም ሲሆን እነዚህ የማህበራዊ ሚድያ ፖስቶች እንደሚናገሩት በምስሉ ላይ ጋዜጠኛዋ የምትመልስለት ባዶ ቼክ ሳይሆን This Morning የሚል ፅሁፍ ያለበት ኩባያ በስጦታ መልክ ስታበረክትለት ነው።

ምስሉን ለማጣራት ሀቅቼክ ሙሉ ቪድዮውን የተመለከተ ሲሆን በቪድዮው ውስጥ ቢልጌት ለጋዜጠኛዋ የሰጣት ምንም አይነት ቼክ እንደሌለ አረጋግጧል። ከዚህ በተጨማሪ ቢልየነሩ ለጋዜጠኛዋ ቼክ እንዳቀረበላት የሚያሳይ ምንም መረጃ ማግኘት አልተቻለም።
👍1
#የሀሰተኛመረጃጥቆማ

ከሰሞኑን በተለያዩ የፌስቡክ ገፆች ላይ የሚዘዋወር የአንድ ሰው ምስልን በማጋራት ሰውየው የህወሓት ቃል አቀባይ የሆነው አቶ ጌታቸው ረዳ እንደሆነ ግምቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። ከዚህ በተጨማሪ በምስሉ ላይ የሚታየው ግለሰብ አንድ እግር የሌለው በመሆኑ ምስሉ በፎቶሾፕ የተቀነባበረ ነው ያሉም አልጠፉም።

ከዚህ ባለፈም ምስሉ ላይ የሚታዩትን የመከላከያ ሰራዊት ልብስ የለበሱ ግለሰቦች እና የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አርማ ያለበትን ወረቀት የተመለከቱ በበኩላቸው ምስሉ የጌታቸው ረዳ ሊሆን የሚችልበት ምንም ምክያንት የለም ሲሉ ተደምጠዋል።

ሀቅቼክም ይህን ከሰሞኑን አወዛጋቢ የነበረውን ምስል ለማጣራት ባደረገው ጥረት ምስሉ ከዚህ በፊት ነሀሴ 5 ቀን 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ ከሌሎች 6 ምስሎች ጋር ተጋርቶ አግኝቶታል። የፕሬስ ድርጅቱ ዜና የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት 75 ሚልዮን ብር የሚገመት የአይነት እና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የሚያስነብብ ሲሆን በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዣንጥራር አባይ እና የመከላከያ ሰራዊት ሚ/ር ዲኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉዊጅ በቦታው ተገኝተው እንደነበር ሪፖርቱ ያስነብባል።

ስለዚህም ሀቅቼክ ባደረገው መረጃውን የማጣራት ስራ ምስሉ የዛሬ አመት የተጋራ እንደሆነ እና ምስሉ በፎቶሾፕ የተቀነባበረ ሳይሆን በምስሉ ላይ የሚታዩት ግለሰብ የህወሓት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ እንዳልሆኑ አረጋግጧል።
ኤደን አብይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ ናት?

በታህሳስ 3 ቀን 2009 ዓ.ም ላይ EthioTube በሚል ስም የተከፈተ አንድ የዩቲዩብ ቻናል ስጦታ ሾው የተሰኘ አንድ ፕሮግራም የጀመረ ሲሆን በተለይም ፕሮግራሙ በአሜሪካ እና አካባቢው የሚኖሩ ስኬታማ እና አርዓያ ይሆናሉ የሚላቸውን ኢትዮጵያውያኖችን እየጋበዘ ልምድ እንዲያካፍሉ ያደርጋል።

በፕሮግራሙ ላይም የመጀመሪያ ተጋባዥ የነበረችው ትውልድ ኢትዮጵያዊቷ ኤደን አብይ ስትሆን በወቅቱም ይህች ግለሰብ በትምህርቷ ውጤታማ ከመሆኗም ባሻገር በአሜሪካው ኋይት ሃውስ የኢንተርንሺፕ ፕሮግራም ላይ እንደተሳተፈች ተገልጿል። በEthioTube ላይ የተላለፈው ይህ ቪድዮም እስካሁን ድረስ ከ118 ሺህ ጊዜ በላይ እይታ ማግኘት ችሏል።

ከዚህ ቪድዮ መለቀቅ በኋላም የተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ መረጃዎች ኤደን አብይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ በማለት መረጃውን ሲያዘዋውሩ የቆዩ ሲሆን በተለይም የኤደን አብይ ከቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ጋር መልኳን በማመሳሰል የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ይህች ሴት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ እንደሆነች ያመኑ አልጠፉም።

ነገር ግን ሀቅቼክ በስፋት እየተዘዋወሩ ያሉት ቪድዮዎች ሀሰተኛ እንደሆኑ እና በቪድዎቹ ላይ የምትታየው ግለሰብም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ እንዳልሆነች ማረጋገጥ ችሏል።

ሙሉ ፅሁፉን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://bit.ly/3wngAQi

የተጣሩ መረጃዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ከሀቅቼክ ገፆች ያግኙ፡
ቴሌግራም፡ t.me/HaqCheck
ፌስቡክ፡ www.facebook.com/HaqCheck
ትዊተር፡ www.twitter.com/HaqCheck
ድረ ገፅ፡ www.haqcheck.org
👍1
በሀገራችን የማህበራዊ ሚዲያ ምህዳሮች ውስጥ በሀሰት የተፈበረኩ መረጃዎች ሊሰራጩ የሚችሉ ይመስሎታል?
A Twitter account shared a post on Aug 20, 2022, Captioned “The United Nations and other organizations should reach out to the Oromo people suffering from Hunger.” The post uses four images to support it's claim. However, HaqCheck inspected the images and rendered the post, Partly False.

https://bit.ly/3QLXR9g
አለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደዘገቡት በ2011 ዓ.ም በሀገራችን ኢትዮጲያ በህብረተሰብ ውስጥ ከተሰራጨ ሀሰተኛ መረጃ የተነሳ ለምርምር በሄዱበት ፣ በአከባቢው ነዋሪዎች ተደብድበው ሁለት አጥኚዎች ህይወታቸው አልፏል።
ለማመን የሚከብድ ነገር አንብበው ወይም ስምተው ያውቃሉ? ማመን ያቃተዎትንስ ነገር ወዳጅዎ የቪድዮ ወይም ምስል ማስረጃ አሳይቶዎት አምነዋል? ነገር ግን መረጃ ተብለው የቀረቡት ምስሎችም ሆኑ ቪድዮዎች ተነካክተው ሊቀየሩ እና ለሌላ አላማ ሊውሉ እንደሚችሉ ላያስቡ ይችላሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቴክኖሎጂ መስፋፋትን ተከትሎ ምስሎችን በፎቶሾፕ አቀናብሮ መስራት ቀላል እየሆነ መጥቷል። ይህም በመሆኑ እነዚህ የተቀናበሩ ምስሎች ትክክለኛ መሆናቸውን ማረጋገጥ ግድ የሚለን ጊዜ ላይ ደርሰናል።
ታድያ እነዚህን መረጃዎች በምን ማረጋገጥ እንችላለን?
እነዚህን የተቀናበሩ እና የተቀየሩ ምስሎችን ለማረጋገጥ ቀላሉ ዘዴ የተገላቢጦሽ የምስል ፍለጋ ዘዴን (reverse image search) በመጠቀም ማግኘት እንችላለን።
ከነዚህ ምስልን ከማግኛ መንገዶች መካከል የGoogle reverse image search እና Tineye ጥቂቶቹ ናቸው።
እነዚህን የመረጃ ማጣርያ ዘዴዎችን ተጠቅመን
1.ምስሉ ከየት እንደመጣ
2.ምስሉ ከዚህ በፊት ምን ጥቅም ላይ እንደዋለ እንዲሁም
3.የተቀየረው ምስል ካለ ለማጣራት ያግዘናል።
👍1
ሀቅቼክ ሀሰተኛ እና የተሳሳቱ መረጃዎችን እያጣራ ለህብረተሰቡ ለማድረስ እያደረገ ያለው ጥረት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት እና ተፅዕኖ እየቀነሰ ይገኛል።
ይህንንም የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ለመቀነስ መንግስት ፤ የሚድያ አካላቶች ፤ ህብረተሰቡ እና ጉዳዩ የሚመለከተው አካል የራሱን አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይገባል።
ሀቅቼክ እያጣራ የሚያቀርባቸውን መረጃዎች ይከታተሉ።
#ትክክለኛመረጃለሁሉም!
ልዩ የበዓል ቆይታ በአርትስ ቴሌቭዥን
ማታ 1:30 ላይ ይጠብቁን
https://youtube.com/c/AddisZeybe